''ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።'' መዝ 40÷1 አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ ሰንበት ት/ቤቶች ከዚህ ቀደም ስያከናውኑ የነበረውን የበጎ አድራጎት ሥራ በተለይም በበዓላት ነዳያንን የመመገብ ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ በዚህ እግዚአብሔር አምላክ እንደሚያድን እና እንደሚጠብቅ በማስገንዘብ በዚህ ዓመትም በአ/አ በሚገኙ ከ231 በላይ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች ላይ ሊደረግ የታሰበውን የነዳያን ምገባ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ምዕመናን ፤ የሚዲያ አካላትና አንቂዎች፤ የሰንበት ት/ቤት ፍሬዎች፤ የኪነ ጥበብ ሰዎች፤ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ሁሉ በየ አካባቢያቸው በሚገኙ ሰንበት ት/ቤቶች በመሔድ በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በልዩ ልዩ ቁሳቁስና ዕውቀት ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ተገልጿል።
''ብድራችንን ብል እና ነቀዝ በማይበላሹት ሌቦችም ቆፍረው በማይሰርቁት በሰማይ ለናንተ መዝገብ ሰብስቡ'' ማቴ 6÷20 እንደተባለ እኛም ኑ በሰማያዊ መዝገባችንን እንጻፍ ብለን ጥሪያችንን እናስተላልፍለን ። በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።
ምንጭ፦የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

የመዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፒዲያ) ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ለማዘጋጀት እንዲቻል በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ምሁራን ዕውቀታቸውንና ልምዳቸውን ማካፈል የሚችሉበት መድረክ
ዛሬ ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በኤሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል እየተካሄደ ነው።
ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብቶች እንዲሁም አስተምህሮዎች ላይ ያተኰረ መዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፔዲያ) ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የሚዘጋጀው መዝገበ አእምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ጥንታዊና ሐዋርያዊ አስተምህሮ፣ ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት እንዲኹም የጳጳሳትን፣ የሊቃውንትን፣ የትልልቅ ገዳማትንና አድባራትን ታሪክ ወዘተ. የሚያካትት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
የመዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፒዲያ) ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ለማዘጋጀት እንዲቻል በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ምሁራን ዕውቀታቸውንና ልምዳቸውን ማካፈል የሚችሉበት መድረክ ማዘጋጀት አስፈልጓል ተብሏል።

ማኅበረ ቅዱሳን #በሽሬ እንደ ሥላሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 1.7 ሚሊዮን ብር ወጭ የሆነበት ማኅበራዊ ድጋፍ አደረገ፡፡
+++
ማኅበረ ቅዱሳን በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ መጠነ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በምእመናን፣ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን ሁለንተናዊ ችግር ለማቃለል የማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር ማኅበራዊና ሰብአዊ ሚናውን እየተወጣ እንዳለ ይታወቃል።
ማኅበሩ እነዚህን ችግሮች በስፋት በማጥናት ላለፉት 6 ዓመታት በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያው በኩል በአርሲ፣ በሐረር ፣በባሌ፣ በወሊሶ፣ በሻሸመኔ፣ በዶዶላ፣ በአጋርፋ፣ በጅጅጋ፣ በሲዳማ፣ በመተከል፣ በቤንሻጉል ጉምዝ፣ በፓዊ፣ በቡለን፣ ፣በሽሬ፣ በአክሱም፣ በቦረና ያቤሎ፣ በጎንደር አዘዞ፣ በአዲግራት፣ በማይ ጨው፣ በሽረ እንደ ሥላሴ ፣በመቐለ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደሴ፣ በወልዲያ፣በሑመራ፣ በላሊበላ ፣በሐይቅ እስጢፋኖስ፣ በወሎ ገራዶ፣ በደባርቅ ፣በጃን አሞራና በሌሎችም የሀገራችን ክፍል ለሚገኙ ተጎጅዎች ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ድጋፍ አድራጊ ምእመናንና ተቋማትን እያስተባበረ የአልባሳት፣ የምግብ እና መሠል አስቸኳይ ድጋፎችን በስፋት ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል።
በዚህ መሠረት በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ተፈናቅለው #በሽሬ እንደ ሥላሴ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ 1033 አባወራዎች 1.7 ሚሊዮን ብር ወጭ የሆነበት 150 ኩንታል የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል። በተጨማሪም በአካባቢው ለሚገኙ አገልጋዮች የአልባሳት ድጋፎች ተደርገዋል።
ድጋፉ የተደረገው ማስተባበሪያው ከአሜሪካ ማእከል ጋር በመሆን ባለፉት ጊዜያት በውጭ ዓለም ከሚገኙ ምእመናን ማኅበራዊ ድጋፍ ባሰባሰበበት ወቅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው።