Telegram Web Link
ዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት መርሐ ግብር ተከናወነ

በማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ በኩል በየሦስት ወሩ የሚከናወነው የዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ተከናውኗል። በ2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በተከናወነው በዚህ መርሐ ግብር ላይ በርካታ ምሩቃን ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ትምህርተ ወንጌልን ጨምሮ ዝማሬ እና የልምድ ልውውጥ የተከናወነ ሲሆን ፕሮፌሰር ማኅተመ በቀለ እና ወይዘሮ ዐይናለም ታዬ የሕይወት ልምዳቸውን ለምሩቃኑ አካፍለዋል። በተለይም የማኅበራዊ ሚድያ አጠቃቀምን በተመለከተ በፍቅር የምንኖርበት፣ አንድነትን የሚያጠነክር በጎ መተሳሰብ ያለበት እንዲሆን በማለት ምክራቸውን አጋርተዋል።

መርሐ ግብሩ በአዲስ አበባ በዋናው ማእከል አስተባባሪነት እና በሌሎች ማእከላት በተመሳሳይ ቀን የሚከናወን ሲሆን ዓላማው ምሩቃን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ጠንክረው ቤተ ክርስቲያንን ማገልገል እንዲችሉ ለማብቃት ታስቦ የሚዘጋጅ መርሐ ግብር ነው።
Holy

The Second Week of The Great Lent
 
Theological definitions of the word Holy stated in The King James Bible New Version are:
 1. Properly, whole, entire or perfect, in a moral sense. Hence, pure in heart, temper or dispositions; free from sin and sinful affections. Applied to the Supreme Being, holy signifies perfectly pure, immaculate and complete in moral character; and man is more or less holy as his heart is more or less sanctified, or purified from evil dispositions. We call a man holy when his heart is conformed in some degree to the image of God, and his life is regulated by the Divine precepts. Hence, holy is used as nearly synonymous with good, pious, godly. “Be holy; for I am holy.  (1 Peter 1:16)
 
2. Hallowed; consecrated or set apart to a sacred use, or to the service or worship of God; a sense frequent in Scripture; as the holy Sabbath; holy oil; holy vessels; a holy nation; the holy temple; a holy priesthood.
 
3. Proceeding from pious principles, or directed to pious purposes; as holy zeal.
 
4. Perfectly just and good; as the holy law of God.
 
5. Sacred; as a holy witness.
 
 The Second Week of the Great Lent is named with this word “Holy.”  Saint Yared (Jared) in his Book of “Tsome Deguwa” has given this name as a dedication of our Lord and Savior Jesus Christ’s coming from the heavens accord the covenant to the first creation Adam, for the salvation and blessing of mankind and as exemplary for holiness in His Divine Wisdom of redemption.
 
The Divine Attributes of God are all holy and thus He told us, His creatures, “Be holy; for I am holy.”  (1 Peter 1:16) This is His Own Divine Wealth but not given to Him by any. Holy Scriptures have become witness for this. As He is holy in His attribute, He is praised like, “Holy Holy Holy.” (Joshua 6:1, 3, 40:25, Revelation 15:4, 1 Samuel 2:2-3).
 
We as well praise Him saying, “Hallowed be Your Name” just as His Holy Son thought us. He is the only One Who bestows holiness. The word “Holy” is given for Angels, Righteous people, Sacred place, Icons and Days of Feast, by the holiness from the Divine Attributes of God. This is known to be “The Holiness of Grace.”   
 
God’s Holy words teaching us through the Apostle Saint Peter saying, “but as He who called you is holy, you also be holy in all your conduct, because it is written, “Be holy, for I am holy,” is the illustration of this notion. (1 Peter 15-16)
 
Saint Paul has said, “God did not call us to uncleanness, but in holiness.” (1 Thessalonians 4:6-8) These words of the apostle are the explanation of man created for holiness from the beginning. He has also thought the people of Ephesians saying “Blessed be the God and Father of our Lord Jesus Christ, who has blessed us with every spiritual blessing in the heavenly places in Christ, just as He chose us in Him before the foundation of the world, that we should be holy and without blame before Him in love.” (Ephesians 1:3-6)
 
God loves mankind dearly for He created the whole universe purposefully for him and “to shine in the world as the pinnacle of His creation connecting the material world with the spiritual realm.” (“Doctrine of Creation” course Module by Teacher Fikre Mariam, 2014) After God created the world, He created man providing all the significant things and placed him in heaven to live in holiness.  
 
Unfortunate to Adam though, for he defied God’s Law eating the forbidden fruit, who was condemned to live earthly life being sent out of heaven. To regain back his grace and holiness, The Holy Son Came Down from the heavens by humility from His Divine Glory and be born from Holy Mother Saint Mary. The Lord’s Divine wisdom did not seize here nor did anyone or thing hindered His work of redemption.  He was baptized, prayed diligently with prostration, beaten, mocked, and endured much more suffering and then crucified for taking back His first creation of mankind Adam, to his previous honor and holiness.    
 
The personhood cleansed by the Blood Shed of Lord and Savior Jesus Christ, is the stamp of our salvation and key to the heavenly Kingdom. The path He paved for us whilst the apostasy age is the way of true life and holiness. He said, “I am the way, the truth, and the life. No one comes to the Father except through Me.” (John 14:6) These words of our Lord are the clarification of the gate to God’s Kingdom which is bestowed through the Holy Son’s scarification for us upon the cross.
 
Dear Brethren! It is therefore important to carry the cross and live Christian life diligently to be cleansed from any curse and preserved from any harm in leaving holy life. Forefathers, Patristic Fathers, Righteous, Saints, Monks, Hermits and Martyrs all lived a holy life by carrying the cross enduring any misery on earth for the truth of God, sacrifice for their faith and religion. And were given the key to His Kingdom after honorably departing from this world escorted by Angels. We need to learn from the lives of children of God and inherit eternal life.
 
May God’s mercy, safeguard and Holy Mother Saint Mary’s intercession be with us, Amen!
 
"ነገን ዛሬ እንሥራ!"

ክፍል ሁለት


ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ባለፈው ሳምንት ‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ›› በሚል ርእስ ባቀረብንላችሁ ጽሑፍ ቤተ ክርስቲያን ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዴት እየተላለፈች ወደ እኛ እንደደረሰችና እኛም እንዴት ከአባቶቻችንና እናቶቻችን እንደተረከብናት በጥቂቱ የዳሰስንበትን ክፍል አድርሰናችኋል፡፡ በዚህ በክፍል ሁለት ደግሞ ከክፍል አንድ የቀጠለውንና “ቤተ ክርስቲያንን እኛስ እንዴት ለቀጣዩ ትውልድ እናስተላልፋት?፡ የሚለውን ክፍል ይዘንላችሁ ቀርበናል፤ መልካም ንባብ!

ቤተ ክርስቲያንን እንዴት እናስተላልፋት?

ቤተ ክርስቲያን እንዲሁ አልጋ አልጋ በሆነ ሁኔታ ወደ እኛ እንዳልደረሰች በክፍል አንድ አይተናል፡፡ ራሳቸውን የካዱና ሁለንተናዊ ሕይወታቸውን ለቤተ ክርስቲያን ክብር አሳልፈው የሰጡ አባቶች ለዚህ ትውልድ በቅብብሎሽ ያደረሷትን ቤተ ክርስቲያን እኛ የዛሬዎቹ ትውልዶችስ እንዴት ለማስተላለፍ ለማውረስ አስበናል? አባቶቻችን ካወረሱን አጉድለን ወይስ አትርፈን ነው የምናስተላልፋት? ክብረ ክህነትን አጎድለን ነው፤ ወይስ አሙልተን? ክብረ ምንኩስናንስ? የምእመናንስ ቁጥር ጨመርን ወይስ ቀነስን? ዶግማ ቀኖናዋንስ ሸራረፍን ወይስ ጠብቀን ዘለቅን? መታፈርና መከበሯንስ ጨመርንላት? ወይስ አጎደልነባት?
በርካታ ልንመልሳቸው የሚከብዱብን ጥያቄዎች፣ ልናስተካክላቸው የሚገቡ ብልሽቶች፣ ልንሞላቸው የሚገቡ ጎደሎዎች እንዲሁም ልንጠግናቸው የሚገቡ ስብራቶች አሉብን፡፡ በብዙ መልኩ ከተቀበልነው አጉድለናል፣ ለክብሯ የሞቱላትን ቤተ ክርስቲያን ተረክበንና ለክብራችን ስንል ዝቅ እንድትል ምክንያት ሁነናል፡፡ ለጥቅሟ ሲሉ በታሰሩላት አባቶችና እናቶች ቦታ ተቀምጠን ለጥቅማችን ስንል ልእልናዋን አስደፍረናል፤ እንድናገለግላት ተመርጠን አገልግይን ብለናታል፤ ወይም ተገልጋይ ሆነንባታል፤ የተሰበሰቡትን እየበተንን፣ የተከበሩትን እያቃለልንና የታፈሩትን እያስደፈርን ቤተ ክርስቲያኗን ሸክሟን በማቅለል ፋንታ ሸክም ሆነንባታል፡፡

ዶግማዋ እየተሸራረፈ፣ ቀኖናዋ እየተጣሰ፣ መታፈር መከበሯ ቀርቶ የውስጥም የውጭም ጠላት በዝቶባት፣ የዜና ማሟሟቂያ የውሬ ማድመቂያ፣ የልጆቿ ማሸማቀቂያ፣ የጠላቶቿ መሳለቂያ የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለልጆቻችን እናወርሳለን? ወይስ በቀደመ ገናንነቷና ክብሯ እናሸጋግራተለን? የሚለው ለነገ የማይባል የቤት ሥራችን ነው፡፡

አሁን ላይ የቤተ ክርስቲያኗ ተግዳሮት በጣም ዘርፈ ብዙ መሆኑ ለማንም የተደበቀ አይደለም፡፡ ከምንም በላይ ተሰሚነቷን፣ ተከባሪነቷን፣ ሉዓላዊነቷን መመለስ የታፈረችና የተከበረች ማድረግ፣ አጥር እንደ ሌለው ቤት ማንም አልፎ ሄያጅ፣ ዘው ብሎ የሚገባባትና የፈለገውን የሚፈጽምባት፣ ቤተ ክርስቲያን ለልጆቻችን ላለማውረስና የትውልድ ባለዕዳ ላለመሆን አብዝተን መትጋት አለብን፡፡ በኦሪት ዘጸአት ላይ ያለውን ታሪክ እናስታውስ፡፡ ‹‹እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፤ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቃለሁ›› (ዘጸ. ፫፥፯)

በዘመናችን ክርስቲያኖች ካስገባሪዎቻቸው የተነሣ መከራቸው በዝቷል፡፡ ደማቸውን በከንቱ የሚያፈሱ፣ ሀብት ንብረታቸውን የሚዘርፉባቸው፣ መድረሻ እንዲያጡ በሜዳ ተበትነው እረኛ እንደሌላቸው በጎች እንዲቅበዘበዙ የተደረገበት ወቅት መሆኑንና በጥቅሉ ቤተ ክርስቲያን በስደት ላይ ያለችበት መሆኑን ማንም አይዘነጋውም፡፡

ከገዥዎቻቸውና ከአስገባሪዎቻቸው የሚታደግ፣ ባሕርን ከፍሎና ደመና ጋርዶ የሚያሻግር፣ ነጻ ሆኖ ነጻ የሚያወጣ ሙሴ መሆን ከቤተ ክርስቲያን አባቶችና አገልጋዮች አሁን ይጠበቃል፡፡ ያለበዚያ አደራውን መብላት ነው፡፡ ክፉ ገዥዎች ሕዝቡን ሊለቁት ይገባል፤ ብዙዎቹን በዘረኝነት፣ በቋንቋ፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በልዩ ልዩ ሁኔታ፣ ግማሾቹን በኃይል ተብትበው ይዘዋቸዋል፡፡ ያገለግሉት ዘንድ ደግሞ እግዚአብሔር ይፈልጋቸዋልና፤ ሙሴን ሆኖ መገኘት በፈርኦን ፊት በድፍረት ቆሞ ያገለግሉት ዘንድ እግዚአብሔር ይፈልጋቸዋልና ሕዝቡን ልቀቅ፡ ብሎ መናገር እውነተኛ ሙሴ መሆን አሁን ያስፈልጋል፡፡ (ዘጸ.፭፥፩) ምክንያቱም በደሙ የዋጃት ቤተ ክርስቲያን በደሙ የዋጃቸው ምእመናን ናቸውና፡፡

ቤተ ክርስቲያን ስደቷ እንዲቆም፣ መከራዋ ዳርቻ እንዲኖረው፣ የሀገር ባለውለታነቷ ተዘንግቶ እየደረሰባት ላለው መከራና ስደት ማብቂያና መቋጫ እንዲኖረው፣ አንድነቷን የሚፈታተኗት ኃይሎች አደብ እንዲገዙ፣ እንደ ወርቅ የነጻው፣ እንደ ዕንቁ የሚያበራው ዶግማዋና ቀኖናዋ ለነገው ትውልድ ተጠብቆ ይተላለፍ ዘንድ ከምንም በላይ የተሰሚነትና ቅቡልነት ደረጃዋን ለማሳደግ ብዙ ሥራዎች መሥራት ይገባናል፡፡

የነገዋ ቤተ ክርስቲያን በክብረ ክህነት፣ በክብረ ምንኩስና፣ በምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት፣ በመልካም አስተዳደር ረገድ፣ በሀብትና ንብረት አስተዳደርና በሰው ኃይል ስምሪት፣ በጋብቻ ሕይወትና በሕፃናት አስተዳደግ እንዲሁም በወጣቶች ሕይወት፣ በወንጌል አገልግሎትና በዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ በመንፈሳዊና በቁሳዊ ልማት ረገድ፣ ማኅበራዊ ተሳትፎዋ የጎላ፣ ተጽእኖ ፈጣሪነቷ ታላቅ እንደ ጥንቱ እንዲሆን፣ ተነጋግረው ብቻ ሳይሆን በዐይን ጥቅሻ የሚግባቡ አባቶች፣ አገልጋዮች እንዲሁም ምእመናን እንዲኖሯት ከፍተኛ ሥራ መሥራት ከዚህ ትውልድ ይጠበቃል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ከእነ ክብሯ ለልጆቻችን ለማስተላለፍ አዲስ ነገር መፍጠር የሚጠበቅብን አይደለም፡፡

ትናንትን ለመመለስ፣ የአባቶቻችንን መንገድ ብቻ መፈተሽ፣ የጥንካሬያቸው ምክንያት ምን እንደነበር መረዳት፣ ቤተ ክርስቲያንን ገናና ያደረጓት፣ ታፍረው ተከብረው ያስከበሯት፣ “ምን ቢያደርጉ፣ እንዴት ቢሠሩ፣ ምን ዓይነት ሰብእናን ቢላበሱ ነው” ብሎ መጠየቅ፣ መልሱንም ከታሪካቸው ከገድላቸው መረዳት ብቻ በቂ ነው፡፡ በእኛ እምነት ቤተ ክርስቲያንን ያተለቃት፣ ያገዘፋት፣ የታፈረች የተከበረች ያደረጋት፣ በጨለማው ዓለም ውስጥ የምትበራ ድንቅ ፋኖስ ያደረጋት ዋና ነገሮች አልጫውን የሚያጣፍጥ፣ ጨለማውን የሚያበራ ድንቅ የሆነ የቅድስና ሕይወት ያላቸው አባቶችና እናቶች የነበሩ መሆኑ ነው፡፡

እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን የነበሩ አባቶቻችን ደግሞ ክብራቸውና ቅድስናቸው ከክብረ ክህነትና ክብረ ምንኩስና የሚመነጭ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በዘመናችን የተፈተነችውና ከቀደመ ልዕልናዋ ዝቅ ያለችው ክብረ ክህነትና ክብረ ምንኩስና በገጠመው ተግዳሮት ነው ብሎ መናገር ድፍረት አይሆንም፡፡ የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ከፍ ያለች እንድትሆን፣ የቀደመ ተወዳጅነቷን፣ ተሰሚነቷን፣ ተከባሪነቷንና ተገዳዳሪነቷን ለመመለስ ብዙ ሥራዎችን መሥራት የሚጠበቅብን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ከሁሉም ሥራዎች የሚቀድሙ፣ ለሁሉም ሥራዎች መሠረትና መሥሪያ ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው ብለን የምናምንባቸው ነገሮች ክብረ ክህነትና ክብረ ምንኩስና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ የቤት ሥራዎቻችን መሆን ሲችሉ ነው፡፡

እነዚህ ሁለት ዐበይት ጉዳዮች ትናንት ለነበረችው፣ ቤተ ክርስቲያን የቅድስና፣ የክብር፣ የልዕልና፣ የመታፈር የመከበር ምንጭ ምክንያት እንደነበሩ፣ እንዚህ ሁለት የቤተ ክርስቲያን ቁልፍ ጉዳዮች ተግዳሮት ሲገጥማቸው ቤተ ክርስቲያን ተግዳሮት እንደገጠማት ፈተና ውስጥ መግባቷን መረዳት አይከብድም፡፡ ስለሆነም ከዛሬዋ ከፍ ያለች፣ ቤተ ክርስቲያን ነገ እንድትኖረን ሐዋርያዊ የሆነው የክህነት ቅብብሎሽና የምድር መላእክት የሰማይ ሰዎች ያስባለው ምንኩስና ወደ ክብሩ ወደ ታሪኩ ሊመለስ ግድ ይላል፡፡

ውድ አንባብያን! የክብረ ክህነትንና ምንኩስናን ምንነትና ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን እንዴት መተላለፍ እንዳለበት በቀጣይ ክፍሎች ይዘን እንቀርባለን፤ ቸር እንሰንብት!
ማኅበረ ቅዱሳን "ኑ ቸርነትን እናድርግ " በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አዘጋጀ

በአገራችን በሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ የሚያስችል ልዩ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ የፊታችን መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም "ኑ ቸርነት እናድርግ " በሚል መሪቃል መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ጉባኤውን በማስመልከት በማኅበሩ ጽ/ቤት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እንደገለጹት ማኅበሩ ከሚያከናውናቸው በርካታ ተግባራት መካከል አንዱ የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍ እንደሆነ ገልጸው ከችግሩ ስፋት አንጻር ባልድርሻ አካላት ለየብቻ የሚያደርጉት ድጋፍ ውጤት ማምጣት ስለማይችል ማኅበሩ ከምእመናን እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እንደሚሠራ አሳውቀዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን የሙያ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ የሆኑት ዲ/ን ንጉሤ ባለውጊዜ እንደተናገሩት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖች እንዲሁም በድርቅ እና በተለያዩ ጊዜያት በሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያተ በከፈተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ አድባራት እና ገዳማት እንደሚገኙ ገልጸው ማኅበሩ እስካሁን ድረስ አጋር አካላትን በማስተባበር የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።

ምክትል ኃላፊው አያይዘው ምእመናን ማኅበሩ በመልሶ ማቋቋም ረገድ እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንዲደግፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የማኅበሩ ምክትል ዋና ጸሐፊ ዲ/ን አንድነት ተፈራ እንደገለጹት ምእመናን መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በሚደረገው መርሐ ግብር ላይ በመገኘት የማኅበሩን አገልግሎት በመደገፍ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን ጥናት እና ምርምር ማእከል ፰ኛውን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት መጽሔት ኅትመት አጠናቀቀ።

በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ምሁራንን በማሳተፍ የጥናት መጽሔቶችን በማሳተም የሚታወቀው የማኅበረ ቅዱሳን ጥናት እና ምርምር ማእከል ፰ኛውን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት መጽሔት ለአንባብያን ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቋል። መጽሔቱ የቤተ ክርስቲያንን ልዩ ልዩ ገጽታዎች ሊያሳዩ የሚችሉ አምስት መጣጥፎችንና አንድ የመጽሐፍ ግምገማን ያካተተ ነው፡፡ ይህም በዘርፉ ያለውን መልከ ብዙ እውቀት በጨረፍታም ቢሆን ለማየት የሚያስችለንን ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡

መጽሔቱ ስድስት የምርምር ውጤቶችን ይዟል። ከእነዚህ መካከል ሦስቱ በአማርኛ ቋንቋ የቀረቡ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ሦስት የምርምር ውጤቶች ደግሞ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፉ ናቸው፡፡ በአማርኛ ቋንቋ ከቀረቡት መካከል የመጀመሪያው መጣጥፍ፣ በኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ከጥንት ጀምሮ እየተተገበረ በኖረው፣ በብራና ጥበብ አሠራርና አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ የእስቴ ወረዳን በማሳያነት የተጠቀመው ይህ ጥናት፣ የብራና ጥበብ አሠራርና አዘገጃጀትን የሚያቀርብ ብቻ ሳይሆን፣ የሙያውን ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ እንዲሁም ታሪካዊ ገጽታ የሚያሳይ ነው፡፡
ሁለተኛው መጣጥፍ፣ የፎክሎር ጥናት የቤተ ክርስቲያንን ገዳማትና ቅዱሳት ቦታዎች በማስተዋወቅ ረገድ የሚያስተላልፈውን አዎንታዊና ገንቢ ሚና በማሳየት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ጥናቱ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ አተኩረው የተሠሩ ቀደምት የፎክሎር ጥናቶችን በመገምገም ባህላዊ ሁነቶችን፣ ንዋያተ ቅድሳትን፣ ገዳማትንና ቅዱሳት ቦታዎችን በጥልቀትና በስፋት ለመረዳት የፎክሎር ጥናቶች ጠቃሚ መሆናቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ያቀረበ ነው፡፡ በዚህ ቅጽ ሥር የተካተተው ሦስተኛው መጣጥፍ ደግሞ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ፋይዳ ያላቸውን ሚኒራሎች ሳይንሳዊ በሆኑ ስሌቶችና ስልቶች ለመተንተን የቻለ ነው፡፡ እነዚህ ሚኒራሎች በዋናነት በቤተ መዘክርና ቤተ መዛግብት ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ በቤተ ክርስቲያን ባለቤትነት ሥር ያሉ ናቸው፡፡

አራተኛውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከቀረቡት መካከል የመጀመሪያ የሆነው መጣጥፍ፣ የኢትዮጵያ ቤተ እምነቶች ካውንስል ከግጭት በኋላ የሚኖረውን ሚና የሚመረምር ነው፡፡ ጥናቱ በተለያዩ ቤተ እምነቶች ውስጥ ያሉ አማኞች ተከባብረው እንዲኖሩ ሃይማኖታዊ ተቋማት ያላቸውን ወደር-የለሽ ድርሻ የሚያስተዋውቅ ነው፡፡ የድጓ መጽሐፍን መነሻ አድርጎ የቀረበው አምስተኛው መጣጥፍ በቅዱስ ያሬድ ጽሑፎች ውስጥ የሚታየውን ስለ ቅድስት ሥላሴ የነገረ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን (Trinitarian Concept of Ecclesiology) የሚያሳይ ነው፡፡ መጣጥፉ ድጓን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ሃይማኖተ አበውን እንደ ማስረጃ በመጥቀስ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማዊ አስተምህሮን የሚመረምር ነው፡፡ 

ቅጹ ከእነዚህ አምስት መጣጥፎች በተጨማሪ በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የተጻፈውንና Sodomites and the Wage of Sin በሚል ርእስ የቀረበውን መጽሐፍ የዳሰሰ ግምገማም አካቷል፡፡ ይህ ግምገማ በመጻሕፍት ላይ አተኩረው ትንተና በማድረግ ከቀረቡ ቀዳሚ የመጻሕፍት ግምገማዎች በተለየ መልኩ ትኩረቱን ያደረገው ጸሓፊውን ቃለ መጠይቅ በማድረግ አነሳሽ ምክንያታቸውንና ሐሳባቸውን ለመረዳት በመሞከር ላይ ነው፡፡ ገምጋሚው የተከተሉት ስልት መጽሐፉን ምዕራፍ በምዕራፍ በመዳሰስ የመጽሐፉን አጠቃላይ ጠንካራና ደካማ ጎን ለአንባቢ ማሳየት ነው፡፡ 

ማኅበረ ቅዱሳን ከሁሉ በፊት የእነዚህን ጥናታዊ ጽሑፎች ባለቤቶች፣ ገምጋሚዎች፣ ተባባሪ አርታዒዎችና የአርትዖት ኮሚቴ አባላት እንዲሁም በዚህ የኅትመት ሂደት ውስጥ የተሳተፉ አገልጋዮችና ባለሙያዎች በሙሉ ይህ ቅጽ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስና ፍሬ እንዲያፈራ ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና እገዛ ምስጋናውን ይገልጻል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት መጽሔትን ወደፊት የምናሳድገውና ዓላማችንን ከግብ ለማድረስ የምንችለው በሁላችን የጋራ ጥረትና ትብብር ነውና እገዛችሁ ወደፊትም አይለየን ይላል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ይህ ቅጽ ለተመራማሪዎች፣ ለምሁራን፣ ለተማሪዎችና በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ የሚነሡ ጉዳዮችን ለማወቅ ጉጉት ላላቸው ግለሰቦች ጠቃሚ የመረጃ ምንጭ ሆኖ እንደሚያገለግል ተስፋ ያደርጋል፡፡አሁን ዝግጅቱ የተጠናቀቀው ቁጥር ፰ የጥናት መጽሔት የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ይመረቃል።

በመጨረሻም፣ ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለቤተ ክርስቲያናችን አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞችና እኅቶች እንዲሁም ለተመራማሪዎች፣ በልዩ ልዩ ዘርፍ ለተሠማራችሁ መምህራንና ተማሪዎች፣ በቀጣይ ለሚዘጋጀው የጥናት መጽሔት. ቁ.፱ ጥናታዊ ጽሑፎችን በመላክ የበኩላችሁን ምሁራዊና ክርስቲያናዊ አስተዋጽኦ እንድታደርጉ በማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል ስም ጥሪ ያቀርባል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በኢትዮጵያ የአርመን አምባሳደርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

በኢትዮጵያ የአርመን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ሰሃክ ሳርግስያን (Sahak Sargsyan ) በዛሬው ዕለት ወደቅዱስነታቸው ቡራኬ የተቀበሉ ሲሆን የኢትዮጵያና የአርመን ግንኙነት፣ ህዝብ እንደ ህዝብ፣ ሀገር እንደ ከሀገር፣ ቤተክርስቲያንም እንደ ቤተክርስቲያ ታሪካዊ እንደሆነ አውስተው ይህቺ ዕለት ለእርሳቸው የተቀደሰች መሆኗን እንዲሁም በቅዱሱ የጾም ወር ቅዱሱን ፓትርያርክ በማግኘት መቀደሳቸውን ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸውም ለክቡር አምባሳደሩ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጡ ንግግር፡―"አርመን ታሪካዊት ሀገር ናት። የአርመን አምባሳደር ሆነው በመምጣትዎና የመጀመሪያው አምባሳደርም በመሆንዎ እንኳን ደስ አለዎት" ካሉ በኋላ የአርመኒያ ኦርቶዶክስ መሪ ወንድማቸውን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ካረኪን 2ኛ የመላዋ አርሜኒያ ካቶሊኮስና የዓለም አብያተክርስቲያናት ፕሬዝዳንት ጤንነት፣ በአርመን የምትገኘዋ ቤተክርስቲያን ሰላም እና የክርስቲያኖችን ሕይወት ደህንነት ጠይቀዋቸዋል።
2024/09/29 08:26:28
Back to Top
HTML Embed Code: