Telegram Web Link
"4 ተገድለው 1 ጠፍተዋል፤ ገዳሙን እና እኛን ለማዳን እነሱ ተሰው፤ የእኛንም በደል እነሱ ከፈሉ"
የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች
++++++++++++++++++++++++++++++

የገዳሙን መጋቤ እና ዋና ጸሐፊ ጨምሮ የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም 4 መነኮሳት በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

ከገዳሙ በስልክ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው የካቲት 12/2016 ዓ.ም የታጠቁ ሰዎች ወደ ገዳሙ በመግባት ሁለት መነኮሳት መውሰዳቸውን እነሱ ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቁ በማግስቱ የካቲት 13/2016 ዓ.ም ታጣቂዎቹ ድጋሚ መጥተው ለውይይት እንፈልጋችኋለን በማለት 3 መነኮሳትን ወደ "ጂዳ ተክለ ሃይማኖት" ወስደዋል ብለዋል።

መነኮሳቱ "ለውይይት" ሲባሉም "ችግር የለውም እናንተ አባቶች እዚህ ቆዩ እኛ አነጋግረናቸው እንመጣለን፤ ተረጋጉ" ብለው ታጣቂዎቹን ተከትለው ከገዳሙ ሂደዋል።

ቀኑን ሙሉ ስልካቸው ክፍት እንደነበረ አመሻሽ ማግኘት ባለመቻላቸው ተጨንቀው የአካባቢውን ምእመናን ሲያጠያይቁ 4ቱ መገደላቸውን እንደነገሯቸው አንደኛው አባት ግን ተለቀዋል ቢባልም እስካሁን ያሉበት እንዳልታወቀ አባቶቹ ለጣቢያችን በእንባ ተናግረዋል።

በታጣቂዎቹ የተገደሉት አባቶች

፩ አባ ተክለ ማርያም አሥራት (የገዳሙ መጋቤ)

፪ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን (የገዳሙ ዋና ጸሐፊ)

፫ አባ ገብረ ማርያም አበበ (ቀዳሽ ካህን፣የመጽሐፍ መምህርና የገዳሙ አስተዳደር አባል)

፬ ባህታዊ ኃ/ማርያም ስሜ (የገዳሙ የአስተዳደር አባል)
ሲሆኑ
እስካሁን ያሉበት ያልታወቀው ደግሞ አባ ኪዳነ ማርያም ገ/ሰንበት ናቸው።
ገዳሙ በተደጋጋሚ በታጠቁ ሰዎች ዐይነተ ብዙ ጥቃት እንደሚደርስበት ነገር ግን መፍትሔ እንዳላገኙ በመግለጽ የአሁኑ ጥቃት ግን በቃላት የማይገለጽ ነው ብለዋል።

"ገዳሙን እና እኛን ለማዳን እነሱ ተሰው፤ የእኛንም በደል እነሱ ከፈሉ፤ ጻድቁን አገልግዬ እዚሁ አርፋለሁ ሲሉ ደመ ከልብ ሆነው ዐፈራቸውንም ሳይቀምሱ ቀርተዋል" ሲሉም መረጃ የሰጡን አባቶች በከፍተኛ ሐዘን ገልጸዋል።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት።


ጥንታዊት፣ ታሪካዊት፣ ብሔራዊትና ዓለም አቀፋዊት በሆነችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር ከሚገኙት ጥንታዊያን ገዳማት መካከል ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አንዱና ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል።

ይህ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም በርካታ ቅርሶችና መናንያን የሚገኙበት ገዳም ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በተከሰተበት ዘረፋና ቃጠሎ ከባድ ጉዳቶችን ያስተናገደ መሆኑም ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት ከሀገረ ስብከቱ በደረሰን መረጃ መሰረትም፦
1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት
የካቲት 12 ቀን "ኦነግ ሸኔ" በተባለው ታጣቂ ቡድን ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ ሲሆን አባ ኪዳነማርያም ገ/ሰንበት የተባሉት አባት ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ታውቋል።

በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከአደራ ጭምር መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
የካቲት ፲፬ቀኝ ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ስለሚገኘው "መነኩሴ"ነኝ ባይ ግለስብ በሀገረ ስብከቱ የማይታወቅ መሆኑን ሀገረ ስብከቱ ገለጸ።

የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ራሱን "መነኩሴ"በማስመሰልና በአርሲ ሀገረ ስብከት አገልጋይ እንደሆነ በመግለጽ የሚንቀሳቀሰውን ግለሰብ የማያውቀውና ሐሰተኛ "መነኩሴ" መሆኑን ለጠቅላይ ቤተክህነት በጻፈው ደብዳቤ አስታወቀ።

ከየካቲት 12/20916 ዓ.ም ጀምሮ በማኀበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የሚገኘው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ተችቶ የማስተቸት ድራማዊ ትዕይንት ላይ የቀረበው አስመሳይ "መነኩሴ"ግለሰብ በሀገረ ስብከታችን በተለይ በአሰላ ከተማ በቅዳሴ መምህርነት በስብከተ ወንጌል እንዳገለ በማስመሰል በሰጠው የሀሰት ምስክርነትን በተመለከተ እውነተኛ ምላሽ መስጠት ማስፈለጉን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ"መንኩሴ "መሳዩ ግለሱብ በሀገረ ስብከቱ በየተኛውም የከተማና የገጠር ገዳማትና አድባራት የማይታወቅና ምንም ዓይነት አገልግሎት ሲሰጥ ያልነበረ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙት ሁሉንም አገልጋዮች የሚታወቁና የተመዘገቡ መሆኑን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ ግለሰቡ በሀገረ ስብከቱ ካሉት አገልጋች መካከል የማይታወቅና ያልተመዘገበ ከመሆኑም በላይ ሀገረ ስብከቱ በፍጹም የማያውቀው ቀሳጢ ነው በማለት ሐሰተኛ ማንነትን በመላበስ የቤተክርስቲያንን ስም ለማጠልሸተ የተሰማራ መሆኑን ገልጿል።

ስለሆነም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ግለሰቡ የቤተ ክርስቲያናችንን ዓርማ ወይም አልባሳት በመልበስና የሀገረ ስብከታችንን መልካም ገጽታ በማጉደፉ ግለሰቡንና እዩ ጩፋ የተባለውን አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በህግ እንዲጠይቅን ስንል በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን፤በማለት ለጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ ጨምሮ ገልጿል።

ምንጭ: የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
The Queenship of Saint Mary

The Divine Wisdom of God for the salvation of the world is done through His tremendous mercy. The primordial covenants of the Old Testament were without the capability of redeeming mankind. The absolute covenant was done by the seventh covenant for the salvation of human race thru Holy Saint Virgin Mary. 

She is given the covenant of mercy and for this we plead calling her “Covenant of Mercy.”  The promise made for Adam is done thru he; for she gave birth to The Holy Son, Lord and Savior Jesus Christ in virginity.  He suffering and was crucifixion on the cross was by her flesh and soul.

As we find it written in Mariology, after Our Lord and Savior Jesus Christ’s ascension, Saint Virgin Mary went to His grave Golgotha and prayed pleading for the salvation of humans. Then He gave her the covenant of mercy on Yekatit 16.  
This holy day that we are bestowed a mercy of covenant is very great and thus Holy Church celebrates it colorfully.  This Queenship of Saint Mary is the confusion of all the previous six covenants which are Covenant of Adam, Covenant of Noah, Covenant of Melchizedek, Covenant of Abraham, Covenant Moses and Covenant of David. In the commemoration of this eternal covenant, we make celebration in Church by praising in Psalm, Maheleate Song and Divine Liturgy.

Dear Brethren, we shall acknowledge this covenant of the New Testament, which is made for our salvation of soul and plead in the name of Saint Mary’s Queen ship and commemorate her feast day by feeding the hunger, water the thirst and aid the deprived.  
May our Holy Mother’s Saint Mary’s intercession and Mediation be with all of us, Amen
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የካቲት 18 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት የሚጀመረውን ጾመ ነነዌ በማስመልከት አባታዊ ቃለ በረከት አስተላለፉ፡፡
አደራ አለብኝ!

የ 2016 ዓ.ም 2ኛ ዙር ጉባኤ

ዓለም ዓቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ

• ቀን፡ መጋቢት 08/2016 ዓ.ም
• ሰዓት፡ ከ 7፡00 ጀምሮ
• ቦታ፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ
በምጽአት ቀን ሕይወትን ልናገኝ እንዲሁም መንግሥተ ሰማያትን ልንወርስ ይገባናል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ፣ ልመናችንን ተቀብሎና ጾማችንን አስቦ ምሕረትን ያድርግልን፤ አሜን!!!
የሦስቱ ቀናት ጾም

ሦስት ቁጥር በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ብዙ ትርጉሞች እንዳለው ቅዱሳት መጻሕፍት ይገልጻሉ፡፡ በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት በዋነኛነት የምናነሣው ስለ ቅድስት ሥላሴ ሦስትነት ነው፡፡ ‹‹አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ናቸው›› እንዲል፤ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ የወረደውም በዕለተ እሑድ ሦስት ሰዓት ላይ ነው፡፡ አምላካችን መድኃኒታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተፀነሰው በሦስት ሰዓት ነው፤ እመ አምላክም የመፀነሱን ብሥራት ከቅዱስ ገብርኤል የሰማቸው በዚሁ ሰዓት ነው፡፡ (ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት/በማኅበረ ቅዱሳን የተዘጋጀ፣ ፲፱፻፺፫ ዓ.ም)

አምላካችን በተወለደ ጊዜም የዜናውን ብሥራት ሰምተው እጅ መንሻ ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ ያመጡለት ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) ቁጥራቸው ሦስት እንደ ሆነ ቅዱስ ወንጌል ይገልጻል፡፡ (ማቴ.፪፥፲፪) ተአምረ ማርያም ደግሞ እመ አምላክ ድንግል ማርያም ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር ሆና ጌታችን ኢየሱስ ፲፪ ዓመት በሆነው ጊዜ በቤተ መቅደስ ለሦስት ቀናት ያህል ፈልጋ እንዳጣችው ይነግረናል፡፡
ጌታችን በዘመነ ሥጋዌ በምድር ላይ ስብከተ ወንጌልን ያስተማረው ለሦስት ዓመታት ነው፤ በቀራንዮ አደባባይ መከራና ሥቃይ የተቀበለው ለሦስት ሰዓታት ነው፤ በመልዕልተ መስቀል ላይ ከሞተም በኋላ የተነሣው ከሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በኋላ ነው፡፡ (ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት/በማኅበረ ቅዱሳን የተዘጋጀ፣ ፲፱፻፺፫ ዓ.ም) ይህን ብቻ አነሣን እንጂ በነገረ መላእክትና በቅዱሳን ገድል ውስጥ ሦስት ቁጥር ለብዙ የእግዚአብሔር ሥራዎች ላይ ሲውል ይስተዋላል፡፡ (መጽሐፈ አክሲማሮስ ዘእሑድ፣ ገድለ ቅዱሳን)
ለምሳሌ ቅዱስ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጋእዝተ ዓለም ሥላሴን ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ፤ አንዱ አብ ቅዱስ ነው፤ አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው፤ አንዱ መንፈስ ቅዱስም ቅዱስ ነው›› በማለት ያመሰገኑት በተወለዱ በሦስተኛው ቀን እሑድ ከጠዋቱ በሦስት ሰዓት ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ሄዶ በአንደበቱ ሊገልጸው የማይችለውን ምሥጢር እንደ ተመለከተ ቅዱስ ወንጌል ይገልጻል፡፡ ብዙ ምሳሌዎች መግለጽ ቢቻልም ጊዜ ይገድበናል፡፡ (ገድለ ተክለ ሃይማኖት፣፪ኛ ቆሮ.፲፪፥፪)

ለዚህ ርእሰ ጉዳይ ትኩረት ያደረግነው ግን አምላካችን ስለ አዘዘው የሦስቱ ቀናት ጾም ነው፡፡ ለማንኛውንም ጥፋትም ሆነ በደል ሥርየት የምናገኘው በጾም፣ በንስሓ፣ በጸሎት፣ በምጽዋት እንዲሁም በስግደት በመሆኑ አምላካችን ሊያድነን ስለ ወደደ ይህን ሥርዓት ሠርቶልናል፡፡ በታሪክ መጻሕፍት ላይ ተመዝግቦ እንደምናገኘው በበደላቸው ምክንያት የነነዌ ሕዝብ ሊጠፉ በመሆናቸው ከሕፃናት ጀምሮ እስከ አረጋዊ ብቻም ሳይሆን እንስሳት ጭምር የጾሙት የሦስት ቀናት ጾም ‹‹ የነነዌ ጾም›› ተብሏል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር የነነዌ ከተማን በሦስት ቀናት ውስጥ ሊያጠፋት እንደ ሆነ ለነቢዩ ዮናስ ሲነግረው ትእዛዙን ከመቀበል ይልቅ ወደ ቴርሰስ ከተማ ለመኮብለል የወሰነው፣ ልብና ኩላሊትን የሚመረምረውንና ምንም ምን ከእርሱ የማይሠወረውን ፈጣሪ ማታለል ስለሚችል ሳይሆን ሐሰተኛ ነቢይ ላለመባል ፈርቶ ነበር እንጂ፡፡

ቸር፣ መሐሪና ይቅር ባይ የሆነው አምላካችን የነነዌ ሕዝብ በንስሓ፣ በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ካልተመለሱ ነነዌ እንደምትጠፋ እንዲያስተምርና እንዲያስጠነቀቅ ካዘዘው በኋላ በቸርነቱ ሲምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እንደሚባል አስቦ መሸሽን መረጠ፡፡ ‹‹ተነሥና ወደ ነነዌ ሀገር ግባ፤ በድለውኛልና ነነዌ በሦስት ቀን ትጠፋለች ብለህ ስበክ›› አለው። ዮናስ ግን ‹‹የአንተ ምሕረት እጅግ የበዛ ሲሆን ትጠፋለች ብዬ ተናግሬ እሳት ከሰማይ ሳይወርድ ቢቀር ሐሰተኛ ነቢይ ልባል አይደለምን?›› አለና ከእግዚአብሔር ሊሸሽ መንገድ ጀመረ። (ዮናስ ፩፥፩-፫)
እግዚአብሔር አምላክም እንደ ስሙ ትርጓሜ የዋህ የነበረውን የዮናስን ልብ ያውቃልና በድንቅ ጥበቡ የጉዞውን አቅጣጫ ቀይሮ ወደ ነነዌ ምድር ወሰደው፡፡ ታላቅ ነፋስን ይጓዝበት በነበረበት መርከብ ላይ ላከ፤ መርከቡም ሊሰበር ደርሶ ተሳፋሪዎቹን ሁሉ አሸበረ፤ ሆኖም ግን ምክንያቱን ለማወቅ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወጣ፤ አንቀላፍቶ የነበረው ዮናስም ‹‹ይህ ማዕበል በእኔ ምክንያት የመጣ ነውና ወደ ባሕሩ ጣሉኝ›› አላቸው፤ እነርሱም እውነቱን ሲረዱ እርሱ እንዳላቸው ባሕር ውስጥ ጣሉት፤ ቀጥሎም አምላክ ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አንበሪ አዘጋጀ፤ ዮናስንም ከዋጠው በኋላ በሆዱ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ቆየ፤ ይህም ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ለመኖሩ ምሳሌ ነው፡፡ (ዮናስ ፩፥፬-፲፯፣ ማቴ.፲፪፥፵-፵፩)

ከዚያም ዓሣ አንበሪው ዮናስን በየብስ እንዲተፋው አደረገ፡፡ ዮናስ ወደ ነነዌ ከተማ ከደረሰ በኋላ የሦስት ቀን መንገድ ዙሮ መስበክ ይጠበቅበት ነበር፡፡ ነገር ግን የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፤ ‹‹በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች›› አለ። የነነዌ ሰዎችም የእግዚአብሔርን ቃል አምነው ተቀበሉ፡፡ ማቅ ለበሱ፤ ድንጋይም ተንተራሱ፤ ንጉሡ ስልምናሶር ሳይቀር ከዙፋኑ ወርዶ መጐናጸፊያውን አወለቀ፤ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ። ሕፃናት ጡት ተከለከሉ፤ እንስሳትም ጭምር ለሦስት ቀናት ያህል ከሚበሉት ተከለከሉ፡፡ ‹‹ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ። እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?›› እንዲል፡፡ (ዮናስ ፫፥፰-፱)

በእርግጥም አምላካችን እግዚአብሔር ወደ እርሱ በመመለሳቸው ምክንያት ለሕዝቡ ምሕረትን አድርጎ የነነዌ ሰዎችን እንዳዳናቸው ከትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ እንረዳለን፡፡ ነቢዩ ዮናስን ግን ይህ ነገር ደስ እንዳላሰኘው ከዚህ በኋላ በተጻፈው ታሪክ እናያለን፡፡ ‹‹ይህም ዮናስን ከቶ ደስ አላሰኘውም፤ እርሱም ተቈጣ። ወደ እግዚአብሔርም ጸለየና። “አቤቱ፥ እለምንሃለሁ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፣ ታጋሽም፣ ምሕረትህም የበዛ፣ ከክፉው ነገርም የተነሣ የምትጸጸት አምላክ እንደ ሆንህ አውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል ፈጥኜ ነበር፡፡ አሁንም አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ” አለው። እግዚአብሔርም “በውኑ ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን?” አለ።

ዮናስም ከከተማይቱ ወጣ፤ ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ፤ ከተማይቱንም የሚያገኛትን እስኪያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥላው በታች ተቀመጠ። እግዚአብሔር አምላክም ቅል አዘጋጀ፤ ከጭንቀቱም ታድነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ላይ ከፍ ከፍ አደረጋት ዮናስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው። በነጋው ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ትልን አዘጋጀ፤ እርስዋም ቅሊቱን እስክትደርቅ ድረስ መታቻት፡፡ ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፤ ዮናስ እስኪዝል ድረስም ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራሱም ሞትን ፈለገና “ከሕይወት ሞት” ይሻለኛል አለ። እግዚአብሔርም ዮናስን “በውኑ ስለዚህች ቅል ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን?” አለው። እርሱም “እስከ ሞት ድረስ እቈጣ ዘንድ ይገባኛል” አለ። እግዚአብሔርም “አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፣ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፣ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል። እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” አለው፡፡›› (ዮናስ ፬፥፩-፲፩)

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ፈጣሪያችን በአርአያውና በአምሳሉ ለፈጠረን ለእኛ ለሰዎች እንደሚያዝን፣ ተጸጽቶ ለሚመለስ ደግሞ ምሕረትን እንደሚያደርግ በዚህ ለነቢዩ ዮናስ በምሳሌ አድርጎ በነገረው መሠረት እንረዳለን፡፡ አምላከ ምሕረት እግዚአብሔር በከፋ ደረጃ ለበደሉት ለነነዌ ሰዎች ምሕረትን ያደረገው በሦስት ቀን ጾም ብቻ ነው፡፡ እኛም በሦስቱ ቀናት ጾም እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ባሕርይውን ዝቅ አድርጎ፣ ሥጋን ለብሶ፣ በምድር እንደ ሰው ተመላልሶ፣ መከራን ተቀብሎና ተሰቅሎ፣ በሦስተኛ ቀን በትንሣኤው ትንሣኤን የሰጠን በሦስተኛው ቀን ነውና ይህን ድንቅ ጥበብና የአምላክ ሥራ በዘመከርና በማመን በእውነት መንገድ ተጉዘን
በምጽአት ቀን ሕይወትን ልናገኝ እንዲሁም መንግሥተ ሰማያትን ልንወርስ ይገባናል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ፣ ልመናችንን ተቀብሎና ጾማችንን አስቦ ምሕረትን ያድርግልን፤ አሜን!!!
ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የአምባሳደር  ምሥረታ መርሐ ግብር አካሄደ ።

የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል በቅርቡ ግንባታውን የሚያስጀምረውን ባለ 12 ወለል ሕንጻ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ድጋፍ የሚያሰባስቡ አምባሳደሮችን የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም  በዮድ አቢሲኒያ  የባሕል ምግብ አዳራሽ በተከናወነ መርሐ ግብር ላይ ሾሟል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁእ አቡነ መቃርዮስ የጅግጅጋ ሀ/ስብከት ሊቀጳጳሳ እና ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ሙሉጌታ ስዩም (ዶ/ር) የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ማእከል ሰብሳቢ የሆኑት ዲ/ን ኃይለ ማርያም መድኅን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዕለቱ የተሾሙት አምባሳደሮች ትውልድን ለመገንባት እና የቤተ ክርስቲያን እና የአገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በበላይነት የሚመሩ እንደሆኑ ጠቁመዋል።

የዕለቱን ትምህርት ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ የሰጡ ሲሆን በዘመናችን እየደረሱ ያሉ ችግሮች መፍትሔ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እና እርሱን ከልብ ማገልገል እንደሆን አጽንኦት ሰጥተዋል።

የማኅበሩ ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ሙሉጌታ ስዩም (ዶ/ር)  በዕለቱ ባስተላለፉት መልእክት አምባሳደር ሆነው ለመሾም ፈቃደኛ በመሆናቸው በማኅበሩ ስም ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ትውልዱን ዘመኑ ከሚያመጣበት ፈተና ለመታደግ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል።
2024/09/30 12:12:47
Back to Top
HTML Embed Code: