Telegram Web Link
#የጥያቄ_እና_መልስ_ምሽት

ውድ ተከታታዮቻችን ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ ዕሮብ ዕሮብ በግሩፓችን (የተዋህዶ ልጆች) ላይ የጥያቄ እና መልስ ምሽት ሁኗል።ስለዚህም እናንተም ግሩፕ ውስጥ በመቀላቀል መንፈሳዊ እውቀቶን ይመዝኑ።ሌሎች ወንድምና እህቶቻችሁን በመጋበዝ ፤ በመጠየቅና በመረዳዳት ይቀጥሉ።

ጥያቄ እና መልሱ ሁሌ ዕሮብ2:30 ጀምሮ እስከ 4:00 ድረስ ይሆናል።

ግሩፑ ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ይጠቀሙ የተዋህዶ ልጆች
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመውን ግድያ አወገዘ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ንጹሐን አማኞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በእጅጉ ያወግዛል

“በንጹሐን ላይ የሚፈጸም ግድያ፣ ኢሰብአዊ ድርጊትና አያያዝ በሁሉም ሃይማኖቶች የሚወገዝ ወንጀል ነው”

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ንፁሐን አማኞች ላይ ግድያ መፈጸሙን የሚገልጽ ከሁለቱ አባል ቤተ እምነቶች ካወጡት መግለጫ ተገንዝበናል፡፡ ድርጊቱ በእጅጉ የሚያሳዝን ከመሆኑም በላይ በሃይማኖት አገልግሎት ላይ የነበሩ ንፁሐን አማኞችን መግደል ደረቅ የወንጀል ተግባር በመሆኑ በእጅጉ የሚወገዝ ድርጊት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን “በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ላይ በኦርቶዶክሳዊያን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በእጅጉ እናወግዛለን፣ የፀጥታ ተቋማትም ጥቃቱን እንዲከላከሉ እንጠይቃለን፡፡” የሚል መግለጫ በቤተ ክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የፌስቡክ ገጽ ያወጣች ሲሆን በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ ሶቤ ሚካኤል፣ በዲገሎ ማርያም፣ በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት 36 ኦርቶዶክሳውያን በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ከሀገረ ስብከቱ የደረሰውን መረጃ ዋቢ በማድረግ መምሪያው ገልጿል፡፡ በተጨማሪም የአማኖች ቤትም ስለመቃጠሉ ዘገባው ይጠቁማል፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ባወጣችው መግለጫ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ፣ መነሃም በመባል በሚታወቀው ቀበሌ “ቶኩማ መነሃም” በተሰኘው የመካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ላይ በቤተ ክርስቲን በጸሎት ላይ ከነበሩት 17 ሰዎች መካከል ማንነታቸው ተጣርቶ ባልታወቁ ታጣቂዎች 9 የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ላይ የጅምላ ግድያ እንደተፈጸመ ከቤተ ክርስቲኒቱ የወጣው መግለጫ ይገልፃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው ዓመት በተለያዩ ቦታዎች ላይ የቤተ ክርስቲኒቱ አማኞች ላይ ግድያ መፈጸሙን መግለጫው ያትታል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ይህ አይነቱ የወንጀል ድርጊት በእጅጉ እያወገዘ የሚመለከተው የመንግስት አካልም የዜጎችንና የሃይማኖት ተቋማትን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ሕገ መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጉባኤው በአጽንኦት ያሳስባል፡፡ በንጹሐን ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸሙትንም ወንጀለኞች በአፋጣኝ በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግና ፍትህን አንዲያስከብር ይጠይቃል፡፡

ከዚህም ባለፈ በሀገራችን የሚታየው ማንኛውንም ዓይነት ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲታረም፣ የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት ሳይሸራረፍ የመጠበቅ መንግስታዊ ሃላፊነተን ሕግንና መመሪን መሠረት በማድረግ ሊሠራ ይገባል፡፡

ጉባኤያችን በንፁሀን ላይ ስለተፈጸመው ጥቃትና ግድያ በድጋሚ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጆች  ዘመዶች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢያሱስ አባቶችና መሪዎች ልባዊ መጽናናትን እንመኛለን፡፡
                   
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!
በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ በመሠረታዊ የርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸውን የመጀመሪያዎቹን ተመራቂዎች ማስተባበሪያው በየወሩ መጨረሻ በሚውለው እሑድ በሚያዘጋጀው የወርኃዊ ጉባኤ መርሐ ግብር ላይ ኅዳር 30/2016 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ ስለሚያስመርቅ በዕለቱ በመገኘት ቃለ እግዚአብሔርን እየተማርን ተመራቂ የርቀት ተማሪዎችን እንድናስመርቅ ሁላችንም ተጋብዘናል!
ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
#የጥያቄ_እና_መልስ_ምሽት ውድ ተከታታዮቻችን ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ ዕሮብ ዕሮብ በግሩፓችን (የተዋህዶ ልጆች) ላይ የጥያቄ እና መልስ ምሽት ሁኗል።ስለዚህም እናንተም ግሩፕ ውስጥ በመቀላቀል መንፈሳዊ እውቀቶን ይመዝኑ።ሌሎች ወንድምና እህቶቻችሁን በመጋበዝ ፤ በመጠየቅና በመረዳዳት ይቀጥሉ። ጥያቄ እና መልሱ ሁሌ ዕሮብ ከ 2:30 ጀምሮ እስከ 4:00 ድረስ ይሆናል። ግሩፑ ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ይጠቀሙ…
#የውይይት_ምሽት

ውድ ተከታታዮቻችን ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ እርስ አርብ በግሩፓችን (የተዋህዶ ልጆች) ላይ የውይይት ምሽት ሁኗል።ስለዚህም እናንተም ግሩፕ ውስጥ በመቀላቀል መወያየት ይችላሉ።ሌሎች ወንድምና እህቶቻችሁን በመጋበዝ ፤ በመጠየቅና በመረዳዳት ይቀጥሉ።

ውይይቱ ሁሌ አርብ ከ 2:30 ጀምሮ እስከ 4:00 ድረስ ይሆናል።

ግሩፑ ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ይጠቀሙ የተዋህዶ ልጆች
#ተከታታይ_ኮርስ

ውድ ተከታታዮቻችን ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ ቅዳሜ እና ሰኞ በግሩፓችን (የተዋህዶ ልጆች) ላይ ኮርስ የምንሰጥ ይሆናል።ስለዚህም እናንተም ግሩፕ ውስጥ በመቀላቀል መማር ይችላሉ።ሌሎች ወንድምና እህቶቻችሁን በመጋበዝ ፤ በመጠየቅና መማር ይቀጥሉ።

ኮርሱ ሁሌ ቅዳሜ እና ሰኞ ከ 2:30 ጀምሮ እስከ 4:00 ድረስ ይሆናል።

ለመመዝገብ የእርሶን ስልክ ቁጥር ፤ ሙሉ ስሞትን ፤ Username ወደዚህ ቦት ይላኩ @Tewahido_lijoch_course_bot

ግሩፑ ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ይጠቀሙ የተዋህዶ ልጆች
በሲነርጂ ሀበሻ ፊልምና ኮሚኒኬሽን በመዘጋጀት ላይ የሚገኘው  የሰማዕቱ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፊልም ጽሑፍ በሊቃውንት ጉባኤ እንዲመረመር ታዘዘ።
***

ኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም
"""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
==============

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሲነርጂ ፊልምና ኮሚኒኬሽን በኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳስ የስማዕትነት ተጋድሎ ዙሪያ የሚያጠነጥን ፊልም ለመስራት የሚያደርገው እንቅስቃሴ
ታሪክን የሚያጎድፍ ሆኖ ስለተገኘ ሊቆም እንደሚገባ በመግለጽ ኅዳር 25 ቀን 2016ዓ.ም  በቁጥር 1673/2789/2016 በተጻፈ ደብዳቤ መግለጹ ይታወሳል።


ይህንን ተከትሎ የፊልሙ ጸሐፊ እና ዳይሬክተር  ሞገስ  ታፈሰ ዶ/ር  እየተዘጋጀ የሚገኘውን  ፊልም ቤተክርስቲያናችን በሊቃውንቶቿ አማካኝነት  መርምራ፣ የሚታረም ካለ አርማና የሚቃናውን አቅንታ በምትሰጠን አስተያየትና ማስተካከያ መሠረት ፊልሙን የምንሠራ መሆኑ  ታውቆ አስፈላጊው ትብብር ሁሉ ይደረግልን። በማለት በጽሑፍና በአካል  ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመገኘት  በፊልሙ ዝግጅት ዙሪያ ማብራሪያ በመስጠት ለተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ይቅርታ ጠይቀዋል።

ብፁዕ  አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም  ዶ/ርሞገስ ታፈሰ ያቀረቡትን ይቅርታ  በመቀበል በአካልና በጽሑፍ በፊልሙ ጽሑፍ ዝግጅት ዙሪያ  መረጃ ከመስጠት ባለፈ በቤተ ክርስቲያናችን በኩል የፊልሙ ጽሑፍ እንዲመረመርላቸውና እርማት በሚያስፈልገው ጉዳይ ዙሪያ እርማት እንዲደረግበት መጠየቃቸው የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህን ተከትሎም  የፊልም ጽሑፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ጉባኤ በሚገባ ተመርምሮና መታረም ያለበት ሁሉ ታርሞ እንዲቀርብ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ መመሪያ የተሰጠ ሲሆን የፊልም ጽሑፉም በሊቃውንት ጉባኤ እየተመረመረ መሆኑ ታውቋል። ሊቃውንት ጉባኤ የፊልሙን  ጽሑፍ መመርመሮ ሲያጠናቅቅም ውጤቱን የምንገልጽ ይሆናል።

ምንጭ: የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
" ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ከተመቱ በኃላ ህክምና ቢደረግላቸውም ሊተርፉ አልቻሉም " - ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉኃን ዘርዓዳዊት ኃይሉ ተገደሉ።

ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ11 ሰዓት ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትተው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ሊተርፉ ሳይችሉ ቀርቶ ሕይወታቸው ማለፉን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ አሳውቀዋል።

ብፁዕነታቸው የግድያው ምክንያት እንደማይታወቅ ገልጸው በክስተቱ የተሰማቸውን መሪር ኃዘን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኢኦተቤ ቴቪ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
በማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስታባበሪያ በርቀት ትምህርት ሲያስተምራቸው የነበሩትን 155 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም አስመረቀ፡፡
+++++++++++++++++++++++++++++++

በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋህዶ በነበረው የምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር)፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሙሉጌታ ሥዩም (ዶ/ር)፣ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መምህር ዋስይሁን በላይ፣ የማስተባበሪያ ኃላፊዎች፣ ተመራቂዎች እና ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

121 ወንዶችና 34 ሴት ተመራቂ ተማሪዎች በኢ ለርኒግና በሞጁል በስምንት ማእከላት ትምህርታቸውን መከታተላቸው በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በዋናነት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለመማር ፍላጎት ላላቸው ኦርቶዶክሳውያን እና በሌላ እምነት ውስጥ ላሉ ወገኖች ባሉበት ቦታ በአመቺ ቴክኖሎጂ ትምህርቱ እንደሚሰጥም ተጠቁማል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስታባበሪያ በኩል ምእመናን በምግባርና በሃይማኖት ጸንተው እንዲኖሩ፣ የጠፉትን ወገኖች ወደ ቤተ ክርስቲያን መመለስና አዳዲስ አማንያንን ማስተማር የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን እንዲያገኙ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባሩ ነው። በማለት መልእክት ያስተላለፉት የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሙሉጌታ ሥዩም (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ሰብሳቢው አክለውም ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት፣ የስብከት ኬላ መሥራት፣ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ማስከፈት፣ ጠረፋማ በሆኑ የሀገሪቱ ክፍሎች ለመምህራን ወርሀዊ ድጎማ በማድረግ ረገድ ዘርፈ ብዙ ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
2024/10/01 04:55:21
Back to Top
HTML Embed Code: