Telegram Web Link
✝️“አለሁ እኔ፣ ለወገኔ” ✝️
ለድጋፍዎ #የወገን ፈንድ አማራጭንም ይጠቀሙ!!
+++
ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ፣ ጠለምት፣ በየዳና ጃና አሞራ፣ እንዲሁም በዋግኸምራ ዞን ሰሃላና አካባቢው ባጋጠመው ድርቅ የተጎዱ ወገኖቼ ለመርዳት አስቸኳይ ድጋፍ እያሰባሰበ ይገኛል። እኔም የከበረ የሰው ሕይዎትን ለማትረፍ የተቻለኝን ድጋፍ አደርጋለሁ። እርስዎስ ?
ድጋፍ ለማድረግም፡-
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
3. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
4. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
5. በአዋሽ ባንክ - 01329817420400 መጠቀም ይችላሉ።
በወገን ፈንድ ለመለገስ የተያያዘውን ሊንክ ይጫኑ።
https://www.wegenfund.com/causes/nu-badereqe-yatagodu-waganocaacenene-hheyete-eneta/
ለበለጠ መረጃ
• 09 84 18 15 44
• 09 43 00 04 03
የማኅበረ ቅዱሳን ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
ሃያ አራቱ አለቆች (መጽሐፈ ስንክሳር)

ምስጋና ለሥሉስ ቅዱስ ይድረስና ሁልጊዜ በየዓመቱ በኅዳር ፳፬ ቀን እኛ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን የካህናተ ሰማይ /ሱራፌ/ በዓልን እንድናከብር አባቶች ሥርዓትን ሠርተውልናል፡፡

ቅዱሳን መላእክት ሱራፌል እግዚአብሔር ለመላእክት መኖሪያነት ከፈጠራቸው ከሦስቱ ሰማዮች መካከል በኢዮር በሦስተኛው ከተማ የሚኖሩ መላእክት ናቸው፡፡ ሱራፌል የነገደ መላእክቱ የብዙ ቁጥራቸው መጠሪያ ሲሆን በነጠላ ስማቸው ሱራፊ (የአንዱ መልአክ መጠሪያ) ይባላሉ፡፡

ስያሜ

ሱራፊ የሚለው ቃል ‹‹የሚያነድ፣ የሚያጤስ፣ የሚያጥን፣ ዐጣኝ›› የሚል ትርጉም ሲኖረው ይኸውም አገልግሎታቸውን ይገልጻል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ ፰፻፹፮) ቅዱሳን መላእክት ሱራፌል ሃያ አራቱ ካህናት፣ ሃያ አራቱ ሊቃናት (አለቆች)፣ አንዳንዴም ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች ተብለው የሚጠሩ ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የእውነት ካህናት የሆኑ ከቅዱሳን ሁሉ በላይ የሆኑና ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ ከፍ ከፍ ያሉ መላእክት ናቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራእዩ ‹‹በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው፣ በራሳቸውም የወርቅ አክሊል፣ ደፍተው ሃያ አራት ሊቃናት ተቀምጠው ነበር›› በማለት ስለ እነርሱ ጽፏል፡፡ (ራእይ ፬፥፲፬)
ቁጥራቸው ሃያ አራት የመሆኑ

መጽሐፍት እና የቤተ ክርስቲያን መምህራን ካህናተ ሰማይ ቁጥራቸው ሃያ አራት የሆነበትን ምክንያት ሲያስተምሩ ሱራፌል በሃያ አራቱ ሰዓት ያለሟቋረጥ ለአምላክ ምስጋናና ጸሎት በማቅረብ ራሳቸውንም ፍጥረትንም ጠብቀው ዋጋቸውን ተቀብለው የሚኖሩ በመሆናቸው አምላካችን እግዚአብሔር ሃያ አራት አድርጓቸዋል በማለት ይናገራሉ፡፡ በተጨማሪ ደግሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ዘሥጋ መነሻ የሆኑት ዐሥራ ሁለቱን አበውና በሐዲስ ኪዳን ደግሞ የእስራኤል ዘነፍስ መሠረት የሆኑትን የቅዱሳን ሐዋርያትን ድምር ስለያዙ ቁጥራቸው ሃያ አራት ሆኗል፡፡ ለቤተ እስራኤል ዐሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ምንጮች እንደሆኑ ለቤተ ክርስቲያንም ቅዱሳን ሐዋርያት ምንጭ /ነቅዕ/ ናቸውና፡፡ (መዝ.፲፯፥፲፭)

አገልግሎታቸው

ሱራፌል ‹‹ዐጠንተ መንበሩ ለልዑል›› በመባል ይጠራሉ፡፡ የካህን ሥራው መንበር ማጠን እንደሆነ እነርሱም ማዕጠንተ-ወርቃቸውን ይዘው፣ አክሊላቸውን ተቀዳጅተው፣ ስለሚያመሰግኑ ካህናተ-ሰማይ ተብለው ይጠራሉ፡፡ አእላፍ መላእክት ሲላላኩ፣ ኪሩቤል መንበሩን ተሸክመው ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› ሲሉ፣ ሠራዊተ-መላእክት ከፊቱ ቆመው ሲሰግዱ፣ ትጉሃን ሲያመሰግኑ፣ ሱራፌልም ማዕጠንተ ወርቃቸውን ይዘው መንበሩን እየዞሩ ያጥናሉ፡፡ ሥራቸውን በመንፈስ ቅዱስ የተመለከተው ቅዱስ ያሬድም ‹‹ፍቁራኒሁ ለአብ ኄራን መተንብላን እለ ይሥእሉ ምሕረተ ለውሉደ ሰብእ›› ይለናል (ኄራን መላእክት ለሰው ልጆች ምሕረትና ይቅርታን ይለምናሉ) ማለት ነው፡፡

በማዕጠንታቸውም ዘወትር ወደ አምላካችን የጻድቃንን ጸሎት፣ ምድራውያን ካህናት የሚሠውትን መሥዋዕት እና የሚያጥኑትን ዕጣን የሚያሳርጉም ቅዱሳን መላእክት ሱራፌል ናቸው፡፡ በቅዱሳን መላእክት ሱራፌል አገልግሎት ውስጥ ስድስቱ ክንፎቻቸው ሦስት ትእምርቶችን ይገልጻሉ፡፡ እነዚህም ትእምርተ ፍርሃት፣ ትእምርተ ተልእኮ እና ትእምርተ መስቀል ናቸው፡፡

ነቢየ ልዑል ኢሳይያስ የእነርሱን ሁኔታ ሲገልጥ ‹‹ሱራፌል በዙሪያው ቆመው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፤ በሁለት ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፤ በሁለት ክንፍ ይበርር ነበር፡፡ አንዱም ላንዱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር፡፡›› ብሏል (ኢሳ.፮፥፪-፫)

በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን መሸፈናቸው፣ በሁለቱ ክንፋቸው እግራቸውን መጋረዳቸው የመለኮቱ እሳትነት /ዋዕየ መለኮ/ እንዳያቃጥላቸው ነው፤ ያስ ቢሆን አካላቸው አይደለም ቢሉ ትእምርተ ፍርሀት ነው፤ አሁን ሰው ሾተል በመዘዙበት፣ ጦር በነጠቁበት ጊዜ እጁን እንደሚጋርድ ነው፡፡

ሁለት ክንፋቸውን ወዲያ እና ወዲህ ማድረጋቸው ትእምርተ ተልእኮ፣ ተልእኮ አለብን ማለታቸውን ይገልጻል፡፡ በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግራቸውን ሲሸፍኑ በሁለቱ ክንፋቸው ጽንፍ እስከ ጽንፍ ሲበሩ በአንድነት ትእምርተ መስቀል ይሆናል፡፡

ቅዱሳን መላእክት ሱራፌል (ካህናተ ሰማይ) ዛሬ የእኛ ሕይወት ፍቅር በማጣት፣ በኃጢአት ከርፍቷልና በወርቅ ማዕጠንታቸው የፍቅርን ዕጣን አጥነውን፣ ከኃጢአታችንም ነጽተንና ሥራችን ሁሉ በጎ መዓዛ ኖሮት በሰላምና በመተሳሰብ ለመኖር ይርዱን፤ አሜን!

ምንጭ፡- መጽሐፍ ቅዱስ፣ ትንቢተ ኢሳይያስ ንባቡና ትርጓሜው (በአንድምታ)፣ መጽሐፈ ስንክሳር ፣ መጽሐፈ አሚን ወሥርዓት በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ ፣ምሥጢረ ሰማይ ( መምህር ማዕበል ፈጠነ)፣ የአንቀጸ ብርሃን አንድምታ ትርጓሜ (መምህር ኃይለማርያም ዘውዱ)
በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በማስመልከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ ፤
**********

"ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ
እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።" 1ኛ ጴጥርስ 4፥12:13

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን       

በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በጥብቅ እናወግዛለን፤ የጸጥታ ተቋማትም ጥቃቱን እንዲከላለሉ እንጠይቃለን።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ ሶሌ ሚካኤል፣ በዲገሎ ማርያም፣ በሮቤ እንደቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት 36 ኦርቶዶክሳዊያን በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ሀገረ ስብከቱ ባደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።

በዚሁ ጥቃት በሶሌ ዲገሉ እና ጢጆ ለቡ በተባሉ ቀበሌዎች 28 ኦርቶዶክሳዊያን ከየቤታቸው ተለቅመው የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም 7ቱ ሴቶችና 21ዱ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል። በዚህ ጥቃትም እድሜያቸው ከሰባ ዓመት አዛውንት እስከ ሃያ ስምንት ቀን ጨቅላ ሕጻናት ይገኙበታል። በዛሬው ዕለት ደግሞ በዲገሉ ማርያም ቤተ ክርስቲያን 5 ኦርቶዶክሳዊያን ከመገደላቸው በተጨማሪ የሦስት ኦርቶዶክሳውያን ቤት ደግሞ ተቃጥሏል። 
ከዚህ ቀደም በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም ቤተክርስቲያን በዓለ ማርያምን አክብረው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ ሦስት ኦርቶዶክሳዊያን ጨለማን ተገን ባደረጉ ነፍሰ ገዳዮች መገደላቸው ይታወሳል።

የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ በሚፈጸመው የኦርቶዶክሳዊያን ጥቃት ዙሪያ በጋራ እየሠሩ የሚገኙ ሲሆን በዚህ ዐይነት የጥቃት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አንዳንድ አካላት ላይ በመንግሥት በኩል የማያዳግም ርምጃ እንደተወሰደባቸው ሀገረ ስብከቱ  በላከው ሪፖርት አረጋግጠዋል።

ይህ ዐይነት ሃይማኖት ተኮር ጥቃት በምእመናን ላይ መድረሱ አግባብነት የሌለውና እምነትን በነጻነት የማራመድ መንግስታዊ መብትን የሚጥስ በመሆኑ መሰል  ሕገ ወጥ ጥቃትን ለመከላከልና  ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት መብቶቻቸውን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ማስከበር እንዲችሉ  ያቋቋሙት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ድርጊቱን በማውገዝ ችግሩ ከመሠረቱ እንዲፈታ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር መፍትሔ መፈለግ ሲገባው በዝምታ በማለፉ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ቅሬታ ተሰምቷታል።

ይህ ዐይነቱ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠረ ግድያ እንዲቆምና የወንጀሉ ፈጻሚዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ በሀገረ ስብከቱ በኩል እየተደረገ ያለው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትም በድርጊቱ እጅጉን ማዘኑን እየገለጸ ጉዳዩን  ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር  በመሆን የሚከታተለው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

በሌሎች ስፍራዎች የሚያጋጥሙ ተመሳሳይ ጥቃቶችን በእንጭጩ ለመቅጨትና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ማበጀት ይቻል ዘንድ አህጉረ ስብከት ችግሮች በሚያጋጥሙ ወቅት ሪፖርት እንዲልኩ ቀደም ሲል በደብዳቤ በተላከላቸው የስልክና ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት በፍጥነት በማሳወቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እያሳሰብንና ለሞቱት ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር መንግሥተ ሰማያትን እንዲያወርስልን በመጸለይ የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥታት የሚደርሱ ሃይማኖት ተኮር ጥቃቶች እንዲቆሙና መሰል ጥቃት እንዳይፈጸም ለኦርቶዶክሳዊያን ወገኖቻችን ከለላ እንዲሰጡልን እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት

ምንጭ: የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
#Update

ቤተክርስቲያኗ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በጥብቅ እንደምታወግዝና የጸጥታ ተቋማትም ጥቃት እንዲከላለሉ ጥሪ አቀረበች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ፦
- በሶሌ ሚካኤል፣
- በዲገሎ ማርያም፣
- በሮቤ እንደቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት 36 ኦርቶዶክሳዊያን በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጿል።

በዚሁ ጥቃት በሶሌ ዲገሉ እና ጢጆ ለቡ በተባሉ ቀበሌዎች 28 ኦርቶዶክሳዊያን ከየቤታቸው #ተለቅመው መገደላቸውን ፤ ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ ሴቶችና 21ዱ ወንዶች መሆናቸው መታወቁን አመልክቷል።

በዚህ ጥቃትም እድሜያቸው ከሰባ ዓመት አዛውንት እስከ ሃያ ስምንት ቀን ጨቅላ ሕጻናት እንደሚገኙበት ገልጿል።

#በዛሬው_ዕለት ደግሞ በዲገሉ ማርያም ቤተክርስቲያን 5 ኦርቶዶክሳዊያን መገደላቸውንና የሦስት ኦርቶዶክሳውያን ቤት መቃጠሉን አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም ቤተክርስቲያን በዓለ ማርያምን አክብረው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ 3 ኦርቶዶክሳዊያን ጨለማን ተገን ባደረጉ ነፍሰ ገዳዮች መገደላቸውን ፅ/ቤቱ አስታውሷል።

የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ በሚፈጸመው የኦርቶዶክሳዊያን ጥቃት ዙሪያ በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ የገለፀው ፅ/ቤቱ  " በዚህ ዐይነት የጥቃት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አንዳንድ አካላት ላይ በመንግሥት በኩል የማያዳግም #ርምጃ_እንደተወሰደባቸው ሀገረ ስብከቱ በላከው ሪፖርት ማረጋገጡን አመልክቷል።

ይህ ዐይነት ሃይማኖት ተኮር ጥቃት በምእመናን ላይ መድረሱ አግባብነት የሌለውና እምነትን በነጻነት የማራመድ መንግስታዊ መብትን የሚጥስ ነው ያለው ፅ/ቤቱ ፤ መሰል ሕገ ወጥ ጥቃትን ለመከላከልና ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት መብቶቻቸውን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ማስከበር እንዲችሉ  ያቋቋሙት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ድርጊቱን በማውገዝ ችግሩ ከመሠረቱ እንዲፈታ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር መፍትሔ መፈለግ ሲገባው በዝምታ በማለፉ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ቅሬታ እንደተሰማት ገልጿል።

" ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠረ ግድያ እንዲቆምና የወንጀሉ ፈጻሚዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ በሀገረ ስብከቱ ጥረት እየተደረገ ነው " ያለው ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመሆን ፅ/ቤቱም ጉዳዩን የሚከታተለው መሆኑን አሳውቋል።

በሌሎች ስፍራዎች የሚያጋጥሙ ተመሳሳይ ጥቃቶችን በእንጭጩ ለመቅጨትና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ማበጀት ይቻል ዘንድ አህጉረ ስብከት ችግሮች በሚያጋጥሙ ወቅት በፍጥነት በማሳወቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት መፍትሔ ሊሰጥባቸው ይገባል ያላቸውን በ13 ነጥቦች የተዘረዘሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሀገረ ስብከቱ በኩል መፍትሔ እንዲሰጣቸው ውሳኔ አስተላለፈ።
****

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ጉባኤ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጋር ባደረገው ውይይት በሀገረ ስብከቱ በኩል የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተመለከተ በተደረገው የጋራ ውይይት በሀገረ ስብከቱ የሚስተዋሉትን ዋናዋና ችግሮች መቅረፍ ይቻል ዘንድ በጠቅላይ ቤተክህነት በኩል ተለይተው የሚታወቁት ዋናዋና ነጥቦች ለሀገረ ስብከቱ እንዲደርሰው ተደርጎ መፍትሔ እንዲሰጥበት የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሔኖክ በጉባኤው ወቅት በሰጡት ማጠቃለያ ሀሳብ ላይ በገለጹት መሰረት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ጉባኤ ኅዳር 24ቀን2016ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ሀገረ ስብከቱ በኩል በአፋጣኝ ምላሽ ሊያገኙ ይገባቸዋል ያላቸውን
13 ነጥቦችን በመለየት ለሀገረ ስብከቱ እንዲደርሰውና ከበዛ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለተጠቀሱት የመልካም አስተዳደር ችግሮች ምላሽ እንዲሰጥና የውሳኔውን መፈጸም አለመፈጸም በተመለከተም ተከታትለው የሚያስፈጽሙ ሦስት የመምሪያ ኃላፊዎችን መድቧል።

የጠቅላይ ቤተክህነቱ ዋና ዓላማ ሕግ፣ደንብና መመሪያ ተከብሮ ስራ እንዲሰራ ፣ፍትሕና ርትዕ እንዲነግስ፣
ተጠያቂነትና ግልጽነትን የተከተለ ተቋማዊ አሰራር እንዲሰፍን ለማድረግ እንደሆነ ከመግለጽ ጋር የሚከሉት ዋና ዋና ነጥቦች በሥራ ላይ እንዲውሉ ሲል ልዩነት በሌለው ድምጽ ወስኗል።
የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አስመልክቶ በጋራ የውይይት መድረክ ችግሮችን በመለየት በውይይት በመፈተሸ በጋራ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንዲቻል አስቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም በወሰነው መሠረት ኅዳር 18 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው የጋራ የውይይት መድረክ እንደ ችግር ተለይተው በቀረቡ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ተመሥርቶ በቀረበው የቃለ ጉባኤ ዘገባ ላይ ተወያይቶ ለመወሰን የተደረገ ስብሰባ ነው፡፡

በመሆኑም ጉባኤው ኅዳር 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ከክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የተደረገውን የጋር የውይይት መድረክ አስመልክቶ ከቃለ ጉባኤ ጸሐፊዎች የቀረበውን የቃለ ጉባኤ ዘገባ በንባብ ካዳመጠ በኋላ የችግሩ መንስዔ ናቸው በማለት የተለዩ ዋና ዋና ነጥቦች፦

1.በሀ/ስብከቱ ረጅም ዘመናት ሲንከባለል የመጣ የመልካም አስተዳደር ችግር መኖሩ የሚታወቅ ቢሆንም በአሁኑም ሰዓት የበለጠ ተባብሶ የቀጠለ መሆኑን፤

2 የመልከም አስተዳደር ችግርሩ መንስዔ የሕጎችና የደንቦች ጥሰት፤በእቅድና በጸደቀ በጀት ላይ ተመስርቶ ያለመሥራት ውጤት መሆኑን፤

3. መተዳደሪያ ደንቡ ተጥሶ በፍላጎት ላይ ያልተመሠረተ ቅጥርና የሠራተኞች መብትን ያላከበረ የዝውውር ምደባ ውጤት መሆኑን፤

4.የሐብትና የገንዘብ ቁጥጥር ሥራው ደካማ መሆኑ፤

5.ከበላይ መስሪያ ቤት ጋር ተናቦ ያለመሥራትና መሰል ችግሮች ያስከተለው ውጤት መሆኑን ከጋራ ስብሰባውና ከዘገባ ሪፖርቱ ለአስተዳደር ጉባኤው ግንዛቤ በመውሰድና በውይይት የተለዩትን ዋና ዋና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አስመልክቶ የሀስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በማጠቃለያ በሰጡት ሐሳብ ላይ የመልካም አስተዳደር ችግሮቹ ተለይተውና ተቆጥረው ይሰጡን ለመፍታት ዝግጁ ነን በማለት በገቡት ቃል መሠረት አስተዳደር ጉባኤው በችግሮቹ ላይ በሰፊው ተወያይቶ የሚከተለውን ውሳኔ ወስኗል፡፡

ው ሳ ኔ
አስተዳደር ጉባኤው ከፍ ብሎ በጋራ የውይይት መድረኩ በዝርዝር የተቀመጡትን ዋና ዋና የችግር መንስኤዎችን በመለየት በሀ/ስብከቱ የተሸለ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት መልካም አስተዳደር ማስፈን ይቻል ዘንድ ፡-

1.በሀ/ስብከቱ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ  ንኡስ ቁጥር  የህግ ድንጋጌ መሠረት ሀ/ስብከቱ ዓመታዊ እቅዱንና በጀቱን አጥንቶና በጉባኤ ወስኖ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አቅርቦ በማጸደቅ ተግባራዊ ያደርጋል በሚል የተደነገገ ቢሆንም እስከአሁን ድረስ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት ቀርቦ የጸደቀ በጀት ባለመኖሩ ሀ/ስብከቱ ዓመታዊ ዕቅዱንና በጀቱን በአስቸኳይ በጉባኤ ወስኖ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አቅርቦ በማጸደቅ ተግባራዊ እንዲያደር፤

2.ሀ/ስብከቱ የሰው ኃይል እጥረት ሳይሆን ያለውን የሰው ኃይል ከሥራው ጋር በማጣጣም ሥራና ሠራተኛን በማገናኘት የማሠራት ችግር መሆኑን ጉባኤው ተረድቷል በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም ቋሚ ሲኖዶስ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ፣ መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም እና ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በወሰነው መሠረት ለሥራው ሲባል መተዳደሪያ ደንቡ ተጠብቆ ከሚደረግ የውስጥ ዝውውርና ሽግሽግ በስተቀር ይህ ውሳኔ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ምንም ዓይነት ቅጥር እንዳይፈጸም፤

3.ሽልማትና ልዩ ልዩ ስጦታዎችን በተመለከተ አንድ ሰው ሊሸለም የሚችለው ዕለት ተዕለት እንዲያከናውን ከተሰጠው የሥራ ተልዕኮ በላይ ለተቋሙ እድገትና ለተሻለ አሠራር በእራሱ ተነሳሽነት ላከናወናቸው ተጨማሪ የሥራ አፈጻጸም የተለየ ብልጫ እንዳስመዘገበ ሲታመን ለበለጠ ሥራ ለማነሳሳትና ለሌሎቹ ምሳሌ መሆኑ የታመነ ነው፤ ነገር ግን እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ከሀ/ስብከት እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ድረስ እየተፈጸመ ያለው ሽልማት ግን ለብዙ ትችትና የሐብት ብክነት የተጋለጠ በመሆኑ ሽልማት መስጠት አስፈላጊነቱ ሲታመንበት የሥራ አፈጻጸምንና የአገልግሎት ትጋትን መሠረት አድርጎ እንዲከናወን እንዲደረግና ከነዚህ መመዘኛ መሥፈርት ውጪ ያሉ ሽልማቶች እንዲቆም፤

4. የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እስከአሁን ሲያደርገው እንደቆየው ሁሉ ሒሳቡን በውጭ ኦዲተር ለማስመርመር በያዘው እቅድ መሠረት ኦዲተሮችን አወዳድሮ ሥራውን ለማስጀመር ዝግጅቱን ያጠቃለለ ሲሆን ሀ/ስብከቱም በአስቸኳይ እስከ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ድረስ የሚገኙትን ሒሳቦች በገለልተኛ የውጭ ኦዲተር አስመርምሮ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያቀርብ፤

5. በክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ደረጃ ለፐርሰንት መሰብሰቢያ በሚል የተከፈቱ የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች እስከ አሁን ድረስ በሀ/ስብከቱና በክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ጣምራ ፊርማ ሲንቀሳቀስ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከሁለቱ ፈራሚዎች በተጨማሪ የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ተጨምረው በሦስት ጣምራ ፊርማ ብቻ እንዲንቀሳቀስና ከፐርሰንቱ የሚገኘው የባንክ ወለድም ተጠቃሎ ወደ ሀ/ስብከቱ የባንክ ሒሳብ ፈሰስ እንዲደረግ፤

6. ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ጀምሮ እስከ ሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ድረስ መስተንግዶ በሚል ሽፋን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ብክነት እየደረሰ እንደሚገኝ ጉባኤው በጋራ ውይይቱ ከተነሱ ሐሳቦች ተገንዝቧል፤ ስለሆነም አስቀድሞ በእቅድ ላይ ተመሥርቶ ከጸደቀ የእህል ውሃ መስተንግዶ በጀት ውጭ ምንም ዓይነት የመስተንግዶ ወጪ እንዳይደረግ፤

7. ሀ/ስብከቱ ለሐብትና ንብረት ቁጥጥር በሚል በወራዊ እና ዓመታዊ ክብረ በዓላት በተቆጣጣሪነት ወደ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሚልካቸው ልኡካን የገንዘብ እና የንብረት ገቢን አስመልክቶ አጠቃላይ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚላኩትም ልኡካን ምደባ እውቀትን፣ የሥራ ልምድንና ታማኝነትን መሠረት ያደረገ እንዲሆንና የሚከፈለውም አበል ከአጥቢያ እስከ ሀ/ስብከት ድረስ በቋሚ ሲኖዶስ በተወሰነው የአበል አከፋፈል መሠረት ብቻ ተፈጻሚ እንዲሆን፤

8. እስከ አሁን ድረስ ለዓመታዊ የሒሳብ ምርመራ የሚላኩ ልኡካን የሒሳብ እውቀት የሌላቸውን ሁሉ በጅምላ በመመደብ የሚፈጸመው ዓመታዊ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሒሳብ ምርመራና የኦዲት ሥራ አግባብነት የሌለውና በርካታ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ በጋራ ውይይቱ ስለተረጋገጠ ሀ/ስብከቱ የሒሳብ ሙያና ልምድ ባላቸው የጽ/ቤቱ ሠራተኞች የኦዲትና ቁጥጥር ሥራውን እንዲያከናውን ሆኖ የሒሳብ ባለሙያ እጥረት ካጋጠመው ከዋናው መሥሪያ ቤት የቁጥጥር መመሪያ አገልግሎት ከሚገኙ ኦዲተሮች ጋር በጣምራ ዓመታዊ የኦዲት ሥራው እንዲያከናውን፤

9. በጋራ የውይይት መድረኩ በተደረሰው ስምምነት መሠረት ልዩ ልዩ አስተዳደራዊ የሥራ በደል ደርሶባቸው አለአግባብ ከሥራ የታገዱ፣ በወቅታዊ ችግር ከሥራ የተፈናቀሉ የትግራይና ሌሎች አካባቢዎች ተወላጅ ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች ፣ ያለ ሥራ የተንሳፈፉና በሕገወጥ መንገድ ከደረጃ ዝቅ ያሉ እንዲሁም በአጥቢያ ደረጃ የተከሰቱ የሰበካ ጉባኤ ምርጫና ሌሎች የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎች በሙሉ ተጠቃለው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተፈተውና ምላሽ አግኝተው ለዋናው መሥሪ ቤት ሪፖርት እንዲቀርብ፤
10.ከሀ/ስብከቱ መተዳደሪያ ደንብ እስከ የበላይ ሕግ የሆነው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ጥብቅ አስተዳዳሪ የሚል የሥራ መደብ በሌለበት ሁኔታ ሀ/ስብከቱ በእራሱ ፍላጎት ስያሜውን ፈጥሮ በርካታ አስተዳዳሪዎች ያለ ሥራ መደብ ተንሳፈው እያለ ከአሥራ ሁለት ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት ጥብቅ በሚል አስተዳዳሪ እየተመሩ መሆናቸውን በመረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ስለሆነም በቀጣይ ከመዋቅር ውጭ በሆነ ስያሜ በየትኛውም አብያተ ክርስቲያናት ጥብቅ አስተዳዳሪ እንዳይመደብ እንዲደረግና አሁን በጥብቅ አስተዳደር በሚል ክፍት በሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ላይ መተዳደሪያ ደንቡ ተጠብቆ ያለ ሥራ የተንሳፈፉና በአቤቱታ ላይ የሚገኙት አስተዳዳሪዎች ምደባ ተጠንቶ እንዲቀርብ፡፡

11. ለሀ/ስብከቱ መልካም አስተዳደር ችግር እንደ ዋና መንስኤ የሆኑት በክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት እና በአጥቢያ ደረጃ የሚፈጸሙ ቅጥር፣ ዝውውርና እግድ በሙሉ እንዲቆም፤

12. ከክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት እስከ ሀ/ስብከት በውይይቱ ተሳታፊ የሆኑ የሥራ ኃላፊዎች ለሀ/ስብከቱ መተዳዳሪያ ደንብ ተፈጻሚነትና ስለ መልካም አስተዳደር ችግሮች አፈታት እስከታች አስፈጻሚ አካል ደረስ ግንዛቤ ይፈጠርልን በማለት በአጽንኦት ባሳሰቡት መሠረት ከሀ/ስብከት አስከ አጥቢያ ድረስ ላሉት የቤተ ክርስቲያናችን አገልጋችና የቢሮ ሰራተኞች እንዲሁም ለሰበካ ጉባኤ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በቀጣይ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት በኩል በአጭር ጊዜ ውስጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅ፤

13. የሀ/ስብከቱ ማኅበራዊ ሚዲያ የተቋቋመበት መሠረታዊ ዓላማ ከሀ/ስብከት እስከ አጥቢያ ያሉትን የዕለት ተዕለት ሐዋርያዊና አስተዳደራዊ ክንውኖችን ለምዕመናን ተደራሽ ለማድረግ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ማኅበራዊ ሚድያው ከቋቋመበት ዓላማ ውጪ የሀ/ስብከቱን የመልካም አስተዳደር ችግር በጋራ ውይይት ለመፍታት የተደረገውን የምክክር መድረክ በተሳሳተ መድረክ በመዘገብ የተዛባ መረጃ ለሕዝብ እንዲደርስ በማድረግ የፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ጉባኤውን በእጅጉ ያሳዘነ አድራጎት ሲሆን ዋናው መሥሪያ ቤት ባደረገው ማጣራትም በድረገጹ ላይ የማይመለከታቸው ግለሰቦች ጭምር የራሳቸውን ፍላጎት የሚለጥፉበት አጋጣሚዎችም እንዳሉ መረጃዎች ቀርበዋል፡፡ ስለሆነም እንዲህ ዓይነቱ ሕገ ወጥ አድራጎት እንዳይደገም ሆኖ በቀጣይ ከሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊውና ከሚመለከታቸው የክፍሉ ሠራተኞች በስተቀር የትኛውም አካል የራሱን ፍላጎትና የተዛባ መረጃ እንዳይለጥፍ በሀ/ስብከቱ በኩል ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግ ሲል ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ወስኖ የዕለቱን ስብሰባ በብፁዕ አባታችን ጸሎትና ቡራኬ አጠናቋል፡፡

ትእዛዝ
1ኛ. የአስተዳደር ጉባኤው የውሳኔ ቃለ ጉባኤ በመሸኛ ደብዳቤ ለሀ/ስብከቱ ይላክ፤
2ኛ. የቅሬታ አቅራቢ ባለጉዳዮች ስም ዝርዝር ከመሸኛ ደብዳቤ ጋር ለሀ/ስብከቱ ይላክ፤
3ኛ. ይህ ውሳኔ በአግባቡ ስለመፈጸሙና አለመፈጸሙ የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ምምሪያ ፤የሕግ አገልግሎት መምሪያና የቁጥጥር አገልግሎት መምሪያ እየተከታተሉ ሪፖርት እንዲያደርጉ፤

ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ውድ ተከታታዮች ከዚህ በኃላ ለሣምንታት የሚቆይ ትምህርተ ሃይማኖት ኮርስ አዘጋጅተናል መምህራንም ካላችሁ የግሩፑን ተቆጣጣሪዎች በማናገር መሳተፍ ትችላላችሁ።

አሁን የእናንተን ፍላጎት ማወቅ ስለምንፈልግ ሁላችሁም አስተያያት እንድትሰጡ ስንል እንጠይቃለን።ለጊዜው ብዙ ሰው ካልሰጠ ኮርሱ የሚቆይ ይሆናል
መማር ምትፈልጉ ከታች ባለው reaction ወይ Admin ማናገር ትችላላችሁ።
 
‹‹የእግዚአብሔር ሰው›› (፩ኛሳሙ.፱፥፮)

ክፍል ሦስት

ሐሰተኞች ነቢያት በየዘመናቱ ነበሩ፡፡ በራሳቸው በነቢያት ዘመንም፣ በሐዋርያት ዘመንም ዛሬም በዘመናችን ሐሰተኞች ነቢያት አሉ፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን በርካቶች ዐውቀው ለገንዘብ ብለው የሐሰት ትንቢት ይናገሩ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ተሳስተው፥ ከራሳቸው ከልባቸው አንቅተው ከራሳቸው የልብ አሳብ ይናገሩ ነበር፡፡ በትንቢተ ሕዝቅኤል ላይ ‹‹ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-ፈጽሞ ሳያዩ ከገዛ ልባቸው አንቅተው ትንቢት ለሚናገሩ ወዮላቸው›› የሚል ቃል አለ፡፡ (ሕዝ.፲፫፥፪)
 
ሌሎቹ ደግሞ በክፉ መንፈስ ተመርተው ትንቢት የሚናገሩ ናቸው፡፡ በመጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ተመዝግቦ እንደምናገኘው ነቢዩ ሚክያስ ከእግዚአብሔር የተነገረውን የትንቢት ቃል ለንጉሡ ለአክዓብ ሁልጊዜ ይነግረውና ያስጠነቅቀው ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን የነቢዩን ትንቢት እውነት  በመሆኑ ለመቀበልም ስለሚያዳግተው እርሱ የሚፈልገውን በጎ ነገር ብቻ በትንቢት መልክ እንዲነግረው ይሻ ነበር፡፡
 
አንድ ቀን የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ከጦር መሪዎቻቸው ጋር በአደባባይ ተቀምጠው ሳለ ነቢያቱ ሁሉ የሐሰት ትንቢት ይናገሩ ነበር፡፡ እነዚያ የንጉሥ አሸርጋጅ የሐሰት ነቢያት ንጉሡን የሚመክሩት ወደ ሬማት ዘገልአድ እንዲዘምት ሶርያውያንንም እንዲወጋቸው፣ እግዚአብሔርም እንደሚረዳው፣ የሶርያውያንንም ንጉሥ እግዚአብሔር አሳልፎ በእጁ እንደሚሰጠው ወዘተ ንጉሡ የሚሻውን በትንቢት መልክ በጎ በጎውን ይናገሩ ነበር፡፡ ንጉሡም የእግዚአብሔር ነቢይ ሚክያስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል ለማወቅ እንዲጠሩት ሰው ላከበት፡፡
 
መልእክተኛውም ሚክያስን ‹‹እነሆ ነቢያት ሁሉ በአንድ አፍ ሆነው ለንጉሡ መልካሙን ይናገራሉ፤ ቃልህም እንደ ቃላቸው እንዲሆን መልካም እንድትናገር እለምንሃለሁ›› ይለዋል፡፡ (፩ኛ ነገ.፳፪፥፲፫) ነቢዩ ግን ‹‹ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር የሚነግረኝን እርሱን እናገራለሁ›› አለው፡፡ ሚክያስም ለንጉሡ መራራውን እውነት ነገረው፡፡ ሶርያውያንንም እንደማያሸንፍ፥ ይልቁንስ እስራኤላውያን ጠባቂ እንደሌላቸው በተራራ ሲበተኑ ማየቱን፣ እርሱም እንደሚሞት ጭምር ነገረው፡፡ በዘመናችንም ያሉ ነቢያት ‹‹ትራንስፎርሜሽን›› (ለውጥ) አየን የሚሉ፣ መሪዎችን በሐሰተኛ ትንቢት ጦርነት ታሸንፋለህ የሚሉ፣ መራራውን እውነት ሳይሆን የመሪዎችን የልብ ትርታ በትንቢት መልክ የሚናገሩ፣ እግዚአብሔርን ሳይሆን ሥርዓትን የሚያገለግሉ ለመሆናቸው ሚድያውን የተቆጣጠሩትን ነቢያት ነን ባዮች ቃል በመስማት ለመረዳት አይከብድም፡፡
 
አክዓብ ግን ኢእዮሣፍጥ ምን አለ? ‹‹ክፉ እንጂ ደግ እንደማይናገርልኝ አላልሁህምን?›› አለው፡፡ ሚክያስ እንደ ክፉ ተናጋሪ ተቆጥሯል፡፡ ምክንያቱም ንጉሡ የፈለገውን ሳይሆን እግዚአብሔር የነገረውን ተናግሯልና፡፡ ዛሬም በሀገራችን፣ በቤተ ክርስቲያናችን ጭምር እንደ ሚክያስ እውነቱን ሊመጣ ያለውን ጉዳት፣ እግዚአብሔር ያልወደደውን ሥራ የሚናገሩ እንደ ክፉ ተናጋሪ፣ እንደ ሟርተኛ፣ በጎ በጎ እንደማይታያቸው ጨለምተኞች ይታያሉ፡፡ ነቢዩ ሚክያስ ግን  ‹‹የእግዚአብሔርን ቃል የሰማሁት እኔ አይደለሁምን?....በሬማት ዘገልአድ ወጥቶ ይወድቅ ዘንድ አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው?›› አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ክፉ መንፈስ ወጥቶ በእግዚአብሔር ፊትም ቆሞ ‹‹እኔ አስተዋለሁ›› አለ፡፡ ‹‹እግዚአብሔርም በምን ታስተዋለህ?›› ቢለው እርሱም ‹‹ወጥቼ በነቢያቱ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ›› አለ፡፡
 
ሚክያስ ግን በንጉሡ ትእዛዝ በጥፊ ተመታ፤ በግዞትም እንዲቀመጥ ተወሰነበት፤ የመከራ እንጀራም መገቡት፤ የመከራ ውኃም እንዲጠጣ ተደረገ፡፡ በዘመናችን ክፉ መንፈስ ወጥቶ በነቢያቱ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ ሆኗል፡፡ እውነት የሚናገሩ ግን በጥፊም፣ በሰይፍም ይመታሉ፤ በግዞትም ይጣላሉ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ናቸው፤ እውነትን ይናገራሉና፡፡
 
ነቢይ ሐሰተኛ ነው የሚባለው ምን ሲሆን ነው? ለሚለው በርካታ ነገሮችን ማንሣት ይቻላል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተገለጡ ምክንያቶች ጥቂቶቹን ለማንሣት እንሞክር፡፡
 
አንደኛ ቃሉ ሳይፈጸም ሲቀር ነው፡፡ ቀደም ሲል በጠቀሰነው በአክዓብና በነቢዩ ሚክያስ ታሪክ ውስጥ ነቢያተ ሐሰት አክዓብን ዝመት ሶርያውያንን ታሸንፋለህ፤ ንጉሡንም እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል ወዘተ የሚል ትንቢት ነግረውት ነበር፡፡ ነገር ግን ሐሰተኛ የቤተ መንግሥት ቅልብ ነቢያት ያሉትን ትንቢት ሰምቶ ሚክያስን ወደ ግዞት ልኮ ለጦርነት የሄደው አክዓብ በሳንባውና በደረቱ መካከል በጦር ተወግቶ፣ ደሙም በከንቱ ፈሶ ሞተ፡፡ (፩ኛ ነገ.፳፪፥፴፬፤ ፪ኛዜ.መ ፲፰፥፳፰-፴፬)  እግዚአብሔር ለነቢዩ ሙሴ ‹‹ያ ነቢይ በእግዚአብሔር ስም ከተናገረው ባይደርስ፣ እንደተናገረውም ባይሆን እግዚአብሔር ያን ቃል አልተናገረውም፤ ነቢዩ በሐሰት ተናግሮታልና አትስማው›› ብሎታል፡፡ (ዘዳ.፲፰፥፳፪)
 
ሁለተኛ ባዕድ አምልኮትን ሲከተል ነው፡፡ በባዕድ አምልኮ የሚኖሩ ነገር ግን “ትንቢት እንናገራለን፤ ራእይ እናያለን፤ ተአምራት እናደርጋለን” የሚሉ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት በየዘመናቱ አሉ፡፡ ምልክትም ተአምራትም ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተአምራት ቢፈጽሙም እንኳን ለፈተና በመሆኑ ከእግዚአብሔር ቃል እንዳንወጣ፣ በአምልኮአቸውም እንዳንከተላቸው የዚያን ሕልም አላሚ ወይም ነቢይ ቃል እንዳንሰማ  በሙሴ አማካኝነት ተነግሮናል፡፡ (ዘዳ.፲፫፥፩-፬)
 
ሦስተኛ አካሄዱ ክፉ ሲሆን ነው፡፡ ስለ እነዚህ የሐሰት ነቢያት ደግሞ ኤርምያስ ሲናገር ‹‹ስለ ነቢያት ልቤ በውስጤ ተሰብሯል፤ አጥንቶቼም ሁሉ ታውከዋል፤ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ ከጌትነቱም ክብር የተነሣ እኔም በመከራ እንደተቀጠቀጠ ሰው፣ የወይን ጠጅ እንዳሸነፈውም እንደ ሰካራም ሰው ሆኛለሁ፡፡ ዝሙታቸው ምድርን ሞልቷልና፤….ነቢዩና ካህኑም ረክሰዋል፤ በቤቴ ውስጥ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ ይላል እግዚአብሔር›› ይላል፡፡
(ኤር.፳፫፥፱) በእውነቱ ይህ ቃለ ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው በእኛ ዘመን አስኪመስል ድረስ ያስደንቀናል፡፡ በተአምራት ስም፣ በትንቢት መናገር ሰበብ፣ በፈውስና በራእይ ሽፋን እንዴት ምድራችን በክፉ ሥራ እንደ ተሞላች ያስረዳናል፡፡ በርካቶች ተአምራትና ፈውስ ፍለጋ፣ ያልደከሙበትን ሀብት ለማግኘት ሲሉ በአምልኮ ስም በዝሙት ረክሰዋል፤ አካሄዳቸው ክፉ በሆኑ ነቢያተ ሐሰት፣ ካህናተ ሐሰት ሕይወታቸው ተመሰቃቅሏል፡፡ ከዚህ የተነሣ የእውነተኞችን ልብ የሚሰብር ርኩሰት በየቀኑ እንሰማለን፡፡
 
አራተኛ ኀጢአት በበዛ ጊዜ ስለ ፍርድ ሳይሆን ስለ ሰላም ሲተነብይ ነው፡፡ ይህንንም ሐሳብ በትንቢተ ኤርምያስ የትንቢት ቃል እንመለከተዋለን፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ በምድር ላይ ኀጢአት ሞልቶ ሲፈስ፣ ስለ መለኮታዊ ፍርድ መናገር ሲገባቸው፣ ስለ ንስሓ መስበክ ትተው፣ በከንቱ ሰላም ሳይሆን ሰላምን የሚሰብኩትን ሐሰተኞች ነቢያት ቃላቸውን እንዳንሰማ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ትንቢት የተናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትስሙ፤ ከንቱነትን ያስተምሯችኋል፡፡ ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ ልባቸው የወጣን ራእይ ይናገራሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ለሚያቃልሉ ሰላም ይሆንላችኋል፤ በፍላጎታቸውና በልቡናቸው ክፋት ለሚሄዱም ሁሉ ክፉ ነገር አያገኛችሁም ይላሉ›› በማለት ይነግረናል፡፡ (ኤር፳፫፥፲፮) ትልቁ የትውልዳችን ፈተና ይህ ነው፡፡ ሰላም ሳይኖር ሰላም ነው የሚሉ፣ ሰው ራሱን እንዳያይ፣ በንስሓ እንዳይመለስ፣ ኀጢአቱን እየዘከረ እንዳይጸጸት፣ የአምላኩን ዳግም መምጣት፣ የእርሱን ለፍርድ
መቅረብ እንዳያስብ፣ አስቦም እንዳይዘጋጅ ድነሃል፤ ዋጋ ተከፍሎልሃል፤ ፍርድ የለብህም እያለ ኀጢአትን የሚያደፋፍር የንስሓን ዋጋ ያቃለለ፣ ክፉ ትምህርት ምድሪቱን ሞልቷታል፡፡
 
እንደ ሀገርና እንደ ቤተ ክርስቲያንም ችግሩ ሰፊ ነው፡፡ በእነዚህ ሐሰተኛ ነቢያት ትንቢት ልምምድ ውስጥ እንድንኖር አድርጎናል፡፡ ሰላም ሳይሆን ሰላም ነው እንላለን፡፡ ተወዳጆች ሆይ!  እያንዳንዱን ዝርዝር ጉዳይ ማንሳት ጊዜ ይገድበናል፡፡ በተጨማሪም በትንቢት ስም፣ በራእይ ስም ትውልዱ ተዘክሮተ ሞትን እንዴት እንደዘነጋ ለብዙዎቻችን የተሰወረ አይደለምና፡፡
 
ቤተ ክርስቲያናችን ግን አስቀድማ ታስጠነቅቀናለች፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት እንደሚነሡ፣ ብዙዎችንም እንደሚያስቱ ከአምላኳ የተነገራትን የወንጌል ቃል ነግራናለች፡፡ የሐሰተኞች ነቢያትን ሥራ የሚሠሩ አሁን በቤተ ክርስቲያናችንም ውስጥ አሉ፡፡ ብዙዎችንም ከእውነት ፈቀቅ እንዲሉ ከወንጌል ቃል ይልቅ አጋንንታዊ ትምህርታቸውን እንዲሰሙ፣ ከጌታ ይልቅ እነርሱን እንዲከተሉ ያደረጉ፣ ከእውነተኛው አምልኮ ወደ አጋንንታዊ አምልኮ የወሰዱ፣ ባሕታዊ ነኝ፤ አጥማቂ ነኝ፤ መምህር ነኝ፤ አዋቂ ነኝ የሚሉ ብዙ ክፉና ሐሰተኞች በመካከላችን አሉና እንጠንቀቅ፡፡
 
በመጨረሻም እግዚአብሔር በነቢዩ ኤርምያስ አድሮ ‹‹የሐሰት ነቢያቶቻችሁንና ሟርተኞቻችሁን፣ ሕልም አላሚዎቻችሁንና ባለ ራእዮቻችሁን መተተኞቻችሁንም አትስሙ፤ ከምድራችሁ እንዳያርቋችሁ፤ እኔም እንዳላሳድዳችሁ እናንተም እንዳትጠፉ›› ሲል ባስጠነቀቀን ቃል እንጨርስ፡፡ (ኤር.፳፯፥፱)
 
ከምድራችን፣ ከርስታችን ከቤተ እግዚአብሔር እንድም ከሰማያዊቷ ርስታችን እንዳያርቁን፣ እርሱም እንዳያሳድደን፣ እኛም እንዳንጠፋ ከሐሰተኞች ነቢያት እንጠበቅ፡፡ እርሱም ይጠብቀን፤ አሜን!!!
#የጥያቄ_እና_መልስ_ምሽት

ውድ ተከታታዮቻችን ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ ዕሮብ ዕሮብ በግሩፓችን (የተዋህዶ ልጆች) ላይ የጥያቄ እና መልስ ምሽት ሁኗል።ስለዚህም እናንተም ግሩፕ ውስጥ በመቀላቀል መንፈሳዊ እውቀቶን ይመዝኑ።ሌሎች ወንድምና እህቶቻችሁን በመጋበዝ ፤ በመጠየቅና በመረዳዳት ይቀጥሉ።

ጥያቄ እና መልሱ ሁሌ ዕሮብ2:30 ጀምሮ እስከ 4:00 ድረስ ይሆናል።

ግሩፑ ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ይጠቀሙ የተዋህዶ ልጆች
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመውን ግድያ አወገዘ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ንጹሐን አማኞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በእጅጉ ያወግዛል

“በንጹሐን ላይ የሚፈጸም ግድያ፣ ኢሰብአዊ ድርጊትና አያያዝ በሁሉም ሃይማኖቶች የሚወገዝ ወንጀል ነው”

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ንፁሐን አማኞች ላይ ግድያ መፈጸሙን የሚገልጽ ከሁለቱ አባል ቤተ እምነቶች ካወጡት መግለጫ ተገንዝበናል፡፡ ድርጊቱ በእጅጉ የሚያሳዝን ከመሆኑም በላይ በሃይማኖት አገልግሎት ላይ የነበሩ ንፁሐን አማኞችን መግደል ደረቅ የወንጀል ተግባር በመሆኑ በእጅጉ የሚወገዝ ድርጊት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን “በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ላይ በኦርቶዶክሳዊያን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በእጅጉ እናወግዛለን፣ የፀጥታ ተቋማትም ጥቃቱን እንዲከላከሉ እንጠይቃለን፡፡” የሚል መግለጫ በቤተ ክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የፌስቡክ ገጽ ያወጣች ሲሆን በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ ሶቤ ሚካኤል፣ በዲገሎ ማርያም፣ በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት 36 ኦርቶዶክሳውያን በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ከሀገረ ስብከቱ የደረሰውን መረጃ ዋቢ በማድረግ መምሪያው ገልጿል፡፡ በተጨማሪም የአማኖች ቤትም ስለመቃጠሉ ዘገባው ይጠቁማል፡፡
2024/09/30 22:18:03
Back to Top
HTML Embed Code: