Telegram Web Link
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

#ጥቅምት_22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ

ቅዱስ ሉቃስ :-
- ሐዋርያ ነው
- ወንጌላዊ ነው
- ሰማዕት ነው
- ዓቃቤ ሥራይ (ዶክተር) ነው
- የጥበብ ሰው (ሰዓሊ) ነው

ዘጋቢ (የሐዋርያትን ዜና ሕይወት የጻፈ) ነው:: ይሕስ እንደምን ነው ቢሉ:-

በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን መነሻ አካባቢ: በተወደደች የጌታ ዓመት ከእሥራኤላውያን ወገኖቹ ቅዱስ ሉቃስ ተወልዷል:: ያደገውም መቄዶንያ አካባቢ ነው:: ጌታችን ተጠምቆ ማስተማር ሲጀምር ከተከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ መካከል 120ውን ለቤተሰብነት መምረጡ ይታወቃል::

ታዲያ እንዲጠቅም አውቆ ቅዱስ ሉቃስን ከ72ቱ አርድእት ደምሮታል:: ቅዱስ ሉቃስ ጌታን ከተከተለ በኋላ ለ3 ዓመት ከ3 ወር: ከዋለበት እየዋለ: ካደረበትም እያደረ የቃሉን ትምሕርት: የእጆቹን ተአምራት በጥሞና ይከታተል ነበር::

ጌታችን ለዓለም ድኅነት ተሰቅሎ: ሙቶ: ከተነሳ በኋላ ስለዚህ ቅዱስ የሚናገር አንድ የወንጌል ክፍል እናገኛለን:: በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ላይ ከምናያቸው የኤማሁስ መንገደኞች አንዱ ይህ ቅዱስ እንደ ሆነ አባቶች አስተምረውናል::

በእርግጥ 'ቀለዮዻ' የሚለው ስም በዘመኑ የብዙዎች መጠሪያ ቢሆንም እርሱም ጌታን ከመከተሉ በፊት በዚህ ስም ይጠራ እንደ ነበር ይታመናል:: በወቅቱ ታዲያ 2ቱ ደቀ መዛሙርት (ሉቃስና ኒቆዲሞስ) ወደ ኤማሁስ ሲሔዱ ጌታ መንገድ ላይ ተገልጦ እያጫወታቸው አብሮ ተጉዟል::

እነርሱም ማንነቱን አላወቁምና ስለ ራሱ ለራሱ እየሰበኩለት ተጉዘዋል:: ከሐዘናቸው ብዛት ማስተዋል ተስኗቸው: ቀቢጸ ተስፋም ወሯቸው ነበርና መድኃኒታችን ክርስቶስ የነቢያትን ትንቢት ተረጐመላቸው::

በዚህ ጊዜም ከነገሩ ማማር: ከምሥጢሩ መሥመር ጋር እየገረማቸው ልቦናቸው ይቃጠል (ይቀልጥባቸው) ነበር:: "አኮኑ ይነድደነ ልበነ" እንዲል:: ወደ ኤማሁስ ሲደርሱ ግን ደጐች ናቸውና "በቤት ካላደርክ: ራት ካልበላህ" ብለው ግድ አሉት::

በማዕድ ሰዓት ግን ቡራኬውን ሰጥቷቸው: ቸር አምላክነቱን ገልጦላቸው ተሰወራቸው:: እነርሱም በሐሴት ከኤማሁት ተመልሰው እየሮጡ ኢየሩሳሌም ደርሰው ትንሳኤውን ሰበኩ::

የመንገዱ ርዝመትም አልታወቃቸውም ነበር:: ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሉቃስ እንደ ሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምሮ: መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::

ቅዱሱ ዶክተር

በትውፊት ትምሕርት እንደ ተማርነው ቅዱስ ሉቃስ ጌታን ከመከተሉ በፊት ሥራው ሐኪምነት (ዶክተር) ነበር:: በዚህም አበው "አቃቤ ሥራይ / ባለ መድኃኒት" ይሉታል:: በተሰጠው ሙያም ብዙዎችን አገልግሏል::

የጌታ ደቀ መዝሙር ከሆነ በኋላ ደግሞ "አቃቤ ሥራይ ዘነፍስ-የነፍስ ሐኪም" ተብሏል:: እንዲያውም አባቶቻችን ሐዋርያትን ያክማቸው ነበር ይባላል:: ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋርያት አብዛኞቹ በሽተኞች ነበርና ነው:: ከደግነታቸው የተነሳም እልፍ አእላፍ ድውያንን በተአምራት ሲፈውሱ እነርሱ ግን በስቃይ ይኖሩ ነበር::

ሕመማቸው ሲጠናባቸው ግን ቅዱሱ ዶክተር ሉቃስ ይራዳቸው ነበር:: ይሕንንም ቅዱስ ዻውሎስ በቆላስይስ መልእክቱ ላይ "የተወደደው ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ: ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላቹሃል" ሲል ገልጾታል:: (ቆላ. 4:14)

ዘጋቢው ሐዋርያ

ቅዱስ ሉቃስ እንደ ዛሬው ነገሮች ምቹ ባልነበሩበት ዘመን እጅግ አድካሚ የሆነ ጉዞ አድርጐ የሐዋርያትን ዜና ሕይወት ዘግቦልናል:: ልክ ወንጌሉን ለታኦፊላ (ቴዎፍሎስ) ደቀ መዝሙሩ እንደ ጻፈለት ግብረ ሐዋርያትንም ለእርሱ በትረካ መልክ አቅርቦለታል::

ሲጽፍለትም "ሰማሁ" እያለ ሳይሆን: አብሮ እያለ ያየውንና የተሳተፈበትን ነው:: አተራረኩም በአንደኛና በ3ኛ መደብ አድርጐ እያቀያየረ ነው:: ማለትም አንዳንዴ "እኛ" እያለ ሌላ ጊዜ ደግሞ "እነርሱ" እያለ ነበር የሚተርክለት::

መጽሐፉም 28 ምዕራፎች ሲኖሩት በጌታ ዕርገት ጀምሮ በኢየሩሳሌምና በአሕዛብ የነበረውን ስብከተ ወንጌል ገልጦ: የቅዱስ ዻውሎስን ጉዞዎች በሰፊው ዳስሶ ይጠናቀቃል::

ወንጌላዊው ሐዋርያ

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን እንዲጽፉ ከተመረጡ (ከተፈቀደላቸው) ሐዋርያት አንዱ ነው:: በቤተ ክርስቲያንም "ዘላሕም" እየተባለ ይጠራል:: ለዚህም ምክንያቱ:-

1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በበረት: በላምና በአህያ መካከል መወለዱን በመጻፉ
2.ጌታችንን "መግዝአ ላሕም-የሚታረድ ሜልገች (ላም)" ብሎ በመግለጹ እና
3.ከ4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል) አንዱ (ገጸ ላሕም) ይራዳው: ይጠብቀውም ስለ ነበር ነው::

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈው ጌታ ባረገ በ22ኛው ዓመት ሲሆን ይኼውም በ56 ዓ/ም አካባቢ ማለት ነው:: ሲጽፍም ብቻውን አልነበረም:: ልክ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን የጻፈው ከሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ጋር እንደ ሆነው ሁሉ: ቅዱስ ሉቃስም የጻፈው ከብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ጋር ነው:: ምክንያቱም ለረዥም ዓመታት አብረው ለስብከተ ወንጌል ተጉዘዋልና::

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን ሲጽፍ በነ ዘካርያስ ቤተሰብ ጀምሮ: ብሥራተ ገብርኤልን: ክብረ ድንግል ማርያምን: የጌታን ልደት: እድገት: መጠመቅ: ማስተማር: መሰቀል: መሞት: መነሳትና ማረግ በቅደም ተከተል ይተርክልናል::

ጥበበኛው (ሰዓሊው) ሐዋርያ

ቅዱስ ሉቃስን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች ሌላኛው ደግሞ ጐበዝ ሰዓሊ የነበረ መሆኑ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም የመጀመሪያውን የእመቤታችንን ስዕል (ምስለ ፍቁር ወልዳን) የሳለው እሱ ነው::

አንድ ቀን የአምላክ እናት ባለችበት ከጌታ አስፈቅዶ የሳላት ስዕለ አድኅኖ ሥጋን የለበሰች: ከፊቷ ወዝ የሚወጣ: የምታለቅስ: ስትወጋ የምትደማና ድውያንን የምትፈውስ ሆና ተገኝታለች:: ይህች ስዕል ዛሬ ሃገራችን ኢትዮዽያ ውስጥ አለች ይባላል።

ሰማዕቱ ሐዋርያ

ቅዱስ ሉቃስ እንዲህ ባለ ሕይወት ሲመላለስ በትጋት (ያለ ዕረፍት) ወንጌልን እየሰበከ ነበር:: በ66 እና በ67 ዓ/ም ብርሃናተ ዓለም ዼጥሮስ ወዻውሎስ በኔሮን ቄሣር እጅ ሲገደሉ የሮም ግዛት ክርስቲያኖች ኃላፊነት በእርሱ ላይ ነበረ::

ከወንጌሉና ግብረ ሐዋርያቱ ባለፈ በመልእክታት: አንድም እየዞረ ክርስቲያኖችን አጸና: አሕዛብንም አሳመነ:: ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ዝናውን የሰማው ኔሮን ሊገድለው ፈለገ:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ ሉቃስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሲላስ የሚባለውን ሽማግሌ መርጦ መጽሐፎቹን ሁሉ አስረከበው::

በድፍረትም ወደ ኔሮን ቄሣር ቀርቦ ተናገረው:: ንጉሡም "ክርስቶስን አምልኩ የምትል ቀኝ እጅህ መቆረጥ አለባት" ብሎ እጁን ከትክሻው በሰይፍ ለይቶ መሬት ላይ ጣለው:: ሁሉ ሰው ሲደነግጥ ቅዱሱ ተጐንብሶ የወደቀች እጁን አነሳትና እንደ ነበረችው አደረጋት::

በዚያ የነበሩ አሕዛብም "ግሩም" አሉ:: መልሶ ግን "አሁን እጄ ሥራዋን ስለ ጨረሰች አልፈልጋትም" ብሎ እንደ ገና ለይቶ ጣላት::

"ከመ ያርኢ ኃይለ ቅድመ ኔሮን ወተዓይኑ:
አስተላጸቃ ወሌለያ ለምትርት የማኑ:
እስመ ላዕሌሁ ተሰውጠ ለክርስቶስ ስልጣኑ::" እንዲል::


የቴሌግራም ገፃችን - https://www.tg-me.com/betel_et
የፌስቡክ ገጻችን - https://www.facebook.com/profile.php?id=61552723809417
እንኳን ለጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት አባ ዮሴፍ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት አባ ዮሴፍ

በእስክንድርያ (ግብጽ) ሊቀ ዽዽስናን ከተሾሙና በጐ ሥራን ከሠሩ አበው አንዱ አባ ዮሴፍ ነው:: እርሱ ለግብጽ 52ኛ ፓትርያርክ ነውና በ9ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ እንደ ነበር ይታመናል::
ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በግብጽ የሚኖሩ የዘመኑ ክርስቲያን ባልና ሚስት ወደ ፈጣሪ ለምነው ልጅ ሲወልዱ 'ዮሴፍ' አሉት:: እጅግ ሃብታሞች ቢሆኑም እርሱ ገና ልጅ እያለ ሁለቱም ዐረፉ:: ሕጻኑ ዮሴፍም ዕጓለ ሙታን (ወላጅ አልባ) ሆነ:: ሕጻኑ ሲያለቅስ የተመለከተ አንድ ደግ ጐረቤቱ ግን ወደ ቤቱ ወሰደው::

እንደ ልጁ ተንከባክቦ: ክርስትናንም አስተምሮ አሳደገው:: እድሜው 20 ሲደርስም "የወላጆችህን ንብረት ንሳ" ብሎ አወረሰው:: ወጣቱ ዮሴፍ ግን "አኮኑ ዝንቱ ኩሉ ኃላፊ-ይህ ሁሉ ሃብት ጠፊ አይደለምን" ብሎ ናቀው::

ለነዳያንም በትኖት እያመሰገነ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገሰገሰ:: በዚያም የአሞክሮ ጊዜውን ፈጽሞ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበለ:: ለዓመታትም በዲቁና ገዳሙን እያገለገለ: እየተጋደለ ኖረ::

የአባ ዮሴፍን ደግነት የሰማው የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ማርቆስም ከገዳም አውጥቶ በመንበረ ዽዽስናው እንዲራዳውና ሕዝቡን እንዲያስተምርለት ወደ ከተማ አመጣው::

ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን አባ ዮሴፍ ወደ ፓትርያርኩ አባ ማርቆስ ቀርቦ "አባቴ! ወደ ገዳሜ አሰናብተኝ:: ለመነኮስ በከተማ መኖር ፍትሕ አይደለምና" ሲል ተማጸነው:: ፓትርያርኩም "እሺ" ብሎ ቅስናን ሹሞ አሰናበተው::

ወደ ገዳመ አስቄጥስ ከተመለሰ ጀምሮ አባ ዮሴፍ በዓት ለየ:: እስከ 59 ዓመቱም ድረስ በጾምና በጸሎት በበዓቱ ጸንቶ ኖረ:: በአጠቃላይ በገዳም የኖረባቸው ዓመታትም 39 ደረሱ::

በዚህ ጊዜ ግን የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ስምዖን (ከአባ ማርቆስ በኋላ 3 ፓትርያርኮች ዐርፈዋል) በማረፉ ግብጽ እረኛን ስትፈልግ ነበር:: 'ማንን እንሹም' እያሉ ሲጨነቁ አንድ ሰው ጉቦ ሰጥቶ ሊሾም መሆኑን አበው ሰሙ:: ይህ ሰው ደግሞ ጭራሹኑ ልጅ ያለው ነው::

አባቶች ተሯሩጠው ያ ጉቦኛ ባለ ሚስት እንዳይሾም አደረጉ:: ቀጥለው ማንን እንደ ሚሾሙ ሲጨነቁ የሁሉም ሕሊና ስለ አንድ ሰው (አባ ዮሴፍ) ያስብ ነበር:: ሁሉም ተሰብሳቢዎች ስለ ነገሩ ተጨዋውተው አባ ዮሴፍን ይሾሙ ዘንድ ቆረጡ::

ተሰብስበው በመንገድ ላይ ሳሉም እንዲህ ተባባሉ:: "ወደ በዓቱ ስንደርስ ቤቱ ክፍት ከቆየን ፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ዝግ ከሆነ ግን ፈጣሪ አልፈቀደም ማለት ነው" ሲሉ ተስማሙ:: ምክንያቱም የአበው በዓት ቶሎ ቶሎ አይከፈትምና::

ነገሩ ጥበበ እግዚአብሔር ነበረበትና ልክ ሲደርሱ እንግዳ ሊሸኝ በዓቱን ከፍቶ አገኙት:: እንዳያመልጣቸው ተረባርበው ያዙት:: ግጥም አድርገው አሥረው "አክዮስ-ይደልዎ-ይገባዋል" እያሉ ሥርዓተ ሲመት አደረሱለት:: እርሱ (አባ ዮሴፍ) ግን "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ: አይገባኝም: ልቀቁኝ" እያለ ይጮህ ነበረ::

አበው ግን ሥርዓተ ሢመቱን ፈጽመው ወስደው በመንበረ ዽዽስና: በቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ዙፋን ላይ አስቀመጡት:: በቁጥርም 52ኛ ሁኖ ተቆጠረ:: አምላክ ደጉን ሰው ጠቁሟቸዋልና ለቤተ ክርስቲያን ይተጋ ጀመር::

ሕዝቡን እያስተማረ: አብያተ ክርስቲያናትን እያነጸ: መጻሕፍትን እየተረጐመ: ተአምራትን እየሠራ: በመንኖ ጥሪት ለ19 ዓመታት አገልግሏል:: ወቅቱም ተንባላት (አማሌቃውያን) በምድረ ግብጽ የሰለጠኑበት ነበርና ብዙ ችግሮችን አሳልፏል::

የግብጹ ሱልጣንም ሊገድለው 2 ጊዜ ሞክሮ አልተሳካለትም:: 2 ጊዜም ለአባ ዮሴፍ የሰነዘረው ሰይፍ በመልአክ እየተመለሰ ተመልክቶ ትቶታል:: አባ ዮሴፍ በዘመኑ ተሰዶ የነበረውን የኢትዮዽያ ዻዻስ አባ ዮሐንስንም ከተሰደደበት ወደ ሃገራችን
እንደ መለሰው በዜና ሕይወቱ ተጽፏል:: አባ ዮሴፍ እንዲህ ተመላልሶ በ78 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል::

ቸር አምላክ በጻድቁ ሊቀ ዻዻሳት ጸሎት ይማረን::

ከበረከቱም ይክፈለን::

#በጥቅምት_23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.አባ ዮሴፍ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት
2.ቅዱስ ዲዮናስዮስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ኢላርዮስ
4.ቅድስት እለእስክንድርያ ሰማዕት

በጥቅምት 23 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል
 

"ኤዺስ ቆዾስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና:: የማይኮራ: የማይቆጣ: የማይሰክር: የማይጨቃጨቅ: ነውረኛ ረብ የማይወድ: ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ: በጐ የሆነውን ነገር የሚወድ: ጠንቃቃ: ጻድቅ: ቅዱስ: ራሱን የሚገዛ ይሁን::"
(ቲቶ. ፩፥፯)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የቴሌግራም ገፃችን - https://www.tg-me.com/betel_et
የፌስቡክ ገጻችን - https://www.facebook.com/profile.php?id=61552723809417
እንኳን ለጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት አባ ዮሴፍ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት አባ ዮሴፍ

በእስክንድርያ (ግብጽ) ሊቀ ዽዽስናን ከተሾሙና በጐ ሥራን ከሠሩ አበው አንዱ አባ ዮሴፍ ነው:: እርሱ ለግብጽ 52ኛ ፓትርያርክ ነውና በ9ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ እንደ ነበር ይታመናል::
ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በግብጽ የሚኖሩ የዘመኑ ክርስቲያን ባልና ሚስት ወደ ፈጣሪ ለምነው ልጅ ሲወልዱ 'ዮሴፍ' አሉት:: እጅግ ሃብታሞች ቢሆኑም እርሱ ገና ልጅ እያለ ሁለቱም ዐረፉ:: ሕጻኑ ዮሴፍም ዕጓለ ሙታን (ወላጅ አልባ) ሆነ:: ሕጻኑ ሲያለቅስ የተመለከተ አንድ ደግ ጐረቤቱ ግን ወደ ቤቱ ወሰደው::

እንደ ልጁ ተንከባክቦ: ክርስትናንም አስተምሮ አሳደገው:: እድሜው 20 ሲደርስም "የወላጆችህን ንብረት ንሳ" ብሎ አወረሰው:: ወጣቱ ዮሴፍ ግን "አኮኑ ዝንቱ ኩሉ ኃላፊ-ይህ ሁሉ ሃብት ጠፊ አይደለምን" ብሎ ናቀው::

ለነዳያንም በትኖት እያመሰገነ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገሰገሰ:: በዚያም የአሞክሮ ጊዜውን ፈጽሞ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበለ:: ለዓመታትም በዲቁና ገዳሙን እያገለገለ: እየተጋደለ ኖረ::

የአባ ዮሴፍን ደግነት የሰማው የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ማርቆስም ከገዳም አውጥቶ በመንበረ ዽዽስናው እንዲራዳውና ሕዝቡን እንዲያስተምርለት ወደ ከተማ አመጣው::

ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን አባ ዮሴፍ ወደ ፓትርያርኩ አባ ማርቆስ ቀርቦ "አባቴ! ወደ ገዳሜ አሰናብተኝ:: ለመነኮስ በከተማ መኖር ፍትሕ አይደለምና" ሲል ተማጸነው:: ፓትርያርኩም "እሺ" ብሎ ቅስናን ሹሞ አሰናበተው::

ወደ ገዳመ አስቄጥስ ከተመለሰ ጀምሮ አባ ዮሴፍ በዓት ለየ:: እስከ 59 ዓመቱም ድረስ በጾምና በጸሎት በበዓቱ ጸንቶ ኖረ:: በአጠቃላይ በገዳም የኖረባቸው ዓመታትም 39 ደረሱ::

በዚህ ጊዜ ግን የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ስምዖን (ከአባ ማርቆስ በኋላ 3 ፓትርያርኮች ዐርፈዋል) በማረፉ ግብጽ እረኛን ስትፈልግ ነበር:: 'ማንን እንሹም' እያሉ ሲጨነቁ አንድ ሰው ጉቦ ሰጥቶ ሊሾም መሆኑን አበው ሰሙ:: ይህ ሰው ደግሞ ጭራሹኑ ልጅ ያለው ነው::

አባቶች ተሯሩጠው ያ ጉቦኛ ባለ ሚስት እንዳይሾም አደረጉ:: ቀጥለው ማንን እንደ ሚሾሙ ሲጨነቁ የሁሉም ሕሊና ስለ አንድ ሰው (አባ ዮሴፍ) ያስብ ነበር:: ሁሉም ተሰብሳቢዎች ስለ ነገሩ ተጨዋውተው አባ ዮሴፍን ይሾሙ ዘንድ ቆረጡ::

ተሰብስበው በመንገድ ላይ ሳሉም እንዲህ ተባባሉ:: "ወደ በዓቱ ስንደርስ ቤቱ ክፍት ከቆየን ፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ዝግ ከሆነ ግን ፈጣሪ አልፈቀደም ማለት ነው" ሲሉ ተስማሙ:: ምክንያቱም የአበው በዓት ቶሎ ቶሎ አይከፈትምና::

ነገሩ ጥበበ እግዚአብሔር ነበረበትና ልክ ሲደርሱ እንግዳ ሊሸኝ በዓቱን ከፍቶ አገኙት:: እንዳያመልጣቸው ተረባርበው ያዙት:: ግጥም አድርገው አሥረው "አክዮስ-ይደልዎ-ይገባዋል" እያሉ ሥርዓተ ሲመት አደረሱለት:: እርሱ (አባ ዮሴፍ) ግን "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ: አይገባኝም: ልቀቁኝ" እያለ ይጮህ ነበረ::

አበው ግን ሥርዓተ ሢመቱን ፈጽመው ወስደው በመንበረ ዽዽስና: በቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ዙፋን ላይ አስቀመጡት:: በቁጥርም 52ኛ ሁኖ ተቆጠረ:: አምላክ ደጉን ሰው ጠቁሟቸዋልና ለቤተ ክርስቲያን ይተጋ ጀመር::

ሕዝቡን እያስተማረ: አብያተ ክርስቲያናትን እያነጸ: መጻሕፍትን እየተረጐመ: ተአምራትን እየሠራ: በመንኖ ጥሪት ለ19 ዓመታት አገልግሏል:: ወቅቱም ተንባላት (አማሌቃውያን) በምድረ ግብጽ የሰለጠኑበት ነበርና ብዙ ችግሮችን አሳልፏል::

የግብጹ ሱልጣንም ሊገድለው 2 ጊዜ ሞክሮ አልተሳካለትም:: 2 ጊዜም ለአባ ዮሴፍ የሰነዘረው ሰይፍ በመልአክ እየተመለሰ ተመልክቶ ትቶታል:: አባ ዮሴፍ በዘመኑ ተሰዶ የነበረውን የኢትዮዽያ ዻዻስ አባ ዮሐንስንም ከተሰደደበት ወደ ሃገራችን
እንደ መለሰው በዜና ሕይወቱ ተጽፏል:: አባ ዮሴፍ እንዲህ ተመላልሶ በ78 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል::

ቸር አምላክ በጻድቁ ሊቀ ዻዻሳት ጸሎት ይማረን::

ከበረከቱም ይክፈለን::

#በጥቅምት_23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.አባ ዮሴፍ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት
2.ቅዱስ ዲዮናስዮስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ኢላርዮስ
4.ቅድስት እለእስክንድርያ ሰማዕት

በጥቅምት 23 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል
 

"ኤዺስ ቆዾስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና:: የማይኮራ: የማይቆጣ: የማይሰክር: የማይጨቃጨቅ: ነውረኛ ረብ የማይወድ: ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ: በጐ የሆነውን ነገር የሚወድ: ጠንቃቃ: ጻድቅ: ቅዱስ: ራሱን የሚገዛ ይሁን::"
(ቲቶ. ፩፥፯)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የቴሌግራም ገፃችን - https://www.tg-me.com/betel_et
የፌስቡክ ገጻችን - https://www.facebook.com/profile.php?id=61552723809417
በድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችችን ለመርዳት #የወገን ፈንድ አማራጭንም ይጠቀሙ!!
+++
በሀገራችን እያጋጠሙ ባሉት ማኅበራዊ ውሶች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወገኖች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ የሚፈልጉ ሆነዋል። በተለይ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተከሰተው ድርቅ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ፣ ጠለምት፣ በየዳና ጃና አሞራ፣ እንዲሁም በዋግኸምራ ዞን ሰሃላና አካባቢው የሚገኙ ወገኖቻችን ለጽኑ ማኅበራዊ ችግር ተጋልጠዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን በእነዚህ አካባቢዎች የነፍስ አድን ሥራዎችን ለማከናወን የተለመደ ድጋፋችሁን በማድረግ ሰብአዊና ማኅበራዊ ኃላፊነትዎ ይወጡ ሲል ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግም፡-
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
3. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
4. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
5. በአዋሽ ባንክ - 01329817420400 መጠቀም የምትሉ መሆኑን እንገልጻለን። በወገን ፈንድ ፡- https://www.wegenfund.com/causes/nu-badereqe-yatagodu-waganocaacenene-hheyete-eneta/
ለበለጠ መረጃ
• 09 43 00 04 03
• 09 1 1 38 27 53
‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› (መሓ.፯፥፩)

ክፍል አራት

ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ከዚህ በፊት የእመቤታችንን የስደቷን ነገር አንሥተን ‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› በሚል ርእስ ከክፍል አንድ እስከ ሦስት አድርሰናችሁ ነበር፡፡ ጥሩ ትምህርት እንዳገኛችሁበት ተስፋ እናደርጋለን፡፡

የዛሬው ትኩረታችን ያን ሁሉ መከራ የተቀበለችበት የስደቷን ምክንያትና ዓላማ መዳሰስ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ግን ስለ ግብጻዊው ወንበዴ ማለትም በጌታ ቀኝና በግራ ስለተሰቀለው ፈያታዊ ዘየማን ትንሽ ታሪክ እንጨምርና ወደ ዋናው ሐሳባችን እንገባለን፡፡

ጥጦስና ዳክርስ የተባሉት ሁለት ወንበዴዎች እመቤታችንን በመንገድ አግኝተው እንደዘረፏት፣ በኋላ ጥጦስ አዝኖላት ንብረታቸውን እንደመለሰና ጌታን አቅፎ እንደሸኘ በክፍል ሦስት ቀንጨብ አድርገን አቅረበንላችሁ ነበር፡፡ ይህ ፈያታዊ ዘየማን ጥጦስ ጌታን አቅፎት ሲሸኛቸው ሳለ ሰይፉ ከእጁ ወድቃ ተሰበረችበትና በጣም አዘነ፡፡ ጌታም ‹‹ኦ ጥጦስ አስተጋብእ ስባራተ ሰይፍከ፤ ጥጦስ ሆይ፥ የሰይፍህን ስባሪ ወደ ሰገባው ክተተው›› አለው፡፡ ሰብስቦ ቢያቀርብለት እንደ ነበረ አድርጎ ሰጠው፡፡ ጥጦስም ደስ ብሎት ‹‹ዝንቱ ሕፃን እምደቂቀ ነቢያት፤ ይህ ሕፃን ከነቢያት ልጆች አንዱ ነው›› አለ፤ ዳክርስ ግን ‹‹እውነትም ከነቢያት ወገን ቢሆን አይደል አንተን ቀማኛውን ገነት ትገባለህ ማለቱ!›› ብሎ ዘበተበት፡፡
የዳክርስ ክፋቱ እስከ መስቀልም አብሮት ዘልቆ በግራው በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ስትጨልም፣ ጨረቃ ደም ስትለብስ፣ ከዋክብት ሲረግፉ፣ መቃብራት ሲከፈቱ፣ ሙታን ሲነሡ፣ ተአምራቱን አይቶ እንኳን አላመነም፡፡ ይልቁንም ‹‹አንተስ ክርስቶስ አይደለህምን ራስህንም አድን፤ እኛንም አድን›› እያለ ይሰድበው ነበር፡፡ (ሉቃ.፳፫፥፴፱) የጥጦስ ግን ወሮታው እንዳይቀርበት ጌታን የታቀፈበትን ልብሱን ቢያጥበው ከወዙ ፫፻ ወቄት የሚያወጣ ሽቱ አግኝቷል፡፡ ጌታን ማርያም እንተ ዕፍረት በ፫፻ ወቄት ገዝታ የቀባችውና ይሁዳ ‹‹ይህስ ተሸጦ ለድሆች ይሆን ነበር›› ብሎ ያንገራጎረበት ሽቱ ይህ ነው፡፡ (ዮሐ.፲፪፥፫ እና ማቴ.፳፮፥፮)
ምክንያተ ስደት፡- በቤተ ልሔም ሲወለድ አጋንንትን በእሳት ፍላጻ የነደፋቸውን፣ አሳዳጆቹን እንደ ፈርዖንና ሠራዊቱ የውኃ ሽታ ሊያድረጋቸው የሚቻለውን፥ ሁሉ በእጁ የሆነ ልጇን ይዛ ስለምን እመቤታችን በረሃ ለበረሃ ተንከራተተች? ግብጽስ ለምን ለስደቷ ተመረጠች?

‹‹እንዘ ኪሩቤል አፍራሲሁ ወሱራፌል ላእካኒሁ ወክነፈ ነፋስ ሠረገላሁ፤ ኪሩቤል ፈረሶቹ ሱራፌልም መልእክተኞቹ የነፋሳት ክንፎቹም ሰረገላዎቹ›› የተባለለት ጌታስ ስለምን ከናዝሬት እስከ ቁስቋም ተራራ በእግሮቹ ሄደ? (መጽሐፈ ሰዓታት)
ሀ. አንዱና ዋናው ስለምን ተሰደደ ቢሉ የቤዛነት ሥራውን የሚፈጽመው ገና በቀራንዮ ነውና ጊዜው ሳይደርስ እንዳይሞት ወደ ግብጽ ነው፡፡

ለ. ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡
ትንቢቱ፡- በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹ወይወርድ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብጽ ተጽዒኖ ዲበ ደመና ቀሊል፤ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል›› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ሊፈጸም ነው፡፡ (ኢሳ.፲፱፥፩) ‹‹እምግብጽ ጸዋእክዎ ለወልድየ፤ ልጄን ከግብጽ ጠራሁት›› የሚልም አለና ‹‹ትንቢት ይቀድሞ ለነገር›› እንዲሉ አስቀድሞ ይህ ትንቢት ተነግሮ ስለነበር፣ ትንቢትን የሚያናግር ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ በመንፈስ ቅዱስ አናጋሪነት የተነገረ ትንቢት ሳይፈጸም አይቀርም፤ ጌታ ደመና ቀሊል በተባለች ድንግል ማርያም ጀርባ ታዝሎ ወደ ምድረ ግብጽ ወረደ፡፡ ደመና ያላት እመቤታችንን ነው፡፡ ዝናመ ሕይወት ክርስቶስን ያዘለች እውነተኛ ደመና እርሷ ናትና፡፡ ‹‹አንቲ ዘበአማን ደመና እንተ ለነ ማየ ዝናም፤ የዝናም ውኃ የታየብሽ እውነተኛ ደመና አንቺ ነሽ›› እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም፡፡

ምሳሌው፡- ዮሴፍን ወንድሞቹ ‹‹ሊሾምብን ሊገዛን ነው›› ብለው በክፋት ተነሥተውበት ሸጠውት ወደ ግብጽ ወርዶ ነበር፡፡ (ዘፍ.፴፯፥፩-፳፰) ጌታም ‹‹ሊሾምብን ሊነግሥብን ነው›› የሚሉ አጋንንትና ሄሮድስ በክፋት ተነሥተው አሳድደውት ወደ ግብጽ ወርዷልና ነው፡፡

ሐ. ክህደት በግብጽ ጸንቶ ነበርና ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡
ክህደት ወደ ጸናበት መሄድ ልማድ ነውና፡፡ በግብጽ አምልኮ ጣዖት የተስፋፋበት ነበር፡፡ ክህደትም በሰው ልቡና የጸናበት እንደነበረ አጋንንንትም በሰው ልቡና ሠልጥነው እንደነበር እና ቁራሽ ኀብስት፣ ጽዋዕ መጠጥ ከልክለዋት እመቤታችን እንዴት እንዳዘነች ቀድመን አይተናል፡፡

መለኮት ዕጓላ ሶበ ጸምዐ ከመ ደቂቅ-------ዘይሰፍሮ በኅፍኑ ለማየ ባሕር ዕሙቅ
በከየት ወትቤ ማርያም ማዕነቅ------------አልቦ እምሰብአ ሀገር ዘየአምራ ለጽድቅ
ሶበ ሰአልክዎሙ ማየ ኢወሀቡኒ በሕቅ---------ወአህጎልኩ ለወልድየ አሳዕኖ ዘወርቅ፡፡

‹‹ጥልቅ የሆነ ባሕርን በእጁ የሚሰፍረውንና የማይመረመር መለኮት የተባለ የባሕርይ አምላክ ልጇ በተጠማ ጊዜ ከዚህች ሀገር ሰዎች ቸርነትን የሚያውቃት የለም፤ ውኃን በእጅጉ ለመንኋቸው፤ አልሰጡኝም፤ የልጄን የወርቅ ጫማውን አስጠፋሁ እያለች ዋኖስ ማርያም አለቀሰች፤›› (ሰቆቃወ ድንግል) በዚህም ወደ ግብጽ በመሰደዳቸው ጣዖታትን አፈራርሷል፤ አጋንንትን ከግብጽ ከሰው ልቡና አሰድዷል፡፡ ‹‹…በዚያች ሀገር ያሉ ጣዖታትም ወድቀው ተሰባበሩ፤ አማልክቱን የሚያመልኩትም ሁሉ ፈሩ፡፡ ወደ ቤታቸውም ገብተው ተደበቁ፤ ….ብዙ ሰዎችም አመኑ፤ የሀገር ሽማግሌዎቹም ጣዖት የሚያመልኩትን ለምን ተሰወራችሁ? አማልክቶቻችሁንስ ለምን ተዋችሁ? አሏቸው፡፡ ይህች ሴት ከልጇ ጋር በገባች ጊዜ ጣዖታቱ ተሰበሩ፤ የአማልክቶቻችን ቤቶችም ወደቁ፤ ሌሊት ሠርተናቸው ሲነጋ ተሰባብረው እናገኛቸዋለን አሉ›› ትላለች እመቤታችን፡፡ (ድርሳነ ማርያም ገጽ ፪፻፰)

መ. ገዳማተ ግብጽን ለመባረክ ወደ ግብጽ ተሰደድዋል፡፡
በግብጽ ታላላቅና ደጋግ ገዳማት እነ ገዳመ ሲሐት፣ እነ ገዳመ አስቄጥስ አሉና ገዳማትን ለመባረክ ወደ ግብጽ ተሰድደዋል፡፡

ሠ. መልኩን አይተው የሚያምኑ አሉና ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡
‹‹ወተበሀላ አዋልደ ሲሐት፤ ንዑ ንርአዮ ለወልደ መንክራት፤ የሲሐት ልጅ ተባለ፤ የወልድን ተአምር ኑ እዮ›› እንዲል፤ (ትርጓሜ ማቴ.፪፥፲፭)

ረ. ሃይማኖት ከሁሉ ቢጠፋ ከግብጽ አይጠፋም ሲል ወደ ግብጽ ተሰደዋል፡፡ እስከ ዕለተ ምጽአት ወልድ ዋሕድ ስትል ትኖራለችና፡፡

ሰ. የበደለ አዳም ከገነት ተሰዶ ነበርና ያልበደለ ክርስቶስ ስለ አዳም ካሣ ሊሆን ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡

ሸ. ለሰማዕታት ስደትን ለመባረክ ተሰደደ/ተሰደደች፡፡ እመቤታችን ‹‹ሰማዕት ዘእንበለ ደም ናት፤ ሰማዕት ያለ ደም መፍሰስ›› ሰማዕትነት በእሳቱ መበላት፣ በስለቱ መወጋት ብቻ አይደለም፡፡ ስደቱ፣ ረኃቡ፣ ጥሙ፣ እርዛቱ፣ እንግልቱ ሁሉ ሰማዕትነት ነውና ለሰማዕታት ስደትን ልትባርክላቸው/ሊባርክላቸው ተሰደደች/ተሰደደ፡፡ ‹‹ወሶበ ይሰድዱክሙ እምዛቲ ሀገር ጒዩ ኀበ ካልእታ፤ …በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ ..›› እንዳለ ጌታ በወንጌል፡፡ (ማቴ.፲፥፳፫) በዚህም ብዙ ሰማዕታት ክብር አግኝተዋል፤ እመቤታችንና አብረዋት የነበሩት ዮሴፍና ሰሎሜ ሰማዕት ዘእንበለ ደም መሆናቸው ብቻ አይደለም፡፡ ሰማዕት በደም የሆነው ጊጋር መስፍነ ሶርያንም እናገኛለን፡፡

መልአከ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ‹‹እናቱንና ሕፃኑን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻዋልና›› ባለው ጊዜ በስደታቸው መጀመሪያ መሽቶባቸው ያደሩት ከጊጋር መስፍነ ሶርያ እንደ ነበር እንረዳለን፡፡ (ማቴ.፪፥፲፫) ገሥግሰው የደረሱ የሄሮድስ ሠራዊት ግን ጊጋርን በሰይፍ ቀልተው ገድለውታልና፡፡ የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው ሰማዕት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በኢትዮጵያ የቅኔ ጉባኤ ቤቶች በትልቁ ከሚተረኩ ታሪኮችና ብዙ የቅኔ ተማሪዎች ቅኔ ከሚቆጥሩበት አንዱ ጊጋር ሰማዕት ነው፡፡

የተወዳጆችሁ የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች! መቼም የስደቷን ታሪክ ተርከን አንዘልቀውምና ከዚህ በላይ ልንጓዝበት አንችልም፡፡ ይሁን እንጂ የእመቤታችንን ስደትና የኢትዮጵያን ግንኙነት ሳይዳስሱ ማለፍ አይቻልም፡፡ ቸር ብንሰነብት፣ የእመቤታችን ከስደት መመለስ ከኢትዮጵያ ጋር አገናኝተን ክፍል አምስትና የመጨረሻውን ክፍል ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡

ይቆየን!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን።

እንኩዋን ለታላቁ "ጻድቅና ሰማዕት አቡነ አቢብ" : "አባ ዕብሎይ" እና "ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)

ይህን ታላቅ ቅዱስ በምን እንመስለዋለን!

እኛ ኃጥአን ጣዕመ ዜናውን: ነገረ ሕይወቱን ሰምተን ደስ ተሰኝተናል!

ቅዱሱ አባታችን:- "ቡላ - የእግዚአብሔር አገልጋይ" ብለን እንጠራሃለን::

ዳግመኛም "አቢብ - የብዙኃን አባት" ብለን እንጠራሃለን::

እርሱ ቅሉ አባትነትህ አንተን ለመሰሉ ቅዱሳን ቢሆንም እኛን ኃጥአንን ቸል እንደማትለንም እናውቃለን::

አባ! ማነው እንዳንተ የክርስቶስን ሕማማት የተሳተፈ!


ማን ነው እንዳንተ በፈጣሪው ፍቅር ብዙ መከራዎችን የተቀበለ!

ማንስ ነው እንዳንተ በአንዲት ጉርሻ አማልዶ ርስትን የሚያወርስ
!

የፍጡራንን እንተወውና በፈጣሪ አንደበት ተመስግነሃልና ቅዱሱ አባታችን ላንተ ክብር: ምስጋናና ስግደት በጸጋ ይገባሃል እንላለን::

ልደት

አባታችን አቡነ አቢብ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ ሮሜ ናት:: ወላጆቹ ቅዱስ አብርሃምና ቅድስት ሐሪክ እጅግ ጽኑ ክርስቲያኖች ነበሩ:: ልጅ ግን አልነበራቸውም:: ዘመነ ሰማዕታት ደርሶ ስደት በሆነ ጊዜ እነርሱም በርሃ ገቡ::

በዚያም ሳሉ በቅዱስ መልአክ ብሥራት ሐሪክ ጸንሳ ብሩሕ የሆነ ልጅ ወለደች:: ቅዱሱ ሕጻን ሲጸነስ ማንም ሳይተክለው የበቀለው ዛፍ ላይ መልአኩ እንዲህ የሚል የብርሃን ጽሑፍ ጽፎበት ወላጆቹ ዐይተዋል::
"ቡላ ገብሩ ለእግዚአብሔር: ወቅዱሱ ለአምላከ ያዕቆብ: ዘየኀድር ውስተ ጽዮን"

ጥምቀት

ቅዱሱ ሕጻን ከተወለደ በሁዋላ ሳይጠመቅ ለ 1 ዓመት ቆየ::
ምክንያቱም ዘመኑ የጭንቅ ነውና ካህናትን እንኩዋን በዱር በከተማም ማግኘት አይቻልም ነበር:: እመቤታችን ግን ወደ ሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ሒዳ "አጥምቀው" አለችው::

ወደ በርሐ ወርዶ ሊያጠምቀው ሲል ሕጻኑ ተነስቶ: እጆቹንም ዘርግቶ:- "አሐዱ አብ ቅዱስ: አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የሕጻኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው:: እነርሱም ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ::

ሰማዕትነት

የቅዱሱ ቡላ ወላጆች ለ10 ዓመታት አሳድገውት ድንገት ሕዳር 7 ቀን ተከታትለው ዐረፉ:: ሕጻኑን የማሳደግ ኃላፊነትን የአካባቢው ሰዎች ሆነ:: ሕጻኑ ቡላ ምንም የ10 ዓመት ሕጻን ቢሆንም ያለ ማቁዋረጥ ሲጾም: ሲጸልይ ክፉ መኮንን "ለጣዖት ስገዱ" እያለ መጣ::

በዚህ ጊዜ በሕጻን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ የተበሳጨ መኮንኑ ስቃያትን አዘዘበት:: በጅራፍ ገረፉት: በዘንግ ደበደቡት: ቆዳውን ገፈፉት: በመጋዝ ቆራርጠውም ጣሉት:: ነገር ግን ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና 2 ጊዜ ከሞት ተነሳ:: በመጨረሻ ግን ሚያዝያ 18 ቀን ተከልሎ ሰማዕት ሆኗል::

ገዳማዊ ሕይወት

ቅዱስ ቡላ ሰማዕትነቱን ከፈጸመ በሁዋላ ቅዱስ ሚካኤል በአክሊላት አክብሮ ወስዶ በገነት አኖረው:: ከሰማዕታትም ጋር ደመረው:: በዚያም ቡላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተመልክቶ ተደነቀ:: መንፈሳዊ ቅንዐትን ቀንቷልና "እባክህን ወደ ዓለም መልሰኝና ስለ ፍቅርህ እንደ ገና ልጋደል" ሲል ጌታን ለመነ::

ጌታችን ግን "ወዳጄ ቡላ! እንግዲህስ ሰማዕትነቱ ይበቃሃል::
ሱታፌ ጻድቃንን ታገኝ ዘንድ ግን ፈቃዴ ነውና ሒድ" አለው:: ቅዱስ ሚካኤልም የቅዱስ ቡላን ነፍስ ከሥጋው ጋር አዋሕዶ: ልብሰ መነኮሳትንም አልብሶ ግብጽ በርሃ ውስጥ አኖረው::

ተጋድሎ

=>አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዐርብ ዐርብ የጌታን ሕማማት እያሰበ ራሱን ያሰቃይ ገባ:: ራሱን ይገርፋል: ፊቱን በጥፊ ይመታል: ሥጋውን እየቆረጠ ለአራዊት ይሰጣል: ከትልቅ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ ወደ ታች ይወረወራል::

በጭንቅላቱ ተተክሎ ለብዙ ጊዜ ጸልዮ ጭንቅላቱ ይፈሳል:: ሌላም ብዙ መከራዎችን የጌታን ሕማማት እያሰበ ይቀበላል:: ስለ ጌታ ፍቅርም ምንም ነገር ሳይቀምስ ለ42 ዓመታት ጹሟል:: ጌታችንም ስለ ክብሩ ዘወትር ይገለጥለት ነበር::

የሚታየውም እንደ ተወለደ: እንደ ተጠመቀ: እንደ ተሰቀለ: እንደ ተነሳ: እንዳረገ እየሆነ ነበር:: አንድ ቀንም ጌታችን መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! እንዳንተ ስለ እኔ ስም መከራ የተቀበለ ሰው የለም:: አንተም የብዙዎች አባት ነሕና ስምህ አቢብ (ሃቢብ) ይሁን" አለው::

"እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ አኮቴት ማሕዘኔ:
ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ኩነኔ:
ዘመጠነዝ ታጻሙ ነፍስከ በቅኔ
" እንዲል::

ዕረፍት

አቡነ አቢብ ታላቁ ዕብሎን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት እየተጨዋወተ ዘለቀ:: በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: በዚህች ቀን ሲያርፍ ገዳሙ በመላእክት ተሞላ::

ጌታም ከድንግል እናቱ ጋር መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! ስምህን የጠራውን: መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ:: አቅም ቢያጣ "አምላከ አቢብ ማረኝ" ብሎ 3 ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን: በስምሕ እንኩዋ ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ" ብሎት ነፍሱን በክብር አሳረገ: በሰማይም ዕልልታ ተደረገ::

ታላቁ አባ ዕብሎይ

ይህ ቅዱስ የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ሲሆን በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳንም ቀዳሚው ነው:: ብዙ መጻሕፍት "ርዕሰ ገዳማውያን" ይሉታል:: የቅዱሱ ተጋድሎ እጅግ ሰፊ በመሆኑ በዕለተ ዕረፍቱ (የካቲት 3 ቀን) እንመለከተዋለንና የዚያ ሰው ይበለን::

ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት

ከሁሉ አስቀደሞ ስለ ሰማዕታት ዜና ሲሰማ ለዚህ ቅዱስ አንክሮ (አድናቆት): ክብርና የጸጋ ውዳሴ ይገባዋል:: ምክንያቱም ገድለ ሰማዕታትን የጻፈልን እርሱ ነውና:: ነገር ግን መጻፍ ሲባል: ነገሮች እንዲህ እንደ እኛው ዘመን ቀላል እንዳይመስሏችሁ:: ቅዱሱ ዜና ሰማዕታትን ለማዘጋጀት ሃብቱን: ንብረቱን: ቤተሰቦቹንና ሕይወቱንም ሰውቷል::

ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በመጨረሻው ዘመነ ሰማዕታት (በ3ኛው መቶ ክ/ዘ) ዓለም በደመ ሰማዕታት ስትሞላ እንኩዋን የሰማዕታቱን ዜና የሚጽፍ: ሥጋቸውን እንኩዋ የሚቀብር አልተገኘም:: "ወኃጥኡ ዘይቀብሮሙ - የሚቀብራቸውም አጡ" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት:: (መዝ. 78:3)


እግዚአብሔር ግን ስለ ወዳጆቹ ሰማዕታት ይህንን ቅዱስ አስነሳ:: ቅዱስ ዮልዮስ በዘመኑ ደግ ክርስቲያን: ትዳርና ልጆች ያሉት: እጅግ ባለ ጸጋና 300 አገልጋዮች ያሉት: ምጽዋትንም የሚወድ ሰው ነበር::

+በወቅቱ የክርስቲያኖች በየመንገዱ ወድቀው መታየታቸው ዕረፍት ቢነሳው ከቤተሰቦቹ ጋር መክሮ መልካም ግን ደግሞ ከባድ ውሳኔን አስተላለፈ:: ውሳኔውንም ታጥቆ ይተገብረው ጀመር::
በእውነት ድንቅ ሰው ነው:: በምን እንመስለዋለን! እርሱን የፈጠረውን ጌታ "ዕጹብ ዕጹብ" ብለን ከማድነቅ በቀር::
ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን። እንኩዋን ለታላቁ "ጻድቅና ሰማዕት አቡነ አቢብ" : "አባ ዕብሎይ" እና "ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። አቡነ አቢብ (አባ ቡላ) ይህን ታላቅ ቅዱስ በምን እንመስለዋለን! እኛ ኃጥአን ጣዕመ ዜናውን: ነገረ ሕይወቱን ሰምተን ደስ ተሰኝተናል! ቅዱሱ አባታችን:- "ቡላ - የእግዚአብሔር አገልጋይ" ብለን እንጠራሃለን::…
ሰማዕታቱም ስለ ደግነቱ የሚመልሱለት ቢያጡ ዝም ብለው ይመርቁት ነበር::+እንዲህ: እንዲህ እያለ ዘመነ ሰማዕታት ሊፈጸም ወራት ቀሩት:: በዚህ ጊዜ ለሰማዕትነት ከመነሳሳቱ የተነሳ ጌታችንን ተማጸነ:: ጌታችንም ተገልጾለት "ሒድና ሰማዕት ሁን: ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: እርሱም ደስ እያለው ዜና ሰማዕታቱን ለሁነኛ ሰው ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን ለነዳያን አካፈለ::

ቀጥሎም ቤተሰቦቹንና አገልጋዮቹን ጨምሮ ወደ ሃገረ ገምኑዲ ሔደ:: በመኮንኑ ፊት የክርስቶስን አምላክነት ቢመሰክር ፈጽመው አሰቃዩት:: በማግስቱም ወታደሮቹ ለጣዖት ካልሰገድክ ሲሉት "ቆዩማ ላሳያችሁ" ብሎ በጸሎቱ ጣዖታትን ከነ ካህናቶቻቸው ምድር ተከፍታ እንድትውጣቸው አደረገ:: በተአምሩም መኮንኑና ሠራዊቱ አምነው ተከተሉት::

በፍጻሜውም በሌላ ሃገር መኮንኑ ቅዱስ ዮልዮስን ከቤተሰቡና ከ1,500 ያህል ተከታዮቹ ጋር: 2ቱን የሃገረ ገዥዎች ጨምሮ አንገታቸውን አሰይፏቸዋል::

አምላከ ጻድቃን ወሰማዕት በቃል ኪዳናቸው እንዲምረን ቸርነቱ ይርዳን:: በረከታቸውንም አትርፎ ይስጠን::

#ጥቅምት_25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
2.አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
3.ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
4.ቅዱሳን አብርሃምና ሐሪክ
5.ቅዱሳን አሞኒና ሙስያ (የታላቁ ዕብሎ ወላጆች)

ወርሐዊ በዓላት

1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.ቅዱስ አቡፋና ጻድቅ
6.ታላቁ አባ ቢጻርዮን

እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ:: መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል:: (ማቴ. 16:24)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የቴሌግራም ገፃችን - https://www.tg-me.com/betel_et
የፌስቡክ ገጻችን - https://www.facebook.com/profile.php?id=61552723809417
#አደራ_አለብኝ!

የ 2016 ዓ.ም 1ኛ ዙር ጉባኤ

ዓለም ዓቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ

ቀን፡ ኅዳር 2/2016 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ

ጉባኤው በሁሉም ማእከላት በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከናወናል።

ቦታ፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ
እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ መታሰቢያ በዓል አደረሰን።

ፍቅር ኃያል ፍቅር ደጉ ወልድን ሳበው ከጸባኦት ከማዕረጉ ፍቅር ደጉ ወልድን ሊያነግሥ በመንበሩ በአንድ ጥለት በየዘርፉ በአንድ ጸና ማኅበሩ ቃልም ከብሮ የዘውድ አክሊል ተቀዳጅቶ ከምድር ላይ ከፍ...ከፍ...ከፍ...ብሎ ታይቶ ተሠየመ በመስቀል ላይ... የነገሥታት ንጉሥ አብርቶ በዚያች ልዩ ዕለት...ቀን ቡሩክ ቀን ፈራጅ በዓለ ሢመቱ ሲታወጅ ኀዘኑም ደስታውም በረከተ ፍቅር ኃያል ፍቅር ሞተ!
✝️“አለሁ እኔ ለወገኔ” ✝️
አስቸኳይ የነፍስ አድን ጥሪ!
+++
ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ፣ ጠለምት፣ በየዳና ጃና አሞራ፣ እንዲሁም በዋግኸምራ ዞን ሰሃላና አካባቢው ባጋጠመው ድርቅ የተጎዱ ወገኖቼ ለመርዳት አስቸኳይ ድጋፍ እያሰባሰበ ይገኛል። እኔም የከበረ የሰው ሕይዎትን ለማትረፍ የተቻለኝን ድጋፍ አደርጋለሁ። እርስዎስ ?
ድጋፍ ለማድረግም፡-
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
3. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
4. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
5. በአዋሽ ባንክ - 01329817420400 መጠቀም ይችላሉ።
በወገን ፈንድ ለመለገስ ከዚህ መልእክት ጋር የተያያዘውን ሊንክ ይጫኑ።
https://www.wegenfund.com/causes/nu-badereqe-yatagodu-waganocaacenene-hheyete-eneta/
ለበለጠ መረጃ
• 09 43 00 04 03
• 09 84 18 15 44
ማኅበረ ቅዱሳን
#አደራ_አለብኝ!

የ 2016 ዓ.ም 1ኛ ዙር ጉባኤ

ዓለም ዓቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ

ቀን፡ ኅዳር 2/2016 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ

ጉባኤው በሁሉም ማእከላት በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከናወናል።

ቦታ፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ
በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የተመራ የተከዜ ምዕራፈ ቅዱሳን ሐዋርያ ክርስቶስ አንድነት ገዳም መነኮሳት ልኡክ የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥንን ጎበኘ፡፡

መነኮሳቱ ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረጉት ጉብኝት የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋስይሁን በላይና የተቋሙ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱም ብሮድካስት አገልግሎት ተቋሙን የተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።

ጉብኝቱ 150 መነኮሳትን ከተከዜ ምዕራፈ ቅዱሳን ሐዋርያ ክርስቶስ አንድነት ገዳም በቅርቡ ወደተገደመው በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት የአቡነ ዜና ማርቆስ ወአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አንድነት ገዳም አድርሰው ሲመለሱ ነው የተከናወነው፡፡
2024/10/01 11:22:40
Back to Top
HTML Embed Code: