Telegram Web Link
Forwarded from የላቀ እይታ
Forwarded from የላቀ እይታ
አልማዝ በተፈጥሮ መንገድ እንዴት እንደሚሰራ ልንገራችሁ። አልማዝ የሚሰራው HPHT በሚባል Process ነው። HPHT ማለት High Pressure High Temperature ማለት ነው። አንድ አልማዝ አልማዝ ከመሆኑ በፊት አራት ደራጃዎችን ማለፍ ይኖርበታል።

አንደኛ ከምድር በታች ከ300 እስከ 600 ኪሎ ሜትር ዝቅ ብሎ መቀመጥ።

ሁለተኛ ከፍተኛ ሙቀት መታደል፣ ከ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ቃጠሎ ውስጥ መቀመጥ።

ሶስተኛ ከፍተኛ ጭነት ማግኘት።

አራተኛ ለረዥም ጊዜ ውስጥ በነዚህ ሁኔታ ውስጥ መቆየት !

እንግዲህ አንድን የድንጋይ ከሰል ወስዳችሁ ከምድር በታች 600 ኪሎ ሜትር ብታወርዱት፣ 1200 ዲግሬ ሴንቲ ግሬድ ቃጠሎ ውስጥ ብታኖሩት፣ በከፍተኛ ፕሬዠር ውስጥ ብታስቀምጡት እና ለረዥም ጊዚያት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብትተዉት ከሰሉ አልማዝ ይሆናል ! ከሰሉ ወደ ዳይመንድ ይለወጣል።

አንዳንዶቻችሁ በህይወታችሁ ግራ ይገባችኋል፣ በጣም የሚወዳችሁ አምላካችሁ ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር አውርዷችሁ ይሆናል።

በማይገባችሁ ፈተና 1200 degree centigrade ቃጠሎ ውስጥ አስቀምጧችሁ ፤ በማጣት፣ በመገለል፣ በመገፋት ለረዥም ጊዚያት እየፈተናችሁ "ምንድነው እየተካሄደ ያለው" ብላችሁ እስክትጠይቁ ድረስ ለአምስት አመት፣ ለአስር አመት ከሰው፣ ከወዳጅ፣ ከዘመድ፣ ከጓደኛ ዝቅ አድርጓችሁ ይሆናል። ....

"ምን ማለት ነው የሚወደኝ አምላክ ይሄን የሚፈቅደው?" ስትሉ ....

አልማዝ አድርጎ ሊሰራችሁ፣
ውብ አድርጎ፣ ሊሰራችሁ፣
የምታበሩ አድርጎ ሊያበጃችሁ፣
እንቁ፣ ዳይመንድ፣ አልማዝ ሊያደርጋችሁ ስላሰበ ነው !

አልማዝ ሰባት ባህሪዎች አሉት:-

አንደኛ ጠንካራ ነው። ወስዳችሁ በድንጋይ ቀጥቅጡት አይሰበርም። በሰይፍ ምቱት አይሰነጠቅም። በመጋዝ ገዝግዙት አይቆረጥም። በአልመዝ ግን ብረት ይቆረጣል፣ በአልማዝ ግን ሰይፍ ይቆረጣል። በአልማዝ ግን ድንጋይ ይፈርሳል። አልማዝ የሚቆረጠው በሌላ አልማዝ ነው።

ሁለተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። ከፍተኛ የማንጸባረቅ ባህሪ አለው። refractive index ይባላል። የተቀበለውን ብርሃን መልሶ የማብራት ባህሪ አለው። ያንጸባርቃል።

ሶስተኛው የአልማዝ ባህሪ የተቀበለውን የጸሐይ ብርሃን፣ ነጩን ብርሃን ወደ ተለያዩ በርካታ ቀለማት የመበተን ችሎታ አለው።

አራተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። እጅግ በጣም ንጹህ ነው። አልማዝ የሚታወቀው በነጹህነቱ ነው።

አምስተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። አልማዝ በእሳት አይቃጠልም። አንድ ቤት ውስጥ አልማዝ አለ እንበል ያ አልማዝ ያለበት ቤት ሙሉ ለሙሉ ቢቃጠል አልማዙ ምንም አይሆንም። ምንም። በነበረው ቅርጹ፣ በነበረው ንጽህናው እናገኘዋለን።

የሚያስገርመኝን ስድስተኛውን የአልማዝን ባህሪ ልንገራችሁ። ወርቅ ላይ አሲድ ድፉበት ወርቁ ይበላሻል። አልማዝ ላይ አሲድ አፍስሱበት ምንም አይሆንም። አይበላሽም።

የመጨረሻው እና ሰባተኛው የአልማዝ ባህሪ በጣም ውድ ነው። በጣም ውድ ነው። የአውራጣትህን ራስ የምታክል ዳይመንድ አንድ ትልቅ ፎቅ ይገዛል። በጣም ውድ ነው።

ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር ወርዳችሁ ፣ በ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ስቃይ ውስጥ ያለፋችሁ፣ በፕሬዠር ውስጥ ለበርካታ አመታት ያለፋችሁ እናንተ አልማዝ ሁናችሁ የተሰራችሁ ሰዎች ናችሁ።

ሰዎች ጠጠር ብትመስሏቸውም አልማዞች ናችሁ። ዋጋችሁ በጣም ውድ ነው።

... ከተማሩ ሰዎች ይልቅ፣ ብዙ ድግሪ ከተሳካላቸው ሰዎች ይልቅ፤ በመከራ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ። ዋጋ የከፈሉ ሰዎችን አከብራለሁ። በስቃይ ውስጥ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ። ምክንያቱም ዋጋቸው በጣም ውድ ነው።

ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ

ፅሁፉን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mwqCRwSCd4&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
Forwarded from የላቀ እይታ
ለአንድ ግለሰብም ሆነ ኅብረተሰብ፣ ቤተሰብም ሆነ አገር የዕድገትም ሆነ የውድቀት ቁልፉ መሬቱ ሳይሆን አዕምሮ ላይ ነው። መሬቱ የሚቆለፈው የሰው አዕምሮ ሲቆለፍ ነው።

አንድ ሰው አዕምሮው ሲከፈትለት ሁሉ ነገር ይከፈትለታል። የአንድ ሀገር ሕዝብ አዕምሮው ሲቆለፍ፣ ሁሉ እያለው ምንም እንደሌለው ሁሉም ነገር ይዘጋጋል።

.... ሌብነት ብትይ ሙስና፣ አምባገነንነት ብትይ ጦርነት፣ ዘረኝነት ብትይ የሐይማኖት ግጭት፣ ሁሉም የአዕምሮ መቆለፍ ምልክት ናቸው።

ስለዚህ አሁን አንገብጋቢውና ትልቁ ቁም ነገር መንገድ መሥራት ወይም ሕንጻ መገንባት ሳይሆን ይህንኑ ማድረግም ሆነ በተሰራው በቅጡ መጠቀም የሚቻለው የሰው አዕምሮ ሲከፈትና ከተኛበት የዘመናት እንቅልፍ ሲነቃ ብቻ መሆኑ ላይ ነው።" ...

ምንጭ:- "የተቆለፈበት ቁልፍ" በምሕረት ደበበ (ዶ/ር)

መልእክቱን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት በርካቶች ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ
Forwarded from የላቀ እይታ
Forwarded from የላቀ እይታ
በድፍን አሜሪካ ዝናዋ የገዘፈና ሰፊ እውቅናን ያገኘች ጋዜጠኛ ስም እንጥራ ካልን #ኦፕራ ዊንፍሬይ ለማለት እንገደዳለን።

ታዲያ ይህች የሚዲያው አለም ንግስት ለአመታት ከነገሰችበት የጋዜጠኝነት ሙያ ድንገት ጡረታ እንደምትወጣ አሳወቀች። በዘርፉ ላበረከተችው መጠነ ሰፊ አገልግሎት ሊያመሰግኗትና ሊያከብሯት በመሻት የጡረታ ስንብቷን በአንድ ትልቅ ስቴዲየም አደረጉ።

አስደናቂው ነገር ግን በዛ ቀን ማንም ሳያውቅ ለ25 ዓመታት 65,000 /ስልሳ አምስት ሺህ/ ድሆችን ትረዳ እንደነበር መታወቁ ነው። ይታያችሁ በሩብ ምዕተ-ዓመት ስልሳ አምስት ሺህ ድሆችን ረድታ ኑሯቸውን ማቃናት ችላለች።

ይህም ሊታወቅ የቻለው በእሷ እገዛ ከትናንት ማንነታቸው ተላቀው ዛሬን በተሻለ ህይወት ላይ የሚኖሩት አብዛኞቹ በስታዲየሙና በፕሮግራሙ በመታደማቸው ነው።

ከታዳሚዎቹ መሃል 450 ሰዎች ሻማ እያበሩ ወጡ....ከነዚህ 450 ሰዎች መካከል ደግሞ አምስቱ በሃርቫርድ ዩንቨርሲቲ ባለ ሙሉ ማዕረግ ፕሮፌሰሮች ናቸው። እነዚህን ሰዎች ወክሎ ንግግር ያደረገው ፕሮፌሰር ሲናገር " የኦፕራ እገዛ ባናገኝ ኖሮ፣ ምናልባት መገኛችን እና ማንነታች ሌላ ቦታ ላይ ሊሆን ይችል ነበር" አለ።

👉አያችሁልኝ?? አንዲት ልበ-ቀና እንስት የ65,000 ሰዎችን ህይወት እንዴት እንደቀየረች???

#የሰውነት_ልኬት

"ሰብዓዊነት ኃይማኖት አይደለም ፣ግን የተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ የሚቆናጠጡት የህይወት ልህቀት ደረጃ ነው" ያለው ሶቅራጥስ በምክንያት መሆኑን ኦፕራ ማሳያ ትሆናለች ብዬ አምናለሁ።

የሃገራችን ሚሊየነሮች ምናለ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፋሽኑ አልቆ ውራጅ የሚሆንን አልባሳት፣ ህንፃ፣ መኪና ቅብጥርስ ከማሳደድ ተቆጥበው.....የድሃ ልጆችን ተንከባክበው የሰብዓዊነት ዋልታና ማገር ቢሆኑ!!!!

👉ፈጣሪ ሆይ እንደ ኦፕራ አይነት ደግ ልብ የቸርካቸውን ባለ ሃብቶች በሃገራችን አብዛልን!!
✍️አለበል ንጋቱ
Forwarded from የላቀ እይታ
Forwarded from የላቀ እይታ
እንግሊዛዊው አንቶኒ በርገስ በ42 ዓመቱ በጭንቅላት ካንሰር ምከንያት በህይወት የሚቆየው ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ዶክተሮች ይነገሩታል ።

በጊዜው በጣም ያዝናል፣ ይሁን እንጂ ሚስቴ ከሞትኩ በኋላ እንዳትቸገር በማለት በቀረችኝ ጊዜ ስራ መስራት አለብኝ፣ ለሚስቴ ጥሪት ማስቀመጥ አለብኝ ብሎ ወሰነ።

አንቶኒ በርገስ ኘሮፌሽናል ደራሲ አልነበረም። ነገር ግን በዉስጡ የተዳፈነ የመፃፍ ችሎታ እንደነበረዉ ያዉቅ ነበርና ወረቀቱን ከጽሕፈት ማሽኑ ጋር አወዳጅቶ መፃፍ ጀመረ።

በሚገርም ሁኔታ በቀረችዉ አንድ አመት ውስጥ 5 መፃሕፍትን አሰናድቶ ጨረሰ። ይህም ታዋቂዉ ደራሲ 'Em foster' በህይወቱ ሙሉ ከፃፈዉ በላይ እሱ በአንድ አመት ዉስጥ የፃፈዉ ይበልጥ ነበር ። እንዲሁም 'J.D.stelenger' የተባለዉ ደራሲ በህይወት ዘመኑ ከፃፈዉ መፅሐፍ በላይ በእጥፍ ፃፈ።

በካንሰር ለመሞት አንድ አመት ቀረህ የተባለው አንቶኒ በርገስ ይህን የአንድ አመት ጊዜ በለንደን ሆስፒታል ውስጥ አሳልፏል። ነገር ግን ከበርካታ የሴሬብራል ምርመራዎች በኋላ ምንም አይነት በሽታ ወይም ዕጢ አልተገኘበትም። በዚህ ጊዜ ነበር የሙሉ ጊዜ ጸሐፊ ለመሆን የወሰነው።

በኖረበት ቀሪ እድሜ (በ76 ዓመቱ ይችን አለም እስከተሰናበተበት ጊዜ ድረስ) 70 መፅሃፍቶችን ለአንባቢያን አበረከተ ። በተለይ 'clock work orange' በሚል ያሳተመዉ መፅሐፍ ታላቅ እዉቅናን ያስገኘለት ስራው ነበር ።

አንቶኒ በርገስ ‘ለመሞት አንድ አመት ነዉ ያለህ’ ባይባልና ሚስቱ እንዳትቸገር 'ጥሪት አስቀምጬ ልሙት' በሚል ሀሳብ ባይነሳ ፣ ይህን ያህል ቁጥር ያለው መፅሐፍ ባልፃፈ ነበር።

#አንተስ "በህይወት የምትቆየው ለአንድ ዓመት ብቻ ነው" ብትባል ምን ታደርጋለህ?


#ይህን ጥያቄ መመለስ በውስጣችን የተዳፈነውን ልዩ ችሎታችንን ወይም አቅማችንን አውጥተን እንድንጠቀም የሚረዳን አይመስላችሁም?

ሃሳባችሁን አጋሩን!

መልእክቱን ከወደዳችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8n6rRbMIYje&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
Forwarded from የላቀ እይታ
Forwarded from የላቀ እይታ
አንዳንድ ሰዎች የማንነታቸውን ዋጋ የሚመዝኑት ካሳለፉት መከራና ከደረሰባቸው ችግር አንጻር ነው፡፡ የደረሰባቸውን የኑሮ ውጣ ውረድ በአካላቸውና በኑሮአቸውም ላይ ያደረሰውን ጉዳት በቀጥታ ከማንነታቸው ዋጋ ጋር ያዛምዱታል፡፡ ሲቸገሩና ሲጎሳቆሉ የማንነታቸውን ዋጋ ይቀንሱታል፡፡

በአንጻሩ ነገሮች በመልካም ሲሄድላቸውና የተሳካላቸው ሲመስላቸው ለራሳቸው የሚሰጡትን ዋጋ ከፍ ያደርጉታል፡፡ ሰዎችም ካለማቋረጥ ይህንኑ መልእክት ለህሊናው እንዲናገሩ ይፈቅዱላቸዋል፡፡ ውጤቱም የወደቀ ማንነትን ነው፡፡

በአንድ በዝቅተኝነት ስሜት የተጎዱ ሰዎች ለምክር በሚመጡበት ማእከል ውስጥ ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል፡፡ ችግራቸው አንድ ነው፣ የኑሮአቸው ሁኔታ በራሳቸው ላይ ያላቸውን አመለካከት ደብድቦ ጥሎታል፡፡ በራሳቸው ላይ የወደቀ አመለካከት አላቸው፡፡

አሰልጣኙ በምን መልኩ ከዚህ አመለካከት ሊያወጣቸው እንደሚችል ካሰበ በኋላ አንድን ምሳሌ ነገራቸው፡፡

በእጁ አንድ ድፍን መቶ ብር ይዟል፡፡ ወደ ሰዎቹ ዘወር አለና፣

“የዚህ ብር ዋጋ ስንት ነው?” አላቸው፡፡

የሁሉም መልስ እንደተጠበቀው፣ “መቶ ብር” የሚል ነበር፡፡

የሚቀጥለው ጥያቄ፣

“ይህ ብር ምን ሊገዛ ይቻላል?” የሚል ነበር፡፡

ሁሉም በመሽቀዳደም ምን ሊገዛ እንደሚችል መናገር ጀመሩ፡፡

በመቀጠልም፣ ይህንን መቶ ብር በመዳፉ አጅግ ጨመደደው፣ ከዚያም ወደ መሬት ጣለውና ረገጠው፡፡ በእጁ አንስቶ ከጨመደደው በኋላ ያንኑ ጥያቄ ጠየቃቸው፣

“የዚህ ብር ዋጋ ስንት ነው?”፡፡

የሁሉም መልስ እንደቀድሞው፣ “መቶ ብር” የሚል ነበር፡፡ ሁለተኛውንም ጥያቄ ደገመው፣ “ይህ ብር ምን ሊገዛ ይቻላል?” የሚል ነበር፡፡ መልሳቸው እንደቀድሞው ነበር፡፡

ከዚያም የሚከተለውን ነገራቸው:-

“ይህ ብር ተጨማደደ፣ ወደቀ፣ ተረገጠ፣ … ዋጋው ግን ያው ነው፡፡ የእናንተም ዋጋ እንዲሁ ነው፡፡ ምንም አይነት ነገር በሕይወታችሁ ቢያልፍ፣ ዋጋችሁ ግን ያው ነው - የውጪ ገጠመኛችሁና ሁኔታችሁ የማንነታችሁን ዋጋ መቀነስም ሆነ መጨመር አይችልም”፡፡

“አንተነትህን የያዘው የሆንከው ማንነትህ አይደለም፣ ነኝ ብለህ ያሰብከው ሃሳብህ እንጂ” - Unknown Source

ከተወለድክባት ቀን ጀምሮ ያለፍክባቸውን ሁኔታዎች መለስ ብለህ ተመልከታቸው፡፡

የወደቅክባቸውንና የተነሳህባቸውን፣ ያዘንክባቸውንና የተደሰትክባቸውን፣ የብቸኝነትህን ጊዜና በወዳጆች የተከበብክባቸውን ጊዜአት … አስባቸው፡፡

እነዚህ ሁኔታዎች የተለያዩ የስሜት ከፍታዎችንና ዝቅታዎችን እንድታሳልፍ ዳርገውሃል፣ ሆኖም በማንነትህ ላይ ጥቂት እንኳ የዋጋ መቀነስ ተጽእኖ የላቸውም፡፡

ማንነትህ፣ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብታልፍም ያው ማንነትህ ነው፡፡
ስኬታማ ሆንክም አልሆንክ፣ ባለጠጋ ሆንክም አልሆንክ፣ እነዚህ ነገሮች ከማንነትህ ጋር በፍጹም አይገናኙም፡፡

በማንነትህ ላይ ያለህ አመለካከትና ለማንነትህ የሰጠኸው ዋጋ ግን በስኬታማነትህ ላይ ታላቅ ተጽእኖ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ያለፈው ታሪክህ፣ አሁን የምታልፍበት የኑሮ ጫናም ሆነ ያለህና የሌለህ ነገር በአንተነትህ ዋጋ ላይ ተመን እንዲያስቀምጡበት የምታደርገው አንተው ብቻ ነህ፡፡ ሰው የመሆንህ ክቡርነት በፍጹም በዋጋ ሊተመን ስለማይችል፣ ከፍም ሆነ ዝቅ ማለት አይችልም፡፡ በራስህ ላይ ያለህ ግምት ግን ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ አመልካችነቱ የስሜትን ከፍታና ዝቅታ እንጂ የማንነትን ዋጋ ከፍታና ዝቅታ አይደለም፡፡

ዋጋህን ሳትቀናንስ፣ ካለፈውና ከአሁኑ ሁኔታህ ላይ አይኖችህን አንስተህ በፊትህ ወዳለው መልካም የወደፊት ስኬት እንድትዘልቅ የሚከተሉትን እውነታዎች ማሰላሰሉ ጠቃሚ ነው፡፡

👉 የሆነልህን እንጂ የሆነብህን አትቁጠር

“ከሃዘኖችህ ይልቅ ሃሴቶችህን፣ ከጠላቶችህ ይልቅ ደግሞ ወዳጆችህን ቁጠር” - Irish Proverb

👉 ራስህን አክብር

“ለራሳችን ያለንን ክብር አሳልፈን ካልሰጠናቸው በስተቀር ሰዎች ሊወስዱብን አይችሉም” - Mahatma Gandhi

(“25 የስኬት ቁልፎች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

ፅሁፉን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👇 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8n8zcdM80z0&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
Forwarded from የላቀ እይታ
በቲክቶክ ገፃችን 👉https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8nC7EVIhhUj&_r=1 መልእክት ያስቀምጡልን/#inbox ያድርጉልን።
Forwarded from የላቀ እይታ
ከ40 ሚሊዮን ቅጂ በላይ ተሽጧል፤ በሰላሳ ቋንቋዎች ተተርጉሞም ለንባብ በቅቷል፡፡ ይህ መጽሐፍ “The 7 Habits of Highly Effective people” ይባላል:: “እጅግ በጣም ስኬታማ የሆኑ ሰዎች 7 ልምዶች”

የመጽሐፉ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ ይባላል፡፡ ይህ መጽሐፍ በግለሰብ ደረጃ ለውጥ ለማምጣት (Personal development) እንዲረዱ ታስበው እስከ ዛሬ ድረስ ከተጻፉ መጽሐፍት መካከል ወደር የማይገኝለት ነው።

የዚህ ድንቅ መጽሐፍ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ “ውስጣዊ ድል ከውጫዊ ድል ይበልጣል” ይላል፡፡ እዚህ ምድር ላይ ማግኘት የምንፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ ለማግኘት አስቀድመን ራሳችንን ማሸነፍ፤ የህይወታችን ሾፌር መሆን፤ ውስጣዊ ማንነታችንን መቆጣጠር ወዘተ አለብን ማለት ነው፡፡ ራስን ማሸነፍ ሌሎች ውጫዊ ነገሮችን የማሸነፊያ ቁልፍ እንደሆነ ፀሀፊው ይመክረናል።

ይህን ድንቅ መፅሐፍ በቅርብ ቀን በ #tiktok ገፃችን የምንዳስሰው ይሆናል።
ዝግጁ ናችሁ?

ይህን #post #like #copylink #share በማድረግ #እንዲሁም ለቲክቶክ ገፃችን አዲስ ከሆናችሁ ይህን የቲክቶክ ገፃችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8nDp7Xvl1S1&_r=1 ማስፈንጠሪያ/link በመጫን #follow እያደረጋችሁ ጠብቁን!
Forwarded from የላቀ እይታ
Forwarded from የላቀ እይታ
ወደዚህች ምድር ስንመጣ በአካልም ይሁን በስነልቦና ያላደግን ደካሞች ሁነን ነው:: ይህም የበታችነት እና ያለመቻል ስሜትን ይፈጥራል::

ለመራመድ ፣ ራሳችንን ችለን ለመመገብ፣ ለማውራት ጊዜያቶችን መጠበቅ ግድ ይለናል:: የስነልቦናችን መዋቅርም ለመብሰል ጊዜን ይፈልጋል::

እነዚህ እድገቶቻችን የወላጆቻችንን/ አሳዳጊዎቻችንን እገዛ የሚሹ ናቸው:: በነዚህ ሰዎች እገዛና ድጋፍ በጊዜ ሂደት በአካልና በልቦና እየጎለመስን እንሄዳለን:: ለማህበረሰብ ማሰብን አሃዱ ብለን የምንማረው ከወላጆቻችን/አሳዳጊዎቻችን ነው::

ደመነብሳዊ ልቦናችን ምልአትን የምትሻ በመሆኗ፡ ከ 4- 5 አመታችን ሁላችንም ልዕልናን እና ስኬትን (striving for success and superiority) ለመቀዳጀት ማለም እንጀምራለን::

ይህ ትልማችን ግላዊ ጥቅመኝነትን(striving for personal superiority): አልያም የሌሎችን ሰዎች ጥቅምን ከግምት ውስጥ ያስገባ(striving for social interest) ሊሆን ይችላል::

ይህ የአድለር አተያይ ውስጣዊ ሃይልን (sex and aggression) እንደ የሰው ልጅ አብይ ባህርይ ዘዋሪ አድርገው ከሚቀበሉት ቀደምት የሳይኮዳይናሚክ አስተምህሮ ተከታዮች ለየት ያደርገዋል::

ታዲያ በዚህ ሁሉ ሂደት አስተዳደጋችን ወሳኝ ሚና አለው::
እድገታችን በፍቅር የተዋጀ እንደሆነ ፥ አብሮን የተፈጠረው የበታችነት ስሜት ለማሸነፍ የሚኖረን መሻት ከማህበረሰቡ ፍላጎት እና እሴት ያላፈነግጠ እና ለራስ ጥቅም ብቻ ያላደላ ይሆናል:: በጥቅሉ ውለታችንን አንረሳም እንደማለት ነው:: እነዚህ ሰዎች መዳረሻቸውን በአግባቡ የሚረዱ እና ንቃተ ህሊናቸው የዳበረ ነው::

በአንጻሩ ደግሞ አጉል ተቀማጥለው አልያም ትኩረት ተነፍገው ያደጉ ልጆች ከልክ ያለፈ ለራስ ጥቅም የማድላትና ግላዊ ልዕልናን የመሻት ዝንባሌ ይስተዋልባቸዋል:: በበታችነት ስሜት የሚፈተኑ ናቸው ይለናል አድለር::

▪️ ትኩረት ተነፍገው ያደጉ እንደሆነ: ማህበረሰቡን በጥርጣሬ አይን የሚያዩ: ከሌሎች ጋር መተባበር የሚቸግራቸው: ቀናተኞች ሊሆኑ ይችላሉ::

▪️ ቅምጥሎቹ ደሞ ከወላጆቻቸው ጋር የነበራቸው ጥገኛ ግንኙነት በሌላ የህይወት ምዕራፋቸውም አብሯቸው ይዘልቃል:: ሁሌም ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ይሻሉ:: ትኩረት ፈላጊዎችም ይሆናሉ::

በዚህ ጽንሰሃሳብ መሰረት ሰዎችን እንረዳለን የሚሉ ግለሰቦችን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን:-

የምር የሰዎች መቸገር አስጨንቋቸው የሚረዱ

Vs

በመርዳት ስም ተረጂው ከነሱ በታች መሆኑን ለማሳየት እና እንዲሽቆጠቆጥላቸው በመፈለግ: እንዲሁም ለጋስ ናቸው ተብለው እንዲወራላቸው በማሰብ የሚረ'ዱ (በእርዳታ ወቅት ካሜራ የማይለያቸው ሰዎችን ለዚህ እንደምሳሌ ማቅረብ ይቻል ይሆን?😏)


እርስዎ የግል ጥቅምዎን ያስቀድማሉ ወይንስ የግል ጥቅምዎን ከማህበረሰብ ፍላጎት ጋር ሳያጋጩ ማስኬድን ያውቁበታል?

ቸር ይግጠመን

✍️ ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
Forwarded from የላቀ እይታ
Forwarded from የላቀ እይታ
1. የሰው ልጆች በመጀመሪያ በውልደት ወደዚህ አለም ሲመጡ የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከሚቀጥሉት አርባ አመታት በላይ የበለጠ ፋይዳ አለው። ምክንያቱም የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከመሞት በፊት ያለው ትልቁ የህይወት ለውጥ ነው።

2. ፍርሃት የፈሪም የጀግናም መነሻ ነው። ፍርሃት ለፈሪ ጭንቀቱ ሲሆን፤ ለጀግና ደግሞ ጀብዱው ነው።

3. መማር ባለሙያ ያደርጋል፤ መኖር ደግሞ አዋቂ ያደርጋል።

4. ሰው የሆነውን የሚሆነው በአጋጣሚ አይደለም።አዋቂው ሰው ህፃኑ ልጅ በልጅ አዕምሮው የፃፈውን ተውኔት የሚተውን ተዋናይ ነው። የልጅ ጭንቅላት የተባለውን ይይዛል፤ አዋቂ ደግሞ የያዘውን ይተገብራል። አዋቂው ሲያለቅስ ወይም ሲያዝን እንደህፃን አባብይው።

5. ተስፋ የመኖር ምክንያት ነው።ሰውን እንዲኖር የሚያደርገው መለወጥ አለመለወጡ ሳይሆን የመለወጥ ተስፋው ነው። ቢሆንም ግን ህይወት ተከታታይ መሆኗን መገንዘብ ይጠቅማል። ዛሬ የምንኖረው በትላንት ምክንያት ነው።

6. ሰው መሆን ማለት ራቁታችንን ከተወለድን በኋላ፤ ከልብስ ጀምሮ አካላችንን ከሚሸፍኑት ሽፋኖች መላቀቅ ነው። ሰው ሰውነቱን የሚያጣው ራቁቱን ከእናቱ ማህፀን ሰው ሆኖ ተወልዶ በማህበረሰብ፣ በልብስ፣ በትምህርት፣ ሃይማኖት፣ በብሔር የመሰሉ ግዑዛን አልባሳትን በመደረብ ነው።

7. እውነተኛ ለውጥ የማይኖረው ሰው ስላልጣረና ስላልሞከረ ሳይሆን ለውጥ ሂደት እንጂ መድረሻ ስላልሆነ ነው።

8. ጎዳና ላይ የሚያድር ሰው ብርዱን ይለምዳል፣ ፀሃዩን ይታገሳል፣ አውሬ ያስለምዳል፤ ሰውን ግን ይፈራል። ቀኑን ሙሉ ብርድ ሳንፈራ ደረታችንን ገልጠን ራቁታችንን የምንውል ሰዎች፤ ልክ ሲመሽ የውጪ በር ቆልፈን፣ከዛ የሳሎን በር ቆልፈን፣ የጓዳ በር ቆልፈን፣ አልጋችን ውስጥ ገብተን ብርድልብስ ለብሰን፣ ብርድ ልብሱ እንዳይኮሰኩሰን አንሶላ ደርበን፣ አንሶላው እንዳይቀዘቅዘን የለሊት ልብስ ለብሰን ...በነዚህ ነገሮች ሁሉ ተከልለን እንተኛለን። ይህን እንዲሆን ደግሞ ያደረገው ፍርሃታችን ነው።

9. በታሪክ ውስጥ ትልቁ አምባገነን ታሪክ ራሱ ነው።ሁላችንም የታሪክ ተገዢዎች ነን።

10. የማታሸንፈውን ሰው ተጠያቂ ማድረግ የፈሪነት መፍትሔ ነው።

11. እውነት እኮ የጊዜና የቦታ ድምር ውጤት ነው። የራስን ሃሳብ ሌላው እንዲገባው ማድረግ ማለት ፤ የራሱን ሃሳብ ድንበር አልፈን የሃሳብና አስተሳሰብ ወረራ አካሄድን ማለት ነው።

12. የሚጠፋ ነገር ዐይንህ ስር ተቀምጦ ያለማየትን የመሰለ ዕውርነት የለም። አንዳንዴ ከሞት በኋላ ስለሚኖር መኖር እየጓጓን የውሸት ማመን የለብንም። ስለፀሎታችንን ምንነት በአንክሮ መፈተሽ ያስፈልጋል

13. ሰው የምታውቀው ፍጡር አይደለም። ሁልጊዜ ሰውን የምናውቀው ይመስለናል። እኔ ሐኪም ስከሆንኩና የአንድ ሰው አካል ቀድጄ ልቡን ስላየሁት ሰውን ያወኩት ይመስለኛል። ነገር ግን ሰው በየትኛውም ደረጃ የሚታወቅ ፍጡር አይደለም።

በደረቁ ሳይንስ አጥንተህ ሰው ውስጥ ያለውን ፕሮቲን እንዴት እንደሚሰራ ስላወቅህ ሰውን አውቃለሁ ማለት አይቻልም።

የመማር አንደኛው ችግር (በተለይ እኛ ሐገር) ቶሎ መታበይና የምናውቀው እውቀት እኛ ያመጣነው ሳይሆን ቀድሞ በሌሎች የተፈጠረ መሆኑን የመርሳት ችግር አለብን። እኛ ያወቅነው ከእኛ በፊት የመጡት የፈጠሩትን ነው። ይህንን እንረሳና እኔ ተምሬ ሳውቅ ራሴን አዋቂና ሐሳቡን እኔ የፈጠርኩት የመምሰል ችግር አለብን።

14. እያወቅክ ስትሔድ ትልቅልነትህን ሳይሆን ትንሽነትህን ነው የምትረዳው "
ብዙ ነገር ለመማር መሞከር እይታህን ያሰፋል። የእይታህ አድማስ ሲሰፋ ደግሞ አንተ እያነስክ ነው የምትሄደው። ሰፊ ከሆነው ዓለም ውስጥ አንተ ምን ያህል ኢምንት እንደሆንክ ትረዳለህ። እያወቅክ ስትሄድ ትልቅነትህን ሳይሆን ትንሽነትህን ነው የምትረዳው።

የትኞቹን ሃሳቦች ወደዳችኋቸው? #comment አድርጉልን

ሃሳቦቹን አስተማሪ ሆነው ካገኛችኋቸው ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ
Forwarded from የላቀ እይታ
👉 ሐመር ውስጥ ውሸት የለም ። ማንም ሐመር ሌላው ሐመር የሚነግረውን ካለ ጥርጣሬና ማመንታት ይቀበላል።

ያየውን አየሁ፤ ያላየውን አላየሁም፤ የሰማውን ሰማሁ፤ ያልሰማውንም አልሰማሁም ይላል።

👉 ሐመሮች የቀን ተቀን ህይወታቸውን በቃል ልውውጥ ነው የሚያቀላጥፉት ።

ያዮትን ላላዮት መንገር ውዴታም ብቻ ሳይሆን ሞራላዊ ግዴታም ነው።

👉 የደከመው፣ የራበውና የጠማው እግሩ ወዳደረሰው ሐመር ቤት ጎራ ይላል። ካለ ይሉኝታና መሽቆጥቆጥ ይበላል ይጠጣል። ይህንን ማድረግ እንደ ውለታም አይቆጠርም።

"አብልቼው፣ አጠጥቼው፣ ቁርበት አንጥፌ አሳድሬው" አይባልም።

መቀበልና መስጠት ለሐመሮች አየር ወደ ሳንባ እንደ ማስገባትና ማስወጣት የሕልውና ሂደት ነው።

👉 በሐመር ስርቆት የለም። የእሱ ያልሆነ ነገር የሚወስድ የለም። ወድቆ የተገኘን አንስቶ ዛፍ ላይ ማንጠልጠል ስርአት ነው።

👉 በሐመር ውስጥ ሕይወት ትርጉም አላት። አንዱ ሐመር የሌላው ሐመር አጋዥ እንጂ እንቅፋት መሆን የለበትም።

ሐመር ውስጥ በጉልበት መመካት: በጉልበት ማጥቃት የለም።

ሐመሮች እንደ ንብ ተባብረው ይቀስማሉ፤ እንደ ንብ ተባብረው ማር ያመርታሉ፤ እንደ ንብ ተባብረው ያዜማሉ፣ ይደንሳሉ....ይኖራሉ።

ሐመሮች 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

(ፍቅረማርቆስ ደስታ)

ከሐመሮች ምን መማር እንችላለን? #comment በማድረግ ሃሳባችሁን አጋሩን። እንወያይበ!

ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏
Forwarded from የላቀ እይታ
Forwarded from የላቀ እይታ
ዘመኑ የግልቦች ነው፡፡ ቁምነገር የሌለው ትውልድ እየተመረተ ነው፡፡ ለጥበብ የሚንጋጋ ዕውቀት ቆፋሪ፣ እውነት መርማሪ እያነሰ ነው፡፡ ሩጫው ገንዘብ ወዳለበት ነው፡፡ እሽቅድምድሙ ቁሳዊ ነው፡፡ ፉክክሩ አለባበስና አበላል ላይ ነው፡፡ የዘንድሮ ቢዝነስ እውነት፣ እምነትና ሃቅ የለበትም፡፡

ሃይማኖቱም፣ ፖለቲካውም፣ ሙያውም፣ ንግዱም፣ ትምህርቱም፣ ፍቅሩም፣ ትዳሩም፣ ወዳጅነቱም፣ ዝምድናውም፣ ወዘተውም እየተሸቀበ ነው፡፡

መንጋው የሚንጋጋው ለራሱም ለሐገሩም የማይጠቅም ጉዳይ ላይ ነው፡፡ ረጋ ብሎ የሚያስብ፣ ከመንጋው ተለይቶ መንጋውን የሚመልስ ጠፍቷል፡፡ መሪውም ተመሪ፤ ተመሪውም ደንባሪ ሆኗል፡፡ ሁሉም እየተምዘገዘገ ያለው ወደገደሉ ነው፡፡ “ሐሰተኛው በእምነት ስም” መፅሐፍ ገፅ 61 ላይ ‹‹ከኋላ የሚከተል መምሕር፣ ከፊት የሚቀድም ደቀመዝሙር፤ ሁኔታው ሁሉ የተምታታ ነው›› እንዳለው እርስበርሱ የተምታታ ሐገር ባለቤት ሆነናል፡፡!

የሐሽማል ደራሲ፡-

‹‹አሁን ዘመኑ የጠቢባን ሳይሆን የግልቦች ነው!›› ይለናል፡፡

እውነትነት አለው! አዎ እምነቱ ግልብ ነው፤ እውቀቱ ግልብ ነው፤ ስርዓቱ ግልብ ነው፣ አመራሩ ግልብ ነው፤ ግልብነት የዘመናችን ምልክት ሆኗል፡፡ ዛሬ ዶክተር ምህረትአብ ደበበ በ‹‹ሌላሰው›› መፅሐፉ እንደሚገልፀው ‹‹ማድረግም አለማድረግም›› ኪሳራ ሆኗል፡፡ በብዙ ነገር ረፍዶብናል፡፡ የያዘን አዚም በቀላሉ የሚለቀን አይደለም፡፡

ዓለማየሁ ገላጋይ ‹‹የተጠላው እንዳልተጠላ›› መፅሐፉ ገፅ 81 ላይ፡

‹‹የማትችለውን ዓለም በሰልፍ የምትኳኳነው፤ የምትችለውን ዓለም ባለመገንባትህ ነው፡፡›› ይላል፡፡

ልክ ነው! አዎ ዓለማችንን ተሰርቀናል፡፡ የእኛ ባልሆነ ዓለም ውስጥ ነው እየተንገላታን ያለነው፡፡ ሌሎች ባዋቀሩት የዓለም ስርዓት ውሰጥ ስለምንኖር ነው ኑሯችን የማይመች፣ ሕይወታችን መከራ ብቻ የሆነው፡፡ በልካችን የተሰፋ ርዕዮት ዓለም ስለሌለን ገልብጠን ያመጣነው ስትራተጂና ፖሊሲ ሱሪ ባንገት ሆኖብናል፡፡ ለህዝባችን የሚሆን፣ እንደሐገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ሊያዋጣን የሚችል ስርዓት የለንም፡፡ መልካሙን የአባቶቻችንን ጥበብ ጥለነዋል፡፡ እኛነታችንን ንቀነዋል፡፡ የእኛ ባልሆነው የባዕድ ጌጣጌጥ ተማርከናል፡፡ በሰው ጥበብ ለማጌጥ እላይ ታች እንላለን፡፡ ምክንያቱም አሳቢ ሰው አጥተናል፡፡ ተመራምሮ አዲስ መንገድ የሚያሳየን ለራሱም ለወገኑም የሚተርፍ ዜጋ ተቸግረናል፡፡ ተማርኩኝ የሚለውም ለሆዱ ብቻ እንጂ ለገዛ ራሱ ነፍስ እንኳን አልተረፈም፤ እውቀቱ ከአንገት በታች ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ.... ንጉስ ሰለሞን ‹‹ልጄ ሆይ...... ከሕዝብ ጋር አትሂድ!›› የሚልህ ከህዝብህ ተለይተህ ጥፋ ለማለት ሳይሆን ለሕዝብህ የሚሆን መፍትሄ ታበጅ ዘንድ ከመንጋው ተለይተህ አስብ እያለህ ነው፡፡ ከህዝብ ጋር ሙሉ ጊዜህን የምታጠፋ ከሆነ የምታስብበት ጊዜ አይኖርህም፡፡ ህዝብ በተፈጥሮው በወል ነው የሚያስበው፡፡ አይመረምርም፣ አይፈትንም፣ የተቀበለውን መስጠት እንጂ አዲስ የሕይወት መንገድ አይቀርፅም፡፡ ህዝብን የምትከተል ከሆነ ለራስህም፣ ለሐገርህም አትሆንም፡፡ ማሰላሰያ፣ ማገናዘቢያ፣ ራስህንም ዓለሙንም ማንበቢያ ጊዜ ከሌለህ ራስህን ዘንግተህ ያንተ ባልሆነው የሌሎች ዓለም ስደተኛ ነው የምትሆነው፡፡ መንጋው ያንጋጋሃል!

ወዳጄ ሆይ.. ወዳጅነት መልካም ነው፤ ዝምድና አይከፋም፣ አብሮአደግነት ደግ ነገር ነው፤ ባልንጀርነት ደስ ይላል፡፡ ነገር ግን የማሰቢያህን ጊዜ የሚሻማ ማንኛውም የማህበራዊ ግንኙነት ሁሉ ዘለቄታዊ ጥቅም አይሰጥህም፡፡ ሰዎች በዘልማድ ባሰመሩት የአኗኗር መስመር ብቻ መሄድ የሚያስገኘው አንዳች ነገር የለም፡፡ የብዙዎቻችን ሕይወት አሰልቺ እየሆነ የመጣው በድግግሞሽ ህይወት ውስጥ ስለምንመላለስ ነው፡፡ ኑሯችን አዙሪት የሆነው በሰጡን ርዕዮት ዓለም፣ ባቀበሉን የአኗኗር ዘይቤ ስለምንጓዝ ነው፡፡

የራሳችን መንገድ የሌለን የማሰቢያ ጊዜ ስላጣን ነው፡፡ የተወጠርንበትና የተጠመድንበት ነገር ሁሉ የሚያለማን ሳይሆን የሚያጠፋን ነው፡፡ በራሳችን መንገድ ካላሰብን የትም አንደርስም፡፡ እንዲሁ የኋሊት እንምዘገዘጋለን፡፡ ህዝብነት አያተርፍም፤ መንጋነት በራስህ እንዳትተማመን ያደርግሃል፡፡ ለህዝብ መቆም እንጂ ከህዝብ ጋር መሄድ የተለየ ውጤት አያስገኝም፡፡ ለህዝብህ ጠብ የሚል መፍትሄ አምጠህ የምትወልደው ከመንጋው ተነጥለህ ማሰብ ስትችል ብቻ ነው፡፡ መነጠልህ እስመጨረሻው የሚለይህ ሳይሆን ህዝብህን መልሶ እንዲጠቅም የሚያደርግ ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ.... ምርጫዎችህን ለመምረጥ፣ የሕይወት መንገድህን ለመቀየስ፣ መነሻህን አሳምረህ ፍጻሜህን ለማስዋብ አንተ አንተን ሆነህ መገኘት አለብህ፡፡ ለራስህ የማታውቅ ከሆነ ሌሎች ባወቁትና በቀረፁት መንገድ ትከተላለህ እንጂ ራስህን አትመራም፡፡ ስታስብ፣ ስትመረምር፣ ስታሰላስል፣ ስታስተውል፣ አዲስ ሃሳብ ስትፈጥር ግን ችግሮችህን ትቀርፋለህ፣ መሰናክሎችህን ትሻገራለህ፣ ስልጣኔን ታመጣለህ፡፡ ራስህን ከሌሎች ባርነት ነፃ ታወጣለህ፡፡

አልያ ግን በመንጋው ተጠልፈህ በራስህ መንገድ ትመላለስ ዘንድ እንዳትችል አቅም ታጣለህ፡፡ ተከታይነት በራስህ ፀንተህ ለመቆም ሃይል እንዳይኖርህ ያደርግሃል፡፡ ተጎታች እንጂ መሪ አትሆንም፤ ጠባቂ እንጂ ሰጪ ትሆን ዘንድ አትችልም፡፡ የሰው ዓለም መፃተኛ እንጂ የራስህ ዓለም ሰሪ ለመሆን አይቻልህም፡፡ በተኮረጀ ሕይወት ዘመንንህን ትጨርሳለህ፡፡

ባለመድሐኒት ሆይ....
ራስህን አድን!
ራስህን


ል!
አንተነትህን
ቀ-ጥ-ል፣
እስትንፋስህን ቀ-ጣ-ጥ-ል፡፡

ቸር ቅጥ’ለት! ደግ ንጥ’ለት!

ፀሐፊው:- እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

ፅሁፉን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👇 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8nJBMFWRApy&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
Forwarded from የላቀ እይታ
ላሚኒ ያማል ይባላል። ከሞሮኳዊ አባትና ከኢኳቶሪያል ጊኒ ከምትገኝ እናት በስፔን የተወለደው ይህ የመጭው ዘመን ኮከብ በ16 አመቱ ለብሄራዊ ቡድን ተሰልፎ በአውሮፓ ዋንጫ ላይ የተጫወተ በእድሜ ትንሹ ተጫዋች በሚል ሪከርድ ተመዝግቦለታል።

ላሚኒ ከእግር ኳስ ተጫዋችነቱ ሌላ ተማሪም ነው። በአንድ ጎን ኳሱን እየተጫወተ ወደማረፊያው ሲሄድ ደግሞ ደብተሩን ገልጦ ያነባል።

ይህ ከላይ የምታዩት ምስል ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያው ቫይራል የሆነ ሲሆን ሀገሩ ስፔንን ወክሎ ለመሳተፍ በሄደበት በጀርመን ባረፈበት የሆቴል ክፍል ውስጥ ሰሞኑን ለሚወስደው ፈተና ለመዘጋጀት በማጥናት ላይ እያለ በጓደኞቹ ተነስቶ የተለቀቀ ምስል ነው።

ይህ የ16 አመት የልጅ ሀብታም ከባርሴሎና ጋር ለሶስት አመታት ተፈራርሞ ከሚያገኘው 5,010,000 ዩሮ ሌላ በየሳምንቱ 32,115 ዩሮ ለኪሱ ይከፈለዋል።

አይደለም እራሱ ሀብታም እየሆነ ያለ ልጅ ይቅርና የሀብታም ልጅ ስለሆነ ብቻ ማጥናት እንደሌለበት የሚያስብ ብዙ ሰው ባለበት በዚህ ወቅት የዚህ ልጅ ለትምህርቱ በዚህ ደረጃ ትኩረት መስጠቱ ብዙዎችን አስገርሟል።

የሃገራችን ወጣቶች ከዚህ ልጅ መማር ይችሉ ዘንድ ይህን #post #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ።

@ Wasihune Tesfaye
Forwarded from የላቀ እይታ
ስሙ Sylvester Stallone ይባላል። አንጋፋ እና በጣም ታዋቂ ከሆኑት የአሜሪካ የፊልም ኮከቦች አንዱ ነው፡፡

በአንድ ወቅት እጅግ በጣም ችግር ውስጥ ከመሆኑ የተነሳ ቤት አልባ የነበረ ሲሆን በኒውዮርክ አውቶቡስ ጣቢያ ለ 3 ቀናት ተኝቷል፡፡ ኪራይ ለመክፈል ወይም ምግብ ለመግዛት አቅም ስላልነበረው እጅግ የሚወደው ውሻውን በ50 ዶላር ብቻ ሸጠው፡፡

በአጋጠመው ችግር ምክንያት ውሻውን ከሸጠ ከሁለት ሳምንት በኋላ ግን የህይወቱን አቅጣጫ የቀየረ አንድ ክስተት ተከሰተ። በMohammed Ali እና Chuck Wepner መካከል የቦክስ ውድድርን ይመለከታል። ይህ ግጥሚያም ROCKY በመባል የሚታወቀውን ታዋቂ የፊልም ስክሪፕቱን ለመጻፍ መነሳሳትን ሰጠው፡፡

የፊልም እስክሪፕቱንም የጻፈው በ20 ሰዓታት ውስጥ ነበር! ይህን ስክሪፕትም በ 35,000 ዶላር ሲሸጠው በእሱ ጥያቄ መሠረትም በፊልሙ ውስጥ እሱ ራሱ Rockyን ሆኖ ዋና ተዋናይ ለመሆን ቻለ፡፡

ይህ ፊልምም በታዋቂው የኦስካር ሽልማት ውድድር ምርጥ የምስል ፣ ምርጥ የዳይሬክቲንግ እና ምርጥ የፊልም ኤዲቲንግ አሸነፈ፡፡ በምርጥ ተዋንያንነትም ታጭቷል! ፊልሙ Rocky በአሜሪካ ብሔራዊ ፊልም መዝገብ ውስጥ ከመቼውም ጊዜ ታላላቅ ፊልሞች መካከል አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል!

በመጨረሻም፤ ከእስክሪፕት ሽያጭ ባገኘው የ35,000 ዶላር የገዛውን የመጀመሪያውን ነገር ታውቃለህ?
የሸጠውን ውሻ ነበር መልሶ የገዛው።

አዎ Stallone በመቸገሩ ምክንያት ብቻ የሸጠውን ውሻውን በጣም ስለሚወደው የሸጠለትን ሰው እየጠበቀ ለ 3 ቀናት በሸጠበት ቦታ ላይ ቆሞ ነበር፡፡ በመጨረሻም ሰውዬውን ከውሻው ጋር አገኘው። በ 50 ዶላር ብቻ የሸጠውን ያው ውሻ 3,000 ዶላር በመክፈል ማስመለስ ቻለ!
ሌላው ታሪክ ነው!

ወዳጄ ያለ ትግል ምንም ነገር አታገኝም!

በህይወትህ ውስጥ የተለያዩ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ ነገር ግን ችግሮችህን መቀረፍ እንደማይችሉ ድክመትህ ከወሰድካቸው በጭራሽ ሊሳካልህ አይችልም። እናም ችግሮችህን ጥንካሬህን የምታወጣባቸው እድሎች ካደረካቸው በህይወት ውስጥ ምንም ልታገኘው የማትችለው ነገር የለም።

@ https://www.tg-me.com/higher_perspective_page
2024/06/26 03:29:20
Back to Top
HTML Embed Code: