Telegram Web Link
━━━━✦🌹🌹✦━━━━
​​🔆 እንቋዕ አብጽሐክሙ አብጽሐክን ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወክልዔቱ ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤ በሰላም በፍቅር ወበጥዒና።

ሠናይ በዓል ይኩን ለኲልክሙ ሕዝበ ክርስቲያን!


“እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፳፻፲፪(2012) ዓመተ ምሕረት የትንሣኤ በዓል በሰላም በፍቅርና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።"

ለሁሉም የክርስቲያን ሕዝብ መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁን

━━━━✦🌹🌹✦━━━━


🔆 ከአማርኛ ወደ ግእዝ ቋንቋ ሲተረጎሙ

እንኳን አደረሰኸ ➜ እንቋዕ አብጽሐከ

እንኳን አደረሰሽ ➜ እንቋዕ አብጽሐኪ

እንኳን አደረሳችሁ ➜ እንቋዕ አብጽሐክሙ

እንኳን አደረሰን ➜ እንቋዕ አብጽሐነ

እንኳን አብሮ አደረሰን ➜ እንቋዕ ኀቢሮ አብጽሐነ

መልካም የትንሣኤ በዓል ➜ ሠናይ በዓለ ትንሣኤ

መልካም በዓል ➜ ሠናይ በዓል


━━━━✦🌹🌹✦━━━━

🔆 የቃሎች ትክክለኛ አጻጻፍ

❗️በአል - የጣዖት ስም
በዓል - የሚከበር ቀን

❗️አመት - አገልጋይ
ዓመት - ዘመን

❗️ትንሳኤ
ትንሣኤ - መነሣት

❗️ሠላም
ሰላም - ሰላም

❗️መሀረ - አስተማረ
መሐረ - (ምሕረት) ➜ ይቅር አለ (ይቅርታ)
ዓመተ ምሕረት - የይቅርታ ዘመን



🌸 መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
━━━━✦🌹🌹✦━━━━
🔆 ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን
➠(ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ)

✿ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
➠(በገናና ኃይልና ሥልጣን)

🔆 አሠሮ ለሰይጣን
➠(ሰይጣንን አሠረው)

✿ አግዓዞ ለአዳም
➠(አዳምን ነጻ አወጣው)

🔆 ሰላም
➠(ፍቅር አንድነት ሆነ)

✿ እምይእዜሰ
➠(ከእንግዲህስ)

🔆 ኮነ
➠(ሆነ)

✿ ፍሥሐ ወሰላም።
➠(ደስታ እና ሰላም)


✏️ መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ትርጉሙን ለሌሎች ያስተምሩ!
#Share ያድርጉት...
​ሰላም ለኵልክሙ 🙌 ሰላም ለእናንተ ይሁን


🦠 ብዙዎቻችን በኮሮና ወረርሺኝ ምክንያት ቤታችን እንድንውል ተገደናል። በዚህም ምክንያት ቤታችን ውስጥ ብዙ ሥራዎችን ለመሥራት ዕድል ተመቻችቶልናል 🦠

✿ ከዚህ በፊት ግእዝ ቋንቋን መማር እና ማወቅ ለሚያስቡ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካላቸው ለቀሩ ፤ እንዲሁም ዕድሉን ላጡ ሰዎች የሚሆን መሠረታዊ የግእዝ ቋንቋ ትምህርት የሚሰጥበት ቻናል እንዳለ ያውቃሉ?
• በአገኘነው በዚህ ዕድል ይህን ቻናል በመቀላቀል መሠረታዊ የሆኑ የግእዝ ቋንቋ ትምህሮቶችን መጀመር ይችላሉ።




●ይህን ይንኩ
Open Here
አርሃው ዘንተ
https://www.tg-me.com/learnGeez1


🏠 ቤታችን ውስጥ እንቀመጥ
#ንንበር_ውስተ_ቤትነ
🧼 እጃቸንን እንታጠብ
#ንትሐጸብ_እደዊነ
👫 ርቀታችንን እንጠብቅ
#ንዕቀብ_ርኁቀነ
📖 ተግታችሁ ጸልዩ
#ትግሁ_ወጸልዩ

🕊ሰላመ እግዚአብሔር ይኩን ምስለ ኲልክሙ
🗣 ሌሎችም ሰዎች እንዲደርሳቸው ይህን መልእክት #Share ያድርጉት...
https://www.tg-me.com/learnGeez1
🚑 በእንተ ሕክምና | ስለ ሕክምና


ሐከመ ➜ አከመ
ሐኪም ➜ አካሚ
ዐቢይ ሐኪም ➜ ዋና ዶክተር
ቤተ ሕክምና ➜ ሆስፒታል
ቤተ ሆሣዕና ➜ መድኃኒት ቤት
ክፍለ ሐተታ ➜ የምርመራ ክፍል

ማህምም ➜ አስታማሚ
ሐመ ➜ ታመመ
ሕሙም ➜ በሽተኛ
ሕሙማን ➜ በሽተኞች
ደዌ ➜ በሽታ


🔸መሠረተ ግእዝ

@learnGeez1 @learnGeez1
━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━
🚑 በእንተ ሕክምና | ስለ ሕክምና


ሐከመ ➜ አከመ
ሐኪም ➜ አካሚ
ዐቢይ ሐኪም ➜ ዋና ዶክተር
ቤተ ሕክምና ➜ ሆስፒታል
ቤተ ሆሣዕና ➜ መድኃኒት ቤት
ክፍለ ሐተታ ➜ የምርመራ ክፍል

ማህምም ➜ አስታማሚ
ሐመ ➜ ታመመ
ሕሙም ➜ በሽተኛ
ሕሙማን ➜ በሽተኞች
ደዌ ➜ በሽታ


🔸መሠረተ ግእዝ

@learnGeez1 @learnGeez1
━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━
━━━━✦🌹🌹✦━━━━

አርእስተ ክፍል ዘእርባ ቅምር።
መጀመሪያ ታላቅ ክፍል ።
እርባ ቅምር።

እርባ ቅምር የሚሉ እርባ ቅምር የሚባሉ በሃያ ስምንት ክፍል ይከፈላሉ እርሳቸውም እሊህ ናቸው።
. መራኁት ።
. አርእስት ።
. ሠራዊት ።
. አዕማድ ።
. አሥራው ።
. ፀዋትው ።
. ዐቢይ አንቀጽ ።
. ንዑስ አንቀጽ ።
. ደቂቅ ።
. ባዕድ ቅጽል ።
. መራሕያን ።
. ሳቢ ዘር ።
. ልማድ ።
. ባዕድ ዘር ።
. ሕርመት ።
. ዝርዝር ቅጽል ።
. ገዳፍያነ ዘመድ ።
. ወሳክያነ ባዕድ ።
. ቱሱሓን ።
. ተጻማሪ ።
. ስንዕው ።
. ሠጋርያን ።
. ወላጤ ግዕዝ ።
. ምዕላድ ።
. አላህላህያን ።
. ወኀጥያን ።
. ተመኲሳይያን ።
. ዝርው ።

ይቀጥላል......


ሼር በማድረግ መረጃውን በመለው አለም ተደራሽነቱን እናስፋ:: የግእዝ ቀደምት ቋንቋችን አይሞትም!!!


👇👇🏻👇🏼👇🏽👇🏾👇🏿👇
https://www.tg-me.com/learnGeez1
https://www.tg-me.com/learnGeez1
ክፍል ፩ መራኁት ።

መራኁት የተባሉ አምስት ናቸው እርሳቸውም የግሥ መነሻ የአርእስትና የሠራዊት በር ከፋቾች የሚሆኑ ቀለማት ግዕዝ ራብዕ ኃምስ ሳድስ ሳብዕ ናቸው። ግሥ ሁሉ በነዚህ ባምስቱ እንጂ በካዕብና በሣልስ ሲነሣ አይገኝም የግሥ ሁሉ መነሻዎችና በር ከፋቾች ስለሆኑ ስለዚህ መራኁት ይባላሉ። መርኆ መክፈቻ ሲያበዛ መራኁት መክፈቻዎች ይላል።

ግሥ በግዕዝ ሲነሣ ሐለመ፤ ከፈለ፤ አእመረ፤ ተንበለ።

በራብዕ ሲነሣ ባረከ፤ ሣረረ፤ ፃዕደወ።

በኀምስ ሲነሣ ሤመ፤ ኄለ፤ ዔለ።

በሳድስ ሲነሣ ብህለ፤ ንህለ፤ ብዕለ።

በሳብዕ ሲነሣ ቆመ፤ ሖረ፤ ጾመ፤ ሆከ ይህን የመሰለ ሁሉ ነው።

ከነዚህ በቀር ግሥ ሁሉ በካዕብና በሣልስ አይነሳም። መድረሻው ወይም መጨረሻው የግሥ ሁሉ ግዕዝ ብቻ ነው። በካዕብ በሣልስ በራብዕ በኀምስ በሳድስ በሳብዕ አይጨርስም። በዚህ እንዳይጨርስ አሁን በተቆጠሩት ግሦች አስተውል። ነባር ግን በግዕዝ በካዕብ በሣልስ በራብዕ በኀምስ በሳድስ በሳብዕ በሰባቱ ፊደላት ሁሉ ይነሣል እንዲሁም በሰባቱ ፊደላት ይጨርሳል። ይህም ከመ፤ እስመ፤ ለሊሁ፤ ቁፋሂ፤ ሣሩሃ፤ በሃ፤ መድሔ፤ ሰዳሔ፤ ለውህ፤ ቅንጽራሆ። ተጽራሕ፤ ቱፋሕ፤ ታእኅ፤ ቴቁሔ፤ ትግቶ፤ ቶማስ፤ ሲህ ማለቱን ያሳያል።

ይቀጥላል......

👇👇🏻👇🏼👇🏽👇🏾👇🏿👇
https://www.tg-me.com/learnGeez1
📖 መዝገበ ቃላት ፍቺ

• አንቆቅሖ ፦ እንቁላል


#መዝገበቃላት_ፍቺ #ስም
📖 www.tg-me.com/learnGeez1
📖 መዝገበ ቃላት ፍቺ

• ዐውድ ፦ አዋጅ
ዖደ ፦ አወጀ

ምሳሌ

ዐውደ ምሕረት (የምሕረት አደባባይ)
ቃለ ዐዋዲ (አዋጅ ነጋሪ)

#መዝገበቃላት_ፍቺ #ግስ
📖 www.tg-me.com/learnGeez1
📜 ዓረፍተ ነገር በግእዝ
ክፍል ፪


◦አበበ ወደ ጤና ጣቢያ ሄደ
አበበ ሖረ ኀበ ቤተ ጥዒና።

◦ቡሩክ እንቁላል በላ
ቡሩክ በልዐ አንቆቅሖ።

◦ልጅህን ወደ እኔ ላከው
ፈኑ ወልድከ ኀቤየ።

◦መልካም ሥራን ሥራ
ግበር ሠናየ ምግባር።

◦እናትና አባትህን አክብር
አክብር አቡከ ወእምከ።

◦ከወንድምህ ጋር ተኛ
ኑም ምስለ እኁከ።

◦አንዴት ነህ
እፎ አንተ።

◦የእኔ ቤት ሩቅ ነው
ቤትየ ሊተ ርኁቅ ውእቱ።

◦መልካም ቀን
ሠናይ መዓልት።

ሸር ያድርጉ እባክዎት
📜📜📜📜📜📜📜📜
#ዓረፍተ_ነገር
📜 መሠረተ ግእዝ 📜
@learnGeez1
tensae geez.pdf
6.7 MB
📚 ትንሣኤ ግእዝ
• መምህር ደሴ
የገጽ ብዛት፦ ፫፻፲፰(318)


#መጽሐፍ ○ መሠረተ ግእዝ

@learnGeez1_Bot

Telegram.me/learnGeez1
መዝገበ ቃላት (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ).pdf
57.3 MB
📚 ግእዝ➧ዐማርኛ መዝገበ ቃላት
• አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ

#መጽሐፍ #መዝገበቃላት
57.3MB ዋይፋይ/package ይጠቀሙ
○ መሠረተ ግእዝ
@learnGeez1_Bot
Telegram.me/learnGeez1

~~~~ሼር~~~~
መሠረተ ግእዝ pinned «መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ 🔸የግእዝ ቋንቋ ታሪክና አመጣጥ ክፍል ፩(1) ቋንቋ ማለት መግባቢያ ማለት ነው ፡፡ የግእዝ ቋንቋ አመጣጥ ከአንዳንድ ቀደምት የታሪክ ጸሓፊዎችና የግእዝ ቋንቋ መጻሕፍትን ጽፈው ካስረከቡን ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶችና የቋንቋው ባለቤቶች እንደምንረዳው፦ የግእዝ ቋንቋ አመጣጥ በኢትዮጵያ መነሻ ሊሆነን የሚችለው ክርስቶስ ከመወለዱ ከ800 ዓመት ጀምሮ ነገደ ሴም (የሴም…»
Forwarded from መሠረተ ግእዝ
🔆 ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን
➠(ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ)

✿ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
➠(በገናና ኃይልና ሥልጣን)

🔆 አሠሮ ለሰይጣን
➠(ሰይጣንን አሠረው)

✿ አግዓዞ ለአዳም
➠(አዳምን ነጻ አወጣው)

🔆 ሰላም
➠(ፍቅር አንድነት ሆነ)

✿ እምይእዜሰ
➠(ከእንግዲህስ)

🔆 ኮነ
➠(ሆነ)

✿ ፍሥሐ ወሰላም።
➠(ደስታ እና ሰላም)


✏️ መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ትርጉሙን ለሌሎች ያስተምሩ!
#Share ያድርጉት...
Forwarded from መሠረተ ግእዝ
🟣 መስተዋድዳን ቃላት (Prepositions)

ክፍል ፩

• ኃበ ➾ ወደ
• መንገለ ➾ ወደ

• ኃቤሁ ➾ ወደሱ
• ኃቤሃ ➾ ወደሷ
• ኃቤሆሙ ➾ ወደነሱ
• ኃቤሆን ➾ ወደነሱ (ለሴቶች)

• ኃቤከ ➾ ወደ አንተ
• ኃቤኪ ➾ ወደ አንቺ
• ኃቤክሙ ➾ ወደ እናንተ
• ኃቤክን ➾ ወደ እናንተ (ለሴቶች)

• ኃቤየ ➾ ወደኔ
• ኃቤነ ➾ ወደኛ

ምሳሌ

➜ ንዒ ኃቤየ
(ነይ ወደኔ)
➜ ሖረ ኃቤሁ
(ወደሱ ሄደ)
➜ ዮም ሖርኩ ኃበ ቤተ ክርስቲያን
(ዛሬ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄድኩ)
➜ ከልብ መጽአ ኃቤነ
(ወደኛ ውሻ መጣ)
➜ ጌሠም እመጽእ ኃቤክሙ
(ነገ ወደ እናንተ እመጣለው)


🔸 መሠረተ ግእዝ 🔸
@learnGeez1
​​🟣 መስተዋድዳን ቃላት (Prepositions)

ክፍል ፪ (2)


• ምስሌሁ ➾ ከእሱ ጋር
• ምስሌሃ ➾ ከእሷ ጋር

• ምስሌሆሙ ➾ ከእነሱ ጋር
• ምስሌሆን ➾ ከእነሱ ጋር (ለሴት)
• ምስሌከ ➾ ከአንተ ጋር
• ምስሌኪ ➾ ከአንቺ ጋር

• ምስሌክሙ ➾ ከእናንተ ጋር
• ምስሌክን ➾ ከእናንተ ጋር (ለሴት)
• ምስሌየ ➾ ከእኔ ጋር
• ምስሌነ ➾ ከእኛ ጋር

ምሳሌ

➜ ንዒ ምስሌየ
(ነይ ከእኔ ጋር)
➜ ሖረ ምስሌሆሙ
(ከእነሱ ጋር ሄደ)
➜ ዮም ሖርኩ ምስሌሁ ኀበ ቤተ ክርስቲያን
(ዛሬ ወደ ቤተ ክርስቲያን ከእሱ ጋር ሄድኩ)
➜ ጌሠም እመጽእ ምስሌኪ
(ነገ ከአንቺ ጋር እመጣለው)


#መስተዋድዳን_ቃሎች
🔸 መሠረተ ፡ ግእዝ 🔸
@learnGeez1
​​​🟣 መስተዋድዳን ቃላት (Prepositions)

ክፍል ፫ (3)


ውስተ ➠ ውስጥ (In)


• ውስቴቱ ➾ በውስጡ
• ውስቴታ ➾ በውስጧ

• ውስቴቶሙ ➾ በውስጣቸው
• ውስቴቶን ➾ በውስጣቸው(ለሴት)
• ውስቴትከ ➾ በውስጥህ
• ውስቴትኪ ➾ በውስጥሽ

• ውስቴትክሙ ➾ በውስጥአችሁ
• ውስቴትክን ➾ በውስጣችሁ (ለሴት)
• ውስቴትየ ➾ በውስጤ
• ውስቴትነ ➾ በውስጣችን

ምሳሌ

➜ ዮም ኀደርነ ውስተ ቤትነ።
(ዛሬ ቤታችን ውስጥ አደርን)
➜ አልቦ ሰብእ ውስተ ቤተ ክርስቲያን።
(ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰው የለም)
➜ ዘምሩ ውስቴትክሙ።
(በውስጣችሁ አመስግኑ)
➜ አቤል ነበረ ውስተ ሐመር።
(አቤል መርከብ ውስጥ ተቀመጠ)


#መስተዋድዳን_ቃሎች
🔸 መሠረተ ፡ ግእዝ 🔸
@learnGeez1
​​​🟣 መስተዋድዳን ቃላት (Prepositions)

ክፍል ፬ (4)


ቅድመ ➠ ፊት / በፊት(Before)


• ቅድሜሁ ➾ በፊቱ/ከፊቱ
• ቅድሜሃ ➾ በፊቷ/ከፊቷ

• ቅድሜሆሙ ➾ ከፊታቸው
• ቅድሜክን ➾ ከፊታቸው(ለሴት)
• ቅድሜከ ➾ ከፊትህ
• ቅድሜኪ ➾ ከፊትሽ

• ቅድሜክክሙ ➾ ከፊታችሁ
• ቅድሜክን ➾ ከፊታችሁ (ለሴት)
• ቅድሜየ ➾ ከፊቴ
• ቅድሜነ ➾ ከፊታችን

ምሳሌ

➜ ሑር ፡ ቅድሜየ።
(ከፊቴ ሂድ)
➜ ሄኖክ ፡ ውእቱ ፡ ቅድሜነ።
(ሄኖክ ከፊታችን ነው)
➜ መጻእኩ ፡ ቅድሜከ።
(ከፊትኸ መጣሁ)
➜ ቅድመ ፡ ልደተ ፡ ክርስቶስ።
(ከክርስቶስ ልደት በፊት)


#መስተዋድዳን_ቃሎች
🔸 መሠረተ ፡ ግእዝ 🔸
@learnGeez1
geezbook-1z.pdf
1.7 MB
Join @learnGeez1

መልክትዎን ያድርሱን👇

@LearnGeez1_Bot
2024/10/03 00:30:11
Back to Top
HTML Embed Code: