Telegram Web Link
🔶 ​ምዕራፍ ፫ (3)

⚪️ ግስ ( Verb )

ክፍል ፩


+ አርእስተ ግስ (Root Verbs)

አርእስተ ግስ ማለት የግስ አለቆች ማለት ሲሆን ብዛታቸው ስምንት ነው ፡፡

እሉኒ (እነሱም)

• ➾ ቀተለ = ገደለ

• ➾ ቀደሰ = አመሰገነ

• ➾ ገብረ = ሠራ

• ➾ አእመረ = አወቀ

• ➾ ባረከ = ባረከ

• ➾ ሤመ = ሾመ

• ➾ ብህለ = አለ

• ➾ ቆመ = ቆመ

ተጨማሪ

• ➾ ዴገነ = ተከተለ
• ➾ ማህረከ = ማረከ
• ➾ ደንገፀ = ደነገጠ
• ➾ ኖለወ = ጠበቀ


#ግስ #ግሶች #መጀመሪያ
◽️ መ ሠ ረ ተ • ግ እ ዝ ◽️
@learnGeez1
​​​⚪️ ግስ ( Verb )

ክፍል ፬


+ አርእስተ ግስ (Root Verbs)

፫. ገብረ ➾ ሠራ

- ላልቶ ይነበባል ፡፡
- ሦስት ፈደላት ብቻ አሉት ፡፡
- መነሻው ፊደል ግእዝ ነው ፡፡
- መሀከል ያለው ፊደል ሳድስ ነው ፡፡

ገ = ግእዝ
ብ = ሳድስ
ረ = ግእዝ

➜ የገብረ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ከብረ = ከበረ
• ➾ አምነ = አመነ
• ➾ መጽአ = መጣ
• ➾ ሰምዐ = ሰማ


• ➾ ወድቀ = ወደቀ
• ➾ ሰክረ = ሰከረ
• ➾ ለብሰ = ለበሰ
• ➾ መስየ = መሸ
• ➾ ከርመ = ከረመ


• ➾ ደክመ = ደከመ
• ➾ ቀርበ = ቀረበ
• ➾ ቀድሐ = ቀዳ
• ➾ ነግሠ = ነገሠ
• ➾ ሰፍሐ = ሰፋ


#የገብረ_ግሶች #ግስ #ግሶች
◽️ መ ሠ ረ ተ • ግ እ ዝ ◽️
@learnGeez1
​​⚪️ ግስ ( Verb )

ክፍል ፭


+ አርእስተ ግስ (Root Verbs)

፬. ተንበለ ➾ ለመነ

- ላልቶ ይነበባል ፡፡
- አራትና ከዚያ በላይ ፈደላት አሉት ፡፡
- መነሻው ፊደል ግእዝ ነው ፡፡
- መኸከለኛው ፊደሉ ሳድስ ና ግእዝ አሉት ፡፡

ተ = ግእዝ
ን = ሳድስ
በ = ግእዝ
ለ = ግእዝ

➜ የተንበለ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ሐንከሰ = አከማቸ
• ➾ አድለወ = አደላ
• ➾ አወፈየ = ሰጠ
• ➾ ሰንበተ = አከበረ

• ➾ አመድበለ = አከማቸ
• ➾ አመስጠረ = አራቀቀ
• ➾ ገልገለ = ገላገለ
• ➾ ደምሰሰ = አጠፋ



፭. ባረከ ➾ ባረከ

- ሦስትና ከዚያ በላይ ፊደላት አሉት
- ላልቶ ይነበባል ፡፡
- መነሻ ፊደሉ ራብዕ ነው ፡፡

ባ = ራብዕ
ረ = ግእዝ
ከ = ግእዝ

የባረከ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ሣረረ = ሠራ
• ➾ ፃመወ = ደከመ
• ➾ ማህረከ = ማረከ

• ➾ ባረወ = ቆፈረ
• ➾ ቃነየ = ደረደረ
• ➾ ሣቀየ = አናወጠ



፮. ክህለ ➾ ቻለ

- ሦስትና ፊደላት አሉት
- ላልቶ ይነበባል ፡፡
- መነሻ ፊደሉ ሳድስ ነው ፡፡

የክህለ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ርእየ = አየ
• ➾ ልህቀ = አደገ
• ➾ ብህለ = አለ
• ➾ ርሕቀ = ራቀ
• ➾ ጥዕመ = ቀመሰ
• ➾ ንዕደ = አማረ



#የተንበለ_ግሶች
#የክህለ_ግሶች
#የባረከ_ግሶች #ግስ #ግሶች
◽️ መ ሠ ረ ተ • ግ እ ዝ ◽️
@learnGeez1
​​​⚪️ ግስ ( Verb )

ክፍል ፮


+ አርእስተ ግስ (Root Verbs)

፯. ዴገነ ➾ ተከተለ

- ላልቶ ይነበባል ፡፡
- ሦስትና ከዚያ በላይ ፈደላት አሉት ፡፡
- መነሻው ፊደል ኃምስ ነው ፡፡

ዴ = ኃምስ
ገ = ሳድስ
ነ = ግእዝ

➜ የዴገነ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ዜነወ = ነገረ
• ➾ ጼነወ = ሸተተ
• ➾ ሌወወ = ጠመጠመ
• ➾ ጤገነ = ጣደ
• ➾ ፄወወ = ማረከ
• ➾ ቴፈነ = ገረፈ



፰. ጦመረ ➾ ጻፈ

- ላልቶ ይነበባል ፡፡
- ሦስትና ከዚያ በላይ ፈደላት አሉት ፡፡
- መነሻው ፊደል (ሳብዕ) መጨረሻ ፊደል ነው ፡፡

ጦ = ሳብዕ
መ = ግእዝ
ረ = ግእዝ

➜ የጦመረ ቤት ለምሳሌ

• ➾ ሞጥሐ = ለበሰ
• ➾ ሞቅሐ = አሰረ
• ➾ ሎለወ = ጠበሰ
• ➾ ኖተወ = ዋጠ
• ➾ ሞፈደ = ጫረ
• ➾ ሞገደ = አወከ


#የዴገነ #የጦመረ_ግሶች #ግስ #ግሶች
◽️ መ ሠ ረ ተ • ግ እ ዝ ◽️
@learnGeez1
መሠረተ ግእዝ pinned «መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ 🔸የግእዝ ቋንቋ ታሪክና አመጣጥ ክፍል ፩(1) ቋንቋ ማለት መግባቢያ ማለት ነው ፡፡ የግእዝ ቋንቋ አመጣጥ ከአንዳንድ ቀደምት የታሪክ ጸሓፊዎችና የግእዝ ቋንቋ መጻሕፍትን ጽፈው ካስረከቡን ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶችና የቋንቋው ባለቤቶች እንደምንረዳው፦ የግእዝ ቋንቋ አመጣጥ በኢትዮጵያ መነሻ ሊሆነን የሚችለው ክርስቶስ ከመወለዱ ከ800 ዓመት ጀምሮ ነገደ ሴም (የሴም…»
ከአባቶች ጋር አብረን በቲቪ ለመፀለይ ይረዳናል
ለወዳጅዎም ይፀልዩበት ዘንድ
#ሼር ያርጉላቸው
💚 @kukuha_haymanot 💚
💛 @kukuha_haymanot 💛
❤️ @kukuha_haymanot ❤️
🗣 ንግግር (ቃለ ምልልስ)


👨🏽 ጥዒና የሀብልየ።
(ጤና ይስጥልኝ)
👨‍🦱 ለኲልነ።
(ለሁላችን)

👨🏽 አይቴ ተሐውር?
(የት ትሄዳለህ)
👨‍🦱 ኀበ ቤተ መጽሐፍት።
(ወደ ቤተመጽሐፍት)

👨🏽 ምስለ መኑ?
(ከማን ጋር)
👨‍🦱 ምስለ ቢጽየ።
(ከጋደኛዬ ጋር)

👨🏽 ትምህርት እፎ ውእቱ?
(ትምህርት እንዴት ነው)
👨‍🦱 ሠናይ ውእቱ።
(ጥሩ ነው)


👨🏽 ድኅረ ቤተ መጻሕፍት አይቴ ውእቱ ዘተሐውር?
(ከቤተ መጻሕፍት በኋላ የት ትሄዳለህ)
👨‍🦱 ኀበ ቤትየ።
(ወደ ቤቴ)

👨🏽 አሐውር ምስሌከ።
(አብሬኸ እሄዳለው)
👨‍🦱 ኦሆ።
(እሺ)

👨🏽 ናሁ ምንተ መጽሐፍ ውእቱ ዘታነብብ?
(አሁን ምን መጽሐፍን ነው የምታነበው)
👨‍🦱 ታሪክ ኢትዮጵያ።
(የኢትዮጵያ ታሪክ)

👨🏽 ሠናይ ንባብ።
(መልካም ጥናት)
👨‍🦱 ለኩልኤነ
(ለሁለታችንም)

👨🏽 በል በምሴት ንትራከብ።
(በል በምሽት እንገናኝ)
👨‍🦱 ዐአቅበከ
(እጠብቃለሁ)


🗣 #ቃለ_ምልልስ
..... መሠረተ ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
•ይህን 'ቻናል' ለሌሎች እንዲደርሳቸው 'Share' ያድርጉ።
#የአባቶቻችን_የቴሌቪዥን_ጸሎት_ትርጉም

በብጹአን አባቶቻችን እየተመራ ከቤተ መቅደሱ የሚወጣው የቤተክርስቲያናችን ልዩ ጸሎት በግእዝ ቢሆንም ትርጉሙን ታውቁት ፀሎቱንም ትረዱት ዘንድ የአማርኛው ትርጉም እንዲህ ነው:: ሃሌ ሉያ ለቤተ ክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው፡፡ ለእርሷ ሲል ታስሮ መጎተትን የቻለ የበደለው በደል ሳይኖር ርኩስ ምራቅን ሲተፋበት የታገሰ አምላክ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ ሃሌ ሃሌ ሉያ አቤቱ ይቅርታህን አሳየን እርዳን አትተወን አቤቱ ማረን ይቅር በለን፡፡ አብ ሆይ ማረን ሃሌ ሉያ ወልድ ሆይ ይቅር በለን ሃሌ ሉያ ይቅር ባይ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በይቅርታህ አስበን ለአንተ ፍጹም ምስጋናን እናቀርባለን፡፡ ቸር ይቅር ባይ ሆይ ማረን ኃጢአታችንን አስተስርይልን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አድነን በነፍስም በሥጋም ጠብቀን፡፡ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይቅር በለን በቸርነትህ ብዛት በደላችንን ደምስስ ይቅርታህን ላክልን፡፡ ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና ሃሌ ሉያ ይቅር ባይ አብ ሆይ ማረን ይቅር በለን መሐሪ የሆንህ አቤቱ ይቅርታን ስጠን የቀድሞ ኃጢአታችንንም አስበህ አታጥፋን፡፡ በቸርነትህ አንተ ይቅር ባይ ነህና ለሚጠሩህ ለሚለምኑህ ሁሉ ይቅርታህ ብዙ ነው፡፡ በእውነት ይጠሩሃል አንተም ዘወትር ትሰማለህ ሁሉን ለማድረግ የምትችል ነህ፡፡ ሁሉን ለማድረግ የሚችል የአምላካችን ቃሉ እውነት ነውና፡፡ይቅርታውን ይልክልን ዘንድ አብን እንለምነው፡፡ አብ ለለመነው ሁሉ ይበቃልና፡፡ ሃሌ ሉያ ለርሱ ምስጋና ይገባል ። ሃሌ ሉያ ለርሱ ክብር ምስጋና ይገባል ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለሁሉ ጌታ ለክርስቶስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዛሬስ ተስፋዬ ማነው? እግዚአብሔር አይደለምን? አቤቱ ነፍሴን ለአንተ አደራ አስጠብቃለሁ ከምስጋና አምላክ ዘንድ ነፍሴን ላንተ አደራ አስጠብቃለሁ ከምህረት ንጉሥ ዘንድ ነፍሴን ላንተ አደራ አስጠብቃለሁ በጌታዬና በአምላኬ ነፍሴን ለአንተ አደራ አስጠብቃለሁ ከክፉ ሥራ ሁሉ ነፍሴን/ሰውነቴን/ አድናት፡፡ ኑ እንለምነው እንለምነው እንማልደው የአምላካችን ቃሉ እውነት ነውና ሁሉን የሚችል የሚሳነው የሌለ እርሱ ነው የድሆች አምላክ ተስፋ ላጡ ተስፋቸው የምትሆን አቤቱ እኛ ወደ አንተ ተማጥነናል፡፡ ከጧት እስከ ማታ እንደ ጠበቅኸን አቤቱ እንዲሁ ከማታ እስከ ጧት ጠብቀን፡፡ ሃሌ ሉያ አቤቱ ምድርህን ይቅር አልክ፡፡ ጸሎታችንና ልመናችንን ስማ፡፡ ኃጢአታችንን አቃልልን (ይቅር በል)፡፡ የዕዝራን ጸሎትና ልመናን የሰማህ አምላክ የእኛንም ጸሎት ስማ ምህላችንን ተቀበል፤ ሰላምህን ስጠን ከመካከላችንም አትራቅ ከእኛ አትለይ፡፡ ሃሌ ሉያ መዓትህን ከእኛ መልስ፡፡ መልካሟ ርግቤ የእኔ ሆይ ወደ እኔ ነዪ፡፡ የአፏ መዓዛ እንደ እንኮይ ነው፡፡ ነገሯም ሁሉ በሰላም ነው፡፡ ሃሌ ሉያ አቤቱ ይቅርታህን አሳየን የሰላማችን መልአክ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ሆይ ስለ እኛ ፈጽመህ ለምንልን፡፡ ከታላቁ ንጉሥ ከመንበሩ ፊት ጸሎታችንን አሳርግልን፡፡ ማርያምን ገብርኤል አበሰራት እንዲህም አላት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ ፤ ለያዕቆብ ቤት ለዘለኣለሙ ይነግሣል፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ
የለውም፡፡ ጊዮርጊስ ሆይ ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ለምንልን፡፡ አርደው ከፋፈሉት ሥጋውንም እንደ ትቢያ በተኑት ወደ ፸ ነገሥታት ወሰዱት፡፡ ምድርን ረገጠ ሙታንን አስነሳ፡፡ አባ ጊዮርጊስ በሰላም በጽናት ተሸጋግሮ የክብር መንግሥትን ወረሰ፡፡ አባ በረከትህን እቀበል ዘንድ ባርከኝ፤ ስለ ቅድሰት ቤተክርስቲን ሰላም ስትል በረከትህን እቀበል ዘንድ ባርከኝ፡፡ ከጌታው ዋጋን ይቀበል ዘንድ በበረሃ የተንገላታ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ንዑድ ነው ክቡር ነው፡፡ በሰላም በደስታ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገባ፡፡ የሰላማችን መገኛ ቅድስት/የተከበረች ድንኳን/ ቅድስት ማርያም ናት፡፡ የሰማእታት እናታቸው የመላእክት እህታቸው ናት፡፡ ከእናታችን ማርያም ፊት ሁላችን እንሰግድ ዘንድ ኑ፡፡ ለዓለም ሁሉ መስቀል ብርሃን ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እርሱ ነው፡፡ ሰላምን የሚሰጥ ዓለምን የተቤዠህ አምላክ ሆይ ሰላምህን ስጠን፡፡ የአብ ሰላም የወልድ ሰላም የመንፈስ ቅዱስ ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡
ሰላም አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወፍቅራ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ሞገሰ መስቀሉ ወሀብተ ረድኤቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም፡፡እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ


💚 @kukuha_haymanot 💚
💛 @kukuha_haymanot 💛
❤️ @kukuha_haymanot ❤️
⭕️ አሉታዊ ቃላት (Negetive Markers)


• አልቦ ➾ የለም
• አልቦቱ ➾ የለውም

• አልባቲ ➾ የላትም
• አልቦሙ ➾ የላቸውም
• አልቦን ➾ የላቸውም(ለሴቶች)

• አልብከ ➾ የለህም
• አልብኪ ➾ የለሽም
• አልብክሙ ➾ የላችሁም
• አልብክን ➾ የላቸሁም(ለሴቶች)

• አልብየ ➾ የለኝም
• አልብነ ➾ የለንም

ምሳሌ

➜ አልቦ ትምህርት
(ትምህርት የለም)
➜ አልባቲ ግብር
(ሥራ የላትም)
➜ አልብነ ቤተ መጽሐፍ
(ቤተ መጽሐፍ የለንም)
➜ አልብየ ንዋይ
(ገንዘብ የለኝም)


⭕️ መሠረተ ግእዝ ⭕️
👇👇👇ቻናላችን ይቀላቀሉ
@learnGeez1
@learnGeez1 @learnGeez1
ሆ ሣ ዕ ና

እፎ ወአልክሙ እንቋዕ አብጽሐክሙ አብጽሐክን ለበዓለ ሆሣዕና በሰላም ወበፍቅር ሠናይ በዓል ይኩን ለኲሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን ፡፡

መለኮቶ አርአየ ለኲሎሙ ሕፃናት እንዘ ይብሉ ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር ወቡሩክ አንተ እግዚአብሔር አምላከ አማልክት ወንጉሠ እስራኤል ፡፡

በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው ፡፡ አንተም የአማልክት አምላክ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር ቡሩክ ነህ እያሉ ለሚያመሰግኑ ሕፃናት ሁሉ ጌትነቱን አሳየ ፡፡

ሠናይ በዓለ ሆሣዕና

◽️ መ ሠ ረ ተ • ግ እ ዝ ◽️
@learnGeez1
🟡 አውሥኦተ ቃል (ቃለ ምልልስ)
(Dialougue)

ክፍል ፪


👱‍♂ዜናዊ
➾እፎ ወአልኪ እኅትየ?
(እንዴት ዋልሽ እኅቴ)

👱🏻‍♀ሠናይት
➾እግዚአብሔር ይትባረክ ፤ እፎ ወአልከ?
(እግዚአብሔር ይመስገን እንዴት ዋልክ)

👱‍♂ዜናዊ
➾ዳኅና እግዚአብሔር ይሴባሕ
(ደኅና እግዚአብሔር ይመስገን)

👱‍♂ዜናዊ
➾ዳዊት ሀሎ?
(ዳዊት አለ)

👱🏻‍♀ሠናይት
➾ናሁ ወጽአ።
(አሁን ወጣ)

👱‍♂ዜናዊ
➾አይቴ ዘሖረ ይመስለኪ?
(የት የሄደ ይስልሻል)

👱🏻‍♀ሠናይት
➾ኀበ ቤተ ትምህርት ውእቱ ዘሖረ።
(ወደ ትምህርት ቤት ነው የሄደው)

👱‍♂ዜናዊ
➾ሠናይ ፤ እስፍንቱ ሰዓት ይትመየጥ?
(ጥሩ ስንት ሰዓት ይመለሳል)

👱🏻‍♀ሠናይት
➾በዐሠርቱ ሰዓት ይመጽአ።
(በዐሥር ሰዓት ይመጣል)

👱‍♂ዜናዊ
➾ኦሆ እኅትየ እምዝንቱ እነብር።
(እሺ እኅቴ እስከዚያ ከዚህ እቀመጣለው)

👱🏻‍♀ሠናይት
➾እወ በጊዜ ውእቱ ዘይበውእ ውስተ ቤቱ።
(አዎ በጊዜ ነው ቤቱ የሚገባው )

👱‍♂ዜናዊ
➾ምንት ነሲኦ ውእቱ ዘሖረ?
(ምን ይዞ ነው የሄደው )

👱🏻‍♀ሠናይት
➾መጽሐፍ

👱‍♂ዜናዊ
➾ኦሆ እኅትየ
(እሺ እኅቴ)


#ቃለ_ምልልስ
◽️ መ ሠ ረ ተ • ግ እ ዝ ◽️
@learnGeez1
• 'ቻናሉ' ለሌሎች እንዲደርሳቸው 'Share' ያድርጉ።
🟣 መስተዋድዳን ቃላት (Prepositions)

ክፍል ፩

• ኃበ ➾ ወደ
• መንገለ ➾ ወደ

• ኃቤሁ ➾ ወደሱ
• ኃቤሃ ➾ ወደሷ
• ኃቤሆሙ ➾ ወደነሱ
• ኃቤሆን ➾ ወደነሱ (ለሴቶች)

• ኃቤከ ➾ ወደ አንተ
• ኃቤኪ ➾ ወደ አንቺ
• ኃቤክሙ ➾ ወደ እናንተ
• ኃቤክን ➾ ወደ እናንተ (ለሴቶች)

• ኃቤየ ➾ ወደኔ
• ኃቤነ ➾ ወደኛ

ምሳሌ

➜ ንዒ ኃቤየ
(ነይ ወደኔ)
➜ ሖረ ኃቤሁ
(ወደሱ ሄደ)
➜ ዮም ሖርኩ ኃበ ቤተ ክርስቲያን
(ዛሬ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄድኩ)
➜ ከልብ መጽአ ኃቤነ
(ወደኛ ውሻ መጣ)
➜ ጌሠም እመጽእ ኃቤክሙ
(ነገ ወደ እናንተ እመጣለው)


🔸 መሠረተ ግእዝ 🔸
@learnGeez1
✴️ ተናባቢ ቃላት
ክፍል ፫


እጅ መጫን ➾ አንብሮተ እድ
ሕዝብ ማሰናበት ➾ ሠርሖተ ሕዝብ
የሥላሴ ነገር ➾ ዜና ሥላሴ
የሊቃውንት ቅኔ ➾ ቅኔ ሊቃውንት

አንደበቱ የቀና ➾ ጥዑመ ልሳን
የምሕረት አደባባይ ➾ ዓውደ ምሕረት
መዓቱ የራቀ ➾ ርኁቀ መዓት
የኒቆዲሞስ ጉባዔ ➾ ጉባዔ ኒቆዲሞስ

የሃይማኖት ምሰሶ ➾ ዓምደ ሃይማኖት
የገንዘብ ፍቅር ➾ ፍቅረ ንዋይ
የጋደኛ ፍቅር ➾ ፍቅረ ቢጽ
በር ጠባቂ ➾ አቃቤ ኆኅት


#ተናባቢ_ቃሎች
✏️ መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
"ነሥአ ደዌነ መጾረ ሕማመነ"


ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፶፫ (53)

፬፡ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።

፭፡ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።


እንቋዕ አብጽሐክሙ አብጽሐክን ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት በሰላም በፍቅር ወበጥዒና ሠናይ በዓል ይኩን ለኲልክሙ ሕዝበ ክርስቲያን።

(እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላምና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን።)
መንፈሳዊ ተክታታይና ወቅታዊ ትምህርት ከዚህ ላይ በመጫን ይግቡና ይማሩ::
👇👇👇👇👇👇👇
@kukuha_haymanot
@kukuha_haymanot
@kukuha_haymanot
━━━━✦🌹🌹✦━━━━

  ✞  እንኳን አደረሳችሁ   ✞ 


 " ይትባረክ እግዚአብሔር አቡሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ  ዘወለደነ በምህረቱ  ለተስፋ እንተ ባቲ ነሀዩ "

      1 ጴጥ 1÷3
━━━━✦🌹🌹✦━━━━
ወምድርኒ (ወንጌልን_ለህዝባችን
#ወምድርኒ

ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ/2/ 
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ /4/ 

ምደር ጸዳች ሐሴት አደረገች /2/ 
በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች/4/ 
@learnGeez1 @learnGeez1
2024/10/03 06:22:12
Back to Top
HTML Embed Code: