Telegram Web Link
ክፍል 2
መጋቤ ብሉይ ዳንኤል አጥናፉ
📜 የግእዝ ቋንቋ ትምህርት
ክፍል ፪ (2)


🎤 በመጋቤ ብሉይ ዳንኤል አጥናፉ

🎤 መሠረተ ግእዝ 🎤
@learnGeez1
🔅 ዓረፍተ ነገር ለመመሥረት የሚረዱን ቅጥያዎች


🔸 እንደ ➝ ከመ

ከመ እንስሳ ▻ እንደ እንስሳ
ከመ ዮም ▻ እንደ ዛሬ
ከመ ጽጌ ▻ እንደ አበባ
ከመ ተፈጸመ ▻ እንደ ተፈጸመ
ከመ ኀለየ ▻ እንዳሰበ

🔸 የ ➝ ለ

ልደታ ለማርያም
ቤቱ ለንጉሥ
ሀገሮሙ ለነቢያት

🔸 እና ➝ ወ

አዳም ወሔዋን
ቃየል ወአቤል
ማርያም ወሰሎሜ

✧ ✧ ✧ ✧ ✧ ✧

🔸 ጋር ፣ ጋራ ➝ ምስለ

ሰብእ ምስለ ሰብእ ▻ ሰወ ከሰው ጋር
ዘመድ ምስለ ዘመድ ▻ ዘመድ ከዘመድ ጋር
አንበሳ ምስለ አንበሳ ▻ አንበሳ ከአንበሳ ጋር
ምስለ መንፈስከ ▻ ከመንፈስህ ጋራ

🔸 በፊት ፣ ከፊት ➝ ቅድመ

ቅድመ ሰብእ ▻ ከሰው በፊት
ቅድመ ልደት ▻ ከልደት በፊት
ቅድመ ሰዓት ▻ ከሰዓት በፊት

🔸 በኋላ ➝ ድኅረ

ድኅረ ዘመን ▻ ከዘመን በኋላ
ድኅረ ልደት ▻ ከልደት በኋላ
ድኅረ ትንሣኤ ▻ ከትንሣኤ በኋላ

🔸 ያለ ፤ በቀር ➝ እንበለ

እንበለ ንዋይ ▻ ያለ ገንዘብ በቀር
እንበለ ዘመድ ▻ ያለ ዘመድ
እንበለ ዐስብ ▻ ያለ ደሞዝ

✧ ✧ ✧ ✧ ✧ ✧

🔸 አለ፣ነበረ ➝ ቦ / ✧ የለም ➝ አልቦ

ቦ ሰላም አልቦ ዝናም
ቦ ፍቅር አልቦ ፍቅር
ቦ ሕግ አልቦ ንዋይ
ቦ ንዋይ
ቦ ሥርዓት

🔸 አይደለም ➝ አኮ

አኮ ኤልያስ መምህር ▻ ኤልያስ መምህር አይደለም
አኮ ጸሓፊት ሐና ▻ ሐና ጸሐፊ አይደለችም
አኮ ሰብእ ▻ ሰው አደለም

🔸 ኢ ➝ አፍራሽ

በልዐ ▻ ኢበልዐ
ጾመ ▻ ኢጾመ
ሖረ ▻ ኢሖረ
ጸሓፈ ▻ ኢጸሓፈ


📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
#ዓረፍተ_ነገር
📜 መሠረተ ግእዝ 📜
@learnGeez1
@learnGeez1
📜 መሠረታዊ ግሶች 📜
ክፍል ፭


ለበሰ ➜ ሞጥሐ
ደረሰ ➜ በጽሐ
ነቃ ➜ ነቅሀ
ረዘመ ➜ ኖኀ
አጨበጨበ ➜ ጠፍሐ

ዘጋ ➜ ዘግሐ
ተጋ ➜ ተግሀ
ነጋ ➜ ነግሀ
ረጨ ➜ ነዝሀ

ነዳ ➜ ነድሐ
ጮኸ ➜ ከልሐ
ተቆጣ ➜ ገንሐ
በራ ➜ በርሀ
ሰፋ ➜ ሰፍሐ


#ግሶች
📜-መሠረተ ግእዝ-📜
📜 @learnGeez1 📜
'''''''''''''''''''''''' ' ' ' ' ' '''''''''''''''''''''''''''
🗣ተረትና ምሳሌያዊ ንግግር በግእዝ
ክፍል ፩


➝ በቃል ያለ ይረሳል በመጽሐፍ ያለ ይወረሳል።
፨ በቃል ዘሀሎ ይትረሳዕ በመጽሐፍ ዘሀሎ ይትወረስ።

➝ ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ነው።
፨ ሜስ በቢረሌ ነገር በምሳሌ ውእቱ።

➝ ከንፈር እና ጥርስ ሲተባበር ያምራል።
፨ ከንፈር ወሰን እመይትሃበር ይሴኒ።

➝ ለብልህ አይነግሩም ለአንበሳ አይመትሩም።
፨ ለጠቢብ ኢይዜንው ለአንበሳ ኢይመትሩ፡፡


#ተረት #ምሳሌያዊ_ንግግር
◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦
መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
🗣ተረትና ምሳሌያዊ ንግግር በግእዝ
ክፍል ፪


➝ ዓሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል።
፨ ኀሣሤ ዓሣ ያውጽእ ተመነ ኀሣሤ ዘሰብእ የኀጥእ ዘርዕሱ።

➝ ለብልህ አይነግሩም ለአንበሳ አይመትሩም።
፨ ለጠቢብ ኢይዜንዉ ለአንበሳ ኢይመትሩ።

➝ ጣዝማ ይሰረስራል ዳኛ ይመረምራል።
፨ ጸዲና ይሤርር ኰናኒ የሐተት።

➝ በአጓት የሰከረ በካሳ የከበረ የለም።
፨ በጸብ ዲበ ዘሰክረ በማደ ዘከብረ አልቦ።

➝ ማር ሲሰፍሩ ማር ይናገራሉ።
፨ መዐር እንዘ ይሰፍሩ መዐረ ይትናገሩ።

➝ በጨለማ ቢያፈጡ በባዕድ ቢቆጡ አይሆንም።
፨ ምጽልመት እመ ያወትሩ ነጽሮተ በባዕድ አመ ይተምዑ ኢይከውን።

➝ የቂም ጸሎት የተራጋጭ ወተት አይጠቅምም።
፨ ዘተቀያሚ ጸሎተ ዘተራጋጺት ሐሊብ ኢይበቁዕ።


#ተረት #ምሳሌያዊ_ንግግር
◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦
መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
@learnGeez1
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
👆👆👆👆👆👆👆👆
📲 ቃለ ስብሐት መተግበሪያ 📱


👉 ግብረ ዲቁና መማር ለሚፈልጉ
👉 ቤተክርስቲያንን በክህነት ማገልገል ለሚሹ ሁሉ
👉 በቅዳሴ ጸሎት ተሰጥኦን በመመለስ መሳተፍ ለሚፈልጉ ምእመናንና በተወሰነ መልኩ ለካህናትም ጭምር የሚያገለግሉ የድምፅ ትምህርቶችን የያዘ መንፈሳዊ መተግበሪያ ነው።
• በሥራ ፤ በቦታ ርቀት እና በተለያዩ ምክንያቶች በተለይም የ'ዩኒቨርሲቲ' ተማሪ ሆናችሁ ይህን የአብነት ትምህርት ለመማር ፍላጎቱ ላላችሁ ከትምህርታችሁ ጎን ለጎን ቃለ ስብሐት ያግዛችኋል፡፡

📌 ቃለ ስብሐት በውስጡ የያዛቸው
➝ ትምህርቶች
➝ ሥርዓተ ቅዳሴ
➝ ምንባብ ዘሰዓታት
➝ መሠረተ ትምህርት ዘአብነት
-- ጸሎት ዘዘወትር
-- ውዳሴ ማርያም ንባብ የሳምንቱን
-- አንቀጸ ብርሃን ንባብ
-- መልክዐ ማርያም
-- መልክዐ ኢየሱስ
➝ የሙሉ ሳምንት
-- ኲሎሙ
-- መቅድመ ተአምር
-- መሐረነ አብ
-- እሴብሕ ጸጋኪ
-- ኪዳን
➝ መቅደመ ኪዳን
➝ መልክዐ ቊርባን
➝ ሠራዊት


መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
@learnGeez1
ቃለ ስብሐትን ለማግኘት Play Store ላይ በቀጥታ “ቃለ ስብሐት” ብሎ በመፈለግ ወይም ይህን 👇 ሊንክ በመጠቀም ወደ ቁሶቻችሁ ማውረድ ትችላላችሁ
https://play.google.com/store/apps/details?id=apps.kaleb.qalesebehate2

💿@learnGeez1💽
👤 መሐንዲስ ካሌብ ብርሃኑ
ምዕራፍ ፩

⚪️ አኃዛተ ግእዝ

የግእዝ ቁጥሮች መደበኛ ፣ ሕገኛ ፣ ክፍላዊ እና እጽፋዊ በመባል ይከፈላሉ ፡፡


🔸 መደበኛ

፩ አሐዱ
፪ ክልዔቱ
፫ ሠለስቱ
፬ አርባዕቱ
.
.
.
እያለ የሚቀጥል ነው ፡፡


🔸 ሕገኛ

ዘተባዕታይ ዘአንስታይ

፩ ቀዳማዊ አሐቲ /ቀዳማዊት
፪ ካልአዊ ካልዒት/ካልዓዊት
፪ ዳግማዊ ዳግማዊት
፫ ሣልሣዊ/ይ ሣልሳይት
፬ ራብዓዊ ራብዓዊት
፭ ኀምሳዊ/ይ ኃምሳይት/ዊት
፮ ሳድሳይ/ዊ ሳድሳይት/ዊት
፯ ሳብዓይ/ዊ ሳብአይት/ዊት
፰ ሳምናይ/ዊ ሳምናይት/ዊት
፱ ታስዓዊ ታስዓይት/ዊት
.
.
.

🔸 ክፍላዊ አኃዝ

መንፈቅ = እኩሌታ = 1/2
ሣልሲት = ሦስትያ (ሲሶ) = 1/3
ራብዒት = አራትያ (ሩብ) = 1/4
ኀምሲት = አምስትያ (ግማሽ) = 1/5
ሳድሲት = ስድስትያ = 1/6
ሳብዒት = ሰባተኛ = 1/7
ሳምኒት = ስምንተኛ = 1/8
ታስዒት = ዘጠነኛ = 1/9
.
.
.

🔸 እጽፋዊ አኃዝ

ካዕበተ አሐዱ(ምእሕዲት) = አንድ እጥፍ

ካዕበተ ክልዔቱ(ምክዕቢት) = ሁለት እጥፍ

ካዕበተ ሠለስቱ(ምሥልሲት) = ሦስት እጥፍ

ካዕበተ አርባዕቱ(ምርብዒት) = አራት እጥፍ

ካዕበተ ኃምስቱ(ምኀምሲት) = አምስት እጥፍ

ካዕበተ ስድስቱ(ምስድሲት) = ስድስት እጥፍ

ካዕበተ ሰብዐቱ(ምስብዒት) = ሰባት እጥፍ

ካዕበተ ሰመንቱ(ምስምኒት) = ስምንት እጥፍ

ካዕበተ ተሰዐቱ(ምትስዒት) = ዘጠኝ እጥፍ

ካዕበተ ዐሠርቱ(ምዕሥሪት) = አሥር እጥፍ
.
.
.

#ቁጥሮች
፩፪፫፬፭፮፯፰፱፲
^ ~ መሠረተ ግእዝ ~ ^
👇👇👇👇👇👇👇
@learnGeez1
@learnGeez1
▢□ @learnGeez1 □▢
🗓 አኀዛተ ዕለታት
በሳምንት ውስጥ ያሉ ቀናት

ዕለተ እሑድ
ዕለተ ሰኑይ (ሰኞ)
ዕለተ ሠሉስ (ማክሰኞ)
ዕለተ ረቡዕ
ዕለተ ኃሙስ
ዕለተ ሰዱስ (ዓርብ)
ዕለተ ሰቡዕ (ቅዳሜ)


🗓 አኃዛተ አውራኅ
በወር ውስጥ ያሉ ቀናት

▹፩. አሚሩ ▸ አንደኛ ቀን
፪. ሰኑዩ ▸ ሁለተኛ ቀን
፫. ሠሉሱ ▸ ሦስተኛ ቀን
፬. ረቡዑ ▸ አራተኛ ቀን
፭. ኃምሱ ▸ አምስተኛ ቀን
፮. ሰዱሱ ▸ ስድስተኛ ቀን
፯. ሰቡዑ ▸ ሰባተኛ ቀን
፰. ሰሙኑ ▸ ስምንተኛ ቀን
፱. ተሱዑ ▸ ዘጠነኛ ቀን
▹፲. ዐሡሩ ▸ ዐሥረኛ ቀን
፲፩. ዐሡሩ ወአሚሩ ▹ ዐሥራ አንደኛ ቀን
፲፪. ዐሡሩ ወሰኑዩ ▹ ዐሥራ ሁለተኛ ቀን
፲፫. ዐሡሩ ወሠሉሱ ▹ ዐሥራ ሦስተኛ ቀን
፲፬. ዐሡሩ ወረቡዑ ▹ ዐሥራ አራተኛ ቀን
፲፭. ዐሡሩ ወኃምሱ ▹ ዐሥራ አምስተኛ ቀን
፲፮. ዐሡሩ ወሰድሱ ▹ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን
፲፯. ዐሡሩ ወሰቡዑ ▹ ዐሥራ ሰባተኛ ቀን
፲፰. ዐሡሩ ወሰሙኑ ▹ ዐሥራ ስምንተኛ ቀን
፲፱. ዐሡሩ ወተሱዑ ▹ ወሥራ ዘጠነኛ ቀን
▸፳. ዕሥራ (ዕሥራሁ) ▸ ሃያኛ ቀን
፳፩. ዕሥራሁ ወአሚሩ ▸ ሃያ አንደኛ ቀን
፳፪. ዕሥራሁ ወሰኑዩ ▸ ሃያ ሁለተኛ ቀን
፳፫. ዕሥራሁ ወሠሉሱ ▸ ሃያ ሦስተኛ ቀን
፳፬. ዕሥራሁ ወረቡዑ ▸ ሃያ አራተኛ ቀን
፳፭. ዕሥራሁ ወኃምሱ ▸ ሃያ አምስተኛ ቀን
፳፮. ዕሥራሁ ወሰዱሱ ▸ ሃያ ስድስት ቀን
፳፯. ዕሥራሁ ወሰቡዑ ▸ ሃያ ሰባት ቀን
፳፰. ዕሥራሁ ወሰሙኑ ▸ ሃያ ስምንት ቀን
፳፱ ዕሥራሁ ወተሱዑ ▸ ሃያ ዘጠነኛ ቀን
▹፴ ሠላሳ ▸ ሠላሳሁ

#ቀኖች
🗓 መሠረተ ግእዝ 🗓
👇👇👇👇
@learnGeez1
@learnGeez1
📜 ምዕራፍ ፪ 📜


📜 ክፍላተ ቃላት


📌 መክሥት (ስም) (Noun)

✧ ምንት ብሂል ቃለ ትርጓሜሁ ለስም?
ስም ማለት ምን ማለት ነው?
(What is noun)

ስም፦ ብሂል ጽዋኤ አሐዱ ነገር ብሒል ውእቱ።
ስም ማለት የአንድ ነገር መጠሪያ ማለት ነው።
በዓይናችን የምናያቸው ለምሳሌ ፦

✧ስመ ሰብእ
ኢዮብ
ዳንኤል
ኤፍራታ
ኤርምያስ
ዘካሪያስ

✧ስመ እንስሳ
ላሕም(ላም)
በግዕ(በግ)
አድግ(አሕያ)
ጠሊ(ፍየል)
ከልብ(ውሻ)

✧ስመ ዕፅዋት
ከርካዕ(ሎሚ)
ሰጌላ(ሾላ)
አርዝ(ዛፍ)
ጽጌ(አበባ)
ሰከኖን(እንዶድ)

✧ ስመ ነገራት
መጽሐፍ
ሐመር(መርከብ)
ጠረጴዛ
መጥቅዕ (ደውል)
ማኅቶት(ጣፍ)


ይቀጥላል...

መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
📜 @learnGeez1📜
📜 ስም

( ስም ንከፍሎ በክልዔቱ ዐበይት ክፍላት )
ስም በሁለት ዐብይ ክፍሎች ይከፈላል።

(እሉኒ) እነሱም ፦ ነባር ስም እና ውሉድ ስም


🔸ነባር ስም ፦ ከግስ የማይመሠረት ሲሆን ከተፈጥሮ የተቀበልነው ነው ፡፡

◦ምሳሌ ፦

እድ (እጅ)
ከርሥ (ሆድ)
ክሣድ (አንገት)
ከልብ (ውሻ)
ማይ (ውሃ)
እዝን (ጆሮ)
አድግ (አህያ)
ስዕርት (ፀጉር) .....ወዘተረፈ


🔸ውሉድ ስም ፦ ከግስ የሚወጣና የሚገኝ ነው ፡፡

◦ምሳሌ ፦

ግስ(Verb) ስም(Noun)
ቀደሰ ቅዳሴ
ሐለየ ሕሊና
ከብረ ክብር
ሞተ ሞት
ዘመረ ዝማሬ
ነግሠ ንጉሥ
ገብረ ምግባር
አፍቀረ ፍቅር
ሰብሐ ስብሐት
ሐይወ ሕይወት
ገብረ ግብር
መሀረ መምህር
ፈተነ ፈተና


📜 መሠረተ ግእዝ 📜
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
📜 በድጋሚ የተለቀቀ...

🔹የግእዝ ፊደላት
ክፍል ፫(3)


ሞክሼ ፊደላት

ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት አንድ አይነት ድምጽ ያላቸው ነገር ግን በቅርጽ እና በስራቸው የተለያዩ ፊደላት የሆኑ ናቸው።

በድሮ ጊዜ ግን አባቶቻችን ን ከ ... ፊደሎችን በድምጽ አወጣጥ ይለዮአቸው ነበር።

እኝህ ፊደላት በቁጥር ፱(9) ሰሆኑ
ሀ ፣ ሐ ፣ ኀ ፣ ሠ ፣ ሰ ፣ አ ፣ ዐ ፣ ጸ ፣ ፀ ናቸው።

➺ ሃሌታው "ሀ" ይባላል።
◦ሃሌ ሉያ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ስለሆነ ሃሌታው "ሀ" ተብሏል።

➺ ሐመሩ "ሐ" ይባላል።
◦ሐመር ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው በዚህ ፊደል ስለሆነ ነው።

➺ ብዙኀኑ "ኀ" ይባላል
◦ብዙህ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።

➺ አልፋው "አ" ይባላል።
◦አልፋ ኦሜጋ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።

➺ ዓይኑ "ዐ" ይባላል።
◦ዓይኑ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።

➺ ንጉሡ "ሠ" ይባላል።
◦ንጉሥ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለ ሆነ ነው።

➺ እሳቱ "ሰ" ይባላል።
◦እሳት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።

➺ ጸሎቱ "ጸ" ይባላል።
◦ጸሎት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለሆነ ነው።

➺ ፀሐዩ "ፀ" ይባላል።
◦ፀሐይ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ነው።

እነዚህ ሞክሼ ፊደላት አንዱ በአንዱ ቦታ መግባት የለበትም ምክንያቱም የትርጉም ለውጥ ያመጣሉ።
ለምሳሌ
➺ ሠረቀ = ወጣ
ሰረቀ = ሰረቀ
➺ አመት = አገልጋይ
ዓመት = ዘመን
➺ በአል = የጣዖት ስም
በዓል = ሚከበር ቀን
➺ ማኅሌት = ማመስገን
ማሕሌት = ማሰብ
➜ ቡሩክ = የተባረከ
ብሩክ = የተረገመ
➜ መካን(ሲላላ)= ቦታ
መካን(ሲጠብቅ)= መዉለድ የማይችል
➺ መሀረ = አስተማረ
መሐረ = ይቅር አለ
➺ ኀለየ = አመሰገነ
ሐለየ = አሰበ
➺ ፈጸመ = ጨረሰ
ፈፀመ = ነጨ



#ፊደሎች
◈◌◊◊◍ 🔆 ◍◊◊◌◈
መሠረተ ግእዝ
@learnGeez1
🔆 እንቋዕ አብጽሐክሙ አብጽሐክን ለበዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወክልዔቱ ዓመተ ምሕረት በሰላም በፍቅር ወበጥዒና
🌸 ሠናይ በዓል ለኲልነ ሕዝበ ክርስቲያን!


🔅እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፳፻፲፪ ዓመተ ምሕረት የልደት በዓል በሰላም በፍቅርና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።
🌼 መልካም የልደት በዓል


እንኳን አደረሰኸ ➜ እንቋዕ አብጽሐከ

እንኳን አደረሰሽ ➜ እንቋዕ አብጽሐኪ

እንኳን አደረሳችሁ ➜ እንቋዕ አብጽሐክሙ

እንኳን አደረሰን ➜ እንቋዕ አብጽሐነ

እንኳን አብሮ አደረሰን ➜ እንቋዕ ኀቢሮ አብጽሐነ

መልካም የልደት በዓል ➜ ሠናይ በዓለ ልደት

መልካም በዓል ➜ ሠናይ በዓል


🌸 መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ

@learnGeez1
#መራሕያን_ገቢር_ተገብሮ
መራሕያን(ተውላጠ ስሞች) ማለት የሚመሩ ፣ መሪዎች ፣ ፊት አውራሪዎች ማለት ነው ።

የግዕዝ ቋንቋ መሪዎች ፲ (10) ናቸው ።

እነርሱም ፦ (አነ ፣አንተ፣ አንቲ፣ ውእቱ፣ይእቲ፣ንሕነ፣አንትሙ፣አንትን፣ ውእቶሙ ፣ውእቶን) በመባል ይታወቃሉ።

#መደብ #መራሕያን #ትርጉም
፩ አነ እኔ
፪ አንተ አንተ
፪ አንቲ አንቺ
፫ ውእቱ እሱ
፫ ይእቲ እሷ
፩ ንሕነ እኛ
፪ አንትሙ እናንተ (ተባዕት)
፪ አንትን እናንተ (አንስት)
፫ ውእቶሙ እነርሱ (ተባእት)
፫ ውእቶን እነርሱ (አንስት)
#ገቢር_ተግብሮ
#ገቢር ማለት አድራጊ ወይንም ወራሽ ማለት ሲሆን #ተገብሮ ደግሞ ተደራጊ ወይም ተወራሽ ማለት ነው ። በስም ጊዜ ባለቤትና ተሳቢ ብሎ መግለጽ ይቻላል። በግሥ ጊዜ ደግሞ ተሳቢ ብሎ መግለፅ ይቻላል። ከዚህም አንፃር ፦ አድራጊ፣አስደራጊ፣አደራራጊ፣ገቢር ናቸው ። ተደራራጊና ተደራጊ ደግሞ ተገብ ናቸው ። ምሳሌ፦
#አድራጊ ፦ አይሁድ ቀተሉ አምላከ (አይሁድ አምላክን ገደሉ ) #አስደራጊ ፦ ሳዖል አቅተለ ዳዊትሀ ጎልያድሀ (ሳዖል ዳዊትን ጎልያድን አስገደለ) #አደራራጊ ፦ ዳዊት አስተራወጸ አሳሄልሀ ምሰለ ፈረስ (ዳዊት አሳሄልን ከፈረስ ጋር አሯሯጠ) ። ተደራጊና ተደራራጊ ያለ #ተ ፊደል አይነገሩም ። ለምሳሌ ፦ አምላክ ተሰብሐ (አምላክ ተመሰገነ) ። ተደራራጊ ተገብሮ ነው የሚጠላና የሚፈቀር በውስጡ አለው ። ምሳሌ፦ በተጠላ አምላክ ተሳነነ ምስለ አይሁድ (አምላክ ከአይሁድ ጋር ተጣላ ) ። #ገቢር የሚያናግሩ ቀለማት ፫ ናቸው ። እነርሱ ፣ ግዕዝ ፣ ኅምስ ፣ ሳብዕ ናቸው ። #ተገብሮ የሚያናግሩ ቀለማት ፫ ናቸው ። እነዚህም ካዕብ ፣ ሣልስ ፣ ሳድስ ናቸው ፤ ራብዕ ግን ተፈቃቃሪ ነው ለሁሉ ይሆናል ። ይኸውም ሲባል ሳድሱን ግዕዝ ይወርሰዋል ፡ ሣልሱን ኀምስ ይወርሰዋል ፡ ሣልሱን ኃምስ ይወርሰዋል ፡ ካዕቡን ሳብዕ ይወርሰዋል ፡ማለታችን ሆኖ ሳለ አንዳንድ ጊዜ ይህ ሕግ ሲጣስ ይስተዋላል። መጨረሻው ሳድስ የሆነ ቀለም #ተገብሮ ይሆናል ። ምሳሌ ፦ አንበሳ ፣ ደብተራ ፣ ደመና ፣ ሐራ የመሰለው ሁሉ።


https://www.tg-me.com/learnGeez1
👨🏽👦🏻 የአባትና የልጅ ቃለምልልስ


👦🏻 ልጅ
➜ እፎ ወአልከ አቡየ እግዚአብሔር ምስሌከ።
✧ አባቴ ሆይ እንዴት ዋልክ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን።

👨🏽 አባት
➜ ኦ ወልድየ እግዚአብሔር ይሴባሕ አምላከ አበዊነ።
✧ ልጄ ሆይ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።

👨🏽 አባት
➜ አንተኑ ወልድየ በሰላም ወአልከኑ።
✧ አንተስ ልጄ በሰላም ዋልክ።

👦🏻 ልጅ
➜ እወ አቡየ እግዚአብሔር ይሴባሕ አምላከ አብርሃም።
✧ አባቴ ሆይ አዎ ደኅና ነኝ የአብርሃም አምላክ አግዚአብሔር ይመስገን።

👨🏽 አባት
✧ ኦ ወልድየ ትምህርተ ሃይማኖት ትትሜሃርኑ።
➜ ልጄ ሆይ የሃይማኖት ትምህርት ትማራለህን።

👦🏻 ልጅ
➜ እወ አቡየ በዕለተ ሰንበት ሐዊርየ ኀበ ቤተክርስቲያን እትሜሃር።
✧ አባቴ ሆይ አዎን በሰንበት ቀን ወደ ቤተክርስቲያን ሔጄ እማራለሁ።

👦🏻 ልጅ
➜ እሴብሐከ አቡየ በነገረ አዳም ንባብከ።
✧ አባቴ ሆይ ስለ መልካም ንግግርህ አመሰግናለሁ።

👨🏽 አባት
➜ ኦ ወልድየ ዳእሙ በጤና ወበሰላም ያስተርክበነ አምላክነ።
✧ ልጄ ሆይ በል ዳግመኛ በሰላምና በጤና አምላካችን ያገናኘን።

👦🏻 ልጅ
➜ አሜን


🗣 #ቃለ_ምልልስ
..... መሠረተ ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
⚪️ የመንግሥታዊና የግለሰብ የሥራ ድርሻ ስያሜዎች


▹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ➜ መባሕት ዘላዕላዊ

▹ መከላከያ ሚኒስቴር ➜ መባሕት ዘምክላዕ

▹ የትምህረት ሚኒስቴር ➜ መባሕት ዘትምህርት

▹ የገንዘብ ሚኒስተር ➜ ዘንዋየ መባሕት

▹ የግብርና ሚኒስቴር ➜ በዓለ መባሕት ዘገራህት


▸ የገቢ ሚኒስቴር ➜ ዘሰብሳብ መባሕት

▸የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ➜ መባሕት ዘጥዒና ዐቂብ

▸ መራሔ ግብር ➜ ዳይሬክተር(ሥራ መሪ)

▸ ዋና ጸሓፊ ➜ ዐቢይ ጸሓፊ

▸ የመዝገብ ቤት ሹም ➜ ዘቤተ መዛግብት ሥዩም


#ስም
-▣ ✦✧ ▣-
◎ መሠረተ ግእዝ ◎
@learnGeez1
2024/10/03 13:23:41
Back to Top
HTML Embed Code: