Telegram Web Link
👩‍⚕️በእድሜ የገፉ እናት/አባት ጤና ያሳስቦታል? የጤንነታቸውን ጉዳይ ለመከታተል ጊዜ ማግኘት አልቻሉም? ያሉበትን የጤና ሁኔታ እንዲሁም መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ እና የሚወስዱትን እያንዳንዱን መድሀኒት በቤትዎ ሆነው በሞባይል ስልክዎ መከታተል ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ሊያና ዲጂታል ሄልዝ ኬር ሶሉሽንስ መፍትሄ ይዞሎት መጥቷል፡፡

👉በየ2 ሳምንት በቤትዎ የሚደረግ የሀኪም ክትትል

👉በየ2 ሳምንት በስፔሻለሊስት እንዲሁም በሰብ ስፔሻሊስት የሚደረግ የርቀት ህክምና (virtual consultation)

👉ነጻ የስነአዕምሮ(psychiatry) ማማከር አገልግሎት

👉በወር አንድ ጊዜ የሚደረግ አስፈላጊ ላብራቶሪ ምርመራ

👉በፈለጉት ጊዜ በመደወል በፈለጉት የጤና ጉዳይ ላይ የሚሰጥ ማብራሪያ እና የምክር አገልግሎት

📌እነዚህን ሁሉ አገልግሎቶች በወር አንድ ጊዜ ብቻ እጅግ ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡

------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755/+251910202776 ይደውሉ፡፡

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
የጉበት ንቅለተከላ (Liver transplantation)

👉የጉበት ንቅለተከላ በትክክል መስራት ያቆመ ጉበት በጤናማ ጉበት የሚተካበት የቀዶጥገና ሂደት ነው፡፡

🔹የጉበት ንቅለተከላ ቀዶጥገና ከ 6-12 ሰዓታትን ሲፈጅ ከ 85% እስከ 95% ስኬታማ የመሆን እድል አለው፡፡

📌በአሜሪካ የጉበት ፋውንዴሽን መረጃ መሰረት በየአመቱ 6000 የሚሆኑ የጉበት ንቅለተከላዎች በአሜሪካ ውስጥ ይካሄዳሉ፡፡ አፍሪካ ውስጥ ግን የጉበት ንቅለተከላ የሚደረገው በጣም በጥቂት ቦታዎች ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህም በየአመቱ አፍሪካ ውስጥ የሚደረጉ የጉበት ንቅለተከላዎች ቁጥር በጣም አናሳ ነው፡፡

🤔ጉበት ከጉዳት በኋላ ራሱን የመጠገን ብቃት ካለው ምን ሲፈጠር ነው ሙሉ በሙሉ መስራት የሚያቆመው?

📎ጉበት ሁለት ሶስተኛ ክፍሉ ቢጎዳ ወይም ተቆርጦ ቢወጣ እንኳን ራሱን መጠገን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ጉበት ራሱን መጠገን እስኪያቅተው ድረስ በጣም ሲጎዳ ራሱን መጠገን ያቅተውና መስራት ለማቆም ይገደዳል፡፡

ጉበት መለገስ የሚችለው ምን አይነት ሰው ነው?

👉የደም አይነቱ ለጉበት ተቀባዩ ሰው ተስማሚ የሆነ ሰው

👉የሰውነት መጠኑ ከተቀባዩ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ሰው፡፡ አንዳንዴ ግን ለጋሽ እና ተቀባዩ ተቀራራቢ መጠን ባይኖራቸውም የጉበት ንቅለ ተከላ ሊደረግ ይችላል፡፡

👉በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኝ ሰው

👉ከሱሶች ነፃ የሆነ ሰው

👉እድሜው ከ 18 እስከ 60 የሆነ ሰው

👉ጤናማ ክብደት ያለው ሰው

የጉበት ንቅለ ተከላ አይነቶች

1.ከሞተ ለጋሽ ተወስዶ የሚደረግ የጉበት ንቅለ ተከላ

🔸በዚህ ሂደት ጤናማ ጉበት ከሞተ ሰው ይወሰድና ለታማሚ ሰው ይሰጠዋል፡፡ ይህ ቀዶ ጥገና ሰውየው በሞተ በ24 ሰዓት ውስጥ ስለሆነ የሚደረገው ጉበት ተቀባዩ በአስቸኳይ ወደ ሆስፒታል እንዲመጣ ሊነገረው ይችላል፡፡

2.በህይወት ካለ ለጋሽ ተወስዶ የሚደረግ የጉበት ንቅለ ተከላ

🔸ይህ የጉበት ንቅለ ተከላ አይነት ከጤናማ ሰው የተወሰነ የጉበት ክፍል ወስዶ ወደ ታማሚ ሰው የሚተላለፍበት ሂደት ነው፡፡ ለጋሽ እና ተቀባዩ ጎን ለጎን ያሉ ቀዶ ጥገና ክፍሎች ውስጥ ሆነው ነው ቀዶ ጥገናው የሚካሄደው፡፡ ጉበት ራሱን የመጠገን ችሎታ ስላለው የለጋሹ እና የተቀባዩ ጉበት ጤናማ ወደሆነ የጉበት መጠን በጊዜ ሂደት ይመለሳሉ፡፡

3. ስፕሊት ዶኔሽን( Split donation)

🔸ከሞተ ሰው የተወሰደ ጉበት ሁለት ቦታ ተከፍሎ ለሁለት ታማሚዎች የሚሰጥበት ሂደት ነው፡፡

በጉበት ንቅለተከላ ጉበት ያገኙ ሰዎች ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የጤና ችግሮች

👉የሰውነት አዲሱን ጉበት መጉዳት(organ rejection)- ይህ የሚፈጠረው የተቀባዩ የበሽታ መከላከል ስርዓት አዲሱን ጉበት እንደ እንግዳ አካል ስለሚያየው ነው፡፡ ይህንን ሂደት ለመቀነስ የበሽታ መከላከል ስርዓትን የሚያዳክሙ መድሀኒቶችን መጠቀም እንችላለን፡፡

👉ኢንፌክሽን

👉ግፊት

👉ስኳር

👉ካንሰር

📌የጉበት ንቅለ ተከላ ካደረጉ ሰዎች 75% ያህሉ ቢያንስ አምስት አመት በህይወት የመቆየት እድል ሲኖራቸው 53% ያህሉ ደግሞ ቢያንስ ሀያ አመት በህይወት የመቆየት እድል አላቸው፡፡

------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 ይደውሉ፡፡

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
The world is moving towards digitization. Our center, Liyana Digital Healthcare Solutions, as the first licensed telemedicine company in Ethiopia, is working tirelessly towards realization of digital healthcare service delivery.

We would love to thank Safaricom Telecommunications Ethiopia in becoming part of this journey. We had such a great session with the employees after presentation of a webinar by our experienced psychiatrist Dr.Selam.

We look forward to a fruitful partnership.
📞ዶክተር split የተባለው ፊልም ላይ ያለው የስነ አዕምሮ ህመም ነው?📞


👍በትክክል
🎞split በተሠኘው 2016g.c የተሠራው ፊልም ላይ የተገለፀው የስነ አእምሮ ህመም "dissociative identity disorder" ሲሆን ዋና ገፀ ባህሪው 23 ልዩ ልዩ ስብዕናዎች አሉት።

🙇‍♂️👼በልጅነት ጊዜው በደል የደረሰበት ኬቨን ዌንዴል ክረምብ 21ቱ ስብዕናዎች ወንዶች ሲሆኑ 1ድ ሴት እና 1ድ የ9 አመት ወንድ ህፃን ልጅ ስብዕናን ይዞ እንመለከታለን።


👨‍⚕️ዲሶሺየቲቭ አይደንቲቲ ዲስኦርደር የስነ አእምሮ ህመም ነው።

👱‍♂️👱👩‍🦳በ "DID" ህመም የተጠቁ ሰዎች ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የተለዩ ማንነቶች አሏቸው።
👨‍👧‍👦 እነዚህ ስብዕናዎች በተለያየ ጊዜ ባህሪያቸውን ይቆጣጠራሉ።

🧍‍♂️🧍🚶‍♂️እያንዳንዱ ማንነት፣ የራሱ የግል ታሪክ ፣ ባሕርያት ፣ የሚወዳቸው/የምትወዳቸው/ እና የሚጠላው ነገሮች ይኖሩታል።

🩺Dissociative identity disorder (DID) ከዚ ቀደም "split personality disorder" ወይም "multiple personality disorder" ተብሎ ይጠራ ነበር።

🔴ዲ.አይ.ዲ የሚያስከትላቸው ችግሮች አንድ ሰው ከእውነታው ጋር የመገናኘት ችሎታ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ።

🧮 ሕመሙ ከ 0.01 እስከ 1% ባለው ሕዝብ ላይ በማንኛውም ዕድሜ ላይ ሊከሰት ይችላል።

🙍‍♀️ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በDID የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

🟢የዲ.አይ.ዲ መከሰት ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

👧👦DID አብዛኛውን ጊዜ በልጅነት ጊዜ የሚደርስ የወሲብ ወይም የአካል ጥቃት ውጤት ነው።

💨🔥🌪አንዳንድ ጊዜ ለተፈጥሮ አደጋ ወይም ለሌሎች እንደ አሰቃቂ ክስተቶች ምላሽ በመስጠት ያድጋል።

🕴ዲአይዲ ያለበት ሰው ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ማንነቶች ቢኖሩትም “ዋናው” ማንነት የግለሰቡ የተለመደው ስብዕና ነው።

🧍‍♂️🧍 “ተለዋዋጮች” የግለሰቡ ተለዋጭ ስብዕናዎች ናቸው። አንዳንድ ዲ.አይ.ዲ ያላቸው ሰዎች እስከ 100 የሚጠጉ ማንነቶች አሏቸው።

🔵ተለዋዋጮች እያንዳንዳቸው በጣም የተለያዩ ይሆናሉ። ይህም ማለት
🔹የተለያዩ ጾታዎች
🔹ስሞች
🔹ባህሪያቶች
🔹ፍላጎቶች እና ከአካባቢያቸው ጋር የሚገናኙባቸው መንገዶች ሊኖራቸው ይችላል።

🥼ሌሎች የተለመዱ የ DID ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ-

🤦‍♂️የመንፈስ ጭንቀት.
🤷‍♂️ግራ መጋባት።
🥃🚬አደንዛዥ ዕፅ ወይም አልኮልን መጠቀም
🤷‍♀️🤷የማስታወስ ችሎታ ማጣት
🪦ራስን የማጥፋት ሀሳቦች ወይም ራስን መጉዳት

🩺ለተነጣጠለ የማንነት መታወክ (ዲ.አይ.ዲ) ሕክምናው ምንድነው?

💊አንዳንድ ለድብርት እና ጭንቀት የሚሠጡ መድሃኒቶች ለተመሣሣይ የ DID ምልክቶች ሊረዱ ይችላሉ።

🥼በጣም ውጤታማው ሕክምና የስነ -ልቦና ሕክምና ነው። በአእምሮ ጤና መታወክ ላይ ልዩ ሥልጠና ያለው የጤና እንክብካቤ አቅራቢ ፣ እንደ ሳይኮሎጂስት ወይም ሳይካትሪስት ፣ ወደ ትክክለኛው ሕክምና ሊመራዎት ይችላል።

👩‍⚕️🧑‍⚕️ከግለሰብ ፣ ከቡድን ወይም ከቤተሰብ ሕክምና ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
Saron Mesfin
(Psychiatry professional )
------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ 7755 ይደውሉ

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
ለምፅ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ ይችላል?

🔸ለምፅ( vitiligo) የቆዳ ቀለምን የሚያመርቱ ህዋሶች(melanocytes) በተለያዩ ምክንያቶች እንከን ሲኖራቸው የሚከሰት ህመም ነው፡፡

📎ይህ ህመም 1% ያህል የሚሆነውን የዓለም ህዝብ እንደሚያጠቃ ሲታሰብ በብዛት የሚከሰተው ቡናማ ወይም ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች ላይ ነው፡፡

👉ለምፅ ከታመመ ሰው ወደ ሌላ ሰው በንክኪ አይተላለፍም፡፡

⚠️አምጪ ምክንያቶች

📎የለምፅን አምጪ ምክንያቶች በእርግጠኝነት መዘርዘር ባይቻልም ብዙ ጥናቶች ግን የሚከተሉት ነገሮች እንደ አምጪ ምክንያቶች ይጠቅሳሉ፡፡

❗️አውቶኢሚዩን ዲስኦርደርስ( Autoimmune disorders)- እነዚህ ህመሞች ያሉባቸው ሰዎች የሰውነታቸው የበሽታ መከላከል ስርዓት የራሳቸውን ህዋሶች በማጥቃት ለህመም ይዳርጋቸዋል፡፡ ይህ የተዛባ በሽታ የመከላከል ስርዓት የቆዳ ቀለምን የሚያመርቱ ህዋሶችን (melanocytes) በሚያጠቃበት ጊዜ ለምፅ ሊከሰት ይችላል፡፡

❗️በቤተሰብ ውስጥ በለምፅ የተያዘ ሰው መኖር

❗️በኬሚካሎች ወይም በፀሀይ ቃጠሎ ምክንያት የሚደርስ የቆዳ ጉዳት

👳ምልክቶች

🔸የቆዳ ቀለም መጥፋት

🔹ያለጊዜው የሚከሰት የሽፋሽፍት߹ የቅንድብ߹ የፂም እንዲሁም የፀጉር መንጣት

🔍ምርመራ

📎አብዛኛውን ጊዜ ለምጽ የሚታወቀው ታማሚው ለሀኪሙ በሚነግረው የህክምና ታሪክ እና ሀኪሙ በሚያደርገው አካላዊ ምርመራ ነው፡፡

🩺ህክምና

አብዛኛውን ጊዜ በለምፅ ምክንያት የሚፈጠር የቆዳ ቀለም ችግር ሙሉ በሙሉ ማስተካከል አይቻልም፡፡ ነገር ግን ከ 10 እስከ 20 % የሚሆኑት የለምጽ ታማሚዎች በህክምና ታግዘው የሰውነት ቀለማቸውን ሙሉ በሙሉ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

📌የለምፅ ታማሚዎች በለምፅ የተጠቃው ቆዳቸውን ከሌላው ቆዳቸው ጋር ለማመሳሰል ሜካፕ መጠቀም ይችላሉ፡፡ የፀጉር ቀለም መቀየር ያጋጠማቸው ታማሚዎች ደግሞ የፀጉር ቀለም መቀባት ይችላሉ፡፡

👩‍⚕️በለምፅ የተጠቃ ሰው ቆዳ ወደ ተፈጥሯዊ ቀለሙ እንዲመለስ ለማድረግ ከሚረዱ ህክምናዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

💊የበሽታ መከላከል አቅምን የሚቀንሱ መድሀኒቶች

👉የብርሀን ህክምና

✂️የቆዳ ንቅለተከላ ህክምና

💊ትክክለኛ የቆዳ ቀለም ያለውን የሰውነት ክፍል በማንጣት በለምፅ የተጠቃውን ቆዳ የሚያስመስሉ መድሀኒቶች

👉ቆዳን ቀለም የሚሰጡ ሴሎች(melanocytes ) ከቆዳ በተጨማሪ በአይን ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህም የለምፅ ታማሚዎች ለአይን ህመም ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም የለምፅ ታማሚዎች መደበኛ የሆነ የአይን ክትትል ሊያደርጉ ይገባል፡፡

🔸በለምፅ የተጠቃው ቆዳ በፀሀይ እንዳይጎዳ ሰንስክሪን (sunscreen) መጠቀም ይመከራል፡፡

------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ 7755 ይደውሉ፡፡

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
የሚዋጠውን የወሊድ መከላኪያ(combined contraceptive/CHOICE) ብረሳ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?

🤔አንድ ኪኒን ብቻ ከተረሳ-ቀጣዩ ቀን ላይ የተረሳውን፤ እንዲሁም የዛን ቀን የሚዋጠውን ኪኒን መውሰድ ነው። እናም እርግዝና የመፈጠር እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነው።

👉ሦስት ወይም ከዛ በላይ ከተረሳ

1.የተረሳው የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ ሳምንት ላይ ከሆነ ያስታወሱት ቀን ጀምሮ መድሀኒቱን መውሰድ ነገር ግን ለቀጣይ ሰባት ቀናት ግንኙነት ከተደረገ እርግዝና የመፈጠር እድል ስላለ ሌላ ተጫማሪ መከላከያ(እንደ ኮንዶም) መጠቀም።

2.የተረሳው ሦስተኛ ሳምንት ላይ ከሆነ ያስታወሱት ቀን ጀምሮ መድሀኒቱን መውሰድ ነገር ግን ለቀጣይ ሰባት ቀናት ግንኙነት ከተደረገ እርግዝና መፈጠር እድል ስላለ ሌላ ተጫማሪ መከላከያ(እንደ ኮንዶም) መጠቀም። እንዲሁም ቀዩን በመተው የቀጣዩ ሆርሞናል (ነጩን ኪኒን) መውሰድ።

📌ቡኒው ወይም ቀዩን (iron) ኪኒን ከተረሳ

የተረሱትን ኪኒኖች በማስወገድ ቀጣዩን መውሰድ ( የእርግዝና መፈጠር እድል አይጨምርም)

------------------------------------------------

📞ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 ይደውሉ::

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
2024/09/29 00:43:03
Back to Top
HTML Embed Code: