Telegram Web Link
የተባበሩት መንግስታት እና "Amplifier" በመባል የሚጠራ የሥነጥበብ ቡድን በመጋቢት ወር ላይ ለአርቲስቶች በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሥነ ጥበብን ስራዎችን እንዲያቀርቡ ባቀረበው የገለልተኝነት ዘመቻዎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስራወች ከተለያዩ አርቲስቶች የተሰበሰቡ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ቡድኖቹ እነዚህን ሥራዎች በመምረጥ ለሕዝብ እያሳዩ መሆናቸውን "goats and soda" የሚባል የዜና ድረገፅ አስታወቀ፡፡
በአለም ዙርያ በአሁኑ ጊዜ በፍጥነት እየተስፋፋ ባለው ወረርሽኝ ምክንያት በየሀገሩ ያሉ የተለያዩ የጤና ሰራተኞች እየከፈሉ ላሉት መስዋዕትነት እውቅና የሚሰጡ እና ምስጋና የተሞሉ አበረታች እና ሕብረተሰብን እያዝናኑ እውቀት የሚያስጨብጡ ጠቃሚ መልክት አዘል የጥበብ ስራዎች በዓለም ዙርያ በየጎዳናው መስተዋል ከጀመሩ ሰነባብተዋል ባለፈዉ ሳምንትም በ"UK" ጎዳናዎች ላይ ለጤና ቢሮውና ሰራተኞች የምስጋና መልክቶችን ያዘሉ የስነጥበብ ስራዎች መታየታቸውን the guardian መፅሄት ዘግቦአል።
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች በቻናላችን ላይ ለ1 ወር የተጀመረውን የስነ-ጥበብ ስልጠና የምትወስዱ ሁሉ የዛሬው የትምሕርት ክፍለጊዜ 9:00 ለይ የሚጀምር በመሆኑ ተዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁን እናሳስባለን።
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች በፕሮግራማችን መሰረት ለስነ-ጥበብ ስራ የሚረዱ ቅድመ ልምምዶች ዛሬ ይዘንላችሁ መተናል። በቪድዮው ላይ ያለውን መመሪያ በመመልከት ቢቻል በትልልቅ ወረቀቶች ላይ ለምሳሌ እንደ ጋዜጣ የመሣሠሉ የወረቀት አይነቶችን በ ምቹ ቦርድ ወይም ግድ ግዳ ላይ በመለጠፍ እጃችሁን ማፍታታት ጠቃሚ የስነጥበብ ጅማሬ ነው።

ማሳሰቢያ
የእርሳስ አያያዛችሁ ልክ በምስሉ ላእንደምትመለከቱት መሆኑ አስፈላጊ በመሆኑ ባይመቻችሁም ራሳችሁን ለማስለመድ ልትሞክሩ ይገባል።
2025/02/23 10:48:31
Back to Top
HTML Embed Code: