Telegram Web Link
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች በፕሮግራማችን መሰረት ለስነ-ጥበብ ስራ የሚረዱ ቅድመ ልምምዶች ዛሬ ይዘንላችሁ መተናል። በቪድዮው ላይ ያለውን መመሪያ በመመልከት ቢቻል በትልልቅ ወረቀቶች ላይ ለምሳሌ እንደ ጋዜጣ የመሣሠሉ የወረቀት አይነቶችን በ ምቹ ቦርድ ወይም ግድ ግዳ ላይ በመለጠፍ እጃችሁን ማፍታታት ጠቃሚ የስነጥበብ ጅማሬ ነው።

ማሳሰቢያ
የእርሳስ አያያዛችሁ ልክ በምስሉ ላእንደምትመለከቱት መሆኑ አስፈላጊ በመሆኑ ባይመቻችሁም ራሳችሁን ለማስለመድ ልትሞክሩ ይገባል።
ጥያቄ እና አስተያየት ካላቹ በግል አካውንቴ ፃፋልኝ
ውድ የጆያብ ስቱድዮ የስነጥበብ ተማሪዎች የፊታችን አርብ ወደ ዋናው ትምሕርታችን የምንገባ በመሆኑ ዛሬ በተማራችሁት መሠረት የሚገባውን የዕጅ ማፍታቻ ልምምድ እያረጋችሁ እንድትቆዩ እናሳስባችሁዋለን።
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮቻችን ዛሬ ከታላላቅ ሰዐሊያን መካከል ብዙዎቻቹ የምታውቁትን ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ
ይዘንላቹ መተናል

ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ
የህዳሴው ዘመን ሠአሊ (The Renaissance artist) በመባል የሚጠራ አለም በብዛት በሠዓሊነቱ የሚያውቀው ድንቅ ሠዓሊ ቢሆንም ከዛ ባለፈ ድንቅ የቅርፃቅርፅ ፣ የኪነ ሕንፃ ጥበብ ፣ የፈጠራ ባለሙያ ፣ የውትድርና ስትራቴጂ ቀራጭ  እና ረቂቅ የሆኑ ሳይንሳዊ እውነታዎችን የሚመረምር ከፍተኛ የማወቅ ጉጉት ያለው ታላቅ ችሎታ ያለው ሰው ነበር።   ይህ ድንቅ አርቲስት የተወለደው-ኤፕሪል 15 ቀን 1452 አንችኖኖ  በምትባል ቦታ ሲሆን ትልቅ ዕውቅና ካላቸው የሥነ-ጥበብ ስራዎቹ መካከል-የመጨረሻው እራት ( the last supper ) እና ሞና ሊሳ  ጥቂቶቹ ናቸው።
The last supper
የመጨረሻው እራት
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የዛሬው ክፍለ ጊዜ ትምሕርታችንን ከወትሮው የትምህርት ክፍለጊዜ ዘግይተን የምንጀምር መሆኑን ከ ይቅርታ ጋር እናሳስባለን
መልካም ቀን!!
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች ያዛሬውን ትምህርታችንን ዘግይተን በመጀመራችን ይቅርታ እየጠየቅን የዛሬውን ትምሕርት እንጀምራለን
የዛሬው ትምህርት እንዴት የእርሳስንድፍ እንደሚጀመር የሚያሳይ ሲሆን
የእርሳስ ምስልዐ(ንድፍ) ለመስራት በመጀመሪያ የምንስለውን አካል ባልተለመደ እና በጣም ቀላል መንገድ ቀይረን መመልከት ይኖርብናል
በምስሉ መሠረት ለመስራት እንድትሞክሩ አበረታታችኋለው
2025/02/23 23:02:21
Back to Top
HTML Embed Code: