Telegram Web Link
#DebreBerhanUniversity

....Yunivaarsitti Debra Birahan Barattoonni Bara 2012 ti Eebbifamattota turtan Muddee 1 fi 2 Gara Mooraa Yunivaarsitti dhuftanii Barumsa Akka egaltan beeksise jiraa

.... Barattoota Eebbifamtoota kan hin ta'ain hundi keessan Muddee 8 fi 9 Akka Gara Morra Yunivaarsitticha seentan jedhee jiraa

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎችን ታህሳስ 1 እና 2 ወደ ትምህርት ተቋማቸው እንዲመለሱ ጥሪ አድርጓል።

ዩኒቨርሲቲው ከተመራቂ ተማሪዎች ውጪ ላሉ ተማሪዎች በሙሉ ታህሳስ 8 እና 9 ዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመገኘት ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ ገልጿል።

ተማሪዎች በጉዞ ላይ ሆነ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት እና ጤና ሚኒሰቴር ያወጡትን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ መመሪያን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲያደርጉም አሳስቧል።

@infosanews @infosanewsbot
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የማታ ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ1ኛ አመት ጀምሮ ለሆኑ ተማሪዎቹ የመልሶ ምዝገባ በሚከተለዉ መሠረት ይካሄዳል፡፡

- የማታ ተማሪዎች ምዝገባ ታህሳስ 10 እና 11 2013 ዓ.ም ነው።

- የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ታህሳስ 19 እና 20 2013 ዓ.ም ነው።

..... Yunivaarsittin Finfinee Barattoota Waga 1faa irraa egalee Guyyaa seensaa ibsee jirraa

..... Barattoota Halkan (Galgala) guyyaan Galmee Muddee 10 fi 11 taa'u isaa ibsee jiraa.

..... Barattoota Iddile Jechuuniis Barattoota Eebbifaman fi kan wagaa 1 olii Guyyaan Galmee Muddee 19 fi 20 taa'u Ibsee Jira
@infosanews @infosanewsbot
"ለአንድ ክልል ሲባል የሚቀየር ህገመንግስት የለም" ጠ/ሚ አብይ አህመድ
.
"ህገመንግስቱ የይዘት ችግር የለበትም። ይስተካከልልኝ የሚል ካለ
በህገመንግስቱ መሰረት በስርአት መጠየቅ ይችላል" ታዬ ደንደአ
.
"ህብረ-ብሄራዊ ፌደራሊዝም የኢትዮጵያ ብቸኛ መዳኛ ነው" ፕ/ት ሽመልስ
አብዲሳ
.
"ከህብረብሄራዊ ፌድራሊዝም ውጭ ያሉ የፌድራሊዝም አይነቶችም ሆነ
አሃዳዊ ስርአት ኢትዮጵያ ውስጥ ለነበረው የብሄር ጭቆና እውቅና አይሰጥም"
ኦቦ አዲሱ አረጋ
©Their Fb face

@infosanwes @infosanwesbot
ዋለልኝ መኮንን-አፈና ያልገታው የአመጽ ድምጽ
-------
ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
-------
ነገ ህዳር 29/2013 የብሄርና ብሄረሰቦች ቀን ሊከበር ነው፡፡ ይህ ቀን ለበዓሉ
አከባበር የተመረጠው የኢፌዴሪ ህገ-መንግሥት የጸደቀበት ስለሆነ ነው
ተብሏል፡፡ ታዲያ በዚሁ ቀን አንድ ታላቅ አብዮታዊ ተገድሎ ነበር፡፡ የሚገርመው
ነገር በዚህ ዕለት የሞተው ሰውዬ በኢትዮጵያ ውስጥ የብሄርና ብሄረሰቦች
መብት መከበር አለበት በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የጻፈ ሰው መሆኑ ነው፡፡
*
ህዳር 29/1964፡፡ ረፋዱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው
ቦይንግ708 ጄት አውሮፕላን ከአዲስ አበባ በአስመራ በኩል ወደ አቴንስ ሊበር
ነው፡፡ በአውሮፕላኑ የሚጓዙ መንገደኞች ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል፡፡ ሰባት የአዲስ
አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ከአውሮፕላኑ ውስጥ ተሳፍረዋል፡፡ የበረራው ሰዓት
ሲደርስ አውሮፕላኑ ከመሬት ተነሳ፡፡ ከሰማዩ ገብቶ መብረር ሲጀምር ግን
ያልታሰበ ሁኔታ ተከሰተ፡፡ እነዚያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አውሮፕላኑን
በቁጥጥራቸው ስር ማዋላቸውን አስታወቁ፡፡ እነርሱ ወደሚፈልጉት ሀገር
እንዲበሩም አብራሪዎቹን አዘዟቸው፡፡ ተማሪዎቹ የጠለፋ እወጃውን ካሰሙ
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ሌላ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ፡፡ አውሮፕላኑን
ከጠለፋ እንዲታደጉ የታዘዙ ኮማንዶዎች በቀጥታ በጠላፊዎቹ ላይ በማነጣጠር
ተኮሱባቸው፡፡ ስድስት ጠላፊዎች ተገደሉ፡፡ አንዲት ጓደኛቸው ደግሞ በከባድ
ሁኔታ ቆሰለች፡፡ የአውሮፕላኑ ወለል በሙታኑ ደም ታጠበ፡፡
*
በዚያች ዕለት የሞተው ታዋቂው የተማሪዎች ንቅናቄ መሪ ዋለልኝ መኮንን ነበር፡፡
ከርሱ ጋር የተገደሉትም ማርታ መብራህቱ፣ ጌታቸው ሀብቴ፣ ተስፋዬ ቢረጋ፣
ዮሐንስ በፈቃዱ እና አማኑኤል ዮሐንስ ናቸው፡፡ እነዚያ ወጣቶች አውሮፕላኑን
ለመጥለፍ የሞከሩት የስርዓቱ ክትትል መፈናፈኛ ስላሳጣቸው ነው፡፡ ዓላማቸው
ወደ ውጪ ከኮበለሉት ጓደኞቻቸው ጋር በመቀላቀል ለስር-ነቀል ለውጥ
የሚታገል ድርጅት መመስረት ነበር፡፡ ከድርጅቱ ምስረታ በኋላም ወደ ሀገር ቤት
ተመልሰው ትግሉን በየአቅጣጫው ለማፋፋም አስበዋል፡፡ ሆኖም እንደተመኙት
አልሆነላቸውም፡፡ አውሮፕላን ለመጥለፍ ማቀዳቸው ቀደም ብሎ ተጠቁሞ
ስለነበር የጸጥታው ክፍል በአየር ላይ አፍኖ አስቀራቸው፡፡
*
ከላይ በተገለጸው አሳዛኝ ገቢር (ትራጄዲ) ህይወቱ የተቋጨው ዋለልኝ መኮንን
በወሎ ክፍለ ሀገር የሳይንት (ቦረና) አውራጃ ተወላጅ ነው፡፡ የአንደኛ ደረጃ
ትምህርቱን በደሴው ንጉሥ ሚካኤል ትምህርት ቤት አጠናቀቀ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ
ትምህርቱንም እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ ደሴ ከተማ በሚገኘው ታሪካዊው
ወይዘሮ ስሒን ት/ቤት ተከታተለ፡፡ አስራ አንደኛና አስራ ሁለተኛ ክፍልን ደግሞ
የዘመኑ ምርጥ ተማሪዎች መማሪያ በነበረው በአዲስ አበባው በዕደማሪያም
ትምህርት ቤት አገባደደ፡፡ በ1958 ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከገባ በኋላም
እጅግ የተለየ አብዮታዊ ሆነ፡፡
ዋለልኝ በ1959 በዩኒቨርሲቲው በተደረገው የግጥም ውድድር “ሙት ወቃሽህ
መጣው” በሚለው ግጥም አንደኛ ወጥቷል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት
ይዘጋጅ በነበረው የታገል መጽሔት ከማንም በላይ የነቃ ተሳትፎ ያደርግ ነበር፡፡
በህቡዕ የሚዘጋጁ ጽሑፎችንም እያዘጋጀ ያሰራጭም ነበር፡፡ በተለይ “አዞዎቹ”
የሚባለው የስር-ነቀል ለውጥ ደጋፊ ተማሪዎች ስብስብ በአቋም ደረጃ
የተስማማባቸውን ሀሳቦች በጽሑፍ እያቀናበረ የሚያዘጋጀው እርሱ እንደነበር
በያኔው እንቅስቃሴ የተሳተፉትም ሆነ የዘመኑን ታሪክ ያጠኑ ምሁራን
ይመሰክራሉ፡፡
ከዋለልኝ ጽሑፎች መካከል ዝነኛ የሆኑት ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው ከላይ
የጠቀስኩትና ህዳር 10/1961 በታተመው “ታገል መጽሔት” ላይ የወጣው
“የብሄረሰቦች ጥያቄ በኢትዮጵያ” የሚል ርዕስ ያለው ጽሑፍ ነው፡፡ ሁለተኛው
ደግሞ በ1962 የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት የነበረው ጥላሁን ግዛው
ሲገደል የአጼው ስርዓት በተማሪዎቹ ላይ ያደረገውን ዛቻ በመቃወም “ለአዋጁ
አዋጅ” በሚል ርዕስ በህቡዕ ጽፎ የበተነው ጽሑፍ ነው፡፡ ዋለልኝ በጽሑፎቹ ሳቢያ
በተደጋጋሚ ጊዜያት ታስሯል፡፡ በተለይ “ለአዋጁ አዋጅ”ን የጻፈው እርሱ መሆኑ
ሲታወቅ በችሎት ፊት ቀርቦ የአምስት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል(ሆኖም
ተማሪዎች ባደረጉት ከፍተኛ የተቃውሞ ጫና ከዓመት በኋላ ተፈትቷል)፡፡
ከ1962 በኋላ ሁለት ክስተቶች የተማሪውን ንቅናቄ አቅጣጫ ቀይረውታል፡፡
እነዚህም ስርዓቱ በተማሪዎቹ ላይ የሚያደርሰው አፈና መጠናከር እና የድርጅት
ምስረታ ጥያቄ መቀስቀስ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደ
ቀድሞው ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ ከማድረግ ይልቅ የጥናት ክበቦችን እየመሰረቱ
መወያየትን መረጡ(የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ግን በተቃውሞአቸው ቀጥለዋ)፡፡
ዋለልኝም በውይይት ክበቡ በሚያደርገው ጥናት ላይ አተኮረ፡፡ ከሀገር ተሰደው
በአልጄሪያ ከሚገኙት እነ ብርሀነ መስቀል ረዳ ጋር በሚያደርገው የደብዳቤ
ልውውጥ አማካኝነት ሰፊ መሰረት ያለው ድርጅት ለመመስረት በሚደረገው
ውይይትም ውስጥ ይሳተፍ ነበር፡፡ ህዳር29/1964 በውጪ ካሉት ጓደኞቹ ጋር
ለመቀላቀል ሲል አውሮፕላን ጠለፈ፡፡ ሆኖም ካሰበው ስፍራ ሳይደርስ
በአውሮፕላኑ ውስጥ ተገደለ፡፡
*
ከያኔው የተማሪዎች ንቅናቄ መሪዎች መካከል ዋለልኝ መኮንን ልዩ የሚያደርገው
አንድ ነገር አለ፡፡ ይህም የተለያየ አመለካከት ባላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ
ታላቅ ሰማዕት የሚታይ መሆኑ ነው፡፡ ደርግ፣ ኢህአፓ፣ ህወሓት፣ ኦነግ፣ ህግሓኤ
(ሻዕቢያ)፣ ተሓኤ (ጀብሃ)፣ መኢሶን፣ ወዘተ… ሁሉም ለርሱ በጎ አመለካከት ነው
ያላቸው፡፡ ታዲያ በዋለልኝ ታሪክ ላይ የሚደረገው ሽሚያም በጣም የጠነከረ
ነው፡፡ አንዳንዶቹ ታሪኩን ከራሳቸው ድርጅት ጋር ለማቆራኘት ይሞክራሉ፡፡ በወቅቱ
የነበረው የርሱና የጓደኞቹ አሰላለፍ ሲገመገም ግን ዋለልኝ ኢህአፓን ከመሰረቱ
ወጣቶች ጋር ተመሳሳይ የፖለቲካ መስመር የነበረው ሆኖ ነው የሚታየው፡፡
ኢህአፓን የመሰረቱትም የእርሱ የቅርብ ጓደኞች ናቸው፡፡ በመሆኑም ዋለልኝ
በህይወት ቢሰነብት ኖሮ የዚሁ ድርጅት አባል ይሆን ነበር ተብሎ ነው
የሚገመተው፡፡
*
ዋለልኝ መኮንን ከብዙ በጥቂቱ ይህ ነበር፡፡ ወደፊት ሰፋ ባለ ሁኔታ ስለርሱ
እጽፋለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ እናንተም በበኩላችሁ የምታውቁትን እንድታጋሩን
በአክብሮት እንጠይቃችኋለን፡፡
------
ሰላም
አፈንዲ ሙተቂ
ህዳር 29/2006
በሸገር ተጻፈ፡፡

@infosanwes @infosanwesbot
Godina Horroo Guduruu Wallaggaa Aanaa Guduruu Ganda
Habeebee jedhamutti Poolisiin Humna Addaa Oromiyaa
dargaggoota lama halkaniin manaa baasuun ajjeesanii
bosanatti gatuu jiraattonni himan.
Aanaa Guduruu ganda Habeebee jedhamu keessatti, halkan
qixxee poolisii humna addaa Oromiyaatiin mana maatii isaanii
keessaa qabamanii mudde 07.2020 rasaasaan ajjeefamanii
bosona keessaa reeffisaanii ganamaan argamuu jiraataan
magaalichaa OMN dubbise himeera.
Dargaggoonni ajjeefaman kunniin, Oromoo Mallasaafi Nugusaa
Geetaachoo kan jedhaman

@infosanews @infosanewsbot
በቅርቡ በሞት የተለዩት ክቡር ዶክተር አርቲስት ለማ ጉያ በተለያዩ ወቅቶች በፍየል ሌጦ ላይ የሳሏቸው ስዕሎች ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ለእይታ ቀርበው ተጎብኝተዋል።
(የቪዲዮ ዘገባ፦ ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ ከሀዋሳ) https://t.co/SXC6EMA6Ov
ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ !

በወልዲያ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ከሶስት ሺህ በላይ የተለያዩ አይነት ተተኳሽ ጥይቶችን ሲያጓጉዙ የነበሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ማታወቁን ኢዜአ ዘገበ።

ተጠርጣሪዎቹ ኮድ 3 - 01470 አፋ በሆነ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ጭነው ከቆቦ መስመር ወደ አፋር ክልል ሲጓዙ ህዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም ሌሊት በጣቢያው ተቆጣጣሪዎች መያዛቸው ተገልጿል።

በተደረገው ፍተሻ 1 ሺህ 941 የብሬን ፣ 1 ሺህ 132 የክላሽ፤ 5 የብሬን ሽንሽን ጥይቶችና 3 የክላሽ ካዝና ተገኝቷል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ከሆነ አሽከርካሪውን ጨምሮ በዚሁ ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት ወንዶች እና ሁለት ሴቶች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ መታየት ጀምሯል።

@infosanews. @infosanewsbot
Godina Wallagga Bahaa Aanaa Kiiramuutti, 'Ilmi keessan
qeerroo nurratti kakaase' jechuun Abbaa warraafi Haadha
Warraa mana isaaniitii qabanii hidhuu maatiin himan.
Aanaa Kiiramuu keessatti hidhaafi reebichi poolisii humna
addaa Oromiyaatiin Uummata nagaarratti raawwataa jiru
hammaatee itti fufuu kan himu jiraataan Aanichaa, barattoota
Yuunvarsiitiitii galanii qe'ee jiran dabalatee, qeerroowwan
Aanicha keessa jiraatan guuranii hidhuurra darbuun doorsisaafi
hidhaan maatii ijoollee hidhaa baqatanii Naannoo sanarraa
siqanii jiran irratti godhamullee hedduu hammaachuu namni
kun himeera.
©OMN

@infosanews. @infosanewsbot
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የተወካዮች ቡድን : በትግራይ የሚገኘውን ሽመልባ የኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያ ካምፕን ለመጎብኘት በሄዱበት ጊዜ "እንደተከለከሉ" : በተጨማሪም "ጥይት እንደተተኮሰባቸው" ሮይተርስ ከ2 ዲፕሎማቶች መረጃው እንዳገኘ ዘግቧል::

@infosanews. @infosanewsbot
Yeroo lakkoofsi namoota sababa waraana ji’a tokkoof ture kanaatin qehee ofii irraa buqahanii gara miliyoona tokkoo gahe kanatti jeequmsichi tattaafii Afrikaan vaayrasii koronaa ittiisuuf gootutti gufuu ta’eera.
Karaa biratin, lakkoofsi namoota qarqaarsa barbaadanii bayyachuurraa dhaabillee hojii qarqaarsaa kennan, naannoo san jiranitti, hunda waliin gahuun itti ulfaachaa dhufuutu ibsame.
ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል መተግበሪያ ተሻሽሎ ጥቅም ላይ ይውላል!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ ምርጫ ቦርድና ብሮድካስት ባለስልጣን በጋራ እያዘጋጁት ያለውና ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል የሚያከናውነው መተግበሪያ በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ መገናኛ ብዙሃንና የተመደበውን የአየር ሠዓት ወደ ሲስተሙ በማስገባት መተግበሪያው ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው ቀመር መሰረት ለእያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲና ሚዲያ የተዘጋጀውን ሠዓት ይደለድላል ተብሏል።

መተግበሪያው በ2007 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ጥቅም የዋለ ሲሆን አስፈላጊው ማሻሻያ ተደርጎ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ነው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር አቶ አብዮት ለሚታ ለኢዜአ ተናግረዋል።

@infosanews. @infosanewsbot
........Yeroo biyyattiin jeequmsa siyaasaa hamaa keessa galtee jirtu kanatti Barattoonni Yuunivarsiitiilee Naannoo Amaraa fi Tigraayitti ramadaman deemanii barachuuf sodaa akka qaban ibsan.


.........Barattoota Yuunivarsiitii Bahir dar fi Walloo barachaa turan keessaa kanneen yaada isaanii bilbilaan OMN'f kennan akka himanitti,asiin duras dhimma kana qaama itti iyyannus dhabnee cal'ifne ammas taanaan hanga furmaanni waaraan
argamutti garasitti deemuuf sodaa guddoo keessa jirra jedhan.


....Muddee 1 irraa jalqabee hamma 2'tti mooraa Yuuniversiitii duraan turreetti dirqamaan deebi'uu qabdu jechuun Mootummaan waamicha taasisee akka jirus barattoonni
kunneen himaniiru.


.....Ajjeechaa barattoota Oromoo irratti waggaa darbe
raawwatameefuu qaama dhimmicha hordofee seeratti
dhiyeessu hin agarre kan jedhan Barattoonni kunneen, nuti
haala hammaataa kana keessatti garasitti deebinee imaluun lubbuu keenyaaf hedduu sodaannee jirra jedhaniiru.
@infosanews. @infosanewsbot
#DrAbiyAhimed

MM Dr. Abiy Ahimad daawwannaa hojii guyyaa lamaaf gara Keeniyaa akka imalan mootummaan Keeniyaa ibse.

Pireezidantiin Keeniyaa Uhuuruu Keeniyaattaa, MM Abiyyiin simachuun kaawuntii Marsabiit keessa ka argamtuu daangaa biyyoota lamaanii Mooyyaaleetti daawwanicha akka eegalan ibsameera.

Buufata daddabarsa sochii daangaa Mooyyaalee jiru waliin akka eebbisaniifi achiis gara magaala buufata doonii taate Laamuuttis argamuun ulaa Laamuudhaa ka'ee Sudaan Kibbaa keessa darbuun Itoophiyaa walqunnamsiisuu ni daawwatus jedhameera.

@infosanews @infosanewsbot
INFOSA News
........Yeroo biyyattiin jeequmsa siyaasaa hamaa keessa galtee jirtu kanatti Barattoonni Yuunivarsiitiilee Naannoo Amaraa fi Tigraayitti ramadaman deemanii barachuuf sodaa akka qaban ibsan. .........Barattoota Yuunivarsiitii Bahir dar fi Walloo barachaa…
......ካለው ሁኔታ አንጻር እኛ በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታችንን ለመቀጠል ለህይወታችን ዋስትና የለንም"ሲሉ ተማሪዎች ተናግረዋል"

ምንጭ OMN
.......በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት "ሁከትን በማነሳሳት" ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው የተከሰሱት አቶ ጃዋር መሃመድ እና ፖለቲከኛ በቀለ ገርባን ጨምሮ በመዝገቡ ስር የተጠቀሱ ተጠርጣሪዎች ንብረት እግድ ክርክር ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠው፡፡


.......አቃቤ ሕግ ፣በተከሳሾቹ ላይ አምስት ተሽከርካሪዎች በኤግዚቢትነት መያዙንና አንዱ ተሸከርካሪ በኮንትሮባንድ ወደ ሃገር ውስጥ የገባ ነው ሲል ባቀረበው ክስ ላይ የተከሳሾች ጠበቆች አስተያየታቸውን እንዲሰጡበት የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም.ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


........ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾች ጠበቆች ስለተከሳሾቹ የቤተሰብ ሁኔታ ማብራሪያ እንዲያመጡና ዐቃቤ ህግም በበኩሉ በታገዱ ንብረቶች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ በጠየቀው መሰረት ዛሪ መከራከሪያቸውን ለችሎቱ አቅርበዋል፡፡ይሁንና እንደ ከዚህ ቀደሙ የታገዱ ንብረቶች ተጠርጣሪዎች፣ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ምርመራ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው በመሆኑ ሊለቀቁ ይገባል በሚል መከራከራቸውን የተከሳሾች ጠበቃ ከድር ቡሎ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡


.....አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬም ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ በችሎቱ ላይ ሳይታደሙ ቀርተዋል፡፡ ከሁለቱ በተጨማሪም አቶ ሃምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃም ከዛሬው ችሎት ሲቀሩ ሌሎች ተከሳሾች ግን በችሎቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡ፖለቲከኞቹ በችሎት ላለመገኘታቸው ያቀረቡት ምክንያት እንደ ከዚህ ቀደሙ "የደህንነት ስጋት" የሚል ነው፡፡


........በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት በቁጥጥር ስር የዋሉት እነ አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 24 ተከሳሾች በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 240ን በመተላላፍ ብሔር እና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ግጭት ቀስቅሰዋል በሚል እና በሌሎች የሽብር ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ እንደመሰረተባቸው የአዲስ አበባው ወኪላችን የስዩም ጌቱ በዘገባው አስታውሷል።

©DW
@infosanews. @infosanewsbot
2025/02/24 11:40:45
Back to Top
HTML Embed Code: