✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_26_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ቆሮንቶስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁴ ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።
³⁵ ይህንም ለራሳችሁ ጥቅም እላለሁ፤ በአገባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም በጌታ እንድትጸኑ ነው እንጂ ላጠምዳችሁ ብዬ አይደለም።
³⁶ ዳሩ ግን ማግባት ወደሚገባው ዕድሜ በደረሰ ጊዜ ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር፥ የወደደውን ያድርግ፤ ኃጢአት የለበትም፤ ይጋቡ።
³⁷ ሳይናወጥ በልቡ የጸና ግን ግድ የለበትም፥ የወደደውን እንዲያደርግ ተፈቅዶለታል፤ ድንግልናውንም በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና፥ መልካም አደረገ።
³⁸ እንዲሁም ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ ያላገባም የተሻለ አደረገ።
³⁹ ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት።
⁴⁰ እንደ ምክሬ ግን እንዳለች ብትኖር ደስተኛ ናት፤ እኔም ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ያለ ይመስለኛል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ዮሐንስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።
¹⁵ የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን።
¹⁶ ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።
¹⁷ ዓመፃ ሁሉ ኃጢአት ነው፥ ሞትም የማይገባው ኃጢአት አለ።
¹⁸ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።
¹⁹ ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።
²⁰ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።
²¹ ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ ልድያ የሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።
¹⁵ እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።
¹⁶ ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።
¹⁷ እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፦ የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_26_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"አዋልደ ንግሥት ለክብርከ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት"። መዝ. 44፥9።
“የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።” መዝ. 44፥9።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_26_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 25
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።
² ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።
³ ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤
⁴ ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ።
⁵ ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
⁶ እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
⁷ በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።
⁸ ሰነፎቹም ልባሞቹን፦ መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው።
⁹ ልባሞቹ ግን መልሰው፦ ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው።
¹⁰ ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ።
¹¹ በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና፦ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ።
¹² እርሱ ግን መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ።
¹³ ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ+ወልደ_ነጎድጓድ ነው። መልካም በዓልና የነቢያት (የገና) ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_27
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ሃያ ሰባት በዚህች ዕለት ኢትዮጵያዊው #ጻድቅ_አባ_በግዑ_ዘሐይቅ ዐረፈ፣ የከበረ ኤጲስ ቆጶስ #አባ_አብሳዲ ሰማዕትነት ዐረፈ፣ #የአባ_አላኒቆስም_መታሰቢያው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_በግዑ_ዘሐይቅ
ታኅሣሥ ሃያ ሰባት በዚህች ዕለት ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አባ በግዑ ዘሐይቅ ዐረፈ፡፡ ይኸውም በመጀመሪያ ሽፍታ የነበረ ሲሆን በመንገድ ላይ ንብረት የያዘን ሰው ማንንም የማያሳልፍ ቀማኛ ሰው ነበር፡፡ ከኃይለኛነቱ የተነሳ ሕዝቡም ሁሉ ይፈራው ነበር፡፡ በእጁ ሰይፍና ጦር ይዞ ሊዘርፍ ወደ ወደደው አገር ይገባል፡፡ እየዘረፈ በሚያገኘው ገንዘብም ራሱን በተለያዩ ምግቦችና መጠጦች ያስደስት ነበር፡፡ ባማሩ ልብሶችም ይዋብ ነበር፡፡ ገንዘቡ የተወሰደበት ሰውም እርሱ እንደወሰደበት ባወቀ ጊዜ ዳግመኛ መጥቶ የተረፈውን ቀምቶ እንዳይወስድበት ምንም አይከሰውም ነበር፡፡ በጉልምስናው ኃይለኛና ብርቱ ስለነበር ወደ እርሱ ማንም አይቀርብ ነበር፡፡
በእንደዚህ ያለ የውንብድና ሥራ ብዙ ዓመታት ከኖረ በኋላ አባ በግዑ በስም ክርስቲያን ነበረና ከዕለታት በአንደኛው ቀን #መንፈስ_ቅዱስ አነሳስቶት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደ፡፡ ካህኑም ባየው ጊዜ ከመንገድ ገለል አደረገውና "የሕይወት ዘመንህን ሁሉ በከንቱ አሳለፍክ ዛሬ ስማ ልንገርህ፣ በዘመንህ ፍጻሜ #እግዚአብሔር ይጎበኝሃል፣ #መንፈስ_ቅዱስም ያድርብሃል፣ ፍጹም መነኵሴ ትሆናለህ፣ በብዙ መከራና ተጋድሎ ትኖራለህ በዚያም የነፍስህ መዳኛ ይሆናል፣ #እግዚአብሔርንም ደስ ታሰኘዋለህ" አለው፡፡ ከዚህም የበዛውን ብዙ ነገር ነገረው፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ቅዱስ ቁርባን ተቀበለ፡፡ ወደቤቱም ከተመለሰ በኋላ ካህኑ የነገሩትን እያሰበ "እስከ መቼ በስንፍናዬ እኖራለሁ? እስከ መቼስ የነፍሴን መዳኛ ሳላስብ እኖራለሁ? …" እያለ አሰበ፡፡
ከዚህም በኋላ ከዘመዶቹ ተለይቶ ከሀገሩ ወጥቶ ሄደና ወደ ባሕር ዳርቻ ደርሶ የቅዱስ እስጢፋኖስን ቤተ ክርስቲያን እጅ ነሣ፡፡ ከመነኰሳትም ማኅበር ገብቶ እነርሱን ማገልገል ጀመረ፡፡ አባ በግዑ በ #እግዚአብሔር ጥሪ ወደ ልቡ ተመልሶ ከመነነ በኋላ ግን እስከሞተበት ዕለት ድረስ የላመ እህል ሳይቀምስ ኖረ፡፡ ምግቡን የዛፍ ፍሬና ሜዳ ላይ የሚበቅል ቅጠል አደረገ፡፡ ዓቢይ ጾም ሲመጣም ከሰኞ እስከ ቀዳሚት ሰንበት ምንም ሳይቀም የሚጾም ሆነ፡፡ ውኃንም ሳይጠጣ ኖረ፣ ማንም ሰው ሳያውቅበት ለ5ወር ምንም ውኃ ሳይጠጣ ተቀመጠ፡፡ ከ5ወር በኋላም የመላእክት አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤል ወደ አባ በግዑ መጣና "የ #እግዚአብሔር ሰው ሰላም ለአንተ ይሁን! በምን ትታወካለህ? ምንስ ያሳዝንሃል?" አለው፡፡ አባ በግዑም "ጌታዬ ከውኃ ጥም የተነሣ በጣም ስለተጨነቅሁ ነው"አለው፡፡ መልአኩም ነጥቆ ወደ ገነት ወሰደውና ከገነት ቅጠል አንሥቶ አቀመሰው፡፡ ወዲያም የአባ በግዑ ሰውነት ታደሰች፡፡ ከዚህም በኋላ" ውኃ ሳልጠጣ ተጋድሎዬን እፈጽም ይሆን!" የሚለው የኅሊና መታወክ ከእርሱ ጠፋለት፡፡
ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባ በግዑ ለሚወደው ለአንድ ወዳጁ ለማንም እንዳይናገር በ #እግዚአብሔር ስም ካስማለው በኋላ ለ5ወር ምንም ውኃ እንዳልጠጣ ምሥጢሩን ነገረው፡፡ ያ ወዳጁም ይህን ሲሰማ ደንግጦ አለቀሰ፡፡ አባ በግዑም አብሮት አለቀሰ፡፡ ወዳጁም "እስከ ዛሬ ከውኃ የተከለከለ በማን ዘንድ ሰማህ? አሁንም ቅዱሳን መነኰሳትና አበምኔቱ አያምኑህም፡፡ ይህን ምሥጢር ዛሬ ብሸሽግ በመጨረሻ ይገለጣል፡፡ ሕዝቡ፣ ነገሥታቱና መኳንንቱም ይህን ነገር ይሰማሉ ነገር ግን አያምኑም። አሁንም የምነግርህን ስማኝና ትኅርምቱን ትተህ ውኃ ጠጣ" አለው፡፡ አባ በግዑም "የነገርከኝ ሁሉ እውነት ነው ሐሰት የለውም ነገር ግን እኔ ከዚህ በኋላ እስክሞት ድረስ ዳግመኛ ውኃ እንዳልጠጣ ስለ #እግዚአብሔር ትቻለሁ፡፡ ሰዎች ባያምኑ እኔ ምን ገዶኝ፣ ነገር ግን፣ በዚህ ገድል #እግዚአብሔር ረዳት ይሆነኝ ዘንድ ጸልይልኝ"አለው፡፡
ከዚህም በኋላ #እግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ብረት አመጣና ሰንሰለቶችን ይሠራለት ዘንድ ለአንጥረኛ ሰጥቶ አሠራ፡፡ ያንን ወዳጁን ጠራውና እጆቹንና እግሮቹን በብረት ችንካር እንዲያስረው አዘዘው፡፡ "አበምኔቱን ጥራልኝ" አለውና ጠራለት፡፡ አባ በግዑም አበምኔቱ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ሲመጣ በፊቱ ሰገደለትና "አባቴ ሆይ! የ #እግዚአብሔርን ትእዛዝ እፈጽም ዘንደ በላዬ ላይ ጸልይልኝ" አለው፡፡ "ከዛሬ ጀምሮ ከበዓቴ አልወጣም፣ ሰውም ወደኔ አይገባም" አለው፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐም በላዩ ከጸለየለት በኋላ "ለእኔም ጸልይልኝ" አለው፡፡ አባ በግዑም በቅዱስ ሚካኤል በዓል ቀን በአባ ኢየሱስ ሞዐ እጅ ቅዱስ ቊርባንን ከተቀበለ በኋላ እጆቹንና እግሮቹን በብረት ችንካር ታስሮ ብቻውን ዘግቶ በጽኑ የተጋድሎ ሕይወት ኖረ፡፡ በዓቱንም ዙሪያውን መውጫ መግቢያ እንዳይኖረው መረገው፡፡ ለምግብ የሚሆነውን የዛፍ ፍሬና የሜዳ ቅጠል ማስገቢያ የሚሆን ትንሽ ቀዳዳን አበጃና ያ ወዳጁ ያስገባለታል፡፡ አባ በግዑም ያንን በሦስት ቀን አንድ ጊዜ ብቻ ይመገባል፡፡
የ #እግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ በእንዲህ ዓይነት ጽኑ በሆነ የተጋድሎ ሕይወት ሲኖር ሰውነቱ ላይ ከቆዳውና ከአጥንቱ በቀር የሚታይ ነገር እስኪጠፋ ድረስ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ፡፡ ውኃንም እስከ ሰባት ዓመት ድረስ አልጠጣም፡፡ መቆምም አይችልም ነበርና መነኰሳቶቹ ለቅዱስ ቊርባን በቃሬዛ አድርገው ወደ ቤተ ክርስቲያን ይወስዱት ነበር፡፡ አባ በግዑ በእንደዚህ ዓይነቱ ለመስማት በሚከብድ እጅ የበዛ ጽኑ ተጋድሎ ካደረገ ከብዙ ድካም በኋላ ታኅሣሥ27 ቀን ዐረፈ፡፡ በዕረፍቱ ጊዜ #ጌታችንም_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል #ማርያምና ከአእላፍ ቅዱሳን መላእክቶቹ ጋር መጥቶ እንዲህ የሚል ቃል ኪዳን ገባለት "ስምህን ለጠራ ፣መታሰቢያህን ላደረገ፣ ወደ ተቀበርክበት ቦታ ሄዶ ለተሳለመ፣ በበዓልህ ቀን ምፅዋት ለሰጠ እስከ ሰባት ትውልድ እምርልሃለሁ ዳግመኛም በጸሎትህ አምኖ ከመልካም ሥራ የሠራ የገድልህን መጽሐፍ የሰማ ሁሉ የእሳቱን ባሕር በግልጽ ይለፍ። ወደ መንግሥተ ሰማያትም ይግባ" አለው።
ለሰው ምንም ውኃ ሳይጠጣ ሰባት ዓመት መኖር ይቻለዋልን!?" በብዙ ሲጋደሉ እንደኖሩ የቅዱሳንን ገድላቸውን ሰምተናል፡፡ ነቢይ ዕዝራ የዱር ዛፍ ፍሬ እየተመገበ ውኃም እየጠጣ በምድረ በዳ እየጾመ ኖረ፡፡ ነቢይ ኢሳይያስም የሜዳ ጎመን እየቆረጠ ከእርሱም እየተመገበ ውኃም እየጠጣ በተራራ እየጾመ ኖረ፡፡ #እግዚአብሔር ስሙን "የበረሃ፡ኮከብ" ብሎ የጠራው የመነኰሳት በኩር የሆነ አባ እንጦንስና አባ መቃርስም በደረቅ ኅብስትና በውኃ ብቻ ሲጋደሉ ኖሩ፡፡ እኚህ ምድራዊያን ሲሆኑ ሰማያውያን ሆኑ፡፡ ነቢይ ኤልያስም በኅብስትና በውኃ ብቻ በምድረ በዳ ሲጋደል ኖረ፡፡ ይህ አባ በግዑ ግን ሰባት ዓመት ሙሉ ውኃ ሳይቀምስ ኖረ፡፡ ከመነነ በኋላ እስከ ሞተበት ዕለት ድረስ እህል የሚባል አልቀመሰም፡፡ እርሱ ግን ራሱን በ #እግዚአብሔር ፊት ዝቅ ያደርግና በትሕትናም ሆኖ ስለ ኃጢአቱ ሁል ጊዜ ያለቅስ ነበር፡፡ ይህም የ #እግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ይህን ሁሉ የተጋደለ በራሱ ኃይል አይደለም፤ በ #እግዚአብሔር ኃይል ነው እንጂ፡፡

"አንተም ወንድሜ ሆይ ራስህን ዕወቅ፡፡ ምንም ተጋድሎን ብታደርግ ጾምኩ፣ ተራብኩ፣ ስለ #እግዚአብሔርም ብዬ ራሴን አደከምኩ፣ #እግዚአብሔርንም ስላገለገልኩ በሥራዬም እድናለሁ አትበል፡፡ መጨረሻህን አታውቅም፡፡ አንተ ግን ስለ #እግዚአብሔር ብለህ ራስህን ኃጥእ አድርግ ያን ጊዜ #እግዚአብሔር ያጸድቅሃልና፡፡ ወዳጄ ሆይ በ #እግዚአብሔር ዘንድ እንድትመሰገን ራስህን አታመስግን፤ ሌሎችም ያመሰግኑህ ዘንድ አትውደድ፡፡ ክብር ታገኝ ዘንድ ትሕትናን ገንዘብ አድርግ መጨረሻውን ሳታውቅ ሰው ሲበድል ብታይ አትጥላው አትናቀውም። አንተ ግን ስለ እርሱ ወደ #እግዚአብሔር በጸሎትህ ይምረው ዘንድ ጸልይ። የ #እግዚአብሔር ምሕረት ብዙ ነውና ኃጥአንን ይምራቸዋል። ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረ ጳውሎስንም ሐዋርያ አደረገው። ቀራጭ የነበረውን ማቴዎስንም የወንጌል ጸሐፊ አደረገው። #እግዚአብሔር ሽፍታ ሆኖ የሰውን ገንዘብ ሲዘርፍ የኖረ ለአባ በግዑ ምሕረት እንዳደረገለት አስተውል። #እግዚአብሔር በቀኙ እንደተሰቀለው ሽፍታ በመጨረሻ ዘመኑ መረጠው የመንግሥተ ሰማያትም ወራሽ አደረገው"።
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። እኛንም በእኚህ አባት ጸሎት ይማረን ለዘለዓለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አላኒቆስ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን የከበረ አባት አላኒቆስ ኤጲስቆጶስ በሰማዕትነት ሞተ። እርሱ ጣዖታቱን እንዲአቃልሉ ለሰዎች እንደሚያስተምራቸው ከሀዲው ንጉሥ በሰማ ጊዜ ይዘው ጽኑ ሥቃይን ያሠቃዩት ዘንድ መልእክተኞችን ላከ።
የንጉሥ መልክተኞች መላካቸውን የተመሰገነ አላኒቆስ ሰምቶ በሀገረ ስበከቱ ያሉትን ሕዝቦች ሰበሰባቸውና የቁርባን ቅዳሴን ቀድሶ #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን አቀበላቸው። ከዚህም በኋላ በቀናች ሃይማኖት ጽኑ ከእንግዲህ ፊቴን አታዩኝም አላቸው። እነርሱም አለቀሱ ሊአስተዉትም አልተቻላቸውም ወጥቶም ራሱን ለንጉሥ መልክተኞች አሳልፎ ሰጠ እነርሱም ወስደው ለእንዴናው አገር መኰንን ሰጡት። እርሱም ወደ ሀገረ እንድኩ ወስዶ በዚያ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ማሠቃየቱም በሰለቸው ጊዜ ትከሻውን በሰይፍ ይሠነጥቁ ዘንድ ራሱንም ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ መሞቱን አውቆ አማንያን ከሆኑ መርከበኞች አንዱን እንዲህ ብሎ አዘዘው ወደ ወደቡ ስትደርሱ ሥጋዬን በኮረብታ ላይ አድርግ እርሱም እንዳዘዘው አደረገ።
ከዚህም በኋላ ምእመናን ሰዎች መጥተው ሥጋውን ወስደው ገነዙት የስደቱም ወራት እስቲያልፍ በእነርሱ ዘንድ አኖሩት ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶች ተደረጉ።

#ቅዱስ_አባ_አብሳዲ
ዳግመኛም በዚህች ዕለት የከበረ አባት ቅዱስ አባ አብሳዲ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ከላይኛው ግብፅ የተገኙት ይህ ጻድቅ ምግባር ሃይማኖታቸው፣ ትሩፋት ተጋድሎአቸው ያማረ ነው፡፡ በዘመናቸው ከሃዲዎች የነገሡበት ዘመን ነበር፡፡ ያን ጊዜ ታላላቆች የሆኑ የላይኛው ግብጽ ኤጲስቆጶሳት አባ አብሳዲና አባ አላኒቆስ የክብር ባለቤት የ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በሆነች በቀናች ሃይማኖት ሕዝቡን እንደሚያጸኑአቸው የአማልክትንም አምልኮ እንደሚሽሩ ዜናቸውን ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ መልክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጥቶ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው። የከበረ አባ አብሳዲ ግን አንዲት ቀን እንዲታገሡት መልክተኞችን ለመናቸውና የቊርባን መሥዋዕትን አዘጋጅቶ ቅዳሴ ቀድሶ ለሕዝቡ #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን አቀበላቸው። በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አስተማራቸው ከዚህም በኋላ በሰላምታ ተሰናብቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ወጣ ሰውነቱንም በ #እግዚአብሔር ላይ ጥሎ ከመልክተኞች ጋር ሔደ ወደ እንዴናው ገዥ ወደ አርያኖስ ወሰዱት።
መኰንኑም አርያኖስም የአባ አብሳዲን ገጽ በአየ ጊዜ ከአርያውና ከግርማው የተነሣ አደነቀ ራራለትም እንዲህም አለው "አንተ የከበርክና የምታስፈራ ሰው ለነፍስህ እዘን የንጉሥንም ቃል ስማ"። አባ አብሳዲም እንዲህ ብሎ መለሰ "እኔ የንጉሥን ቃል ሰምቼ በዚህ በኃላፊው ዓለም ሕይወት መንግሥት ሰማያትን አልለውጥም" በመካከላቸውም ብዙ የነገር ምልልስ ሆነ ከበጎ ምክር ባተመለሰ ጊዜ በመንኰራኵር ያሠቃዩትና ከእሳት ማንደጃ ውስጥም ይጨምሩት ዘንድ መኰንኑ አዘዘ ይህን ሁሉ ታገሠ #እግዚአብሔርም ያለ ጉዳት በጤና አስነሣው።
ከዚህም በኋላ ራሱን ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ አባ አብሳዲም ሰምቶ ደስ አለው ልብሰ ተክህኖ ለብሶ እጆቹንም ዘርግቶ አንገቱን ለሰይፍ ሰጠ የከበረች ራሱንም ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ_27 እና #ከገድላት_አንደበት)

Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
ከልጅነታቹ ጀምሮ የምታደንቁት የናንተ ተወዳጅ ዘማሪ/ት ማነው ⁉️
"በስመ #አብ _ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለንዑስ በዓል ለአንዱ #ለኖላዊ መታሰቢያ በዓል #እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሃሌ ሉያ በ፪ "#ኖላዊ_ዘመጽአ_ውስተ_ዓለም ወልዱ ወቃሉ #ለእግዚአብሔር፤ ዘወረደ እምላዕሉ በአቅሙ #ክርስቶስ፤ እስመ ውእቱ #እግዚአ_ለሰንበት፤ ይቤሎ #አብ_ለወልዱ_ወልድየ_ንበር_በየማንየ። ትርጉም፦ ወደ ዓለም የመጣው #እረኛ_የእግዚአብሔር_አብ ቃሉና ልጁ ነው ከላይ የወረደውም #ክርስቶስ ተብሎ ይጠራ ዘንድ ነው። (ፍጹመ አካል ፍጹመ ክብር ነው) #የሰንበት_ጌታ እሱ ነውና #አብ_ልጁን_ልጄ_በቀኜ_ተቀመጥ_አለው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
❤ " #ኖላዊ_ኄር "
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 21 ይህችን ዕለት "ኖላዊ ሔር" ብላ ታከብራለች። ይሕንንም ለሳምንት ያህል ታዘክራለች (ከታኅሣሥ 21-27)። በነዚህ ቀኖች እሑድ የዋለበት ቀን ማኅሌት ተቆሞ ኖላዊ ተብሎ ይከበራል። መሠረታዊ መነሻዋም (ዮሐ. 10፥1) ነው። "ኖላዊ" ማለት በቁሙ "እረኛ" ማለት ሲሆን "ሔር" ደግሞ "ቸር-ርሕሩሕ-አዛኝ" እንደ ማለት ነው።
ገጥመን ብንተረጉመው ደግሞ "ቸር እረኛ" የሚል ትርጉምን ይሰጠናል። ከአባታችን አዳም ስህተት በኋላ ተፈጥረው ከነበሩ ችግሮች አንዱ ቸር እረኛ ማጣት ነው። #እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ። ቸር እረኛ ሆኖ በገነት አሰማርቶት ነበር።
ኤዶም ገነት የለመለመች። ፈሳሾች የሞሉባት መልካም መስክ ናትና። አባታችን ቅዱስ አዳም ደግሞ እንደ አቅሙ የጸጋ እረኝነት ተሰጥቶት ነበር። ድቀት ካገኘው በሁዋላ ግን ከነፍስ እረኛው ጋር ተጣልቶ ከመልካሟ መስክ ገነት ወጣ።
እርሷንና የነፍሱን እረኛ ሲሻም አለቀሰ። ተስፋ ድኅነት ሲሰጠውም ለልጆቹ ነገራቸው። ከዚያም በመንጋው ላይ በአዳም ሴት ተተካ። ከሴ፣ ኄኖስ፣ ከኄኖስ፣ ቃይናን . . . እያለ ከኖኅ ደረሰ።
ከኖኅም በሴም ከአብርሃም፣ ከአብርሃምም በይስሐቅና በያዕቆብ ወርዶ ከሙሴ ደረሰ። ከሙሴም በኢያሱ አልፎ ከነቢየ #እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ደረሰ። እነዚህ ሁሉ እረኞች ምንም እንኩዋ ለ #እግዚአብሔር ሕዝብ በትጋት ቢሠሩም ሕዝቡን ከሲዖል ማዳን አልቻሉም።
ከሲዖል የሚያድን የነፍስ እረኛ ነውና ያን ጊዜ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የራሱን የአባቶቹንና የልጆቹን ጩኸት ባንድ አድርጐ ጮኸላቸው። "ኖላዊሆሙ ለእሥራኤል አጽምዕ - የእሥራኤል እረኛ ሆይ ስማን!" አለ። (መዝ. 79:1)
ጩኸቱም ቅድመ #እግዚአብሔር ደረሰ። ይህንን የሰማ #ጌታም በጊዜው ከድንግል #ማርያም ተወለደ። በየጥቂቱ አድጐ ቸር እረኝነቱን ገለጠ። #መድኃኒታችን እንዳስተማረን እርሱ ቸር እረኛ ነው።
ከእርሱ በፊት የተነሱት ቴዎዳስ ዘግብጽና ይሁዳ ዘገሊላ (ሐዋ. 5፥36, ዮሐ. 10፥8) ሐሰተኛ እረኞች ነበሩ። እርሱ ግን እውነተኛው የበጐች በር ነውና (ዮሐ 10፥7) በእርሱ የሚገቡ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛሉ።
እርሱ እውነተኛ እረኛ ነውና (ዮሐ 10፥11) ለመንጋው ራሱን አሳልፎ ይሰጣል። በእሥራኤል ባሕል እረኞች ከፊት መንጋው (በጐቹ) ከኋላ ሆነው ይሔዳሉና ገዳይ ቢመጣ መጀመሪያ የሚገድለው እረኛውን ነው።
#መድኃኒታችን_ክርስቶስ በሞቱ ሕይወትን፤ በመራቆቱ የጸጋ ልብስን፤ በውርደቱ ክብርን: በድካሙ ኃይልን ይሰጠን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ። የማይሞት ንጉሥ ስለ መንጋው ሞተ። ሰማይን ከነግሡ ምድርንም ከነልብሱ የፈጠረ ጌታ (ዘፍ 1፥1, ዮሐ. 1፥2) ስለ በጐቹ ይህንን ሁሉ ታግሦ ከሲዖል አዳነን።
በሚያርግ ጊዜም በእርሱ ፈንታ ባለ ሙሉ ስልጣን እረኞችን፤ ሐዋርያትን (ዮሐ 21፥15) ሊቃነ ዻዻሳትን (ሐዋ 20፥28) ካህናትን (ማቴ 18፥18) ሾመልን። እነርሱን እረኞች አሰኝቶ እርሱ "ሊቀ ኖሎት-የእረኞች አለቃ" ተባለ። እነርሱም እስከ ዓለም ፍጻም የ #ክርስቶስን መንጋ ሊጠብቁ ስልጣኑም፤ ኃላፊነቱም አለባቸው። (ማቴ 28፥19) ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ፔጅ።

#ታኅሣሥ_27_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዕብራውያን 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።
¹⁷ ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ።
¹⁸ ጸልዩልን፤ በነገር ሁሉ በመልካም እንድንኖር ወደን፥ መልካም ሕሊና እንዳለን ተረድተናልና።
¹⁹ ይልቁንም ፈጥኜ እንድመለስላችሁ ይህን ታደርጉ ዘንድ አጥብቄ እለምናችኋለሁ።
²⁰ በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥
²¹ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
²² ወንድሞች ሆይ፥ የምክርን ቃል እንድትታገሡ እመክራችኋለሁ፥ በጥቂት ቃል ጽፌላችኋለሁና።
²³ ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደ ተፈታ እወቁ፥ ቶሎ ብሎም ቢመጣ ከእርሱ ጋር አያችኋለሁ።
²⁴ ለዋኖቻችሁ ሁሉና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከኢጣልያ የሆኑቱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
²⁵ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።
²² እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤
²³ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
²⁴ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።
²⁵ እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ወሬውም በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ስለ እነርሱ ተሰማ፥ በርናባስንም ወደ አንጾኪያ ላኩት፤
²³ እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ጸጋ ባየ ጊዜ ደስ አለው፥ ሁሉንም በልባቸው ፈቃድ በጌታ ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው፤
²⁴ ደግ ሰውና መንፈስ ቅዱስ እምነትም የሞላበት ነበረና። ብዙ ሕዝብም ወደ ጌታ ተጨመሩ።
²⁵ በርናባስም ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ መጣ፤
²⁶ ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።
²⁷ በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤
²⁸ ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ፤ ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ።
²⁹ ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤
³⁰ እንዲህም ደግሞ አደረጉ፥ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_27_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምዕ። ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ለዮሴፍ። ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ"። መዝ.79÷1
“ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፤ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ተገለጥ።” መዝ.79÷1
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_27_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤
² በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።
³ ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል።
⁴ የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤
⁵ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።
⁶ ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ምን እንደ ሆነ አላስተዋሉም።
⁷ ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
⁸ ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም።
⁹ በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።
¹⁰ ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።
¹¹ መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።
¹² እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል።
¹³ ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።
¹⁴-¹⁵ መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።
¹⁶ ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።
¹⁷ ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል።
¹⁸ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።
¹⁹ እንግዲህ ከዚህ ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ሆነ።
²⁰ ከእነርሱም ብዙዎች፦ ጋኔን አለበት አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ? አሉ።
²¹ ሌሎችም፦ ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዕውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን? አሉ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ #ቅዳሴ_እግዚእነ ነው። መልካም የኖላዊ በዓል፣ ዕለተ ሰንበትና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

#ታኅሣሥ_28
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ሃያ ስምንት በህች ዕለት #የጌና_በዓል ሆነ። ይኸውም የልደት በዓል ነው፣ ከእንዴናው አገር ሰዎች መቶ ሃምሳ ወንዶች ሃያ አራት ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ዕለተ_ጌና
ታኅሣሥ ሃያ ስምንት በዚህች ዕለት የጌና በዓል ሆነ። ይኸውም የልደት በዓል ነው። ይህም እንዲህ ነው በአምላካችን በረቀቀ ጥበቡ ሰዎች ሁሉ ይቈጠሩ ዘንድ ስማቸውንም ይጻፋና ይመዘገቡ ዘንድ ከንጉሥ ቄሣር ትእዛዝ መጣ። ስለዚህም ከእመቤታችን ከከበረች ድንግል #ማርያም ጋር ሊቆጠር ቅዱስ ዮሴፍ ከናዝሬት ወደ ቤተልሔም የርሱንና የቡርክት ድንግል #ማርያምን ስም ሊስመዘግብ ወጣ እርሱ ከይሁዳ ነገድ ከዳዊት ወገን ነውና ቤተልሔምም የዳዊት ቦታው ናትና።
የከበረ ወንጌል እንደተናገረ ከዚህም በኋላ ከዚያ ሳሉ የምትወልድበት ቀን ደረሰ የበኵር ልጇንም ወለደች አውራ ጣቱንም አሠረችው በጨርቅም ጠቅልላ በበረት አስተኛችው ለማደሪያቸውም ቦታ አልነበራቸውምና። በዚያ ሰፈር እረኞች ነበሩ ሌሊትም በየተራቸው ተግተው መንጋቸውን ይጠብቁ ነበር። እነሆ የ #እግዚአብሔር መልአክ አጠገባቸው ቆመ የ #እግዚአብሔርም ብርሃን በላያቸው በራ ታላቅ ፍርሀትም ፈሩ መልአኩም "ለእናንተና ለመላው ዓለም ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ" አላቸው።
"እነሆ ዛሬ በዳዊት አገር መድኅን የሆነ #ጌታ_ክርስቶስ ተወልዶላችኋልና። ለእናንተም ምልክት እንዲህ ነው ሕፃኑ አውራ ጣቱን ታሥሮ በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኙታላችሁ" አላቸው። ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት #እግዚአብሔርን እያመሰገኑ "በሰማይ ለ #እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም በሰው በጎ ፈቃድ እያለ መጡ።
ከዚህም በኋላ መላእክት ከእነርሱ ዘንድ ባረጉ ጊዜ እነዚህ እረኞች ሰዎች እርስበርሳቸው "ኑ ወደ ቤተ ልሔም ሔደን ይህን #እግዚአብሔር የገለጠውንን ነገር እንወቅ" አሉ። ፈጥነውም ሔዱ #ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በበረት ውስጥ ተኝተ አገኟቸው። አይተውም የነገሩዋቸው ስለዚህ ሕፃን እንደሆነ አወቁ እረኞች የነገሩዋቸውን የሰሙ ሁሉ አደነቁ። እረኞችም ለሕፃኑ ሰግደው #እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቦታቸውም ተመለሱ።
ከወገናችን ሰው ሁኖ ለጐበኘንና ይቅር ላለን #እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#174ቱ_ሰማዕታት (የቅዱስ ጳውሎስ ማኅበር)
በዚችም ዕለት ደግሞ ከእንዴናው አገር ሰዎች መቶ ሃምሳ ወንዶች ሃያ አራት ሴቶች በሰማዕትነት አረፉ።
እሊህም ቀድሞ ከሀ*ዲያን ነበሩ የእንዴናው መኰንን የከበረ ሶርያዊ ጳውሎስን በሚያሠቃየው ጊዜ ከዚያ ነበሩ ሲአሠቃየውም ይመለከቱ ነበር መኰንኑም ችንካሮችን በእሳት አግለው ዐይኖቹን እንዲአወልቁ አዘዘ ይህንንም ባደረጉበት ጊዜ ዐይኖቹ ወለቁ ከወህኒ ቤትም ጣሉት። በማግሥቱም እሊኒ ሰዎች ሊያዩት በሔዱ ጊዜ ያለ ምንም ጉዳት ድኖ ጤነኛ ሁኖ አገኙት የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አድኖታልና።
ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው እጅግ አደነቁ ጣዖ*ቶቻ*ቸውም ምንም መሥራት እንደማይችሉ አስተዋሉ። የክርስቲያኖች አምላክ እርሱ እውነተኛ አምላክ እንደ ሆነ አወቁ ወደከበረ ጳውሎስ ሒደው ሰገዱለት እንዲጸልይላቸውም ለመኑት እርሱም ባረካቸው #እግዚአብሔር እምነታችሁን ተቀብሎ ከሰማዕታት ጋር ይቊጠራችሁ አላቸው።
ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ቀርበው በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ራሶቻቸውን ቊረ*ጡ ብሎ አዘዘና ቈረ*ጧቸው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ_28)

#ታኅሣሥ_28_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³-⁴ ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ።
⁵ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።
⁶ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
⁷ ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤
⁸ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም።
⁹ እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም።
¹⁰ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው።
¹¹ ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።
¹² እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ዕዳ አለብን፥ እንደ ሥጋ ፈቃድ ግን እንኖር ዘንድ ለሥጋ አይደለም።
¹³ እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ።
¹⁴ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
¹⁵ አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።
¹⁶ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
¹⁷ ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
¹⁸ ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ዮሐንስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።
² የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥
³ ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።
⁴ ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።
⁵ እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ ዓለሙም ይሰማቸዋል።
⁶ እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ በዚህ እናውቃለን።
⁷ ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።
⁸ ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።
⁹ በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ሙሴም ለአባቶች፦ ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል፤ በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት።
²³ ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች አለ።
²⁴ ሁለተኛም ከሳሙኤል ጀምሮ ከእርሱም በኋላ የተናገሩት ነቢያት ሁሉ ደግሞ ስለዚህ ወራት ተናገሩ።
²⁵ እናንተ የነቢያት ልጆችና እግዚአብሔር ለአብርሃም፦ በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ፥ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ።
²⁶ ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_28_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ ወኵሎ ዓሚረ ይድኅርዎ። (መዝ.71÷15) ትርጉም👇
“እርሱ ይኖራል ከዓረብም ወርቅ ይሰጡታል፤ ሁልጊዜም ወደ እርሱ ይጸልያሉ፥ ዘወትርም ይባርኩታል።” (መዝ.71÷15)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_28_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።
² አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤
³ ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤
⁴ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤
⁵ ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤
⁶ እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤
⁷ ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤
⁸ አሣፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤
⁹ ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤
¹⁰ አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤ ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞፅን ወለደ፤
¹¹ አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ።
¹² ከባቢሎንም ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤
¹³ ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤
¹⁴ አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤
¹⁵ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤
¹⁶ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።
¹⁷ እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው።
¹⁸ የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የእግዝትነ #ማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የልደት (ጌና) በዓልና የገሀድና የነብያት ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።