✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_19_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ተሰሎንቄ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶-⁷ ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።
⁸ እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤
⁹-¹⁰ በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር፥ ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊገረም ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።
¹¹-¹² ስለዚህም ደግሞ እንደ አምላካችን እንደ ጌታም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር እናንተም በእርሱ ዘንድ ልትከብሩ፥ አምላካችን ለመጥራቱ የምትበቁ አድርጎ ይቈጥራችሁ ዘንድ፥ የበጎነትንም ፈቃድ ሁሉ የእምነትንም ሥራ በኃይል ይፈጽም ዘንድ ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ይሁዳ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
²¹ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
²² አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥
²³ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።
²⁴ ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው
²⁵ ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ አርባ ዓመትም ሲሞላ የጌታ መልአክ በሲና ተራራ ምድረ በዳ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው።
³¹-³² ሙሴም አይቶ ባየው ተደነቀ፤ ሊመለከትም ሲቀርብ የጌታ ቃል፦ እኔ የአባቶችህ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ ብሎ ወደ እርሱ መጣ። ሙሴም ተንቀጥቅጦ ሊመለከት አልደፈረም።
³³ ጌታም፦ የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች ምድር ናትና የእግርህን ጫማ አውልቅ።
³⁴ በግብፅ ያሉትን የሕዝቤን መከራ ፈጽሜ አይቼ መቃተታቸውንም ሰምቼ ላድናቸው ወረድሁ፤ አሁንም ና፥ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ አለው።
³⁵ ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_19_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስምከ"። መዝ 137፥1-2።
"አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ የአፌን ነገር ሰምተኸኛልና፤ በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ። ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና"። መዝ 137፥1-2።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_19_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።
¹² ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት።
¹³ መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።
¹⁴ ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።
¹⁵ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤
¹⁶ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል።
¹⁷ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።
¹⁸ ዘካርያስም መልአኩን፦ እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው።
¹⁹ መልአኩም መልሶ፦ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤
²⁰ እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም አለው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታችን_የማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ገብርኤል በዓል፣ የቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ የዕረፍት በዓል፣ የአቡነ ስነ ኢየሱስ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
📷 እርግጠኛ ነኝ ፕሮፍይሎን ለመቀየር ፈልገው ፕሮፍይል የሚያደርጉት ጠፍቶ ተቸግረው ያውቃሉ።
የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ መንፈሳዊ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው👇👇👇👇👇👇📷
https://www.tg-me.com/addlist/gpX29GzfGs43MWE0

#ታኅሣሥ_20
#ቅዱስ_ሐጌ_ነቢዩ
አንድ አምላክ በሚሆን በ አብ በ #ወልድ በ #መንፈስ_ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ሃያ በዚህች ዕለት ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ፣ ከሌዊ ነገድ ከአሮን ትውልድ የሆነው ቅዱስ ሐጌ ዐረፈ። እርሱም ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው። ናቡከደነጾርም የኢየሩሳሌምን ሕዝብ በማረከ ጊዜ የዚህ ጻድቅ ነቢይ ወላጆች ከእስራኤል ልጆች ጋር ወደ ባቢሎን አገር ተማርከው ሔዱ ዳርዮስ የተባለውም ኵርዝ በነገሠ ጊዜ በሁለተኛው ዘመነ መንግሥቱ ይህ ነቢይ ትንቢት ተናገረ።
የእስራኤልን ልጆች ወደ አገራቸው ይገቡ ዘንድ ኵርዝ ዳርዮስ በአሰናበታቸው ጊዜ እነርሱም ከገቡ በኋላ ቤተ መቅደስን ከመሥራት ቸለል በአሉ ጊዜ እነርሱ ግን በአማሩና በተሸለመ ቤቶች ውስጥ ይኖሩ ነበርና እንዲህ አላቸው። "ሁሉን የሚገዛ #እግዚአብሔር እንዲህ አለ የኔ ቤት ፈርሷል እናንተ ግን ሁላችሁም ቤታችሁን ታጸናላችሁ" አላቸው። "ስለዚህ ከምድር በላይ ያለች ሰማይ ዝናም ለዘር ትነሣለች ምድርም ፍሬዋን አትሰጥም" አላቸው።
ከሕዝቡም ደናጎቻቸው ሰምተው እጅግ ፈሩ የ #እግዚአብሔርንም መመስገኛ ቤት እንደሚገባ መሥራት ጀመሩ። ይህም ጻድቅ ነቢይ ሰባ ዓመት ያህል ኖረ የትንቢቱም ወራት ክብር ይግባውና #ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በአራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነው። ከዚህ በኋላም በሰላም በፍቅር ታኅሣሥ 20 ቀን ዐረፈ።
"#ሰላም_ለሐጌ_ዘተነበየ_በፆታ። ሚጠተ ፂዉዋን ሕዝብ ወሕንፀተ መቅደስ ድኅረ ንስተታ። በእንተ ማርያምኒ ዘተደንገለት በመንታ። ለቤት ደኀሪት እንተ ትገብር ድሉታ። እምነ ቀዳሚት ይቤ ይኄይስ ትርሲታ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የታኅሣሥ 20።
በተጨማሪ በዚች ቀን #ከንግሥት_ታውፊና፣ #ከአውጋንዮስና #ከማድዮስም መታሰቢያቸው ነው።
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ሐጌ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ_20)

#ታኅሣሥ_20_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።
¹² ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።
¹³ በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤
¹⁴ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤
² ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤
³ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።
⁴ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።
⁵ ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።
⁶ ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤
⁷ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
⁸ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
⁹ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
¹⁰ ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ስለዚህም ነገ ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ ስሄድ፥
¹³ ንጉሥ ሆይ፥ በመንገድ ሳለሁ እኩል ቀን ሲሆን በዙሪያዬና ከእኔ ጋር በሄዱት ዙሪያ ከፀሐይ ብሩህነት የበለጠ ብርሃን ከሰማይ ሲበራ አየሁ፤
¹⁴ ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ።
¹⁵ እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ ማንነህ? አልሁ። እርሱም አለኝ፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።
¹⁶ ነገር ግን ተነሣና በእግርህ ቁም፤ ስለዚህ እኔን ባየህበት ነገር ለአንተም በምታይበት ነገር አገልጋይና ምስክር ትሆን ዘንድ ልሾምህ ታይቼልሃለሁና።
¹⁷-¹⁸ የኃጢአትንም ስርየት በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ዓይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥ ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_20_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ። እማንቱ ይምርሓኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ። መዝ. 42÷3-4
“ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።” መዝ. 42÷3-4
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_20_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
² ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
³ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።
⁴ በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።
⁵ ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።
⁶ ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤
⁷ ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ።
⁸ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም።
⁹ ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።
¹⁰ በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።
¹¹ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።
¹² ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
¹³ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።
¹⁴ ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።
¹⁵ ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ፦ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።
¹⁶ እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤
¹⁷ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።
¹⁸ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።
¹⁹ አይሁድም፦ አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_አትናቴዎስ_ቅዳሴ ነው። መልካም ከጌታችን 9ኙ ንዑሳን በዓላት ለእለተ #ብርሃን በዓል፣ ለነብዩ ቅዱስ ሐጌ የዕረፍት በዓል፣ መልካም ዕለተ ሰንበት እና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ነብዩ_ሐጌ
በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
#ሐጌ ማለት በዓል፣ ደስታ ማለት ነው፡፡ የስሙ ትርጓሜ ሕዝቡ ከምርኮ የሚመለሱ ስለኾነ ይኽን ደስታ የሚያስረዳ ነው፡፡
➛በብሉይ ኪዳን በመጨረሻ የምናገኛቸው ሦስቱን መጻሕፍት ማለትም ትንቢተ ሐጌ፣ ትንቢተ ዘካርያስና ትንቢተ ሚልክያስ ከምርኮ በኋላ ስላለው ጊዜ እንዲኹም አይሁድ ከምርኮ እንዴት ወደ አገራቸው እንደተመለሱ የሚያስረዱ ናቸው፡፡ በዚያ አንጻር ግን ደቂቀ አዳም ከዲያብሎስ ምርኮ እንደምን ወደ #እግዚአብሔር እንደተመለሱ የሚያስረዱ ናቸው፡፡
➛ነቢዩ ሐጌ የተወለደው በምርኮ በባቢሎን ሲኾን ትንቢቱን ሲናገር የ፸፭ ዓመት ሽማግሌ ነበር፡፡ የእስራኤል ቅሪቶች ወደ ኢየሩሳሌም በዘሩባቤል አማካኝነት ሲመለሱ ነቢዩ ሐጌም ከተመለሱት ጋር አንዱ ነበር፡፡
➛በ፭፻፴፰ ቅ.ል.ክ. ላይ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ አንድ አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡ አዋጁም አይሁድ ወደ አገራቸው እንዲመለሱና ቤተ መቅደሱን እንዲሠሩ የሚፈቅድ ነበር /ዕዝራ ፩፡፩-፲፩/፡፡ በዚኽም መሠረት የቤተ መቅደሱን ሥራ በ፭፻፴፮ ላይ የቤተ መቅደሱን ሥራ ዠምረዋል፡፡ ነገር ግን አይሁድ ወደ አገራቸው ሲገቡ አገራቸው ባድማ ኾና ስለነበር፣ የዘር ፍሬ በአገሩ ስላልነበረ፣ እንዲኹም በሌሎች ችግሮች ምክንያት ቤተ መቅደሱን መሥራት ትተው ወደየግላቸው ተግባር ተሰማርተው ነበር፡፡ በመኾኑም መንፈሳዊ ሕይወታቸው ዝሎ ነበር፡፡ #እግዚአብሔር ነቢዩ ሐጌንና ነቢዩ ዘካርያስን የላከበት ዋና ምክንያትም የተዠመረውን ቤተ መቅደስ እንዲያጠናቅቁት ለማሳሰብ ነበር፡፡
➛ነቢዩ ሐጌ በሚያገለግልበት ወራት የነበረው ንጉሥ ዘሩባቤል ሲኾን፤ በዚያ ሰዓት የነበረው ሊቀ ካህናት ደግሞ ኢያሱ ይባላል /፩፡፩/፡፡
#ትንቢተ_ሐጌ
➛ነቢዩ ሐጌ በ #እግዚአብሔር ሰዓት የ #እግዚአብሔር ሰው ኾኖ የተገኘ ነቢይ ነው፡፡ አገልግሎቱን በ፭፻፳ ቅ.ል.ክ. ላይ ሲዠምር ጠንካራና ፬ ተከታታይ ስብከቶችን በመስጠት ነበር፡፡ ለሕዝቡ የቤተ መቅደሱ ሥራ እንደተቋረጠ ነገራቸው፤ ሕዝቡ ከቤተ #እግዚአብሔር ይልቅ የራሳቸውን ቤት በመሸላለም እንደተሳቡ ገለጠላቸው፡፡ አራቱን ስብከቶቹም እንደሚከተለው የቀረቡ ናቸው፡-
1. የቤተ መቅደሱን ሥራ እንዲያጠናቅቁት አሳሰባቸው /ምዕ. ፩/፡፡ በዘሩባቤል አማካኝነት ቅሪቶቹ ከባቢሎን ምርኮ ሲመለሱ የ #እግዚአብሔርን ቤት መሥራት ዠምረው ነበር፡፡ ነገር ግን ሥራው ብዙም ሳይቈይ ቆመ፤ ለ፲፮ ዓመት ያኽልም ተስተጓጐለ፡፡ ሕዝቡ የራሳቸውን ቤት ሸላልመው የመሥራት ችግር አልነበረባቸውም፤ ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ግን “ጊዜ አልነበራቸውም”፡፡ እንደዉም፡- “ኢኮነ ጊዜኹ ለሐኒፀ ቤተ #እግዚአብሔር - የ #እግዚአብሔር ቤት የሚሠራበት ዘመን አኹን አይደለም” እያሉ ያመካኙ ነበር፡፡ #እግዚአብሔር ግን በቀጥታ በነቢዩ ሐጌ፣ በአለቃቸው በዘሩባቤልና በሊቀ ካህናቱ በኢያሱ በኵል ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ሰሙ፤ ከ፳፫ ቀን በኋላም የቤተ መቅደሱን ሥራ በድጋሜ ዠመሩት፡፡
2. የኹለተኛው ቤተ መቅደስ ክብር እንዴት እንደኾነ አስረዳቸው /፪፡፩-፱/፡፡ ሕዝቡ የቤተ መቅደሱን ሥራ ለጥቂት ሳምንታት ከቀጠሉ በኋላ ግን አኹንም ተስፋ መቊረጥ ዠመሩ፡፡ ሽማግሌዎቹ የቀድሞው የሰሎሞን ቤተ መቅደስ እንዴት እንደነበረ አስታወሱና ይኽ አኹን የሚሠሩትን ቤተ መቅደስ አቃለሉት፡፡ ነቢዩ ሐጌ ግን የ #እግዚአብሔር ቃል ኪዳን አስታወሳቸው፡፡ #እግዚአብሔር በዚኽ ቤት ያለው ዓላማ ሲገልጥም፡- “ከፊተኛው ይልቅ የዚኽ የኹለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል ይላል የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር” አላቸው /፪፡፱/፡፡ በዚኽ ቤተ መቅደስ አንጻርም በ #ክርስቶስ ስለምትሠራውና በደሙ ስለምትከብረው ቤተ ክርስቲያን ትንቢት ሲናገር ነው፡፡ እንደዉም ቊጥር ፭ ላይ በግልጥ ስለ #መንፈስ_ቅዱስ የሚናገር ነው፡፡
3. የመታዘዛቸው ውጤት የኾነ በረከትን እንደሚባረኩ ነገራቸው /፪፡፲-፲፱/፡፡ ነቢዩ ሐጌ አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ የ #እግዚአብሔር በረከት እንዴት እንደሚርቀው ለካህናቱ አስተማራቸው፡፡ አኹን ግን ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ስለታዘዙ ከዚያች ቀን ዠምሮ እንደምን ባለ በረከት እንደሚባርካቸው አስተማራቸው፡፡
4. በመታዘዛቸው ምክንያት ሊመጣ ያለው በረከት እንዴት እንደኾነ አስታወቃቸው /፪፡፳-፳፫/፡፡ ነቢዩ ሐጌ ሕዝቡ ለ #እግዚአብሔር በመታዘዛቸው እንደምን ባለ የአኹን በረከት እንደሚባርካቸው ከገለጠ በኋላ ዳግመኛም ለዘሩባቤል እንዲኽ አለው፡- “ሰማያትንና ምድርን አናውጣለኹ፤ የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለኹ፤ የአሕዛብንም መንግሥታት ኃይል አጠፋለኹ” /፪፡፳-፳፩/፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስተምሩት ዘሩባቤል የመሲሑ የ #ጌታችንና_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ በዘሩባቤል አንጻር፡- “ዘሩባቤል ሆይ! በዚያ ቀን እወስድኻለኹ ይላል የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር፡፡ እኔ መርጬኻለኹና ይላል የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር፤ እንደ ቀለበት ማተሚያ (እንደ ዳዊት) አደርግኻለኹ ይላል የሠራዊት #ጌታ_እግዚአብሔር” ማለቱም ይኽን የሚያስረዳ ነው /ቊ. ፳፫/፡፡
✍️በአጠቃላይ የነቢዩ ሐጌ ዓላማ
➛ሕዝቡ የትኛው ማስቀደም እንዳለባቸው ለማሳሰብና ምንም ነገር ከመጠበቃቸው በፊት የቤተ መቅደሱን ሥራ እንዲጨርሱት ለማስገንዘብ ነበር፡፡ ነቢዩ ሐጌ እንደነገራቸው ሕዝቡ ከ #እግዚአብሔር በፊት የራሳቸውን ነገር ሲያስቀድሙ ነገሮች እንዴት ከባድ እንደኾኑባቸው ነግሯቸዋል፡፡ ለ 💐እግዚአብሔር ታዝዘው #እግዚአብሔርን ሲያስቀድሙም እንደምን ባለ በረከት እንደሚባርካቸው ግልጽ አድርጐ ነግሯቸዋል፡፡
#እኛስ_ከዚኽ_ምን_እንማራለን ?
📌መጽሐፉን በጥንቃቄ አንብበነው ከኾነ ቃሉ መጣ የሚለው “በነቢዩ በሐጌ እጅ” ነው የሚለው /፩፡፩፣ ፪፡፩፣ ፪፡፲/፡፡ የ #እግዚአብሔር ቃል የሚመጣው በነቢያት አፍ ነው፤ እዚኽ ግን የተገለጠው በነቢዩ እጅ ነው፡፡ ምን ለማለት ነው? ጄሮም የተባለ የጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ሊቅ እንዲኽ ይላል፡- “እጆቻችንን ለመልካም ሥራ ስናነሣ #ክርስቶስም በኹለንተናችን ላይ ይነግሣል፤ ዲያብሎስን ከእኛ ያርቅልናል፡፡ እጅ ሲባል መልካም ሥራን የሚያመለክት ነው፡፡ … #እግዚአብሔር ወደ ሕይወታችን የሚመጣው ስለ ተናገርን አይደለም፤ መልካም ሥራን ስንሠራ እንጂ፡፡”
📌አይሁድ ቤተ መቅደሱን ላለመሥራት ሲያመካኙ የነበረው “ኢኮነ ጊዜሁ - ጊዜው ገና ነው” በማለት ነበር፡፡ ተወዳጆች ሆይ! ብዙዎቻችን በዚኽ መንፈስ የተያዝንበት ዘመን ቢኖር አኹን፡፡ “ጊዜው ገና ነው፤ ቤተ መቅደሱን የምሠራበት ጊዜ አይደለም፤ ገና ወጣት ስለኾንኩ አኹን ወደ #እግዚአብሔር የምቀርበብበት ዘመን አይደለም” እያልን እናመካኛለንና፡፡ ነገ በሕይወት ለመኖራችን ግን እርግጠኞች አይደለንም፡፡ እንኪያስ ሰባኪው እንዳለው የጭንቅ ቀን ሳይመጣ፣ በጕብዝናችን ወራት፣ አፈርም (ሥጋችን) ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ ፈጣሪያችንን እናስብ እንጂ በማመካኘት ጊዜአችንን አናጥፋ /መክ.፲፪፡፩፣፯/፡፡

📌በተራራው ስብከቱ ላይ ጌታ፡- “አስቀድማችሁ የ #እግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፤ ይኽም ኹሉ ይጨመርላችኋል” እንዳለን /ማቴ.፮፡፴፫/ በሕይወታችን ላይ #እግዚአብሔር የማናስቀድም ከኾነ ግን ብዙ ብንዘራም የምናስገባው ጥቂት ነው፤ ብንበላም አንጠግብም፤ ብንጠጣም አንረካም፤ ብንለብስም አይሞቀንም፤ ደመወዛችንን ብንቀበልም በቀዳዳ ኪስ እንደማስቀመጥ ነው /ሐጌ.፩፡፮/፡፡ አዝመራውን በእርሻው ሳለ ባየነው ጊዜ ብዙ ቢመስለንም ወደ ቤታችን ሲገባ በረከት የለውም፤ ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር ይነሣል (ይከለክላል)፤ ምድር የዘራንባትን አታበቅልም፤ የተከልንባትን አታጸድቅም፡፡ በአጭር ቃል በረከት ከእኛ ይርቃል /ሐጌ.፩፡፱-፲፩/፡፡
📌በ #ወልድ ውሉድ በ #ክርስቶስ ክርስቲያን ተብለን ተጠርተን ሳለ፣ በጥምቀት ከማይጠፋ ዘር ተቈጥረን ሳለ ምድራዊ ቤትን (ፈቃደ ሥጋን) ለመሥራት አማናዊው መቅደሳችንን (ፈቃደ ነፍሳችንን) የምንረሳ ከኾነ በዚኽ ምድር ከእኛ የባሰ ጐስቋላ ሰው የለም /ሐጌ.፩፡፲-፲፩/፡፡
📌ቤተ መቅደሱን (ፈቃደ ነፍሳችንን) የምንሠራ ከኾነ ግን #እግዚአብሔር በረድኤቱ ከእኛ ጋር ይኾናል፤ ጸጋ #መንፈስ_ቅዱስ በእኛ ላይ ትበዛለች፡፡ “ቤተ #እግዚአብሔርን ከሠራችሁበት ቀን ዠምሮ እኽሉን ወይኑን በአውድማ ትርፍርፍ ብሎ ታዩታላችሁ፤ በለሱን ሮማኑን ዘይቱን የሚያፈራውን እንጨት ኹሉ ከዛሬ ዠምሮ አበረክታለኹ” ሲል ይኽን ያመለክታል /ሐጌ.፪፡፳/፡፡
ይኽን እንድናደርግ ሰውን በመውደዱ ሰው የኾነው #ጌታችንና_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ይርዳን አሜን!!!
#ታኅሣሥ_20_በዓለ_ዕረፍቱ_ለነብዩ_ቅዱስ_ሐጌ

#ታኅሣሥ_21
ታኅሣሥ ሃያ አንድ ይህችን ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን #ኖላዊ_ሔር ብላ ታከብራለች፣ #የሐዋርያው_ቅዱስ_በርናባስ ዕረፍቱ ነው፣ #የአባ_ይስሐቅ_ገዳማዊ መታሰቢያው ነው::
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ኖላዊ_ሔር
ታኅሣሥ ሃያ አንድ ይህችን ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን "ኖላዊ ሔር" ብላ ታከብራለች:: ይሕንንም ለሳምንት ያህል ታዘክራለች:: መሠረታዊ መነሻዋም (ዮሐ. 10፥1) ነው:: "ኖላዊ" ማለት በቁሙ "እረኛ" ማለት ሲሆን "ሔር" ደግሞ "ቸር፣ ርሕሩሕ፣ አዛኝ" እንደ ማለት ነው:: ገጥመን ብንተረጉመው ደግሞ "ቸር እረኛ" የሚል ትርጉምን ይሰጠናል:: ከአባታችን አዳም ስህተት በኋላ ተፈጥረው ከነበሩ ችግሮች አንዱ ቸር እረኛ ማጣት ነው። #እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ: ቸር እረኛ ሆኖ በገነት አሰማርቶት ነበር።
ኤዶም ገነት የለመለመች: ፈሳሾች የሞሉባት መልካም መስክ ናትና:: አባታችን ቅዱስ አዳም ደግሞ እንደ አቅሙ የጸጋ እረኝነት ተሰጥቶት ነበር:: ድቀት ካገኘው በሁዋላ ግን ከነፍስ እረኛው ጋር ተጣልቶ ከመልካሟ መስክ ገነት ወጣ:: እርሷንና የነፍሱን እረኛ ሲሻም አለቀሰ:: ተስፋ ድኅነት ሲሰጠውም ለልጆቹ ነገራቸው:: ከዚያም በመንጋው ላይ በአዳም ሴት ተተካ:: ከሴት ኄኖስ፣ ከኄኖስ: ቃይናን . . . እያለ ከኖኅ ደረሰ።
ከኖኅም በሴም ከአብርሃም: ከአብርሃምም በይስሐቅና በያዕቆብ ወርዶ ከሙሴ ደረሰ:: ከሙሴም በኢያሱ አልፎ ከነቢየ #እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ደረሰ:: እነዚህ ሁሉ እረኞች ምንም እንኩዋ ለ #እግዚአብሔር ሕዝብ በትጋት ቢሠሩም ሕዝቡን ከሲዖል ማዳን አልቻሉም:: ከሲዖል የሚያድን የነፍስ እረኛ ነውና ያን ጊዜ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የራሱን: የአባቶቹንና የልጆቹን ጩኸት ባንድ አድርጐ ጮኸላቸው:: "ኖላዊሆሙ ለእሥራኤል አጽምዕ - የእሥራኤል እረኛ ሆይ ስማን!" አለ:: (መዝ. 79:1)
ጩኸቱም ቅድመ #እግዚአብሔር ደረሰ:: ይህንን የሰማ ጌታም በጊዜው ከድንግል #ማርያም ተወለደ:: በየጥቂቱ አድጐ ቸር እረኝነቱን ገለጠ:: #መድኃኒታችን እንዳስተማረን እርሱ ቸር እረኛ ነው:: ከእርሱ በፊት የተነሱት ቴዎዳስ ዘግብጽና ይሁዳ ዘገሊላ (ሐዋ. 5:36, ዮሐ. 10:8) ሐሰተኛ እረኞች ነበሩ:: እርሱ ግን እውነተኛው የበጐች በር ነውና (ዮሐ. 10:7) በእርሱ የሚገቡ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛሉ:: እርሱ እውነተኛ እረኛ ነውና (ዮሐ. 10:11) ለመንጋው ራሱን አሳልፎ ይሰጣል:: በእሥራኤል ባሕል እረኞች ከፊት: መንጋው (በጐቹ) ከሁዋላ ሆነው ይሔዳሉና ገዳይ ቢመጣ መጀመሪያ የሚገድለው እረኛውን ነው::
#መድኃኒታችን_ክርስቶስ በሞቱ ሕይወትን: በመራቆቱ የጸጋ ልብስን: በውርደቱ ክብርን: በድካሙ ኃይልን ይሰጠን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ:: የማይሞት ንጉሥ ስለ መንጋው ሞተ:: ሰማይን ከነግሡ ምድርንም ከነልብሱ የፈጠረ #ጌታ (ዘፍ. 1:1, ዮሐ. 1:2) ስለ በጐቹ ይህንን ሁሉ ታግሦ ከሲዖል አዳነን:: በሚያርግ ጊዜም በእርሱ ፈንታ ባለ ሙሉ ስልጣን እረኞችን: ሐዋርያትን (ዮሐ. 21:15) ሊቃነ ዻዻሳትን (ሐዋ. 20:28) ካህናትን (ማቴ. 18:18) ሾመልን:: እነርሱን እረኞች አሰኝቶ እርሱ "ሊቀ ኖሎት-የእረኞች አለቃ" ተባለ:: እነርሱም እስከ ዓለም ፍጻሜ የክርስቶስን መንጋ ሊጠብቁ ስልጣኑም ኃላፊነቱም አለባቸው:: (ማቴ. 28:19)
➛በልበ አምላክ ክቡር ዳዊትም “ #እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝ የለም በለመለመ መስክ ያሳድረኛል መዝ (22፡1) ተብሎ እንደተጻፈ በዚህ የጾም ወቅት አቤቱ ብርሀንህንና ጽድቅህን ላክ፣ ቸሩ እረኛችን ሆይ ተቅበዝብዘናልና እባክህ አስበን፣ የቀዘቀዘው ፍቅራችንን መልስልን፣ አንተ እውነተኛ ሰላምህን ስጠን እያልን ምንም ወደ ማያሳጣን ወደ እውነተኛው እረኛችን ወደ #መድኃኒታችን_ኢየሱስ _ክርስቶስ በንስሐ ልንመለስ ይገባል።
➛ከተኩላዎች ተጠበቁ፦ ለክርስቲያኖች ሁሉ የታመነ ጠባቂ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው፡፡ በተጨማሪም ‹‹በጎቼን ጠብቅ›› ብሎ ቅዱስ በጴጥሮስ በኩል አደራ የተሰጣቸው ካህናተ ቤተክርስቲያን የመንጋው ጠባቂ ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ሐሰተኛ በበዛበት ዘመን እውነተኞቹን እረኞች ከተኩላዎቹ መለየት ያስፈልጋል፡፡ የምንለያቸውም በፍሬያቸው ነው (ማቴ 7፡15)፡፡ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬ እንዲያፈራ መልካም እረኛም ለበጎቹ መልካምን ያደርጋል፡፡ ተኩላ ግን በጎችን ሊጠብቅ ሳይሆን ሊነጥቅ እንደሚመጣ ሐሰተኞች እረኞችም ምዕመናንን ሊጠብቋቸው ሳይሆን ሊነጥቋቸው ይፍጨረጨራሉ፡፡ ነገር ግን መጨረሻቸው ጥፋት ስለሆነ ልናውቅባቸው ይገባል፡፡
ለእርሱ ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_በርባስ
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ በርናባስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ሐዋርያ ከሊዊ ነገድ የሆነ አገሩ ቆጵሮስ ነው የቀድሞ ስሙ ዮሴፍ ነው ክብር ይግባውና #ጌታችን ከመከራው በፊት ይሰብኩ ዘንድ ከላካቸው ከሰባ ሁለት አርድእት ጋር መረጠው ስሙንም በርናባስ ብሎ ጠራው። በርናባስ ማለትም የመፅናናት ልጅ ማለት ነው። ከ #ጌታችን እግር ስር ቁጭ ብሎ ተምሯል ተዓምራቱንም ሁሉ ተመልክቷል። ከጌታ ዕርገትም በኋላ አጽናኝ #መንፈስ_ቅዱስ በወረደ ጊዜ እርሱም ከሐዋርያት ጋር የ #መንፈስ_ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ስም አስተማረ። በጊዜውም በአበው ሐዋርያት በይሁዳ ፈንታ ከአሥራቱ ሁለቱ ሐዋርያት የሚቆጠረውን ሰው ለመምረጥ ሁለት ሰዎችን አቅርበው ነበርና አንዱ ይህ ቅዱስ ነው። እዚያውም ላይ #ጌታችንን ከመጀመሪያ ጀምሮ ማገልገሉ ተመስክሮለታል። (ሐዋ.1÷22) ስሙንም ኢዮስጦስ ብለውታል። ባለ ሦስት ስም ነበርና። በወቅቱም ዕጣ በቅዱስ ማትያስ ስለ ወደቀ ቅዱስ በርናባስ ከሰባ ሁለቱ አርድእት ቅዱስ ማትያስ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ሆነው ቀጠሉ። ➛በሐዋርያት ዜና መፅሐፍ ላይ ስለ ቅዱስ በርናባስ የተፃፉ ዜናዎች➛ቅዱሳን ሐዋርያት የእኔ የሚሉት ንብረት ሳይኖራቸው ያላቸውን በጋራ እየተጠቀሙ በፍቅር ይኖሩ ዘንድ የ #መንፈስ_ቅዱስ ትዕዛዝ ነበር እና ያለውን ሁሉ የእርሻ ቦታ ነበረውና ሽጦ ዋጋውን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር በታች አኖረው። (ሐዋ.4÷36)
ቅዱስ ጳውሎስም በ #ጌታችን አምኖ ወደ ሐዋርያት በመጣ ጊዜ ክብር ይግባውና ለ #ክርስቶስ እርሱ ደቀ መዝሙሩ እንደሆነ ሐዋርያት አላመኑትም ነበር። ይህ በርናባስ #ጌታችን በመንገድ እንደ ተገለጸለትና እንደ አነጋገረው እርሱም በ #ጌታ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም በደማስቆ እንደ አስተማረ ነገራቸው።(ሐዋ.9÷26) ከዚህም በኋላ የ #እግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙ ሲጸልዩ #መንፈስ_ቅዱስ " ቅዱሳን ሳውልና በርናባስን እኔ እነርሱን ለመረጥኩት ሥራ ለዩልኝ" አላቸው።(ሐዋ.13÷1) ከዚህም በኋላ ጹመው ጸልየው እጆቻቸውን በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሟቸው። ከ #መንፈስ_ቅዱስም ተሹመው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ ከዚያም ወደ ቆጵሮስ ሔዱ የ #እግዚአብሔርንም ቃል በአገሩ ሁሉ አስተማሩ። ልስጥራን በተባለ አገርም ልምሾ የነበረውን ሰው በአዳኑት ጊዜ የልስጥራን ሰዎች ሊያመልኳቸው መሥዋዕትን ሊሠዉላቸው ወደዱ። ሐዋርያት ቅዱስ ጳውሎስና በርናባስም በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀድው ወደ ሕዝቡ ሔዱ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንዲህ አሏቸው "እናንት ሰዎች ይህ ነገር ምንድን ነው እኛማ እንደናንተ የምንሞት ሰዎች አይደለንምን ይህን ከንቱ ነገር ትታችሁ ሰማይና ምድርን ባሕርንም በውስጣቸው

ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደሕያው #እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ እናስተምራችኋለን" አሏቸው እንዲህም ብለው መሠዋትን በጭንቅ አስተዋቸው።(ሐዋ.14÷8-18፣ ዘጸ.20÷1)
በአንጾኪያ የነበሩ አሕዛብ ክርስትናን በተቀበሉ ጊዜ ከሐዋርያት ተልዕኮ ሒዶ በጎ ጎዳናን መራቸው።(ሐዋ.11÷22)
ከዚያም ብዙ አገሮችን ከአስተማሩ በኋላ ቅዱስ በርናባስ ከቅዱስ ጳውሎስ ተለይቶ ቅዱስ ማርቆስን ይዞ ወደ ቆጵሮስ ሔደ በዚያም አስተማረ ብዙዎችን ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳቸውና የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።
በቆጵሮስ አገር የሚኖሩ አይሁድም ቀኑበት በመኳንንትም ዘንድ ወነጀሉት በእግር ብረትም አሥረው ጽኑ ግርፋትን ገረፉት ከዚህም በኋላ በደንጊያ ወገሩት ዳግመኛም ወስደው ከእሳት ጨመሩት ምስክርነቱንም ፈጸመ። ቅዱስ ማርቆስም ከርሱ ጋር አለ ግን #እግዚአብሔር ጠብቆ አተረፈው። እርሱም ቅዱስ በርናባስን ከእሳት ውስጥ አወጣው ሥጋውንም እሳት ከቶ አልነካውም በአማሩ ልብሶችም ገንዘውና ተሸክሞ ወስዶ ከቆጵሮስ ከተማ ውጭ በዋሻ ውስጥ አኖረው።
#ስለእርሱ መፅሐፍ "ደግ #መንፈስ_ቅዱስ የሞላበት ነው።" ይላልና ክብር ይገባዋል።(ሐዋ.11÷24)
#አባ_ይስሐቅ_ጻድቅ
ይህ ቅዱስ በመካከለኛው ዘመን በምድረ ግብጽ የነበረ ገዳማዊ ነው:: መንኖ ለብዙ ዘመናት በገዳም ሲኖር ምኞቱ አንዲት ብቻ ነበረች:: #እመቤታችንን በአካል መመልከትን ይፈልግ ነበር::
የገዳሙ ጠባቂ በመሆኑ መነኮሳት ሲተኙ መቅደሱን ከፍቶ በድንግል #ማርያም ስዕል ፊት ይጸልይ: ይሰግድ: ያነባ ነበር:: እንዲህ ለ7 ዓመታት ስለ ተጋ ድንግል #እመ_ብርሃን ልመናውን ሰማች::
በዚህ ዕለትም ከፀሐይ 7 እጅ ደምቃ ወደ እርሱ መጣች:: ደንግጦ ሲወድቅ አነሳችው:: "ከ3 ቀናት በሁዋላ እመለሳለሁ" ብላም ተሠወረችው:: በ23ም ዐረፈ::
"በዛቲ ዕለት ሶበ ጸለየ ጥቡዐ::
ለይስሐቅ አስተርዓየቶ እም አይቆናሃ ወጺአ::
እምጸዳለ መብረቅ ጥቀ እንዘ ትጸድል ስብአ::" እንዳለ ደራሲ:: (አርኬ)
የመድኃኔዓለም ቸርነቱ የድንግል እናቱ ምልጃዋ ከእኛ ጋር ይሁን፤ በሐዋርያ ቅዱስ በርናባስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ_21 )

#ታኅሣሥ_21_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ገላትያ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከዚያ ወዲያ ከአሥራ አራት ዓመት በኋላ ከበርናባስ ጋር ቲቶን ደግሞ ይዤ ወደ ኢየሩሳሌም ሁለተኛ ወጣሁ፤
² እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ ምናልባትም በከንቱ እንዳልሮጥ ወይም በከንቱ ሮጬ እንዳልሆን በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል አስታወቅኋቸው፤ ዋኖች ግን መስለው ለሚታዩ ለብቻቸው አስታወቅኋቸው።
³ ነገር ግን ከእኔ ጋር የነበረ ቲቶ እንኳ የግሪክ ሰው ሲሆን ይገረዝ ዘንድ ግድ አላሉትም፤
⁴ ነገር ግን ባሪያዎች ሊያደርጉን በክርስቶስ ኢየሱስ ያለንን አርነታችንን ይሰልሉ ዘንድ ሾልከው በስውር ስለ ገቡ ስለ ሐሰተኞች ወንድሞች ነበረ።
⁵ የወንጌልም እውነት በእናንተ ዘንድ ጸንቶ እንዲኖር ለአንድ ሰዓት እንኳ ለቅቀን አልተገዛንላቸውም።
⁶ አለቆች የመሰሉት ግን፥ በፊት ማን እንደ ነበሩ አይገደኝም፤ እግዚአብሔር የሰውን ፊት አይቶ አያደላም፤ አለቆች የመሰሉት አንዳች እንኳ አልጨመሩልኝምና፥
⁷ ተመልሰው ግን ጴጥሮስ ለተገረዙት የሆነው ወንጌል አደራ እንደ ተሰጠው እንዲሁ ለእኔ ላልተገረዙት የሆነው ወንጌል አደራ እንደ ተሰጠኝ አዩ፤
⁸ ለተገረዙት ሐዋርያ እንዲሆን ለጴጥሮስ የሠራለት፥ ለእኔ ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ እንድሆን ሠርቶአልና።
⁹ ደግሞ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ እነርሱም ወደ ተገረዙት ይሄዱ ዘንድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤
¹⁰ ድሆችን እናስብ ዘንድ ብቻ ለመኑን፥ ይህንም ደግሞ ላደርግ ተጋሁ።
¹¹ ነገር ግን ኬፋ ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃወምሁት፥ ይፈረድበት ዘንድ ይገባ ነበርና።
¹² አንዳንድ ከያዕቆብ ዘንድ ሳይመጡ ከአሕዛብ ጋር አብሮ ይበላ ነበርና፤ በመጡ ጊዜ ግን ከተገረዙት ወገን ያሉትን ፈርቶ ያፈገፍግ ነበርና ከእነርሱ ተለየ።
¹³ የቀሩትም አይሁድ ደግሞ፥ በርናባስ ስንኳ በግብዝነታቸው እስከ ተሳበ ድረስ፥ ከእርሱ ጋር አብረው ግብዞች ሆኑ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ቆላስይስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ጌቶች ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና ለባሪያዎቻችሁ በጽድቅና በቅንነት አድርጉላቸው።
² ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ፤
³ በዚያን ጊዜም ስለ እርሱ ደግሞ የታሰርሁበትን የክርስቶስን ምሥጢር እንድንነግር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን ዘንድ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤
⁴ ልናገር እንደሚገባኝ ያህል እገልጠው ዘንድ ጸልዩልኝ።
⁵ ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ።
⁶ ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።
⁷ የተወደደ ወንድምና የታመነ አገልጋይ በጌታም አብሮኝ ባሪያ የሆነ ቲኪቆስ ኑሮዬን ሁሉ ያስታውቃችኋል፤
⁸-⁹ ወሬያችንን እንድታውቁና ልባችሁን እንዲያጽናና፥ ከእናንተ ከሆነውና ከታመነው ከተወደደውም ወንድም ከአናሲሞስ ጋር ወደ እናንተ የምልከው ስለዚህ ምክንያት ነው፤ የዚህን ስፍራ ወሬ ሁሉ ያስታውቁአችኋል።
¹⁰-¹¹ ከተገረዙት ወገን ያሉት፥ አብሮ ከእኔ ጋር የታሰረ አርስጥሮኮስ የበርናባስም የወንድሙ ልጅ ማርቆስ ኢዮስጦስም የተባለ ኢያሱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ስለ ማርቆስ፦ ወደ እናንተ ቢመጣ፥ ተቀበሉት የሚል ትእዛዝ ተቀበላችሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት እነዚህ ብቻ ናቸው፥ እኔንም አጽናንተውኛል።
¹² ከእናንተ የሆነ የክርስቶስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይጋደላል።
¹³ ስለ እናንተ በሎዶቅያም በኢያራ ከተማም ስላሉቱ እጅግ እንዲቀና እመሰክርለታለሁና።
¹⁴ የተወደደው ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
¹⁵ በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልን።
¹⁶ ይህችም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበች በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምትገኘውን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።
¹⁷ ለአክሪጳም፦ በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ በሉልኝ።
¹⁸ በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው። እስራቴን አስቡ። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ጸጋ ባየ ጊዜ ደስ አለው፥ ሁሉንም በልባቸው ፈቃድ በጌታ ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው፤
²⁴ ደግ ሰውና መንፈስ ቅዱስ እምነትም የሞላበት ነበረና። ብዙ ሕዝብም ወደ ጌታ ተጨመሩ።
²⁵ በርናባስም ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ መጣ፤
²⁶ ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።
²⁷ በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤
²⁸ ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ፤ ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ።
²⁹ ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤
³⁰ እንዲህም ደግሞ አደረጉ፥ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_21_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ 44፥9-10።
"የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች። ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ"፤ መዝ 44፥9-10።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_21_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።
¹⁸ ዘካርያስም መልአኩን፦ እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው።
¹⁹ መልአኩም መልሶ፦ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤
²⁰ እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም አለው።
²¹ ሕዝቡም ዘካርያስን ይጠብቁት ነበር፤ በቤተ መቅደስም ውስጥ ስለ ዘገየ ይደነቁ ነበር።