Telegram Web Link
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_18_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ቆሮ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ በመጽናናታችንም ስለ ቲቶ ደስታ አብልጦ ደስ አለን፥ መንፈሱ በሁላችሁ ዐርፎአልና፤
¹⁴ ለእርሱ በምንም ስለ እናንተ የተመካሁ እንደ ሆነ አላፈርሁምና፥ ነገር ግን ሁሉን ለእናንተ በእውነት እንደ ተናገርን፥ እንደዚህ ደግሞ ትምክህታችን በቲቶ ፊት እውነት ሆነ።
¹⁵ ስለዚህም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደተቀበላችሁት፥ የሁላችሁን መታዘዝ እያሰበ ፍቅሩ በእናንተ ላይ እጅግ በዝቶአል።
¹⁶ በነገር ሁሉ ተማምኜባችኋለሁና ደስ ይለኛል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ይሁዳ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤
¹⁸ እነርሱ፦ በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና።
¹⁹ እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው።
²⁰ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
²¹ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
²² አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥
²³ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።
²⁴ ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው
²⁵ ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² በሐዋርያትም እጅ ብዙ ምልክትና ድንቅ በሕዝብ መካከል ይደረግ ነበር፤ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ ነበሩ።
¹³ ከሌሎችም አንድ ስንኳ ሊተባበራቸው የሚደፍር አልነበረም፥
¹⁴ ሕዝቡ ግን ያከብሩአቸው ነበር፤ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙ ነበሩ።
¹⁵ ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_18_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4።
"ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም። ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ"። መዝ 18፥3-4።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_18_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ኢየሱስም መልሶ፦ ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤
¹⁰ በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል አላቸው።
¹¹ ይህን ተናገረ፤ ከዚህም በኋላ፦ ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ አላቸው።
¹² እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ፦ ጌታ ሆይ፥ ተኝቶስ እንደ ሆነ ይድናል አሉት።
¹³ ኢየሱስስ ስለ ሞቱ ተናግሮ ነበር፤ እነርሱ ግን ስለ እንቅልፍ መተኛት እንደ ተናገረ መሰላቸው።
¹⁴ እንግዲህ ያን ጊዜ ኢየሱስ በግልጥ፦ አልዓዛር ሞተ፤
¹⁵ እንድታምኑም በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ወደ እርሱ እንሂድ አላቸው።
¹⁶ ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት፦ ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን #ሐዋርያት_ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የሲመት በዓልና የሐዋራዊው ቅዱስ ቶማስና የቅዱስ ቲቶ የሥጋ ፍልሰት በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#የዕለቱ_አንገርጋሪ_ግእዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "#ብፁዕ_ውእቱ_አባ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን ሰበከ ምጽአቶ #ለወልደ_እግዚአብሔር ሜጦሙ ለኃጥአን እምጽልመት ውስተ ብርሃን"፡፡ ትርጉም፦ #አባ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን (ብርሃንን የሚገልጽ) ንዑድ ክቡር ነው። #የወልደ_እግዚአብሔርን መምጣት አስተማረ ኃጢአተኞችን ከጨለማ ወደ ብርሃን መለሳቸው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ
#ታኅሣሥ_19

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ ቀን በዚህች ዕለት #ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ውስጥ ያዳነበት ዕለት ነው፣ መልአከ ሞትን ለሦስት ወራት ከበራቸው ላይ ያቆሙት #አቡነ_ስነ_ኢየሱስ ዕረፍታቸው ነው፣#አቡነ_ዮሐንስ_ዘቡርልስ ዕረፍታቸው ነው፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል

ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ያዳነበት ነው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር ከአባታቸው ከይሁዳው ንጉሥ ከኢዮአቄም ጋር የማረካቸው አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ #እግዚአብሔር በዚህች ዕለት መልአኩን ልኮ ታላቅ ተአምር አድርጎላቸዋል፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር እነዚህን ወጣቶች በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ጥበብን እያስተማረ ካሳደጋቸው በኋላ በባቢሎን ሀገሮች ሁሉ ውስጥ ሾማቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉ ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ለጣዖቱ ባለመስገድ #እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ የጸኑት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ስለ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡-
‹‹ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፡፡ ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፣ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፣ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፣ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፣ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ፡፡ አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፡- ‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ! የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፣ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል፡፡ ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡፡› ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፣ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፤ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ፡፡

በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ፡፡ ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ ‹ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ፡፡ አንተ ንጉሥ ሆይ የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤ ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ፡፡ በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም፡፡› ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው፡፡ ናቡከደነፆርም ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ! አምላኬን አለማምለካችሁ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?›› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡን ‹ናቡከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም፡፡ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ› አሉት፡፡

የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፡፡ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፡፡ እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ፡፡ ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ፡፡ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ፡፡ የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ‹ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ እርሱም ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል› ብሎ መለሰ፡፡ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ ‹እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም! ኑ ውጡ› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ፡፡

መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፣ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡ ናቡከደነፆርም መልሶ ‹መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፣ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ፡፡ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፣ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ› አለ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡›› ትንቢተ ዳንኤል 3፡1-30፡፡

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_ስነ_ኢየሱስ

በዚኽች ዕለትም መልአከ ሞት መስከረም 19 ቀን መጥቶ "ጊዜ ዕረፍትህ ደርሷል" ቢላቸው "የ #ቅዱስ_ገብርኤልን በዓል ሳላከብር አይሆንም" ብለው መልአከ ሞትን ለ3 ወራት ከበራቸው ላይ ገዝተው ያቆሙት ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ስነ ኢየሱስ ዕረፍታቸው ነው።
አቡነ ስነ ኢየሱስ የትውልድ ሀገራቸው ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን ልዩ ቦታው ልብሆ ይባላል። አባታቸው አብርሃም እናታቸው አስካለ ማርያም ይባላሉ። ጻድቁ ስነ ኢየሱስ ከሽዋ ምድር ተነሥተው ወደ ታች አርማጭሆ በመሄድ በበረሃ ውስጥ በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ በ #ቅዱስ_ገብርኤል መሪነት በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ወደ ሰሜን ጎንደር አርማጭሆ በመሄድ የወርቅ ለብሆ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ የተባለው ገዳም እንደገና አቅንተው በጽኑዕ ተጋድሎ ለብዙ ጊዜ ኖረዋል። ገዳማቸው ታች አርማጭሆ ከሳንጃ ከተማ የ3 ሰዓት መንገድ ይወስዳል።

መልአከ ሞትን ገዝተው ያቆሙት ጻድቁ ለ300 ዓመት በአንዲት ዐለት ላይ ቆመው ጸልየዋል። አቡነ ስነ ኢየሱስ ብዙ መናንያን አርድእትን ያፈሩ ታላቅ አባት ሲሆኑ በደመና እየተጫኑ ከመጓዝ ጀምሮ በርካታ አስገራሚ ተአምራትን በማድረግም ይታወቃሉ፡፡ ጻድቁ "የ #ቅዱስ_ገብርኤልን በዓል ሳላከብር አይሆንም" ብለው መልአከ ሞትን ለ3 ወራት ከበራቸው ላይ ካቆሙትና በዓሉን ካከበሩ በኃላ ታኅሣሥ 19 ቀን በሰላም ዐርፈዋል፡፡

በእርሳቸውም ግዝት መሠረት መልአከ ሞት ከቆመበት ሳይነቃነቅ ከመስከረም 1 ቀን እስከ ታኅሣሥ 19 ቀን ቆመ። ጻድቁም የ #ቅዱስ_ገብርኤልን ዝክር ዘክረው እንደፈጸሙ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ታኅሣሥ 19 ቀን ድንግል እናቱን ቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕይት #ድንግል_ማርያምን፣ እልፍ አእላፍ መላእክትን፣ ሐዋርያትን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ የከበሩ መነኮሳትን አስከትሎ በመምጣት እንዲህ የሚል ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፦ "ቦታህን ሊሳለም የመጣውን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሄደ እቆጥርለታለሁ፤ በቦታህ ከወደቀው ፍርፋሪ እንኳን በስምህ የወደቀውን ምግብ ቢመገብ አማናዊውን ሥጋዬን ደሜን እንዲቀበል አደርገዋለሁ፤ የእጀ ሰብዕ ሥራይ የተደረገበት ሰው ከመቃብርህ አፈር አዋሕዶ በውኃ ቢረጨው ሥራዩን እፈታለታለሁ:: በሬም ላምም ቢሆን ቢታመምበት በስምህ ጻድቁ ስነ ኢየሱስ ብሎ ቢማጸን በደልና ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ።" ጻድቁ በዚኽች ዕለት ዐርፈዋል።

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አቡነ ስነ ኢየሱስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ዮሐንስ_ዘቡርልስ

ዳግመኛም በዚኽች ዕለት በሚቀድስበት ጊዜ ፊቱ እሳት ሆኖ ይታይ የነበረውና በጸሎቱ እሳት ከሰማይ አውርዶ መናፍቃንን ያቃጥል የነበረው አቡነ ዮሐንስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም ቅዱስ ቡርልስ በምትባል አገር ኤጲስቆጶስ የነበረው ነው፡፡ በሕፃንነቱ ወላጆቹ እጅግ የከበሩ ስለነበሩ እነርሱ በሞቱ ጊዜ የወላጆቹን የተትረፈረፈ ንብረት ወስዶ ቤተ ክርስቲያን ሠራበት፡፡ የእንግዳ ማረፊያ ሕመምተኞች የሚያርፉበት ቤትም ሠራበትና በውስጡ ብዙ ነዳያንን አስቀምጦ ይንከባከባቸው ነበር፡፡ ገንዘቡንም ሁሉ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጥቶ አባ ዳንኤል ለአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት በነበረበት ወቅት ወደ አስቄጥስ ገዳም ገብቶ በአንድ ዋሻ ውስጥ እየተጋደለ መኖር ጀመረ፡፡ አባ ዳንኤልም አመነኮሱት፡፡ ሰይጣናትም በተጋድሎው ቀንተውበት በብዙ መከራና ሕመማም ፈተኑት፤ #ጌታችንም ፈወሰው፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ዮሐንስ ቡርልስ በምትባ አገር ኤጲስቆጶስ ሆኖ ተሾመ፡፡

በዘመኑም በሀገሮች ውስጥ ኑፋቄ የያዙ ሐሰተኞች የበዙ ነበሩ፡፡ ከላይኛው ግብፅ የተነሣ አንድ ሰው ‹‹ቅዱስ ሚካኤል ምሥጢር ይገልጥልኛል›› በማለት ብዙዎችን አሳታቸው፡፡ አባ ዮሐንስም ይህን አሳች ሰው ይዘው እንዲገርፉት አዘዘ፡፡ በተገረፈም ጊዜ ስህተቱን አምኖ ከሀገር አሳደዱት፡፡ ‹‹ነቢይ ዕንባቆም ይታየኛል ብዙ ምሥጢርም ይገልጥልኛል›› የሚል ሌላ ሰውም ተነሥቶ ነበር፡፡ በሐሰት ትምህርቱም ብዙ ተከታዮችን አፈራ፡፡ አባ ዮሐንስ ይህንንም አሳች ገርፈው እንዲያባርሩት አደረገ:: መጻሕፍቶቹንም አቃጠላቸው፡፡ የሳቱትንም በትምህርቱ መለሳቸው፡፡

አባ ዮሐንስ በሚቀድስበት ጊዜ ፊቱ እሳት ይሆናል፡፡ ሥጋውም ከእሳት ምድጃ ውስጥ እንደወጣ ይሆናል፡፡ የመላእክትን ሠራዊት በመሠዊያው ዙሪያ በግልጽ ያያቸዋልና ዕንባውንም እንደ ዝናብ ያዘንባል፡፡ ኅብስቱን በሚፈትት ጊዜ ጽዋውን ሲባርከው እንደፍሕም የጋለ ሆኖ ጽዋውን ያገኘዋል፡፡ በቀን በልተው የሚቆርቡ ክፉ ሰዎች ተነሥተው ሳለ አስተምሮ ሊመልሳቸው ቢሞክር ፈጽመው እምቢ አሉት፡፡ ባልተመለሱም ጊዜ አወገዛቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ዮሐንስ ወደ #ጌታችን ቢጸልይ እሳት ከሰማይ ወርዳ አቃጠለቻቸውና ለብዙዎች መቀጣጫ ሆኑ፡፡ የአባ ዮሐንስ ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ እንጦንስንና መቃርስን #ጌታችን ልኳቸው መጥተው የቅዱስ ዮሐንስን ዕረፍቱን ነገሩት፡፡ ሕዝቡንም ሰብስቦ በቀናች ሃይማኖት እንዲኖሩ ካስጠነቀቃቸው በኋላ ታኅሣሥ 19 በሰላም ዐረፈ፡፡

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን መላእክት፣ በጻድቃን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ_19 እና #ከገድላት_አንደበት)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_19_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ተሰሎንቄ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶-⁷ ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።
⁸ እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤
⁹-¹⁰ በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር፥ ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊገረም ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።
¹¹-¹² ስለዚህም ደግሞ እንደ አምላካችን እንደ ጌታም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር እናንተም በእርሱ ዘንድ ልትከብሩ፥ አምላካችን ለመጥራቱ የምትበቁ አድርጎ ይቈጥራችሁ ዘንድ፥ የበጎነትንም ፈቃድ ሁሉ የእምነትንም ሥራ በኃይል ይፈጽም ዘንድ ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ይሁዳ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
²¹ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
²² አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥
²³ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።
²⁴ ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው
²⁵ ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ አርባ ዓመትም ሲሞላ የጌታ መልአክ በሲና ተራራ ምድረ በዳ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው።
³¹-³² ሙሴም አይቶ ባየው ተደነቀ፤ ሊመለከትም ሲቀርብ የጌታ ቃል፦ እኔ የአባቶችህ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ ብሎ ወደ እርሱ መጣ። ሙሴም ተንቀጥቅጦ ሊመለከት አልደፈረም።
³³ ጌታም፦ የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች ምድር ናትና የእግርህን ጫማ አውልቅ።
³⁴ በግብፅ ያሉትን የሕዝቤን መከራ ፈጽሜ አይቼ መቃተታቸውንም ሰምቼ ላድናቸው ወረድሁ፤ አሁንም ና፥ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ አለው።
³⁵ ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_19_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
  "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስምከ"። መዝ 137፥1-2።
"አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ የአፌን ነገር ሰምተኸኛልና፤ በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ። ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና"። መዝ 137፥1-2።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_19_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።
¹² ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት።
¹³ መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።
¹⁴ ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።
¹⁵ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤
¹⁶ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል።
¹⁷ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።
¹⁸ ዘካርያስም መልአኩን፦ እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው።
¹⁹ መልአኩም መልሶ፦ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤
²⁰ እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም አለው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታችን_የማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ገብርኤል በዓል፣ የቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ የዕረፍት በዓል፣ የአቡነ ስነ ኢየሱስ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
📷 እርግጠኛ ነኝ ፕሮፍይሎን ለመቀየር ፈልገው ፕሮፍይል የሚያደርጉት ጠፍቶ  ተቸግረው ያውቃሉ።

የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ መንፈሳዊ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው👇👇👇👇👇👇📷

https://www.tg-me.com/addlist/gpX29GzfGs43MWE0
#ታኅሣሥ_20

#ቅዱስ_ሐጌ_ነቢዩ

አንድ አምላክ በሚሆን በ አብ በ #ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም

ታኅሣሥ ሃያ በዚህች ዕለት ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ፣ ከሌዊ ነገድ ከአሮን ትውልድ የሆነው ቅዱስ ሐጌ ዐረፈ። እርሱም ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው። ናቡከደነጾርም የኢየሩሳሌምን ሕዝብ በማረከ ጊዜ የዚህ ጻድቅ ነቢይ ወላጆች ከእስራኤል ልጆች ጋር ወደ ባቢሎን አገር ተማርከው ሔዱ ዳርዮስ የተባለውም ኵርዝ በነገሠ ጊዜ በሁለተኛው ዘመነ መንግሥቱ ይህ ነቢይ ትንቢት ተናገረ።

የእስራኤልን ልጆች ወደ አገራቸው ይገቡ ዘንድ ኵርዝ ዳርዮስ በአሰናበታቸው ጊዜ እነርሱም ከገቡ በኋላ ቤተ መቅደስን ከመሥራት ቸለል በአሉ ጊዜ እነርሱ ግን በአማሩና በተሸለመ ቤቶች ውስጥ ይኖሩ ነበርና እንዲህ አላቸው። "ሁሉን የሚገዛ #እግዚአብሔር እንዲህ አለ የኔ ቤት ፈርሷል እናንተ ግን ሁላችሁም ቤታችሁን ታጸናላችሁ" አላቸው። "ስለዚህ ከምድር በላይ ያለች ሰማይ ዝናም ለዘር ትነሣለች ምድርም ፍሬዋን አትሰጥም" አላቸው።

ከሕዝቡም ደናጎቻቸው ሰምተው እጅግ ፈሩ የ #እግዚአብሔርንም መመስገኛ ቤት እንደሚገባ መሥራት ጀመሩ። ይህም ጻድቅ ነቢይ ሰባ ዓመት ያህል ኖረ የትንቢቱም ወራት ክብር ይግባውና #ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በአራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነው። ከዚህ በኋላም በሰላም በፍቅር ታኅሣሥ 20 ቀን ዐረፈ።

"#ሰላም_ለሐጌ_ዘተነበየ_በፆታ። ሚጠተ ፂዉዋን ሕዝብ ወሕንፀተ መቅደስ ድኅረ ንስተታ። በእንተ ማርያምኒ ዘተደንገለት በመንታ። ለቤት ደኀሪት እንተ ትገብር ድሉታ። እምነ ቀዳሚት ይቤ ይኄይስ ትርሲታ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የታኅሣሥ 20።

በተጨማሪ በዚች ቀን #ከንግሥት_ታውፊና#ከአውጋንዮስና #ከማድዮስም መታሰቢያቸው ነው።

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ሐጌ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ_20)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_20_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።
¹² ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።
¹³ በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤
¹⁴ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤
² ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤
³ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።
⁴ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።
⁵ ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።
⁶ ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤
⁷ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
⁸ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
⁹ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
¹⁰ ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ስለዚህም ነገ ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ ስሄድ፥
¹³ ንጉሥ ሆይ፥ በመንገድ ሳለሁ እኩል ቀን ሲሆን በዙሪያዬና ከእኔ ጋር በሄዱት ዙሪያ ከፀሐይ ብሩህነት የበለጠ ብርሃን ከሰማይ ሲበራ አየሁ፤
¹⁴ ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ።
¹⁵ እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ ማንነህ? አልሁ። እርሱም አለኝ፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።
¹⁶ ነገር ግን ተነሣና በእግርህ ቁም፤ ስለዚህ እኔን ባየህበት ነገር ለአንተም በምታይበት ነገር አገልጋይና ምስክር ትሆን ዘንድ ልሾምህ ታይቼልሃለሁና።
¹⁷-¹⁸ የኃጢአትንም ስርየት በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ዓይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥ ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_20_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ። እማንቱ ይምርሓኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ። መዝ. 42÷3-4
“ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።” መዝ. 42÷3-4
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_20_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
² ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
³ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።
⁴ በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።
⁵ ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።
⁶ ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤
⁷ ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ።
⁸ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም።
⁹ ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።
¹⁰ በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።
¹¹ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።
¹² ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
¹³ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።
¹⁴ ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።
¹⁵ ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ፦ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።
¹⁶ እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤
¹⁷ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።
¹⁸ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።
¹⁹ አይሁድም፦ አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_አትናቴዎስ_ቅዳሴ ነው። መልካም ከጌታችን 9ኙ ንዑሳን በዓላት ለእለተ #ብርሃን በዓል፣ ለነብዩ ቅዱስ ሐጌ የዕረፍት በዓል፣ መልካም ዕለተ ሰንበት እና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
መልካም ዜና ለአእላፍት ዝማሬ ቤተሰቦች ❤️‍🔥

የአእላፍት ዝማሬ መዝሙሮችን በነፃ የምታገኙበት አዲስ ቻናል ተገኝቷል፣ በቀላሉ ቻናሉን ለማግኘት
👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ነብዩ_ሐጌ

በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

#ሐጌ ማለት በዓል፣ ደስታ ማለት ነው፡፡ የስሙ ትርጓሜ ሕዝቡ ከምርኮ የሚመለሱ ስለኾነ ይኽን ደስታ የሚያስረዳ ነው፡፡

➛በብሉይ ኪዳን በመጨረሻ የምናገኛቸው ሦስቱን መጻሕፍት ማለትም ትንቢተ ሐጌ፣ ትንቢተ ዘካርያስና ትንቢተ ሚልክያስ ከምርኮ በኋላ ስላለው ጊዜ እንዲኹም አይሁድ ከምርኮ እንዴት ወደ አገራቸው እንደተመለሱ የሚያስረዱ ናቸው፡፡ በዚያ አንጻር ግን ደቂቀ አዳም ከዲያብሎስ ምርኮ እንደምን ወደ #እግዚአብሔር እንደተመለሱ የሚያስረዱ ናቸው፡፡

➛ነቢዩ ሐጌ የተወለደው በምርኮ በባቢሎን ሲኾን ትንቢቱን ሲናገር የ፸፭ ዓመት ሽማግሌ ነበር፡፡ የእስራኤል ቅሪቶች ወደ ኢየሩሳሌም በዘሩባቤል አማካኝነት ሲመለሱ ነቢዩ ሐጌም ከተመለሱት ጋር አንዱ ነበር፡፡

➛በ፭፻፴፰ ቅ.ል.ክ. ላይ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ አንድ አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡ አዋጁም አይሁድ ወደ አገራቸው እንዲመለሱና ቤተ መቅደሱን እንዲሠሩ የሚፈቅድ ነበር /ዕዝራ ፩፡፩-፲፩/፡፡ በዚኽም መሠረት የቤተ መቅደሱን ሥራ በ፭፻፴፮ ላይ የቤተ መቅደሱን ሥራ ዠምረዋል፡፡ ነገር ግን አይሁድ ወደ አገራቸው ሲገቡ አገራቸው ባድማ ኾና ስለነበር፣ የዘር ፍሬ በአገሩ ስላልነበረ፣ እንዲኹም በሌሎች ችግሮች ምክንያት ቤተ መቅደሱን መሥራት ትተው ወደየግላቸው ተግባር ተሰማርተው ነበር፡፡ በመኾኑም መንፈሳዊ ሕይወታቸው ዝሎ ነበር፡፡ #እግዚአብሔር ነቢዩ ሐጌንና ነቢዩ ዘካርያስን የላከበት ዋና ምክንያትም የተዠመረውን ቤተ መቅደስ እንዲያጠናቅቁት ለማሳሰብ ነበር፡፡

➛ነቢዩ ሐጌ በሚያገለግልበት ወራት የነበረው ንጉሥ ዘሩባቤል ሲኾን፤ በዚያ ሰዓት የነበረው ሊቀ ካህናት ደግሞ ኢያሱ ይባላል /፩፡፩/፡፡

#ትንቢተ_ሐጌ

➛ነቢዩ ሐጌ በ #እግዚአብሔር ሰዓት የ #እግዚአብሔር ሰው ኾኖ የተገኘ ነቢይ ነው፡፡ አገልግሎቱን በ፭፻፳ ቅ.ል.ክ. ላይ ሲዠምር ጠንካራና ፬ ተከታታይ ስብከቶችን በመስጠት ነበር፡፡ ለሕዝቡ የቤተ መቅደሱ ሥራ እንደተቋረጠ ነገራቸው፤ ሕዝቡ ከቤተ #እግዚአብሔር ይልቅ የራሳቸውን ቤት በመሸላለም እንደተሳቡ ገለጠላቸው፡፡ አራቱን ስብከቶቹም እንደሚከተለው የቀረቡ ናቸው፡-

1. የቤተ መቅደሱን ሥራ እንዲያጠናቅቁት አሳሰባቸው /ምዕ. ፩/፡፡ በዘሩባቤል አማካኝነት ቅሪቶቹ ከባቢሎን ምርኮ ሲመለሱ የ #እግዚአብሔርን ቤት መሥራት ዠምረው ነበር፡፡ ነገር ግን ሥራው ብዙም ሳይቈይ ቆመ፤ ለ፲፮ ዓመት ያኽልም ተስተጓጐለ፡፡ ሕዝቡ የራሳቸውን ቤት ሸላልመው የመሥራት ችግር አልነበረባቸውም፤ ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ግን “ጊዜ አልነበራቸውም”፡፡ እንደዉም፡- “ኢኮነ ጊዜኹ ለሐኒፀ ቤተ #እግዚአብሔር - የ #እግዚአብሔር ቤት የሚሠራበት ዘመን አኹን አይደለም” እያሉ ያመካኙ ነበር፡፡ #እግዚአብሔር ግን በቀጥታ በነቢዩ ሐጌ፣ በአለቃቸው በዘሩባቤልና በሊቀ ካህናቱ በኢያሱ በኵል ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ሰሙ፤ ከ፳፫ ቀን በኋላም የቤተ መቅደሱን ሥራ በድጋሜ ዠመሩት፡፡

2. የኹለተኛው ቤተ መቅደስ ክብር እንዴት እንደኾነ አስረዳቸው /፪፡፩-፱/፡፡ ሕዝቡ የቤተ መቅደሱን ሥራ ለጥቂት ሳምንታት ከቀጠሉ በኋላ ግን አኹንም ተስፋ መቊረጥ ዠመሩ፡፡ ሽማግሌዎቹ የቀድሞው የሰሎሞን ቤተ መቅደስ እንዴት እንደነበረ አስታወሱና ይኽ አኹን የሚሠሩትን ቤተ መቅደስ አቃለሉት፡፡ ነቢዩ ሐጌ ግን የ #እግዚአብሔር ቃል ኪዳን አስታወሳቸው፡፡ #እግዚአብሔር በዚኽ ቤት ያለው ዓላማ ሲገልጥም፡- “ከፊተኛው ይልቅ የዚኽ የኹለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል ይላል የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር” አላቸው /፪፡፱/፡፡ በዚኽ ቤተ መቅደስ አንጻርም በ #ክርስቶስ ስለምትሠራውና በደሙ ስለምትከብረው ቤተ ክርስቲያን ትንቢት ሲናገር ነው፡፡ እንደዉም ቊጥር ፭ ላይ በግልጥ ስለ #መንፈስ_ቅዱስ የሚናገር ነው፡፡

3. የመታዘዛቸው ውጤት የኾነ በረከትን እንደሚባረኩ ነገራቸው /፪፡፲-፲፱/፡፡ ነቢዩ ሐጌ አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ የ #እግዚአብሔር በረከት እንዴት እንደሚርቀው ለካህናቱ አስተማራቸው፡፡ አኹን ግን ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ስለታዘዙ ከዚያች ቀን ዠምሮ እንደምን ባለ በረከት እንደሚባርካቸው አስተማራቸው፡፡

4. በመታዘዛቸው ምክንያት ሊመጣ ያለው በረከት እንዴት እንደኾነ አስታወቃቸው /፪፡፳-፳፫/፡፡ ነቢዩ ሐጌ ሕዝቡ ለ #እግዚአብሔር በመታዘዛቸው እንደምን ባለ የአኹን በረከት እንደሚባርካቸው ከገለጠ በኋላ ዳግመኛም ለዘሩባቤል እንዲኽ አለው፡- “ሰማያትንና ምድርን አናውጣለኹ፤ የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለኹ፤ የአሕዛብንም መንግሥታት ኃይል አጠፋለኹ” /፪፡፳-፳፩/፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስተምሩት ዘሩባቤል የመሲሑ የ #ጌታችንና_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ በዘሩባቤል አንጻር፡- “ዘሩባቤል ሆይ! በዚያ ቀን እወስድኻለኹ ይላል የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር፡፡ እኔ መርጬኻለኹና ይላል የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር፤ እንደ ቀለበት ማተሚያ (እንደ ዳዊት) አደርግኻለኹ ይላል የሠራዊት #ጌታ_እግዚአብሔር” ማለቱም ይኽን የሚያስረዳ ነው /ቊ. ፳፫/፡፡

✍️በአጠቃላይ የነቢዩ ሐጌ ዓላማ

➛ሕዝቡ የትኛው ማስቀደም እንዳለባቸው ለማሳሰብና ምንም ነገር ከመጠበቃቸው በፊት የቤተ መቅደሱን ሥራ እንዲጨርሱት ለማስገንዘብ ነበር፡፡ ነቢዩ ሐጌ እንደነገራቸው ሕዝቡ ከ #እግዚአብሔር በፊት የራሳቸውን ነገር ሲያስቀድሙ ነገሮች እንዴት ከባድ እንደኾኑባቸው ነግሯቸዋል፡፡ ለ 💐እግዚአብሔር ታዝዘው #እግዚአብሔርን ሲያስቀድሙም እንደምን ባለ በረከት እንደሚባርካቸው ግልጽ አድርጐ ነግሯቸዋል፡፡

#እኛስ_ከዚኽ_ምን_እንማራለን ?

📌መጽሐፉን በጥንቃቄ አንብበነው ከኾነ ቃሉ መጣ የሚለው “በነቢዩ በሐጌ እጅ” ነው የሚለው /፩፡፩፣ ፪፡፩፣ ፪፡፲/፡፡ የ #እግዚአብሔር ቃል የሚመጣው በነቢያት አፍ ነው፤ እዚኽ ግን የተገለጠው በነቢዩ እጅ ነው፡፡ ምን ለማለት ነው? ጄሮም የተባለ የጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ሊቅ እንዲኽ ይላል፡- “እጆቻችንን ለመልካም ሥራ ስናነሣ #ክርስቶስም በኹለንተናችን ላይ ይነግሣል፤ ዲያብሎስን ከእኛ ያርቅልናል፡፡ እጅ ሲባል መልካም ሥራን የሚያመለክት ነው፡፡ … #እግዚአብሔር ወደ ሕይወታችን የሚመጣው ስለ ተናገርን አይደለም፤ መልካም ሥራን ስንሠራ እንጂ፡፡”

📌አይሁድ ቤተ መቅደሱን ላለመሥራት ሲያመካኙ የነበረው “ኢኮነ ጊዜሁ - ጊዜው ገና ነው” በማለት ነበር፡፡ ተወዳጆች ሆይ! ብዙዎቻችን በዚኽ መንፈስ የተያዝንበት ዘመን ቢኖር አኹን፡፡ “ጊዜው ገና ነው፤ ቤተ መቅደሱን የምሠራበት ጊዜ አይደለም፤ ገና ወጣት ስለኾንኩ አኹን ወደ #እግዚአብሔር የምቀርበብበት ዘመን አይደለም” እያልን እናመካኛለንና፡፡ ነገ በሕይወት ለመኖራችን ግን እርግጠኞች አይደለንም፡፡ እንኪያስ ሰባኪው እንዳለው የጭንቅ ቀን ሳይመጣ፣ በጕብዝናችን ወራት፣ አፈርም (ሥጋችን) ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ ፈጣሪያችንን እናስብ እንጂ በማመካኘት ጊዜአችንን አናጥፋ /መክ.፲፪፡፩፣፯/፡፡
📌በተራራው ስብከቱ ላይ ጌታ፡- “አስቀድማችሁ የ #እግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፤ ይኽም ኹሉ ይጨመርላችኋል” እንዳለን /ማቴ.፮፡፴፫/ በሕይወታችን ላይ #እግዚአብሔር የማናስቀድም ከኾነ ግን ብዙ ብንዘራም የምናስገባው ጥቂት ነው፤ ብንበላም አንጠግብም፤ ብንጠጣም አንረካም፤ ብንለብስም አይሞቀንም፤ ደመወዛችንን ብንቀበልም በቀዳዳ ኪስ እንደማስቀመጥ ነው /ሐጌ.፩፡፮/፡፡ አዝመራውን በእርሻው ሳለ ባየነው ጊዜ ብዙ ቢመስለንም ወደ ቤታችን ሲገባ በረከት የለውም፤ ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር ይነሣል (ይከለክላል)፤ ምድር የዘራንባትን አታበቅልም፤ የተከልንባትን አታጸድቅም፡፡ በአጭር ቃል በረከት ከእኛ ይርቃል /ሐጌ.፩፡፱-፲፩/፡፡

📌#ወልድ ውሉድ በ #ክርስቶስ ክርስቲያን ተብለን ተጠርተን ሳለ፣ በጥምቀት ከማይጠፋ ዘር ተቈጥረን ሳለ ምድራዊ ቤትን (ፈቃደ ሥጋን) ለመሥራት አማናዊው መቅደሳችንን (ፈቃደ ነፍሳችንን) የምንረሳ ከኾነ በዚኽ ምድር ከእኛ የባሰ ጐስቋላ ሰው የለም /ሐጌ.፩፡፲-፲፩/፡፡

📌ቤተ መቅደሱን (ፈቃደ ነፍሳችንን) የምንሠራ ከኾነ ግን #እግዚአብሔር በረድኤቱ ከእኛ ጋር ይኾናል፤ ጸጋ #መንፈስ_ቅዱስ በእኛ ላይ ትበዛለች፡፡ “ቤተ #እግዚአብሔርን ከሠራችሁበት ቀን ዠምሮ እኽሉን ወይኑን በአውድማ ትርፍርፍ ብሎ ታዩታላችሁ፤ በለሱን ሮማኑን ዘይቱን የሚያፈራውን እንጨት ኹሉ ከዛሬ ዠምሮ አበረክታለኹ” ሲል ይኽን ያመለክታል /ሐጌ.፪፡፳/፡፡

ይኽን እንድናደርግ ሰውን በመውደዱ ሰው የኾነው #ጌታችንና_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ይርዳን አሜን!!!

#ታኅሣሥ_20_በዓለ_ዕረፍቱ_ለነብዩ_ቅዱስ_ሐጌ
2025/01/10 02:08:42
Back to Top
HTML Embed Code: