Telegram Web Link
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
📷 እርግጠኛ ነኝ ፕሮፍይሎን ለመቀየር ፈልገው ፕሮፍይል የሚያደርጉት ጠፍቶ  ተቸግረው ያውቃሉ።

የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ መንፈሳዊ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው👇👇👇👇👇👇📷

https://www.tg-me.com/addlist/gpX29GzfGs43MWE0
#ታኅሣሥ_13

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ዐስራ ሦስት በዚህች ቀን #ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱና ተአምር ያደረገበት ዕለት ነው፣ ታላቁ አባት #አባ_መቃርስ_ገዳማዊ ዓመታዊ የዕርገታቸው መታሰቢያ ነው፣ መነኮስ #አቡነ_አብራኮስ_ገዳማዊ ዕረፍታቸው ነው፣ የሰማዕት #ቅዱስ_በጽንፍርዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሩፋኤል

ታኅሣሥ ዐስራ ሦስት በዚህች ቀን በዚህች ዕለት ፈታሄ ማህጸን ሊቀ መልአክት #ቅዱስ_ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱና ተአምር ያደረገበት ዕለት ነው፡፡ ሰማያውያን ከሆኑ ከመላአክት አለቆች ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ 3ተኛ ነው፡፡ "ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል፡፡ ጦቢት 12፡15፡፡ ሩፋኤል የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል መልአከ የሰላምና የጤና መልአክ ይባላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቁስል ይፈወስ ዘንድ ከልዑል #እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” መጽሐፈ ሄኖክ 6፡3፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡” በማለት ሄኖክ ከ #እግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል፡፡ ሄኖክ 10፡13፡፡ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ በማኅፀን ላለ ችግርና ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት በማሕፀን እያለ ማለትም በ #ሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነት ያለን ረቂቅ ርኩስ መንፈስ ያውቃል፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ጭን ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሠቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል ጦቢት 3፡8-17፡፡

ዳግመኛም #እግዚአብሔር ሩፋኤልን አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ሄኖክ 3፡5-7፡፡ በዚህ መሠረት ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሄኖክ 2፡18፡፡ ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠብቃቸው #እግዚአብሔር እንዳዘዘዉ የሚከፍታቸዉ የሚዘረጋቸዉ ይህ ታላቅ መልአክ ነዉ፡፡

የምህረትና የረድኤት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሥራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል፡፡ "ፈታሄ ማህጸን" ይባላል-እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰዉነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል፡፡ እንደ እምነታቸዉ ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡ ዳግመኛም "ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ" ይባላል-ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ ስለሆነ ነው፡፡ ዳግመኛም "መራሔ ፍኖት" ይባላል-ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና ነው፡፡ እንዲሁም "መላከ ክብካብ" ይባላል-ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ ነው፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዓል እስኪፈፀም ድረስ በከበረ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎፍሎስ ዘመን በምድረ ግብጽ ውስጥ ከእስክንድርያ ውጭ በታናፀች አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ከአሳ አንበሪ ላይ የታነፀች ነበር፡፡ ነገር ግን በወደቡ አጠገብ ከነበረ ግዙፍ አንበሪ ጀርባ ላይ መታነጿን ቀድሞ ያነጿት ሰዎች ቢሆኑ ከካህናትም ቢኾን ያወቀ አልነበረም፡፡

ያ አንበሪም የቤተክርስቲያኑ ህንጻ በከበደው ጊዜ ፈጽሞ ተንቀሳቀሰ፡፡ ከአሸዋማው መሬት ላይ በባህሩ ዳርቻ የታነፀች ይህች ቤተ ክርስቲያንም ከመሰረቷ አናወጻት፡፡ ያን ጊዜ ትልቁም ትንሹም ወንዱም፣ ሴቶችም፣ የተሾሙ ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ሕዝቡም ሁሉ ደነገጡ ታወኩ፡፡ አሣ አንበሪው ግን መንቀሳቀሱን አልተወም፡፡ በመንቀሳቀሱም የቤተ ክርስያኗ ሕንፃ እኩሌታ ይሰነጠቅ ዘንድ ጀመረ፣ ምድርን ተናወፀች፣ ንጉስና፣ ሊቀ ጳጳሳቱም፣ ካህናቱም፣ ዲያቆናቱም፣ ህዝቡም፣ ሁሉም ካሉበት በባህሩ ወደብ ከተሰራች ከዚህች ቤተ ክርስቲያን መናወጥ የተነሳ ፍርሃት መንቀጥቀጥ በላያቸው ወረደ፡፡ ያ አንበሪ ግን በባህሩ ውስጥ ወደፊት መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗም በጀርባው ላይ ነበረች፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የሉትም ሁሉ ያ አሳ አንበሪ ወደ ባሕሩ ውስጥ ሊያሰጥመን ነው ሲሉ አሠቡ፡፡ ያን ጊዜም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ስዕል ፊት በጽኑ አለቀሱ፡፡ በአንድ ቃልም "ገናናው የ #እግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ ርዳታህ ፈጥኖ ይደርስልን ዘንድ በቅድስት ቤተክርስቲያን ወደተሰበሰብን ወዳጆችህ ተመልከት" እያሉ ይጸልዩ ጀመር፡፡ ያንጊዜም የ #እግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ ያችን ቤተክርስቲያን በብሩሃት ክንፎቹ እንደደመና ጋረዳት፡፡ በእጁ በተያዘ የብርሃን በትረ #መስቀሉ ያን ኣሣ አንበሪ ወገቶ "በ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሃይል ከቦታህ ሳትንቀሳቀስ እስከትውልድ ፍፃሜ ዘመን ለዘለአለም ትኖር ዘንድ አዝዝሃለሁ" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያኗን ከነመዓዘኗ ከግርግዳዎቿ ከመሠዊያዋ በውስጧ ተተክለው ካሉት ሁሉ ጋር ከጀርባው ላይ እያለች ያንን አሳ አንበሪ ወግቶ በያዘበት ብርሃናዊ በትረ #መስቀሉ ወደቀድሞው የባሕሩ ወደብ ጎተተው፡፡ ያንጊዜም ግንቡ ቦታውን ሳይለቅ እርስ በእርሱ ተጣበቀ፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አሣ አንበሪውን በቀድሞ ሥፍራው ያቺን ቤተክርስቲያን በቀደመ መሠረቷ ላይ አጽንቷቸዋልና፡፡ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤልም አዳኝ የሆነ የ #ጌታው_የኢየሱስ_ክርስቶስን ስም ጠርቶ ከሞት እንዳዳናቸው ሁሉም አስተዋሉ፡፡ በድንቅ ተዓምራቱ የዳኑ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ በሊቀ መላእክቱ ቅዱስ ሩፋኤል ላይ አድሮ ድንቅ ተዓምራቱን ስለገለጸላቸው የቅዱስ ሩፋኤልን አምላክ #እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ የዚህች ቤተክርስቲያን ታሪክም በዓለም ሁሉ በየአውራጃዎቹም ተሰማ፡፡ የቅርብም የሩቅም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ታላቁ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የለመኑትን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ የነገሩትን ያማልዳቸው ዘንድ በውስጧ ይጸልያሉ፡፡ በዚችም ቤተክርስትያን ብዙ ውስጥ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ታኅሣሥ 13 ቀንም ተአምራቶቹ ከተፈጸመባቸው ዕለታት አንዷ ናት፡፡ ቅዳሴ ቤቱም በዚሁ ዕለት ተከናውኗል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሊቀ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_መቃርስ_ገዳማዊ
ዳግመኛም በዚህች እለት ታላቁ አባት አባ መቃርስ ገዳማዊ ዓመታዊ የዕርገታቸው መታሰቢያ ነው፡፡ ይኸኛው መቃርስ ዕረፍቱ መጋቢት 27 ከሚውለው ከታላቁ መቃርስ ይለያል፡፡ በመቃርስ ስም የሚጠሩ ከ8 በላይ ሌሎች ቅዱሳንም አሉ፡፡ ታኅሣሥ 13 ቀን የዕርገቱ በዓል የሆነው መቃርስ ግን ቆቅ ይመገብ የነበረው መቃርስ ነው፡፡ እርሱም በልጅነቱ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እየተማረ አደገ፡፡ የዓለምን ከንቱነት ተመልክቶ ዳግመኛም የኃጥአንንና የጻቃንን ዋጋቸውን አይቶ ወደ ገዳም ገብቶ መነኮሰ፡፡ ከመነኮሰም በኋላ የ10 ቀን መንገድ ተጉዞ ኩዕንትና ቆቆች ውኃም ካለበት ተራራ ላይ ደረሰ፡፡ እንዲህም አለ፡- ‹‹ለምግቤ ኩዕንትን ወደ መልቀም ብሰማራ የስግደቴና የጸሎቴ ሥራ ይቋረጣል፣ በዚህም ተራራ ላይ ብቸኛ ነኝና ሰብስቦ የሚያስገባልኝ የለም፡፡ ሥጋ አትብላ ያለውስ የባልንጀራችንን ሥጋ በሐሜት የምንበላውን አይደለምን? ሌላ ምግብ እንደሌለኝ ፈጣሪዬ ያውቃል›› ብሎ ከዚያች ዕለት ወዲህ ለምግቡ ቆቅ የሚያጠምድ ሆኖ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ በየቀኑ አንድ አንድ ቆቅ የሚያዙለት ሆነ፡፡ በየቀኑም አንድ አንድ ቆቅ እየተመገበ ውኃ እየጠጣ ፈጣሪውን እያመሰገነ በታላቅ ተጋድሎ ሆኖ የሰውን ፊት ሳያይና ከማንም ጋር ሳይነጋገር ብዙ ዘመን ኖረ፡፡

ከቍስጥንጥንያ ከተማ የመጣ አንድ መነኩሴ ዋሻ ሲፈልግ አባ መቃርስ ደግሞ ቆቅ ሲያጠምድ አየውና ለሐሜት ቸኩሎ ወደ ቍስጥንጥንያ ተመልሶ ሄዶ ለሊቀ ጳጳሳቱ ‹‹ቆቅ እያጠመደ ሥጋ የሚበላ መነኩሴ አገኘሁ፣ እርሱም በሕዝብ ዘንድ ሊያስነቅፈን ነው›› ብሎ ነገረው፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱም ከአንድ ሌላ መነኩሴ ጋር ድጋሚ እንዲያረጋግጡ ላካቸው፡፡ እነርሱም ገና ከበዓቱ ሳይደርሱ አባ መቃርስ ቆቅ ሊያጠምድ ሄደና ያለወትሮው በአንዲት ወጥመድ ሦስት ቆቆችን ተያዙለት፡፡ ሌላ ጊዜ በቀን አንድ ብቻ ነበር የሚያዝለት ዛሬ ግን #እግዚአብሔርም ለሚመጡት እንግዶችም ጭምር ሲያዘጋጅላቸው ነው ያለወትሮው ዛሬ ሦስት ሆነው የተያዙለት፡፡

አባ መቃርስም ሁለቱን መነኮሳት ሲያያቸው ሁለቱ ተጨማሪ ሆነው የተያዙለት ቆቆች የእንግዶቹ መሆናቸውን ዐውቆ #ጌታችንን አመሰገነው፡፡ እነርሱ ግን ማዕድ ሠርቶ እስካቀረበላቸው ድረስ በመቃርስ ላይ ይጠቋቆሙበት ነበር፡፡ አባ መቃርስም ምግብን አዘጋጅቶ ሲጨርስ የራሱን ድርሻ አንዷን ቆቅ አስቀርቶ ሁለቱን ለእንግዶቹ አቀረበላቸው፡፡ እርሱ በልቶ ጨርሶ ቀና ሲል እንግዶቹ መነኮሳት እንዳልበሉ ተመለከተና ‹‹አባቶቼ ለምን አልበላችሁም?›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹እኛ መነኮሳት ስለሆንን ሥጋ አንበላም ትኅርምትም አለን›› አሉት፡፡ አባ መቃርስም ‹‹እሺ ተውት›› አላቸውና እነዚያን አብስሎ በገበታ ላይ ለምግብነት ያቀረባቸውን ሁለት ቆቆች ሦስት ጊዜ በእስትንፋሱ እፍ ቢልባቸው ሕይወት ዘርተው በረሩና ወደ ጫካ ሄዱ፡፡ እነዚያ መነኮሳትም እጅግ ደንግጠው ‹‹ማረን ይቅር በለን፣ ቅዱሱን የ #እግዚአብሔር ሰው በከንቱ አምተንሃል›› ብለው እግሩ ሥር ሲወድቁ ‹‹ #እግዚአብሔር የሁላችንን በደል ይቅር ይበለን›› አላቸው፡፡

ሁለቱ መነኮሳት ወደ ቍስጥንጥንያ ተመልሰው ለሊቀ ጳጳሳቱና ለሕዝቡ ያዩትን ነገር መሰከሩ፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱም እጅግ ተደንቆ ወደ ንጉሡ ደብዳቤ ጽፎ ‹‹በምድራችን ጻድቅ ሰው ተገኝቷልና አንተም ና ሄደን በረከቱን እንቀበል›› ብሎ መልእክት ላከበት፡፡ ንጉሡም እሺ ብሎ ከሠራዊቱ ጋር ተነሥቶ ከካህናቱ ጋር ወደ አባ መቃርስ ዘንድ ሄዱ፡፡ ወደ ገዳሙም በቀረቡ ጊዜ አባ መቃርስን ወደ ብሔረ ሕያዋን ያደርሰው ዘንድ መልአክ አንሥቶ በክንፎቹ ተሸክሞት ሲያርግ አዩት፡፡ እነርሱም ‹‹የ #እግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ ባርከን፣ የምንድንበትንም አንዲት ቃል ንገረን›› አሉት፡፡ አባ መቃርስም ‹‹ከሐሜትና ከነገር ሥራ አንደበታችሁ ይከልከል፤ ካህን ብዙ ባይማር ትዕቢትና መታጀር ባልመጣበት ነበር፣ መነኩሴም ትኅርምት ባያበዛ ባልተመካም ነበር፡፡ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ #እግዚአብሔር አድሮባችሁ ይኑር›› አላቸው፡፡ ይህንንም ከተናገራቸውና ከባረካቸው በኋላ ከዐይናቸው ተሰወረ፡፡ ይህም ዕርገቱ ታኅሣሥ 13 ቀን የተፈጸመ ነው፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ መቃርስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_አብራኮስ_ገዳማዊ

ዳግመኛም በዚህች ቀን መነኮስ አቡነ አብራኮስ ገዳማዊ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ይኽም ቅዱስ ዕድሜው 20 ዓመት በሆነው ጊዜ የዚህን ዓለም ኃላፊነት ተረድቶ የነፍሱን ድኅነት ሽቶ መንኩሶ ገዳም ገባ፡፡ በዚያም በታላቅ ተጋድሎ ሲኖር ሰይጣን በቅናት ተነሳስቶበት ብዙ ፈተናዎችን አመጣበት ነገር ግን ቅዱስ አብራኮስ ጽኑ በሆነው መንፈሳዊ ተጋድሎው ሰይጣንን ድልነሣው፡፡ ሰይጣንም በተደጋጋሚ መሸነፉን አይቶ የፈተናውን ዓይነት ለወጥ አድርጎ በስንፍና ሊጥለው ፈለገ፡፡ እናም ሰይጣን በግልጽ ፊት ለፊት ተገልጦ ቅዱስ አብራኮስን ‹‹እነሆ ከዚህ ዕድሜህ ሌላ 50 ዓመት ቀረህ›› አለው፡፡ ቅዱስ አብራኮስም ሰይጣን በስንፍና ሊጥለው ያመጣበት ፈተና መሆኑን ዐውቆ በተራው ሰይጣን ላይ ተራቀቀበት፡፡ እንዲህም አለው፡- ‹‹አሁንስ ልቤን አሳዘንከው፣ እኔ ሌላ መቶ ዓመት እኖር ዘንድ ስላሰብኩ ቸል ብያለሁ ነገር ግን አንተ እንዳልከው 50 ዓመት ከሆነ የምኖረው ከቀድሞው እጅግ አብዝቼ እጋደል ዘንድ ይገባኛል›› አለው፡፡ ሰይጣንም ይህን ጊዜ አፍሮ ከእርሱ ሸሸ፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አብራኮስ ጽኑ የሆነ ተጋድሎውን በገድል መጠመዱን አብዝቶ ከ70 ዓመት ተጋድሎው በኋላ በሰላም ዐረፈ፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_በጽንፍርዮስ_ሰማዕት

በዚህች እለት የሰማዕት ቅዱስ በጽንፍርዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኽም ቅዱስ አባት ዓለምን ንቆ በመመንኮስ በታላቅ ተጋድሎ ይኖር ነበር፡፡ የሚያገለግለውም በምስር አገር በወንዝ ዳር ባለች በሊቀ መላእክት በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡ ስለቀናች ተዋሕዶ ሃይማኖቱም ከእስላሞች መሳፍንት ጋር ተከራከረ፡፡ የ #ጌታችንም_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስን አምላክነቱን ገለጠላቸው፡፡ እስላሞችም ባፈሩ ጊዜ በእርሱ ላይ ተቆጡ፡፡ ከዚህም በኋላ እስላሞች አባ በጽንፍርዮስን ይዘው በእጅጉ አሠቃዩት፡፡ በመጨረሻ ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ፡፡

ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅድስት ሐና እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያምን ጸነሰቻት የሚሉ አሉ። ጸሎቷና በረከቷ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ዳግመኛ በዚህች ዕለት በደብረ ቀለሞን የሚኖር የገዳማዊ የአባ #ሚካኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን መልእክት አና ጻድቃን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታህሣሥ_13 እና #ከገድላት_አንደበት))
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
ኢኦቲሲ ቲቪ በአዲስ አቀራረብ በተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ፕሮግራሞች መዝሙር ፣ ስብከት ፣ ወቅታዊ ዜና ፣ እንዲሁም በሌሎች ፕሮግራሞች በ ቴሌግራም መቷል ሊንክ ለማግኘት ከስር ያሉትን ይጠቀሙ 👇👇👇
ታኅሣሥ 13 #እንኳን_ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ከ9ኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ለሆነው ለ #ስብከት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

#ከታህሳስ ❼ እስከ ታህሳስ ⓭ ቀን ድረስ ያሉት ዕለታት ናቸው፡፡ የእነርሱም ኢየአርግና ኢይወርድ አለው ይኸውም ታህሳስ 1 ኤልያስ ማክሰኞ ቢውል ስብከት ታህሳስ 13 ቀን ይገባል ኤልያስ ረቡዕ ቢውል ስብከት በ12 ይገባል ኤልያስ ሐሙስ ቢውል ስብከት በ11 ይገባል ኤልያስ ዓርብ ቢውል ስብከት በ10 ይገባል ኤልያስ ቅዳሜ ቢውል ስብከት በ9 ይገባል ኤልያስ እሁድ ቢውል ስብከት በ8 ይገባል ኤልያስ ሰኞ ቢውል ስብከት በ7 ይገባል ከእነዚህ ቀን አይበልጥም አያንስም፡፡

ስብከት ማለት ትምህርት ማለት ነው፡፡ ነቢያት የ #ጌታን ሥጋዌ ማስተማራቸው ይነገርበታል፡፡ በዚህ ውስጥም ትንቢት ተናግረዋል ምሳሌ መስለዋል፡፡ ከዚህም ውስጥ

#ትንቢቱ፡- ዳዊት ‹‹ብሩክ ዘይመጽዕ በስመ #እግዚአብሔር›› (መዝ 117-26)
‹‹ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ ወረከብ ናሁ በውስተ ገዳም››(መዝ 131-6)
ኢሳይያስ‹‹ናሁ ድንግል ትጸንስ ወትወልድ ወልደ ወይ ሰመይ #አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ #እግዚአብሔር ምስሌነ››(ት.ኢሳ 7-14)
‹‹ሕጻን ተወልደ ለነ ወልድ ተውህበ ለነ›› ኢሳ 9-6 ላይ ብሏል

ምሳሌዎቹ 1.አዳም የ #ጌታ ምሳሌ ነው አዳም በኃጢአቱ ሰውን ሁሉ እንደጎዳ #ጌታም በትሩፋቱ ሰውን ሁሉ አድኗል አዳም ከኀቱም ምድር ተገኝቷል #ጌታም በኀቱም ማህፀን ተወልዷል፡፡ቨ

❤️አቤል፦ የ #ጌታ ምሳሌ ነው አቤል የገዛ ወንድሙ ገድሎታል /ዘፍ 4-8/ #ጌታም ደቀ መዝሙሩ ይሁዳ ሸጦታልና፡፡

ይስሀቅ የ #ጌታ ምሳሌ ነው ቨ
ይስሀቅ እንደሚሰዋ እያወቀ በእጁ እሳት በትከሻው እንጨት ተሸክሞ አባቱን ተከትሏል፡፡/ዘፍ 21-19/ #ጌታም የሚሰቀልበትን #መስቀል ይዞ ቀራንዮ ወጥቷል፡፡?ቨቨቨ።፡።።
ዮሴፍ የ #ጌታ ምሳሌ ነው
ዮሴፍ ወንድሞቹ ጠልተውት ተመቅኘው በ20 ብር ሸጠውታል
#ጌታም ደቀ መዝሙሩ በ30 ብር ሸጦታል ዮሴፍን ወንድሞቹ ከሸጡት በኋላ ልብሱን በጠቦት ደም ነክረው ለአባቱ አሳይተውታል ➛ልብሱ የትስብዕት
➛ዮሴፍ የመለኮት
➛ደም የህማም የሞቱ ምሳሌ
#ደም ከልብሱ እንጂ ከዮሴፍ አለመገኘቱ ሕማሙ ሞቱ በትስብዕት/በሥጋ/ እንጅ በመለኮት ላለመኖሩ ምሳሌ ነው
#አንድም ዮሴፍ ልጥላቸው አላለም ይልቁንም ምግባቸውን ልብሳቸውን ሰጥቷቸዋል፡፡/ዘፍ 43-34/ #ጌታም መግደል ማጥፋት ሲቻለው ሲገርፉት ሲቸነክሩት ልጥላቸው ላጥፋቸው ሳይል‹‹አባ ስረይ ሎሙ›› ብሏልና ሉቃ 23-34

ገራህተ ሙሴ:-
ሙሴ #ጌታን ፊትህን ላይ እወዳለሁ ባለ ጊዜ #ጌታ ዘር ካልወደቀባት ምድር የበቀለች ስንዴ አምጥተህ ብትሰዋልኝ እታይሀለው ብሎታል፡፡/ዘጸ 33÷12-23/
#ገራህት_የእመቤታችን
#ስንዴ_የጌታ ምሳሌ ነው
#ከድንግል ያለ ዘርዐ ብእሲ ተወልጄ መስዋዕት ሆኜ በምቀርብበት ጊዜ በደብረ ታቦር እታይሀለው ሲለው ነው፡፡

መሰንቆ ዘዳዊት
ዳዊት :- ሀብተ መሰንቆ ተሰጥቶታል በሚደረድርም ጊዜ ከመሰንቆው የሚወጣ ድምጽ ህሙማንን የሚፈውስ ነበር፡፡/1ኛ ሳሙ 16-20
#መሰንቆ_የእመቤታችን
#ድምጹ_የጌታ ምሳሌ
#ከመሰንቆው በሚወጣ ድምጽ ህሙማን መፈወሳቸው➛ ከ #እመቤታችን በተወለደ በ #ጌታ ድህነተ ዓለም ፈውሰ ዓለም ለመገኘቱ ምሳሌ ነው፡፡

ምስራቀ ፀሐይ :- ፀሐይ በምስራቅ ይወጣል
#ፀሐይ_የጌታ
#ምስራቅ_የእመቤታችን ምሳሌ ነው
#ቅዱስ_ያሬድ ‹‹አንቲ ምስራቅ ወወለድኪ ፀሐየ ጽድቅ›› እንዳለ
#ፀሐይ_በምስራቅ ወጥታ ዓለምን እንደምታበራ ጨለማን እንደምገፍ ሁሉ
#ከእመቤታችንም_ክርስቶስ ተወልዶ ለዓለም ሁሉ ብርሃን ሆኖ ጨለማ/መርገመ ስጋ መርገመ ነፍሳችንን/ የማባረሩ የመደምሰሱ ምሳሌ ነው፡፡ ‹‹አነ ውእቱ ብርሀኑ ለዓለም›› እንዳለ ጌታችን በዘመነ ስጋዌው፡፡

አክሊል:- ዘሰሎሞን
ሰሎሞን ስመ አምላክ የተቀረጸበት ሐቲም ቀለበት ነበረው ግርማ ሞገሱ ትምህርተ መንግስቱ ነው፡፡ መንግስቱን አጥቶ ሁለት ሳምንት ያህል በገዛ ከተማው ሲለምን ከቆየ በኋላ ከሞተ አሳ ሆድ ውስጥ አግኝቶት እስራኤል አጅበውት ወደ መንግስቱ ተመልሷል፡፡
#ቀለበቱ_የእመቤታችን
#መንግስቱ_የአዳም_ምሳሌ_ነው
#መንግስቱ በቀለበቱ እንደተመለሰለት አዳምም በዕፀ በለስ ምክንያት ያጣትን ልጅነት በ #እመቤታችን ምክንያት አግኝቷልና፡፡

ሰዋሰው ዘወርቅ(የወርቅ መሰላል):- #ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ሌሊት በህልሙ የወርቅ መሰላል ከምድር እስከ ሰማይ ተተክላ መላዕክት ሲወጡባትና ሲወርዱባት በላይዋ ዙፋን ተጎናፅፎ በዙፋኑ ላይ ንጉሥ ተቀምጦ አይቷል ዘፍ 28-10
#የወርቅ_መሰላል_የእመቤታች #እመቤታችን መሆኗን ያጠይቃል።
በነዚህ እና በመተለያዩ ምሳሌዎች ነቢያት እየመሰሉ #ክርስቶስ እንደሚወለድ ይሰብኩ ነበርና ይህ ወቅት ዘመነ ስብከት ተብሏል።

✍️መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
ኢኦቲሲ ቲቪ በአዲስ አቀራረብ በተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ፕሮግራሞች መዝሙር ፣ ስብከት ፣ ወቅታዊ ዜና ፣ እንዲሁም በሌሎች ፕሮግራሞች በ ቴሌግራም መቷል ሊንክ ለማግኘት ከስር ያሉትን ይጠቀሙ 👇👇👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_13_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዕብራውያን 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥
² ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤
³ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤
⁴ ከመላእክት ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ ይበልጣል።
⁵ ከመላእክትስ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፥ ደግሞም፦ እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል ያለው ከቶ ለማን ነው?
⁶ ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ ይላል።
⁷ ስለ መላእክትም፦ መላእክቱን መናፍስት አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ ይላል፤
⁸ ስለ ልጁ ግን፦ አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።
⁹ ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ ይላል።
¹⁰ ደግሞ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤
¹¹ እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥
¹² እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ይላል።
¹³ ነገር ግን ከመላእክት፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ ከቶ ለማን ብሎአል?
¹⁴ ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ጴጥሮስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የምጽፍላችሁ መልእክት ይህች ሁለተኛይቱ ናት። በቅዱሳን ነቢያትም ቀድሞ የተባለውን ቃል በሐዋርያቶቻችሁም ያገኛችኋትን የጌታንና የመድኃኒትን ትእዛዝ እንድታስቡ በሁለቱ እያሳሰብኋችሁ ቅን ልቡናችሁን አነቃቃለሁ።
³ በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ፤
⁴ እርሱም፦ የመምጣቱ የተስፋ ቃል ወዴት ነው? አባቶች ከሞቱባት ጊዜ፥ ከፍጥረት መጀመሪያ ይዞ ሁሉ እንዳለ ይኖራልና ይላሉ።
⁵ ሰማያት ከጥንት ጀምረው ምድርም በእግዚአብሔር ቃል ከውኃ ተጋጥማ በውኃ መካከል እንደ ነበሩ ወደው አያስተውሉምና፤
⁶ በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረ ዓለም በውኃ ሰጥሞ ጠፋ፤
⁷ አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።
⁸ እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
⁹ ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
¹⁰ የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ አሁንም፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ እንደ አለቆቻችሁ ደግሞ ባለማወቅ እንዳደረጋችሁት አውቄአለሁ፤
¹⁸ እግዚአብሔር ግን ክርስቶስ መከራ እንዲቀበል አስቀድሞ በነቢያት ሁሉ አፍ የተናገረውን እንዲሁ ፈጸመው።
¹⁹-²⁰ እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።
²¹ እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና።
²² ሙሴም ለአባቶች፦ ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል፤ በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት።
²³ ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች አለ።
²⁴ ሁለተኛም ከሳሙኤል ጀምሮ ከእርሱም በኋላ የተናገሩት ነቢያት ሁሉ ደግሞ ስለዚህ ወራት ተናገሩ።
²⁵ እናንተ የነቢያት ልጆችና እግዚአብሔር ለአብርሃም፦ በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ፥ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ።
²⁶ ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_13_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ፈኑ እዴከ እምአርያም። አድኅነኒ ወባልሐኒ እማይ ብዙኅ። ወእምእዴሆሙ ለደቂቀ ነኪር"። መዝ 143፥7።
“እጅህን ከአርያም ላክ አድነኝም ከብዙ ውኆች፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥ ቀኛቸው የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ።” መዝ 143፥7።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_13_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴⁴ በነገው ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊወጣ ወደደ፥ ፊልጶስንም አገኘና፦ ተከተለኝ አለው።
⁴⁵ ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ።
⁴⁶ ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው።
⁴⁷ ናትናኤልም፦ ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ፦ መጥተህ እይ አለው።
⁴⁸ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ፦ ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ።
⁴⁹ ናትናኤልም፦ ከወዴት ታውቀኛለህ? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ በታች ሳለህ፥ አየሁህ አለው።
⁵⁰ ናትናኤልም መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለው።
⁵¹ ኢየሱስም መልሶ፦ ከበለስ በታች አየሁህ ስላልሁህ አመንህን? ከዚህ የሚበልጥ ነገር ታያለህ አለው።
⁵² እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ አለው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ #ቅዳሴ_እግዚእነ ነው። መልካም የስብከት በዓልና የነቢያት (የገና) ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2024/12/28 01:22:50
Back to Top
HTML Embed Code: