✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_12_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዕብራውያን 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው።
³ እግዚአብሔርም ቢፈቅድ ይህን እናደርጋለን።
⁴ አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን
⁵ መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን
⁶ በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና።
⁷ ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፥ ለሚያርሱአትም ደግሞ የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል፥ ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፤
⁸ እሾህና ኵርንችትን ግን ብታወጣ፥ የተጣለች ናት ለመረገምም ትቀርባለች፥ መጨረሻዋም መቃጠል ነው።
⁹ ስለ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ምንም እንኳ እንዲሁ ብንናገር፥ አብልጦ የሚሻለውና ለመዳን የሚሆነው እንዲሆንላችሁ ተረድተናል።
¹⁰ እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።
¹¹-¹² በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ይሁዳ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦ ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።
¹⁰ እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፥ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ።
¹¹ ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።
¹² እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውኃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥
¹³ የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው። ወይም👇
ያዕቆብ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።
¹⁵ የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።
¹⁶ እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።
¹⁷ ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥
¹⁸ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች።
¹⁹ ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥
²⁰ ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን፥ የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ።
³ ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል፦ ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው።
⁴ እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ፦ ጌታ ሆይ፥ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው፦ ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።
⁵ አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ።
⁶ እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቍርበት ፋቂው በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጦአል፤ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል።
⁷ የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ፥ ከሎሌዎቹ ሁለቱን፥ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፥
⁸ ነገሩን ሁሉ ተረከላቸው ወደ ኢዮጴም ላካቸው። ወይም👇
ሐዋርያት 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁹ ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ፦ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።
³⁰ እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፤
³¹ ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ፥ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።
³² እኛም ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፥ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ምስክር ነው።
³³ እነርሱም ሲሰሙ በጣም ተቈጡ ሊገድሉአቸውም አሰቡ።
³⁴ ነገር ግን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ፥
³⁵ እንዲህም አላቸው፦ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ስለ እነዚህ ሰዎች ምን እንደምታደርጉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
³⁶ ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ፦ እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፥ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ።
³⁷ ከዚህ በኋላ ሰዎች በተጻፉበት ዘመን የገሊላው ይሁዳ ተነሣ ብዙ ሰዎችንም አሸፍቶ አስከተለ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ።
³⁸ አሁንም እላችኋለሁ፦ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤
³⁹ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_12_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር #እግዚአብሔር"። መዝ.33÷7-8 ትርጉም👇
"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል። #እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው"። መዝ.33÷7-8 ወይም
"ወሳሙኤልኒ ምስለ እለ ይጼውዑ ስሞ። ይጼውዕዎ ለ #እግዚአብሔር ውእቱኒ ይሠጠዎሙ ወይትናገሮሙ በዐምደ ደመና"። መዝ.98÷6-7 ትርጉም👇
"ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው፤ #እግዚአብሔርን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው። በደመና ዓምድም ተናገራቸው፤ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ"። መዝ.98÷6-7 👈የነገው የቅዳሴ ምስባክ ከሁለቱ አንዱ ነው የሚሆነ ግጻዌው ነው የሚያዘው ስለዚህ ሁለቱንም ተለማመዱት🙏

#ታኅሣሥ_12_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን?
¹³ ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል።
¹⁴ እንደዚሁ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ ፈቃድ አይደለም።
¹⁵ ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤
¹⁶ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤
¹⁷ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።
¹⁸ እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።
¹⁹ ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል።
²⁰ ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።
²¹ በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።
²² ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ_ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ፣ የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ የዕረፍት በዓል፣ የቅዱሳን ሰማዕታት አንቂጦስና ፎጢኖስ የዕረፍት በዓል፣ የቅዱሳን ኤጲስቆጶሳት የቀሳውስትና የዲያቆናት የአንድነት ስብሰባ በዓልና የነብያት የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

❤ "#ሰላም_ለጸአተ_ነፍስከ እማኅደረ ሥጋ ወደም። ወለበድነ ሥጋከ ሰላም #ውስተ_ሐቅለ_ዋሊ_ገዳም። መናኔ #ፍትወታት_ሳሙኤል ወሐሣሢ ሐዲስ ዓለም። #ለጴጥሮስ_ወለጳውሊ ከመ ለሀወቶሙ ሮም። ለሀወተ ገዳምከ በሞትከ ዮም"። ትርጉም፦ #በዋሊ_ገዳም በርሓ ውስጥ ለሥጋ በድን እና ከሥጋና ከደም ማደሪያ #ለነፍስህ_መውጣት_ሰላምታ_ይገባል፤ አዲስ ዓለምን የምትፈልግና ዓለምን የናቅህ #አባታችን_ቅዱስ_ሳሙኤል ሆይ! #ለቅዱስ_ጴጥሮስና_ለቅዱስ_ጳውሎስ እንዳለቀሰችላቸው በሞትህ ዕለት ዛሬ ገዳምህ አለቀሰች። #መልክዐ_አቡነ_ሳሙኤል።
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
📷 እርግጠኛ ነኝ ፕሮፍይሎን ለመቀየር ፈልገው ፕሮፍይል የሚያደርጉት ጠፍቶ ተቸግረው ያውቃሉ።
የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ መንፈሳዊ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው👇👇👇👇👇👇📷
https://www.tg-me.com/addlist/gpX29GzfGs43MWE0

#ታኅሣሥ_13
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ዐስራ ሦስት በዚህች ቀን #ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱና ተአምር ያደረገበት ዕለት ነው፣ ታላቁ አባት #አባ_መቃርስ_ገዳማዊ ዓመታዊ የዕርገታቸው መታሰቢያ ነው፣ መነኮስ #አቡነ_አብራኮስ_ገዳማዊ ዕረፍታቸው ነው፣ የሰማዕት #ቅዱስ_በጽንፍርዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሩፋኤል
ታኅሣሥ ዐስራ ሦስት በዚህች ቀን በዚህች ዕለት ፈታሄ ማህጸን ሊቀ መልአክት #ቅዱስ_ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱና ተአምር ያደረገበት ዕለት ነው፡፡ ሰማያውያን ከሆኑ ከመላአክት አለቆች ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ 3ተኛ ነው፡፡ "ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል፡፡ ጦቢት 12፡15፡፡ ሩፋኤል የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል መልአከ የሰላምና የጤና መልአክ ይባላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቁስል ይፈወስ ዘንድ ከልዑል #እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” መጽሐፈ ሄኖክ 6፡3፡፡
ቅዱስ ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡” በማለት ሄኖክ ከ #እግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል፡፡ ሄኖክ 10፡13፡፡ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ በማኅፀን ላለ ችግርና ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት በማሕፀን እያለ ማለትም በ #ሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነት ያለን ረቂቅ ርኩስ መንፈስ ያውቃል፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ጭን ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሠቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል ጦቢት 3፡8-17፡፡
ዳግመኛም #እግዚአብሔር ሩፋኤልን አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ሄኖክ 3፡5-7፡፡ በዚህ መሠረት ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሄኖክ 2፡18፡፡ ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠብቃቸው #እግዚአብሔር እንዳዘዘዉ የሚከፍታቸዉ የሚዘረጋቸዉ ይህ ታላቅ መልአክ ነዉ፡፡
የምህረትና የረድኤት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሥራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል፡፡ "ፈታሄ ማህጸን" ይባላል-እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰዉነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል፡፡ እንደ እምነታቸዉ ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡ ዳግመኛም "ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ" ይባላል-ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ ስለሆነ ነው፡፡ ዳግመኛም "መራሔ ፍኖት" ይባላል-ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና ነው፡፡ እንዲሁም "መላከ ክብካብ" ይባላል-ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ ነው፡፡
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዓል እስኪፈፀም ድረስ በከበረ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎፍሎስ ዘመን በምድረ ግብጽ ውስጥ ከእስክንድርያ ውጭ በታናፀች አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ከአሳ አንበሪ ላይ የታነፀች ነበር፡፡ ነገር ግን በወደቡ አጠገብ ከነበረ ግዙፍ አንበሪ ጀርባ ላይ መታነጿን ቀድሞ ያነጿት ሰዎች ቢሆኑ ከካህናትም ቢኾን ያወቀ አልነበረም፡፡
ያ አንበሪም የቤተክርስቲያኑ ህንጻ በከበደው ጊዜ ፈጽሞ ተንቀሳቀሰ፡፡ ከአሸዋማው መሬት ላይ በባህሩ ዳርቻ የታነፀች ይህች ቤተ ክርስቲያንም ከመሰረቷ አናወጻት፡፡ ያን ጊዜ ትልቁም ትንሹም ወንዱም፣ ሴቶችም፣ የተሾሙ ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ሕዝቡም ሁሉ ደነገጡ ታወኩ፡፡ አሣ አንበሪው ግን መንቀሳቀሱን አልተወም፡፡ በመንቀሳቀሱም የቤተ ክርስያኗ ሕንፃ እኩሌታ ይሰነጠቅ ዘንድ ጀመረ፣ ምድርን ተናወፀች፣ ንጉስና፣ ሊቀ ጳጳሳቱም፣ ካህናቱም፣ ዲያቆናቱም፣ ህዝቡም፣ ሁሉም ካሉበት በባህሩ ወደብ ከተሰራች ከዚህች ቤተ ክርስቲያን መናወጥ የተነሳ ፍርሃት መንቀጥቀጥ በላያቸው ወረደ፡፡ ያ አንበሪ ግን በባህሩ ውስጥ ወደፊት መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗም በጀርባው ላይ ነበረች፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የሉትም ሁሉ ያ አሳ አንበሪ ወደ ባሕሩ ውስጥ ሊያሰጥመን ነው ሲሉ አሠቡ፡፡ ያን ጊዜም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ስዕል ፊት በጽኑ አለቀሱ፡፡ በአንድ ቃልም "ገናናው የ #እግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ ርዳታህ ፈጥኖ ይደርስልን ዘንድ በቅድስት ቤተክርስቲያን ወደተሰበሰብን ወዳጆችህ ተመልከት" እያሉ ይጸልዩ ጀመር፡፡ ያንጊዜም የ #እግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ ያችን ቤተክርስቲያን በብሩሃት ክንፎቹ እንደደመና ጋረዳት፡፡ በእጁ በተያዘ የብርሃን በትረ #መስቀሉ ያን ኣሣ አንበሪ ወገቶ "በ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሃይል ከቦታህ ሳትንቀሳቀስ እስከትውልድ ፍፃሜ ዘመን ለዘለአለም ትኖር ዘንድ አዝዝሃለሁ" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያኗን ከነመዓዘኗ ከግርግዳዎቿ ከመሠዊያዋ በውስጧ ተተክለው ካሉት ሁሉ ጋር ከጀርባው ላይ እያለች ያንን አሳ አንበሪ ወግቶ በያዘበት ብርሃናዊ በትረ #መስቀሉ ወደቀድሞው የባሕሩ ወደብ ጎተተው፡፡ ያንጊዜም ግንቡ ቦታውን ሳይለቅ እርስ በእርሱ ተጣበቀ፡፡
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አሣ አንበሪውን በቀድሞ ሥፍራው ያቺን ቤተክርስቲያን በቀደመ መሠረቷ ላይ አጽንቷቸዋልና፡፡ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤልም አዳኝ የሆነ የ #ጌታው_የኢየሱስ_ክርስቶስን ስም ጠርቶ ከሞት እንዳዳናቸው ሁሉም አስተዋሉ፡፡ በድንቅ ተዓምራቱ የዳኑ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ በሊቀ መላእክቱ ቅዱስ ሩፋኤል ላይ አድሮ ድንቅ ተዓምራቱን ስለገለጸላቸው የቅዱስ ሩፋኤልን አምላክ #እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ የዚህች ቤተክርስቲያን ታሪክም በዓለም ሁሉ በየአውራጃዎቹም ተሰማ፡፡ የቅርብም የሩቅም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ታላቁ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የለመኑትን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ የነገሩትን ያማልዳቸው ዘንድ በውስጧ ይጸልያሉ፡፡ በዚችም ቤተክርስትያን ብዙ ውስጥ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ታኅሣሥ 13 ቀንም ተአምራቶቹ ከተፈጸመባቸው ዕለታት አንዷ ናት፡፡ ቅዳሴ ቤቱም በዚሁ ዕለት ተከናውኗል፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሊቀ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_መቃርስ_ገዳማዊ

ዳግመኛም በዚህች እለት ታላቁ አባት አባ መቃርስ ገዳማዊ ዓመታዊ የዕርገታቸው መታሰቢያ ነው፡፡ ይኸኛው መቃርስ ዕረፍቱ መጋቢት 27 ከሚውለው ከታላቁ መቃርስ ይለያል፡፡ በመቃርስ ስም የሚጠሩ ከ8 በላይ ሌሎች ቅዱሳንም አሉ፡፡ ታኅሣሥ 13 ቀን የዕርገቱ በዓል የሆነው መቃርስ ግን ቆቅ ይመገብ የነበረው መቃርስ ነው፡፡ እርሱም በልጅነቱ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እየተማረ አደገ፡፡ የዓለምን ከንቱነት ተመልክቶ ዳግመኛም የኃጥአንንና የጻቃንን ዋጋቸውን አይቶ ወደ ገዳም ገብቶ መነኮሰ፡፡ ከመነኮሰም በኋላ የ10 ቀን መንገድ ተጉዞ ኩዕንትና ቆቆች ውኃም ካለበት ተራራ ላይ ደረሰ፡፡ እንዲህም አለ፡- ‹‹ለምግቤ ኩዕንትን ወደ መልቀም ብሰማራ የስግደቴና የጸሎቴ ሥራ ይቋረጣል፣ በዚህም ተራራ ላይ ብቸኛ ነኝና ሰብስቦ የሚያስገባልኝ የለም፡፡ ሥጋ አትብላ ያለውስ የባልንጀራችንን ሥጋ በሐሜት የምንበላውን አይደለምን? ሌላ ምግብ እንደሌለኝ ፈጣሪዬ ያውቃል›› ብሎ ከዚያች ዕለት ወዲህ ለምግቡ ቆቅ የሚያጠምድ ሆኖ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ በየቀኑ አንድ አንድ ቆቅ የሚያዙለት ሆነ፡፡ በየቀኑም አንድ አንድ ቆቅ እየተመገበ ውኃ እየጠጣ ፈጣሪውን እያመሰገነ በታላቅ ተጋድሎ ሆኖ የሰውን ፊት ሳያይና ከማንም ጋር ሳይነጋገር ብዙ ዘመን ኖረ፡፡
ከቍስጥንጥንያ ከተማ የመጣ አንድ መነኩሴ ዋሻ ሲፈልግ አባ መቃርስ ደግሞ ቆቅ ሲያጠምድ አየውና ለሐሜት ቸኩሎ ወደ ቍስጥንጥንያ ተመልሶ ሄዶ ለሊቀ ጳጳሳቱ ‹‹ቆቅ እያጠመደ ሥጋ የሚበላ መነኩሴ አገኘሁ፣ እርሱም በሕዝብ ዘንድ ሊያስነቅፈን ነው›› ብሎ ነገረው፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱም ከአንድ ሌላ መነኩሴ ጋር ድጋሚ እንዲያረጋግጡ ላካቸው፡፡ እነርሱም ገና ከበዓቱ ሳይደርሱ አባ መቃርስ ቆቅ ሊያጠምድ ሄደና ያለወትሮው በአንዲት ወጥመድ ሦስት ቆቆችን ተያዙለት፡፡ ሌላ ጊዜ በቀን አንድ ብቻ ነበር የሚያዝለት ዛሬ ግን #እግዚአብሔርም ለሚመጡት እንግዶችም ጭምር ሲያዘጋጅላቸው ነው ያለወትሮው ዛሬ ሦስት ሆነው የተያዙለት፡፡
አባ መቃርስም ሁለቱን መነኮሳት ሲያያቸው ሁለቱ ተጨማሪ ሆነው የተያዙለት ቆቆች የእንግዶቹ መሆናቸውን ዐውቆ #ጌታችንን አመሰገነው፡፡ እነርሱ ግን ማዕድ ሠርቶ እስካቀረበላቸው ድረስ በመቃርስ ላይ ይጠቋቆሙበት ነበር፡፡ አባ መቃርስም ምግብን አዘጋጅቶ ሲጨርስ የራሱን ድርሻ አንዷን ቆቅ አስቀርቶ ሁለቱን ለእንግዶቹ አቀረበላቸው፡፡ እርሱ በልቶ ጨርሶ ቀና ሲል እንግዶቹ መነኮሳት እንዳልበሉ ተመለከተና ‹‹አባቶቼ ለምን አልበላችሁም?›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹እኛ መነኮሳት ስለሆንን ሥጋ አንበላም ትኅርምትም አለን›› አሉት፡፡ አባ መቃርስም ‹‹እሺ ተውት›› አላቸውና እነዚያን አብስሎ በገበታ ላይ ለምግብነት ያቀረባቸውን ሁለት ቆቆች ሦስት ጊዜ በእስትንፋሱ እፍ ቢልባቸው ሕይወት ዘርተው በረሩና ወደ ጫካ ሄዱ፡፡ እነዚያ መነኮሳትም እጅግ ደንግጠው ‹‹ማረን ይቅር በለን፣ ቅዱሱን የ #እግዚአብሔር ሰው በከንቱ አምተንሃል›› ብለው እግሩ ሥር ሲወድቁ ‹‹ #እግዚአብሔር የሁላችንን በደል ይቅር ይበለን›› አላቸው፡፡
ሁለቱ መነኮሳት ወደ ቍስጥንጥንያ ተመልሰው ለሊቀ ጳጳሳቱና ለሕዝቡ ያዩትን ነገር መሰከሩ፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱም እጅግ ተደንቆ ወደ ንጉሡ ደብዳቤ ጽፎ ‹‹በምድራችን ጻድቅ ሰው ተገኝቷልና አንተም ና ሄደን በረከቱን እንቀበል›› ብሎ መልእክት ላከበት፡፡ ንጉሡም እሺ ብሎ ከሠራዊቱ ጋር ተነሥቶ ከካህናቱ ጋር ወደ አባ መቃርስ ዘንድ ሄዱ፡፡ ወደ ገዳሙም በቀረቡ ጊዜ አባ መቃርስን ወደ ብሔረ ሕያዋን ያደርሰው ዘንድ መልአክ አንሥቶ በክንፎቹ ተሸክሞት ሲያርግ አዩት፡፡ እነርሱም ‹‹የ #እግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ ባርከን፣ የምንድንበትንም አንዲት ቃል ንገረን›› አሉት፡፡ አባ መቃርስም ‹‹ከሐሜትና ከነገር ሥራ አንደበታችሁ ይከልከል፤ ካህን ብዙ ባይማር ትዕቢትና መታጀር ባልመጣበት ነበር፣ መነኩሴም ትኅርምት ባያበዛ ባልተመካም ነበር፡፡ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ #እግዚአብሔር አድሮባችሁ ይኑር›› አላቸው፡፡ ይህንንም ከተናገራቸውና ከባረካቸው በኋላ ከዐይናቸው ተሰወረ፡፡ ይህም ዕርገቱ ታኅሣሥ 13 ቀን የተፈጸመ ነው፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ መቃርስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_አብራኮስ_ገዳማዊ
ዳግመኛም በዚህች ቀን መነኮስ አቡነ አብራኮስ ገዳማዊ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ይኽም ቅዱስ ዕድሜው 20 ዓመት በሆነው ጊዜ የዚህን ዓለም ኃላፊነት ተረድቶ የነፍሱን ድኅነት ሽቶ መንኩሶ ገዳም ገባ፡፡ በዚያም በታላቅ ተጋድሎ ሲኖር ሰይጣን በቅናት ተነሳስቶበት ብዙ ፈተናዎችን አመጣበት ነገር ግን ቅዱስ አብራኮስ ጽኑ በሆነው መንፈሳዊ ተጋድሎው ሰይጣንን ድልነሣው፡፡ ሰይጣንም በተደጋጋሚ መሸነፉን አይቶ የፈተናውን ዓይነት ለወጥ አድርጎ በስንፍና ሊጥለው ፈለገ፡፡ እናም ሰይጣን በግልጽ ፊት ለፊት ተገልጦ ቅዱስ አብራኮስን ‹‹እነሆ ከዚህ ዕድሜህ ሌላ 50 ዓመት ቀረህ›› አለው፡፡ ቅዱስ አብራኮስም ሰይጣን በስንፍና ሊጥለው ያመጣበት ፈተና መሆኑን ዐውቆ በተራው ሰይጣን ላይ ተራቀቀበት፡፡ እንዲህም አለው፡- ‹‹አሁንስ ልቤን አሳዘንከው፣ እኔ ሌላ መቶ ዓመት እኖር ዘንድ ስላሰብኩ ቸል ብያለሁ ነገር ግን አንተ እንዳልከው 50 ዓመት ከሆነ የምኖረው ከቀድሞው እጅግ አብዝቼ እጋደል ዘንድ ይገባኛል›› አለው፡፡ ሰይጣንም ይህን ጊዜ አፍሮ ከእርሱ ሸሸ፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አብራኮስ ጽኑ የሆነ ተጋድሎውን በገድል መጠመዱን አብዝቶ ከ70 ዓመት ተጋድሎው በኋላ በሰላም ዐረፈ፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_በጽንፍርዮስ_ሰማዕት
በዚህች እለት የሰማዕት ቅዱስ በጽንፍርዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኽም ቅዱስ አባት ዓለምን ንቆ በመመንኮስ በታላቅ ተጋድሎ ይኖር ነበር፡፡ የሚያገለግለውም በምስር አገር በወንዝ ዳር ባለች በሊቀ መላእክት በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡ ስለቀናች ተዋሕዶ ሃይማኖቱም ከእስላሞች መሳፍንት ጋር ተከራከረ፡፡ የ #ጌታችንም_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስን አምላክነቱን ገለጠላቸው፡፡ እስላሞችም ባፈሩ ጊዜ በእርሱ ላይ ተቆጡ፡፡ ከዚህም በኋላ እስላሞች አባ በጽንፍርዮስን ይዘው በእጅጉ አሠቃዩት፡፡ በመጨረሻ ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ፡፡
ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅድስት ሐና እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያምን ጸነሰቻት የሚሉ አሉ። ጸሎቷና በረከቷ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ዳግመኛ በዚህች ዕለት በደብረ ቀለሞን የሚኖር የገዳማዊ የአባ #ሚካኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን መልእክት አና ጻድቃን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታህሣሥ_13 እና #ከገድላት_አንደበት))

ታኅሣሥ 13 #እንኳን_ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ከ9ኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ለሆነው ለ #ስብከት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
#ከታህሳስ ❼ እስከ ታህሳስ ⓭ ቀን ድረስ ያሉት ዕለታት ናቸው፡፡ የእነርሱም ኢየአርግና ኢይወርድ አለው ይኸውም ታህሳስ 1 ኤልያስ ማክሰኞ ቢውል ስብከት ታህሳስ 13 ቀን ይገባል ኤልያስ ረቡዕ ቢውል ስብከት በ12 ይገባል ኤልያስ ሐሙስ ቢውል ስብከት በ11 ይገባል ኤልያስ ዓርብ ቢውል ስብከት በ10 ይገባል ኤልያስ ቅዳሜ ቢውል ስብከት በ9 ይገባል ኤልያስ እሁድ ቢውል ስብከት በ8 ይገባል ኤልያስ ሰኞ ቢውል ስብከት በ7 ይገባል ከእነዚህ ቀን አይበልጥም አያንስም፡፡
❤ስብከት ማለት ትምህርት ማለት ነው፡፡ ነቢያት የ #ጌታን ሥጋዌ ማስተማራቸው ይነገርበታል፡፡ በዚህ ውስጥም ትንቢት ተናግረዋል ምሳሌ መስለዋል፡፡ ከዚህም ውስጥ
#ትንቢቱ፡- ዳዊት ‹‹ብሩክ ዘይመጽዕ በስመ #እግዚአብሔር›› (መዝ 117-26)
‹‹ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ ወረከብ ናሁ በውስተ ገዳም››(መዝ 131-6)
ኢሳይያስ‹‹ናሁ ድንግል ትጸንስ ወትወልድ ወልደ ወይ ሰመይ #አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ #እግዚአብሔር ምስሌነ››(ት.ኢሳ 7-14)
‹‹ሕጻን ተወልደ ለነ ወልድ ተውህበ ለነ›› ኢሳ 9-6 ላይ ብሏል
❤ምሳሌዎቹ 1.አዳም የ #ጌታ ምሳሌ ነው አዳም በኃጢአቱ ሰውን ሁሉ እንደጎዳ #ጌታም በትሩፋቱ ሰውን ሁሉ አድኗል አዳም ከኀቱም ምድር ተገኝቷል #ጌታም በኀቱም ማህፀን ተወልዷል፡፡ቨ
❤️አቤል፦ የ #ጌታ ምሳሌ ነው አቤል የገዛ ወንድሙ ገድሎታል /ዘፍ 4-8/ #ጌታም ደቀ መዝሙሩ ይሁዳ ሸጦታልና፡፡
❤ይስሀቅ የ #ጌታ ምሳሌ ነው ቨ
ይስሀቅ እንደሚሰዋ እያወቀ በእጁ እሳት በትከሻው እንጨት ተሸክሞ አባቱን ተከትሏል፡፡/ዘፍ 21-19/ #ጌታም የሚሰቀልበትን #መስቀል ይዞ ቀራንዮ ወጥቷል፡፡?ቨቨቨ።፡።።
❤ዮሴፍ የ #ጌታ ምሳሌ ነው
ዮሴፍ ወንድሞቹ ጠልተውት ተመቅኘው በ20 ብር ሸጠውታል
#ጌታም ደቀ መዝሙሩ በ30 ብር ሸጦታል ዮሴፍን ወንድሞቹ ከሸጡት በኋላ ልብሱን በጠቦት ደም ነክረው ለአባቱ አሳይተውታል ➛ልብሱ የትስብዕት
➛ዮሴፍ የመለኮት
➛ደም የህማም የሞቱ ምሳሌ
#ደም ከልብሱ እንጂ ከዮሴፍ አለመገኘቱ ሕማሙ ሞቱ በትስብዕት/በሥጋ/ እንጅ በመለኮት ላለመኖሩ ምሳሌ ነው
#አንድም ዮሴፍ ልጥላቸው አላለም ይልቁንም ምግባቸውን ልብሳቸውን ሰጥቷቸዋል፡፡/ዘፍ 43-34/ #ጌታም መግደል ማጥፋት ሲቻለው ሲገርፉት ሲቸነክሩት ልጥላቸው ላጥፋቸው ሳይል‹‹አባ ስረይ ሎሙ›› ብሏልና ሉቃ 23-34
❤ገራህተ ሙሴ:-
ሙሴ #ጌታን ፊትህን ላይ እወዳለሁ ባለ ጊዜ #ጌታ ዘር ካልወደቀባት ምድር የበቀለች ስንዴ አምጥተህ ብትሰዋልኝ እታይሀለው ብሎታል፡፡/ዘጸ 33÷12-23/
#ገራህት_የእመቤታችን
#ስንዴ_የጌታ ምሳሌ ነው
#ከድንግል ያለ ዘርዐ ብእሲ ተወልጄ መስዋዕት ሆኜ በምቀርብበት ጊዜ በደብረ ታቦር እታይሀለው ሲለው ነው፡፡
❤መሰንቆ ዘዳዊት
ዳዊት :- ሀብተ መሰንቆ ተሰጥቶታል በሚደረድርም ጊዜ ከመሰንቆው የሚወጣ ድምጽ ህሙማንን የሚፈውስ ነበር፡፡/1ኛ ሳሙ 16-20
#መሰንቆ_የእመቤታችን
#ድምጹ_የጌታ ምሳሌ
#ከመሰንቆው በሚወጣ ድምጽ ህሙማን መፈወሳቸው➛ ከ #እመቤታችን በተወለደ በ #ጌታ ድህነተ ዓለም ፈውሰ ዓለም ለመገኘቱ ምሳሌ ነው፡፡
❤ምስራቀ ፀሐይ :- ፀሐይ በምስራቅ ይወጣል
#ፀሐይ_የጌታ
#ምስራቅ_የእመቤታችን ምሳሌ ነው
#ቅዱስ_ያሬድ ‹‹አንቲ ምስራቅ ወወለድኪ ፀሐየ ጽድቅ›› እንዳለ
#ፀሐይ_በምስራቅ ወጥታ ዓለምን እንደምታበራ ጨለማን እንደምገፍ ሁሉ
#ከእመቤታችንም_ክርስቶስ ተወልዶ ለዓለም ሁሉ ብርሃን ሆኖ ጨለማ/መርገመ ስጋ መርገመ ነፍሳችንን/ የማባረሩ የመደምሰሱ ምሳሌ ነው፡፡ ‹‹አነ ውእቱ ብርሀኑ ለዓለም›› እንዳለ ጌታችን በዘመነ ስጋዌው፡፡
❤አክሊል:- ዘሰሎሞን
ሰሎሞን ስመ አምላክ የተቀረጸበት ሐቲም ቀለበት ነበረው ግርማ ሞገሱ ትምህርተ መንግስቱ ነው፡፡ መንግስቱን አጥቶ ሁለት ሳምንት ያህል በገዛ ከተማው ሲለምን ከቆየ በኋላ ከሞተ አሳ ሆድ ውስጥ አግኝቶት እስራኤል አጅበውት ወደ መንግስቱ ተመልሷል፡፡
#ቀለበቱ_የእመቤታችን
#መንግስቱ_የአዳም_ምሳሌ_ነው
#መንግስቱ በቀለበቱ እንደተመለሰለት አዳምም በዕፀ በለስ ምክንያት ያጣትን ልጅነት በ #እመቤታችን ምክንያት አግኝቷልና፡፡
❤ሰዋሰው ዘወርቅ(የወርቅ መሰላል):- #ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ሌሊት በህልሙ የወርቅ መሰላል ከምድር እስከ ሰማይ ተተክላ መላዕክት ሲወጡባትና ሲወርዱባት በላይዋ ዙፋን ተጎናፅፎ በዙፋኑ ላይ ንጉሥ ተቀምጦ አይቷል ዘፍ 28-10
#የወርቅ_መሰላል_የእመቤታች #እመቤታችን መሆኗን ያጠይቃል።
በነዚህ እና በመተለያዩ ምሳሌዎች ነቢያት እየመሰሉ #ክርስቶስ እንደሚወለድ ይሰብኩ ነበርና ይህ ወቅት ዘመነ ስብከት ተብሏል።
✍️መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ