✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_6_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ቆሮንቶስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ የሚሰበክ ከሆነ ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ፦ ትንሣኤ ሙታን የለም እንዴት ይላሉ?
¹³ ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሣማ፤
¹⁴ ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤
¹⁵ ደግሞም፦ ክርስቶስን አስነሥቶታል ብለን በእግዚአብሔር ላይ ስለ መሰከርን ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን ግን የማይነሡ ከሆነ እርሱን አላስነሣውም።
¹⁶ ሙታን የማይነሡ ከሆነ ክርስቶስ አልተነሣማ፤
¹⁷ ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ።
¹⁸ እንግዲያስ በክርስቶስ ያንቀላፉት ደግሞ ጠፍተዋላ።
¹⁹ በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን።
²⁰ አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።
²¹ ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።
²² ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።
²³ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤
²⁴ በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል።
²⁵ ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።
²⁶ የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፤
²⁷ ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን፦ ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው።
²⁸ ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል።
²⁹ እንዲያማ ካልሆነ፥ ስለ ሙታን የሚጠመቁ ምን ያደርጋሉ? ሙታንስ ከቶ የማይነሡ ከሆነ፥ ስለ እነርሱ የሚጠመቁ ስለ ምንድር ነው?
³⁰ እኛስ ዘወትር በሚያስፈራ ኑሮ የምንኖር ስለ ምንድር ነው?
³¹ በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለኝ በእናንተ ትምክህት እየማልሁ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ዕለት ዕለት እሞታለሁ።
³² እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልሁ፥ ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል? ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ።
³³ አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ጴጥሮስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
¹¹-¹² ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤
¹³ ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።
¹⁴ ስለዚህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ፥
¹⁵ የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ። እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደ ተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ፥ በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ።
¹⁶ በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።
¹⁷ እንግዲህ እናንተ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ፥ በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤
¹⁸ ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
²⁹-³⁰ ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
³¹ ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።
³² አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።
³³ ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤
³⁴ እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ።
³⁵ እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፦ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።
³⁶ ይህንም ብሎ ተንበርክኮ ከሁላቸው ጋር ጸለየ።
³⁷ ሁሉም እጅግ አለቀሱ፥ ጳውሎስንም አንገቱን አቅፈው ይስሙት ነበር፤
³⁸ ይልቁንም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም ስላላቸው ነገር እጅግ አዘኑ። እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_6_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወለነዳያኒሃኒ አጸግቦሙ እክለ። ወለካህናቲሃኒ አለብሶሙ ሕይወተ። ወጻድቃኒሃኒ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ። መዝ.131÷15-16
"አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ።
ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል"። መዝ.131÷15-16
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_6_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።
³³ ያላችሁን ሽጡ ምጽዋትም ስጡ፤ ሌባ በማይቀርብበት ብልም በማያጠፋበት በሰማያት የማያልቅ መዝገብ የሚሆኑትን የማያረጁትንም ኮረጆዎች ለራሳችሁ አድርጉ፤
³⁴ መዝገባችሁ ባለበት ልባችሁ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።
³⁵ ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤
³⁶ እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ፤
³⁷ ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
³⁸ ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፥ እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው።

³⁹ ይህን ግን እወቁ ባለቤት በምን ሰዓት ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ፥ ቤቱም እንዲቆፈር ባልፈቀደም ነበር።
⁴⁰ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_አትናቴዎስ_ቅዳሴ ነው። መልካም ዕለተ ሰንበት መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_7
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ሰባት በዚችም ዕለት ከቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚወለድ #በከበሩ_ነቢያት አፍ ለመሰበኩ መታሰቢያ ነው፣ በደብረ ሲሐት የሚኖር #አባ_ዳንኤል አረፈ፣ #ቅዱስ_አባት_አባ_ማቴዎስ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ስብከተ_ነቢያት
ታኅሣሥ ሰባት በዚህችም ዕለት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል #ማርያም ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ እንደሚወለድ በከበሩ ነቢያት አፍ ለመሰበኩ መታሰቢያ ሆነ ።
ይህች ዕለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት "ስብከት" ትባላለች። ስብከት ማለት በቁሙ "የምስራች፣ አዲስ ዜና መንገርን" የሚመለከት ሲሆን ዋናው ምሥጢር ግን ከነገረ ድኅነት (ከመዳን ትምሕርት) ጋር የተገናኘ ነው።
በዚህ ዕለት (ሳምንት) ሁሉም ነቢያት ከነ ትንቢታቸው ይታሰባሉ። ዘመነ ስብከትም ከታሕሳስ 7 እስከ 13 ያለውን ይይዛል። ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ #እግዚአብሔር አዳምን በ7 ሃብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው "አትብላ" የተባለውን ዕፀ በለስ በላ። በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ፣ በርደተ መቃብር፣ ርደተ ገሃነም ተፈረደበት። በሁዋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ "ከ5 ቀን ተኩል (5,500 ዘመን) በሁዋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃል ኪዳንን ሰጠው።
ከዚህ በሁዋላ ለ5,500 ዘመናት ጊዜ ወደ ታች ይቆጠር ጀመር። ስለ #እግዚአብሔር ሰው መሆንና ዓለምን ማዳንም ትንቢት ይነገር፣ ሱባኤ ይቆጠር፣ ምሳሌም ይመሰል ገባ።
ከአዳም እስከ ሙሴ (ዘመነ አበው) ምሳሌያት ይበዛሉ። ከሙሴ እስከ ዳዊት (ዘመነ መሣፍንት) ምሳሌያቱ እየጐሉ መጥተዋል:: ከልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ሚልክያስ ድረስ (በዘመነ ነቢያት/ነገሥት) ግን ትንቢቶች ስለ #ክርስቶስና ስለ ማደሪያ እናቱ እንደ ጐርፍ ፈሰዋል።
ነቢያትም የመሲህን መምጣት እየጠበቁ በጾም፣ በጸሎትና በትሕርምት ኑረዋል። እንባቸውንም አፍሰው ቅድመ #እግዚአብሔር ደርሶላቸዋል። መድኅን #ክርስቶስም ተወልዶ አድኗቸዋል።
ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር) መጻዕያትን (ለወደ ፊት የሚሆነውን) የሚያውቅ ሰው ማለት ነው። ሃብተ ትንቢት የ #እግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ።
ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን #እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም። በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ። (ሐዋ.11፥27) ቅዱሳን ነቢያት ከ #እግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ።
ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም #እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል፣ "እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለ #እግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ። (ቅዳሴ ማርያም)
የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ አንዳንዶቹም በእሳት፣ አንዳንዶቹም በሰይፍ፣ አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል። ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል።
ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል። #ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል። (ዮሐ.4፥36)
ነቢያት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን እና #ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል ሽተዋልም። "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ #ጌታ በወንጌል። (ማቴ. 13፥16፣ 1ዼጥ.1፥10) ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ።
ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት 15ቱ አበው ነቢያት: 4ቱ ዐበይት ነቢያት: 12ቱ ደቂቀ ነቢያት እና ካልአን ነቢያት ተብለው በ4 ይከፈላሉ::
#15ቱ_አበው_ነቢያት ማለት፦ ቅዱስ አዳም አባታችን፣ ሴት፣ ሔኖስ፣ ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣ ኄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ ኖኅ፣ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ ሙሴ እና ሳሙኤል ናቸው።
#4ቱ_ዐበይት_ነቢያት ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል፣ ቅዱስ ኤርምያስ፣ ቅዱስ ሕዝቅኤልና፣ ቅዱስ ዳንኤል ናቸው።
#12ቱ_ደቂቀ_ነቢያት የሚባሉት ሆሴዕ፣ አሞጽ፣ ሚክያስ፣ ዮናስ፣ ናሆም፣ አብድዩ፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ኢዩኤል፣ ዕንባቆም፣ ዘካርያስ እና ሚልክያስ ናቸው።
#ካልአን_ነቢያት የሚባሉት ደግሞ፦ ኢያሱ፣ ሶምሶን፣ ዮፍታሔ፣ ጌዴዎን፣ ዳዊት፣ ሰሎሞን፣ ኤልያስ እና ኤልሳዕ ሌሎችም ናቸው::
ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ፦
*የይሁዳ (ኢየሩሳሌም)፣ የሰማርያ (እሥራኤል) እና የባቢሎን (በምርኮ ጊዜ) ተብለው ይጠራሉ::
በዘመን አከፋፈል ደግሞ:-
* ከአዳም እስከ ዮሴፍ #የዘመነ_አበው_ነቢያት፣
* ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል #የዘመ_መሳፍንት_ነቢያት፣
* ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት #የዘመነ_ነገሥት_ነቢያት፣
* ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ #የዘመነ_ካህናት_ነቢያት ይባላሉ።
የአምላካችን የልዑል #እግዚአብሔር ይቅርታው ቸርነቱ ይደረግልን የቅዱሳን ነብያት ረድኤት በረከታቸውን ያሳድርብን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ዳንኤል_ገዳማዊ
በዚህች ቀን በአባ መቃርስ ገዳም በደብረ ሲሐት የሚኖር አባ ዳንኤል አረፈ። ይህም አባ ዳንኤል ስሟን እንጣልዮስ አስኝያ የነበረች ንግሥት በጥሪቃን የገነዛት ነው እርሷም ከሞቷ በኋላ እንጂ ሴት እንደሆነች አልታወቀችም ነበር።
በአንዲት ቀንም ወደ እስክንድርያ አገር ከረድኡ ጋር ሲጓዝ ስሙ ምህርካ የሚባል እብድ አገኘ ብዙ እብዶችም ይከተሉታል ለአገር ሰዎችም በእውነት ያበደ ይመስላቸው ነበር አባ ዳንኤልም እጁን ይዞ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ወስዶ ትሩፋቱን ተጋድሎውን ነገረው እንዲነግራቸውም በአማሉት ጊዜ ከዝሙት ጦር በመሸሽ ራሱን እብድ እንዳስመሰለ ነገራቸው ሰምተውም #እግዚአብሔርን አመሰገኑት።
በአንዲትም ዕለት ወደ አንዲት አገር ደረሰ በዚያም አውሎጊስ የሚባል ለድኆች የሚራራ እንግዳም የሚቀበል ደንጊያ በመውቀር የሚኖር ሰው አገኘ እርሱንም ተቀብሎ በደስታ አሳደረው መልካም ሥራውንም በአየ ጊዜ ድኆችን የሚረዳበት ገንዘብን ለአውሎጊስ ይሰጠው ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር ስለርሱ ለመነ #ጌታችንም በሕፃን አምሳል ተገለጠለትና ገንዘብ ባገኘ ጊዜ ጠባዩን እንዳይለውጥ አንተ ትዋሰዋለህን አለው አባ ዳንኤልም አዎን እዋሰዋለሁ አለ።
ከዚህም በኋላ አውሎጊስ በድስት የመላ ወርቅን አግኝቶ ያንን ይዞ ወደ ንጉሥ ሒዶ የጭፍራ አለቃ ሆኖ ተሾመ ጠባዩንም ለወጠ። ጠባዩንም እንደለወጠ አባ ዳንኤል ሰምቶ ሊመክረውና ሊገሥጸው ሔደ የአውሎጊስ ወታደሮችም ለመሞት እስኪደርስ ድረስ ደበደቡት በዚህም እያዘነ ሳለ ያ ሕፃን በሕልም ታየው አባ ዳንኤልንም ለምን በሌላ ሰው ነገር ገባህ ብሎ እንዲሰቅሉት አዘዘ። ከዚህም በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም መጥታ ለሕፃኑ ሰገደች እግሮቹንም እየሳመች ስለ አባ ዳንኤል ለምና ከስቅለት አዳነችው።

ከዚህም በኋላ ሌላ ንጉሥ በነገሠ ጊዜ አውሎጊስን ሊገድለው ፈለገው ያን ጊዜ አውሎጊስ ሸሸ ወደ አገሩም ደርሶ ወደ ቀድሞ ሥራው ተመለሰ። በአንዲት ቀንም በሌሊት በበረሀ ውስጥ በጨረቃ ብርሃን ሲጓዝ በተራራ ላይ ተቀምጣ ሴት አገኘ ጠጉሩዋም ሥጋዋን ሁሉ ሸፍኖአል እየተጋደለች ሠላሳ ስምንት ዓመት የኖረች ናት ምሥጢርዋንም ሁሉ ነግራው ከዚህ በኋላ አረፈች።
ከዚህም በኋላ በአንዲት ዕለት የልዮንን ደብዳቤ ሰዎች አምጥተው በሕዝብ ፊት አነበቧት አባ ዳንኤልም ዘሎ የልዮንን ደብዳቤ ነጥቆ ቀደዳትና የኬልቄዶን ሃይማኖት የተገወዘ ነው አለ ወታደሮችም አይተው ደበደቡት ከገዳሙም አሳደዱት።
በአንዲት ዕለትም አባ ዳንኤል ከደናግል ገዳም ደርሶ ደጁን አንኳኳ አባ ዳንኤልም እንደሆነ አውቀው ከፈቱለትና በደስታ ተቀበሉት ከእነርሱም አንዲቷ ራሷን እብድ አስመስላ በደጅ የምትተኛ አለች ስለርሷ እመ ምኔቷን ጠየቃት እርሷም እብድ ናት አለችው። እርሱም መስተጋድልት ቅድስት ሴት እንጂ እብድ እንዳልሆነች ነገራት። እብድ የተባለችውም በሌሊት ተነሥታ የከበራችሁ እኅቶቼ ስለ አሳዘንኳችሁ ይቅር በሉኝ ብላ ጽፋ ያንን ትታ ታጣች ደናግሉም እጅግ አዘኑ ተጸጸቱም።
በውስጡ ብዙ ደናግል የሚኖሩበት ገዳም ነበረ መዝጊያውም የጸና ነው። ገንዘባቸውንም ይበረብሩአቸው ዘንድ ሰይጣን ወንበዴዎችን በላያቸው አስነሣ የወንበዴዎች አለቃም በመራቀቅ በራሱ ላይ ቆብ አድርጎ በአባ ዳንኤል አምሳያ ለብሶ ደጃፋቸውን ሒዶ በማንኳኳት አባ ዳንኤል ነኝ አለ አይተውም ከፈቱለት በደስታም ተቀብለው እግሩን አጠቡትና ስለ በረከት የእግሮቹን እጣቢ በየፊታቸው ረጩት ከውስጣቸው አንዲት ዕውር ነበረች ውኃው ሲነካት ዐያኖቿ በሩላት ደናግሉም አንተ አባ ዳንኤል ንዑድ ክቡር ነህ አሉት የሽፍቶቹም አለቃ አይቶ ደነገጠ ተጸጸተም ከአባ ዳንኤልም ዘንድ መንኲሶ የሚጋደል ሆነ።
ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የ #እግዚአብሔር መልአክ ነገረው ጥቂት ጊዜም ታመመ ክብር ይግባውና ወደ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ጸለየና በሰላም አረፈ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዳንኤል ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባት_አባ_ማቴዎስ
በዚህችም ቀን ለታወቀች እስዋን ለተባለች ገዳም አበ ምኔት የሆነ የሚጋደል ቅዱስ አባት አባ ማቴዎስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ በፈሪሀ #እግዚአብሔር ጸንቶ ያደገ ነው ከገዳማትም በአንዱ መንኲሶ በጾም በጸሎት ተወስኖ የሚጋደል ሆነ በገዳሙም ውስጥ ለራሱ መኖሪያ ሠራ ደቀ መዛሙርቱ አባ ሰራብዮንና አባ ኅድራ ሥራውን ተጋድሎውንና ተአምራቱን እንደተናገሩ መረብንም በመሥራት ሽያጩን ለድኆች ይመጸውታል።
እነርሱም እንዲህ ብለው ተናገሩ በአንዲት ዕለት ከማደሪያው በውጭ ተቀምጠን ሳለ በማደሪያው ውስጥ አንዱ ከሌላው ጋር እንደሚነጋገር ሁኖ ቃልን ሰማን በገባንም ጊዜ ከእርሱ በቀር ያገኘነው የለም። አባታችን ሆይ በውጭ ሳለን ከአንተ ጋር ሰው እንደሚነጋገር ድምፅ ሰምተን ነበር በገባን ጊዜ ከአንተ በቀር ያገኘነው የለም አልነው ። በብዙ ትሕትና እንዲህ አለን ልጆቼ ሆይ የምትጠብቀኝን የሞት ፃዕርና ሥቃዮችን ለነፍሴ በማሳሰብ የኃጢአቴን ብዛት አስቤ ከራሴ ጋር ተነጋገርኩ። ለድኃ ማቴዎስ ወዮለት ንጽሕናን ቅድስናን በለበሱ የመላእክት የጻድቃንና የሰማዕታት ጉባኤ አንድነት በአለበት በልዑል #እግዚአብሔር መንበር ፊት ራቁቱን ያቆሙታልና እንዲህም አድርጎ የኃጥአንን ሥቃይ የጻድቃንን መልካም ዋጋ ለልጆቹ አስተማራቸው።
ቅዱስ ማቴዎስም በሠራት ገዳም ውስጥ ጸሎትን ተጋድሎን አገልግሎትን በማድረግ ጸንቶ ኖረ ገዳሙንም በአባ ጳኩሚስ ስም አከበረ እርሷም የታወቀች ሰሌን ያለባት ተራራ ናት።
ርኩሳን የሆኑ ረቂቃን ሰይጣናትም በቀንና በሌሊት የሚያስፈራሩት ሆኑ በየዓይነቱ በተለያየ መልክ ፊት ለፊት እያያቸው እነርሱ በፊቱ ይሮጣሉ በኋላውም ይከተሉታል እርሱ ግን አይፈራቸውም እጁንም ዘርግቶ በ #መስቀል ምልክት ሲአማትብ በዚያን ጊዜ በነፋስ ፊት እንዳለ ጢስ ይበተናሉ።
በአንዲትም ዕለት ጥቂት እንጀራና ውኃ በመንቀል ከገዳም ውስጥ ይዞ በበረሀ ውስጥ ወደአለች ዋሻው እንዲሔድና እርሱ በማግሥቱ እስቲመጣ በዚያ እንዲጠብቀው ረድኡን ሰራብዮንን አዘዘው። ሰራብዮንም ወደ ዋሻው ሲደርስ ሁለት ታላላቅ አራዊት በውስጥ ተኝተው አገኘ ፈርቶ በሩን ዘግቶ ከዐለት ቋጥኝ ላይ ወጣ።
ከዚህም በኋላ አባ ማቴዎስ የዳዊትን መዝሙር እያነበበ መጣ ረድኡንም አይቶ ፈገግ ብሎ ሳቀ ሰራብዮን ሆይ እኔ ወዳንተ እስከምመጣ ወደ ዋሻው ውስጥ ለምን አልገባህም አለው ። እርሱም ረድኡ አባቴ ሆይ ሁለት ታላላቅ አውሬዎች ተኝተው ስለ አገኘሁ እነርሱን ፈርቼ አልገባሁም አለው ።
ንጽሐ ነፍስ ያለው የዋህ የሆነ የተመሰገነ አረጋዊም ልጄ እመነኝ እኔ ከእነርሱ ጋር ስኖር ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነኝ ያሳደግኋቸውም እኔ ነኝ ይህንንም እንጀራና ውኃ እንድታመጣ ያዘዝኩህ ለእነርሱ ነው አለው ።
ከዚህም በኋላ በሩን በከፈተ ጊዜ እነዚያ አውሬዎች ወደርሱ መጥተው ቅዱስ አባ ማቴዎስን እግሮቹን ላሱ ባልንጀሮችም ሁነውት በታላቅ መለማመጥ ተገዙለት ያንንም ውኃ ከገንዳ ላይ አፍስሶላቸው ጠጡ እንጀራውንም በሉ ከዚያም በኋላ ወደ ዱር ሔዱ ።
ይህም አባ ማቴዎስ የዜናው መሰማት በቦታው ሁሉ እስከመላ ድረስ ተአምራትን እያደረገ ኖረ በየዓይነቱ በሆነ ደዌ የተያዙትን ያመጡለታል ። እርሱም በላዩ በአደረች በ #እግዚአብሔር ኃይል ይፈውሳቸዋል ።
ከተአምራቶቹም አንዱ በአንዲት ቀን ጋኔን ያደረበት ዲዳ ሰውን ወደርሱ አመጡ ቅዱስ ማቴዎስንም በአየው ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ሰውዬውን ከምድር ላይ ጣለው ቅዱሱም በዘይት ላይ ጸለየ በ #መስቀል ምልክትም አማትቦ ቀባው በዚያንም ጊዜ ድኖ አእምሮው ተመለሰ የሚሰማና የሚናገርም ሆነ ደስ ብሎትም ወደቤቱ ሔደ ።
ጨዋዎችም በመጡ ጊዜ ማዕድ ያቀርብላቸውና በሰላም በፍቅር ያሰናብታቸዋል እነርሱም ለበረከት እያሉ ጥቂት ቁራሽ ወደ ቤታቸው ይወስዳሉ በበሽተኞችም ላይም በአደረጉት ጊዜ ወዲያውኑ ድነው #እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል።
ሁለተኛ ተአምር በአንዲትም ዕለት ደም ግባቷ ያማረ ጋኔን ያደረባትን ብላቴና ወደርሱ አመጡ እርሷ ብዙ ጊዜ ልብሷን ትቀዳለች ወደርሷም መቅረብ የሚችል የለም ወላጆቿም በታላቅ ኀዘን ውስጥ ይኖራሉ ቅዱስ አባ ማቴዎስም በላይዋ ጸለየና ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ዘይቱን ቀብቶ አዳናት።
ሦስተኛ ተአምር በአንዲት ዕለት እጅግ በከፋችና ታላቅ በሆነች ኃጢአት ላይ የወደቀች ኃጢአተኛ ሴት ወደርሱ አመጡ እርሷ ፀንሳ የመውለጃዋ ጊዜ የደረሰ ነው በቀንና በሌሊትም በምጥ ሕማም ትሠቃይ ነበረ አባ ማቴዎስም ልጄ ሆይ ኃጢአትሽን እመኚ በ #እግዚአብሔር ፊት አትዋሺ አላት። እርሷም እንዲህ አለችው እኔ ከሁለት ወንድማማቾች ጋር እነርሱ ሳያውቁ ሳመነዝር ኖርኩ በጸነስኩም ጊዜ ሕፃኑን በመርዝ አውጥቼ ለውሾች ሰጠሁት አባ ማቴዎስም በሰማ ጊዜ ወደ #እግዚአብሔር ጸለየ በዚያንም ጊዜ ለሌሎች መቀጣጫ ትሆን ዘንድ ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻት።

የዚህም አባት ተአምራቶቹ ብዙ ናቸው ተነግሮ አያልቅም በአንዲትም ቀን በበረሀ ውስጥ ሲጓዝ ጅብ ልብሶቹን በጥርሶቻ ይዛ ሳበችውና በሠንጣቃ ገደል ውስጥ የወደቁ ልጆቿን አሳየችው በአወጣላትም ጊዜ ሰገደችለት እግሮቹንም ላሰች።
ከዚህም በኋላ ዕረፍቱ ሲቀርብ በታኅሣሥ ሦስት ቀን ወደ ሠርግ እንደሚጠራው ራእይን አየ ይኸውም የቅዱሳን አባቶች የአባ እንጦንስ፣ የአባ መቃርስ፣ የአባ ጳኪሚስ፣ የአባ ቴዎድሮስ፣ የአባ ሙሴ ጸሊም፣ የአባ ሲኖዳ የአንድነት ተድላ ደስታ ወዳለበት ነው። እነርሱም በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእኛ ጋር ትኖር ዘንድ ወደእኛ መምጣትህ መልካም ነው አሉት ብዙ አትክልቶችና ዙፋኖች ወዳሉት ታላቅ አዳራሽም ደጅ አደረሱት ማቴዎስ ይገባ ዘንድ የአዳራሹን ደጆች ክፈቱ የሚልንም ቃል ሰማ ከዚህም በኋላ በዚሁ ወር በሰባት አረፈ ሦስት አክሊላትንም ተቀበለ።
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን በጻድቅ በነቢያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታህሣሥ_7ና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)

#ታህሳስ_7
የዜማ ቀን የዛሬዋ ዕለት የቅዱስ ያሬድ ዜማ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የዋለበት ዕለት ናት፡፡
ስለዚህ ቀን ከማለታችን በፊት ስለ ቅዱስ ያሬድ እና ስለ ዜማው ትንሽ እንበል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ሚያዚያ 5 ቀን በ505ዓ.ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡ አባቱ አብዩድ ወይም ይስሐቅ ይባላል እናቱ ክሪስቲና ወይም ታውክልያ ትባላለች፡፡ ቅዱስ ያሬድ በተወለደ በ7 ዓመቱ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ገበዝ ለነበረው ለአጎቱ ለጌዴዎን እንዲያሳድገውና እንዲያስተምረው አደራ ሰጠችው፡፡ ከአጎቱ ዘንድ መዝሙረ ዳዊት በሚማርበት ጊዜ ስለሚቆጣውና ስለሚገርፈው መታገስ ተስኖት ማይኪራህ ወደምትባል ቦታ ሄዶ ተደበቀ ያም ቦታ የቀዳማዊ ምኒልክ መቃብር ቦታ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም ወደ አንዲት ዛፍ ስር ተጠግቶ አርፎ እያለ አንዲት ትል የዛፍ ፍሬ ለመብላት ዛፉ ላይ ለመውጣት ስድስት ጊዜ ሲወጣና ሲወርድ ከቆያ በኃላ በሰባተኛው ከዛፉ ላይ ወጥቶ የዛፉን ፍሬ ሲበላ ተመለከተ፡፡
➛ቅዱስ ያሬድ የትሉን ተስፋ አለመቁረጥ ከፍተኛ የሆነ ትጋቱን እንዲሁም ወደላይ ለመውጣት ብዙ ጊዜ እየሞከረ ቢወድቅም ከዓላማው ሳይናወጥ ከብዙ ድካምና ጥረት በኃላ ያሰበው እንደተፈጸመለት ተመልክቶ “ሰውነቴ ሆይ ግርፋትን ለምን አትታገሽም፤ መከራንስ ለምን አትቀበይም” ብሎ ሰውነቱን ከገሰጸ በኃላ ወደ መምህሩ ተመልሶ “አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝ እንደቀድሞ አስተምረኝ” አለው፡፡
➛መምህሩ ጌዴዋንም ተቀብሎ ያስተምረው ጀመር፡፡ ወደ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን አዘውትሮ እየሄደ ጥበብና እውቀትን የሚገልጽ
የ #ጌታዬ_እናቱ_እመቤቴ_ሆይ አይነ ልቦናዬን ያበራልኝ ዘንድ ለምኝልኝ እያለ ይለምን ነበር፡፡ ከዚያም በአንድ ቀን 150 መዝሙረ ዳዊት፣
መኃልየ ነቢያት፣ መኃልየ ሰሎሞን ሌሎችን እና ትርጓሜ መጻሕፍት ብሉያትና ሐዲሳትን አወቀ፡፡ በዚያ ዘመን ድምጽን ከፍ አድርጎ #እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ዜማ አልነበረም ቀስ ብሎ እንደ ውርድ ንባብ እያዜሙ ያመሰግኑ ነበር እንጂ፡፡
#እግዚአብሔርም በያሬድ ቃልና ከፍ ባለ ዜማ መመስገን በወደደ ጊዜ ኅዳር 5 ቀን 527ዓ.ም በኤዶም ገነት በ #ሥላሴ አምሳል ሦስት አእዋፍን ወደ እርሱ ላከ እነሱም በግዕዝ፣ ዕዝል እና በአራራይ ዜማ እንደዚሁ በ #አብ በ #ወልድ በ #መንፈስ_ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ ሦስቱ አእዋፍ ቅዱስ ያሬድ በቆመበት ቦታ ፊት ለፊት በአየር ላይ ቆመው “ብፁዕ ያሬድ ብፅዕት ከርሥ እንተ ጾረተከ ወብፁዕት አጥባት እለ ሐፀናከ፤ የተመሰገንክና የተከበርክ ያሬድ ሆይ አንተን የተሸከመች ማህጸን የተመሰገነች ናት አንተን ያሳደጉ ጡቶችም የተመሰገኑ ናቸው” አለችው ቅዱስ ያሬድም ይህንን ቃል በሰማ ጊዜ ወደ ሰማይ ተመልክቶ እናንተ በሰው አንደበት የምትናገሩ ወፎች ከወዴት መጣችሁ አላቸው ከሦስቱ አንዲቱ እንዲህ ስትል ተናገረችው ከኤዶም ገነት ወደ አንተ ተልከን ሲሆን ይኸውም ከሃያ አራቱ ካህነት ሰማይ ማኅሌትን ትማር ዘንድ ልንነግርህ መጣን አሉት፡፡
➛ከዚያም ቅዱሳን መላእክት በዜማ ወደ ሚያመሰግኑባት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም በአካል ተነጠቀ፡፡ በዚያም መላእክት ሰማያውያንና ምድራውያን ደቂቀ አዳምን የፈጠረ #እግዚአብሔርን በማኅሌት በቅኔ በከፍተኛ ድምጽ ያለማቋረጥ በመንበሩ ዙሪያ
ሆነው ሲያመሰግኑት በሰማ ጊዜ ካለበት ስፍራ ተነስቶ እነሱ ወዳ አሉበት ቦታ ሊገባ ወደደ ነገር ግን አልተቻለውም፡፡ ከዚያም በኃላ እነዛ አእዋፎቹ ወደ እርሱ ተመልሰው መጥተው ያሬድ ሆይ “የሰማኸውን አስተውለኸዋል” ብለው ጠየቁት “አላስተዋልሁም” ብሎ መለሰላቸ እንግዲያውስ አዲሱን የ #እግዚአብሔርን ምስጋና ጥራ እርሱም የ #ጌታችን_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ነው አለችው።
➛ ቅዱስ ያሬድም “ማኅሌትን በዓይነቱ ልቤ መልካምን ነገር አውጥቶ ተናገረ” እያለ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ተማረ፡፡ ቅዱስ ያሬድም የመላእክት ሥርዐታቸውን ዐይቶ፣ ማሕሌታቸውን አጥንቶ ኅዳር 6 ቀን 527 ዓ.ም በጠዋት ሦስት ሰዓት ወደ ቀድሞ ቦታው ተመልሷል፡፡ ከዚያም አክሱም ከተማ ወደምትገኝው ወደ ጽዮን ቤተክርስቲያን ገብቶ በዓውደ ምህረቱ ቆሞ ድምጹን ከፍ አድርጎ “ሃሌ ሉያ ለ #አብ፣ ሃሌ ሉያ ለ #ወልድ፣ ሃሌ ሉያ ወለ #መንፈስ_ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ ብሎ በልሳነ ግዕዝ አዜመ፡፡ ይህም ማለት ዓለም ሳይፈጠር ለነበረና ዓለምን አሳልፎ ለዘለዓለም ለሚኖር ለ #አብ ምስጋና ይገባል፤ ለ #ወልድም ምስጋና ይገባል፤ ለ #መንፈስ_ቅዱስም ምስጋና ይገባል፤ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ፤ ዳግመኛም ደብተራ ኦሪትን እንዴት አድርጎ መሥራት እንዳለበት ለሙሴ አሳየው ማለት ነው፡፡” ከሰማይ እንደተመለሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣዕመ ዜማውን ያሰማበት ቦታ “ሙራደ ቃል” (የቃል መውረጃ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ይኸውም ዜማው ከሰማይ የወረደ ለመሆኑ እውነተኛ ማስረጃ ነው፡፡ ይህችንም ዜማ “አርያም” አላት፡፡ ይህም ማለት ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘች ማለት ነው፡፡ ይህንንም ዜማ ከፍ አድርጎ በሚያሰማ/ በሚያዜም/ ጊዜ ሰው፣እንስሳና አዕዋፍ ሁሉ እርሱ ወዳለበት ቦታ ተሰብስበው ከጣዕሙ የተነሣ መንፈስን የሚያድሰውን ልቡናን የሚያስደስተውንና አጥንትን የሚያለመልመውን ሰማያዊን ዜማ ይሰማሉ፡፡
➛ቅዱስ ያሬድ በግእዝ፣ በዕዝልና በዓራራይ ዜማውን እያስማማ #እግዚአብሔርን
ማመስገኑን ቀጠለ፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀል የዜማውን ጣዕም ከሰሙና ከተረዱ በኋላ #እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን መገልገያና ለሕዝቡ መባረኪያ የሰጣቸው መሆኑን በመገንዘብ ሊቃውንቱንና ካህናቱን “ተቀበሉትና ለቤተ ክርስቲያን መገልገያ ይኹን” ብለው አዘዟቸው፤ ነገር ግን ካህናቱና ሊቃውንቱ ምን ምልክት ዐይተን እንቀበለው ብለው መለሱላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ንጉሡ እርሱ #አምላካችን_እግዚአብሔር ይግለጽልን ብለው ከታኅሣሥ አንድ ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ሰባት ቀን ሱባዔ እንዲያዝ አወጁ፡፡ ታኅሣሥ አንድ ቀን ሰኞ ዕለት ውሎ ነበርና ከሰኞ እሰከ እሑድ አንድ ሱባዔ ይዘው በየቀኑ የአክሱም ጽዮን #ማርያምን ቤተክርስቲያን እየዞሩ አራት መቶ እግዚኦታና አርባ አንድ
በእንተ #ማርያም እያደረሱ ምሕላውን አካሔዱ፡፡ በሰባተኛው ቀን እሑድ ዕለተ ምሕላውን ጨርሰው ሲያሳርጉ፦" #ጌታ በዕለተ ዐርብ እንደተሰቀለ ሆኖ በአክሱም ጽዮን #ማርያም ቤተክርስቲያን ጉልላት ላይ ተገለጸ፡፡ ከዚህም አያይዞ ቅዱስ ያሬድ “ዘበ #መስቀሉ ተቀነወ ወበነቢያት ተሰብከ መላእክት ወሊቃነ መላእክት ሰብሕዎ ኪያሁ ንሰብክ መድኅነ” ብሎ ነገረ #መስቀሉን በማውሳት የ #ወልድ ምሳሌ በሆነው በዕዝል ዜማ ዘመረ፡፡ ትርጓሜውም “በነቢያት ትንቢት የተነገረለትና በ #መስቀሉ ላይ የተቸነከረው #ጌታ መላእክትና የመላእክት አለቆች አመሰገኑት፤ እኛም እርሱ #መድኃኒት እንደሆነ እንናገራለን” ማለት ነው፡፡
➛በዚህ በተገለጸው ምስክርነት መሠረት ዜማው ከ #እግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠ መሆኑ ታምኖ ከዚያን ዕለት ጀምሮ የቅዱስ ያሬድ ዜማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መደበኛ መገልገያ ሆነ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ይህ ቀን ስብከት ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ስብከት መባሉም ቅዱስ ያሬድ ዜማ ማስተማር የጀመረበት ነቢያት ይወርዳል፣ ይወለዳል ብለው የተናገሩት ትንቢት ለመፈጸሙ መታሰቢያ ስለሆነ ነው ይህም ቀን እስከ ታኅሣሥ 13 ታስቦ ይውላል፡፡

#ታኅሣሥ_7_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ኤፌሶን 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።
¹¹ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።
¹² መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።
¹³ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።
¹⁴-¹⁵ እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤
¹⁶ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤
¹⁷ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
¹⁸ በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤
¹⁹ ደግሞ የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንዳስታውቅ አፌን በመክፈት ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ለምኑ፤
²⁰ ስለ ወንጌልም በሰንሰለት መልእክተኛ የሆንሁ፥ መናገር እንደሚገባኝ ስለ እርሱ በግልጥ እናገር ዘንድ ለምኑ።
²¹ ነገር ግን እናንተ ደግሞ እንዴት እንዳለሁ ኑሮዬን እንድታውቁ የተወደደ ወንድምና በጌታ የታመነ አገልጋይ ቲኪቆስ ሁሉን ያስታውቃችኋል፤
²² ወሬአችንን እንድታውቁና ልባችሁን እንዲያጽናና ወደ እናንተ የምልከው ስለዚህ ምክንያት ነው።
²³ ከእግዚአብሔር አብ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፍቅር ከእምነት ጋር ለወንድሞች ይሁን።
²⁴ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ባለመጥፋት ከሚወዱ ሁሉ ጋር ጸጋ ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤
¹¹ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤
¹² የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።
¹³ በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው?
¹⁴ ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ ብፁዓን ናችሁ። ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም፥
¹⁵ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።
¹⁷ እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፦ የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር።
¹⁸ ይህንም እጅግ ቀን አደረገች። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱን፦ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።
¹⁹ ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤
²⁰ ወደ ገዢዎችም አቅርበው፦ እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ከተማችንን እጅግ ያናውጣሉ።
²¹ እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ አሉ።
²² ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤
²³ በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።
²⁴ እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው።
²⁵ በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_7_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ሌሊተ ተዛዋዕኩ ምስለ ልብየ ወአንቃሕክዋ ለነፍስየ። ቦኑ ለዓለም ይገድፍ እግዚአብሔር። ወኢይደግምኑ እንከ ተሣህሎ"። መዝ 76፥6-7።
"በሌሊት ከልቤ ጋር ተጫወትሁ፥ ነፍሴንም አነቃቃኋት። እግዚአብሔር ለዘላለም ይጥላልን? እንግዲህስ ቸርነቱን አይጨምርምን"? መዝ 76፥6-7።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_7_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ ኢየሱስም ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ።
²² እነሆም፥ ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላ ጮኸች።
²³ እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት እያሉ ለመኑት።
²⁴ እርሱም መልሶ፦ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።
²⁵ እርስዋ ግን መጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ እርዳኝ እያለች ሰገደችለት።
²⁶ እርሱ ግን መልሶ፦ የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም አለ።
²⁷ እርስዋም፦ አዎን ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለች።
²⁸ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ፦ አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች።
ወይም👇
ማርቆስ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
¹⁶ ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።
¹⁷ ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥
¹⁸ የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።
¹⁹ ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።
²⁰ እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ቄርሎስ_ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

#ታኅሣሥ_8
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ስምንት በዚህች ዕለት #የአቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ተወለዱ፣ በዚህች ቀን የድባው #አቡነ_ሙሴ ልደታቸው ነው፣ #ብፅዕት_እንባመሪና ተወለደች፣ ታላቅ አባት #አባ_ኪሮስ ልደቱ ነው፣ የከበሩ ሴቶች #ቅድስት_በርባራና_ቅድስ_ዮልያና በሰማዕትነት አረፉ፣ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ #አባ_ያሮክላ አረፈ፣ #አባ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ቀልሞን አረፈ፣ #ቅዱሳን_አባ_ኤሲና_እኅቱ_ቴክላ በሰማዕትነት አረፉ፣ #አባ_ዮሐንስ_ዘደማስቆ አረፈ፣ የደብረ ድማሕ #ቅዱስ_ተክለ_አልፋ አረፈ፣ ሰማዕት ቅዱስ_ገብረ_ማርያም ዕረፍቱ ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_እስትፋሰ_ክርስቶስ (ልደታቸው)
ታኅሣሥ ስምንት በዚህች ዕለት የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የልደታቸው መታሰቢያ በዓል ነው፡፡ ታሪካቸውን ከዛሬው ከወርሃዊ በዓላቸው ጋር እናየዋለን፡- አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለ #አብ ስብሐት ለ #ወልድ ስብሐት ለ #መንፈስ_ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል፡፡ የስማቸው ትርጓሜ የ #አብ የ #ወልድ የ #መንፈስ_ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የ #ክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ #መንፈስ_ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡፡
በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ #እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡ ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡፡ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ #ጌታችን_ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡
አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከ #ጌታችን_ከመድኃኒታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡ አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡ ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ #ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ›› ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው ‹‹ #እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል #ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ #መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የ #መድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት ይደግማሉ፡፡ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ #ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የ #መድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ጸሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡ ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልደው ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ሙሴ_የድባው
በዚህች ቀን የድባው አቡነ መሴ ልደታቸው ነው። የትውልድ አገራቸው እስራኤል ልዩ ቦታው ቃና ዘገሊላ ነው። ጽንሰታቸውን ቅዱስ ሩፋኤል መጋቢት 8 ቀን ሲያበስር ልደታቸውን ደግሞ ቅዱስ ገብርኤል ታኅሣሥ 8 ቀን የመወለዳቸውን ብሥራት ተናግሯል፡፡ ሲወለዱ ሚካኤል ወገብርኤል በሰው አምሳል ተገልጠው "የ #እግዚአብሔር ሰው ሙሴ" ብለው ስም አወጡላቸው፡፡
በተወለዱም በ40ኛ ቀናቸው ከተጠመቁ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል አቅፎ ይዟቸው #ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ አቁርቧቸዋል፡፡ በእሳቸውም ምክንያት በዚያች ዕለት በቤተ ክርስቲያን የነበሩት ሰዎች ሁሉ ክቡራን በሆኑ በ #ጌታችን እጆች ቆርበዋል፡፡ የአቡነ ሙሴ አባታቸው ዮስጦስ ለሐዋርያው ናትናኤል አጎቱ ነው፡፡ እናታቸው ጵርስቅላ #ጌታችን በሠርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን የለወጠለት የዶኪማስ ልጅ ናት፡፡
#ጌታችን ወደ ዶኪማስ ቤት ሠርግ ተጠርቶ የሄደው ዶኪማስ ናትናኤልን ‹‹ሠርጌን እንዲባርክልኝ #ጌታ_ኢየሱስን ከእናቱ ጋር ጥራልኝ›› ብሎት ነው፡፡ #ጌታችን በስብከቱ ‹‹ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልሏቸው›› ብሎ ብሎ ካቀፋቸውና
ካስተማረባቸው ሕፃናት አንዱ ይኽ አቡነ ሙሴ ናቸው፡፡ ጻድቁ ዋሻዎችን እየፈለፈሉ የቅዱሳን ሐዋርያትን ዐፅም በክብር ያስቀምጡ ነበር፡፡ የተሠወሩ አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ ወንጌልን በማስተማር ብዙ መከራ የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ በግብፅ "ንጉሥ አንስጣስዮስ" ተብለው 40 ዓመት በንግሥና እና በድንግልና ኖረዋል፡፡

ከዚህም በኋላ በ #እግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ በመልአክም ምክር ዮናኒ የተባለውን ሌላ ሰው አንግሠው ወደ አስቄጥስ ገዳም ገብተው መነኮሱ፡፡ በገዳሙም በታላቅ ተጋድሎ ከኖሩ በኋላ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የእኛ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ሲያርፉ በቅዱስ አትናቴዎስ ተሹመው 2ኛው የኢትዮጵያ ጳጳስ ሆነው ‹‹አቡነ ሰላማ ካልዕ›› ተብለው ተሾመው ወደ አገራችን መጡ፡፡ ከመሾማቸው በፊት አባቶቻችን አቡነ አትናቴዎስን ‹‹ጳጳስ ይላኩልን›› ብለው መልእክት ሲልኩባቸው አቡነ አትናቴዎስም ወደ አስቄጥስ ገዳም በመሄድ #እግዚአብሔርን በጸሎት ቢጠይቁት የታዘዘ መልአክ መጥቶ ‹‹የ #እግዚአብሔር ሰው ሙሴን ላክላቸው›› አላቸው፡፡ መነኮሳቱም ሁሉ እንዲሁ አሉ፡፡ ከዚህም በኋላ ሲሾሙ ቅዱሳን ሚካኤልና ገብርኤል በወርቅ ወንበር ላይ አስቀምጠዋቸው ‹‹ይገባዋል ይገባዋል›› ብለው ቅብአ ክህነት ቀብተዋቸዋል (ጵጵስና ሾመዋቸዋል፡፡) አቡነ ሙሴም ከተሾሙ በኋላ 14000 መነኮሳትን አስከትለው ወደ ቅድስት አገራችን መጡ፡፡ አቡነ ሙሴ ንግሥናቸውን ትተው ወደ ኢትዮጵያ መተው 16 ፍልፍል ቤተመቅደሶችን የሠሩ ሲሆን 8ቱ የተሰወሩ ናቸው፡፡
በገዳማቸው በቅድስቱ ውስጥ ጥልቀቱ የማይታወቅ እጅግ ጥልቅ የሆነ ጉድጓድ አለ፡፡ በውስጡም ስውራኑ አብያተ ክርስቲያናት ይገኙበታል፡፡ ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተቀረጸውና ፍልፍል የሆነው የገዳማቸው የቤተልሔሙ ስፋት ሜትር ከሃያ ሲሆን ጣራው እንደ አቡነ አሮን ክፍት ሆኖ ሳለ ዝናብ ግን አይገባበትም፡፡ ዝናብ የማያስገባው የቀዳዳው ስፋት አንድ ሜትር በአንድ ሜትር ነው፡፡ ጻድቁ በሀገራችንም ዕፁብ ድንቅ የሆኑ ብዙ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽና ወንጌልን በማስተማር ብዙ ደክመዋል፡፡ በተለይም በዋናነት የሚታወቁት በሰሜን ወሎ አውራጃ ወልድያ ወረዳ መቄት ልዩ ቦታው ገረገራ የሚገኘው ‹‹አዲስ አንባ ዋሻ #መድኃኔዓለም›› እና መጀመሪያ እንደመጡ ያረፉባት ‹‹ድባ ማርያም›› ይጠቀሳሉ፡፡
ይህችውም ድባ ማርያም ገዳም ታላቁ አባት እስትንፋሰ ክርስቶስ የመነኮሱባት ናት፡፡ ጻድቁ አቡነ ሙሴ መስከረም 4 ቀን #ጌታችን ቃልኪዳን ሲገባላቸው እነዚህን ሁለት ገዳማቸውን ‹‹እንደ አስቄጥስ ገዳም እንደ አቡነ እንጦንስ ማኅበር ይሁኑልህ›› ብሏቸዋል፡፡ በገዳማቸው ከሚኖሩት ቅዱሳን ውስጥ 400 ወንዶች መነኮሳትና 200 ሴቶች መነኮሳያት እንደተሰወሩ መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል፡፡
ጻድቁ ሌላው ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ገና በእናቷ ማኅፀን ሳትፀነስ የቅድስት አርሴማን ጽላት ያሠሩላት መሆናቸው ነው፡፡ ቁመቱ 2 ሜትር ከ70 የሆነ ግሩም ቤተ መቅደስም ፈልፍለው አንጸውላታል፡፡ #ጌታችንም የሰማዕቷን ጽናትና ረድኤት ከቦታው እንደማይለይባቸው ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ በቃል ኪዳናቸው የታመኑትን ልጆቻቸውን መተትና መርዝ አይጎዳቸውም፡፡ ይህም #ጌታችን የሰጣቸው ልዩ ቃልኪዳናቸው ነው፡፡ ጻድቁ እንደ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ 12 ክንፍ የተሰጣቸው ታላቅ የምሕረት አባት ናቸው፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ ሙሴ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_እንባመሪና
በዚችም ዕለት የብፅዕት እንባመሪና የተወለደችበት ነው። ቅድስት መሪና ገና ልጅ ሳለች እናቷ ማርያም ሞተችባት:: ደግ አባት አንድ ልጁን በሥጋዊም: በመንፈሳዊም ሳያጐድልባት አሳደጋት:: ዕድሜዋ አሥራ አምስት ዓመት በሆነ ጊዜ ወደ ፊቱ አቅርቦ "ልጄ! እኔ ወደ ገዳም ስለምሔድ አንቺን መልካም ባል ላጋባሽ::" አላት::
ቅድስት መሪናም "ነፍሰ ዚአከ ታድኅን: ነፍሰ ዚአየኑ ታጠፍእ - የአንተን ነፍስ አድነህ እንዴት የእኔን ትተዋታለህ? እኔም እመንናለሁ::" አለችው:: አባቷ የተናገረችው ከልቧ እንደሆነ ሲያውቅ "ልጄ! ገዳም ሁሉ በአካባቢው የወንድ ብቻ ነውና ስሚኝ::" አላት::
እርሷ ግን "አባቴ! ግዴለህም: ስሜን እንደ ወንድ ቀይረህ: አለባበሴንም ለውጥ::" አለችው:: (እንደ ወንድ ለበሰች ማለት ግን እንደ ዘመኑ ዓይነት እንዳይመስላችሁ አደራ!)
ከዚያ አባትና ልጅ ሃብት ንብረታቸውን ሸጠው ለነዳያን አካፈሉ:: በፍጹም ልባቸውም መነኑ:: በደረሱበት ገዳም ቅድስት መሪና በወንድ ስም "እንባ መሪና" በሚል ገባች:: ቀጣዩ ሥራዋ እንደ ወንዶች እኩል መስገድ: መጾምና መጸለይ ነበር::
ይህችን ቅድስት ልናደንቃት ግድ ይለናል:: ማንም በእርሷ አይፈተንም:: አያውቋትምና:: እርሷ ግን ወጣት ሆና: አንድም ሴት በሌለበት ገዳም ጸንቶ መቆየት በራሱ ልዩ ነው:: መልአካዊ ኃይልንም ይጠይቃል::
ተጋድሎዋ በጣም ስለ በዛ ወንድሞች መነኮሳት ይደነቁባት ነበር:: ጺም ስለሌላትና ድምጿ ቀጭን ስለሆነ አልተጠራጠሩም:: ምክንያቱም ጃንደረባ ናት ብለው አስበዋልና:: ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን አባቷ ታሞ ከማረፉ በፊት አበ ምኔቱን ጠርቶ "ወደ ከተማ ልጄን እንዳትልክብኝ: አደራ!" ብሎት ነበር::
ያም ሆኖ አንዳንድ መነኮሳት ቅሬታ በማንሳታቸው ወደ ከተማ ተላከች:: ችግሩ ለተልእኮ ባደሩበት ቤት አንድ ጐረምሳ ገብቶ የአሳዳሪውን ልጅ ከክብር አሳንሷት ሔደ:: ሲወጣም "ድንግልናሽን ያጠፋ ማን ነው? ካሉሽ ያ ወጣት መነኩሴ አባ እንባ መሪና ነው በይ::" አላት::
ከሦስት ወራት በኋላ የዚያች ዘማ ሴት ጽንስ በታወቀ ጊዜ ለአባቷ "አባ እንባ መሪና እንዲህ አደረገኝ::" አለችው::
አባት መጥቶ እየጮኸ መነኮሳትን ተሳደበ:: አበ ምኔቱ ግራ ተጋብቶ ቢጠይቀው "የአንተ ደቀ መዝሙር እንባ መሪና ልጄን ከክብር አሳነሳት::" አለው:: አበ ምኔቱ እውነት መስሎታልና ቅድስቲቱን ጠርቶ ቁጣና እርግማንን አወረደባት:: በዚያች ሰዓት ተንበርክካ አንድ ነገር ወሰነች::
"ሴት ነኝ" ብሎ መናገሩስ ቀላል ነው:: ግን ደግ ናትና የእነዛን አመጸኛ ሰዎች ኃጢአት ልትሸከም ወሰነች:: ቀና ብላ "ማሩኝ ወጣትነት ቢያስተኝ ነው?" አለቻቸው:: ተቆጥተው ዕለቱን እየገፉ ከገዳም አስወጧት:: ከባድ ቀኖናም ጫኑባት:: ከስድስት ወራት በኋላም የእርሷ ልጅ ነው የተባለ ሕፃን አምጥተው ሰጧት::
ይህኛው ግን ከባድ ፈተና ሆነባት። እንዳታጠባው አካሏ በገድል ደርቁአል:: በዚያ ላይ ድንግል የሆነች ሴት ወተት የላትም:: ነገር ግን በ #እግዚአብሔር ቸርነት: የበጋውን ሐሩር: የክረምቱን ቁር ራሷ ታግሣ ለሕፃኑ ከእረኞች ወተት እየለመነች: እየመገበች ሦስት ዓመታት አለፉ::
በዚህ ጊዜ ወደ ገዳሙ ከከባድ ቀኖና ጋር ተመለሰች:: ሕፃኑን ስታሳድግ: ለገዳሙ ስትላላክ: ምግብ ስታዘጋጅ: ውኃ ስትቀዳ: የእያንዳንዱን ቤት ስታጸዳ ሰላሳ ሰባት ዓመታት አለፉ:: ሕፃኑም አድጐ ደግ መናኝ ወጣው:: (የቅድስቷ እጆች ያሳደጉት የታደለ ነው::)
በመጨረሻ ቅድስት መሪና (እንባ መሪና) ታማ ዐረፈች:: እንገንዛለን ብለው ቢቀርቡ ሴት ናት:: እጅግ ደንግጠው አበ ምኔቱን ጠሩት:: በዙሪያዋ ከበው እንባቸውን አፈሰሱ:: ጸጸት እንደ እሳት በላቻቸው:: ሥጋዋን በክብር ገንዘው: በአጐበር ጋርደው: በራሳቸው ተሸክመው ምሕላ ገቡ::
ሙሉውን ቀን "ስለ ቅድስት መሪና ብለህ #ክርስቶስ ሆይ ማረን?" ሲሉ ዋሉ:: ድንገት ግን ከተባረከ ሥጋዋ "ይቅር ይበለን::" የሚል ድምጽን ሰምተው ደስ ብሏቸው ቀበሯት:: እነዚያ ዝሙተኞችም ከእርሷ ይቅርታን እስካገኙበት ቀን አብደው ኑረዋል::
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስቷ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ኪሮስ

በዚችም ዕለት በምዕራባዊ በረሀ የሚኖር ታላቅና ክቡር አባት የሆነው የአባ ኪሮስ የልደቱ መታሰቢያ ሆነ።
ይህም ቅዱስ የታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ወንድሙ ነበር በከተማ ውስጥ የሚሠራውን ዐመፅ በአየ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ትቶ ከሀገሩ ወጣ። #ጌታቸንም መርቶ ወደዚች ምዕራባዊት በረሀ አደረሰው በውስጧም ብዙ ዘመናት ብቻውን ኖረ ከሰው ማንም አላየውም በዚህ ሁሉ ዘመን የዱር አራዊትም ቢሆኑ ።
በአስቄጥስም ገዳም ስሙ አባ ባውማ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ እርሱም የንጉሥ ዘይኑን ልጅ ቅድስት ኢላርያን ሥጋዋን የገነዘ ነው ። እርሱም እንዲህ አለ በቤተ ክርስቲያን ወስጥ እያለሁ አባ ባውማ ሆይ ተነሥ ወደ በረሀው ውስጥ ገብተህ ወደ ፀሐይ መግቢያ ሒድ ከቅዱሳን ሁሉ አብዝቶ ፈቃዴን የፈጸመውን የአንድ ገዳማዊ ሥጋ ትገንዝ ዘንድ የሚለኝን ቃል ከሰማይ ሰማሁ።
ያን ጊዜም ደስ ብሎኝ ተነሣሁ በበረሀውም ውስጥ ሦስት ቀን ተጉዤ ከአንድ ገዳማዊ በዓት ደርሼ ደጁን አንኳኳሁ አንድ ሽማግሌ ገዳማዊም ከፈተልኝና እርስ በርሳችን ሰላምታ ተለዋወጥን በዚች በረሀ ሌላ ገዳማዊ አለን ብዬ ጠየቅሁት አዎን አለኝ ። ሁለተኛም ስምህ ማነው አባቴ ሆይ በዚችስ በረሀ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ኖርክ አልሁት ስሜ ስምዖን ነው በዚች በረሀ የኖርኩትም ሰባ ዓመታት ነው አለኝ።
ከእርሱ ዘንድም ወጥቼ ሦስት ቀን ተጓዝኩ ሁለተኛም ስሙ ባሞን የሚባል ገዳማዊ አገኘሁ ሰላምታም ሰጠሁትና በዚች በረሀ ሌላ ገዳማዊ አለን አልሁት አዎን አለ አለኝ ። አራት ቀንም ተጓዝኩ ወደ አባ ኪሮስ በዓት ደረስኩ ቅዱስ አባት ሆይ ባርከኝ እያልኩ ደጁን አንኳኳሁ አባ ባውማ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው ብሎ ከውስጥ ተናገረኝ ። #እግዚአብሔር ያከበረህ ሰው በሰላም በፍቅር ወደእኔ ግባ አለኝ ያን ጊዜ ገብቼ ከእርሱ ተባረክሁ በፊቱም የ #እግዚአብሔርን ጸጋ ክብር አየሁ የራሱ ጠጉርና ጽሕሙ እንደ በረድ የነጣ ነበር ።
ከዚህም በኋላ ተቀመጥሁ በብብቻውም አቀፈኝ እንዲህም አለኝ እነሆ ይችን ሰዓት እየጠበቅኋት በዚች በዓት ሃምሳ ሰባት ዓመት ኖርኩ ይህንንም ሲል ጥቂት ታመመና ተኛ እየደነገጠ ያቺን ሌሊት አደረ ሲነጋም በበዓቱ ውስጥ ታላቅ ብርሃን በራ ብርሃናዊ ሰውም ገባ በእጁም የብርሃን #መስቀል አለ በአባ ኪሮስ አጠገብም ተቀምጦ ሳመዉ ባረከውም አጽናናው ሰላምን ፍቅርን አንድነትን አደረገለት ከእርሱም ተሠወረ እኔም ፈራሁ እንዲህ የሚበራ ይህን ክብር የተጐናጸፈ ይህ ማነው አልሁት ።
እርሱም ልጄ ሆይ ይህ የ #እግዚአብሔር ልጅ #ጌታ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው ልማዱ ስለ ሆነ ሁልጊዜ ይመጣል ያጽናናኛልም አለኝ ። በቀዳሚት ሰንበት ዕለትም ዘጠኝ ሰዓት በሆነ ጊዜ እስከ ሰማይ የሚደርስ ታላቅ ጩኸትን ሰማሁ ከጩኸታቸውም ኃይል የተነሣ ምድር ተናወጸች። እኔም ይህ የምሰማው ጩኸት ምንድነው ብዬ ጠየቅሁት እርሱም ልጄ ሆይ ይህ በሲኦል የሚኖሩ የኃጥአን ጩኸት ነው ስለ ቅድስት ትንሣኤው የእሑድ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ #እግዚአብሔር ያሳርፋቸዋልና ስለዚህም #እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል አለኝ ።
ሐምሌ ሰባት ቀን ቅዱስ አባ ኪሮስ ጩኾ አለቀሰ ዛሬ በግብጽ አገር ታላቅ ምሰሶ ወደቀ ይኸውም የገዳማውያን አለቃ ቅዱስ አባ ሲኖዳ ነው አለ ።
ከዚህም በኋላ ከደዌው ጽናት የተነሣ እሑድ ሌሊት እጅግ ደነገጠ በበዓቱም ውስጥ እነሆ ታላቅ ብርሃን በራ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ገብቶ በአባ ኪሮስ ራስ አጠገብ ተቀመጠ ። አባ ኪሮስም #መድኃኒታችንን_ጌታዬ_ሆይ ይህን ሰው ባርከው አለው #መድኃኒታችንም የመረጥሁህ አባ ባውማ ሆይ ጽና አትፍራም ሰላሜ በረከቴም ከአንተ ጋራ ይኑር ። አሁንም ታማኝ አገልጋዬ የሆነ የዚህን የቅዱስ ኪሮስን ያየኸውንና የሰማኸውን ወደፊትም ዳግመኛ የምታየውንና የምትሰማውን ገድሉን ጻፍ አለኝ ።
ከዚህም በኋላ #መድኃኒታችን አባ ኪሮስን እንዲህ አለው እነሆ አንተ ትሞታለህና አትዘን ሞትህ ሞት አይደለም የዘላለም ሕይወት ነው እንጂ ። የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውን የሚሰማውንም ሁሉ በምድርም መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ በደብረ ጽዮን በሚደረገው የሽህ ዓመት በዓል ምሳ ከእኔ ጋር ይቀመጥ ዘንድ አደርገዋለሁ ከቅዱሳኖቼም ጋራ እቆጥረዋለሁ ። የኃጢአቱንም መጽሐፍ ቀድጄ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ ። ለመሥዋዕት የሚገባውንም ዕጣኑንና ወይኑን መብራቱንም መባ አድርጎ ለሚሰጥም በስምህም ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋትን ለሚያደርግ ዓይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰው ልቡናም ያልታሰበውን በጎ ዋጋ እኔ እጥፍ ድርብ አድርጌ እሰጠዋለሁ ። በበኵር ቤተ ክርስቲያንም ቅዱሴ ሥጋዬንና ክቡር ደሜን አቀብላቸዋለሁ በዚህም ዓለም ቤታቸውን እባርካለሁ ። ልጆቻቸውን አሳድጋለሁ ከበጎ ነገር ሁሉ ምንም ምን አያጡም ።
አሁንም ከዚህ ዓለም ድካም ወደ ዕረፍት የዘላለም ተድላ ደስታ ወዳለበት ወደ ብርሃን ቦታ እወስድህ ዘንድ ጊዜው ደረሰ #መድኃኒታችንም ይህን ሲናገር እነሆ ነቢዩና ዘማሪው ዳዊት መጣ መሰንቆውም ከእርሱ ጋራ ነበረች። ይቺ ዕለት በእርሷ ፈጽሞ ሐሤት እናደርግ ዘንድ #እግዚአብሔር የሠራት ናት እያለ አመሰገነባት።
#መድኃኒታችንም አባ ኪሮስን እነሆ ዘማሪው ዳዊት መጥቷልና ይዘምርልህ ዘንድ የምትሻውን ንገር አለው። ዳዊትም ቅዱስ አባ ኪሮስን በየትኛው አውታር እንድዘምርልህ ትሻለህ ደግሞስ በየትኛው ዜማ በየትኛው ስልት በመጀመሪያው ነውን ወይስ በሁለተኛው ወይስ በሦስተኛው አለው። ቅዱስ አባ ኪሮስም በዐሥሩም አውታር በየስልታቸውና በየዜማቸው ልሰማ እሻለሁ አለ። ያን ጊዜ ቅዱስ ዳዊት መሰንቆውን አዘጋጅቶ የጻድቅ ሞቱ በ #እግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው አለ ዳግመኛም ጐለመስሁ አረጀሁም የሚወድቅ ጻድቅን አላየሁም አለ ። ዳዊትም ድምፁን አሣምሮ ዘመረ መሰንቆውንም በስልት መታት ። ያን ጊዜም የቅዱስ አባ ኪሮስ ነፍሱ ወጣች #መድኃኒታችንም ተቀብሎ ሳማት ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤልም ሰጣት ።
እኔ አባ ባውማም የቅዱስ አባ ኪሮስን ሥጋውን ቀበርኩ ከበዓቱም በወጣሁ ጊዜ በረሀው በሰማይ ሠራዊት ተመልቶ አየሁ #መድኃኒታችንም የቅዱስ አባ ኪሮስ ሥጋው ባለበት በዓት ላይ #መስቀሉን አኑሮ ዘጋት ። ከዚህም በኋላ #መድኃኒታችን ለኔ ሰላምታ ሰጥቶኝ መላእክትና የመላእክት አለቆች በፊቱ እያመሰገኑና እየዘመሩ በታላቅ ክብር ዐረገ ። የቅዱስ አባ ኪሮስን ነፍስ ከ #መድኃኒታችን ጋራ እንደዚህ አሳረጓት ። እርሷም በተሰጣት ክብር ደስ እያላት ዐረገች ።
እኔም አባ ባውማ በዚያ ቦታ ብቻዬን ቀረሁ ተመልሼም ወደ አባ አሞን በዓት ደረስሁ ። ከዚያም የሦስት ቀን መንገድ ተጉዤ ወደ አባ ስምዖን በዓት ደረስሁ ። ከዚያም ሦስት ቀን ተጉዤ ወደ ቦታዬ ወደ አስቄጥስ ገዳም ደረስኩ። ለመነኰሳቱም ሁሉ ያየሁትንና የሰማሁትን ሁሉ የቅዱስ አባ ኪሮስን ገድሉን ስለ አባ ሲኖዳም ዕረፍት ትንቢት እንደ ተናገረ ነገርኋቸው።
መነኰሳቱም ሰምተው እጅግ አደነቁ የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ። እኔ አባ ባውማም የቅዱስ አባ ኪሮስን ገድሉን ጽፌ ለሚያነበውና ለሚሰማው ሁሉ መጽናኛ ይሆን ዘንድ ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉና ወደ ገዳማትም ላክሁ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አቡነ ኪሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_በርባራና_ቅድስት_ዮልያና

በዚችም ቀን የከበሩ ሴቶች በርባራና ዮልያና በሰማዕትነት አረፉ ። ይችም ቅድስት በርባራ በከሀዲው መክስምያኖስ ዘመነ መንግሥት በቤተ መንግሥት ውስጥ ታላቅ መስፍን ለሆነ ሰው ልጁ ናት ስሙም ዲዮስቆሮስ ነው እርሱም ለልጁ ለበርባራ ማንም እንዳያያት ታላቅ ጽኑ የሆነ ሕንፃ አሠራ ከዚህም ዳግመኛ መታጠቢያ የውሽባ ቤት በግንብ ሠራ የሚከፈቱ ሁለት መስኮቶችንም በውስጡ እንዲሠሩ አዘዘ ። ቅድስት በርባራም ሁለቱን መስኮቶች በአየች ጊዜ ሦስተኛ መስኮትን እንዲሠሩ ሐናፂዎችን አዘዘቻቸው ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና የ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን አዳኝ የሆነ የ #መስቀሉን ምልክት በውኃ መታጠቢያው ላይ አሠራች ።
አባቷም ወደዚህ ሕንፃ በገባ ጊዜ ይህን ልጁ ያሠራችውን አይቶ አናፂዎችን ጠየቀ እነርሱም ይህን እንድንሠራ ልጅህ አዘዘችን አሉት እርሷንም ጠርቶ ለምን እንዲህ አደረግሽ አላት። እርሷም አባቴ ሆይ አስተውል ልዩ ሦስት በሆነ በ #ሥላሴ ስም ሥራ ሁሉ ይፈጸማልና ስለዚህ ሦስተኛ መስኮት አሠራሁ ይህም #መስቀል ዓለሙ ሁሉ በእርሱ በዳነበት በ #መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #መስቀል አምሳል ነው አንተም አባቴ ሆይ ከስሕተትህ ተመልሰህ የፈጠረህን አምላክ አምልከው አለችው ።
አባቷም ከእርሷ ይህን በሰማ ጊዜ ሰይፉን መዝዞ በኋላዋ ሮጠ እርሷም ሸሸች በፊቷም የነበረች ዐለት ተሠንጥቃ በውስጧ ገብታ ሠወረቻት ። ከዚህም በኋላ ወደ አባቷ ተመለሰች እርሱም እንዲአሠቃያት ለሌላ መኰንን አሳልፎ ሰጣት እርሱም ታላቅ ሥቃይን አሠቃያት በዚያም ዮልያና የምትባል ሴት ነበረች ቅድስት በርባራንም አየቻትና የምታጽናናትና የምታረጋጋት ሆነች ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ለቅድስት በርባራ ተገለጸላትና አረጋጋት።
ከዚህም በኋላ አባቷ በሰይፍ ራሷን እንዲቆርጡ የባልንጀራዋ የዮልያናንም ራስ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጧቸው የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ ። በዚያንም ጊዜ ከሰማይ እሳት ወርዶ አባቷንና ጓደኛው የሆነ መኰንን መርትያኖስን አቃጠላቸው ያም በውሽባ ቤት ውስጥ በ #መስቀል ምልክት ያሠራቸው መታጠቢያ ለታመመ ሁሉ ከእርሱ በታጠበ ጊዜ የሚያድን በውስጡ ታላቅ ፈውስ ያለበት ሆነ ።
ከዚህም በኋላ የቅዱሳት ሰማዕታትን ሥጋቸውን ወስደው ከከተማ ውጭ ባለች ቤተ ክርስቲያን ስሟ ገላልያ በሚባል ቦታ አኖሩአቸው ይህ ሥጋቸውም በቅዱሳን ሰማዕታት በአቡቂርና በዮሐንስ በምስር አገር በአለ ቤተ ክርስቲያናቸው እስከ ዛሬ አለ ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አንእስት ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባት_አባ_ያሮክላ
በዚህች ቀን የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ያሮክላ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዐሥራ ሦስተኛ ቊጥር ነው ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አስቀድሞ አረማውያን ነበሩ በወለዱትም ጊዜ የአረማውያንን ትምህርት መጻሕፍቶቻቸውንም ሁሉ አስተማሩት ።
ከዚህም በኋላ አምነው ተጠመቁ ይህን ልጃቸውንም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማሩት የሐዋርያትንም መጻሕፍት አጠና ሊቀ ጳጳሳት ድሜጥሮስም ዲቁና ሾመው ከዚህም በኋላ በእስክንድርያ አገር ቤተ ክርስቲያን ቅስና ሾመው መንጋውንም በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ ።
ሥራውንም ፈጸመ የቤተ ክርስቲያንንም ሕግ ጠንቅቆ አወቀ። አባት ድሜጥሮስም በአረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት እርሱም ክብር ይግባውና የ #ክርስቶስን መንጋዎች በቀናች ሃይማኖት አጽንቶ ጠበቀ ከአረማውያንም ብዙዎችን ክብር ይግባውና #ክርስቶስን ወደ ማመን መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው ።
ለቅዱስ ዲዮናስዮስም ለምእመናን እንዲፈርድ ሥልጣን ሰጠው እርሱ ግን ዓላው ያንን ወደ ቀናች ሃይማኖት እስከሚመልሳቸው ድረስ ያስተምራቸውና ይገሥጻቸው ነበር ። በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም ዐሥራ ሦስት ዓመት ኑሮ በሰላም አረፈ ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ቅዱስ አባት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ቀልሞን
በዚችም ቀን ቅዱስ አባት የደብረ ቀልሞን አባ ሳሙኤል አረፈ ይህም ቅዱስ ለግብጽ ደቡብ ከሆነ መጺል ከሚባል አገር ደክሉባ ከሚባል መንደር ነው ። ወላጆቹም ቅዱሳንና ንጹሐን ናቸው ያለ እርሱም ልጅ አልነበራቸውም አባቱም ቄስ ነበር ። በሌሊት በራእይ ፊቱ ብሩህ የሆነ ሰው አየ ። ይህ ልጅህ ለብዙ ሰዎች የታመነ ቸር መምህር ይሆን ዘንድ አለው በዘመኑም ሁሉ ለ #እግዚአብሔር የተመረጠ ይሆናል አለው ።
አባ ሳሙኤልም ከታናሽነቱ ጀምሮ እንደ ነቢዩ ሳሙኤል ንጹሕ ነው ሁልጊዜም የምንኲስና ልብስን ይለብስ ዘንድ ያስብ ነበር ። በአንዲትም ቀን ወደ አስቄጥስ ገዳም ይሔድ ዘንድ ምክንያት አግኝቶ ከአባቱ ዘንድ ወጣ ግን መንገዱን አያውቅም ነበር ። የ #እግዚአብሔርም መልአክ በመነኵሴ አምሳል ሁኖ እየመራው አብሮት ተጓዘ በአደረሰውም ጊዜ በበዓት ውስጥ ለሚኖር ለአንድ ስሙ አባ አጋቶን ለሚባል ሽማግሌ መነኰስ ሰጠው እርሱ እጅግ ጻድቅ ሰው ነውና ። ይህም መልአክ ስለ አባ ሳሙኤል ለአባ አጋቶን እንዲህ ብሎ ነገረው ሳሙኤልን ደስ ብሎህ ተቀበለው የምንኲስናንም ልብስ አልብሰው እርሱ የሽምግልናህን ድካም የሚያጽናና ዕውነተኛ ልጅን ይሆንሃልና አንተም የምንኲስናን ሕግ ሁሉ አስተምረው ይህንንም ከተናገረው በኋላ መልአኩ ከእርሱ ተሠወረ ።
ሳሙኤልም በደረሰ ጊዜ አባ አጋቶን በደስታ ተቀበለው እንዲህም አለው የ #እግዚአብሔር አገልጋይ ሳሙኤል ሆይ መምጣትህ መልካም ነው በሽምግልናዬ ጊዜ ጌታ ወደእኔ ልኮሃልና አለው ወዲያውኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገባውና ከፀጉር በተሠራው ቀሚስና በቆቡ ላይ በቅናትና በአስኬማ ላይ ጸለየና ባረከው የአባቶቼ የአባ እንጦንዮስና የአባ መቃርዮስ ፈጣሪ ከአንተ ጋር ይኑር ልጄ ሳሙኤል ሆይ በችግርህ ሁሉ ረዳት ይሁንህ ብሎ እኒያን የምንኲስና ልብሶችን አለበሰው ።
ቅዱስ አጋቶንም ለአባ ሳሙኤል ትሕትናን አርምሞን አስተማረው አባ ሳሙኤልም ቅዱስና ቡሩክ የሆንክ አባቴ ሆይ ይቅር በለኝ ከእኔ ጋርም ፍቅርን አድርግ አስተምረኝም #እግዚአብሔርም የሚወደውን የምሠራ ያደርገኝ ዘንድ በከበረች ጸሎትህ አስበኝ ይለው ነበር ሁልጊዜ መንፈሳዊ የሆነ የምንኲስናን ሥርዓትም ሁሉ ተማረ ። ቅዱስ አባ ሳሙኤልም በሥራው ሁሉ ይራዳው ነበረ የሚያዝዘውንም ሁሉ እየሠራ ከአባ አጋቶን ጋር ሦስት ዓመት ኖረ ከዚህም በኋላ አባ አጋቶን አረፈ ።
አባ ሳሙኤልም ሰባት ሰባት ቀን እየጾመና ታላቅ ተጋድሎን እየታገለ ኖረ ከዚህም በኋላ በአስቄጠስ በአለች በከበረች በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ቅስና ተሾመ ።
ከጥቂት ቀኖች በኋላም የልዮንን ደብዳቤ ወደ አስቄጥስ ገዳም አምጥተው አነበቧት አረጋውያን መነኰሳትም በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ አባ ሳሙኤል መንፈሳዊ ቅናትን ቀና ከሰዎችም መካከል ተነሥቶ ያቺን ደብዳቤ ነጥቆ ቀደዳት እንዲህም አለ የቀናች የአባቶቻችንን ሃይማኖት የሚለውጥ ሁሉ የተወገዘ ነው ።

የንጉሥ መልክተኛም በአየ ጊዜ ቁጣን ተመላ አባ ሳሙኤልንም በብረት ዘንጎች እንዲደበዱቡት በክንዱም ሰቅለው ፊቱን እንዲጸፉት አዘዘ በጸፉትም ጊዜ አንዲት ዐይኑ ወለቀች ከዚህም በኋላ ከአስቄጥስ ገዳም እንዲአሳድዱት ሁለተኛ አዘዘ ።
ከ #እግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ለአባ ሳሙኤል ተገለጸለትና ወደ ቀልሞን ተራራ ሒዶ በዚያ ይኖር ዘንድ አዘዘው ወዲያውኑ ሒዶ በዚያ ኖረ የቀናች ሃይማኖትንም ለሰዎች ሁሉ እያስተማረ ተቀመጠ ። ሊቀ ጳጳሳት የሆነው መለካዊ የእስክንድርያ መኰንን ምቆዝዝም ዜናውን ሰምቶ ወደ ቅዱስ አባ ሳሙኤል መጥቶ ታላቅ ግርፋትንም ገርፎ ከገዳሙ አሳደደው ።
ወደ ቀልሞን ገዳም ቤተክርስቲያንም ሒዶ በዚያ ተቀመጠ በዚያም ወራት የበርበር አረማውያን ወደዚያ መጡ ወደ አገራቸውም ሊወስዱት አባ ሳሙኤልን ያዙት ከእርሳቸውም እጅ ያድነው ዘንድ ክብር ይግባውና #ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ለመነው በአንድ ግመል ላይም በጫኑት ጊዜ ያ ግመል መንቀሳቀስ አልቻለም ታላቅ ድብደባም ደበደቡት በተሳናቸውም ጊዜ ትተውት ሔዱ እርሱም ወደ ቀልሞን ገዳሙ ተመልሶ በምንኲስና ሥርዓት በመጠመድ በሁሉ ተጋድሎ እየተጋደለ ኖረ ።
ከዚህም በኋላ የበርበር አረማውያን ዳግመኛ መጡ ከእርሳቸውም የተነሣ ፈራ ሳሙኤል ሆይ አትፍራ ግን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተህ ዝም በል ከእርሳቸው ጋር አትናገር እኔም አንዳያዩህ አደርጋቸዋለሁ የሚልን ቃል ሰማ በዚያንም ጊዜ የተመዘዙ ሰይፎቻቸውን ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገቡ እነርሱም እጅግ በሚያስፈራ ድምፃቸው ይጮኹ ነበር ቅዱስ ሳሚኤልም በቤተ መቅደስ ውስጥ ኃጢአትን ሲሠሩ ተመለከተ ስለ ድፍረታቸውም ዝም ማለት አልተቻለውም ተናገራቸው እንጂ #እግዚአብሔርን መፍራት የሌላችሁ እናንተ ከሀድያን #እግዚአብሔር እንደ ክፉ ሥራችሁ ይክፈላችሁ አላቸው ።
እነዚያ አረማውያንም አንተ ከዚህ ነበርክን እኛ ግን አላየንህም አሉት ከዚህም በኋላ ይዘው ከቤተ ክርስቲያኑ ምሰሶ ጋር አሠሩት ለመሞት እስቲቀርብም ገረፉት ከማሠሪያውም ሲፈቱት በግምባሩ ተደፋ ግመሎች እስካሉበትም ቦታ ጉተቱት ራሱንም በጫማ መቱት ከድብደባ ብዛት የተነሣ መንቀሳቀስ አልተቻለውም በግመልም ጫኑት ከሕመሙም ጽናት የተነሣ መሪር ልቅሶን የሚያለቅስ ሆነ ያም ግመል ወደርሱ ተመልሶ በሰው ቋንቋ እንዲህ ብሎ ተናገረው መደብደብህን መልካም አደረጉ ዝም በል አትናገር ያለህን የፈጣሪህን የ #እግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ተላለፍክ ሞት ይገባሃልና አለው አባ ሳሙኤልም ሲሰማ በእውነት በድያለሁ ነገር ግን #እግዚአብሔር ቻይ ነውና መተላለፌን ይቅር ይበለኝ አለ ።
ከዚህም በኋላ ወደ አገራቸው ወሰዱት በዚያም የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት የሆነውን ከእርሱ አስቀድሞ የማረኩትን አባ ዮሐንስን አገኘውና እርስበርሳቸው ተጽናኑ ። የአባ ሳሙኤልም ጌታው ፀሐይን እንዲአመልክ ያስገድደው ነበር እርሱ ግን ከቶ አልሰማውም ከዚህም በኋላ ከአንዲት ብላቴና ጋር በሰይጣን ምክር እግሩን አቆራኝቶ ግመሎችን እንዲጠብቁ ወደጫካ ሰደዳቸው ቅዱስ ሳሙኤል ከእርሷ ጋር በኃጢአት እንደ ሚወድቅና ዲያብሎስ በአስተማረውና በመከረው ሁሉ እንደሚታዘዝለት አስቧልና ።
በዚህም ሁሉ ቅዱስ ሳሙኤል ኃይልና ብርታት የሚጨመርለት ሁኖ ጌታው ታሞ ለሞት እስከ ቀረበ ድረስ በዚያ ኖረ ። አባ ሳሙኤልም በላዩ ጸለየና ከደዌው ፈወሰው ዜናውም በሀገሩ ሁሉ ተሰምቶ ደዌ ያለባቸው ሁሉ ወደርሱ የሚመጡ ሆኑ እርሱም በዘይቱ ላይ ጸልዮ ሲቀባቸው ወዲያውኑ ይድናሉ ጌታውም ይህን አይቶ እጅግ አደነቀ በአንተ ላይ ያደረግሁትን በደሌን ሁሉ ይቅር በለኝ ብሎ ሰገደለት እጅግም ወደደው አከበረውም የምትሻውንም ጠይቀኝ አደርግልሃለሁ አለው ። አባ ሳሙኤልም ወደ ሀገሬ እመለስ ዘንድ እሻለሁ አለው ጌታውም እጅ መንሻ ብዙ ገንዘብንና ግመሎችን አዘጋጅቶ በፍቅር በሰላም ሸኘው ።
ልጆቹ መነኰሳትም ወደርሱ ተሰበሰቡ አእላፋትም እስከሆኑ ድረስ እጅግ በዙ ቅድስት ድንግል እመቤታችን #ማርያምም ተገልጻለት ይህ ቦታ ለዘላለም ማደሪያዬ ይሆናል አለችው ። ከዚያቺም ዕለት ወዲህ ወደዚህ ገዳም አረማውያን ተመልሰው አልመጡም ። ይህ አባት ሳሙኤልም ብዙ ድርሳናትን ደረሰ ስለ እስላሞችም መምጣት መንግሥትንም ስለመያዛቸው የክርስቲያን ወገኖችንም በቦታው ሁሉ እንደሚአሠቃዩአቸው ትንቢት ተናገረ እነርሱም የአጋር ልጆች ናቸው ።
ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ መነኰሳት ልጆቹን ሰበሰባቸውና በ #እግዚአብሔር ሕግ ጸንተው እንዲኖሩ እስከ መጨረሻዪቱም ሕቅታ ድረስ ስለ ቀናች ሃይማኖት እንዲጋደሉ አዘዛቸው ። ከዚህም በኋላ ጥቂት ታሞ በሰላም አረፈ ።
ስለርሱም እንዲህ ተባለ አንድ ቀን ከልጆቹ ውስጥ አንዱ አረፈ አባ ሳሙኤልም ወደርሱ በመጣ ጊዜ ነፍሱ ተመልሳለት በመነኰሳቱ ፊት ተነሣ የኃጥአንን ሥቃይ የጻድቃንንም ተድላ ደስታቸውን እንዳየ ተናግሮ ተመልሶ አረፈ ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባት ሳሙኤል ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አማን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_አባ_ኤሲና_እኅቱ_ቴክላ
በዚችም ቀን ለእስሙናይን በስተምዕራብ ካለ አውራጃ ብጺር ከሚባል መንደር ቅዱሳን አባ ኤሲና እኅቱ ቴክላ በሰማዕትነት አረፉ ። ይህም አባ ኤሲ እጅግ ብዙ ገንዘብ ቦታዎችና በጎችም አሉት የበጎቹንም ጠጉር ሽያጭ ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋት አድርጎ ይሰጥ ነበር እርሱ #እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ ነበርና እህቱ ቴክላም እንደርሱ #እግዚአብሔርን የምትፈራ ናት።
የአባታቸውም ስም ኤልያስ የእናታቸውም ማርያም ይባላል እነርሱም ልጃቸውን ኤሲን የተወደድክ ልጃችን ሆይ በሕይወታችን ሳለን ልናጋባህና በአንተ ደስ እንዲለን እንወዳለን ብለው ለመኑት እርሱ ግን ይህን አልወደደም እንዲህም አላችው የተባረካችሁ አባቴና እናቴ ሆይ ጸልዩልኝ የምታዝዙኝም ሁሉ በደስታ እቀበላለሁ ስለጋብቻ ግን አትናገሩኝ አላደርገውምና ከዚያንም ጊዜ ወዲህ ስለ ጋብቻ ከቶ አልተናገሩትም እጅግ ይወዱት ነበርና ።
ከዚህም በኋላ ዕድሜው ሃያ ዓመት ሲሆነው አባቱ ሞተ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ እናቱ ሞተች ከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም በዚያ ወራት ሰው ሁሉ ጣዖት እንዲሰግድ አዘዘ ቅዱስ ኤሲም የንግድ ዕቃውን ይሸጥ ዘንድ ወደ እስክንድርያ ሔደ ።
ለአባ ኤሲም በእስክንድርያ አገር ጳውሎስ የሚባል ወዳጅ አለው እርሱም ጽኑ በሆነ ደዌ ታሞ ነበር ከደዌውም እስከሚድን አባ ኤሲ በርሱ ዘንድ ተቀመጠ በዚያም ወራት በክርስቲያን ወገኖች ላይ ታላቅ መከራ ሁኖ ነበር ። እኒህ የከበሩ ኤሲና ወዳጁ ጳውሎስ ጣፋጭና መልካም የሆነውን መብል በገንዘባቸው እየገዙ በእስክንድርያ አገር ለሚኖሩ ቅዱሳን ይወስዳሉ እንዲሁም ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም የታሠሩትን ይጎበኙዋቸዋል ያረጋጓቸዋልም እንደ ባሮችም ያገለግሏቸው ነበር እኒህ ቅዱሳንም የሰማዕትነት አክሊልን እናንተ ትቀበሉ ዘንድ አላችሁ ብለው በእነርሱ ላይ ትንቢት ተናገሩ ።
በዚህም ወራት የህርማኖስ ልጅ ቅዱስ ፊቅጦርን ወደ እስክንድርያ አገር አመጡት አባ ኤሲና ወዳጁ ጳውሎስም በአዩት ጊዜ አደነቁ መንፈሳዊ ቅንአትንም ቀኑበት እርሱ የዚህን የኃላፊውን ዓለም መንግሥት ንቋልና ። ከዚህም በኋላ አባ ኤሲ ወደ መኰንኑ ቀርቦ በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ያሠቃዩት ዘንድ አዘዘ በአለንጋዎችም ብዙ ግርፋትን ገረፉት ሕዋሳቱንም በሾተሎች ሠንጣጠቁ በሥጋውም የችቦ መብራቶችን አደረጉ በሰንሰለትም አሠሩት ሁለተኛም ነበልባሉ እጅግ ከፍ ከፍ

እስከሚል በማንደጃ ውስጥ እሳትን አነደዱ ። አባ ኤሲንም ከውስጡ ጣሉት እርሱም እንዲህ ብሎ ጸለየ ጌትነት ገንዘብህ የሆነ #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ሆይ ሠለስቱ ደቂቅን ከነደደ እሳት ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ ምስክርህ ፊቅጦርንም ከውሽባ ቤት እሳት ያዳንካቸው አንተ ነህና እንደ እነርሱ አድነኝ የሚረዳኝንም ቸር መልአክ ላክልኝ ለአንተም ምስጋና ይሁን አሜን ።
ይህንንም ጸሎት በጸለየ ጊዜ እነሆ ቅዱስ ሱርያል መልአክ ከሰማይ ወርዶ በአባ ኤሲ ቀኝ ቆመና ጻድቅ ሰው ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን #እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ከመከራህም ሁሉ እርሱ ያድንሃልና አትፍራ አለው ።
በዚያንም ጊዜ የእሳቱ ማንደጃ እንደ ቀዝቃዛ ጠል ሆነ መልአኩም የእቶኑን ግድግዳ ሠንጥቆ የከበረ አባ ኤሲን እጁን ይዞ ያለ ጥፋት በጤና አወጣው በዚያንም ጊዜ አባ ኤሲ ወደ መኰንኑ ሒዶ እንዲህ ብሎ ጮኸ አንተ ከከሀዲ ንጉሥህና ከረከሱ ጣዖቶችህ ጋር እፈር ። ሕዝቡም ሕያው ሁኖ ያለ ጉዳት አባ ኤሲን በአዩት ጊዜ እጅግ አደነቁ በአንድ ቃልም እኛ በግልጥ ክርስቲያን ነን በቅዱስ አባ ኤሲ አምላክ እናምናለን ብለው ጮኹ መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክልሊን ተቀበሉ ።
ከዚህም በኋላ አባ ኤሲን ወደ እሥር ቤት እንዲወስዱት መኰንኑ አዘዘ እንዳዘዛቸውም አደረጉ ። ለእህቱም ለቴክላ የ #እግዚአብሔር መልአክ ተገልጾላት ወንድሟን አባ ኤሲን ትጎበኘው ዘንድ ወደ እስክንድርያ አገር እንድትሔድ አዘዛት ያን ጊዜ ከእንዴናው ከተማ ተነሥታ ከባሕር ዳርቻ ደረሰች መንፈሳዊት መርከብም ተገለጸችላት ።
እመቤታችን ቅድስት ደንግል #ማርያምም ከመጥምቁ ዮሐንስ እናት ከኤልሳቤጥ ጋር በውስጧ አለች አዝነውም ተመለከተቻቸውና እመቤቶቼ ሆይ የደረሰባችሁ ምንድን ነው አዝናችሁ አያለሁና አለቻቸው ቅድስት ኤልሳቤጥም በእርጅናዬ ወራት የወለድኩት አንድ ልጅ ነበረኝ ወስደው አረዱብኝ አለቻት እመቤታችንም ቅድስት ድንግል #ማርያምም ለእኔም አንድ ልጅ ነበረኝ እርሱንም ወስደው ሰቅለው ገደሉብኝ አለቻት ። ቴክላም እመቤቶቼ ሆይ በእውነት ጽኑዕ ኀዘን አግኝቷችኋል አለቻቸው ይህንንም እየተነጋገሩ ወንድሟ አባ ኤሲ ወዳለበት አደረሷት የተገለጹላት እነማን እንደሆኑ አላወቀችም ነበር ።
አባ ኤሲም እኅቱ ቴክላን በአያት ጊዜ ፈጽሞ ደስ አለው እርሷም ከእርሱ ጋር በሰማዕትነት ትሞት ዘንድ ተስማማች ።
ከዚህም በኋላ የሌሊቱ እኩሌታ በሆነ ጊዜ የ #እግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሱርያል ለአባ ኤሲ ተገለጸለት በብርሃናውያን ክንፎቹም ተሸክሞ ወደ ሰማይ አወጣው ኢየሩሳሌም ሰማያዊትንም አሳየው ። ቅዱሳንም ሁሉ ወጥተው ሰላምታ ሰጡት የሰው አንደበት ስለርሷ ሊናገር የማይቻለው ልዕልናዋንና ክብርዋን አሳየው በወርቅ በዕንቁ ያጌጡ አደባባዮቿንም ከፀሐይ ብርሃን ሰባት እጅ የሚበልጥ በውስጧ ያለውንም ብርሃን አሳየው ስለ ክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም መከራ የተቀበሉ የጻድቃንንና የሰማዕታትን መኖሪያንም ዳግመኛ አሳየው ።
ከዚህም በኋላ የ #እግዚአብሔር መልአክ ወደ ሌላ ቦታ ወስደውና ታላቅ አዳራሽንም አሳየው በውስጡም በወርቅ በዕንቁ የተሸለሙ ሦስት መቶ ምሰሶዎች አሉ ዙፋኖችም በዕንቁ የተሸለሙ አሉ በዚያም አዳራሽ ውስጥ ሁለት መቶ ጭፍሮች ቁመው ነበር ። እነርሱም በወርቅ ዝናር የታጠቁና ያጌጡ ናቸው ከእርሳቸውም እያንዳንዱ ርዝመቱ ዐሥራ አምስት ዐሥራ አምስት ክንድ ይሆናል እኔም ኤሲ ያንን መልአክ ከዓለም ሰዎች ውስጥ በዚህ አዳራሽ አምሳል ማንም ሊሠራ የማይቻለው ይህ አዳራሽ ለማን ነው አልሁት።
መልአኩም እንዲህ አለኝ ወንድሜ አባ ኤሲ ሆይ የምድር ነገሥታት ሁሉም ከዓለሙ ሁሉ ጋር ቢሰበሰቡ ይህን አዳራሽ ከተሸከሙት ከእሊህ ከሦስት መቶ ምሰሶዎች የአንዱን ምሰሶ ሽያጭ ዋጋ አይችሉም አለኝ እኔም አይቼ አደነቅሁ #እግዚአብሔርንም አመሰገንሁት ።
ሁለተኛም ይህ የከበረና ያማረ ታላቅ አዳራሽ ለማን ይሆናል አልሁት ያ መልአክም የሠራዊት አለቃ ለነበረ ለህርማኖስ ልጅ ለሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር ይህ ሁሉ ተሰጠ ። እርሱ ምድራዊ መንግሥትን ሽልማቱንና ጌጡን ክብሩን ሁሉ ንቆ ትቶ መከራ መስቀሉን ተሸክሞ የክብር ባለቤት የሆነ #ጌታውን_ክርስቶስን ተከትሎታልና ስለዚህ ስለ ኃላፊው ምድራዊ መንግሥት ፈንታ የማይጠፋ መንግሥትን #እግዚአብሔር ሰጠው አለኝ ።
ዳግመኛም እንዲህ ብዬ ጠየቅሁት እነዚህ ዙፋኖች እነዚህም ፍሬያቸው ያማረ ዕንጨቶች እሊህም የሚያበሩ አክሊሎች ምንድን ናቸው አልሁት ። እርሱም እንዲህ አለኝ አባ ኤሲ ሆይ እሊህ የዕረፍትና የተድላ ቦታዎች የቅዱሳን ሰማዕታትን መታሰቢያቸውን በምድር ላይ ለሚያደርጉት ሰዎች #እግዚአብሔር ያዘጋጀላቸው ነው አባ ኤሲ ሆይ ስማ እኔ ላስረዳህ በሰማዕታት በስማቸው ቤተ ክርስቲያንን የሚሠራ ሰው ሁሉ ወይም ሥጋቸውን የገነዘ ወይም መሥዋዕትን የሰጠ መብራትንም ወይም የተራበ ያበላ የተራቆተም ያለበሰ ወይም ለቤተ ክርስቲያናቸው መጻሕፍትን ገዝቶ የሰጠ ወይም ገድላቸውንና ምስክርነታቸውን የጻፈ በችሎታው መጠን በመታሰቢያቸው ቀን በጎ ሥራ የሠራ ቀዝቃዛ የጽዋ ውኃ የሰጠ ዋጋውን አያጣም ብሎ ክብር ይግባውና #ጌታችን በከበረ ወንጌል እንደ ተናገረ ።
ከሰማዕታት ላንዱ ወይም ከጻድቃን መታሰቢያቸውን ሲያደርግ የነበረ ሰው በሞተ ጊዜ ያ ሰማዕት ወይም ጻድቁ መጥቶ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት ይሰግዳል #ጌታዬና_ፈጣሪዬ_ሆይ በምድር መታሰቢያየን ስታደርግ ኑራለችና ይቺን ነፍስ ስጠኝ ይላል እርሷንም ይሰጠዋል እርሱም ተቀብሎ ወደዚህ ተድላ ደስታ ወደ አለበት ቦታ ያስገባታል ።
ያቺ ነፍስ እጅግ ኃጢአተኛ ከሆነች ግን ከ #እግዚአብሔር ዘንድ ቃል ይወጣል በመላእክት አለቃ በሚካኤልም አፍ እንዲህ ተብሎ ይነገራል ሁሉን የያዘ #እግዚአብሔር ይቺን ነፍስ ለአንዲት ቅጽበት አንድ ጊዜ እንዲወረውሩዋት አዘዘ ። ከዚያም በኋላ ስለርሷ ለማለደ ለዚያ ሰማዕት ወይም ለጻድቁ ይስጡት ይላል እንደዚህም ለዚያ ሰማዕት ወይም ለጻድቁ ትሰጠዋለች እርሱም ተቀብሎ ይወስዳታል በመጠመቂያም ውስጥ ያጠምቋታል ያማሩ ልብሶችንም አልብሰው ከእነዚህ ከምታያቸው ዙፋኖች በአንዱ ዙፋን ላይ ያስቀምጧታል በማይጠፋ አክሊልም ይጋርዷታል ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ደስ እያላት ለዘላለሙ ትኖራለች ።
ከዚህም በኋላ ያ መልአክ ተሸክሞ ወደ እሥር ቤት መለሰኝ ሰላምታም ሰጥቶኝ ወደ ሰማይ ዐረገ እኔም ስለ ከበረ ስሙ ለሚጋደሉ ስለሚሰጥ ታላቅ ሀብት እጅግ አደነቅሁ ።
በነጋም ጊዜ ቅዱስ አባ ኤሲን ከእኅቱ ቴክላ ጋር ያመጡት ዘንድ መኰንኑ አዘዘ አምጥተውም በጽኑ ሥቃይ በተሽከርካሪዎች መሣሪያ በእሳት ቃጠሎ በብረት ችንካሮች የራሳቸውንም ቆዳ በመግፈፍ አሠቃዩአቸው ። #እግዚአብሔርም ያለ ጉዳት በጤና አስነሣቸው ከሥቃያቻውም የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ወደ ላይኛው ግብጽ ይወስዳቸው ዘንድ ለእንዴናው አገር መኰንን አሳልፎ ሰጣቸው ስምንት ቀንም ያህል እንደ ተጓዙ መርከቢቱ ከባሕሩ ዳር ቆመች መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ ቅዱሳን አባ ኤሲና እኅቱ ቴክላም እጅግ ደስ አላቸው ጸሎታቸውንም ጸልየው በፈጸሙ ጊዜ በሰይፍ ራሶቻቸውን ቆረጧቸው ።