Telegram Web Link
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_24_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጢሞቴዎስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።
¹⁸ መጽሐፍ፦ የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፥ ደግሞ፦ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል ይላልና።
¹⁹ ከሁለት ወይም ከሦስት ምስክር በቀር በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል።
²⁰ ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኃጢአት የሚሰሩትን በሁሉ ፊት ገሥጻቸው።
²¹ አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ መዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።
²² በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፥ በሌሎችም ኃጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽህና ጠብቅ።
²³ ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፥ ወደ ፊት ውኃ ብቻ አትጠጣ።
²⁴ የአንዳንዶች ሰዎች ኃጢአት የተገለጠ ነው ፍርድንም ያመለክታል፥ ሌሎችን ግን ይከተላቸዋል፤
²⁵ እንዲሁ መልካም ሥራ ደግሞ የተገለጠ ነው፥ ያልተገለጠም ከሆነ ሊሰወር አይችልም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ያዕቆብ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ከሁሉም በፊት፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ በሰማይ ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፥ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን።
¹³ ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር።
¹⁴ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።
¹⁵ የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።
¹⁶ እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።
¹⁷ ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥
¹⁸ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች።
¹⁹ ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥
²⁰ ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን፥ የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ እርሱም፦ ፍጠን ከኢየሩሳሌምም ቶሎ ውጣ፥ ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉህምና ሲለኝ አየሁት።
¹⁹ እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ በአንተ የሚያምኑትን በምኵራብ ሁሉ እኔ በወኅኒ አገባና እደበድብ እንደ ነበርሁ እነርሱ ያውቃሉ፤
²⁰ የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ።
²¹ እርሱም፦ ሂድ፥ እኔ ወደ አሕዛብ ከዚህ ወደ ሩቅ እልክሃለሁና አለኝ። ወይም👇

ሐዋርያት 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ሄሮድስም ሊያወጣው ባሰበ ጊዜ፥ በዚያች ሌሊት ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለት ታስሮ ከሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ሆነው ወኅኒውን ይጠብቁ ነበር።
⁷ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና፦ ፈጥነህ ተነሣ አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ።
⁸ መልአኩም፦ ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ።
⁹ ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም።
¹⁰ የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም አንዲት ስላች አለፉ ወዲያውም መልአኩ ከእርሱ ተለየ።
¹¹ ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ፦ ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_24_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ባርክዎ ለእግዚአብሔር ኵልክሙ መላእክቲሁ። ጽኑዓን ወኃያላን እለ ትገብሩ ቃሎ። ወእለ ትሰምዑ ቃለ ነገሩ"። መዝ 102፥20።
“ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኃያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ።” መዝ 102፥20።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_24_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁶ በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፦ የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት።
³⁷ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤
³⁸ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤
³⁹ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።
⁴⁰ እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።
⁴¹ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥
⁴² ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
⁴³ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ሠለስቱ_ምዕት ወይም የ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ_ቅዳሴ ነው። መልካም የሃያ አራቱ #ካህናተ_ሰማይ፣ የ #አቡነ_ተክለሃይማኖት በዓል፤ የ #አቡነ_ዜና_ማርቆስ የልደት በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

ኅዳር 24 የ #ሥላሴን መንበር የሚያጥኑ የ24ቱ ካህናተ ሰማይ(ቅዱሳን ሱራፌል) ዓመታዊ በዓልና የመላእክቱ ስማቸው

1 ,ቅዱስ አካኤል
2 ,ቅዱስ ፋኑኤል
3 ,ቅዱስ ጋኑኤል
4 ,ቅዱስ ታድኤል
5 ,ቅዱስ እፍድኤል
6 ,ቅዱስ ዘራኤል
7 ,ቅዱስ ኤልኤል
8 ,ቅዱስ ተዳኤል
9 ,ቅዱስ ዮካኤል
10,ቅዱስ ገርድኤል
11,ቅዱስ ልፍድኤል
12 ,ቅዱስ መርጥኤል
13,ቅዱስ ኑራኤል
14,ቅዱስ ክስልቱኤል
15,ቅዱስ ኡራኤል
16,ቅዱስ ባቱኤል
17,ቅዱስ ሩአኤል
18,ቅዱስ ሰላትኤል
19,ቅዱስ ጣርኤል
20,ቅዱስ እምኑኤል
21,ቅዱስ ፔላልኤል
22 ,ቅዱስ ታልዲኤል
23 ,ቅዱስ ስልዱኤል
24 ,ቅዱስ አሌቲኤል➛ለሚባሉ ስሞቻቸው ሰላምታ ይገባል።

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

፨በእጆቻቸው ውስጥ ላለ ማዕጠንትም ሰላምታ ይገባል

ሙድ፣ሙጦስ፣ሙት፣ከትና፣ሊአን፣ኪና፣አራጽ፣አንዮስ፣አንስ1፣ስርዲ፣ካሊን፣ኡስሬን፣ማሪአክ፣ዋሮክ፣ወሪአክ፣አጽማኤል፣አናአል፣ቶራን፣አርኒ፣ማሪክ፣ላንስካ፣ስና፣አሚዮስ፣ዳዉሪ

፨በራሶቻቸው ላይ ላሉ አክሊላትም ሰላምታ ይገባል

አርኒኤል፣ዊተር፣ ና፣ ኡማስ፣ ቲራን፣ አርናስ፣ ዘሪክ፣እብጣ ፣ ትርሞን፣ያኒስኮ፣ ሚስንኪስ፣ ማቲርናሳኪብ፣ አክሳኑ፣ ኒዮስ፣ ኡናር፣ በርኪያስ፣ራስቴዎን፣ዳኪያስ፣አርንያስ ፣ ፈራስ፣ ኪናስ፣አብጻሎን፣አንስኮ ።

❖ ልዑል #እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ ሊቁ በአክሲማሮስ እንደገለጸው ከቅዱሳን መላእክት መኻከል

“ወእምዝ ነሥአ #እግዚአብሔር እምሰራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ፤ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን #መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት” ይላል።

ከሰራዊተ ሩፋኤል 24ት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል

ሕዝ 1፥11-12

❖ ቊጥራቸውን ኻያ አራት ማድረጉ በኻያ አራቱ ጊዜያት ጸልየው ሌላውንም ራሳቸውንም ጠብቀው ዋጋቸውን ተቀብለው የሚኖሩ በመኾናቸው ሲኾን እነዚኽንም መላእክት “ካህናተ ሰማይ” ሲላቸው የእሳት የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ ደፍቶላቸዋል፤ የብርሃን ዘንግ ማኅተሙ #መስቀል የኾነ ሲያሲዛቸው የብርሃን ካባ ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋው፤ ቁጥራቸው 24 መኾኑም በ24ቱ ሰዓት ጸልየው አመስግነው በጸሎታቸው ሌላውን ጠብቀው የሚኖሩ ናቸውና ነው፨

ዮሐንስም በራእዩ ላይ “በዙፋኑ ዙሪያም ኻያ አራት ዙፋኖች ነበሩ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ኻያ አራት ሊቃናት ተቀምጠው ነበር … ኻያ አራቱ ሊቃናት በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ #ጌታችንና_አምላካችን ሆይ አንተ ኹሉን ፈጥረኻልና ስለ ፈቃድኽም ኾነዋልና ተፈጥረውማልና ክብርን ውዳሴንና ኀይልንም ልትቀበል ይገባኻል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ” በማለት ገልጾታል፡፡

ራእ 4፥4-5፤

ራእ 4፥10-11

❖ እነዚኽ ሰማያውያን ካህናት በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ ዛሬ በክረምት ጊዜ ጉም ተራራውን እንደሚሸፍነው ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፣ ድምፁ ነጐድጓድ፣ መዐዛው መልካም የኾነና ጽርሐ አርያም፣ መንበረ መንግሥት የተባሉትን የብርሃን ሰማያት የሚሸፍንና የሚጋርድና ከጢሱ ጋር የቅዱሳን ጸሎት ዐብሮ ወደ #እግዚአብሔር ፊት ይወጣል።

“ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በ #እግዚአብሔር ፊት ወጣ” እንዳለ ዮሐንስ በራእዩ ራእ 8፥3-5

❖ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ “ወቦ ኪሩቤል ይቀውሙ በየማን በአምሳለ ቀሳውስት ወሱራፌል ይቀውሙ በአምሳለ ዲያቆናት ወድኅሬሆሙ ካህናተ ሰማይ ወቦ እልፍ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት መብረቅ ወነጐድጓድ ወሠረገላሆሙኒ ምሉኣነ አዕይንት” እንዳለ ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ከፍ ብለው ካህናተ ሰማይ ክንፍ ለክንፍ ገጥመው በስተኋላቸው ሲታዩ በሰማይ ውዱድ ዙሪያ እልፍ አእላፋት መብረቅ፣ ነጐድጓድ፣ ሠረገላ፣ እንደ መስታየት ብሩህ የኾነ ሲኖርበት እነዚኽ ቅዱሳን መላእክትም ሳያቋርጡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ #እግዚአብሔር” እያሉ ፈጣሪያቸውን በአንድነቱ በሦስትነቱ ያመሰግኑታል

ራእ 4፥8

❖ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በኆኅተ ብርሃን መጽሐፉ ላይ

“ወይምጽኡ ካህናት ሰማያውያን፣ ልቡሳነ ብርሃን ወጸወርተ ዕጣን፣ እለ ያቈርቡ ቅድመ ምሥዋዒከ ጸሎተ ቅዱሳን፣ እለ ይቀውሙ ዐሠርቱ ወክልኤተ እምይምን ወዐሠርቱ ወክልኤቱ እምፅግም፣ ወፍያላተ ያቄርቡ ለስብሐተ መለኮትከ፤ ዕሥራ ወአርባዕቱ ኊልቆሙ ዕሥራ ወአርባዕቱ መናብርቲሆሙ፣ ዕሥራ ወአርባዕቱ አክሊላቲሆሙ፣ ዕሥራ ወአርባዕቱ ማዕጠንታቲሆሙ”

ብርሃንን የለበሱ ዕጣንንም የተሸከሙ የቅዱሳንን ጸሎት ወደ መሠዊያኽ ፊት የሚያቀርቡ ዐሥራ ኹለቱ ከቀኝ ዐሥራ ኹለቱ ከግራ የሚቆሙ ለጌትነትኽም ምስጋና ጽዋዎችን የሚያቀርቡ ሰማያውያን ካህናት ይምጡ፤ ቊጥራቸው ኻያ አራት ነው ወንበሮቻቸውም ኻያ አራት ናቸው፣ አክሊሎቻቸውም ኻያ አራት ናቸው፤ ማዕጠንቶቻቸውም ኻያ አራት ናቸው በማለት ስለ ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ አስተምሯል፡፡

❖ ይኸው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፋቸው ላይ ስማቸውን ጭምር በመጥቀስ ለኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ሰላምታ ሲያቀርብ

"ሰላም ለ፳ወ፬ቱ ካህናት ሰማያውያን እለ ዐውደ መንበሩ ለአብ፡፡ ወሰላም ለማዕጠንት ዘውስተ እደዊሆሙ ወሰላም ለአክሊላት ዘዲበ አርዕስቲሆሙ፤ ወሰላም ለአስማቲሆሙ፤ አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል፣ ታድኤል፣ እፍድኤል፣ ዘራኤል፣ ኤልኤል፣ ተዳኤል፣ ዮካኤል፣ ገርድኤል፣ ልፍድኤል፣ መርዋኤል፣ ኑራኤል፣ ክስልቱኤል፣ ኡራኤል፣ ባቱኤል፣ ሩአኤል፣ ሰላትኤል፣ ጣውርኤል፣ እምኑኤል፣ ፔላልኤል፣ ታልዲኤል፣ ፐስልዱኤል፣ አሌቲኤል”፡፡

#አብ መንበር ዙሪያ ላሉ ለ24ቱ ሰማያውያን ካህናት ሰላምታ ይገባል፤ በእጆቻቸው ውስጥ ላለ ማዕጠንትም ሰላምታ ይገባል፤ በራሶቻቸው ላይ ላሉ አክሊላትም ሰላምታ ይገባል፤ አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል፣ ታድኤል፣ እፍድኤል፣ ዘራኤል፣ ኤልኤል፣ ተዳኤል፣ ዮካኤል፣ ገርድኤል፣ ልፍድኤል፣ መርዋኤል፣ ኑራኤል፣ ክስልቱኤል፣ ኡራኤል፣ ባቱኤል፣ ሩአኤል፣ ሰላትኤል፣ ጣውርኤል፣ እምኑኤል፣ ፔላልኤል፣ ታልዲኤል፣ ፐስልዱኤል፣ አሌቲኤል ለተባሉ ስሞቻቸውም ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሷቸዋል።

የልዑል #እግዚአብሔርን ዙፋን የሚያጥኑ ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ በማዕጠንታቸው ጸሎታችንን ወደ ጸባኦት ዙፋን ያድርሱልን፤ በጸሎታቸው ሀገራችን ሰላም ፍቅር ያድርጉልን።

ምንጭ መፅሀፈ አክሲማሮስ......
#ኅዳር_25

#ቅዱስ_መርቆሬዎስ_ሰማዕት (ፒሉፓዴር)

አንድ አምላክ በሆነ በ #አብ#ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም
ኅዳር ሃያ አምስት በዚች ቀን የስሙ ትርጓሜ መርቆሬዎስ የሆነ ፒሉፓዴር በሰማዕትነት አረፈ። መርቆሬዎስም ማለት የ #አብ ወዳጅ ማለት ነው በሁለተኛ ትርጓሜ የ #ኢየሱስ_ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው።

ይህም ቅዱስ አስሊጥ ከምትባል አገር ነው እርሷም የአባቱና የአያቱ አገር ናት እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው። የአባቱና የአያቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ነበር በአንዲት ዕለትም እንደልማዳቸው ለማደን ወጡ ከገጸ ከለባት ወገንም ሁለት ወንዶች ተገናኙአቸውና የቅዱስ መርቆሬዎስን አያት በሉት። ሁለተኛም አባቱን ሊበሉት ፈለጉ ከ #እግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም ከለከላቸው፤ ከእርሱ የሚወጣ መልካም ፍሬ ስለአለ አትንኩት አላቸው።

ከዚህም በኋላ የ #እግዚአብሔር መልአክ ዙሪያቸውን በእሳት ከበባቸው። በተቸገሩ ጊዜም ወደ ቅዱስ መርቆሬዎስ አባት መጥተው ሰገዱለት። በዚያንም ጊዜ #እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደ በጎች የዋሆች ሆኑ። አብረውትም ወደ መንደር ገቡ።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ በተወለደ ጊዜ ስሙን ፒሉፓዴር ብለው ጠሩት። የውሻ መልክ ያላቸውም በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት የሚኖሩ ሆኑ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ። የቅዱስ መርቆሬዎስ ወላጆች አስቀድሞ አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትንም ጸጋ በተቀበሉ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ኖኅ ብለው ሰየሙት። እናቱንም ታቦት አሏት። ፒሉፓዴርንም መርቆሬዎስ ብለው ሰየሙት።

የውሻ መልክ ያላቸው ግን የ #እግዚአብሔር መልአክ በተገለጸላቸው ጊዜ እንደ ነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ። ንጉሡም የኖኅንና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜና በሰማ ጊዜ ወደርሱ አስቀረባቸው በዚያንም ጊዜ #እግዚአብሔር በንጉሡ ፊት የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው ንጉሡ ያቀረባቸውን ሁሉንም አራዊት አጠፏቸው።

ንጉሡም ይህን በአየ ጊዜ እጅግ ፈራ፤ የአራዊትንም ተፈጥሮአቸውን ያርቅ ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር እንዲማልድ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ለመነው። እርሱም በለመነ ጊዜ ክብር ይግባውና #ጌታችን ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ።

ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ንጉሡ ወስዶ ገዥና የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው። የውሻ አርአያ ያላቸውም ይታዘዙለት ነበር። ከእርሳቸውም የተነሣ ሁሉም ይፈሩ ነበር።

ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የሾመውን ንጉሥ ይወጋ ዘንድ ከሀዲ ንጉሥ ተነሣ። ንጉሡም ከጦር ሠራዊት ጋር የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ላከው። ከሀዲው ንጉሥ ግን እነዚያን የውሻ አርአያ ያላቸውን አባብለውና ሸንግለው ወደርሱ ያመጧቸው ዘንድ ወታደሮችን ላከ። በአመጧቸውም ጊዜ ሃይማኖታቸውን ይለውጡ ዘንድ አብዝቶ ሸነገላቸው፤ ባልሰሙትም ጊዜ ሊአሠቃያቸው ጀመረ አንዱ አምልጦ ሸሽቶ ወደ ጌታው ሔደ። ሁለተኛውም በሰማዕትነት ሞተ።

ከጦር ሜዳ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት በተመለሰ ጊዜ ሚስቱንና ልጁን ፈለጋቸው ግን አላገኛቸውም። ንጉሡ የሱ ወገኖች ድል እንደሆኑ በሰማ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት መኰንኑ የሞተ መስሎት ነበርና የቅዱስ መርቆሬዎስን እናት ወስዶ ሊአገባት ፈለገ። ከንጉሥ ወታደሮችም አንዱ ንጉሡ ያሰበውን በጽሙና ነገራት። እርሷም ይህንኑ ወታደር ከሀገር ውስጥ በሥውር ያወጣት ዘንድ ለመነችውና ከልጇ ከብፁዕ መርቆሬዎስ ጋር ወጥታ ወደ ሌላ አገር ሔደች።

ንጉሡም ከእርሱ የሆነውን የመኰንኑም የመርቆሬዎስን አባት ሚስቱን ለማግባት ማሰቡን እንዳይነግሩት አዘዘ። የውሻ መልኮች ያላቸው ከእርሱ ጋር እንዳሉ የተቆጣም እንደሆነ እንደሚአመጣቸውና አገሮችን ያጠፋሉ ብሎ ይጠራጠራልና ስለዚህ እጅግ ይፈራዋል።

ከዚህም በኋላ ደግሞ በንጉሡ ላይ ጦርነት ተነሣ። የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት ወደ ጦርነቱ ወጣ በ #እግዚአብሔርም ፈቃድ ይዘው ማረኩት። ወደ ሮሜውም ንጉሥ አቀረቡት ንጉሡም ክርስቲያን ነበርና የተማረከው መኰንን ክርስቲያን መሆኑን በአወቀ ጊዜ አልገደለውም። በክብር አኖረው እንጂ እጅግም ወደደውና ከጥቂት ቀኖች በኋላ በመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ላይ ገዥ አድርጎ ሾመው።

ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ፈቃድ ሚስቱና ልጁ መርቆሬዎስ ወዳሉበት አገር ደረሰ። ሚስቱም በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ በአየችው ጊዜ ባሏ አንደሆነ አወቀችው። እርሱ ግን አላወቃትም።

በአንዲትም ዕለት እርሱና ጭፍሮቹ ከእንግዳ ማረፊያ ቤት በወጡ ጊዜ ልጅዋን ቅዱስ መርቆሬዎስን ወስዳ ያማሩ ልብሶችን አልብሳ ሒዶ ከመኰንኑ ፈረስ ላይ እንዲቀመጥ አዘዘችው። እርሱም አባቱ ነው። በተቀመጠ ጊዜም ጭፍሮች ይዘው ወደ መኰንኑ ፊት አቀረቡት መኰንኑም ልጁ እንደሆነ አላወቀምና በእርሱ ላይ ተቆጣ።

የመርቆሬዎስም እናት መጥታ ጌታዬ ሆይ እኛ መጻተኞች ነን አንተም መጻተኛ እንደሆንክ በአወቅሁ ጊዜ ልጅህ ሁኖ ልጄ ከአንተ ጋር እንዲሆን አሰብኩ አለችው። እርሱም ጠየቃት እንዴት እንደተሰደደችም መረመራት እርሷም ሚስቱ እንደሆነች ነገረችው በዚያንም ጊዜ አወቃት ልጁን መርቆሬዎስንም አወቀው እጅግም ደስ ብሏቸው #እግዚአብሔርን አመሰገኑት ያንንም የእንግዳ ማረፊያ ቤት ቤተ ክርስቲያን አደረጉት #እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በአንድነት ኖሩ።

ከዚህም በኋላ አባቱና እናቱ በሞቱ ጊዜ ንጉሡ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወስዶ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው። ቅዱስ መርቆሬዎስም መኰንንነትን በተሾመ ጊዜ ያ ገጸ ከልብ ከርሱ ጋር ነበር ወደ ጦርነትም አብሮት የሚወጣ ሆነ።

ለመዋጋትም በሚሻ ጊዜ የቀድሞ የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን #እግዚአብሔር ይመልስለት ነበር ማንም ሊቋቋመው የሚችል የለም። ለቅዱስ መርቆሬዎስም ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠው ዜናውም በሁሉ ቦታ ተሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችም ከፍ ከፍ አለ።

እንዲህም ሆነ ያን ጊዜ በዚያን ወራት በሮሜ አገር ጣዖትን የሚያመልክ ዳኬዎስ የሚባል ንጉሥ አለ። ጠላቶቹም የበርበር ሰዎች ተነሡበት። እርሱም ከእርሳቸው ጋር ሊዋጋ ሠራዊቱን ሰብስቦ ወጣ። እነርሱ ግን እንደ ባሕር አሸዋ ብዙ ነበሩ ብዛታቸውንም በአየ ጊዜ ደንግጦ እጅግ ፈራ። ቅዱስ መርቆሬዎስም #እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ በእጃችንም አሳልፎ ሊሰጣቸው አለውና አትፍራ አለው።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ የ #እግዚአብሔርን መልአክ በውጊያው ውስጥ አየው የተሳለ ሰይፍም በእጁ ውስጥ አለ ያቺንም ሰይፍ ሰጠውና እንዲህ አለው ጠላቶችህን ድል በአደረግህ ጊዜ ፈጣሪህ #እግዚአብሔርን አስበው።

ጠላቶቹንም ድል አድርጎ በሰላም ተመለሰ መልአኩም ዳግመኛ ተገልጦለት ለምን የፈጣሪህን የ #እግዚአብሔርን ስም መጥራት ረሳህ አለው።

ጦርነቱም ከተፈጸመ በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን ሊያደርግ ወደደ። ቅዱስ መርቆሬዎስም ለበዓል ማክበር አብሮት አልወጣም ወደ ቤቱ ሔደ እንጂ። ሰዎችም ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳልመጣና ዕጣንን በማሳረግም እንዳልተባበረ አስረዱት።

በዚያንም ጊዜ ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወደርሱ አስመጣው። በመዘግየቱም አድንቆ ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልመጣህ የእኔን ፍቅር እንዴት ተውህ አለው። በዚያንም ጊዜ ትጥቁንና ልብሱን ወረወረለትና ንጉሡን እንዲህ አለው። እኔ ክብር ይግባውና #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም።
ንጉሥ ዳኬዎስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ። እርጥብ በሆኑ የሽመል በትሮች እንዲደበድቡት አዘዘ። ሁለተኛም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ይገርፉት ዘንድ አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘ ይህን ሁሉ አደረጉበት።

በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳይነሡበት ፈርቶ የቀጰዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ሆነች ወደ ቂሣርያ በብረት ማሠሪያ አሥሮ ላከው። በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ ከአሠቃዩትም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ተጋድሎውን ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት የሕይወት አክሊልን ተቀበለ።

የማይጠፋ ሰማያዊ አክሊልንም ተቀዳጅቶ ወደ ዘላለም ሕይወት ከገባ በኋላ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስተያናት ታነፁለት። #እግዚአብሔርም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራትን በውስጣቸው ገለጠ።

#ተአምር_ዘቅዱስ_መርቆሬዎስ - ፩

ከተአምራቱም አንዲቱ ዑልያኖስ በነገሠ ጊዜ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ካደ። በዚያንም ወራት ቅዱስ ባስልዮስ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ነበረ ተአምራቱ በተጻፉበት መጽሐፍ እንደተጻፈ ምእመናን በጽኑዕ ሥቃይ ዑልያኖስ ባሠቃየ ጊዜ መክሮ አስተምሮ ከስሕተቱ ይመልሰው ዘንድ ቅዱስ ባስልዮስ ወደርሱ መጣ።

ዑልያኖስም ቅዱስ ባስልዮስን በአየው ጊዜ ክብር ይግባውና #ጌታችንን ሰደበ። ቅዱስ ባስልዮስንም አሠረው። በዚያ በእሥር ቤትም የቅዱስ መርቆሬዎስን ሥዕል አይቶ በፊቱ ቅዱስ ባስልዮስ ጸለየ ሥዕሉም ከቦታው ታጣ። ያን ጊዜ ወደ ዑልያኖስ ሒዷልና በጦርም ወግቶ ገደለውና ወዲያውኑ ወደቦታው ተመለሰ ከጦሩም አንደበት ደም ይንጠፈጠፍ ነበር። ቅዱስ ባስልዮስም ከሀዲ ዑልያኖስን እንደገደለው አውቆ እንዲህ ብሎ ተናገረ የ #ክርስቶስ ምስክር ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ሥዕሉ ራሱን ዘንበል አደረገ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት #እግዚአብሔርን አመሰገነ።

#ተአምር_ዘቅዱስ_መርቆሬዎስ - ፪

የዚህም የቅዱስ መርቆሬዎስ ሌላው ተአምር ከምስር አገር ከመሳፍንት ወገን የሆነ አንድ የእስላም ወጣት ነበረ የእስላሞችንም ሕጋቸውንና መጻሕፍቶቻቸውን ተምሮአል። በአንዲትም ዕለት ወደ ባሕር ዳርቻ በመንገድ አልፎ ሲሔድ አንድ የተፈረደበትን ሰው አገኘ። አስቀድሞ እስላም የነበረ አሁን የክርስትና ጥምቀትን የተጠመቀ የንጉሥ ጭፍሮችም ይዘውታል። ሊአቃጥሉትም ጉድጓድን ምሰው በውስጡ ታላቅ እሳት አንድደው አዘጋጅተውለታል። ብዙዎች ሰዎችም ሲቃጠል ለማየት ተሰብስበው ነበር።

ያም የመስፍን ልጅ ወጣት እስላም ወደ ተፈረደበት ሰው ቀረብ ብሎ "አንተ ከሀዲ ሰው ወደ ሲኦል ለመግባት ለምን ትሮጣለህ በኋላም በገሀነም እሳት ውስጥ ለመኖር አንተ #እግዚአብሔርን ባለ ልጅ ታደርገዋለህና ሦስት አማልክትንም የምታምን ነህና ክፉ ነገር ነውና ይህን ስድብ ትተህ እኔን ስማኝ" አለው ።

ያ የተፈረደበትም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኛ የክርስቲያን ወገኖች ሦስት አማልክትን የምናመልክ ከሀድያን አይደለንም። አንድ አምላክን እናመልካለን እንጂ ይኸውም #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ ነው። #ወልድ ከአባቱ ከ #እግዚአብሔር ልዩ አይደለም። የራሱ ቃሉ ነው እንጂ። #መንፈስ_ቅዱስም ሕይወቱ ነው። የሃይማኖታችን ምሥጢር ከአናንተ የተሠወረ ድንቅ ነው። ዛሬ ለአንተ ልብህ ጨለማ ነው በውስጡ የሃይማኖት ብርሃን አልበራም በኋላ ግን ልብህ በርቶልህ እንደ እኔ ስለ #ክርስቶስ ስም በመጋደል መከራውን ትቀበላለህ።"

ያም ወጣት እስላም በሰማው ጊዜ እጅግ ተቆጣ ጫማውንም ከእግሮቹ አውልቆ አፉን ፊቱንና ራሱን ጸፋው። ይህ የምትለው ከእኔ ዘንድ አይደረግም እያለ አብዝቶ አሠቃየው። የተከበረው ሰማዕትም ይህን ያልኩህን አስበህ የምትጸጸትበት ጊዜ አለህ አለው።

በዚያንም ጊዜ ራሱን በሰይፍ ቆርጠው ሥጋውን ከእሳት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩ ከዚህም በኋላ እሳቱ ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ታላቅ አጥር ሆነ። የንጉሥም ወታደሮች እየጠበቁት ሦስት ቀን ኖረ። ከዚህም በኋላ ከቶ እሳት ምንም ሳይነካው እንደ ተፈተነ ወርቅ ሆኖ ሥጋውን አገኙት። ይህንንም ለንጉሥ ነገሩት። እርሱም እንዲቀብሩት አዘዘ።

ያ ወጣት እስላም ግን እያዘነ ወደ ቤቱ ገባ እርሱ ክርስቲያን እንደሚሆን ስለተናገረው ከኀዘኑ ብዛት የተነሣ የማይበላና የማይጠጣ ሆነ። እናቱና ወንድሞቹም ወደርሱ ተሰብስበው የማትበላ የማትጠጣ በአንተ ላይ የደረሰ ምንድን ነው አሉት። ክብር ይግባውና ለ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ምስክር የሆነው የተናገረውን ነገራቸው። እነርሱም ይህ አሳች የተናገረውን ተወው በልብህ አታስበው እያሉ አጽናኑት። እርሱ ግን ከቶ ምንም አልተጽናናም።

በዚያም ወራት ወደሐሰተኛ ነቢያቸው መቃብር ለመሔድ የሚሹ ሰዎችን አይቶ ከእሳቸው ጋር መሔድ እፈልጋለሁ ብሎ ለአባቱ ነገረው። አባቱም እጅግ ደስ ብሎት የሚበቃውን ያህል የወርቅ ዲናር ሰጠው ለወዳጁም አደራ ብሎ ሰጠውና አብሮት ሔደ።

በሌሊትም ሲጓዙ እነሆ ብርሃን የለበሰ አረጋዊ መነኰስ ተገለጸለት በፊቱም ቁሞ ትድን ዘንድ ና ተከተለኝ አለው እንዲሁም ሁለተኛና ሦስተኛ ተገልጦ ተናገረው።

በደረሱም ጊዜ ሥራቸውን ፈጽመው ወደ አገራቸው ተመለሱ ሰባት ቀንም ያህል ተጓዙ። እነርሱም በሌሊት ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጅ ያ ወጣት ከገመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ። ባልንጀሮቹም በበረሀ ውስጥ ትተውት ሔዱ ከእሳቸው ጋር የሚጓዝ መስሏቸዋልና በተነሣም ጊዜ ተቅበዘበዘ ወዴት እንደሚሔድ አላወቀምና አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ ደነገጠ።

በዘያንም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕት የቅዱሰ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ እንዲህ አለ። ሰዎች ሁሉ በእርሷ ዘንድ እየተሳሉ ይፈጸምላቸዋል። በዚያንም ጊዜ የ #ክርስቶስ ምስክር መርቆሬዎስ ሆይ በዚህ በረሀ ካሉ አራዊት አፍ በዛሬዋ ሌሊት ካዳንከኝና ያለ ጥፋት ካወጣኸኝ እኔ ክርስቲያን እሆናለሁ ብሎ ተሳለ።

ወዲያውኑ መልኩ የሚያምር ጎልማሳ የከበረ ልብስ የለበሰና የወርቅ መታጠቂያ በወገቡ የታጠቀ በፈረስ ተቀምጦ ወደርሱ መጣና አንተ ከወዴት ነህ እንዴት በዚህ በረሀ ውስጥ ጠፋህ አለው። ወጣቱም ስለ ሥጋ ግዳጅ ከገመል ላይ ወረድኩ ባልነጀሮቼ ትተውኝ ሔዱ አለው ባለ ፈረሱም ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ አለው በዚያንም ጊዜ ወደ አየር በረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች ከውስጧ አስገባው። ከፈረሱም ላይ አውርዶ በዚያ አቆመው ወደ መጋረጃ ውስጥም ገብቶ ከእርሱ ተሠወረ።

የቤተ ክርስቲያኑም መጋቤ በሌሊት በመጣ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከፍቶ ሲገባ ይህን ወጣት ከመካከል ቁሞ አገኘው። ደንግጦ ሊጮህ ፈለገ ጠቀሰውና ወደኔ ዝም ብለህ ና አለው ወደርሱም ሲቀርብ ይቺ ቦታ የማናት አለው የቤተ ክርስቲያኒቱ መጋቢም ይቺ በምስር አገር ያለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ናት። አንተን ግን ልቡ እንደ ጠፋ ሰው ስትናገር አይሃለሁ ከዚህ ምን አመጣህ አሁንም ንገረኝ አለው። ወጣቱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ልቤ እንዴት አይጠፋ እኔ በዛሬው ሌሊት በእገሌ በረሀ ሳለሁ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ሰው ተገለጠልኝና ከኋላው በፈረሱ አፈናጠጠኝ ከዚህም አድርሶ ተወኝ አለው።
መጋቢውም የዚያችን በረሀ ስም በሰማ ጊዜ አደነቀ እንዲህም አለው ልብህ ጠፍቷል በማለቴ መልካም የተናገርኩህ አይደለምን የምትናገረውን አታውቅምና የዚያ በረሀ መጠኑ የሃያ ሁለት ቀን ጉዞ የሚያስጉዝ ስለ ሆነ በእርግጥ አንተ ወንበዴ ነህ የቅዱስ ሰማዕት መርቆሬዎስ ኃይል ያለ ገመድ አሥሮሃል፣ እርሱ የዚህን ዓለም ክብር ንቆ የተወ፣ ክብር ይግባውና ስለ #ክርስቶስ ስም ከሀዲዎች ጽኑ ሥቃይ አሠቃይተው የገደሉት፣ #ክርስቶስም በመንግሥቱ ውስጥ የተቀበለው፣ በቦታዎችም ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነፁለት በውስጣቸውም #እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል። እርሱ መርቆሬዎስ ለተማፀነበት ሁሉ ይማልዳልና ድንቆች የሆኑ ታላላቅ ተአምራትንም ያደርጋልና።

ያም ወጣት መጋቢውን መልኩ እንዴት ነው ምን ይመስላል አለው መጋቢውም አካሉ አንተን ይመስላል አለው ይህንንም ብሎ ወደ ሥዕሉ ወስዶ ገልጦ አሳየው ወጣቱም በእገሌ በረሀ የታየኝ በእውነት ይህ ነው። በፈረሱም ላይ አፈናጥጦ ወደዚህ ያደረሰኝ ይህ ነው። እነሆ ታጥቋት በወገቡ ላይ ያየኋት የወርቅ መታጠቂያው ይቺ ናት። ስማኝ ልንገርህ እኔ በዚች አገር የምኖር አባቴም ስሙ ረጋ የሚባል መስፍን የሆነ እስላም የሆንኩ ሰው ነኝ። ክርስቲያንም ለመሆን ይች ምልክት ትበቃኛለች አሁንም በቦታ ውስጥ ሠውረኝ ለማንም ሥራዬን አትግለጥ። የክርስትና ትምህርትን አስተምሮ የ #እግዚአብሔርን መንገድ የሚመራኝን አምጣልኝ አለው። እርሱም ያለውን ሁሉ አደረገለት የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው።

ከዚህም በኋላ ወደ ነቢያቸው መቃብር የሔዱ እሊያ እስላሞች በአንድ ወራቸው ደረሱ። ዘመዶቻቸውም ሊቀበሏቸው ወጡ። ይህን ወጣት የመስፍን ልጅ ግን አላገኙትም። አባቱም አደራ ያስጠበቀውን ወዳጁን በጠየቀው ጊዜ እርሱም በበረሀ ውስጥ ቀርቶ እንደ ጠፋ እያለቀሰ ነገረው አባቱም በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀዶ አለቀሰ እንዲሁም ቤተሰቦቹ ሁሉም አርባ ቀኖች ያህል አለቀሱለት።

ከዚህም በኋላ በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ሲወጣ ይህን ክርስቲያን የሆነውን ወጣት አንድ እስላም አየው። ወደ ወላጆቹም ሒዶ እንዲህ ብሎ ነገራቸው ልጃችሁ በበረሀ ውስጥ የሞተ ከሆነ በመርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ደጅ ያየሁት እርሱን ባልመሰለኝ ነበር፤ እስቲ ሒዳችሁ አረጋግጡ። በሰሙም ጊዜ በስውር ሒደው ፈለጉት አግኝተውትም ይዘው ወሰዱት። እንዲህም አሉት በወገኖቻችን መካከል ልታሳፍረን ይህ የሠራኸው ምንድን ነው አሉት። እርሱም እኔ በሕያው #እግዚአብሔር ልጅ በ #ጌታዬና_በፈጣሪዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ ብሎ መለሰላቸው።

ይህንንም ሲል ታላቅ ሥቃይን አሠቃይተው ከጨለመ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት። ሽንታቸውን በላዩ እየደፉ የቤት ጥራጊም እያፈሰሱበት ያለ መብልና ያለ መጠጥ በዚያ ሰባት ቀንና ሌሊት ኖረ። እናቱ ግን ቀንም ሌሊትም በላዩ የምታለቅስ ሆነች ከልቅሶዋም ብዛት የተነሣ ከጉድጓድ አውጥተው እኛ ወደማናይህ ቦታ ሒድ አሉት። ወዲያውኑ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በዚያ እያገለገለና እየተጋደለ ሁለት ዓመት ኖረ።

ከዚህም በኋላ በላዩ የትንቢት ጸጋ ያደረበት አንድ መነኰስ ወደ ምስር ከተማ ሒደህ ሃይማኖትህን ከምትገልጽ በቀር በዚህ መኖር ለአንተ አይጠቅምህም አለው። ወዲያውኑ ተነሥቶ ወደ ምስር ከተማ ሔደ።

አባቱም በአየው ጊዜ ሐኪም ወደ ሚባል ንጉሥ ወስዶ ይህ ልጃችን ነበር የእስልምና ሃይማኖትን ትቶ ወደ ክርስቲያን ሃይማኖት ገብቷል አለው። ንጉሡም ስለአንተ የሚናገሩት ዕውነት ነውን አለው። እርሱም በበረሀ ውስጥ ሳለ በሌሊት ቅዱስ መርቆሬዎስ እንደ ተገለጸለትና ከእርሱ ጋር በፈረስ እንዳስቀመጠው፣ በምስር አገር ወዳለች ቤተ ክርስቲያኑ የሃያ ሁለት ቀን መንገድ እንደ ዐይን ጥቅሻ አድርሶ ከውስጥዋ እንዳስገባው፣ ሥዕሉንም አይቶ ያመጣው እርሱ መሆኑን እንደ ተረዳ ለንጉሡ ነገረው።

ንጉሡም በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ። ታላቅ ፍርሀትም አደረበት አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምነኝ አለው። እርሱም በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ዳግመኛም በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን እንድሠራ ታዝልኝ ዘንድ እሻለሁ አለው።

ንጉሡም በአስቸኳይ እንዲታነፁለት አዘዘለት። በውስጣቸውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። እርሱም አበ ምኔት ሁኖ ወደርሱ ብዙዎች መነኰሳት ተሰበሰቡ። ሁለት ድርሳናትንም ደረሰ። ከሀዲያንንም አስተምሮ ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው #እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ ። ለዚህም መነኰስ የክርስትና ጥምቀትን በተቀበለ ጊዜ ያወጡለት ስም ዮሐንስ ነው።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ መርቆሬዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_25)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_25_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ቆሮ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ስለ እናንተ እምነቴ ታላቅ ነው፥ በእናንተ ምክንያት ትምክህቴ ታላቅ ነው፤ መጽናናት ሞልቶብኛል፤ በመከራችን ሁሉ ደስታዬ ከመጠን ይልቅ ይበዛል።
⁵ ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሥጋችን ዕረፍት አልነበረውም፤ በውጭ ጠብ ነበረ፥ በውስጥ ፍርሃት ነበረ።
⁶ ነገር ግን ኀዘንተኞችን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን፤
⁷ በመምጣቱም ብቻ አይደለም ነገር ግን ናፍቆታችሁንና ልቅሶአችሁን ስለ እኔም ቅንዓታችሁን ሲናገረን በእናንተ ላይ በተጽናናበት መጽናናት ደግሞ ነው፤ ስለዚህም ከፊት ይልቅ ደስ አለን።
⁸ በመልእክቴ ያሳዘንኋችሁ ብሆን እንኳ አልጸጸትም፤ የተጸጸትሁ ብሆን እንኳ፥ ያ መልእክት ጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳሳዘናችሁ አያለሁና አሁን ለንስሐ ስላዘናችሁ ደስ ብሎኛል እንጂ ስላዘናችሁ አይደለም፤
⁹ በምንም ከእኛ የተነሣ እንዳትጎዱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አዝናችኋልና።
¹⁰ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።
¹¹ እነሆ፥ ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን እንዴት ያለ ትጋት፥ እንዴት ያለ መልስ፥ እንዴት ያለ ቁጣ፥ እንዴት ያለ ፍርሃት፥ እንዴት ያለ ናፍቆት፥ እንዴት ያለ ቅንዓት፥ እንዴት ያለ በቀል በመካከላችሁ አደረገ። በዚህ ነገር ንጹሐን እንደ ሆናችሁ በሁሉ አስረድታችኋል።
¹² እንግዲያስ የጻፍሁላችሁ ብሆን እንኳ፥ ስለ እኛ ያላችሁ ትጋታችሁ ከእናንተ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንዲገለጥ እንጂ፥ ስለ በዳዩ ወይም ስለ ተበዳዩ አልጻፍሁም። ስለዚህ ተጽናንተናል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤
¹³ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።
¹⁴ ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።
¹⁵ ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤
¹⁶ ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።
¹⁷ ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?
¹⁸ ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?
¹⁹ ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ በቤተ ክርስቲያን ሁሉና ይህንም በሰሙ ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።
¹² በሐዋርያትም እጅ ብዙ ምልክትና ድንቅ በሕዝብ መካከል ይደረግ ነበር፤ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ ነበሩ።
¹³ ከሌሎችም አንድ ስንኳ ሊተባበራቸው የሚደፍር አልነበረም፥
¹⁴ ሕዝቡ ግን ያከብሩአቸው ነበር፤ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙ ነበሩ።
¹⁵ ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።
¹⁶ ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለችው ከተማ ድውያንንና በርኵሳን መናፍስት የተሣቀዩትን እያመጡ ብዙ ሰዎች ይሰበስቡ ነበር፤ ሁሉም ይፈወሱ ነበር።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_25_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ልሳነ ከለባቲከ ላዕለ ጸላዕቱ። አስተርእየ ፍናዊከ እግዚኦ። ፍናዊሁ ለአምላክነ ለንጉሥ ዘውስተ መቅደስ። መዝ.67÷23-24
"እግሮችህ በደም ይረገጡ ዘንድ፥ የውሾችህ ምላስ በጠላቶች ላይ ይሆን ዘንድ። የአምላኬ የንጉሥ መንገድ በመቅደሱ፥ አቤቱ፥ መንገድህ ተገለጠ"። መዝ.67÷23-24
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_25_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።
¹⁷ ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤
¹⁸ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ።
¹⁹ አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤
²⁰ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።
²¹ ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል።
²² በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
²³ በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
²⁴ ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም።
²⁵ ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!
²⁶ እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና።
²⁷ በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።
²⁸ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።
²⁹ ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም።
³⁰ የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል።
³¹ እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።
³² ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ የዕረፍት በዓልና፣ የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵
አመ ፳ወ፭ ለህዳር ለቅዱስ መርቆሬዎስ ስረዓተ ማኅሌት
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሉ አለም፤በአሐቲ ቃል
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ገባሬ ኩሉ
@EOTCmahlet
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም
ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም
ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም
ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም
ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።
@EOTCmahlet
ዚቅ-
ሠራዊተ መላእክቲሁ ለመድኃኔ ዓለም፤ ይቀዉሙ ቅድሜሁ ለመድኃኔ ዓለም፤ ወይኬልልዎ ለመድኃኔ ዓለም፤ ሥጋሁ ወደሙ ለመድኃኔ ዓለም፤ ወንብጻሕ ቅድመ ገጹ ለመድኃኔ ዓለም፤ በአሚነ ዚአሁ ሰማዕታት ከዓዉ ደሞሙ በእንቲአሁ።
👉@EOTCmahlet
ዓዲ
፩ አብ ቅዱስ ፩ ወልድ ቅዱስ፤ ፩ ዉእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘአድኃኖሙ ለሰማዕት።
👉@EOTCmahlet
መልከአ ሚካኤል ለሕፅንከ፦
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ለረዲኦትየ ከመ ዘይሰርር ዖፍ፤እንዘ ትሰርር ነዓ በክልዔ አክናፍ።
👉@EOTCmahlet

ዚቅ፦
ሚካኤል መልአክ ወረደ እምሰማይ፤ ኀበ ቅዱስ መርቆሬዎስ፤ ወአጥፍአ ኃይለ እሳት፤ ወኢለከፎ ስጋሁ።

  👉 @EOTCmahlet
ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
👉@EOTCmahlet
  ዚቅ፦
አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት፤ሠያሚሆሙ ለካህናት፤ ነያ ጽዮን መድኃኒት።
👉@EOTCmahlet
👉@EOTCmahlet
መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለዝክረ ስምከ ገብረ ኢየሱስ ብኢል፤ ወለስርዕትከ ጸሊም ዘቆናዚሁ ፍቱል፤ መርቆሬዎስ ሰማእት ገባሬ ተአምር ወኃይል፤ ለዮሐንስ ፍና ድኂን ከመ መራህኮ በኀቅል፤ ምርሀኒ ለወልድከ ፍና ጽድቅ ወሣህል።
👉@EOTCmahlet
👉@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ወሀሎ ፩ ብእሲ ዘስሙ ፒሉፖዴር፤ ዘበትርጓሜሁ መርቆሬዎስ ብሂል፤ ነገረ ገድሉ መዓርዒር ለተናግሮ ዕፁብ ግብር፤ ወዲበ ርእሱኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል።
👉@EOTCmahlet
ወረብ፦
ወሀሎ ፩ ብእሲ ዘስሙ ፒሉፖዴር ዘበትርጓሜሁ መርቆሬዎስ ብሂል/፪/
መዓርዒር ለተናግሮ ተናግሮ ዕፁብ ግብር/፪/
👉@EOTCmahlet
መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለከናፍሪከ ወለአፉከ ዘተናገረ፤ ዕበደ ዕልው ዳኬዎስ ወኀጒለ አርዳሚስ ድህረ፤ መርቆሬዎስ ሰማእት አመ አፆሩከ ፆረ፤ ተዐገስከ እስከ ለሞት እንዘ ትትዌከፍ ሐሣረ፤ በዓለመ ተስፋ ሐዳስ ከመ ትንሣእ ክቡረ።
👉@EOTCmahlet
  ዚቅ፦
ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ፤ወርእሶ አምተረ ዓቢያተ ተናገረ፤አስተምህር ለነ ዮሐንስ ዘአጥመቀ ቃለ።
👉@EOTCmahlet
ወረብ፦
ዓቢያተ ተናገረ ወርእሶ አምተረ ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ/፪/
አስተምህር ለነ መርቆሬዎስ ዘሰበከ ቃለ/፪/
👉@EOTCmahlet
👉@EOTCmahlet
  መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለልብከ ወለኅሊናከ ዘሐለየ፤ በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትትዌከፍ ሥቃየ፤ መርቆሬዎስ ሥዕልከ ከመ ጽንዐ ኃይሉ አርአየ፤ ላዕለ ዑልያኖስ መዓምፅ አመ ባስልዮስ ጸለየ፤ ኃይለ ረድኤትከ ይርአይ ዓላዊ ፀርየ።
👉@EOTCmahlet
👉@EOTCmahlet
  ዚቅ፦
ጸልዩ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ ኀበ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ፤ ደነነ ሥዕል ከመ ኦሆ ዘይብል፤ ሰምዖሙ ጸሎቶሙ፤ ወቀተለ ፀሮሙ።
👉@EOTCmahlet
ወረብ፦
ጸልዩ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ ኀበ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ/፪/
ደነነ ሥዕል ከመ ኦሆ ዘይብል ወተፈሥሑ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ/፪/
👉@EOTCmahlet
ወረብ ዓዲ፦
👉@EOTCmahlet
ጸልዩ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ ኀበ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ/፪/
ደነነ ሥዕል ከመ ኦሆ ሰምዖሙ ጸሎቶሙ/፪/
👉@EOTCmahlet
👉@EOTCmahlet
መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለጸአተ ነፍስከ ድኀረ ፈጸሙት ህማማ፤ በአፈ ጕድብ ሰይፍ በሊህ አመ ክሣዳ ተገዝመ፤ መርቆሬዎስ ቅድሜከ ሶበ እግረ ልብየ ቆመ፤ ሐውፀኒ ለለጽባሑ ወጸግወኒ ሰላም ፤እስመ ረሰይኩከ አበ ወሰናይት እመ።
👉@EOTCmahlet
  ዚቅ፦
መጠወ ነፍሶ ወመተርዎ ክሣደ፤ወተፈፀመ ስምዑ ለቅዱስ መርቆሬዎስ።
👉@EOTCmahlet
  አመላለስ፦
መጠወ ነፍሶ ወመተርዎ ክሣዶ/፪/ ወተፈፀመ ስምዑ ለቅዱስ/፪/
👉@EOTCmahlet
👉@EOTCmahlet
ወረብ፦
መጠወ ነፍሶ ወመተርዎ ክሣዶ፤
ወተፈፀመ ስምዑ ለቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ መርቆሬዎስ/፪/
በብዙኅ ትዕግሥት እምሠጡ እምኲናት ሰማዕት አጥፍዑ ኃይለ እሳት/፪/
👉@EOTCmahlet
መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለበድነ ስጋከ ንጹሕ ወቅዱስ፤ ወለግንዘትከ ፀዓዳ በማየ ደም ግፍዕ ርሑስ፤ መርቆሬዎስ ሰማእት መኰንነ አስሊጥ ወፋርስ፤ ላዕሌየ ይኅድር እግዚኦ በጸሎትከ ክርስቶስ፤ እስመ ማኅደሩ ውእቱ ልቦና ወነፍስ።
  👉@EOTCmahlet
👉@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ከመ ኮከብ ብሩህ፤ ወከመ ዕጣን ንፁህ፤ መርቆሬዎስ ኃያል መስተጋድል፤ ዘዓቢየ ኃይለ ይገብር።
👉@EOTCmahlet
👉@EOTCmahlet
መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለመቃብሪከ ለህላዌከ መካኑ፤ ወለስጋከ ቀይጠኑ፤ መርቆሬዎስ ከማከ ኢተንስአ በበዘመኑ፤ መኑ መኑ ዝይትማስለከ መኑ፤ እንበለ ጊዮርጊስ ሰማእት ዘአዳም ስኑ።
👉@EOTCmahlet
  ዚቅ፦
ጸለየ መርቆሬዎስ እንዘ ይብል ኀበ ይብል ኃበ ተቀብረ ሥጋየ ወተክዕወ ደምየ ህየ በረከት
👉@EOTCmahlet
ምልጣን
ፈጸመ ሰምዓ ቅዱስ መርቆሬዎስ፤ በመዋዕሊሁ ለዳኬዎስ ንጉስ፤ ወኮነ መድኃኒተ ለኩሉ ዘነፍስ፤ ወተፈሥሑ፤ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ።
👉@EOTCmahlet
👉@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ወተፈሥሑ ባስልዮስ/፪/
ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ/፬/
👉@EOTCmahlet
ወረብ፦
ፈጸመ ሰምዓ ቅዱስ መርቆሬዎስ በመዋዕሊሁ ለዳኬዎስ ንጉስ/፪/
ወኮነ መድኃኒተ ለኩሉ ዘነፍስ ወተፈሥሑ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ/፪/
👉@EOTCmahlet
👉@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም
ኢፈርህዎ ለሞት ከመ ይንሥኡ ዕሤቶሙ፤ እምኀበ አብ እምሰማያት፤ በብዙኅ ትዕግሥት እምሠጡ እምኲናት፤ ሰማዕት አጥፍዑ ኃይለ እሳት፤ አድምፁ ተስፋ ዓቂቦሙ ሃይማኖተ፤ ሰማ ስነ ራእዮሙ ጥቀ አዳም፤ ሰማዕት አጥፍዑ ኃይለ እሳት፤ ሰማዕት አጥፍዑ ኃይለ እሳት።
👉@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ሰማዕት አጥፍዑ ኃይለ እሳት/፪/
ሰማዕት አጥፍዑ ኃይለ እሳት/፬/

👉@EOTCmahlet
ወረብ ዘእስመ ለአለም፦
ኢፈርህዎ ለሞት ከመ ይንሥኡ ዕሤቶሙ እምኀበ አብ እምሰማያት/፪/
በብዙኅ ትዕግሥት እምሠጡ እምኲናት ሰማዕት አጥፍዑ ኃይለ እሳት/፪/

   🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
    👉@EOTCmahlet👈                 
    👉@EOTCmahlet👈
    👉@EOTCmahlet👈
   🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    # Join & share #
#ኅዳር_26

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ሃያ ስድስት በዚህች ዕለት #አቡነ_ኢየሱስ_ሞዓ ዕረፍት ነው፣ #የአቡነ_ሀብተ_ማርያም ዕረፍት ነው፣ #የሀገረ_ናግራን_ሰማዕታትና የአባታቸውም #የቅዱስ_ኂሩት መታሰቢያቸውም ነው፣ #የቅዱስ_ቢላርያኖስ_ሚስቱ_ኪልቅያና_እኅቱ_ታቱስብያ በሰማዕትነት ያረፉበት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አቡነ_ኢየሱስ_ሞዓ_ዘሐይቅ

ኅዳር ሃያ ስድስት በዚህች ዕለት አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ዘሐይቅ እረፍታቸው ነው። በጐንደር ክፍለ ሀገር ስማዳ ወረዳ ዳህና ሚካኤል በተባለው ቦታ ከአባታቸው ከዘክርስቶስና ከእናታቸው ከእግዚእ ክብራ በ1210 ዓ.ም ነው ተወለዱ። ዕድሜያቸው 3ዐ ዓመት እስከሚደርስ ከቤተሰቦቻቸው ትምህርተ ሃይማኖትንና ግብረ ገብን ሲማሩ ከቆዩ በኋላ በ124ዐ ዓ.ም ይኼንን ዓለም በመተው ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ገቡ። በደብረ ዳሞ ገዳም መነኰሳቱን እየረዱ፣ ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን እያጠኑ፣ ትምህርተ ቅዱሳት መጻሕፍትን እየገለበጡ ለሰባት ዓመታት ከቆዩ በኋላ የደብረ ዳሞ 3ኛ አበ ምኔት ከሆኑት ከአባ ዮሐኒ ምንኩስናን ተቀበሉ (1247 ዓ.ም.)።

አንድ ቀን ሌሊት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደርሳቸው መጥቶ (ገድልህና ትሩፋትህ በዓለም ሕዝብ ሁሉ ትተህ የስምህ መክበርያ ወደሆነው ሐይቅ ወደ ተባለው ሥፍራ ሂድ) አላቸው። አባታችን "ቦታውን እንዴት ዐውቀዋለሁ" በማለት ቢጠይቁት "ተነሥ። ጉዞህን ጀምር ቦታውን እኔ አሳይሃለሁ" አላቸው። አባ ኢየሱስ ሞዓ በመልአኩ እንደታዘዙት ከበአታቸው ተነሥተው ተከተሉት። የብዙ ወራት መንገድ የሆነው ጐዳናም በስድስት ሰዓት አለቀላቸው።

በዚያን ወቅት ከሐይቅ ገዳም በስተ ሰሜን ወደነበረው ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ደረሱ። ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከመግባታቸውም በፊት ለ6 ወራት ያህል በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን አገልግለዋል። ያገለግሉበት በነበረው ቤተ ክርስቲያን ቀን ቀን ሕዝቡን ሲያስተምሩ በመዋል ሲመሽ ወደ ሐይቁ በመግባት ሲጸልዩ ያድሩ ነበር። በሐይቅ እስጢፋኖስና በዙርያው ለነበሩ አበውም ማታ ማታ አንድ ብርሃን ወደ ሐይቁ ሲገባ ጠዋት ጠዋትም ሲወጣ ይታያቸው እንደነበር ዛሬ በገዳማቸው የሚገኘው ገድለ ኢየሱስ ሞዓ ያስረዳል።

በመጨረሻም በገዳሙ አባቶች ልመናና በልዑል #እግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ ሐይቅ ገዳም ገብተው አበምኔት ሆኑ። ሐይቅ እስጢፋኖስ ማለት ከደሴ 30 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ሲሆን የመሰረቱት ካልዕ ሰላማ የተባሉ ግብጻዊ ጻድቅ ናቸው፤ ገዳሙን ከሰሩ በኃላ የማንን ታቦት እናስገባ ብለው ሲያስቡ ቶራ የምትባል እንስሳ ጭነት ተጭና ከመካከላቸው ተገኘች፤ ጭነቱን አውርደው ቢያዩት በሐር ጨርቅ የተጠቀለለ ሁለት ታቦት አገኙ አንዱ የእስጢፋኖስ አንዱ የጊዮርጊስ " ይህንን ታቦት በእየሩሳሌም የሚኖሩ የተሰወሩ ቅዱሳን ከ #እግዚያብሔር ታዘው የላኩት ነው" የሚል ጽሑፍም አገኙ ይላል። ይህ ከሆነ ከ 400 ዘመን በኃላ ነው አባ እየሱስ ሞኣ ወደዚህ ቦታ የመጡት ለ 52 ዓመት ቀን ቀን መንፈሳዊ ስራቸውን ይሰራሉ ሌሊት ሌሊት ሐይቁ ውስጥ ቆመው ሲጸልዩ ያድራሉ።

አባ ኢየሱስ ሞዓ በሐይቅ እስጢፋኖስ በአበምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ከየገዳማቱ ቅዱሳን መጻሕፍትን በመገልበጥና በማስገልበጥ ብሎም በማሰባሰብ የመጀመርያው ዘመናዊ የቤተ ክርስቲያን ቤተ መጻሕፍት በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም እንዲቋቋም አድርገዋል። በዚሁ ገዳም ውስጥም የመጀመርያውን የቤተ ክርስቲያን ቋሚ ትምህርት ቤት በማቋቋም 8ዐዐ መነኮሳትን በትምህርተ ሃይማኖት አሠልጥነው በንቡረ ዕድነት ማዕረግ በመላ ሀገሪቱ እንዲሠማሩ አድርገዋቸዋል።

ከተማሪዎቻቸውም መካከል አቡነ ተክለ ሃይማኖት (ዘደብረ ሊባኖስ)፣ አባ ተክለሃይማኖት ያመነኮሱ አባት ናቸው። አባ ኂሩተ አምላክ (ዘጣና ሐይቅ)፣ አባ ጊዮርጊስ (ዘጋሥጫ)፣ አባ ዘኢየሱስ፣ አባ በጸሎተ ሚካኤል፣ አባ አሮን (ዘደብረ ዳሬት) ጥቂቶች ናቸው። አፄ ይኩኖ አምላክንም በትምህርተ ሃይማኖት ያነፁት እርሳቸው ናቸው።

እንደዚህ ነው የመነኮሳት አባት እንጦንስ ነው እንጦንስ መቃርስን ወለደ መቃርስ ጳኩሚስን ጳኩሚስ አቡነ አረጋዊን አቡነ አረጋዊ አባ ዮሐኒን አባ ዮሐኒ የሐይቁን አባ እየሱስ ሞአን ወለዱ አባ ኢየሱስ ሞዓ ደግሞ ተክለሃይማኖትን ወለዱ።

በዮዲት ጉዲት ተጐድታ የነበረችው ሀገራችን ዳግም የወንጌሉ ብርሃን እንዲበራባት ሊቃውንት እንዲይነጥፉባት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዳይቆነጻጸሉ፣ መነኮሳት አባቶች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወርደው ገዳማትን እንዲያስፋፉ ያደረጉት አባ ኢየሱስ ሞዓ ናቸው። በተለይም የሐይቅ እስጢፋኖስ ያፈራቸው 8ዐዐ ሊቃውንት በመላዋ ሀገሪቱ በመሠማራታቸው ዛሬ የምናያቸውን አብዛኞቹን ገዳማትና ቅዱሳት መጻሕፍት አቆይተውናል።

አባታችን አባ ኢየሱስ ሞዓ ለ45 ዓመታት ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከቆዩ በኋላ ኅዳር 26/1292 ዓ.ም በዕለተ እሑድ በ82 ዓመታቸው ዐረፉ። በዚያች ዕለትም በቦታው የታየው ብርሃን ሀገሪቱን መልቷት እንደነበረ ገድላቸው ይመሠክራል።

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አቡነ_ሀብተ_ማርያም

በዚህችም ቀን የተመሰገነና የከበረ ንጹሕም የሆነ የኢትዮጵያዊ አባታችን የሀብተ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

የዚህ ቅዱስ አባት የትውልድ አገሩ የራውዕይ በምትባል በስተ ምሥራቅ ባለች ሀገር ውስጥ ነው በዚያም ስሙ ፍሬ ቡሩክ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ይህም ክቡራንና ታላላቅ ከሚባሉት ከዚች አገር ታላላቅ ሰዎች አንዱ ነው ። እጅግም ሀብታም ነበር ብዙ ንብረትም አለው በሕጋዊ ጋብቻም ስሟ ዮስቴና የምትባል ብላቴና ድንግልን አገባ ይቺም የተመረጠች በበጎ ሥራ የተሸለመችና ያጌጠች ናት።

ነገር ግን አስቀድመን በዚህ ዓለም ከሕግ ባሏ ጋር በንጹሕ ጋብቻ #እግዚአብሔርን በመፍራት ምጽዋትን በመስጠት የዋህነትን ትሕትናን ፍቅርን ትዕግሥትን ገንዘብ አድርጋ በጾም በጸሎት ተወስና እንደኖረች እንነግራችኋለን ። በእንደዚህም ሳለች #ጌታችን በወንጌል ሰው ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ካጠፋ ምን ይጠቅመዋል እንዳለ ላንቺ በዚህ ዓለም መኖር ምን ይረባሽ የሚል ሐሳብ መጣባት ።

ከዚህም በኋላ ወጣች ፈጥናም በሀገርዋ ትይዩ ወደሆነ ምድረ በዳ ደርሳ ወደ መካከሉ ገባች በዚያም በረሀ አራዊት እንጂ ሰው አይኖርበትም በዚያም ደጃፍዋ የተከፈተ ታናሽ ዋሻ አግኝታ ምንም ምን ሳትነጋገር ወደ ውስጧ ገብታ ቆመች የዳዊትንም መዝሙር የሚጸልይ ሰው አይታ ደነገጠች።

እርሱም ባያት ጊዜ ፍርሀትና መንቀጥቀጥ በላዩ ወረደበት በ #መስቀል ምልክትም በላይዋ አማትቦ የ #እግዚአብሔርን ስም ጠራ እንዳልሸሸችም አይቶ ሰው መሆንዋን አወቀ በአወቀም ጊዜ እንዲህ ብሎ ገሠጻት ወደዚህ ምን አመጣሽ ለእኔ እንቅፋት ልትሆኚ ነውን አሁንም ከዚህ ፈጥነሽ ሒጂ አላት ።

እርሷም አባቴ ሆይ አንተ እንዳሰብከው አይደለሁም እኔ ለሕያው #እግዚአብሔር ልጅ ለ #ኢየሱስ_ክርስቶስ አገልጋዩ ነኝ እንጂ በእርሱ ፍቅርና በእናቱ በእመቤቴ በቅድስት ድንግል #ማርያም ፍቅር ያለኝን ሁሉ ትቼ ንቄ ከዓለም ወጥቼ ወደዚህ መጣሁ በዚህ ቦታም ከአራዊት በቀር ሰው እንዳለ አላወቅሁም አሁንም አባቴ ይቅርታ አድርግልኝ ወደ ሌላ ቦታ እሔዳለሁ አለችው ።
በዚያንም ጊዜ ከርሷ የሚሆነውን #መንፈስ_ቅዱስ ገልጾለት እንዲህ አላት ዜናው ወደ ዓለም ሁሉ የሚወጣ በሕይወተ ሥጋም እያለ የብዙዎች ሰዎች ነፍሳትን ከሲኦል የሚያወጣ እንደ መላእክትም ክንፎች ተሰጥተውት ወደ አርያም ወጥቶ የ #ሥላሴን የአንድነትና የሦስትነትን ምሥጢር የሚያይ ልጅን ትወልጂ ዘንድ አለሽና ወደ ቤትሽ ተመለሽ አላት ።

ቅድስት ዮስቴናም ከዚያ ሽማግሌ ባሕታዊ ይህን በሰማች ጊዜ አድንቃ የፈጣሪዬ ፈቃዱ ከሆነ ብላ ወደቤቷ ተመለሰች።

ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ፀንሳ ይህን ደም ግባቱ መልኩ የሚያምር ልጅን ወለደች በእናትና በአባቱ ቤትም ታላቅ ደስታ ሁኖ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ለዘመዶቻቸውና ለጎረቤቶቻቸው ታላቅ ምሳ አደረጉ እነርሱም በጠገቡ ጊዜ እነርሱንም ሕፃኑንም መረቋቸው ።

ሕፃኑም አርባ ቀን በሆነው ጊዜ እንደ ሕጉና እንደ ሥርዓቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወሰዱት ካህኑም ተቀብሎ በአጠመቀው ጊዜ ስሙን ሀብተ ማርያም ብሎ ሰይሞ ለክርስትና አባቱ ሰጠው ሕፃኑም ጥቂት በአደገ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እግዚኦ መሐረነ #ክርስቶስ ሲሉ ሰምቶ ሕፃኑ ሀብተ ማርያም በልቡ ይቺ ጸሎት መልካም ናት እኔም መርጫታለሁ በዚህ ዓለም ስሕተትን አስቦ ከመሥራት በሚመጣውም ዓለም ከገሀነም እንደምድንባት አውቃለሁና አለ ። ይህንንም ብሎ የሚሠራውን ማንም ሳያውቅበት ይህን ጸሎት ከማዘውተር ጋር ሌሊቱን ሁሉ በመስገድ ይፀልይ ነበር ።

ከዚህም በኋላ አባቱ የበጎች ጠባቂ አደረገው በአንዲት ዕለትም በጎቹን አየጠበቀ ሳለ ብዙ የበግ ጠባቂዎች እሸት ተሸክመው መጥተው ና እንብላ አሉት እርሱ ግን ከወዴት እንዳመጣችሁት የማላውቀውን አልበላም አላቸው እነርሱም በቁጣ ዐይን ተመልክተው ተጠቃቀሱበት ።

እሸቱንም በልተው ከጨረሱ በኋላ የከበረ ሕፃን ሀብተ ማርያምም ታላቅ ዝናም ስለመጣ ወደየቤታችን እንመለስ ከዚህ የምንጠለልበትና የምንጠጋበት ቤት ወይም ዋሻ የለምና አላቸው ። እነርሱም እኛ የማናየውን የሚያይ ሌላ ዐይን አለህን በሰማይ ፊት ምንም ደመና ሳይኖር ሀገሩም ብራ ሆኖ ሲታይ እንዴት ይዘንማል ትላለህ አሉት እርሱም እኔ የማውቀውን እናንተ አታውቁትም ግን ወደ ቤታችሁ ግቡ አላቸው እረኞችም ባልሰሙት ጊዜ ፈጥኖ ተነሥቶ በጎቹን እያስሮጠ ወደ ቤቱ ገባ ። ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ታላቅ ዝናም መጣ ነፋሳትም ነፈሱ መብረቆችም ተብለጨለጩ ነጎድጓድም ተሰማ ደመናትም ተነዋወጹ ይህ ሁሉ በላያቸው ሲወርድ መሸሺያ አላገኙም ።

ከጥቂት ቀኖችም በኋላ በጎቹን እየጠበቀ ሳለ ብዙ የበግ እረኞችም አብረውት ነበሩ አንድ የበግ ጠባቂም መጥቶ የወጣት ሀብተ ማርያምን በትር ነጠቀውና ሔደ ብላቴና ሀብተ ምርያምም በትሬን ለምን ትቀማኛለህ አለው እረኛውም በትዕቢት ቃል በጉልበቴ ነጥቄሃለሁ አለው ብላቴና ሀብተ ማርያምም እኔ ኃይል የለኝም ነገር ግን በጎቼን የምጠብቅበትን በትሬን እንዳትወስድብኝ በሕያው #እግዚአብሔር ስም አምልሃለሁ አለው ያም የበግ ጠባቂ እምቢ አልኩህ አለው ።

ብላቴናው ሀብተ ማርያምም አንድ ጊዜ በፈጣሪዬ ስም አማልኩህ ከእንግዲህ ወዲያ ደግሜ አላምልህም በአንተ ላይ የሚደረገውን ራስህ ታውቀዋለህ ይህንንም ተናግሮ ዝም አለ ። በዚያንም ጊዜ ያ የበግ ጠባቂ በአየር ውስጥ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ የ #እግዚአብሔር አገልጋይ ሀብተ ማርያም ማረኝ እያለ ይጮህ ጀመረ የልዑል #እግዚአብሔርን ስም አቃልሏልና ተሰቅሎ ዋለ እረኞች ሁሉም አይተው አደነቁ ፈሩትም ይህን ሰነፍ ማርልን #እግዚአብሔር ያደረገልህን ኃይል አይተናልና አሁንም ስለ እምቤታችን ድንግል #ማርያም ይቅር በለው አሉት ። ብላቴናው ሀብተ ማርያምም በውኑ እኔ የሰቀልኩት ነውን በ #እግዚአብሔር ስም አማልኩት እንጂ የኃይሉን ጽናት በላዩ ሊገልጥ እርሱ #እግዚአብሔር ሰቀለው አሁን እርሱ ከፈቀደ ያውርደው እርሱ መሐሪና ይቅር ባይ ነውና ይህንንም በተናገረ ጊዜ ወርዶ በእግሩ ቆመ ወደርሱም መጥቶ ሰገደለት ።

ከረጂም ዘመናትም በኋላ ስሟ እለአድባር ወደምትባል ገዳም ሒዶ ከዚያም የምንኩስናን ሥርዓትና ሕግ በአበምኔቱ በተመረጠ አባ መልከጸዴቅ እጅ ተቀበለ ከዚያም ቅዱሳን መነኰሳት ወደሚኖሩበት ሔዶ ታላቅ ተጋድሎ ጀመረ ።

እርሱም በባሕር መካከል በመቆም የዳዊትን መዝሙር ሁሉንም ያነባል በባሕር ውስጥም ሰጥሞ ግምባሩ አሸዋ እስቲነካው አምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳል ከሰንበት ቀኖችም በቀር እህል አይቀምስም ነበር ከዚህም በኋላ እህልን ትቶ እንደ ዋልያዎች የዱር ቅጠል የሚመገብ ሆነ ።

አርባ አርባ ሰማንያ ሰማንያ ቀን የሚጾምበት ጊዜ አለ በባሕር ውስጥ በሌሊት ቁሞ በማደር በቀንም አራቱን ወንጌላት ያነባል ሌሎች መጻሕፍትንም በእንዲህ ያለ ሥራ ብዙ ዘመን ኖረ።

ብዙ ተጋድሎንና ድካምንም በአስረዘመ ጊዜ #ጌታችንና_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደርሱ ተገልጦ መጣ ከእርሱ ጋርም የመላእክት አለቆች የከበሩ ሚካኤልና ገብርኤል የመላእክት ማኅበርም ሁሉ በዙሪያው ሁነው እያመሰገኑት ነበር ወዳጄ ሀብተ ማርያም ሰላም ላንተ ይሁን አለው ። በዚያንም ጊዜ ከግርማው የተነሣ ወድቆ እንደ በድን ሆነ #ጌታችንም በከበሩ እጆቹ አንሥቶ እፍ አለበትና ጽና ኃይልህን ላድሳት እንጂ ላጠፋህ አልመጣሁምና ተጋድሎህና ድካምህ ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት እንደ ተጻፈ በእውነት እነግርሃለሁ ።

እነሆ እኔ በጎ ዋጋህን በዚህም ዓለም በሚመጣውም ዓለም እከፍልሃለሁ የማቴዎስንና የማርቆስን ወንጌል በምታነብ ጊዜ በተራራዎችና በዋሻዎች በፍርኩታ ተሠውረው ወደሚኖሩ እንዳንተ ካሉ ቅዱሳን ጋር ለመገናኘት በላዩ ተቀምጠህ ወደ ምሥራቅ ወደ ምዕራብ ወደ ሰሜንና ደቡብ የምትበርበት የብርሃን ሠረገላ ሰጠሁህ ሉቃስና ዮሐንስ የጻፉትን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ ቅዱስ ሥጋዬንና ክቡር ደሜን በዚያ ትቀበል ዘንድ በላዩ ተቀምጠህ ወደ ኢየሩሳሌም የምትሔድበት የእሳት ሠረገላ ሰጠሁህ አለው ።

ከብዙ ዘመናትና ከብዙ ተጋድሎ በኋላ የሚሞትበት ጊዜ ሲደርስ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር ያዘው ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደርሱ መጥቶ ወዳጄ ሀብተ ማርያም ሰላም ላንተ ይሁን ዛሬ ግን የመጣሁት ከድካም ወደ እረፍት ልወስድህ ነው እነሆ ሰባት አክሊላትን አዘጋጅቼልሃለሁና አንዱ ስለ ድንግልናህ ሁለተኛው ዓለምንና በውስጡ ያለውን ሁሉን ትተህ በመውጣትህ ሦስተኛው ፍጹም ስለሆነው ምንኩስናህ አራተኛው አራቱን ወንጌሎች አዘውትረህ የምታነብ በመሆንህ አምስተኛው ስለ እኔ ፍቅር መራብና መጠማትን ስለታገሥክ ስድስተኛው በልብህ ቂምና በቀልን ባለማሳደርህ ሰባተኛውም ስለ ንጹሕ ክህነትህና ስለምታሳርገው ያማረ የተወደደ ዕጣንህና መሥዋዕትህ ሰጠሁህ እሊህ ሰባቱ አክሊላትም ለየአንዳንዳቸው ዐሥራ አምስት ዐሥራ አምስት ኅብር አላቸው ።

መታሰቢያህን ካደረጉና በጸሎትህ ከተማፀኑ ጋር የምትገባበትን ቤት በውስጧ አምስት መቶ የወርቅ አምዶች የተተከሉባትን ሰጠሁህ ደግሞ የእሳት #መስቀልን የወርቅ ጫማን የብርሀን ልብስን ሥውር የሆነ መና እሰጥሃለሁ አለው ።

#መድኃኒታችንም ይህን ቃል ኪዳን ሲሰጠው በየነገዳቸውና በየሥርዓታቸው ዘጠና ዘጠኝ የመላእክት ሠራዊት መጥተው ወዳጃችን ሰላም ላንተ ይሁን ዛሬስ ከፀሐይ ሰባት እጅ ወደምታበራ ሀገራችን በዝማሬና በማኅሌት አክብረን ልንወስድህ መጣን አሉት ። አባታችን አባ ሀብተ ማርያምም በሰማያት ለ #እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ሆነ የሰው ነጻነቱ ሊሰጠው አለ ።
ይህንንም በተናገረ ጊዜ #ጌታችን በሦስትነቱ ተገልጦ ታየውና የመጥምቁ ዮሐንስን ሀገር ተጠጋግታ ያለች ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ ሀገርን እሰጥህ ዘንድ በራሴ ማልኩልህ አለው ።

መታሰቢያህን የሚያደርገውን በስምህ ለቤተ ክርስቲያን መባ የሚሰጠውን ስምህንም የጠራውን ወደዚች አገር አገባዋለሁ አራቱን ወንጌሎችም እያነበብክ ስለኖርክ የየአንዲቱን ቃል ፍሬዋን አንዳንድ ሽህ አደረግሁልህ ይኸውም ካንተ በኋላ ለሚመጡ ልጆችህ መጽሐፈ ገድልህን ለሚያነቡና በእምነት ለሚሰሙ የገድልህ መጽሐፍ በተነበበበት ውኃ ለሚረጩ ለሚነከሩበት ይህን ቃል ኪዳን ሰጥቼሃለሁ ።

ከዚህም በኋላ #መድኃኒታችን አፉን ሦስት ጊዜ ሳመው በዚያንም ጊዜ ከፍቅሩ ጣዕም ብዛት የተነሣ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች #ጌታችንም ተቀብሎ አቅፎ ከእርሱ ጋር አሳረጋት ። በመላእክት ጉባኤም ብዙ ምስጋና ተደረገ ።

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አቡነ ሐብተ ማርያም ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ኂሩት_አረጋዊ

በዚህችም ቀን የሀገረ ናግራን ሰማዕታትና የአባታቸውም የቅዱስ ኂሩት መታሰቢያቸው ነው። ይህም ዮስጢኖስ ለቁስጥንጥንያ በነገሠ በአምስተኛው ዓመት ለኢየሩሳሌም አባ ዮሐንስ ለእስክንድርያ አባ ጢሞቴዎስ ለቁስጥንጥንያም አባ ጢሞቴዎስ ለአንጾኪያ አባ አውፍራስዮስ ሊቃነ ጳጳሳት ሁነው ሳለ በኢትዮጵያም ጻድቁ ካሌብ ነግሦ ሳለ በዚያን ወራት ለአይሁድ ስሙ ፊንሐስ የሚባል አይሁዳዊ ነገሠ ።

በመጀመሪያ ግን ሳባ የተባለች አገር በኢትዮጵያ ነገሥታት እጅ ውስጥ ነበረች የሮም ነገሥታት አስባስያኖስና ጥጦስ ከኢየሩሳሌም አይሁድን በአሳደዷቸው ጊዜ ይቺን ሳባን አይሁድ ወረሷት።

በውስጧም በ #ኢየሱስ_ክርስቶስ የሚያምኑ ብዙዎች ክርስቲያኖች የሚኖሩባት ታላቅ ከተማ አለች ይህም የተረገመ አይሁዳዊ ፊንሐስ ሊአጠፋት በመጣ ጊዜ የዚችን የከበረች ሀገር በ #መስቀል ምልክት በዙሪያዋ ያለ ቅጽርዋን በበሮቿና በግንብ አጥርዋ ላይ ያሉ ብዙ አርበኞች ሠራዊትን አይቶ በምንም ምክንያት ሊገባባት ስለአልተቻለው ተቆጣ ። #እግዚአብሔር አጽንቷታልና ነገር ግን በውጭ ያገኛቸውን ገበሬዎች ገደለ ታናናሾችንም ማርኮ ለባሮቹ ሰጣቸው ።

ይህም ዲያብሎስን የሚመስለው አይሁዳዊ የኦሪትና የነቢያት ፈጣሪ በሆነ በ #እግዚአብሔር ስም እየማለ በተንኰል መልእክትን ላከ እንዲህም አላቸው እኔ ከእናንተ ጋር ጠብ አልሻም ከሀገር ሰው አንዱን እንኳ ማጥፋት አልፈልግም በሀገሪቱም ውስጥ የደም ጠብታ አይፈስም ነገር ግን የከተማዋን አሠራርዋን አደባባዮቿን ገበያዎቿን ማየት እሻለሁ ለሀገር ሰዎችም የተናገረው ዕውነት መሰላቸው ።

የካዕቢ ልጅ አባት ኂሩት ይህን አይሁዳዊ አትመኑት ሐሰተኛ ነውና ደጁንም አትክፈቱለት አላቸው አባት ኂሩትንም አልሰሙትም ደጁንም ከፈቱለትና ገባ ከገባ በኋላም አስቀድሞ የአገሪቱን ሰዎች ገንዘባቸውን እንዲዘርፉአቸው አዘዘ ። ሁለተኛም ነበልባሉ ወደ አየር እስቲደርስ እሳትን አንድደው የሀገሪቱን ኤጲስቆጶስ አባ ጳውሎስን እንዲአመጡት አዘዘ እርሱ እንደ ሞተም በነገሩት ጊዜ ዐፅሙን ከመቃብር አውጥቶ አቃጠለው ።

ከዚህም በኋላ ቀሳውስትን ዲያቆናትን መነኰሳትን አንባቢዎችንና መዘምራኑን በቀንና በሌሊት መጻሕፍትን በማንበብ የሚተጉትን ሰበሰበ እነርሱንም ከእሳት ውስጥ ጨመራቸው ቁጥራቸውም አራት ሺህ ሃያ ሰባት ነፍስ ሆነ ክርስቲያኖችን በዚህ ሊአስፈራራቸው አስቧልና።

ዳግመኛም የብረት ዛንጅር በቅዱስ አባት ኂሩት አንገት ውስጥ እንዲአስገቡ እጆቹንና አግሮቹንም እንዲአሥሩት አዘዘ ታላላቆችንና የሀገሩን መኳንንትንም እንዲአሥሩአቸው #ክርስቶስን የማይክደው ሁሉ እንዲህ ተሠቃይቶ በክፉ አሟሟት ይሞታል የሚል ዐዋጅ ነጋሪ እየጮኸ በከተማው ውስጥ እንዲአዞሩአቸው አዘዘ ።

ቅዱሳን የክርስቲያን ወገኖች በሰሙ ጊዜ እንዲህ እያሉ ጮኹ እኛ ያመንበትንና በስሙ የተጠመቅንበትን ክብር ይግባውና #ክርስቶስን አንክደውም ይህ ርጉም አይሁዳዊም ሰምቶ ወንዶችና ሴቶችን ወጣቶችንና ሕፃናትን ሽማግሎችን ሁሉንም እንዲገድሉ አዘዘና ገደሉአቸው ቁጥራቸውም አራት ሺህ ሁለት መቶ ኃምሳ ሁለት ነፍስ ሆነ ።

ከዚህም በኋላ የቅዱስ ኂሩትን ሚስት ቅድስት ድማህን ከሁለት ሴቶች ልጆቿ ጋር ያዛት እነርሱም በቤታቸው መስኮት ከሚገባው በቀር ፀሐይ ያልነካቸው ናቸው ደርሰውም በአይሁዳዊ ንጉሥ ፊት በቆሙ ጊዜ እርሱም ሃይማኖታቸውን ያስክዳቸው ዘንድ በብዙ ተንኮል ሊሸነግላቸው ጀመረ እምቢ ባሉትም ጊዜ የራሳቸውን መሸፈኛ እንዲገልጧቸው አዘዘ የሀገር ሴቶችም እስከ ሚያለቅሱ ድረስ ከልጆቹም የምታንስ አንዲቱ ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆነ ከንጉሡ ፊት ላይ ምራቋን ተፋችበት ።

ወታደሩም አይቶ ሰይፉን መዝዞ አንገቷን ቆረጠ የእኅቷንም አንገት ቆረጠ ። ይህ የረከሰ አይሁዳዊ ንጉሥም ለቅድስት ድማህ የልጆቿን ደም እንዲአጠጧት አዘዘ እርሷም ቀምሳ የሕያው #እግዚአብሔር ልጅ #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶሰ ሆይ አመሰግንሃለሁ እንደቁርባን መሥዋዕት የሆነውን የልጆቼን ደም እኔ ባሪያህ እንድቀምስ አድርገሃልና አለች ። በዚያንም ጊዜ ርሷንም በሰይፍ አንገቷን እንዲቆርጡ ዳግመኛ አዘዘ ተጋድሎአቸውንም ፈጸሙ ።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ኂሩትን ከእሥር ቤት እንዲአመጡት ንጉሥ አዘዘ ከርሱም ጋር አንድ ሺህ አርባ እሥረኞች ሰዎች አሉ ሃይማኖቱንም ይተው ዘንድ አስገደደው ። ቅዱስ ኂሩትም ንጉሡን እንዲህ አለው ክብር ይግባውና ጌታዬን_ኢየሱስ_ክርስቶስን እያመለክሁት ስኖር ሰባ ስምንት ዓመት ሆነኝ እስከ አራት ትውልድ ለማየትም ደርሼአለሁ ዛሬም ስለ ከበረ ስሙ ምስክር ሁኜ ስሞት እጅግ ደስ ይለኛል ።

እኔኮ አስቀድሜ መሐላህን እንዳያምኑ ለወገኖቼ ነግሬአቸው ነበር አንተ ሐሰተኛ ነህና ነገር ግን ይህ ሁሉ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ነው የሆነው ለዚህም ተጋድሎ ላደረሰኝ ለእርሱ ምስጋና ይሁን ንጉሡም ይህን ሰምቶ ተቆጣ ወደ ወንዝም ወስደው በዚያ አንገቱን እንዲቆርጡት አዘዘ ።

ቅዱስ አባት ኂሩትም በሰማ ጊዜ ደስ አለው የሮምንና የኢትዮጵያን መንግሥት ያጸና ዘንድ የተረገመ የአይሁዳዊውን መንግሥት ያጠፋ ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር ጸለየ ሕዝቡንም ባረካቸው ።

ከእርሳቸው ጋር በሰላምታ ተሰናበታቸው ከዚህም በኋላ የቅዱሳኑን ራሶቻቸውን ቆረጧቸው በዚያም የአምስት ዓመት ልጅ ያላት አንዲት ክርስቲያን ሴት ነበረች ከቅዱሳን ደም ወስዳ ተቀባች ልጅዋንም ቀባችው ወታደሮችም አይተው አሥረው ወደ ንጉሡ አድርሰው ከእሳት ጨመርዋት ልጅዋን ግን አይሁድ ወደ እነርሱ ወስደው ወደ ንጉሡ አቀረቡት ንጉሡም እኔን ትወዳለህን ወይስ #ክርስቶስ የሚሉትን አለው ሕፃኑም እኔስ የእጁ ሥራ ነኝና #ክርስቶስን እወደዋለሁ ይልቅስ ልቀቀኝ ወደ እናቴ ልሒድ አለው በከለከለውም ጊዜ እግሩን ነከሰው አምልጦም ሩጦ ከእሳቱ ውስጥ ገባ ።

ሁለ👈ተኛም የዐሥር ወር ሕፃን እንደ ተሸከመች አንዲትን ሴት አመጧት እርሷም ልጄ ሆይ ላዝንልህ አልቻልኩም አለችው ያ ሕፃንም እናቴ ሆይ በፍጥነት ወደ ዘላለም ሕይወት እንሒድ ይቺን እሳት ከዛሬ በቀር አናያትምና አላት በዚያንም ጊዜ ከልጅዋ ጋር ወደ እሳት ውስጥ ተወረወረች ።
የክርስቲያን ወገኖችም ይህን አይተው እኩሌቶቹ ወደ እሳት እኩሌቶቹም ወደ ሰይፍ ተቀዳደሙ የአይሁድ ጉባኤ ዕጹብ ዕጹብ ብለው እስኪያደንቁ ድረስ ከዚህም በኋላ እሳቱ በሰማይ ውስጥ መልቶ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ታየ ።

የአይሁድ ንጉሥ ፊንሐስም ወደሀገሩ በሔደ ጊዜ ወደ ነገሥታቱ ሁሉ በኃይሉ እየተመካ ላከባቸው የሮሜ ንጉሥ ዮስጢኖስም ሰምቶ ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ ጢሞቴዎስ ላከ በሀገረ ናግራን ለሚኖሩ የክርስቲያን ወገኖች ደማቸውን ይበቀል ዘንድ ለኢትዮጵያ ንጉሥ ለካሌብ መልእክት እንዲልክ ነው ።

የኢትዮጵያ ንጉሥ ካሌብም መልእክት በደረሰው ጊዜ ፈጥኖ ተነሣ በዋሻ ከሚኖር ከአባ ጰንጠሌዎን በረከትን ተቀብሎ ከብዙ ሠራዊት ጋር በመርከቦች ተጭኖ ሔደ በደረሰም ጊዜ የሳባን ንጉሥ የፊንሐስን አገር አጠፋ ሰውም ሆነ እንስሳም ሆነ ሸሽቶ የሚያመልጥ እንኳ ምንም ምን ሳያስቀር አጠፋቸው የናግራንን ከተማ ሕንፃዋን አደሰ የሰማዕታትንም መታሰቢያ አቆመ ። ከዚህም በኋላ ወደ ሮሜ ንጉሥ ዮስጢኖስ ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጢሞቴዎስ የምሥራች ላከ እነርሱም ሰምተው እጅግ ደስ አላቸው #እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_ቢላርያኖስ_ኪልቅያና_ታቱስብያ (ሰማዕታት)

ዳግመኛ በዚህች ቀን ቅዱስ ቢላርያኖስ ሚስቱ ኪልቅያና እኅቱ ታቱስብያ በሰማዕትነት አረፉ ።

ይህም ቅዱስ የሮም አገር ሰው ነው ወላጆቹም አረማውያን ናቸው ከሮሜ አገር ከታላላቆች ሰዎች ልጆች ውስጥ ሚስትን አጋቡት እርሷም ስሟ ኪልቅያ የሚባል ክርስቲያን ናት እጅግም ወደዳት እንደወደዳትም በአወቀች ጊዜ የቀናች የክርስቲያን ሃይማኖትን በግልጽ ታስተምረው ጀመረች እርሱም አምኖ ተጠመቀ ልቡም ብሩህ የሆነ መለኮታዊት ጸጋም አደረችበት እርሱም ታቱስብያ የተባለች እኅቱን አስተማራት እርሷም አምና ተጠመቀች ።

ይህም ቅዱስ ቢላርያኖስ መላእክት ሁልጊዜ ወደርሱ መጥተው የሚሻውን ምሥጢራትን እስከሚገልጡለትና እስከሚያስተምሩት ድረስ ታላቅ ተጋድሎን መጋደል ጀመረ ።

ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስም በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖችን አሠቃያቸው ብዙዎችንም አሠቃይቶ በሰማዕትነት አረፉ ። ይህ ቅዱስ ቢላርያኖስም ከእኅቱ ታቱስብያ ጋር እየዞሩ የሰማዕታትን በድናቸውን እያነሡ የሚቀብሩዋቸው ሆኑ አንድ ክፉ የሆነ ሰውም በአወቀባቸው ጊዜ የንጉሥ ወዳጁ ለሆነ ለአግማስዮስ ሒዶ ነገረው እርሱም ወደርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘ በፊቱም በቆሙ ጊዜ ስለ ሃይማኖታቸው ጠየቃቸው እነርሱም ክርስቲያኖች እንደሆኑ አመኑ ።

ይህም መኰንን ሸነገላቸው ለአማልክት ይሠዉ ዘንድ ብዙ ቃል ኪዳንንም ገባላቸው እነርሱ ግን አልሰሙትም እንዲህም ብሎ አሰፈራራቸው ካልሰማችሁኝና ለአማልክት ካልሠዋችሁ እኔ በጽኑ ሥቃይ አሠቃያችኋለሁ አላቸው እነርሱም ሥቃዩን ከቶ አልፈሩም ።

ጽናታቸውንና ትዕግሥታቸውን አይቶ አንገታቸውን ለሚቆርጥ አሳልፎ ሰጣቸው ራሶቻቸውንም በቆረጧቸው ጊዜ ከዚያ ያሉ ሁሉ ነፍሶቻቸውን በደስታ ሲቀበሉ ብርሃናውያን መላእክትን አዩአቸው መኰንኑም ይህን አይቶ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ። ንጉሡም ሦስት ቀን አሠረው በአራተኛውም ከእሥር ቤት አውጥቶ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው ከቅዱስ ቢላርያኖስና ከሚስቱ ኪልቅያ ከእኅቱ ታቱስብያ ጋር የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_26#ገድለ_አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ እና #ከገድላት_አንደበት)
2025/01/01 02:25:40
Back to Top
HTML Embed Code: