ቅድስት ማርያም ግብፃዊት ከዝሙት ሕይወት ተመልሳ በበረሀ በተጋድሎ ስንት አመት ኖረች?
Anonymous Quiz
20%
50 አመት
31%
45 አመት
21%
65 አመት
29%
47 አመት
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †††
††† እንኩዋን ለጻድቅ ሰው "ቅዱስ ኢያቄም" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††
+*" ቅዱስ ኢያቄም "*+
=>ቅዱስ ሰው ኢያቄም የሰማይና የምድር ንግስት እመቤታችን ድንግል ማርያም አባት ነው:: ቅዱሱ ከቅስራ አባቱ የተወለደ የቅዱስ ዳዊት ዘመድ ሲሆን "ኢያቄም : ሳዶቅ እና ዮናኪር" በሚባሉ 3 ሰሞቹ ይታወቃል::
+ቅዱስ ኢያቄም እንደ ኦሪቱ ሥርዓት አድጎ : ከነገደ ሌዊ የተወለደች : የማጣትና ("ጣ" ጠብቆ ይነበብ) ሔርሜላን ልጅ ሐናን አግብቷል:: ሁለቱም በንጽሕናና በምጽዋት እንደ ሕጉ ቢኖሩም መውለድ የማይችሉ መካኖች ነበሩ::
+በዚሕ ምክንያት ከወገኖቻቸው ሽሙጥን ታግሰው በታላቅ ሐዘን ኑረዋል:: ከጊዜ በሁዋላ ግን ስም አጠራሯ የከበረ : ደም ግባቷ ያማረ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር መረጣቸውና ከተባረከ ሰውነታቸው ድንግል ማርያምን ወለዱ::
+እርሷ "ወላዲተ አምላክ" ተብላ እነርሱን "የእግዚአብሔር የሥጋ አያቶች" አሰኘቻቸው:: ቅዱስ ኢያቄም እመቤታችንን ቤተ መቅደስ ካስገቡ ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ በመልካም ሽምግልና አርፎ ከቅድስት ሐና ጋር በጌቴሴማኒ ተቀብሯል::
+ቅዱሱ ሰው ያረፈበት ዓመት ግልጽ ባይሆንም ድንግል እመቤታችን 8 ዓመት ሲሞላት 2ቱም ቅዱሳን ወላጆቿ በሕይወተ ሥጋ እንዳልነበሩ አበው ነግረውናል:: በማረፍ ደግሞ ቅድስት ሐና ትቀድማለች:: መቃብሩ ዛሬ ድረስ አለ:: ያደለው ከቦታው ደርሶ ይሳለመዋል::
=>አምላካችን ከቅዱስ ኢያቄም በረከት ያሳትፈን::
=>ሚያዝያ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ኢያቄም (የድንግል ማርያም አባት)
2.ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት
3.ቅድስት ቴዎድራ ሰማዕት
4.ቅዱስ አባ መቅሩፋ ጻድቅ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
=>+"+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው . . .
ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::
በውስጥዋም ሰው ተወለደ::
እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:1-6)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

ከ13ቱ ሕማማተ መስቀል ውስጥ የማይገባው የማይቆጠረው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
58%
ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በአይሁድ እግር መረገጡ)፣
9%
አክሊለ ሦክ (የእሾህ አክሊል)፣
27%
ወሪቀ ምራቅ (የምራቅ መተፋት)፣
5%
ተቀሥፎ ዘባን (ጀርባን መገረፍ)፣
ስለ ቅዱስ ኢያቄም ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
18%
ለክብር ባለቤት ክርስቶስ አያት መሆኑ፣
30%
ሚያዝያ 7 ቀን ማረፉ፣
3%
የቅድስት ሐና ባለቤት መሆኑ፣
49%
የሌዊ ነገድ መሆኑ፣
ቅዱስ ኢያቄም ከነገደ_______ነው?
Anonymous Quiz
28%
ከነገደ ሌዊ ከዳዊት ዘር
47%
ከነገደ ይሁዳ ከዳዊት ዘር
15%
ከነገደ አሮን ከዳዊት ዘር
10%
ከነገደ ሴም ከዳዊት ዘር
“የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታቶላቸው፥ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ የሰጠ" ንጉሥ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
2%
ሐና
17%
ሄሮድስ
73%
ጲላጦስ
7%
ቀያፋ
"አርጋኖን" መጽሐፍ የጻፉልን(የደረሱልን) አባት ማን ይባላሉ?
Anonymous Quiz
11%
አባ ሚካኤል
2%
አባ ገብርኤል
83%
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
2%
ቅዱስ ያሬድ
2%
ቅዱስ ኤፍሬም
የ"ሥላሴ" የስም ሶስትነት እንዴት ነው?
Anonymous Quiz
77%
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ
3%
ልብነት፣ ቃልነት፣ እስትንፋስነት
15%
ወላዲ፣ ተወላዲ፣ ሰራጺ
6%
አካል፣ ገጽ፣ መልክ
ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ የማን ደቀ መዝሙር ነበር?
Anonymous Quiz
30%
የወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ
33%
የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ
14%
የወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ
23%
የወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ
✝✝✝ እንኩዋን ለቅዱሳት ደናግል ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝
+*" ቅዱሳት ደናግል "*+
=>ቅዱሳት ደናግሉ አጋሊዝ (አጋሊስ): ኢራኒና ሱስንያ ይባላሉ:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ተሰሎንቄ የምትባል ሃገር ውስጥ ይኖሩ ነበር:: ሦስቱም እጅግ ቆንጆዎችና ከብዙ ወንዶች ዐይን የሚገባ መልክ ቢኖራቸውም የእነርሱ ምርጫ ግን ሰማያዊ ሙሽርነት ነበርና በጾምና በጸሎት ተወሰኑ::
+ለብዙ ዓመታትም ደናግሉ በሚኖሩበት ደብር ውስጥ በቅድስና ኑረዋል:: ከቆይታ በሁዋላ ያ የመከራ ዘመን (ዘመነ ሰማዕታት) ሲመጣ ለጊዜውም ቢሆን ወደ በርሃ ሸሽተው ተቀመጡ::
+ያሉበትን ቦታ የምታውቅ አንዲት ደግ ባልቴት እየሔደች ትጎበኛቸው : በእጃቸው የሚሠሩዋቸውን የተለያዩ እቃወችንም እየሸጠች እኩሉን በስማቸው መጽውታ በተረፈው ለራት የሚሆን ደረቅ ቂጣ ትገዛላቸው ነበር::
+አንድ ቀን ግን አንድ አረማዊ ሰው ተከትሏት መጥቶ በማየቱ 3ቱንም ደናግል ወደ ከሐዲው ንጉሥ አቀረባቸው:: ንጉሡ ሃይማኖታቸውን ቢክዱ የሐብትና የስልጣን ተስፋ እንዳላቸው ነገራቸው:: ደናግሉ ግን በፍቅረ ክርስቶስ በመጽናታቸው ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በዚሕች ቀን አስገድሏቸዋል::
=>የጌታችን በጐ ምሕረቱ በሁላችን ትደርብን:: ከደናግሉ በረከትን ያሳትፈን::
=>ሚያዝያ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳት ደናግል አጋሊዝ: ኢራኒና ሱስንያ
2."150" ቅዱሳን ሰማዕታት (ፋርስ (ኢራን) ውስጥ የተሰየፉ)
3.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://www.tg-me.com/zikirekdusn

Telegram
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
የቅዱሳት አጋሊስ ኤራኒና ሱስንያ ሰማዕትነት እንዴት ነው?
Anonymous Quiz
52%
አንገታቸውን በሰይፍ በመቆረጥ
19%
ወደ እሳት ውስጥ በመጨመር
15%
በድንጋይ በመወገር
15%
በፍላጻ በመነደፍ
ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን
እግሩን አጥቦ እጣቢውን ይጠጣው የነበር አባት ማን ይባላሉ?
እግሩን አጥቦ እጣቢውን ይጠጣው የነበር አባት ማን ይባላሉ?
Anonymous Quiz
27%
አባ በርሱማ
20%
አባ ባውማ
39%
አባ ብሶይ
14%
አባ ገብርኤል