Telegram Web Link
እንደ ኮከብ ብሩህ 16k
መዝሙረ ዳዊት {በቴሌግራም}
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

ሊቀ-መዘምራን ኪነ-ጥበብ ወልደ-ቂርቆስ

✤ እንደ ኮከብ ብረህ ✤

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
💚@mezmurochh💚
💛@mezmurochh💛
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
††† እንኳን ለቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ኤስድሮስ †††

††† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው::
"አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም:: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት::" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ!

በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

ቤተ ክርስቲያናችን ኢትዮዽያዊውን የጐንደር ዘመን ሊቅ ጨምሮ በዚህ ስም የምትዘክራቸው አያሌ ቅዱሳንና ሊቃውንት አሏት::

ዛሬ የምናከብረው ሰማዕቱ ቅዱስ ኤስድሮስ በዘመነ ሰማዕታት የነበረ: ቅዱስ ፃና የሚባል ደግ ጉዋደኛ የነበረው: ሁለቱንም እናቶቻቸው እንደሚገባ ያሳደጉዋቸው የ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖች ነበሩ::

በወጣትነት ዘመናቸው በድንግልና: ቅዱስ ፃና የሠራዊት አለቃ: ቅዱስ ኤስድሮስ ደግሞ የልብስ ዝግጅት ባለሙያ ነበሩ:: ከሚያገኙት ገቢ ለዕለት ጉርስ ብቻ እያስቀሩ ለነዳያን ይመጸውቱ ነበር::
በመከራ ዘመን (ዘመነ-ሰማዕታት) ቅዱሳኑ ያላቸውን ሁሉ ለነዳያን አካፍለው በክርስቶስ ስም መሞትን መርጠዋል::

በዚህች ቀንም አስቀድሞ ቅዱስ ኤስድሮስ አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል::

††† ፈጣሪ ከሰማዕቱ ክብር ያድለን::

††† መጋቢት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ

††† "የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ::
ሰባኪው:- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል::" †††
(መክ. 12:1-9)

††† "ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል:: እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ:: ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ:: ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ::" †††
(1ዼጥ. 4:7)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
††† እንኳን ለቅዱሳኑ የአስከናፍር ቤተሰብ ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ አስከናፍር †††

††† ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት አስከናፍር የሚባል ደግ ክርስቲያን ማርታ የምትባል በሃይማኖትና ምግባር የምትመስለውን ሴት አግብቶ ይኖር ነበር:: እንደ ሕጉና ሥርዓቱ በሥጋ ወደሙ ተወሥነው እንግዳ ቢቀበሉ: ነዳያንን ቢያበሉ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ አርቃድዮስና ዮሐንስ የሚባሉ ልጆችን ሰጣቸው::

አስከናፍርና ማርታ ልጆቻቸውን ጥበብ መንፈሳዊን (ቃለ እግዚአብሔርን) አስቀድመው አስተምረው : ሥጋዊ ጥበብን እዲማሩላቸው ቢልኩዋቸው መንገድ ላይ መርከብ ተሰብሮባቸው ብዙዎቹ ሲሞቱ ወንድማማቾች ግን የመርከብ ስባሪ ወደተለያየ ቦታ አድርሷቸዋል::

አርቃድዮስና ዮሐንስ "ወደ ዓለም አንመለስም" ብለው መነኑ:: ወላጆቻቸው የሆነውን ሰምተው በጭንቅ ሃዘንና ለቅሶ ለብዙ ጊዜ ኑረዋል:: ከዘመናት በሁዋላ ግን የልጆቻቸውን መኖር በራዕይ የተረዱት አስከናፍርና ማርታ ሃብት ንብረታቸውን ለነዳያን አካፍለው ወደ በርሃ መንነው ሔደዋል::

ጥበበኛ እግዚአብሔር አራቱንም አገናኝቷቸው ለብዙ ዓመታት በአንድ ገዳም ውስጥ ተጋድለዋል::
በዚሕች ዕለትም አራቱም ወደ ሰማያዊው ሠርግ ተጠርተዋል::

††† ቸር አምላክ ከቅዱሱ ቤተሰብ በረከት ይክፈለን::

††† መጋቢት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አስከናፍር : ሚስቱ ማርታ : ልጆቹ አርቃድዮስና ዮሐንስ
2.ቅዱስ አርስጥቦሎስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት-የቅዱስ ዻውሎስ ደቀ መዝሙር)
3.ሰባቱ ቅዱሳን ሰማዕታት (ከተለያየ ቦታ ተሰብስበው በክርስቶስ ስም የሞቱ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

††† "እንግዲህ ወንዶች በሥፍራ ሁሉ አለ ቁጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሱ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ:: እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ:: እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ: ወይም በዕንቁ: ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ::" †††
(1ጢሞ. 2:8)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† እንኩዋን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛርን ከሞት ላስነሳበት ደግ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

+*" ሐዋርያ ቅዱስ አልዓዛር "*+

=>ከቀናት በፊት ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ አልዓዛር አረፈ ብለን ነበር:: ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ::

+ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው::
"አዳም ወዴት ነህ" ያለ (ዘፍ. 3:10) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::

+ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር! አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች::
(ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው)

+ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ነውና) : ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ : በ74 ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::

=>የጌታችን ቸርነቱ : የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::

=>መጋቢት 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ (የጌታ ወዳጅ)
2.ቅድስትና ብጽዕት ሰማዕት አስጠራጦኒቃ (ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱዋ)
3.ቅዱሳን ሰማዕታት (የቅ/አስጠራጦኒቃ ማሕበር)
4.እናታችን ቅድስት ጽጌ-ሥላሴ (ኢትዮዽያዊት)
5.ቅዱስ አስቃራን ሰማዕት
6.አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
4.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
5.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
6.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት

=>+"+ ጌታ ኢየሱስም 'ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት . . . ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ 'አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና' ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም 'ፍቱትና ይሂድ ተውት' አላቸው:: +"+ (ዮሐ. 11:40-44)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
<<< የጌታ ወዳጅ : ጻድቅና ሐዋርያ የአልዓዛር መቃብር >>>

{{ የዛሬ 1974 ዓመት : በዚህች ቀን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁን ቅዱስ አልዓዛርን በአምላካዊ ጥሪ ከሞት አስነስቶታል:: }}

<< የጌታ ቸርነቱ : የአልዓዛር በረከቱ ይደርብን !! >>
https://www.tg-me.com/zikirekdusn
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

           #መጋቢት ፳፩ (21) ቀን።

እንኳን ለታላቁ አባት የአባታችን #የአቡነ_የተክለ_ሃይማኖት ገዳም "ደብረ ሊባኖስ" በስማቸው ለተሰየመላቸው፤ ከዐለት ላይ ውኃ እያፈለቁ ድውያንን ለሚፈውሱት ለታምረኛው አባት፤ #ለአባ_ሊባኖስ (ዘመጣዕ) ዓለምን ፍጹም በመናቅ ለመነኑበት ነው ለመታሰቢያ ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

                          
#አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ፦ እርሳቸውም የአባታችን የተክለ ሃይማኖት ገዳም "ደብረ ሊባኖስ" በስማቸው የተሰየመላቸው ናቸው፡፡ አባ ሊባኖስ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት ይባላሉ፡፡ እነርሱም በወርቅና በብር እጅግ የበለጸጉ ሮማዊ ናቸው፡፡ ልጃቸውን አባ ሊባኖስን በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው ካሳደጓቸው በኋላ ዕድሜያቸው ሲደርስ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያጋቧቸው ዘንድ ከቁስጥንጥንያ አገር ሚስት ባመጡለት ጊዜ እርሱ ግን ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ወደጫጉላቤትም መግባትን እምቢ አለ፡፡ በዚህም ጊዜ ነቢዩ ሳሙኤልን እንደጠራው አባታችንንም እግዚአብሔር ሦስት ጊዜ በስማቸው ጠራቸውና "ከአባትህ ተለይ አንተ የመንግሥተ ሰማያት ሙሽራ ነህ እንጂ የዚህ ምድራዊ ዓለም ሙሽራ አይደለህም" አላቸው፡፡ አባታችንም "ወዴት እሄዳለሁ? ምንስ ላድርግ?" ባሉ ጊዜ ወዲያው የታዘዘ መልአክ በሌሊት መጥቶ ከአባታቸው ቤት አውጥቶ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው፡፡ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስም ለአባ ሊባኖስ በዓት በመስጠት ገዳመ ሥርዓትን፣ አስኬማ መላእክትን፣ ቅናተ ዮሐንስን አስተምረዋቸው አመነኰሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡፡

ከዚህም በኋላ ያ ከአባታቸው ቤት ወስዶ አባ ጳኩሚስ ገዳም ያደረሳቸው ያ መልአክ ድጋሚ ተገለጠላቸውና "ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድለህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ" አላቸው፡፡ ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአክሱም ተቀመጡ፡፡ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው ከዓመታት ቆይታ በኋላ ተመልሰው አክሱም ሄዱ፡፡ በአክሱምም 7 የተለያዩ ጸበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ዕውራንን አበሩ፡፡ በዓታቸውንም ከአክሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ጸበል "ተራ ውሃ ነው" ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች፡፡ ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጥጧት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ፡፡ ሴትዮዋም ስትጮህ አባ ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል፡፡ ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ "አምላከ አባ ሊባኖስ" ብሎ አመሰገነ፡፡

ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው "ምትሃት ነው የሚያሳየው" ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው፡፡ አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው፡፡ ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው፡፡ አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአክሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ፡፡ በዚያም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል፡፡ በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው "አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን፣ በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን ጸልይን" ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ፡፡ አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው፡፡ ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ፡፡

ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ፡፡ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው "ሊባኖስ ሆይ! ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም፣ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ጻድቅ ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው፣ የብዙ መነኰሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል" አላቸው፡፡ በኋላ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያጸኑ ቦታው ግን "ደብረ ሊባኖስ" ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ፡፡ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አክሱም ወሰዳቸው፡፡ ከዚያም "ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ" አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ፣ ለምፃሞችን እያዳኑ፣ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ "ሊባኖስ ዘመጣዕ" የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ፡፡ በወቅቱ የነበረው ዐፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡

ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡ ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።

@sigewe

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886


https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKw
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

           #መጋቢት ፳፩ (21) ቀን።

እንኳን #የክብር_ባለቤት_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሙታን ለይቶ ወደ አስነሣው ወደ አልዓዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ለሔደበት፣ አምላክ ለወለደች #ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም ለወራዊ በዓሏ መታሰቢያና ለማቱሳላ ልጅ #ለቅዱስ_ላሜህ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓሉ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ለከበሩ ሰማዕታት #ከቅዱሳን_ቴዎድሮስና_ከጢሞቴዎስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

                           
በዚችም ዕለት የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሙታን ለይቶ ወደ አስነሣው ወደ አልዓዛር ቤት ከቀደ መዛሙርቱ ጋራ ሔደ በዚያም ምሳ አዘጋጁለት ማርታም ምግብ በማቅረብ ታገለግላቸው ነበር። ሁለተኛዋ ማርያም ግን እግሮቹን ሽቱ እየቀባች በጸጒሩዋ ታሸው ነበር።

ጌታችንም አመሰገናት "እርሷ ለመቀበሪያዬ ጠብቃዋለች" በማለት ስለ ቅርብ ሞቱ አመለከተ። ዳግመኛም "ድኆች ሁል ጊዜ ከእንተ ጋራ ይኖራሉ እኔ ግን ከእናንተ ጋራ አልኖርም" አለ በዚህም ተሰቅሎ የሚሞትበት ጊዜ ቅርብ መሆን ያመለክታል ለርሱም ክብር ከሃሊነት ገንዘቡ ስለሆነ ምስጋና ይገባዋል ለዘላለሙ አሜን።

                             
በዚችም ቀን አልዓዛርን ሊገሉት የካህናት አለቆች ተማከሩ ገናና ስለሆነች ምልክት በእርሱ ምክንያት ብዙዎች በጌታችን የሚያምኑ ሁነዋልና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

                           
#የማቱሳላ_ልጅ_ቅዱስ_ላሜህ፦ እርሱም አንድ መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኑሮ ኖኅን ወለደው ከወለደውም በኋላ አምስት መቶ ስልሳ አምስት ዓመት ኖረ። በድምሩ ሰባት መቶ አርባ ሰባት ዓመት ኖረ። እግዚአብሔርንም አገልግሎት በሰላም ዐረፈ። የማቱሳላ ልጅ የቅዱስ ላሜህ የፈጣሪው በረከት ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት 21 ስንክሳር።

                           
#የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ሚጥ ገጸከ እምኃጢአትየ። ወደምስስ ሊተ ኵሎ አበሳየ። ልበ ንጹሕ ፍጥር ሊተ እግዚኦ"። መዝ 50፥9-10። የማሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥1-12።

                             
#የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ 44፥9-10። የሚነበቡት ወንጌል ኤፌ 2፥13-ፍ.ም፣ 2ኛ ዮሐ 1፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 7፥40-51። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ1፥20-39። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ወይም የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። በሁላችንም ይሁንልን።

@sigewe

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886


https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKw
2024/09/29 21:35:58
Back to Top
HTML Embed Code: