Telegram Web Link
🛑 አዲስ የንስሃ መዝሙር "እንደ እኔ የማርከው ማንን ነው" | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
🙏 '' እንደ እኔ የማርከው ''🙏


እንደኔ የማርከው ማንን ነው
እንደኔ ይቅር ያልከው ማንን ነው
ሀጢያቱ በዝቶበት በደሉ በዝቶበት
የማርከው እንደኔ ከቶ ማነው/2/



በሞገስ አስጊጠህ በዜማ ቃኘኸኝ
ፊትህ ምታቆመኝ ጌታዬ እኔ ማነኝ
ለኔ ያደረከው አቤት ደግነትህ
ምረኸኝ ምረኸኝ አያልቅም ምህረትህ
        አይተኸኝ በምህረት/2/
        ዛሬ አለሁኝ በህይወት

አዝ__

የምስጋና መስዋዕት ማቅረቢያ መሰዊያ
ልቤ ንጹህ ባይሆን ጸጋዬን አለቀማህ
ትቀበለኛለህ ሞልተኽ በጎደለው
እኔን የወደደ እንዳንተ ማን አለ
         አይተኸኝ በምህረት/2/
         ዛሬ አለሁኝ በህይወት

አዝ__

በምኞት ተስቤ ለሀጢያት ተሽጬ
በመስቀልህ ስራ ከሞት ጣር አምልጬ
አንተ እንዳዳንከው ሰው መሆን ቢያቅትም
እኔ ተስፋ ብቆርጥ ተስፋ አትቆጥርብኝም
         አይተኸኝ በምህረት/2/
         ዛሬ አለሁኝ በህይወት

አዝ___

በኖርኩበት ዘመን የቁጣ ልጅ ሆኜ
ምዕራፉ ተዘጋ በአንተ በአዳኜ
ከኔ ምንም ሳይኖር አንተ ሁሉን ሆነህ
ሰገነት ታየሁኝ ስለኔ ተንቀህ
         አይተኸኝ በምህረት/2/
         ዛሬም አለሁኝ በህይወት

አዝ___

እኔን ማረኝ ከምል ከፊትህ ወድቄ
በሌላው ፈራጅ ነኝ እራሴን አጽድቄ
መመልከት ባልችልም የአይኔን ምሰሶ
ያኖረኝ ፍቅርህ ነው ይህ ሁሉ ታግሶ
         አይተኸኝ በምህረት/2/
         ዛሬም አለሁኝ በህወት



🛑 አዲስ የንስሃ መዝሙር
"እንደ እኔ የማርከው ማንን ነው"
| ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ✞

† ታላቁ አባ መርትያኖስ †

=>አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ዕለት የተጋዳይ መነኰስ የአባ መርትያኖስ ሥጋው ከአቴና አገር ወደ አንጾኪያ የፈለሰበት ሆነ። እርሱም ሽንግላ በኃጢያት ልትጥለው በወደደች ጊዜ ከአመንዝራ ሴት ከተፈተነ በኋላ እርሱ ግን መንኵሳ በገድል እስከ ተጸመደች ድረስ ስቦ ወደ ንስሓ መልሷታል።

«« ከዚህም በኋላ መኖሪያውን ትቶላት ከሀገር ወደ ሀገር የሚዞር ሆነ ከአቴና አገርም ደርሶ በዚያ ጥቂት ቀን ኖረ ጥቂትም ታመመና በሰላም አገፈ ዜናው በግንቦት በሃያ አንድ ቀን እንደተጻፈ።

የከበረ ቴዎድሮስም ለአንጾኪያ ሀገር በከሀዲው የፋርስ ንጉሥ ዘመን ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ይህ አባት የካህናት አለቆችንና ምእመናንን ልኮ ሥጋውን ከአቴና አፍልሰው ወደ አንጾኪያ ከተማ አመጡት በምስጋናም እየዘመሩ አክብረው ተቀበሉት ሊቀ ጳጳሳቱም ተሳለመው በሣጥንም አድርጐ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖረው። በዚችም ዕለት በዓልን አደረጉለት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

=>የካቲት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ታላቁ አባ መርትያኖስ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

=>+"+ . . . በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ:: በመጋዝ ተሰነጠቁ:: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: +"+ (ዕብ. 11:36)

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለጻድቁ "አቡነ ክፍለ ማርያም" እና ለሰማዕቱ ቅዱስ "ፊልሞን መዓንዝር" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" አቡነ ክፍለ-ማርያም "*+

=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ክፍለ-ማርያም በሐዋርያዊ አገልግሎቱ የተመሠከረለት: ለበርካታ ዓመታት በጾምና በጸሎት በአቱን አጽንቶ የኖረ: ከቅድስናው የተነሳ መላዕክት ሰማያዊ ኅብስት ይመግቡት: ውሃም ከአለት ላይ ይፈልቅለት የነበረ አባት ነው::

+በዘመኑም ረሃብ ነበርና እርሷ ሳታውቀው እናቱን በረሃብ ጠውልጋ ቢያያት በጣም በማዘኑ እንዲባርከው ከቀረበለት የሰንበት ቁርስ ለእናቱ አድልቶ ብዙ ሰጣት:: በዚሕ ምክንያት መልዐኩም ሰማያዊ ኅብስቱን አስቀረበት: ምንጩም ደረቀች::

+ጥፋቱ የገባው አባ ክፍለ-ማርያም ለ11 ዓመታት ንስሃ ገብቶ እግዚአብሔር መልሶለታል:: ከብዙ የገድል ዓመታት በሁዋላም በዚህች ቀን ተሠውሯል::

+*" ቅዱስ ፊልሞን ሰማዕት "*+

=>ይህን ቅዱስ "ፊልሞን መዓንዝር" ብሎ መጥራቱ
የተለመደ ነው:: እርሱ በቀደመ ሕይወቱ አዝማሪ (ዘፋኝ)
ነበርና:: ዘፋኝነት (አዝማሪነት) ደግሞ በክርስትና
ከተከለከሉ ተግባራት አንዱና ዋነኛው በመሆኑ ዘፈን
(ሙዚቃ) መስማትም ሆነ ማድመጡ ኃጢአት ነው::

+ነገር ግን ሁሉ እንዲድን የሚፈቅድ ጌታችን ጥሪውን ወደ
ሁሉም ሰው በየጊዜው ይልካል:: ቅዱስ ፊልሞንም
የክርስቶስ ጥሪ የደረሰው በከንቱ የዘፋኝነት (የአዝማሪነት)
ኑሮ ውስጥ ሳለ ነው:: ነገሩ እንዲህ ነው:-

+በ3ኛው ክ/ዘ መጨረሻ (በ290ዎቹ) አርያኖስ የሚባል
ሹም በግብጽ (እንዴናው) ክርስቲያኖችን ጨፈጨፈ::
ባለማወቅም ክርስቶስን የሚያመልኩ ሚሊየኖችን በሰይፍ
በላቸው:: ከዚህ ድርጊቱ መልስ ደግሞ በጣዖቱ (አዽሎን)
ፊት እያስዘፈነ ከንቱነትን ይሰዋ : ይዝናናም ነበር::

+ከዘፋኞቹ መካከል ደግሞ ይህ ፊልሞን አንዱ ሆኖ
ለዘመናት በፊቱ ተጫወተለት:: አንድ ቀን ግን እንዲህ
ሆነ:: አስቃሎን የሚባል ቅዱስ ክርስቲያን ለጣዖት
እንዲሰዋ ታዘዘ::

+ይህ አስቃሎን (አብላንዮስም ይባላል) ወንድሙን
ፊልሞንን ያድነው ዘንድ ተጠበበ:: ወደ ፊልሞን ሒዶ "እኔ
ገንዘብ እሰጥሃለሁ:: የእኔን ልብስ ለብሰህ : እኔን መስለህ
ለጣዖት ሰዋልኝ" አለው:: አስቃሎን ይህንን ያለው
ለጥበቡ ሲሆን ፊልሞን ግን "ገንዘብ ካገኘሁ" ብሎ
የባልንጀራውን ልብስ ተሸፋፍኖ ወደ ጣዖቱ ፊት ቀረበ::

+ያን ጊዜ ተሸፍኖ መስዋዕት ማቅረብ ክልክል ነውና ሹሙ
አርያኖስ ግለጡት ሲል አዘዘ:: ቢገልጡት ፊልሞን ሁኖ
ተገኘ:: መኮንኑ ገርሞት "ምን እያደረክ ነው?" ቢለው "እኔ
ክርስቲያን ነኝ" ሲል አሰምቶ ተናገረ::

+ለጊዜው ሁሉም እየቀለደ መስሏቸው ነበር:: ፊልሞን
ግን ይህንን ያለው ከልቡ ነው:: ምክንያት በቅዱስ
አስቃሎን ልብስ ተመስሎ መንፈስ ቅዱስ ልቡን ለውጦለት
ነበር:: ተገልጦ ቀና ሲልም ቅዱሳን መላእክት ከበውት
አይቶ ልቡ ጸንቶለታል::

+ሹሙ አርያኖስም የቀልዱን እንዳልሆነ ሲያውቅ
"ታብዳለህ?" ቢለው ፊልሞን "ምን አብዳለሁ! ዛሬ ገና
ከእብደቴ ሁሉ ዳንሁ እንጂ" ሲል መልሶለታል:: አሕዛብ
ሁሉ እያዩም በዚያች ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ በደመና
አምሳል ወርዶ አጥምቆታል::

+በሆነው ሁሉ የተበሳጨው ሹሙም ቅዱስ ፊልሞንን
ከክርስቶስ ፍቅር ይለየው ዘንድ ደበደበው : ገረፈው :
ጥርሱን አረገፈው : ደሙንም መሬት ላይ አፈሰሰው::
በዚህ ሁሉ ግን ጸና:: ቅዱስ አስቃሎንም ፈጥኖ መጥቶ
በመከራው መሰለው::

+በመጨረሻም 2ቱም ቅዱሳን በቀስት ተነድፈው ይገደሉ
ዘንድ ተፈረደባቸው:: ነገር ግን ለእነሱ የተወረወረ ቀስት
መንገዱን ስቶ የሹሙን (የአርያኖስን) ዐይን በማጥፋቱ
ወታደሮቹ በንዴት 2ቱንም ሰይፈው ገድለዋቸዋል::

+ዐይኑ የጠፋበት አርያኖስም ስቃዩ ሲበዛበትና
ከሚያመልካቸው የረከሱ ጣዖታት መፍትሔ ሲያጣ
ከቅዱሳኑ ደም ተቀባ:: ዐይኑም ፈጥኖ በራለት:: በዚህም
ምክንያት ምድራዊ ሹመቱን : ሃብት ንብረቱን : ትዳርና
ቤቱን : ጣዖት አምልኮውን ትቶ በክርስቶስ አምኖ
ለሰማዕትነት በቅቷል::

=>አምላከ ቅዱሳን በወዳጆቹ አማላጅነት
የምናስተውልበትን አዕምሮ አይንሳን:: በረከታቸውንም
ያድለን::

=>የካቲት 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ክፍለ-ማርያም ዘዲባጋ (የተሰወረበት)
2.አቡነ ገብረ-መርዐዊ ዘአግዶ (ኢትዮዽያዊ)
3.ቅዱስ ፊልሞን መዐንዝር (ከአዝማሪነት በክርስቶስ አምኖ ለሰማዕትነት የበቃ ቅዱስ ሰው)
4.ቅዱስ አስቃሎን አናጉንስጢስ (ሰማዕት)
5.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት (የታላቁ ሐዋርያዊ አትናቴዎስ ደቀ መዝሙር)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
4.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ
5.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
6.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት

=>+"+ ስትጦሙም እንደ ግብዞች አትጠውልጉ . . . አንተ ግን ስትጦም በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ: ፊትህንም ታጠብ:: በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ያስረክብሃል:: +"+ (ማቴ. 6:16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
☞አርኬ ዘአባ መርትያኖስ (መነኮስ ኃያል) የካቲት ፲፱፦

ሰላም ለፍልሠተ ሥጋከ እምሃገረ አቴና ሰቂማ፤
ኀበ አንጾኪያ መካነ ሰማዕት እስመ ከማሁ ስማ፤
መርትያኖስ ኃያል ልቡሰ ዐቢይ ግርማ፤
በከመ አድኃንካ ለፎጢና እምነ ርጉም መስቴማ፤
ሥረይ ኃጢአታ ለነፍስየ ዘማ!

(ዝክረ ቅዱሳን ፥ ርቱዓነ ሃይማኖት)
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://www.tg-me.com/zikirekdusn

በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

          #የካቲት ፳ (20) ቀን።

እንኳን #ለኢትዮጵያውያን_ጻድቅ ውኃ ከዓለት ድንጋይ ላይ እያፈለቁ አሕዛብን ሁሉ እያስተማሩ ያጠምቁ ለነበረ፤ ኅብስትም ከሰማይ እየወረደላቸው ሕዝቡን ያቆርቡ ለነበረ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ክፍለ_ማርያም_ዘድባጋ ከዚህ ዓለም እንደነ #ቅዱሳን_ሄኖክና_ኤልያስ ከሞት ለተሰወሩበት በዓልና #ለአባ_ገብረ_መርዓዊ_ዘአግዶ_ገዳም ለመታሰቢያ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።

                             
#ለአቡነ_ክፍለ_ማርያም_ዘድባጋ፦ ትውልዳቸው እንደርታ ሲሆን በ14 ዓመታቸው መንኵሰው፡ መንነው በቅተው ሲኖሩ በአንድ ወቅት ወደ አክሱም ሄዱና ወላጆቻቸው ካሉበት ደረሱ። ከቅዳሴ በኋላ መክፈልት ቆርሰው ሲያድሉ ወላጅ እናታቸው ከስተውና ጠቁረው ስላዩአቸው ለእናታቸው አዳልተው በብዙ ሰጧቸው። እናትየው ግን ጻድቁ የሰሩትን አያወቁም ነበር። ጻድቁ ከብቃታቸው የተነሳ መና ከሰማይ አየወረደላቸው ከዓለትም ላይ ውኃ እያፈለቁ ይጠጡ ነበር። አድሎ ስላደረጉ ግን በዚህ ድርጊታቸው እግዚአብሔር ተቆጥቷቸው የሰጣቸውን ይህን ጸጋውን ነሳቸው። አቡነ ክፍለ ማርያምም ይህን ባወቁ ጊዜ "ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ" ብለው ከሰው ሳይገናኙ ዋሻ ገብተው ድፍን 11ዓመት በለቅሶና በዋይታ እግዚአብሔርን ለምነው ነው ይቅር ተብለው የቀደመ ጸጋቸውና ክብራቸው የተመለሰላቸው።

ከዛ በኋላ ውኃ ከደረቅ ጭንጫ ላይ እያፈለቁ አሕዛብን ሁሉ እያስተማሩ ያጠምቁ ጀመር። ኅብስትም ከሰማይ እየወረደላቸው ሕዝቡን ያቆርቡ ጀመር። ጻድቁ በመጨረሻ በየካቲት20 ቀን እንደነ ሄኖክና ኤልያስ ዐርገዋል እንጂ በምድር ሞት አልቀመሱም። ትልቅና አስደናቂ ገድላቸው በአክሱም ይገኛል። ከአቡነ ክፍለ ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።

@sigewe

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL    
                         
"በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ  አሜን"።

            #የካቲት ፳ (20) ቀን።

እንኳን #መኰንን_አርያኖስን_ለሚያጫውተው ለበገና ደርዳሪው #ለቅዱስ_ፊልሞንና ለጓደኛው #ለአናጉንስጢስ_ለቅዱስ_አስቃሎን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለእስክድርያ አገር ሃያ አንደኛ ሊቀ ጳጳስ #ከሐዋርያው_ቅዱስ_አትናቴዎስ በኋላ ለተሹመት #ለአባ_ጴጥሮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከማታሰቡ፦ ከከበሩ #ከቅዱሳን_ባስልዮስ_ከቴዎድሮስና #ከጢሞቴዎስ_በእስክድርያ አገር በሰማዕትነት ከዐረፉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
                          

                           
በገና ደርዳሪው #ቅዱስ_ፊልሞን ጓደኛው #ለአናጉንስጢስ_ለቅዱስ_አስቃሎን ፦ በአንዲትም ዕለት አርያኖስ አናጉንስጢስ አስቃሎንን ጠርቶ "ለአጵሎን ሠዋ" አለው አስቃሎንም ወደ ፊልሞን ሒዶ "በእኔ ፈንታ ብትሠዋ አራት የወርቅ ዲናር እስጥሃለሁ" አለው  ፊልሞንም "ልብስህን ስጠኝና ተሸፋፍኜ በአንተ ፈንታ እሠዋለሁ" አለው። በገባም ጊዜ አውቀውት "ምን ሆንክ" አሉት ፊልሞንም "በክርስቶስ የማን ክርስቲያን ነኝ"አላቸው። አርያኖስም "በሕይወት እንድትኖር ለአማልክት ሰዋ" አለው። "ፊልሞንም በክርስቶስ ስም ከመሞት በቀር ሕይወት የለም" አለው። አርያኖስም "ጥምቀትን ሳታገኝ ፈጥኜ እገድልሃለሁ ተስፋህን ታጣለህ" አለው። ፊልሞንም ሰምቶ የክርስትና ጥምቀትን ያድለው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ በዚያንም ጊዜ ከሰማይ ብሩህ ደመና መጥቶ አጠመቀው። አርያኖስም አፍሮ ቢመለስ ብሎ ሦስት ወታደሮች እንዲጸፋት አዘዘ ፊልሞንም "የእግዚአብሔር መላእክት ስለ እኔ ደስ ሲላቸው አያለሁና ከዚህ የከፋ ቢጻፋኝም አልፍርም" አለ። አርያኖስም ባላ ባለው ግንድ ላይ ሰቅለው በፍላፃዎች ይነድፉት ዘንድ አዘዘ ግን ምንም የነካው የለም ፍላፃውም እንዳልካው ለአርያኖስ ነገሩት ዳግመኛም እርሱ እንደ ቆመ ይነድፉት ዘንድ አዘዘ አንዲትም ፍላፃ ተመልሳ፡ የአርያኖስን ዐይን ነድፋ ዐሳወረችው በዚያን ጊዜ ከተሰቀለበት አውርደው ከአናጉንስጢስ አስቃሎን ጋር ራሱን እንዲቆርጡ አዘዘ ገድላቸውን፡ ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊል የካቲት20 ተቀበሉ።

መኰንኑም በፍላፃው ሕመም በተሠቃየ ጊዜ ከቅዱሳን ደም ወስዶ ከዐይኑ ውስጥ እንዲጨምር ሰዎች መከሩት ይህንንም ሲያደርግ ዳነ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አመነ እሥረኞችንም ሁሉ ፈታቸው እርሱም መጋቢት ስምንት ቀን በዲዮቅልጥያኖስ እጅ በሰማዕትነት ዐረፈ። የሰማዕታትም በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን።
                         
                           
#አባ_ጴጥሮስ፦ የእስክድርያ ሃያ አንደኛ ሊቀ ጳጳስ ነው። ይህንንም ቅዱስ ከሐዋርያዊ አትናቴዎስ በኋላ በሹመቱ ወንበር በተቀበጠ ጊዜ ከንጉሥ ዳርዮስ ከከሀዲ አርዮስ ወገኖች ብዙ መከራ ደርሶበታል። ሊገሉትም በፈለጉ ጊዜ ሸሽቶ ሁለት ዓመት ያህል ተሠወረ አርዮሳውያንም ሉቅዮስ የተባለ ከሀዲውን ሰው በእርሱ ፈንታ በወንበሩ ላይ አስቀምጠው ሁለት ዓመት ኖረ። ከዚያም በኋላ ሃይማኖታቸው የቀና ምዕመናን ሁሉም ተነሥተው አርዮሳዊ ሉቅዮስን አሳደዱትና ይህን አባት ጴጥሮስን ወደ መንበረ ሢመቱ መለሱት አርዮሳውያንንም በመጣላት እያወገዛቸው እያሳደዳቸው ሰባት ዓመት ኖረ። ከዚህም በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም የካቲት20 ዐርፎ ወደ ዘላለም ዕረፍት ሔደ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጴጥሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት 20 ስንክሳር።
                           
                            
"#ሰላም_እብል_ለባስልዮስ_ብፁዕ። #ወቴዎድሮስ_ካዕለ#ወጢሞቴዎስ_ሣልስ ቅኑታነ ኃይል ወጽንዕ። ውስተ ቤተ መረዓ አምሳለ እሡራን ሰብእ። ዘተጸዋዕክሙ ኅቡረ ለስምዕ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_20


                           
#የዕለቱ_ምስባክ፦ "ኵሉ ማዕበልከ ወሞገድከ እንተ ላዕሌየ ኃለፈ። ዓልተ ይኤዝዝ እግዚአብሔር ሣህሎ ወሌሊተ ይነግር። እምኀቤየ ብፅዐተ ሕይወትየ ለእግዚአብሔር"። መዝ 41፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 5፥1-6፣ ይሁ 1፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 14፥21-24። የሚበበው ወንጌል ማቴ 16፥1-5። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የጾም፣ የጸሎትና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። 
                               
@sigewe

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL    
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

+"+ እንኩዋን ለቅዱስ "አናሲሞስ ሐዋርያ" እና ለእመቤታችን "ቅድስት ድንግል ማርያም" በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" ድንግል ማርያም "*+

=>የአምላክ እናቱ እመ-ብርሃን ድንግል ማርያም:-
*በ3 ወገን (በሥጋ: በነፍስ: በልቡና) ድንግል
*በ3 ወገን (ከኀልዮ: ከነቢብ: ከገቢር) ንጽሕት
*ሳትጸንስ: በጸነሰች ጊዜና ከጸነሰች በሗላ ድንግል
*ጌታን ሳትወልድ : በወለደችው ጊዜና ከወለደችው በሗላ ድንግል ስትሆን እናትም ድንግልም መሆኗን አምነን እመሰክራለን::

+እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ በላይ ክብርትና ንዕድ ናት:: ሊቃውንት አበው እንዳስተማሩን በዚህ ዕለት እንዲህ ብለን እንጸልያለን::
"ረስዪ ፍና ትሕትና አእጋርየ ይሑሩ:
ትዕቢትሰ ለአምላክ ጸሩ"
(እመቤቴ ሆይ ትዕቢትን አምላክ ይጠላልና እግሮቻችን በትሕትና እንዲሔዱ አድርጊ)

+*" ቅዱስ አናሲሞስ ሐዋርያ "*+

=>በዘመነ ሐዋርያት ምስጉን ከነበሩ አበው አንዱ ቅዱስ አናሲሞስ ነው:: ስለ ቀና አገልግሎቱና መልካም እረኛነቱ አባቶቻችን ሐዋርያት አብዝተው በቀኖናቸው መስክረውለታል:: እርሱ ከኃጢአት ኑሮ ወደ ዘለዓለማዊ የቅድስና ሕይወት መጥቷልና::
¤ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

=>በሮም ከተማ የሚኖር ፊልሞና የሚባል አንድ ባለጸጋ ነበር:: ይህ ሰው በስብከተ ቅዱስ ዻውሎስ አምኖ ከርስቲያን ሆነና በመንፈሳዊ አገልግሎት ተጠመደ:: ነገር ግን ከአገልጋዮቹ መካከል ያላመነ አንድ ሰው ነበር:: "ተጽዕኖ አላደርግበትም" ብሎ ዝም ይለዋል:: ግን ክርስትና እንዲገባው ለተልዕኮ መንፈሳዊ በሚሔድበት ሥፍራ ያስከትለው ነበር::
+አገልጋዩ ግን በመለወጥ ፈንታ ሌብነትን ለመደ:: ይባስ ብሎም የአሳዳሪውን (የፊልሞናን) ገንዘብ ሠርቆ ወደ ሮም ጠፍቶ ተመለሰ:: ቅዱስ ፊልሞናም ለገንዘቡ ሳይሆን ለሕይወቱ አዘነ::

+ያ ሠርቆ የጠፋው አገልጋይ ግን በሮም ከተማ ሲመላለስ ስብከተ ወንጌልን ይሰማል:: ሰባኪው ደግሞ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ነበር:: ቁጭ ብሎ ሲማርም ልቡናው በርቶለት ተጸጸተ:: ከሐዋርያውም ዘንድ ቀርቦ ኃጢአቱን ተናዞ ተጠመቀ::
+ከዚያች ዕለት ጀምሮም ብርቱ ክርስቲያን ሆነ:: በጥቂት ጊዜም የተጋ ሰባኪ : ርሕሩሕ እረኛ ሆነ:: ፈጣሪውንም ደስ አሰኘ:: ነገር ግን ስለ አንድ ነገር ፈጽሞ ያዝን : ይተክዝም ነበር::

+የድሮ አሳዳሪው ቅዱስ ፊልሞና እንዳዘነበት እያወቀ ዝም ማለት ባያስችለው ለመምህሩ ቅዱስ ዻውሎስ ነገረው:: ያን ጊዜም ሐዋርያው በእሥራትና በግርፋት ይሰቃይ ነበር:: በሮም ሳለም አጭር ክታብ (ደብዳቤን) ጽፎ ለዚህ ደቀ መዝሙሩ ሰጠውና ወደ ቀድሞ አሳዳሪው ወደ ፊልሞና ላከው::
+ይህች ጦማር (ክታብ) ዛሬም ድረስ ከ81ዱ አሥራው መጻሕፍት : ከቅዱስ ዻውሎስ 14 መልዕክታት አንዷ ሆና ተቆጥራ እንጠቀምባታለን:: ክታቧ እጅግ አጭር ብትሆንም ምሥጢሯ ግን ሰፊ ነው::

+ያ የተላከ ክርስቲያንም ያችን ክታብ ወስዶ ለቅዱስ ፊልሞና (ለቀድሞ አሳዳሪው) አስረከበ:: ቅዱስ ፊልሞናም በደስታ አቅፎ ሳመው:: ቀድሞውንም ያዘነ በወጣቱ አገልጋይ የነፍስ እዳ እንጂ በገንዘቡ አልነበረምና:: ያ ተላኪ ሰውም በአካባቢው ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ቅዱስ ዻውሎስ ተመልሷል:: ደቀ መዝሙሩ ሆኖም ብዙ አገልግሏል::
+#ቅዱስ_አናሲሞስ ማለት . . . የቀድሞ የሰው አገልጋይ . . . ዛሬ የክርስቶስ ባሪያ . . . ቀድሞ ሠራቂ . . . ዛሬ ግን ለመንጋው የሚራራ ሰው የሆነው ይህ ክርስቲያን ነው::

+በ67 ዓ/ም ቅዱስ ዻውሎስ መሰየፉን ተከትሎ እርሱንም አሳድደው : አሰቃይተው : ጭኑንም ሰብረው አሕዛብ ገድለውታል:: በሰማይም የሐዋርያነትና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጅቷል:: (ጢሞ. 4:6-8, ፊልሞና 1:1-25)
=>አምላከ ቅዱሳን የአናሲሞስን መመለስ : ንስሃና በረከት ያድለን::

=>የካቲት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ቅዱስ አናሲሞስ ሐዋርያ (የቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ ደቀ መዝሙር ሲሆን ከ14ቱ መልዕክታት አንዱ የሆነው 'ወደ ፊልሞና' የተጻፈው በዚህ ቅዱስ ምክንያት ነው:: ፊል. 1:11)
2.አባ ዘካርያስ ዘሃገረ ስሃ
3.አባ አካክዮስ ጻድቅ
4.አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት
5.አባ ገብርኤል (የኢትዮዽያ ዻዻስ)

=>ወርኀዊ በዓላት

1.ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ

=>+"+ ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . . አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ:: የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ:: በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ:: +"+ (ኢሳ. 62:1-3)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
#የእርዳታ_ጥሪ_በዕለተ_ቀኗ ስለ የጭንቅ ደራሿ #እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም እና #ቸሩ_መድኃኔዓለም_ዓለም_። ሁላችን የተዋሕዶ ልጆች #ሼር_ሼር_ሼር_እናድርግ

ውድ የቴሌግራሜ ቻናል ተከታታይ ተወዳጅ ቤተሰቦች እንዴት አመሻችሁ #በሰሜን_ሸዋ_ሀገረ_ስብከት_በግሼ_ወረዳ ለሚገኘው ለጥንታዊው በእምዬ በዐፄ ምኒልክ እና በግብጻዊው ጳጳስ እንደ ገዳምነት ተመስርቶ ለነበረው #ለግጅማ_ደብረ_ሐመልማል_መድኃኔዓለም እና ለምትገኘው ለጥንታዊቷ #ጎራዶ_ወይራ_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን ቦታው ገጠራማ እና መብራት የሌለው ስለሆነ የአጥቢያው ምዕመን ጥቂት አርሶ አደር ምንም ገቢ የሌለው በመሆኑ ለአገልግሎት መጠቀሚያ የሚሆኑ ነገሮች ከዚህ በታች የተዘሩዘሩት ነገሮች ለሁለቱ ቤተ ክርስቲያን ምን የሌላቸው ስለሆነ፦

1,ኛ ሶላር (በፀሐይ ብርሃን የሚሠራ መብራት)
2ኛ, ድምጽ ማጉያ ከእነ ማይኩና ከአፒሊፍየር ጋር
3ኛ, እንጣ፣ ዘቢብ፣ ጧፍና ሻማ።

👉 ለቸሩ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ጥምቀት የሚያከብሩበት ታቦቱ የሚያሳድሩበት ምን አይነት ድንኳን ስሌለ፦

👉 የታቦት ማደሪያ አነስተኛ ድንኳን።

👉 ለእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ጣሪያው ክፈፍና ሄሮድስ ያስፈጃቸው 144 ሺህ ሕፃናት አንድም የመላዕክት ምሳሌ ነሆነው መርገፍ ስሌለው፦


👉 የጣሪያ ክፈፍና መርገፈ።
#ስለ_ጭንቅ_ደራሿ_አዛኝቷ_ጎራዶ_ወይራ_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን አንድ ነገር ላስቸግራች መቼም አታሳፍሩኝም።

👉 ሁላችንም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ልጆች ምዕመናንና ምዕመናት በአገሩ ውስጥም በባሕር ማዶ ያለን በጸሎት፣ በገንዘብና ማቴሪያል (እቃው ገዝቶ በመስጠት) የበኩላችን አስተዋጽ እናድርግ።

👉 የእመቤታችን ደብሩ የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር፦1000205412127 goradoweyra kidst maryam (ጎራዶ ወይራ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን)

👉 የቸሩ መድኃኔዓለም አካውንት ስሌላቸው አውጥተን ሲልኩልኝ post አደርገዋለው።

👉 #ለበለጠ_መረጃ፦ #0911414852። በአገር ውስጥ በባሕር ማዶ ያላችን ለመርዳት የምትችሉ ምዕመናን በዚሁ ቁጥር #በኢሞ_በዋትሳፕ_በቴሌግራም(#@Teamhokidusan)  ማውራት ትችላላችሁ ከበረከቱም የምትሳተፉ ስመ ክርስትናችሁ አባቶች በጸሎት እዲያስባችሁ ላኩልን።

@sigewe

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL
2024/09/24 23:19:29
Back to Top
HTML Embed Code: