Telegram Web Link
" ጸበለ ጸዐዳ-ነጩ እምነት! "
ይኽ በደብረ ደብረ ድማኅ የሚገኘው የአቡነ መርቆሬዎስ ነጭ እምነት እጅግ ፈዋሽ ለመሆኑ እኔም ብዙ ተኣምር አይቼበታለሁ። ገዳሙ በጣም በተለየ ሁኔታ የሚታወቀው በዚሁ ነጭ እምነቱ ነው፡፡ ይኽም የሆነው በጻድቁ ልመናና ቃልኪዳን ነው፡፡ ይኸውም አቡነ መርቆሬዎስ፣ አቡነ አብዲሳና አቡነ ፊልጶስ ሦስቱ አንድ ላይ ሆነው ጉዳዕ በተባለ አከባቢ ደብረ ድማኅ ገዳም ሮራ ተራራ ላይ ሆነው የየራሳቸውን ምኞት ሲጸልዩ አቡነ ፊልጶስ ስለሚያርፉባት ገዳም ጸለዩ፤ አቡነ አብዲሳም ልጆቻቸው ይበዙ ዘንድ ሲጸልዩ አቡነ መርቆሬዎስ ደግሞ ‹‹…እኔ የምኖርባትን ገዳም ነጭ፣ የልጆቼንም ኅሊናቸው እንደ ነጭ ንጹሕ አድርግልኝ›› ብለው ጸለዩ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም እንደየጸሎታቸው ለሦስቱም ቅዱሳን ሰጣቸው፡፡ በዚኽም መሠረት የአቡነ መርቆሬዎስ እምነታቸው ነጭ አፈር ሆነ፤ ይኽም እምነታቸው ለሁሉም ዓይነት ሕማም በጣም ፈዋሽ ሲሆን በተለይም ለአጋንንት በሽታዎችና ለነቀርሳ የታወቀ መድኀኒት ነው፡፡ የገዳሙ አባቶች ይኽን አስደናቂና ፈዋሽ እምነት ከአንድ ቦታ ላይ ቆፍረው እያወጡ ለሚመጣው ሕዝብ ሁሉ ሲያድሉ ከ600 አመታት በላይ ቢሆናቸውም በጣም በሚያስገርም መልኩ እምነቱ ተቆፍሮ የሚወጣበት ቦታ አንድ ስንዝር ያህል እንኳን ወደታች አለመጎድጎዱ ነው፡፡ በተለይም በየዓመቱ በጻድቁ የዕረፍታቸው ዕለት ታኅሣሥ 16 ቀን በጣም ብዙ ሕዝብ ለክብረ በዓሉ ወደ ገዳሙ እየሔደ እምነቱን ከአባቶች በብዛት እየተቀበለ ቢመለስም ተቆፍሮ የሚወጣበት ቦታ ምንም ሳይጎድል ከዓመት እስከ ዓመት ያው ነው፡፡

ጻድቁ ለአገልግሎት ወደ ሌላ ቦታ ሔደው ተመልሰው ሲመጡ ዉጡሕ በተባለ ቦታ ላይ በኣት አጽንተው ሱባኤ ያዙ፡፡ እርሳቸውም በዕለተ ዐርብ መጋቢት 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤል በዓል ዕለት በኣታቸው ውስጥ እየጸለዩ ሳሉ ድንገት ቁመቱ 170 ክንድ ጎኑ ደግሞ 9 ክንድ ከስንዝር የሚሆን ሰይጣን ከነጭፍሮቹ በውስጡ ያደረበት ታላቅ ዘንዶ ይውጣቸው ዘንድ መጣ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሳቸው ጋር ስለነበር ጸሎታቸውን ሰምቶ ቅዱስ ሚካኤልን ላከላቸው፡፡ መልአኩም ድል የሚያደርጉበትን መስቀል ሰጣቸው፡፡ ጻድቁም ከመልአኩ በተቀበሉት ቅዱስ መስቀል በሥላሴ ስም ቢያማትቡበት ዘንዶው ተሰንጥቆ በውስጡ አድረውበት የነበሩት አጋንንትከዘንዶው ወጥተው ሮጠው ሊያመልጡ ሲሉ አባታችን አወገዟቸው፡፡ ዘንድውንም ወስደው ዱበና በሚባል በረሓ ውስጥ ጣሉት፡፡

ጻድቁም ዘንዶውን ስለገደሉላቸው ለአካባቢው ሰዎችም ሆነ ለፍጥረታት ሁሉ ሰላምና ዕረፍት ሆነላቸው፡፡ ይኽንንም መሠረት በማድረግ በየአመቱ መጋቢት 12 ቀን መነኰሳት
አባቶች ከገዳም ታቦት ይዘው ወደዚህ ቦታ በመሔድ ይቀድሳሉ፣ በዓሉንም ያከብራሉ፡፡ በወቅቱ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል የሰጣቸው ረጅም መስቀልም እስከ አሁን ድረስ የተለያየ ተኣምራት እያደረገ በገዳሙ ይገኛል፡፡

የአቡነ መርቆሬዎስ ጸሎታቸው በረከታቸው ከሁላችን ሕዝበ ክርስትያን ጋር ይሁን።
✞ ✞ ✞

(ለ3ኛ ጊዜ በተከፈተው አዲስ ቻናል በኩልም በጽሑፍና በድምፅ ይከታተሉ።)
https://www.tg-me.com/kegedilatandebet27217
እንኩዋን ለታላቁ ጻድቅ "ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ "*+

=>"ዘዓምድ" በሚል ስም ከሚታወቁ የቤተ ክርስቲያን አበው መካከል 4ቱ ቅድሚያውን ይይዛሉ:: እነዚህም:-
*ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ:
*ቅዱስ አጋቶን ዘዓምድ:
*ቅዱስ ዳንኤል ዘዓምድ: እና
*ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ ናቸው::

+"ዘዓምድ" የሚለውን ቃል ምሥራቃውያን በልሳናቸው "THE STYLITE" ይሉታል:: የእኛው ቃል ደግሞ ከግዕዝ የተወረሰ ነውና በቁሙ ቢተረጐም "የምሰሶው" የሚል ትርጉምን ይይዛል:: ይህም በ2 ምክንያቶች ነው::

+አንደኛው ቅዱሳኑ ተጋድሏቸውን የፈጸሙት ከረዥም ምሰሶ ላይ ወጥተው በመጸለይ ስለሆነ ነው:: ሌላኛው ምክንያት ደግሞ እነዚህ አባቶች በዘመኑ ለነበሩ ምዕመናንና መነኮሳት አጽናኝ: አስተማሪ: መሪና ፈዋሽ በመሆናቸውና እንደ ምሰሶ ተተክለው ሳይነቃነቁ በመጸለያቸው ነው::

+ልክ ከዓለም ሃገራት ብዙ ስውራንን እና ቅዱሳን ነገሥታትን በመያዝ ሃገራችን ቀዳሚ እንደ ሆነችው ሁሉ ምሰሶ ላይ ወጥተው የሚጋደሉ ቅዱሳንም ሶርያውያንና ምሥራቃውያን ናቸው:: በዚህ ዕለትም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የታላቁን ቅዱስ ዘዓምድ ሉቃስን በዓል ታከብራለችና ከዜና ሕይወቱ ለበረከት ጥቂት እንካፈል::

+ቅዱስ ሉቃስ ተወልዶ ያደገው በፋርስ (በአሁኗ ኢራን) ሲሆን ዘመኑም ዘመነ ጻድቃን (ከ3ኛው እስከ 6ኛው ክ/ዘመን ድረስ) እንደ ሆነ ይታመናል:: ዛሬን አያድርገውና በጊዜው በጣም ብዙ: በዚያም ላይ ጽኑዕ የሆኑ ክርስቲያኖች በሃገሪቱ ነበሩ::

+በወቅቱ በየሥፍራው ዜና ቅዱሳን ሰፍቶ ነበርና ብዙዎቹ ወደ ምናኔ እየሔዱ ገዳማትን አጨናንቀው ነበር:: መንፈሳዊ ቅንዓት የሚያቃጥላቸው ክርስቲያኖችም ብዙ ነበሩ::

+ቅዱስ ሉቃስ ከልጅነቱ መሠረቱ ክርስትና ነው:: ልጅ ሳለም ሃይማኖቱን በሚገባ አውቁዋል:: ወጣት በሆነ ጊዜ ሠርቶ መብላት ሃይማኖታዊ ግዴታም ነውና ሥራ ፍለጋ ወጣ::

+በጊዜው ደግሞ በቀላሉ የሚገኝ ሥራ የሠራዊት አባል ወይም በዘመኑ ልሳን "ወታደር" መሆን ነበርና ሒዶ ገባ:: ውትድርና የኃጢአት ሥራ አይደለም:: ሃገርን: ዳርን: ድንበርን እየጠበቁ ራስን መስዋእት ማድረግ ነውና::

+ነገር ግን አንዳንዶቻችን የማይገባ ሥራ ስንሠራበት: ለእኛም ለወገንም የማይበጅ ድርጊት ስንፈጽም ይታያል:: ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔር በምድርም ሆነ በሰማይ ይፈርዳልና ሁላችንም በተሠማራንበት ሙያ ሁሉ እንደሚገባ ልንኖር ግድ ይለናል:: የአባቶች ሕይወት እንዲህ ነበርና::

+ቅዱስ ሉቃስም ወታደር (ጭፍራ) ነው:: ግን ደግሞ ክርስቲያን ነው:: በ2ቱም ማንነቶቹ የሚጠበቁበትን እየተወጣ: የወጣትነት ስሜቱን በፈጣሪው ኃይል እየገታ: ራሱን ለእግዚአብሔር እያስገዛ ቀጠለ::

+እንደሚታወቀው ሰው በሥራው መጠን ክፍያው (ደሞዙ) እና ማዕረጉ (ሥልጣኑ) ከፍ እያለ መሔዱ አይቀርም:: ምንም እንኩዋ ብዙ እንዲህ ዓይነት ተግባራት በዘመናችን ቀዝቃዞች ቢሆኑም:: የሠራውን ትቶ ላልሠራው መሸለም በክርስትናው ዓለም ትልቅ ስህተት ነው::

+ምናልባትም ይሔው ገርሞት ይመስለኛል:-
"ሃገሬ ኢትዮዽያ ሞኝ ነሽ ተላላ::
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ::" ሲል የሃገራችን ሕዝብ የተቀኘው::

+ቅዱስ ሉቃስም እንደ ሥራው መጠን ከፍ እያለ ሒዶ የፋርስ ሠራዊት ሃቤ ምዕት (የመቶ አለቃ) ለመሆን በቃ::

+ቅዱስ ሉቃስ የጦር መሪነት ስራውን እያከናወነ ጐን ለጐን ለፈጣሪው ይገዛ መጻሕፍትን ያነብ ነበር:: በተለይ ዜና ቅዱሳን ዕለት ዕለት ይስበው ነበርና ልቡናው ወደ ፍቅረ ክርስቶስ ተመሰጠ:: ይህችን ዓለም ትቷት ሊሔድም ተመኘ::

+በጐ ምኞትን የሚፈጽም ጌታም ልቡን አበርትቶለት ከዓለማዊ ንብረቱ አንድም ነገርን ሳያስከትል: ሹመቱንም ትቶ በርሃ ገባ:: በዚያም በረድዕ ሥርዓት የአባቶች ደቀ መዝሙር ሆነ:: አዛዥነትን ትቶ ታዛዥ: ተገልጋይነትን ትቶ አገልጋይ ሆነ::

+ትሕትናውንና ትጋቱን የተመለከቱ አበውም ወደ ምንኩስና ማዕረግ ከፍ አደረጉት:: አሁንም ታጥቆ አገልግሎቱን ቀጠለ:: እውቀቱን: ማስተዋሉንና ቅድስናውን ያዩ አባቶች በጐ እረኛ እንደሚሆን ስላወቁም ቅስናን ሾሙት::

+ከዚህ በሁዋላ ግን ቅዱስ ሉቃስ የተጋድሎውን ደረጃ ከፍ አደረገ:: በመጀመሪያ ጾሙን ከአንድ ቀን ወደ 3 ቀን አሸጋገረ:: ትንሽ ቆይቶ ግን ጾሙ 7 ቀን ሆነ:: ምን ጊዜም እህልን የሚቀምሰው በዕለተ ሰንበት (እሑድ) ብቻ ሆነ::

+ሁልጊዜም በዕለተ ሰንበት ቅዳሴን ይቀድሳል:: ለእርሱ ሥጋ ወደሙን ተቀብሎ ለሌሎቹ ያቀብላል:: ከዚያም ወደ በዓቱ ሒዶ አንዲት ዻኩሲማን ይመገባል:: "ዻኩሲማን" አባቶች በቀደመ ልሳን "የዳቦ ለከት" ይሉታል:: በዘመኑ ልሳን "ትንሽ የዳቦ ቁራጭ" እንደ ማለት ነው::

+ከዚህ ጐንም ወገቡን በሰንሰለት ታጥቆ በፍጹም መንፈሱ ይጸልይና ይሰግድ ነበር:: በዚህ ተጋድሎ ላይ ሳለም በታላቁ አባ አጋቶን ሕይወት መቅናትን ቀና:: በአንደበት ከሚወጣ ኃጢአት ይጠበቅ ዘንድም ሙልሙል ድንጋይ አዘጋጅቶ ጐረሰው::

+ያ ድንጋይ የሚወጣው በሳምንት አንዴ: ለሥጋ ወደሙና ለቁርባን ብቻ ነበር:: ማንም ምንም ቢያደርገውም ሆነ ቢናገረው ምንም አይመልስም:: ይህም ተጋድሎ "አርምሞና ትዕግስት" ይባላል::

+አርምሞ (ዝምታ) አንደበትን መቀደስ ሲሆን ትዕግስት ደግሞ ልብን ጸጥ አድርጐ መቀደስ ነው:: 2ቱ ጸጥ ካሉ ሰውነትም ከኃጢአት ማዕበል ጸጥ ይላልና:: የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስም በመዋዕለ ስብከቱ ማርያምን "ኃርየት መክፈልተ ሠናየ - በጐ እድልን መረጠች" ያላት ስለዚህ ሃብቷ እንደ ሆነ መተርጉማን አትተዋል:: (ሉቃ. 10, ቅዳሴ ማርያም)

+ቅዱስ ሉቃስ በዚህ ሕይወቱ ለ3 ዓመታት ቆየ:: በሁዋላ አምላክ ቅዱስ መልአኩን ልኮ ወደ ቁስጥንጥንያ መራው:: የብርሃን መስቀል እየመራውም ወደ ምሥራቅ ተጉዋዘ::

+በዚያም እስከ ዛሬ ድረስ የሚታወቅበትን ተጋድሎ ጀመረ:: ከቁስጥንጥንያ ከተማ አቅራቢያ አንድ ምሰሶ አግኝቶ በላዩ ላይ ወጣ:: በዚያም ከእርሱ በፊት የነበሩ ቅዱሳን አባ ስምዖንና አባ አጋቶን ዘዓምድ እንዳደረጉት ያደርግ ጀመር::

+በምሰሶው ላይ መቀመጥ ስለ ማይቻል ትልቁና የመጀመሪያው ገድል ያለ ዕረፍት መቆም ነው:: በተረፈ ግን ለአካባቢው ምዕመናን መሪ: አስተማሪ ነበር:: ዝናውን እየሰሙ ሰዎች ከተለያየ አሕጉር ይመጡ ነበር::

+ያላመኑትን በስብከቱ ማሳመን: ያመኑትንም በምክሩ ማጽናትን ቀጠለ:: እርሱ አስተምሮት የማይለወጥ አልነበረም:: ምክንያቱም ምሉዓ መንፈስ ቅዱስ (መንፈስ ቅዱስ የመላበት) ነውና አጋንንት በሥፍራው አይቆሙምና::

+በጊዜውም ዻዻሳቱም: ካህናቱም: ሕዝቡም: መሣፍንቱም ይወዱት ነበር:: ቢያዝኑ አጽናኝ: ቢታመሙ ፈዋሽ: ከፈጣሪ ቢጣሉ አስታራቂ ነበርና:: እንዲህ ባለ ተጋድሎ ቅዱስ ሉቃስ ለ45 ዓመታት በምሰሶው ላይ ቆየ:: ስለዚህ እስከ ዛሬም ድረስ "ዘዓምድ" (THE STYLITE) እየተባለ ይጠራል::

+እግዚአብሔር ሊያሳርፈው በፈለገ ጊዜም ደቀ መዝሙሩን ጠርቶ ወደ ከተማ ላከው:: መልእክቱን የሰሙት የቁስጥንጥንያ ከተማ መሣፍንት: ዻዻሳት: ሕዝቡና ካህናቱ እየተሯሯጡ ቢመጡ ታኅሳስ 15 ቀን በፍቅር ዐርፎ አገኙ::

+እያዘኑ በታላቅ ለቅሶና ዝማሬ ወደ ቁስጥንጥንያ አደረሱት:: በዚያም በክብር በዚህች ቀን ከአበው መቃብር ቀበሩት::
<< ዛሬም ድረስ በአካባቢው ክቡር አባት ነው !! >>

=>አምላከ ቅዱስ ሉቃስ መካሪ: ዘካሪ አባቶችን አያሳጣን:: ከቅዱሱ በረከትም

ያሳትፈን::

=>ታሕሳስ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ
2.ቅዱስ ናትናኤል ጻማዊ
3.ቅዱስ ማርቆስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ወቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ
8.ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ

=>+"+ ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል::
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል::
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል::
በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ::
ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ::
ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ:: +"+ (መዝ. 91:12)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
††† እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል: ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ እና አቡነ ስነ ኢየሱስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††

††† በቤተ ክርስቲያን ክቡር ከሆኑ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብርኤል ብዙ የክብር ስሞች አሉት:: በተለይ ግን:-
*ሊቀ አርባብ:
*መጋቤ ሐዲስ:
*መልአከ ሰላም:
*ብሥራታዊ:
*ዖፍ አርያማዊ:
*ፍሡሐ ገጽ:
*ቤዛዊ መልአክ:
*ዘአልቦ ሙስና . . . እየተባለ ይጠራል::

በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ስሙ በብዛት ተጠቅሷል:: ስለ ረዳትነቱና አማላጅነቱም ቤተ ክርስቲያን በስሙ ታቦት ቀርጻ: መቅደስ አንጻ በሥርዓት ክብሩን ትገልጻለች::

ከእነዚህም አንዱ ሠለስቱ ደቂቅን እንዳዳነ የሚታሰብበት አንዱ በዓሉ ዛሬ ነው::
"ለዝንቱ ዜናዊ መልአከ ኃይል::
በዛቲ ዕለት ከመ ይትገበር በዓል::
መምሕራን አዘዙ ወሠርዑ በቃል::" እንዲል:: (አርኬ)

ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአሕዛብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ::

ምንም እንኳ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ: ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ::

አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ: ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው::

ከነገር ሁሉ በኋላ አሕዛብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ ስገዱ ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጓዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም::

ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳ አሕዛብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ::

ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን
"አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው::
አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው:: (መልክዐ ገብርኤል)

††† ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ †††

††† ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ የከበረ ነው:: ሊቅም: ጻድቅም: ጳጳስም: ገዳማዊም ነው:: ከሁሉም በላይ ግን ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን በተድላ ለምትጠቀምባቸው መጻሕፍት (ስንክሳር: ግጻዌ እና ሃይማኖተ አበው) መሠረትን የጣለ ቅዱስ ሰው ነው::

ቅዱስ ዮሐንስ በትውልዱ ግብጻዊ ሲሆን ጊዜውም 5ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች: በዚያውም ላይ ሞልቶ የተረፋቸው ባለ ጠጐች ነበሩ:: እንደ ሕጉ ወጣት እስኪሆንና ራሱን እስኪችል ድረስ አሳደጉት::

ከዚያ ግን ድንገት አባቱና እናቱ ተከታትለው ዐረፉ:: ከቁጥር የበዛ ሃብትን የግሉ ያደረገው ቅዱስ ዮሐንስ ምን እንደሚያደርግበት ጨነቀው:: አንድ ትልቅ ነገር ግን ከማይሆን ጐዳና ጠበቀው::

ወላጆቹ ሁሌም መዝገብን በሰማያት ያገኙ ዘንድ ለነዳያን ይራሩ ነበርና ይህንኑ ለመቀጠል ወሰነ:: መልካም ፍሬ ከመልካም ዛፍ ነውና (ማቴ. 7:16) ወላጅ ለልጁ ማውረስ ያለበት ምድራዊ ሃብትን ሳይሆን በጐ ሕሊናን ነው:: ሳይሠሩ ያገኙት ሃብት ብዙዎችን አጥፍቷቸዋል::

ለዛም ይመስላል ዛሬ አንዳንዶቻችን በቤተሰቦቻችን ሃብት ከእኛ አልፈን ትውልዱን እየገደልንበት ያለው:: ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔር ንስሃ ካልገባን ይመጣብናል:: መቅረዛችን (ሕይወታችንም) ከእኛ ላይ ይወስዳል::

ፍርድ የሚሆነው በክፉው ትውልድ ላይ ብቻ አይደለም:: ይህንን ትውልድ በፈጠርነውና መልካሙን መንገድ ባልመራነው በሁላችንም ላይ እንጂ:: (ራዕ. 2:5)

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ዮሐንስ በወላጆቹ ሃብት የእንግዶች ማረፊያ የሚሆኑ ቤቶችን አንጾ ነዳያንን ይንከባከብ ገባ:: ሙሉውን ቀን ለነዳያን ሲራራ ይውላል:: አመሻሽ ላይ እንግዶችን ተቀብሎ: አብልቶ ያሳርፋል::

ከዚያም ፈጣሪውን ያመሰግናል:: በእንዲህ ያለ ሕይወት ዘመናትን ካሳለፈ በኋላ አንድ እንግዳ መነኮስ ወደ ቤቱ መጣ:: አስተናግዶት ሲጨዋወቱ አደሩ:: ሌሊት ላይ ግን ስለ ምንኩስና ሕይወትና ስለ ክብሩ ነግሮት ነበርና ልቡ ተመሰጠ::

መነኮሱን ከሸኘው በኋላም ይመንን ዘንድ ቆረጠ:: ነዳያንን ሰብስቦ ሃብቱን አካፈላቸው:: ከዚያም ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሒዶ የታላቁ አባ ዳንኤል ደቀ መዝሙር ሆነ:: በትሕትና ለአባቶች እየታዘዘ ከቆየ በኋላ በጭንቅ ደዌ ተያዘ:: ሰይጣን በቅንዓት ገርፎት ነበርና::

እርሱ ግን በደዌው ምክንያት ለዓመታት መሬት ላይ ወድቆ ቢቆይም ፈጣሪውን ፈጽሞ ያመሰግን ነበር:: እግዚአብሔር ደግሞ በፈውስና በኃይል አስነሳው::

በጊዜው የቡርልስ ጳጳስ ዐርፎ ነበርና አባት ፍለጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም መጥተው ነበር:: መንፈስ ቅዱስ መርጦታልና አበው ቅዱስ ዮሐንስ ጳጳስ ይሆን ዘንድ አስገደዱት:: እርሱም የፈጣሪ ፈቃድ መሆኑን ስላወቀ ሔደ::

በዚያም (በሃገረ ቡርልስ) ታላቁን ገድል ተጋደለ:: ወደ ከተማዋ ሲገባ ብዙ ነገሮች ከሚገባው ሥርዓት የወጡ ነበሩ:: ብዙ ሰው የእግዚአብሔርን ድምጽ ከመስማት ይልቅ ባላስፈላጊ ነገሮች ላይ ተጠምዶ ነበርና መንጋውን ያድን ዘንድ ተጋ::

ሳይሆኑ "ባሕታዊ": "አጥማቂ" ነን እያሉ ሕዝቡን የሚያሳስቱ ተኩላዎችንም አስወገደ:: ለሕዝቡ አጉል ሕልም: ሟርትን የሚያስተምሩትን ገሠጸ:: አንመለስም ያሉ መናፍቃንን እሳት ከሰማይ ወርዳ በላቻቸው::

ቅዱስ ዮሐንስ ከቅድስናው ብዛት ዘወትር ሲቀድስ መድኃኒታችንንና አእላፍ መላእክትን ያይ ነበር:: ከከዊነ እሳት ማዕረግ በመድረሱም አካሉ በመፈተት ሰዓት እንደ እሳት ይነድ ነበር:: እንባውም እንደ ውኃ ይፈስ ነበር::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ ጐን ዛሬም ድረስ የሚታወቅበትን ታላቅ ሥራም ሠርቷል:: መንፈስ ቅዱስ አነሳስቷቸው ቅዱሱና የሃገረ አትሪብ ጳጳስ የነበረው ሊቁ አባ ሚካኤል መጽሐፈ ስንክሳርን : መጽሐፈ ግጻዌንና ሃይማኖተ አበውን ለመጀመሪያ ጊዜ አዘጋጅተዋል::

"ስንክሳር" የቅዱሳንና የፈጣሪን ነገር በየዕለቱ የሚዘግብ መጽሐፍ ሲሆን "ግጻዌ" የየዕለቱን በዓላት ከምስባክና ምንባባት ጋር አስማምቶ የያዘ መጽሐፍ ነው:: "ሃይማኖተ አበው" ደግሞ የዶግማ መጽሐፍ ሆኖ ከሐዋርያት እስከ ሊቃውንት ድረስ የጻፉትን የያዘ ነው:: ሦስቱን የሚያመሳስላቸው "ስብስብ / እስትጉቡዕ / Collection" መሆናቸው ነው::

ቅዱሱ ዮሐንስ በሃገረ ቡርልስ በከፍተኛ ድካም ይህንን ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† አቡነ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ †††

††† ጻድቁ በመካከለኛው (የብርሃን) ዘመን የነበሩ ኢትዮጵያዊ::
*ከምድረ ሽዋ ወደ ታች አርማጭሆ የሔዱ መናኝ:
*ጭው ባለ በርሃ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ገዳምን ያነጹ አባት:
*ብዙ አርድእትን ያፈሩ መናኝ:
*ብዙ ተአምራትን የሠሩና ወንጌልን ያስተማሩ መነኮስ ናቸው::
በደመናም ይጫኑ ነበር:: ገዳማቸውም (ታች አርማጭሆ: ከሳንጃ ከተማ የ3 ሰዓት መንገድ ይወስዳል) ድንቅና ባለ ብዙ ቃል ኪዳን ነው:: መልአከ ሞት መስከረም 1 ቀን ቢመጣ "የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ሳላከብርአይሆንም" ብለው ለ3 ወራት በበራቸው አቁመውታል:: ታኅሣሥ 19 ቀንም ዐርፈዋል::

††† አምላከ ቅዱሳን በመልአኩ ረድኤት ጠብቆ ለጻድቃኑ በረከት ያብቃን::

††† ታኅሣሥ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ
3.አቡነ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
2.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
3.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
4.ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ

††† ". . . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም . . ." †††
(ዳን. ፱፥፳)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
https://www.tg-me.com/zikirekdusn

2024/09/27 15:25:43
Back to Top
HTML Embed Code: