Telegram Web Link
#እገታ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በተለይም አሰላ ከተማ ዙሪያ ላይ ያሉ ነዋሪዎች እየተባባሰ የመጣዉ የእገታ ወንጀል እንዳማረራቸው ተናግረዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

-  ሰዎችን አግቶ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብን የመጠየቅ ተግባር ህብረተሰቡን አማሯል።

- ከአሰላ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙ ገጠራማ ቀበሌያት፤ በተለይም ሄጦሳ ወረዳ፤ #ቂሊሳ በሚባል አከባቢ በሌሊት ሰዎችን በማገት ገንዘብ መጠየቅ እየተለመደ የመጣ ተግባር ሆኗል። ይህ ቦታ ቁሉምሳ ከሚባለው የአሰላ ከተማ መግቢያ አከባቢ እጅግ ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው።

- በዶዶታም ተመሳሳይ የእገታ ተግባር በሌሊት ይፈፅማል።

- ከከተማ ውጪ ያለው የትኛውም አከባቢ መሰል ስጋት አለ፡፡

-  ሰዎች ሲታገቱ ባላቸው የኢኮኖሚ አቅም የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲከፍሉ በአጋቾቻው ይወሰንባቸዋል።

- የታገቱት ሰዎች የተጠየቁትን ተደራድረው ከፍለው ከመውጣት ውጪ ህይወታቸውን የማቆያ ሌላ ስልት የለም።

- አጋቾቹ እነማን እንደሆኑ አይታወቅም እሱ ነው ትልቁ ችግር።

- ከፍተኛ የአርሶ አደር የኢኮኖሚ አቅም የሚስተዋልበት አከባቢ ነው በቀጣይም ለመሰል ዘረፋ ተጋላጭ እንዳኆን ስጋት አለን።

- ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው አርሶ አደሮች አከባቢውን ለቀው ወደ ከተማ በመሸሽ ላይ ሲሆኑ አቅም የሌለው ግን አከባቢው ላይ ተቀምጦ የሰቀቀን ህይወት ይመራል።

ፖሊስ ምን ይላል ?

የአርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ ከድር ፦

▸ ችግሩ ጎልቶ የሚስተዋለው ከከተማ ራቅ ባሉ ደናማ አከባቢዎች ነው፡፡ እንደሚባለው ሳይሆንም አልፎ አልፎ በአንዳንድ አከባቢዎች በደን በተሸፈኑ ገጠራማ አከባቢዎች በተለይ ወደ አኖሌ ባሉ ደናማ የዝዋይ ዱግዳ ወረዳ አዋሳኝ ነው።

▸ በተለያዩ ጊዜያት ተግባሩን ለማስቆም የሚወሰዱ ኦፕሬሽኖች በመኖራቸው እንዲህ ጎልቶ በከተማ ዙሪያ የሚፈጸም ነገር የለም፡፡

▸ በተለይ በአሰላ ከተማ ዙሪያም ሆነ በአስፓልት መንገዶች ላይ እንዲህ ያለ ነገር የለም፡፡ ወንጀሉ አልፎ አልፎ የሚስተዋለው በዶዶታ እና ሁሩታ ወረዳዎች ዳገታማ አከባቢዎች እና ከምስራቅ ሸዋ ዝዋይ ዱግዳ ጋር ከሚያዋስኑን አከባቢ ነው፡፡

▸ መሰል ተግባርን የሚፈጽሙ በውንብድና ስራ የተሰማሩ አሉ፡፡ አንዳዴ ኦነግ ሸኔ በሚል ትጥቅ አንግቦ በጫካ የሚንቀሳቀሰውን ሃይል እንደ ሽፋን በመጠቀም በዝርፊያው የተሰማሩ መኖራቸውን አረጋግጠናል፤ በዝርፊያ ላይ እያሉም ጭምር ተቆጣጥረን ለህግ ያቀረብናቸው አሉ።

• ምን ያህል ሰዎች ተያዙ ? የሚለውም ጥያቄ ላይ ዝርዝር ምላሽ ሳይሰጡ አልፈዋል።

▸ በተለያየ ጊዜ ኦፕሬሽኖችን እያካሄድን ነው ፤ ከታጣቂዎች በተጨማሪ በታጣቂዎች ስም የተደራጁ መኖራቸውን ህዝቡን እናስገነዝባለን፡፡ እነዚህ ማህበረሰቡን በስልክ ጭምር እየደወሉ የሚያስፈራሩትን ተከታትለን እየያዝን ነው፡፡

(ከዶቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ ቃለምልልስ የተወሰደ)

@tikvahethiopia
#ኅዳር_4_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበውን_ወንጌል_እናንብብ📖
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤
³³ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።
³⁴ በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።
³⁵ ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤
³⁶ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።
³⁷ ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤
³⁸ መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።
³⁹ ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል።
⁴⁰ እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።
⁴¹ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።
⁴² ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
# ኅዳር_4_የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም የቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ፣ የቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ፣ የቅዱሳን አቢማኮስና ወአዛርያኖስ፣ ለታላቁ አባት ዘካርያስ፣ ለጉባኤ ቅዱሳን ሰማዕታት እንዲሁም ለአባ አበይዶ የዕረፍት በዓልና የጽጌ ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
Audio
AudioLab
ስለ #ወጣትነት እና #እጮኝነት ተከታታይ ትምህርት ክፍል ፩ (1)
#share እያደረጋችሁ ለሁሉም አድርሱ

በመምህር አቤል
ንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠   
/(ማቴ ፫:፫/)

❇️ዝክረ ቅዱሳን ተማሩ ላልደረሳቸው አጋሩ!!!❇️

እንኳን አደረሰን!!


ኅዳር 20 የቅዱስ ማር ቴዎድሮስ በዓል ቆሞ 7ጊዜ የሚጸለይ።

አምላከ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ

አምላከ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ

አምላከ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ

አምላከ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ

አምላከ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ

አምላከ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ

አምላከ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ

ነብያት ወሐዋርያት ጻድቃን ወሰማዕት ደናግል ወመነኮሳት አዕሩግ ወሕጻናት ገዳማውያን ወሊቃውንት ሰአሉ ለነ ኩልክሙ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት።

❇️ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)❇️
" ❇️ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::❇️
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር

🛑በዩቲብለመከታተል👉https://youtube.com/@ZekereKedusan?si=7acGUCDCLO2Qxl37

🛑በቴሌግራም👉
https://www.tg-me.com/zikirekdusn
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር)" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ቅዱስ መርቆሬዎስ ኃያል "*+

=>ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት:: ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው::

+ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ (ሁለተኛው) ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ (አስሌጥ) ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት: እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር::

+አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: 2 ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር::

+እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል::

+እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና:- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው::

+"ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ 2ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት::

+ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና 2ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ::

+አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው::

+ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ::

+ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን 2ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ::

+በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ5 ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው::

+እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ::

+በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት::

+በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ::

+ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው::

+በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቁዋቁዋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት::

+እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ (አብሮት ያደገ ነው) ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም::

+ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ::

+በ3ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው::

+"ሃብትከ ወክብርከ ይኵንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: (ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ)" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው::

+ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት:-
"አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም::
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም::
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት::

+ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር 25 ቀን አንገቱን ሰይፈውታል::

+እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ200 ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ220 ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ225 ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል::
<<የቅዱሱ ክብር ታላቅ ነው>>

=>አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

=>ኅዳር 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅዱሳን ታቦትና ኖኅ (ወላጆቹ)
3.ቅዱስ ሮማኖስ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.ቅዱስ አቡፋና ጻድቅ
6.ታላቁ አባ ቢጻርዮን
=>+"+ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ: በመጋዝ ተሰነጠቁ: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና . . . +"+ (ዕብ. 11:35)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://www.tg-me.com/zikirekdusn
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 25-የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ‹‹መርቆሬዎስ›› ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ አስሊጥ ከምትባል ሀገር ቢሆኑም እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡

አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡
ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሮአቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡
ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡

መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብሮት ነበር፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡ ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡
ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡

እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡ ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡

ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ ከጦሩም አንገት ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡

ሌላው የሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ተአምር ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ ኢስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የመሐመድን መቃብር ለመሳለም በሔደው ኢስላም ላይ ያሳየው ታላቅ ተአምር ነው፡፡ ሙሉ ታሪኩን ነገ ላይ እናየዋለን፡፡

ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!
የታላቁን ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከቱ ይድርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 27-የደብረ ጽሙናው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሐዋርያት ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ከሃዲዎች መላ አካሉ እጆቹንና እግሮቹን እስከ ጭኖቹ ድረስ በየተራ ቆራርጠው ደረቱና አካሉ ግንድ እስከሚመስል ድረስ 42 ቦታ ቆራርጠው በማሠቃየት የገደሉት ሰማዕቱ ቅዱስ ያዕቆብ ግሙድ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ጌታችን ተገልጦላቸው ስለስሙ መስክረው ሰማዕት ይሆኑ ዘንድ ያዘዛቸው ሰማዕቱ ቅዱስ ጢሞቴዎስና ባለቤቱ ቅድስት ሞራ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ከ72ቱ አርድእት ውስጥ አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ፊልሞና ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡

ሰማዕቱ ያዕቆብ ግሙድ፡- አስቀድሞ የጥሩ ክርስቲያን ቤተሰብ ልጅ ነበር፡፡ በኋላም የፋርሱ ንጉሥ የሰክራድ ባለሟልና የቅርብ አማካሪ ሆነ፡፡ ንጉሡም እጅግ ይወደው ስለነበር በመንግሥቱ ሁሉ ከእርሱ ጋር ሳይማከር ምንም አያደርግም ነበር፡፡ የንጉሡ ልዩ አማካሪ በሆነ ጊዜ ልቡናው አዘንብሎ በከሃዲው ንጉሥ እምነት በማመን በፀሐይና በእሳት አመነ፡፡ በአማልክቶቹ በእሳትና በፀሐይም እንዲያምን ይመክረው ስለነበር ወደ ጣኦትም እምነት ገባ፡፡

እናቱና እኅቱ በንጉሡ ከንቱ እምነት ማመኑንና ከንጉሡም ጋር በመስማማት የክርስትና እምነቱን መካዱን ሲሰሙ ‹‹…የቀናች የክርስቶስን ሃይማኖት ትተህ ወደ ጣኦት አምልኮ እንዴት ትገባለህ? የፍጡራንን ጠባይ ለምን ተከተልህ? ከዛሬ ጀምሮ በንጉሡ ሃይማኖት ከኖርክ እኛ ከአንተ የተለየን ነን›› እያሉ ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሱ ጻፉለት፡፡ ‹‹ወደ እውነተኛዋ ሃይማኖትህን ባትመለስ አንተ ከእኛ የተለየህ ትሆናህ›› አሉት፡፡ እርሱም ደብዳቤውን አንብቦ እንደጨረሰ መሪር ልቅሶን አለቀሰ፡፡ ከዚህም በኋላ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ማንበብ ጀመረ፡፡ የክርስቶስን ፍቅሩን አስቦ ለፍርድ ሲመጣ ‹‹በፊቱ እንዴት ልቆም እችላለሁ?›› ብሎ በማሰብ ወደ ልቡ ተመለሰ፡፡ የፋርሱን ንጉሥ አገልግሎቱንም አቆመ፡፡ ለንጉሡም ‹‹ያዕቆብ አማልክትን ማምለክ ትቷል›› ብለው በነገሩት ጊዜ አስጠርቶት ጠየቀው፡፡ ያዕቆብም ንጉሡን ‹‹ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ ወንጌሉ ‹በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ….›› ብሏልና ስለዚህ አገልግሎትህን፣ ፍቅርህንና አማልክቶችህን ማምለክ ፈጽሞ ትቻለሁ፡፤ ሰማይንና መድርን፣ ጨረቃንና ፀሐይን፣ የሚታየውንና የማይታየውን የፈጠረውን አምላክ የእግዚአብሔርን ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁ፣ ለእርሱም እሰግድለታለሁ›› አለው፡፡ ንጉሡም እጅግ ተናዶ ደሙ እንደ ውኃ እስኪፈስ ድረስ አስገረፈው፡፡ ዳግመኛም ለአማልክቶቼ ስገድ ብሎ ብዙ አሠቃየው፡፡ እንዳልተመለሰለትም ሲያውቅ እያንዳንዱን ህዋሳቱን (አካሉን) በየዕለቱ እንዲቆርጡትና ተሠቃይቶ እንዲሞት አዘዘ፡፡

በንጉሡም ትእዛዝ መሠረት ሃያውንም የእግሮቹንና የእጆቹን ጣቶች በየጊዜው ቆረጧቸው፡፡ ቀጥለውም ክንዶቹንና እግሮቹን እስከ ጭኖቹ ድረስ በየተራ ቆረጡት፡፡ እንዲህም እያደረጉ እስከ 42 ቁራጭ ድረስ በጥቂቱ እየቆራረጡ አሠቃዩት፡፡ ያዕቆብም መላ አካሉ ተቆራርጦ ደረቱና አካሉ እንደ ግንድ ድብልብል ሆኖ በቀረ ጊዜ ነፍሱን ለመስጠት እንደደረሰ ዐውቆ በዓለም ውስጥ ያሉ ኃጢአተኛ ሰዎችን ሁሉ ይምራቸው ዘንድ ጌታችንን ለመነው፡፡ ስለ ዓለምም ሁሉ መለመን በጀመረ ጊዜ እንዲህ አለ ‹‹አቤቱ ወደ አንተ የማነሳው አካል አልቀረልኝም ሕዋሳቶቼ ሁሉ ተቆራርጠው በፊቴ የወደቁ ስለሆነ አሁንም ነፍሴን ተቀበል…›› እያለ ልመናውን ወደ ፈጣሪው አቀረበ፡፡ ጌታችንም ተገልጦለት ካረጋጋውና ካጽናናው በኋላ ታላቅ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ ‹‹ልጄ አይዞህ ሰማዕትነትህን ፈጽመሃል ዋጋህንም እኔ እከፍልሃልሁ›› አለው፡፡

ከዚህም በኋላ ከንጉሡ ጭፍሮች አንዱ መጥቶ የቅዱስ ያዕቆብን አንገት በሰይፍ ቆረጠውና ኅዳር 27 ቀን የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ሆነ፡፡ እናቱና እኅቱም በሰማዕትነት ማረፉን በሰሙ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው፡፡ መጥተውም ሥጋውን ተሳለሙት፡፡ ሽቶም እረጩት እንጂ አላለቀሱለትም፡፡ በደጋጎቹ ነገሥታት በአኖሬዎስና በአርቃዴዎስ ዘመን አብያተ ክርስቲያናት ታነጹ፡፡ ምእመናንም ለቅዱስ ያዕቆብ ውብ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በዚያ በክብር አኖሩ፡፡ በዚያም እጅግ ታላላቅ ተአምራት ተፈጸሙ፡፡
ረድኤት በረከታቸው ይደረርብን በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +

ሰማዕቱ ቅዱስ ጢሞቴዎስና ባለቤቱ ቅድስት ሞራ፡- ይህም ቅዱስ በንሑር ከምትባል አገር የተገኘ ሰማዕት ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሁልጊዜ በጾም በጸሎት ተጠምዶ የሚኖር ሆነ፡፡ ሞራ የምትባል ሚስት ነበረችውና እርሷም በሥራዋ ሁሉ የምታስደስተው ናት፡፡ እነርሱም በፍቅር በሚኖሩበት ዘመን ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ አብያተ ክርስቲያናት እንዲዘጉ በዓለም ላይ ባሉ ግዛቶቹ ሁሉ አዋጅ አስነግሮ ጣዖት አቁሞ ለእርሱ ያልሰገዱትን ክርስቲያኖች ሁሉ በግፍ መግደል ጀመረ፡፡

ቅዱስ ጢሞቴዎስም ይህንን የንጉሡን አዋጅ በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው እርሱ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ደሙን ያፈስ ዘንድ ይህን ዘመን ይጠብቀው ነበርና፡፡ ለሚስቱም ሰማዕት ሊሆን እንዳሰበ ሲነግራት እርሷም ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን አለችው፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጢሞቴዎስ መንገዱን ያቀናለት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜ ጌታችን በራእይ ተገለጠለትና ‹‹ወዳጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፡፡ እነሆ ከጻድቃኖቼ ቁጥር ውስጥ ቆጥሬሃለሁ፣ አሁንም ሚስትህን ይዘህ ወደ ብህንሳ ከተማ ሄዳችሁ ጣዖትን በሚያመልኩ ሁሉ ሕዝብ ፊት በስሜ ታመኑ›› አለው፡፡

ጌታችን ለሚስቱ ሞራም ይህንኑ ነገር በራእይ ነግሯትና ነበርና ሲነጋ ራእያቸውን ተነጋግረው እጅግ ደስ ተሰኙ፡፡ ተነሥተውም በአንድነት ወደ ተነገራቸው ቦታ በመሄድ መኮንኑ ቁልቁልያኖስ ዘንድ ረደሱ፡፡ እርሱም ማሲንቆና እንዚራ እያስመታ ለጣዖቱ በዓልን ሲያከብር አገኙትና በፊቱ ቆመው ክርስቲያን መሆናቸውን በመግለጽ የጌታችንን አምላክነት መሰከሩ፡፡ መኮንኑም ለጣዖቱ እንዲሰግዱ ሊያግባባቸው ሞከረ፡፡ ቅዱስ ጢሞቴዎስና ሚስቱ ቅድስት ሞራ ግን በሕዝቡ ሁሉ ፊት የጌታችንን አምላክነት መሰከሩ፡፡ የመኮንኑንም የረከሰች ሃይማኖቱን በነቀፉበት ጊዜ ተቆጥቶ ካስገረፋቸው በኋላ ወደእሥር ቤት አስገባቸው፡፡ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ሁለቱን ቅዱሳን ወደ አደባባይ አውጥተው ደማቸው እንደውኃ እስከፈስ ድረስ በአለንጋ ገረፏቸው፡፡ ቅድስት ሞራም በዚሁ ምስክርነቷን ፈጽማ የክብርን አክሊል ተቀዳጀች፡፡

መኮንኑንም ቅዱስ ጢሞቴዎስን ሊያባብለው ቢሞክርም ቅዱሱ ግን ጣዖታቱን እየረገመበት በጌታችን ታመነ፡፡ መኮንኑም በዚህ ጊዜ እጅግ ተናዶ የነዳጅ ድፍድፍ ሰውነቱን ከቀባው በኋላ እሳት ውስጥ ጨመረው፡፡ በዚህም ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ፈጥኖ ወርዶ ሠለስቱ ደቂቅን እንዳዳናቸው ቅዱስ ጢሞቴዎስንም ከሚነደው እሳቱ አዳነው፡፡ ሁለተኛም ወደ ወህኒ ቤት በመለሱት ጊዜ ብዙ ተአምራት የሚያደርግ ሆነ፡፡ በአንዲት ዕለትም በወህኒ ቤት ሲጸልይ ጌታችን ተገለጠለትና ቃልኪዳን ከገባለት በኋላ በመግሥቱ ከእሥር ቤቱ አውጥተው ወደ በንሑር ከተማ ወስደው ራሱን በሰይፍ ቆረጡት፡፡ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀዳጀ፡፡ መእመናንም የመከራው ዘመን እስኪያልፍ ሥጋውን በክብር ደብቀው አኖሩት፡፡ ደግ ዘመን በመጣ ጊዜ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ቅዱስ ሥጋውን ሰኔ 27 ቀን በውስጧ አኖሩ፡፡ ከሥጋውም ብዙ አስገራሚ ተምራት ተገለጡ፡፡
ረድኤት በረከቱ ይደረርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
አቡነ ተክለ ሐዋርያት፡- አባታቸው የእናርዕት አገረ ገዥ የነበሩት እንድርያስ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ እሌኒ ይባላሉ፡፡ የትውልድ ሀገራቸው ሸዋ ሲሆን በዚሁ የምትገኘውን ታላቋን የደብረ ጽሙናን ገዳም የመሠረቱ ሲሆን በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን የነበሩ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ገና በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ አጋንንትን እያቃጠሉ ያጠፏቸው ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ተምረው ከጨረሱ በኋላ ገና በድቁና እያገለገሉ ሳለ 40 ቀን በማክፈል ይጾሙና ይጸልዩ ነበር፡፡

አባታችን የመነኮሱትና ብዙ ተጋድሎአቸን ፈጽመው ወደ ሰማይ ተነጥቀው ሥላሴን እስከማየት የደረሱት በደብረ ሊባኖስ ነው፡፡ ያመነኮሷቸውም ሁሉን በስውር ያለውን የሚውቁት አቡነ ዮሐንስ ከማ ናቸው፡፡ አባታችን ማታ ማታ ከባሕር ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ እያደሩ በቀን 30 ፍሬ አተር ብቻ እየተመገቡ ይጾሙ ነበር፡፡ ስውራን የሆኑ ቅዱሳን አባታችም እየተገለጡላቸው ምሥጢራትን ይነግሯቸዋል፡፡ ከስግደታቸውም ብዛት የተነሣ የአባታችን ሁለት የእጆቻቸው አጥንቶች ተሰበሩ፡፡ ከቁመታቸውም ብዛት የተነሣ እግሮቻቸው አበጡ፡፡ ስምንት ስለታም ጦሮችን ያሉበትን የብረት ሰንሰለት በወገባቸው ታጥቀው ሁለት ሁለቱን በፊት በኋላ በቀኝ በግራ አድርገው ታጠቁ፡፡ እነዚህም ጦሮች ከልደት፣ ከጥምቀትና ከትነሣኤ በዓል በቀር ከወገባቸው ላይ አያወጧቸውም ነበር፡፡ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ሲቀመጡ፣ ሲነሡና ሲሰግዱ ጦሮቹ ሰውነታቸውን ሲወጓቸው በዚያን ጊዜ የጌታችንን በጦር መወጋቱንና መከራውን ያስባሉ፡፡ በታመሙም ጊዜ ‹‹ኃጢአተኛ ሰውነቴ ሆይ ስለአንቺ የተቀበለውን የክርስቶስን መከራ አስቢ›› እያሉ ሰውነታቸውን ይጎስማሉ፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነጥቆ ወስዶ ከገነት ዕፅ አምጥቶ አባታችንን ካሸታቸው በኋላ ግን ርሃብና ጥም የሚባል ነገር ጠፍቶላቸዋልና ምድራዊውን ነገር ለመቅመስ የሚጸየፉ ሆኑ፡፡ ጻድቁ ቅስና እንዲሾሙ የገዳሙ አበምኔት ግድ ቢሏቸውም አባታችን ግን እምቢ ስላሉ ‹‹ለጳጳሱ መልእክት አድርስልኝ›› ብለው በዘዴ ልከዋቸው ጳጳሱም በመንፈስ ተረድተው ቅስና ሾመዋቸዋል፡፡

ጻድቁ በአቡነ አትናቴዎስ መቃብር ላይ ሄደው አጥብቀው ይጸልዩ በነበረበት ወቅት ብርሃን ይወርድላቸው እንደነበር እግዚእ ክብራ የተባለች አንዲት ትልቅ ጻድቅ እናት ትመለከት ነበር፡፡ አባታችን ሁልጊዜ ‹‹ሦስት ነገሮችን እፈልጋለሁ እነርሱም ከሐሜት ስለመራቅ፣ ክፉ ነገርን ከማየት ስለመራቅና ከንቱ ነገርን ከመስማት ስለመራቅ ናቸው›› እያሉ ይናገሩ ነበር፡፡ አቡነ ተክለ ሐዋርያት የታላቁን አባት የአቡነ አትናቴዎስን መቃብር ለማየት በሄዱ ጊዜ ቆመው ሲጸልዩ ከእግራቸው በታች ጸበል ፈልቆ በጽዋ ውኃ ሲፈስ አገኙት፡፡ ውኃውንም ወስደው ቦታውን ላሳየቻቸው ለእግዚእ ክብራ ሰጧት፡፡ እርሷም መካን ለነበረችው ገረዷ ሰጠቻትና ገረዷም በጻድቁ ጸሎት የፈለቀውን ውኃ ጠጥታ ልጅ ወለደች፡፡ ይህ አባታችን ያፈለቁት ጸበል ዛሬም ድረስ ሲፈስና ሕሙማንን ሲፈውስ ይገኛል፡፡

ጸድቁን የታዘዘ መልአክ መጥቶ ወደ በረሃ እንዲገቡ ስለነገራቸው ወደ ምድረ ሐጋይ ሄደው በዚያ ታላቅ በረሃ ውስጥ ለ41 ዓመታት ጽኑ ተጋድሎን ተጋድለዋል፡፡ ባሕር ውስጥ በሚገኝ ዋሻ ውስጥም ገብተው ብዙ ዘመን በጸሎት ኖረዋል፡፡ ሰዎች የአባታችንን የእግራቸውን እጣቢ ሕመምተኞች ላይ በረጩት ጊዜ በላያቸው ላይ ያደረባቸው ርኩስ መንፈስ እየጮኸ ይወጣል፡፡ ቅዱሳን መላእክት ዘወትር እየመጡ አባታችንን ይጎበነኟቸዋል፡፡ እመቤታችን ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን አስከትላ እየመጣች ትጎበኛቸዋለች፡፡ ብዙ ተጋድሎ ባደረጉበት ዋሻ ውስጥም ሳሉ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ተገልጦላቸው በቦታው ላይ ታላቅ ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ መላእክትም ወደ ሰማይ አሳርገዋቸው በሥሉስ ቅዱስ መንበር ፊት አቁመዋቸው ታላቅ ምሥጢርን አይተዋል፡፡

አቡነ ተክለ ሐዋርያት ለመድኃኔዓለም ሥጋና ደም ትልቅ ክብር ያላቸው አባት ናቸው፡፡ አንድ በከባድ በሽታ ይሠቃይ የነበረ ሰው ‹‹ነፍሴ ከሥጋዬ ሳትለይ ፈጥናችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውሰዱኝና የጌታችንን ሥጋና ደም ልቀበል›› ብሎ ቤተሰቦቹን ለመነ፡፡ ቤተሰቦቹም ወደ ቤተ ክርስቲያን ወስደውት ሥጋ ወደሙን ከተቀበለ በኋላ ከሆዱ ውስጥ ዥንጉርጉር ደምና ሐሞት ከመግል ጋር ወጣ፡፡ በዚህም ጊዜ ካህናቱ ስለ ሥጋ ወደሙ ክብር ብለው በዕቃ ተቀበሉት፡፡ ሽታው ግን ቤተ ክርስቲያኑን አናወጸው፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ተክለ ሐዋርያት መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለእኛ ብሎ በዕለተ ዐርብ መራራ ሐሞትና ከርቤ መጠጣቱን አስበው ከሰውየው ሆድ ውስጥ የወጣውን ደም የተቀላቀለበትን መግልና ሐሞት ስለ ሥጋ ወደሙ ክብር ብለው በቤተ ክርስቲያኑ በተሰበሰቡት ሰዎች ፊት አንሥተው ጠጡት፡፡ ይህም የሆነበት ዕለት እሁድ ነበርና አባታችን እዚያው ቤተ ክርስቲያኑ ዋሉ፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስም አባታችን ወዳሉበት መጥቶ ‹‹ወዳጄ ተክለ ሐዋርያት ሆይ ሰላምታ ይገባሃል፡፡ በሰው ሁሉ ፊት እንዳከበርከኝ እኔም በምድራውያንና በሰማያውያን መላእክት ሁሉ ፊት አከብርሃለሁ›› ካላቸው በኋላ ሌላም ብዙ ቃልኪዳን ገባላቸው፡፡ ሰባት አክሊላትንም ካቀዳጃቸው በኋላ ዕጣ ክፍላቸው ከመጥምቁ ዮሐንስና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር መሆኑን ነግሯቸዋል፡፡

ከዚህም በኋላ አባታችን ወደተለያዩ የሀገራችን ገዳማት በመሄድ ከቅዱሳን በረከትን ከተቀበሉ በኋላ በየሄዱባቸው ገዳማት 40 ቀንና 40 ሌሊት ይጾማሉ፡፡ ከሰንበት በቀርም ምንም ምንመ አይቀምሱም፡፡ ሰንበትም በሆነ ጊዜ የዕንጨቶችን ፍሬ ብቻ ይመገባሉ፡፡ አባታችን ከዋልድባ ገዳም ወጥተው ወደ ደባብ ገዳም በመሄድ በዚያ አርባዋን ቀን ከጾሙ በኋላ ጌታችን ተገለጠላቸውና ‹‹ተነሥተህ ወደአልተጠመቁ አሕዛብ አገር ሂድ በዚያ በአንተ እጅ የሚጠመቁና የሚድኑ ብዙ አሕዛብ አሉና በስሜ አስተምር›› አላቸው፡፡ አባታችንም ተነሥተው ‹‹ሀገረ ጽልመት›› ወደሚባል ወዳልተጠመቁ አሕዛብ አገር ሄደው የአገሪቱን ንጉሥና ሕዝቡንም በጠቅላላ አስተምረው በተአምራቶቻቸው አሳምነው አጥምቀዋቸዋል፡፡ በዚያም ሀገር ለአሕዛብ እየጠነቆለ የሚኖር አንድ መሠርይ ነበርና አባታችንን አግኝተውት አስተምረው በላዩ ያለበትን ርኩስ መንፈስ አውጥተውለት አጥምቀውታል፡፡

አባታችን የእግዚአብሔርን ወዳጅ የሊቀ ነቢያትን መቃብር ያሳቸው ዘንድ ጌታችንን በለመኑት ጊዜ ጌታችን በሌሊት ተገልጦላቸው ወስዶ የሙሴን መቃብር አሳይቷቸዋል፡፡ የአባታችን በትራቸው እንደሙሴ በትር ተአምር ትሠራ ነበር፡፡ ሕመምተኞች በትሯን አጥበው የእጣቢውን ውኃ ሲጠጡት ፈጥነው ከሕመማቸው ይፈወሱ ነበር፡፡ በጌታችን የጥምቀት በዓል ቀን አባታችን ተክለ ሐዋርያት ጸሎት በማድረግ ሰዎችን ሲያጠምቁ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሳቸው ላይ ይታይ ነበር፡፡ በቆሙበትም ቦታ የብርሃን ምሰሶም እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶ ተተክሎ ታይቷል፡፡ አባታችን ቅዱሳት ገዳማትን ለመሳለም ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ የሚዘዋወሩት በብርሃን ሰረገላ ነበር፡፡ በደመናም ተጭነው ሲሄዱ ያዩአቸው ቅዱሳን አሉ፡፡ የመኮትን ቃል ወንጌልን ሲጸልዩ ቅዱሳን መላእክት መጥተው በክንፋቸው ይጋርዷቸው ነበር፡፡ የአቡቀለምሲስን ራእይ በጸለዩ ጊዜ ራሱ ዮሐንስ ወንጌላዊው መጥቶ በአጠገባቸው ይቆም ነበር፡፡
አባታችን የዕረፍታቸው ጊዜ በደረሰ ሰዓት የብርሃን እናቱ እመቤታችን ሚካኤልንና ገብርኤልን ሰማዕቱን ቅዱስ ጊዮርጊስን አስከትላ መጥታ ‹‹የጳውሎስ አበባ የጴጥሮስ ፍሬ የልጄ ተክል ወዳጄ ተክለ ሐዋርያት ሆይ ሰላምታ ይገባሃል›› አለቻቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹እነሆ የተመኘኸውን ታገኘዋለህና፣ ጊዜው ቀርቧልና ጽና በርታ እኔንና ልጄን የለመንከንን ነገር አስብ›› ብላቸው ተሰወረች፡፡ አባታችን በተደጋጋሚ እመቤታችንንና ጌታችንን ስለ ስሙ ብለው ሰማዕት ይሆኑ ዘንድ ይለምኑ ስለነበረ ነው እመቤታችን ይህንን የነገረቻው፡፡

ከዚህም በኋላ የንጉሡ የዐፀ ዘርዐ ያዕቆብ ባለቤት አባታችንን ‹‹ስለ ክርስቶስ ብለሁ መጥተው አስትምሩን ምከሩን›› ብላ ለመነቻቸውና አባታችን ሄደው መከሯት፡፡ ልጃቸውን ገላውዴዎስን አስተምረው ባረኩት፡፡ ለንጉሡ ዐፀ ዘርዐ ያዕቆብም ብዙ ምሥጢርን ነገሩት፡፡ ንጉሡም በአቅራቢያው የእመቤታችን ታቦት ካለችበት ቦታ ሦስት ወር ከእርሱ እንዲቀመጡ ለመናቸው፡፡ እሳቸውም በዚያ ሲቆዩ የንጉሡ ወታደሮች በፈረስ ግልቢያና በድብደባ እየተገዳደሉ አይተው አዘኑ፡፡ ‹‹ይህ የአረመኔዎች ሥራ ነው›› ብለው ሕግንና ሥርዓትን ሊያስተማሯቸው አስበው ወደ ንጉሡ ዐፀ ዘርዐ ያዕቆብ እንዲያናግራቸው መልእክተኛ ላኩበት፡፡ ንጉሡም ‹‹ዛሬ አይመቸኝም›› አላቸው፡፡ አባታችንም መልአክተኛውን ስለ ሰዎቹ በከንቱ መሞትና ሌላንም መልእክቶችን ላኩለት፡፡ መልእክተኛውም የመዘምራን አለቃ ደብተራ ስለነበር አባታችንን ‹‹እኔ እያለሁ ለአንተ ነቢይነትን ማን ሰጠህ?›› ብሎ በክፉ ቃል ተናገራቸውና ሄዶ ከንጉሡ ጋር በክፉ ወሬ አጣላቸው፡፡ ወደ ንጉሡ ገብቶ ‹‹ንጉሥ ሆይ ይህ መነኩሴ ጻድቅ ነኝ ይላል፣ አንተን ግን ይሰድብሃል ባንተ ላይም ብዙ ዘለፋ ይናገራል…›› አለው፡፡ ንጉሡም በጣም ተቆጥቶ አባተችን አስመጥቶ ‹‹ለምን ይዘልፉኛል/›› አላቸው፡፡ አባታችንም ዘለፋ ሳይሆን ሊሆን የማይገባውን ነገር ሁሉ ነገሩት፡፡ ይልቁንም ስለሴቶቸና ስለፍርድና መሥራት ስለማይገባው ነገር ሁሉ ሲናገሩት ንጉሡም ደፍረው ስለተናገሩት በኃይል ይደበድቧቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ ከአፍና አፍንጫቸውም ደም እንደውኃ እስኪርድ ድረስ ደበደቧቸውና አሠሯቸው፡፡

ዳግመኛም ንጉሡ ቢያስመጣቸው ደግመው ስለጥፋቱ ገሠጹት፡፡ አሁንም ጽኑ ድብደባን አደረሱባቸውና አሠሯቸው፡፡ በዚያም ብዙ አሠቃዩአቸው፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን ለአባታችን ለተልጣላቸው ‹‹እነሆ የልጄን ትእዛዝ ፈጸምህ የተመኘኸውን አገኘህ፣ ነገር ግን ሁለት የትዕግስት በር ይቀርሃል እርሱን ከፈጸምክ ልጄ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ያሳርፍሃል›› አለቻቸው፡፡ አባታችንም እመቤታችንን ‹‹ሰማዕትነት ስጪኝ ያልኩሽ በክርስቲያናዊ እጅ ነውን? ነገር ግን አማላጅነትሽ ሰማዕትነትን ለመፈጸም ያጽናኝ›› አሏት፡፡

ከዚህም በኋላ የንጉሡ ጭፍሮች አባታችንን በጠጠር ጎዳና ላይ እየጎተቷቸው ብዙ አሠቃዩአቸው፡፡ የንጉሡ ስምንት ጭፍሮች በመቀጣጠብ ‹‹ንጉሡ መቼ እሞታለሁ›› ብሎሃል እያሉ በመሾፍ አባታችንን ወደ ዱር ወስደው በአቅማቸውን ያህል በኃይል ደበደቧቸው፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ባያጸናቸው ኖሮ በአንደኛው ሰው ዱላ ብቻ ነፍሳቸው በወጣች ነበር፡፡ በእሥርም 8 ወር ከተቀመጡ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት የሚያርፉበት ጊዜ ስለደረሰ ቅዱሳን መላእክት ከእሥር ቤት ነጥቀው ወስደው ወደ ሰማይ አሰረጓቸውና በሥሉስ ቅዱስ ፊት አቆሟቸው፡፡ በዚያም ለሦስት ሳምንት ቆዩ፡፡ ጌታችንም ለአባታችን ብዙ የሕይወትን ምሥጢር ነገራቸው፡፡ እንደጸሐይ የምታበራዋን የምድርን ማዕዘነ ዓለም የምታክል ሰማያዊት ሀገር ርስት አድርጎ ሰጣቸው፡፡ ‹‹ስምህን ከሚጠሩ ልጆችህ፣ የገድልህን መጽሐፍ ከጻፉ ካጻፉ ከሰሙ፣ ዝክርን ካዘከሩ በጸሎትህ ከተማኑ ልጆችህ ጋር የምትኖርባት ዕድል ፈንታህ ናት›› አላቸው፡፡

አባታችንም ጌታችንን ‹‹አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ ይህን ቃልኪዳን የሰጠኸኝ አንተን የሚያስደስት ምን ነገር አደረኩልህ በቸርነትህ ነው እንጂ›› አሉት፡፡ ጌታችንም ‹‹ዕድል ፈንታህ ጽዋ ተርታህ እውነተኛ የእኔ ምስክር ከሚሆን ጊዮርጊስና ወዳጄ ከሚሆን ከዮሐንስ ጋራ ይሁን›› አላቸው፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ሰባት አክሊትን አቀዳጃቸውና ‹‹አንዱ ስለ ድንግልናህ ነው፣ አንዱ ሃይማኖትህን ለማስተማር ከአንዱ ሀገር ወደ አንዱ አገር ስለሄድክ ነው፣ አንዱ ቅዱሳንን ለመጎብኘት እየተዘዋወርክ ከቅዱሳን ጋራ ስለተነጋገርክበት ነው፣ አንዱ ስለየዋህነትህ ኃላፊ ዓለምን ስለመናቅህ ነው፣ አንዱ ስለተወደደ ክህነትህ ነው፣ አንዱ ታግሰህ ስለመጋደልህ ነው፣ አንዱም ደምህን ስለማፍሰስህ ነው›› አላቸው፡፡ ጌታችን ይህን ቃልኪዳንና ክብር ከሰጣቸው በኋለ ‹‹ከዚህ ከሚጠፋው ዓለም አሳርፍሃለሁ›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ከተነጠቁበት ከሦስት ሳምንት በኋላ ተመልሰው ከእሥር ቤቱ ሆነው ያዩትን ሁሉ ለአንድ ወዳጃቸው ለሆነ ቄስ ተክለ ኢየሱስ ነገሩት፡፡

ዳግመኛም አባታችን በእሥር ቤት ሳሉ በመላአክት እጅ ተነጥቀው ወደ ሰማይ ከተወሰዱና ከጌታችን ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኋላ የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን እንዳነጋገረቻቸው ተናገሩ፡፡ ‹‹እመቤታችን ማርያም ‹ዘርዐ ያዕቆብን ይቅር በልልኝ፣ ኃጢአቱንም ተውለት፣ በልጄ ፊት ቀርበህ ‹ግፌን ተመልከትልኝ› አትበል እርሱ ዘወትር ስሜን ይጠራልና፣ ስለ ድንግልናዬም የሚያስተምር ነውና› አለኝ፡፡ እኔም የእመ ብርሃንን ርኅራኄ አደነቅሁና ‹እመቤቴ ሆይ! አንቺ እያዘዝሽኝ ወድጄ ነውን የምመረው! እኔ ኃጢአተኛ ለምን ይቅር አልልም ይቅር እላለሁ እንጂ ነገር ግን የአንቺ ጸሎት ሁላችንንም ይማረን› አልኋት፡፡››

አቡነ ተክለ ሐዋርያት በመጨረሻ ዘመናቸው በንጉሡ አደባባይ ኅዳር 27 ቀን ሲያርፉ ቅዱሳን መላእክት መጥተው ገንዘው ቀብረዋቸዋል፡፡ በመካነ መቃብራቸውም ላይ ብርሃን ተተክሎ ታይቷል፡፡ ንጉሡ ዘርዐ ያዕቆብም በመካነ መቃብራቸው ላይ ብርሃን መውረዱንና ብዙ ተአምራት ማድረጉን በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ፡፡ ብዙ ምልክትም አገኘ፡፡ አባታችን ሰማዕትነትን ይቀበሉ ዘንድ ተመኝተው ራሳቸው ለምነዋልና መደብደብ መሠቃየታቸው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ ንጉሡም መነኮሳት ልጆቻቸውንም ጠርቶ የአባታችንን ሥጋ በክብር እንዲያፈልሱ ነገራቸው፡፡ ርስት ጉልት የሚሆን መሬት ሰጣቸው፡፡ ነገር ግን ዐፅማቸው ከመፍለሱ በፊት ንጉሡ በሞት ስላረፈ ልጁ በእደ ማርያም በአባቱ ትእዛዝ መሠረት የአባታችንን ዐፅም ከ13 ዓመት በኋላ ወደ ደብረ ጽሞና በክብር አፍልሶታል፡፡ ታቦታቸው ደብረ ሊባኖስ አውራጃ አጋት መድኃኔዓለም ይገኛል፡፡

የአቡነ ተክለ ሐዋርያት ረድኤት በረከታቸው ይደረርብን በጸሎታቸው ይማረን!
2024/11/15 17:02:59
Back to Top
HTML Embed Code: