#የዕለቱ_አንገርጋሪ_ግእዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሊያ "ዮም ፍሥሐ ኮነ #በእንተ_ልደቱ_ለክርስቶስ_እምቅድስት_ድንግል_ውእቱ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ አማን መንክር #ስብሐተ_ልደቱ"፡፡ ትርጉም፦ #ከቅድስት_ድንግል_ክርስቶስ_ስለተወለደ ዛሬ ደስታ ሆነ ለእርሱ ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) ሰገዱለት በእውነት #የልደቱ_ምስጋና_ድንቅ_ክቡር_ነው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
"#ሰላም_ለልደቱ_እምድንግል_በቤተልሔም ዘበትርጓሜሁ ቤተ ኅብስት ብሂል። #ሰላም_ለጎል ዘሰከበ ውስቴቱ ከመ ሕፃን ወተጠብለለ ዲበ ምፅንጋዕ በአጽርቅተ ከመ ሰብእ"። ትርጉም፦ የእንጀራ ቤት በተባለ #በቤተልሔም_ከድንግል_ለተወለደው_ለልደቱ_ሰላምታ_ይገባል። እንደ ሰው በግርግም ላይ በጨርቅ የተጠቀለለና በውስጡ እንደ ሕፃን #ለተኛበት_በረት_ሰላምታ_ይገባል። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ።

#ታኅሣሥ_30
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ሠላሳ በዚች ቀን በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ አበ ምኔት የሆነ የከበረ አባት #አባ_ዮሐንስ አረፈ፣ የትንቢትና በሽተኞችን የመፈወስ ሀብት ተሰጠው የተመሰገነ #የአባ_ዮሐንስ_ብጹዕ አረፈ፣ #ቅዱሳን_ኮርዮንና_ፊልሞና ከእነርሱም ጋር አርባ ወታደሮች በሰማዕትነት ሞቱ፣ ተጋዳይ የሆነ #አባ_ዘካርያስ_ገዳማዊ አረፈ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ዮሐንስ_አበ_ምኔት
ታኅሣሥ ሠላሳ በዚህች ቀን በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ አበ ምኔት የሆነ የከበረ አባት አባ ዮሐንስ አረፈ።
ይህም አባት በተሾመ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በራች ለብዙ ቅዱሳንም አባት ሆነ ከእርሳቸውም ውስጥ ታላላቅ ከዋክብት የሆኑ አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም የሀገረ ተሙዝ ኤጲስቆጶስ አባ ሚናስ የሀገረ ስሐ አባ ዘካርያስ ለብዙ ሰዎች ነፍሳት ወደብ የሆኑ እነርሱን የመሰሉ ሌሎች ብዙዎች አሉ። ለሕዝቡ ቅዱስ ቊርባንን በሚያቈርብ ጊዜ ኃጢአተኛውና ጻድቁ ይገለጥለታል ከቅዱሳን መላእክቶቹ ጋር #ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስንም በመሠዊያው ላይ ብዙ ጊዜ አየው።
በአንዲትም ዕለት ሥራው የከፋ አንዱን ቄስ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ አየው ከእርሱም ጋር ያሉ ብዙዎች ርኩሳን የረቀቁ አጋንንት ከበውት አፉ ውስጥ ልጓም አድርገዋል ወደ ቤተ ክርስቲያንም ከመግባቱ በፊት የ #እግዚአብሔር መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ በእሳት ሰይፍ ከእርሱ ከቄሱ መናፍስትን አሳደዳቸው ቄሱም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ መቀደሻውን የክህነት ልብስ ለበሰ ሁለመናውም እንደ እሳት ሆነ ቀድሶም ለሕዝቡ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን አቀበላቸው።
ልብሰ ተክህኖውንና የመቀደሻውን ሽልማት ከላዩ አውልቆ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜ እንዚያ የጠቆሩ መናፍስት ርኩሳን ተቀብለው እንደቀድሞው አደረጉበት።
አባ ዮሐንስም ይህን ነገር ለመነኰሳቱ ሲያስረዳ እንዲህ አላቸው በቅዳሴ አገልግሎት ጊዜ ለኃጢአተኛውና ለጻድቁ ቄስ ልዩነት የለም ስለ ሕዝቡ እምነት ያ ኅብስት ተለውጦ የ #ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋ ይሆናልና ወይኑም የከበረ ደሙን ይሆናልና።
ዳግመኛ በምሳሌ እንዲህ አላቸው በብረት በወርቅና በብር ላይ እንደሚቀረጽ እንደ ንጉሥ ማኅተም ነው። ማኅተሙም አይለወጥም እንዲሁ ከካህናትም የክህነት ጸጋ አይለወጥም እርሱ #እግዚአብሔር በጊዜው ጊዜ ለሁሉም ለየአንዳንዱ እንደሠራው ይከፈለዋል እንጂ።
ይህንም የከበረ ዮሐንስ ታላቅ መከራ ደርሶበታል አረማውያን በርበር ማረከው ወደ አገራቸወደ ወስደውታልና እያሠቃዩትም በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመን ታሥሮ ኖረ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ገዳሙ መለሰው።
ከመሞቱ በፊት የሚሞትበትን ጊዜ አውቆ መነኰሳቱን ሰበሰባቸውና የወንጌልን ትዕዛዝ ይጠብቁ ዘንድ በሰማያዊ መንግሥት በጎ ዕድልን ርስትንም ከእርሳቸው ጋር ይቀበሉ ዘንድ እንደ ቅዱሳን አባቶች አካሄድ እንዲጓዙ አዘዛቸው።
ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመ ነፍሱን ሊቀበሉ የቅዱሳንን አንድነት ሲመጡ አያቸውና ፈጽሞ ደስ አለው ነፍሱንም በ #እግዚአብሔር እጅ ሰጠ መነኰሳቱ ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ተሸክመው ወስደው በመዘመርና በታላቅ ምስጋና ገንዘው ቀበሩት እርሱንም ከመውደዳቸው የተነሣ ከተገነዘበት ልብስ ቆርጠው በእነርሱ ዘንድ አኖሩት ለሚታመም ሁሉ የሚፈውስ ሆነ የዚህም አባት ዕድሜ ዘጠና ዓመት ሆነ በግቢግ የሚልዋት መኖሪያው እስከ ዛሬ አለች።
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእኚህ አባት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ዮሐንስ_ብጹዕ
በዚህችም ቀን ደግሞ የተመሰገነ የአባ ዮሐንስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ይህም ተጋዳይ የምንኲስና ልብስን ከለበሰ ጀምሮ የትንቢትና በሽተኞችን የመፈወስ ሀብት ተሰጠው ዜናውም በሀገሩ ሁሉ ተሰማ።
ይህን አባ ዮሐንስን ሁል ጊዜ የሚጐበኘው አንድ መኰንን ነበረ የመኰንኑም ሚስት ወደ አባ ዮሐንስ ዘንድ እንዲወስዳት ባሏን ታምለውና ታስገደድው ነበር እርሱም የከበረ አባ ዮሐንስ ከአርባ ዓመት ጀምሮ የሴቶችን ፊት አላየም አላት። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሒዶ ሚስቱ ያለችውን ለአባ ዮሐንስ ነገረው አባ ዮሐንስም በ #እግዚአብሔር ፈቃድ የፈለገችውን እፈጽምላታለሁ አለው።
በዚያችም ሌሊት የከበረ ዮሐንስ ለዚያች ሴት በሕልም ተገልጾ እንዲህ አላት ጻድቅ ያልሆንኩ ወይም ነቢይ የኔን ፊት ታዪ ዘንድ የምትሺ አንቺ ሴት ከእኔ ምን አለሽ እኔስ ካንቺ ምን አለኝ እንግዲህስ ፊቴን ማየት አትሺ ይህንንም ብሎ በላይዋ ጸልዮ ባረካት።
በማግሥቱም የከበረ አባ ዮሐንስ በመንፈስ እንደታያት ለባሏ ነገረችው። መልኩንና አምሳያውን አመለከተችው ከዚህም በኋላ ከብዙ ሙገሳና ምስጋና ጋር ባሏን ወደ አባ ዮሐንስ ላከችው።
የከበረ ዮሐንስም ባሏን በአየው ጊዜ ፈገግ ብሎ የሚስትህ ምኞቷ የተፈጸመላት አይደለምን በዚች ዕለት በ #እግዚአብሔር ፈቃድ አግኝታኛለችና አለው መኰንኑም ሰምቶ ከትሩፋቱና ከደግነቱ የተነሣ እጅግ አደነቀ። ይህም አባ ዮሐንስ ጭንቅ በሆነ ተጋድሎ ዘጠና ዓመት ያህል ኖረ ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።

#ቅዱሳን_ኮርዮንና_ፊልሞና
በዚህችም ዕለት የመኰንኑ አርያኖስ የጭፍሮቹ ታላላቆች ኮርዮንና ፊልሞና ከእርሳቸውም ጋር ካሉ አርባ ወታደሮች ጋር በሰማዕትነት ሞቱ።
የሰማዕትነታቸውም ምክንያት የአክሚም ታላላቆች ከሆኑ ከሰማዕታት ዲዮስቆሮስ ከሰከላብዮስና ከብኑዲያስ የተደረገውን ተአምራት በአዩ ጊዜ የወታደርነት የማዕረግ ሽልማታቸውን ጣሉ በመኰንኑ አርያኖስም ፊት ቁመው እኛ በእውነተኛ አምላክ በ #ክርስቶስ የምናምን በግልጥ ክርስቲያን ነን ብለው ጮኹ። መኰንኑም ከእሳት ማንደጃ ውስጥ ይጥሏቸው ዘንድ አዘዘ ራሳቸውንም ሲወረወሩ ብዙዎች አዩአቸው ገድላቸውንም እንዲህ ፈጸሙ።
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ዘካርያስ_ገዳማዊ
በዚህችም ዕለት ተጋዳይ የሆነ ዘካርያስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከመመንኰሱ በፊት በጐዳና ሲጓዝ አረማውያን በርበር ተነሡበትና ያዙት ሊያርዱትም ወደዱ በ #እግዚአብሔርም ፈቃድ የገዳሙ አለቃ በዚያት ጐዳና ሲያልፍ በላያቸው ጮኸ እነርሱም ሠራዊት እንደደረሰባቸው ተጠራጠሩ ፈርተውም ሸሹ ሲሸሹም ከባሕር ገብተው ሰጠሙ።
ዘካርያስም ከመገደል በዳነ ጊዜ ይሸጥ ዘንድ ገንዘባቸውን ይዞ ወደ ከተማ ገባ የሀገሩም ገዥ ያዘው ሌባ እንደ ሆነ አስቦ ሊገለው ወደደ ግን ሥራውን በአወቀ ጊዜ ተወው።
ከዚህም በኋላ ወደ አባ ጳኩሚስ ገዳም ሒዶ የምንኲስናን ልብስ ለበሰ ሰይጣንም እስከ ቀናበት ድረስ በጾምና በጸሎት ተጠመደ ከዚህም በኋላ በአባቱ ተመስሎ በሕልም ታየውና መሞቻዬ ጊዜ ደርሷልና ትቀብረኝ ዘንድ ና አለው ቅዱሱም እውነት እንደሆነ አስቦ ወደ አባቱ ሔደ ግን በጤንነት አገኘው። የሰይጣን ተንኰልም እንደሆነ አውቆ ወደ መኖሪያው ተመለሰ ሰይጣንንም ድል እስከአደረገው ድረስ በሩን ዘግቶ እየተጋደለ ኖረ።
በሆሣዕናም ዕለት ወደ አበ ምኔቱ ሒዶ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ ፈቃድ ለመነው ፈቀደለትም በማግሥቱም ፊታቸው የሚያባራ ሦስት ሰዎች ሲጠብቁት አገኛቸውና አብሮዋቸው ሔደ።

ከዚህም በኋላ አበ ምኔቱ የአባ ዘካርያስን ቤት ሊጎበኝ ሔደ ሦስት ታላላቅ ዘንዶዎችም በምድር ላይ ሲርመሰመሱ አግኝቶ በአያቸው ጊዜ ፈራቸው እነርሱም በስሙ ጠሩት ወደነርሱም ዘወር ሲል አባት ሆይ ሲመግበን የነበረ #ጌታችን ዘካርያስ ከዚህ ወደየት ሔደ ብለው በሰው አንደበት ተናገሩት። አበ ምኔቱም ሰምቶ አደነቀ መብልንም ሰጣቸው።
አባ ዘካርያስም ወደ መኖሪያው ተመልሶ በብዙ ተጋድሎ ኖረ። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ_30)

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_30_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ፊልጵስዩስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ እንግዲህ ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ፤ በአንዳች ነገርም ልዩ አሳብ ቢኖራችሁ፥ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል፤
¹⁶ ሆኖም በደረስንበት በዚያ እንመላለስ።
¹⁷ ወንድሞች ሆይ፥ እኔን የምትመስሉ ሁኑ፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ።
¹⁸ ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ።
¹⁹ መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።
²⁰ እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤
²¹ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
¹³ ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤
¹⁴ ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።
¹⁵ በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤
¹⁶ አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።
¹⁷ ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ።
¹⁸ ሎሌዎች ሆይ፥ ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ።
¹⁹ በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባዋልና።
²⁰ ኃጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።
²¹ የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ወደ ምኵራብም ገብቶ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተነጋገረና እያስረዳቸው ሦስት ወር ያህል በግልጥ ይናገር ነበር።
⁹ አንዳንዶች ግን እልከኞች ሆነው በሕዝብ ፊት መንገዱን እየሰደቡ ባላመኑ ጊዜ፥ ከእነርሱ ርቆ ደቀ መዛሙርትን ለየ፥ ጢራኖስም በሚሉት በትምህርት ቤት ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር።
¹⁰ በእስያም የኖሩት ሁሉ አይሁድም የግሪክ ሰዎችም የጌታን ቃል እስኪሰሙ ድረስ ሁለት ዓመት ያህል እንዲህ ሆነ።
¹¹ እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥
¹² ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር።
¹³ አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች፦ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ።
¹⁴ የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት።
¹⁵ ክፉው መንፈስ ግን መልሶ፦ ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው።
¹⁶ ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም።
¹⁷ ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤
¹⁸ አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር።
¹⁹ ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_30_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ ወኵሎ ዓሚረ ይድኅርዎ። (መዝ.71÷15) ትርጉም👇
“እርሱ ይኖራል ከዓረብም ወርቅ ይሰጡታል፤ ሁልጊዜም ወደ እርሱ ይጸልያሉ፥ ዘወትርም ይባርኩታል።” (መዝ.71÷15)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_30_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
³ ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤
⁴ የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።
⁵-⁶ እነርሱም፦ አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት።
⁷ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥
⁸ ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ፦ ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው።
⁹ እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።
¹⁰ ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።
¹¹ ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
¹² ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታችን_የማርያም_ቅዳሴ_ነው። መልካም የ #ብርሃነ_ልደቱ በዓል ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
✝✝" #ጥር 1 "
✝<<< እንኩዋን ለቅዱስ "እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት" እና "ለአክሚም ሰማዕታት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ >>>✝
+*" ✝ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት✝ "*+
=>በሕገ ወንጌል (ክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው:: ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ:: (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ:: የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5:33 ላይ ተጠቅሷል::
+በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን : ዻውሎስን : ናትናኤልን : ኒቆዲሞስን . . .) አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል::
+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር::
+በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ6 ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ::
+ለ6 ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በሁዋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ:: በወቅቱ
የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ
መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው::
"ከእኔ ይልቅ
ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው:: ቅዱሱም
ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ:: (ሉቃ. 7:18)
በዚያውም
የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ:: ጌታም ከ72ቱ አርድእት
አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው:: አጋንንትም
ተገዙለት::
(ሉቃ. 10:17)
ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ
ዓለም ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን
ተማረ::
ምሥጢር አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ
ከተነሳ በኋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ
ባርኳል:: በዚህ
ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን
(ዽዽስናን) ተሹሟል:: በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ
በወረደ ጊዜ ከ72ቱ
አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት:ምሥጢርም
የተገለጠለት የለም:: በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን
ይሰብክ ገባ::
በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት
ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ 7
ዲያቆናት
ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ6ቱ ዲያቆናት
አለቃ እና የ8ሺው ማሕበር መሪ (አስተዳዳሪ) ሆኗል::
8ሺ ሰውን
ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ
ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው::
አንድን ሰው
ተቆጣጥሮ
ለድኅነት ማብቃት እንኳ እጅግ ፈተና ነው:: መጽሐፍ
እንደሚል ግን 'መንፈስ ቅዱስ የሞላበት: ማሕደረ
እግዚአብሔር'
ነውና ለእርሱ ተቻለው:: (ሐዋ. 6:5) አንዳንዶቻችን ቅዱስ
እስጢፋኖስ 'ሊቀ ዲያቆናት' ሲባል እንደ ዘመኑ ይመስለን
ይሆናል:: እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው::
ዲቁናው ለእርሱ 'በራት ላይ ዳረጐት' ነው እንጂ እንዲሁ
ዲያቆን
ብቻ አይደለም::
ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ
ለ 1 ዓመት ያህል 8ሺውን ማኅበር እየመራ: ወንጌልን
እየሰበከ
ቢጋደል ኦሪት 'እጠፋ እጠፋ': ወንጌል ደግሞ 'እሰፋ እሰፋ'
አለች:: በዚህ ጊዜ 'ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው
ቅዱስ
እስጢፋኖስን መግደል
ነው' ብለው አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም
አልቀሩ ገደሉት::
+እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ
ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: በመጨረሻውም ስለ
እነሱ ምሕረትን
እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ
ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት::
*"ፍልሠት"*
+ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ300 ዓመታት በኋላ
በኢየሩሳሌም የሚኖር አንድ ደግ ሰው ነበር:: ስሙም
ሉክያኖስ ይባል
ነበር:: በተደጋጋሚ በራዕይ ቅዱሱ እየተገለጠ "ሥጋየን
አውጣ" ይለው ነበርና ሒዶ ለዻዻሱ ነገረው:: ዻዻሱም
ደስ ብሎት
ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ወደ አጸደ ገማልያል
(የመምሕሩ ርስት ነው) ሔደ::
+ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ::
መላእክት ሲያጥኑ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ዝማሬ መላእክትም
ተሰማ:: ሕዝቡና
ዻዻሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው: በታላቅ
ዝማሬና በሐሴት ዐጽሙን ከዚያ አውጥተው: በጽርሐ
ጽዮን (በተቀደሰችው
ቤት) አኖሩት::
እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተ
ክርስቲያን አንጾለት ወደዚያ አገቡት:: ከ5 ዓመታት
በኋላም
እለ እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጐን
ስለ ፍቅሩ አኖሩት::ሚስቱ ወደ ሃገሯ ቁስጥንጥንያ
ስትመለስ
የባሏን ሥጋ መስሏት የቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ
በመርከብ ጭና ወሰደችው:: መንገድ ላይ ከሳጥኑ ውስጥ
ዝማሬ ሰምታ
ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው:: እጅግ ደስ
አላት: አምላክ ለዚህ አድሏታልና::
እርሷም ወስዳ ለታላቁ
ንጉሥ
ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አስረከበች:: በከተማውም ታላቅ
ሐሴት ተደረገ::ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው
ሲወስዱትም በቅሎዋ
በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች:: በዚያም ላይ
ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ታንጾለታል:: ቅዱስ እስጢፋኖስ
ሲመቱ
ጥቅምት 17: ዕረፍቱ ጥር 1:ፍልሠቱ ደግሞ መስከረም
15 ቀን ነው::
'' ሰማዕታተ አክሚም ''
+በቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ታሪክ አሰቃቂ ጭፍጨፋ
ከተካሔደባቸው አካባቢዎች አንዷ ሃገረ አክሚም ናት::
አክሚም
ማለት የቀድሞ የግብጽ አውራጃ ናት:: በተለይ በ3ኛው
መቶ ክ/ዘመን በርካታ ክርስቲያኖች በፍቅር ይኖሩባት
ነበር::
በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ጥቡዓን:
ታማኞች:ሥጋውን ደሙን የሚቀበሉና ዘወትር ቅዱስ ቃሉን
ለመስማት
የሚተጉ ነበሩ:: ለዚህም ደግሞ ከሊቀ ዻዻሱ አባ
ብኑድያስ ጀምሮ ካህናቱ: ዲያቆናቱ: ንፍቅ ዲያቆናቱ:
መጋቢዎቹ:
አናጉንስጢሶቹ (አንባቢዎቹ): መምሕራኑ: መሣፍንቱም
ሳይቀር ለክርስቶስ ፍቅር የተጉ መሆናቸው አስተዋጽኦ
ነበረው::
በተለይ ግን 2 ወንድማማቾች የነበራቸው ቅድስና
ብዙዎችን ስቧል:: እኒህ ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና ሰከላብዮስ
ይባላሉ::
ከባለ ጸጋና ባለ ስልጣን ቤተሰብ ቢወለዱም ክርስትናቸው
አልቀዘቀዘም:: የወጣትነት ስሜት ሳያሸንፋቸውም ወደ
በርሃ ተጓዙ::
+በዚያም በቅድስና ኑረው ለክህነት ማዕረግ በቅተዋል::
ቅዱሳኑ በገዳም ሳሉም መድኃኒታችን ክርስቶስ ተገልጦ
"ወደ ትውልድ ሃገራችሁ አክሚም ተመለሱ:: ክብረ ሰማዕታት

ይጠብቃቹሃል" አላቸው:: እነርሱም ደስ እያላቸው
በፍጥነት ወደ
አክሚም ወጡ::በዚያ ሰሞን የጌና ጾም ተፈጽሞ
የአክሚም ክርስቲያኖች ለበዓለ ልደት ዝግጅት ሲያደርጉ
በጠላት ሠራዊት
ተከበቡ::ይህ ሠራዊት የተላከው ከርጉም
ዲዮቅልጢያኖስ ሲሆን መሪው ደግሞ አርያኖስ ነው::
ዋናው ተልዕኮው
ክርስቲያኖችን ለጣዖት ማሰገድ: እንቢ ካሉ ደግሞ
መግደል ነው:: ክርስቲያኖቹ መከበባቸውን እያወቁ
አልፈሩም:: ታኅሳስ
29 ቀንም ሁሉም የከተማዋ ክርስቲያኖች ወደ ቤተ
ክርስቲያን ተሰበሰቡ::በዚያም ሊቀ ዻዻሱ ሥርዓተ ቅዳሴን
አደረሱ::
ሁሉም
በተመስጦ ይጸልዩ ነበርና የክብር ባለቤት ክርስቶስ
በገሃድ ተገለጠላቸው:: በዓይናቸው እያዩም ሥጋ ወደሙን
አቀበላቸው::
ቅዳሴው ሲጠናቀቅ ግን አርያኖስና ሠራዊቱ ደርሰው
ሁሉንም ክርስቲያኖች ያዛቸው::
+ክርስቶስን ክደው ከመገደል እንዲድኑ ተጠየቁ:: እነርሱ
ግን በአንድ ድምጽ "አይሆንም" አሉ:: በዚያን ጊዜ
ወታደሮቹ
በክርስቲያኖች አንገት ላይ በሰይፍ ይጫወቱ ያዙ::በተራ
አሰልፈው ዻዻሱን: ካህናቱን: ዲያቆናቱን:
አንባቢዎችን:መሣፍንቱን ሳይጨምር ከ16,000 በላይ
ክርስቲያኖች ደማቸው ፈሰሰ:: የቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር
ሞልቶ ደም
ወደ ውጭ 20 ክንድ ያህል ፈሰሰ::
በክርስቲያኖች ላይ
ግፍ ተፈጸመ::አካባቢውም ያለ ወሬ ነጋሪ ቀረ:: ግድያው
ለ3
ቀናት ቀጥሎ ጥር 1 አንድ ቀን ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና
ሰከላብዮስ ሲገደሉ ተጠናቀቀ::
✞አምላከ ሰማዕታት ፍቅረ ሃይማኖታቸውን ያሳድርብን::
ከበረከታቸውም ይክፈለን::
✞ጥር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት (ሊቀ ዲያቆናት)
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ አክሚም
3.ቅዱሳን ዲዮስቆሮስ ወሰከላብዮስ
4.ቅዱስ ለውንድዮስ ሰማዕት
5.አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት
በ 01 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
✞እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል
ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር . . . አንዳንዶቹ
ተነስተው
እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም
ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ
በሙሴ
ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር
ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ . . . በሸንጐም
የተቀመጡት ሁሉ
ትኩር
ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት::
(ሐዋ. 6:8-15)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
በፍጥነት ወደ
አክሚም ወጡ::በዚያ ሰሞን የጌና ጾም ተፈጽሞ
የአክሚም ክርስቲያኖች ለበዓለ ልደት ዝግጅት ሲያደርጉ
በጠላት ሠራዊት
ተከበቡ::ይህ ሠራዊት የተላከው ከርጉም
ዲዮቅልጢያኖስ ሲሆን መሪው ደግሞ አርያኖስ ነው::
ዋናው ተልዕኮው
ክርስቲያኖችን ለጣዖት ማሰገድ: እንቢ ካሉ ደግሞ
መግደል ነው:: ክርስቲያኖቹ መከበባቸውን እያወቁ
አልፈሩም:: ታኅሳስ
29 ቀንም ሁሉም የከተማዋ ክርስቲያኖች ወደ ቤተ
ክርስቲያን ተሰበሰቡ::በዚያም ሊቀ ዻዻሱ ሥርዓተ ቅዳሴን
አደረሱ::
ሁሉም
በተመስጦ ይጸልዩ ነበርና የክብር ባለቤት ክርስቶስ
በገሃድ ተገለጠላቸው:: በዓይናቸው እያዩም ሥጋ ወደሙን
አቀበላቸው::
ቅዳሴው ሲጠናቀቅ ግን አርያኖስና ሠራዊቱ ደርሰው
ሁሉንም ክርስቲያኖች ያዛቸው::
+ክርስቶስን ክደው ከመገደል እንዲድኑ ተጠየቁ:: እነርሱ
ግን በአንድ ድምጽ "አይሆንም" አሉ:: በዚያን ጊዜ
ወታደሮቹ
በክርስቲያኖች አንገት ላይ በሰይፍ ይጫወቱ ያዙ::በተራ
አሰልፈው ዻዻሱን: ካህናቱን: ዲያቆናቱን:
አንባቢዎችን:መሣፍንቱን ሳይጨምር ከ16,000 በላይ
ክርስቲያኖች ደማቸው ፈሰሰ:: የቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር
ሞልቶ ደም
ወደ ውጭ 20 ክንድ ያህል ፈሰሰ::
በክርስቲያኖች ላይ
ግፍ ተፈጸመ::አካባቢውም ያለ ወሬ ነጋሪ ቀረ:: ግድያው
ለ3
ቀናት ቀጥሎ ጥር 1 አንድ ቀን ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና
ሰከላብዮስ ሲገደሉ ተጠናቀቀ::
✞አምላከ ሰማዕታት ፍቅረ ሃይማኖታቸውን ያሳድርብን::
ከበረከታቸውም ይክፈለን::
✞ጥር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት (ሊቀ ዲያቆናት)
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ አክሚም
3.ቅዱሳን ዲዮስቆሮስ ወሰከላብዮስ
4.ቅዱስ ለውንድዮስ ሰማዕት
5.አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት
በ 01 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
✞እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል
ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር . . . አንዳንዶቹ
ተነስተው
እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም
ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ
በሙሴ
ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር
ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ . . . በሸንጐም
የተቀመጡት ሁሉ
ትኩር
ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት::
(ሐዋ. 6:8-15)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>