Telegram Web Link
ቅዱስ ላሊበላ ሥራውን ከዚህች ቦታ እንደሚጀምርና መጀመርያ የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን እንደሚሰራ አወቀ በዚህም መሰረት በመጀመርያ ደረጃ ቤተ #ማርያም ሠራ። ከዚያም ቤተ #መድኃኔዓለም፣ ቤተ #መስቀልን፣ ቤተ ደናግል፣ ቤተ ጊዮርጊስ፣ቤተ ገብርኤል ወቤተ ሚካኤል፣ ቤተ መርቆሬዎስ፣ ቤተ #አማኑኤል፣ ቤተ አባ ሊባኖስ። እነዚህን ቤተ መቅደሶች #መንፈስ_ቅዱስ ጥበብን ገልፆታልና ግድግዳውን፣ ጣራውን፣ በሩንና መስኮቱን፣ አእማዱን ቅኔ ማህሌቱን ልዩ ልዩ ቅርፅ እያመጣ እያስጌጠና እያሳመረ ከመላዕክት ጋር እመቤታችን እየተራዳችው በ23 ዓመት በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ እነዚህን አስደናቂ ቤተ መቅደሶች ሰርቶ አጠናቀቀ።

ቅዱስ ላሊበላ የአነፃቸው አብያተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ በውጭም አገር ብዙ እንደሆኑ ታሪኩ ይገልጻል። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን እንደ ምሳሌ ብንመለከታቸው፦ አዲዲ ማርያም፣ አሸተ ማርያም ጀምሮ ነበር፣ ሶማርያ መቅደስ ማርያምን (መቃዲሾ ውስጥ) ብዙ የተጀመሩና ተሰብስበው አገልግሎት የሚሰጡ በኢትዮጵያ ብቻ 23 እንደሚደርሱ ታሪክ ያወሳል።

ቅዱስ ላሊበላ መዋዕለ ዘመኑን በሰላም፣ በፅኑ፣ በእምነት፣ በፍቅርና በአንድነት ከአሳለፈ በኋላ ንግስናውን ለወንድሙ ልጅ እንዲሁም ለአሳደገውና በረከቱን ለሰጠው ለቅዱስ ነአኵቶ ለአብ አስረክቦ በጾም በፀሎት ተወስኖ ኖረ። ከዚህም በኋላ የሚያርፍበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በብርሃን ሠረገላ ተቀምጦ የሚአስፈራ መብረቅን ተጐናጸፎ አእላፋት ሠራዊቶቹ ዙሪያውን ሁነው ወደርሱ መጥቶ እንዲህ አለው "ወዳጄ ላሊበላ ሆይ ሰላም ይሁንልህ እኔ በማይታበል ቃሌ እነግርሃለሁ ማደሪያህ ክብርር ሁሉ ከከበሩ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያቶቼ ጋራ ይሁን። በጸሎትህና በቃልኪዳንህ ለሚታመን እምነቱ እንደ ቅዱሳን ጴጥሮስኔ ጳውሎስ ደም መፍሰስ ይሆንለታል።

ወደ ቤተ መቅደስህም የሔደ በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደሴ እንደ ሔደ ይሆንለታል መቃብርህንም የተሳለመ የሥጋዬን መቃብር እንደ ተሳለመ ይሆንለታል በዓመታቱ ወሮች ሁሉ የተራቡትን እያጠገበ፣ የተጠሙትንም እያጠጣ መታሰቢያህን የሚያደርግ እኔ የተሠወረ መና እመግበዋለሁ የሕይወት ጽዋንም አጠጣዋለሁ። በመታሰቢያህ ቀንም ዕጣን ወይም ስንዴ የሚያገባውን እኔ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት በውስጠኛው መጋረጃ አስቀምጬ ከተቆረሰው ሥጋዬ አቆርበዋለሁ፤ በአማላጅነትህም እየታመነ የገድልህንና የቃል ኪዳንህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ያንተ ስም በተጻፈበት ቦታ እኔ ስሙን እጽፋለሁ፣ በፍጹም ልቡ ለሚያምን ይሁን የማይታበይ ቃል የተናገርኩ የሕያው #እግዚአብሔር ልጅ እኔ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ነኝ" አለው።

ቅዱስ ላሊበላም ይህን ቃል ኪዳን ስለ አጸናለት ክብር ይግባውና #ጌታችንን እያመሰገነ በምድር ላይ ወድቆ ሰገደ። #ጌታችንም ሰላምታ ሰጥቶት በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ። ከዚህም በኋላ ጥቂት ሕማም ታሞ ሰኔ12 ቀን በ1197ዓ.ም በ96 ዓመቱ በሰላም ዐረፈ። ሲያርፍም ደገኛው ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጋር ነገራተ #እግዚአብሔርን እየተነጋገሩ እንዳለ ድንገት እንደ እንቅልፍ ሸለብ አድርጎት እንደሆነ ታሪኩ ይገልፃል። ነፍሱንም የብርሃን መላእክት ተቀብለው የዘላለም ሕይወት ማደሪያ ወደሆነ ማረፊያው አስገቡት። (የሰኔ12 ስንክሳርና ቅዱሳንና ድንቅ ሥራቸው የአራቱ ቅዱሳን ነገሥታት ታሪክ ከሚለው መጽሐፍ።)

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ላሊበላ ጸሎት ይማረን በረከቱም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ኢያሱ_ነቢይ

በዚህችም ዕለት ከኤፍሬም ወገን መስፍኑ ኢያሱ ተወለደ እርሱም ለእስራኤል ልጆች ከጠላት ሰልፍ መድኃኒት ሁኖ ያዳናቸው ነው። የ #ጌታችንም መወለድ ለአዳምና ለልጆቹ መድኃኒት ሆናቸው። የርሱም የቀድሞ ስሙ ሆሴዕ ነበረ እስራኤልን ከአማሌቅ ጦርነት በራፌድ በአዳናቸው ጊዜ ኢያሱ ተብሎ ተጠራ ይህም አዳኝ ማለት ነው።

ሙሴም ከሞተ በኋላ #እግዚአብሔር መረጠውና ለእስራኤል መስፍን አድርጎ ሾመው ልዩ ከሆኑ አሕዛብም ጦርነት አዳናቸው ርስታቸውንም አወረሳቸው ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ኢያሱ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጻድቅ_አቃርዮስ

በዚህችም ዕለት የሮሀ ንጉሥ አቃርዮስ አረፈ የርሱም ግዛቱ በሶርያ አገር ሰርሜን በምትባል ክፍል ነው እርሷም ሮሀ ናት።

ጣዖትን የሚያመልክ ሆኖ ኖረ መፃጉዕም ነበረ ለባለ መድኃኒቶችም ገንዘቡን ሁሉ ሰጥቶ ሊአድኑት አልቻሉም። የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በሽተኞችን በማዳን አጋንንትን በማስወጣት የዕውሮችን ዐይኖች በመግለጥ ሙታንን በማስነሣት የሚሠራውን ድንቅ ተአምራቱን በሰማ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደርሱ ላከ።
የሰውን ሥጋ ለብሰህ በኢየሩሳሌም የተገለጥክ የ #እግዚአብሔር ልጅ ምስጋና ይድረስህ ከእርሱ ሳትለይ ወደታች ለላከህ ለቸር #አባትህም ምስጋና ይድረሰው አንተ የምትስተካከለው #ክርስቶስ እንደሆንክ በሕሊናየ ለገለጠልኝ #መንፈስ_ቅዱስም ምስጋና ይሁን። ያለወንድ ዘር በድንግልና ለወለደችህም እናትህ ምስጋና ይሁን ለሚያምኑብህ ሁሉ ሰላምታ ይድረሳቸው።

እኔም በአንተ አምኜ ከንቱ ጣዖትን ከማምለክ አንተን ወደ ማምለክ ተመለስኩ በኔ ላይም ንጉሥ ትሆን ዘንድ ሀገሬንም ትባርክ ዘንድ ከበሽታዬም ታድነኝ ዘንድ ከኃጢአቴም ታነጻኝ ዘንድ ወደኔ ና #ጌታዬ_ሆይ የከበረ ስምህን አይሁድ ሲጠሉ ለአንተ በኢየሩሳሌም መኖር ምን ያደርግልሃል። በከንቱ ለምን ትደክማለህ መካር ያጡ ወገኖች ናቸውና በቀድሞ ዘመንም ድንቆች ተአምራቶችን በማድረግ ከግብጽ አገር በአወጣኻቸው ጊዜ አላመኑብህም በበረሀም አርባ ዓመት መናውን በመገብካቸው ጊዜ ተቆጥተህ ለጥፋት እስከ አደረስካቸው በአንተ ላይ ምን ያህል አጒረመረሙብህ በሚራብና በሚጠማ ምድራዊ ሥጋማ ሲያዩህ እንዴት ነዋ ኀሳባቸው ከዚህ የተለየ ይመስልሃልን አንተ ከጥንት ጀምሮ የተሠወረውን ታውቃለህና። ይኸንንና ይህን የመሰለውን ጽፎ ደብዳቤ ወደርሱ ላከ።

የንጉሥ መልክተኞችም ወደ #ጌታችን በደረሱ ጊዜ ሳይነግሩት የሰመጡለትን መልእክት አውቆ ነጭ ልብስ አነሥቶ ፊቱን አሸበት የፊቱም መልክ ወደ ልብሱ ገባ ከደቀ መዝሙሩ ከታዴዎስ ጋር እንዲህ ብሎ ላከለት ይህን የኔ መልክ የሆነውን ሥዕል ተቀበል እርሱም የምትሻውን ሁሉ ይፈጽምልሃል ከበሽታህም ይፈውስሃል ሀገርህንም ይባርካል መንግሥትህንም ያጸናል ይህ ሥዕል እኔን ነውና ይለወጥ እንደሆነ በውኃ በእሳት ፈትነው።

መልክተኞችም ወደ ንጉሥ አቃርዮስ በደረሱ ጊዜ ያንን ሥዕል ሰጡት በእሳትና በውኃም ፈተናውና ምንም ምን ጥፋት አልደረሰበትም የሮሀ አገር ሰዎችም ከንጉሣቸው ጋር በ #ጌታችን የመለኮት ሥልጣን አመኑ ይህ ሥዕል ቊጥር የሌለው ብዙ ድንቅ ተአምራትን አደረገ ንጉሡንም ከበሽታው ፈወሰው ከዚህም በኋላ ዕድሜውን ሲፈጽም በዚች ዕለት አረፈ።

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አቃርዮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቆሪል_ገመላዊ

በዚህችም ዕለት ሰምኑድ ከሚባል አገር ገመላዊው ቅዱስ ቆሪል አረፈ። እርሱም በጾም በጸሎት ተወስኖ የሚኖር ነው #እግዚአብሔርም የተሰወሩ ምሥጢራት ማወቅን ሰጠው የሚገለገልባቸው ከማሳም ተልባ የሚጭንባቸው ሦስት ግመሎች አሉት።
ፈራጉን በሚባል አገር ለእመቤታችን #ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካህናት የሆነ አንድ ሰው ነበረ ቤተ ክርስቲያኒቱም ነገሥታትና መኳንንት በየጊዜው የሰጧት ብዙ ገንዘብ አላት በሊቀ ካህናቱም ዘንድ የዕቃው ሣጥን በሥውር ይኖር ነበር የዚያንም ዕቃ ቊጥር ኤጲስቆጶሱ ያውቃል ያ ሊቀ ካህናት በእርሱ ሥልጣን ሥር ነበርና ከዚህም በኋላ የዕቃው ሣጥን ያለበትን ለልጁ ሳይነግር ያ ሊቀ ካህናት በድንገት ሞተ።

ኤጲስቆጶሱም የሊቀ ካህናቱን ሞት በሰማ ጊዜ ወደዚያች ቤተ ክርስቲያን መጥቶ ከልጁ ገንዘቧን ፈለገ ያም ልጅ አባተ በድንገተኛ ሞት ስለተነጠቀና ስለ አልነገረኝም ዕቃው ያለበትን አላወቅሁም አለው። ኤጲስቆጶሱም ሰምቶ ተቆጣ ሊአሠቃየውም ፈለገ ያም ልጅ ኤጲስቆጶሱን ዕቃው ያለበትን ቦታ እስከምፈልግ ድረስ ቆየኝ ባላገኘሁትም ጊዜ የወደድከውን ታደርግብኛለህ ብሎ ለመነው እርሱም ጊዜ ሰጠው።

ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ችግሩን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት። እርሷም በ #እግዚአብሔር ታምነህ በአባ መቃርስ ገዳም ወዳሉ አባቶች መነኰሳት ወደ ጎረቤቶቻቸውም ሒድ እነርሱ ይነግሩሃልና አለችው። ወደዚያም ሲደርስ ችግሩን ይፈጽሙለት ዘንድ ለመነኰሳቱ ነገራቸው የሚነግረውም አጥቶ ተስፋ ቆረጠ። አንድ ባሕታዊም ጠቀሰውና እንዲህ አለው ሰምኑድ ወደሚሉት አገር ሒደህ ስለ ባለ ገመሉ ቆሪል ጠይቅ በእርሱም ዘንድ እደር እርሱም ይነግርሃል አለው።

ወደ ሰምኑድ መንደርም ደርሶ ስለርሱ ስለቆሪል ጠየቀ ሰዎችም ነገሩት ያለበትንም አመለከቱት በሔደ ጊዜም ከመኖሪያው አገኘው ሦስቱ ግመሎቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ አባ ቆሪልም ፍላጎቱን በ #መንፈስ_ቅዱስ አውቆ ወደ ማደሪያው አስገብቶ መብልን አቀረበለት አባቴ ሆይ ችግሬን ሳትፈጽምልኝ እኔ አልበላም አለው ቆሪልም ችግርህ በጊዜው ጊዜ ይፈጸማልና አሁመን ብላ አለው።

ከራትም በኋላ በየመኝታቸው ተኙ የሌሊቱም እኩሌታ ሲሆን ያ ሰው ቆሪልን ከግመሎቹ ጋር ቁሞ አየው ሲሰግድ ይሰግዳሉ ሲቆምም ይቆማሉ። በነጋ ጊዜም ተልባ ይጭንባቸው ዘንድ ወደ ማሳ ወሰዳቸው ያም ሰው ሊራዳው አብሮ ሔደ ወደ ማሳውም በደረሱ ጊዜ ቆሪል በገመል ላይ መጫን ጀመረ ያም ሰው ሁለተኛውን ገመል ወስዶ ያለ አቅሙ ሸክሙን አክብዶ ጫነው ገመሉም መንቀሳቀስ ተሳነው ሊመታው ፈልጎ በትር አነሣ። ገመሉም አባቴ ቆሪል ሆይ በላዬ ጉዳት እንዳያደርስ ይህን ሰው አታሰናብተውም እርሱ ያለ ችሎታዬ አሸክሞኛልና ብሎ በሰው አንደበት ጮኸ ቆሪልም መጥቶ ሸክሙን አቀለለለት ያንንም ሰው ልጄ ሆይ በማይችለው መጠን ለምን አሸከምከው አንተ የምትአዝነው ልትሸከመው የማትችለውን ሸክም በላይህ ስለ አመጡብህ አይደለምን አለው።

ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ያ ሰው ስለ ችግሩ የዕቃውን ቦታ ይገለጥለት ዘንድ አባ ቆሪልን ለመነው እርሱም ለሌላ እንዳይናገር ከአማለው በኋላ ገለጠለት እንዲህም አለው በዚያች ቤተ ክርስቲያን በስተምሥራቅ ታናሽ ዋሻ አለ ዕቃውም በዚያ አለ።

ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ለሚስቱ ነገራት በአንድነትም ወደዚያ ቦታ ሔዱ ከነገሥታት መዛግብት እንኳ የሚመስለው የሌለ መዝገብን አገኙ ከዚህም በኋላ ለኤጲስቆጶስ ነገረው ኤጲስቆጶስም ይጠብቅ ዘንድ ለርሱ ስጠው። ይህም ጻድቅ ሰው ቆሪል ብዙ ተጋድሎን ከተጋደለ በኋላ በመልካም ሽምግልና አረፈ።

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቆሪል ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#የአክሚም_ሰማዕታት

በዚህችም ቀን የአክሚም ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው። እነርሱም በከበረ የልደት በዓል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የቊርባን ቅዳሴ አድርገው ተሰብስበው ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን በመሠዊያው ላይ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሕዝቡ ሲያቀብላቸው አዩት።
በዚህም ታላቅ ደስታ ውስጥ እያሉ መኰንኑ አርያኖስ መጥቶ ከበባቸው ወደ ቤተ ክርስቲያንም ገብቶ ስማቸው በሕዋፋና ወኒን የሚባል ሁለቱን የሀገር አለቆች ይዞ ራሳቸውን በሰይፍ ቆረጠ ከዚህም በኋላ ቀሳውስትን ዲያቆናትን ንፍቀ ዲያቆናትን መምህራንን የቤተ ክርስቲያንን ሹማምንት ገደለ ደማቸው ከቤተ ክርስቲያኑ ደጃፍ ወጥቶ ሃያ ክንድ ያህል እስቲጎርፍ ወንዶችን ሴቶችንና ልጆችንም ምንም ሳያስቀር አሳረዳቸው።
ኤጲስቆጶሱን አባ ብኑድያኖስን ዲዮስቆሮስን ሰከላብዮስን ከኤጲስቆጶሱ ጋር ያሉ መነኰሳትንም እነርሱን እንደታሠሩ አርያኖስ ከእርሱ ጋር ወሰዳቸው እነሆ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ጥር አንድ ቀን ተፅፎአል።

ለእርሱም ከቸር አባቱ ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ሰጊድ ከርሱ ጋር በትክክልነት ይገባል፤ እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክስር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ_29)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_29_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ገላትያ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥
² ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው።
³ እንዲሁ እኛ ደግሞ ሕፃናት ሆነን ሳለን ከዓለም መጀመሪያ ትምህርት በታች ተገዝተን ባሪያዎች ነበርን፤
⁴ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤
⁵ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።
⁶ ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።
⁷ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።
⁸ ነገር ግን በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን ሳታውቁ በባሕርያቸው አማልክት ለማይሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ ተገዛችሁ፤
⁹ አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?
¹⁰ ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።
¹¹ ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።
¹² ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ሆኜአለሁና፦ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ። አንዳችም አልበደላችሁኝም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ዮሐንስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።
¹⁰ ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።
¹¹ ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።
¹² እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።
¹³ ከመንፈሱ ስለ ሰጠን፥ በእርሱ እንድንኖር እርሱም በእኛ እንዲኖር በዚህ እናውቃለን።
¹⁴ እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።
¹⁵ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።
¹⁶ እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
¹⁷ በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።
¹⁸ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።
¹⁹ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።
²⁰ ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
²¹ እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ጳውሎስም ተነሣና በእጁ ጠቅሶ እንዲህ አለ፦ የእስራኤል ሰዎችና እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ፥ ስሙ።
¹⁷ የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መርጦ በግብፅ አገር በእንግድነት ሳሉ ሕዝቡን ከፍ ከፍ አደረጋቸው፥ ከፍ ባለችውም ክንዱ ከዚያ አወጣቸው።
¹⁸ በበረሀም አርባ ዓመት ያህል መገባቸው።
¹⁹ በከነዓንም አገር ሰባት አሕዛብን አጥፍቶ ምድራቸውን አወረሳቸው።
²⁰ ከዚህም በኋላ እስከ ነቢዩ እስከ ሳሙኤል ድረስ አራት መቶ አምሳ ዓመት ያህል መሳፍንትን ሰጣቸው።
²¹ ከዚያም ወዲያ ንጉሥን ያነግሥላቸው ዘንድ ለመኑ፥ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን የሚሆን ሰው የቂስን ልጅ ሳኦልን አርባ ዓመት ሰጣቸው፤
²² እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም፦ እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_29_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ ወኵሎ ዓሚረ ይድኅርዎ። (መዝ.71÷15) ትርጉም👇
“እርሱ ይኖራል ከዓረብም ወርቅ ይሰጡታል፤ ሁልጊዜም ወደ እርሱ ይጸልያሉ፥ ዘወትርም ይባርኩታል።” (መዝ.71÷15)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_29_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች።
² ቄሬኔዎስ በሶርያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ።
³ ሁሉም እያንዳንዱ ይጻፍ ዘንድ ወደ ከተማው ሄደ።
⁴-⁵ ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።
⁶ በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥
⁷ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።
⁸ በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።
⁹ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።
¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
¹² ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
¹³ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦
¹⁴ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።
¹⁵ መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው፦ እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ።
¹⁶ ፈጥነውም መጡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ።
¹⁷ አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ።
¹⁸ የሰሙትን ሁሉ እረኞቹ በነገሩአቸው ነገር አደነቁ፤
¹⁹ ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር።
²⁰ እረኞችም እንደ ተባለላቸው ስለ ሰሙትና ስላዩት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ ተመለሱ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ካልእ_ቅዳሴ ነው። መልካም የ #ብርሃነ_ልደቱ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#የዕለቱ_አንገርጋሪ_ግእዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሊያ "ዮም ፍሥሐ ኮነ #በእንተ_ልደቱ_ለክርስቶስ_እምቅድስት_ድንግል_ውእቱ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ አማን መንክር #ስብሐተ_ልደቱ"፡፡ ትርጉም፦ #ከቅድስት_ድንግል_ክርስቶስ_ስለተወለደ ዛሬ ደስታ ሆነ ለእርሱ ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) ሰገዱለት በእውነት #የልደቱ_ምስጋና_ድንቅ_ክቡር_ነው#ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ

"#ሰላም_ለልደቱ_እምድንግል_በቤተልሔም ዘበትርጓሜሁ ቤተ ኅብስት ብሂል። #ሰላም_ለጎል ዘሰከበ ውስቴቱ ከመ ሕፃን ወተጠብለለ ዲበ ምፅንጋዕ በአጽርቅተ ከመ ሰብእ"። ትርጉም፦ የእንጀራ ቤት በተባለ #በቤተልሔም_ከድንግል_ለተወለደው_ለልደቱ_ሰላምታ_ይገባል። እንደ ሰው በግርግም ላይ በጨርቅ የተጠቀለለና በውስጡ እንደ ሕፃን #ለተኛበት_በረት_ሰላምታ_ይገባል#ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
🎄የቲኛዉን ኦርቶዶክሳዊ ቻናል ማግኘት ይፈልጋሉ
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
🎄የገና በዓል ስጦታ 🎁
#ታኅሣሥ_30

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ሠላሳ በዚች ቀን በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ አበ ምኔት የሆነ የከበረ አባት #አባ_ዮሐንስ አረፈ፣ የትንቢትና በሽተኞችን የመፈወስ ሀብት ተሰጠው የተመሰገነ #የአባ_ዮሐንስ_ብጹዕ አረፈ፣ #ቅዱሳን_ኮርዮንና_ፊልሞና ከእነርሱም ጋር አርባ ወታደሮች በሰማዕትነት ሞቱ፣ ተጋዳይ የሆነ #አባ_ዘካርያስ_ገዳማዊ አረፈ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ዮሐንስ_አበ_ምኔት

ታኅሣሥ ሠላሳ በዚህች ቀን በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ አበ ምኔት የሆነ የከበረ አባት አባ ዮሐንስ አረፈ።

ይህም አባት በተሾመ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በራች ለብዙ ቅዱሳንም አባት ሆነ ከእርሳቸውም ውስጥ ታላላቅ ከዋክብት የሆኑ አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም የሀገረ ተሙዝ ኤጲስቆጶስ አባ ሚናስ የሀገረ ስሐ አባ ዘካርያስ ለብዙ ሰዎች ነፍሳት ወደብ የሆኑ እነርሱን የመሰሉ ሌሎች ብዙዎች አሉ። ለሕዝቡ ቅዱስ ቊርባንን በሚያቈርብ ጊዜ ኃጢአተኛውና ጻድቁ ይገለጥለታል ከቅዱሳን መላእክቶቹ ጋር #ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስንም በመሠዊያው ላይ ብዙ ጊዜ አየው።

በአንዲትም ዕለት ሥራው የከፋ አንዱን ቄስ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ አየው ከእርሱም ጋር ያሉ ብዙዎች ርኩሳን የረቀቁ አጋንንት ከበውት አፉ ውስጥ ልጓም አድርገዋል ወደ ቤተ ክርስቲያንም ከመግባቱ በፊት የ #እግዚአብሔር መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ በእሳት ሰይፍ ከእርሱ ከቄሱ መናፍስትን አሳደዳቸው ቄሱም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ መቀደሻውን የክህነት ልብስ ለበሰ ሁለመናውም እንደ እሳት ሆነ ቀድሶም ለሕዝቡ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን አቀበላቸው።
ልብሰ ተክህኖውንና የመቀደሻውን ሽልማት ከላዩ አውልቆ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜ እንዚያ የጠቆሩ መናፍስት ርኩሳን ተቀብለው እንደቀድሞው አደረጉበት።

አባ ዮሐንስም ይህን ነገር ለመነኰሳቱ ሲያስረዳ እንዲህ አላቸው በቅዳሴ አገልግሎት ጊዜ ለኃጢአተኛውና ለጻድቁ ቄስ ልዩነት የለም ስለ ሕዝቡ እምነት ያ ኅብስት ተለውጦ የ #ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋ ይሆናልና ወይኑም የከበረ ደሙን ይሆናልና።

ዳግመኛ በምሳሌ እንዲህ አላቸው በብረት በወርቅና በብር ላይ እንደሚቀረጽ እንደ ንጉሥ ማኅተም ነው። ማኅተሙም አይለወጥም እንዲሁ ከካህናትም የክህነት ጸጋ አይለወጥም እርሱ #እግዚአብሔር በጊዜው ጊዜ ለሁሉም ለየአንዳንዱ እንደሠራው ይከፈለዋል እንጂ።

ይህንም የከበረ ዮሐንስ ታላቅ መከራ ደርሶበታል አረማውያን በርበር ማረከው ወደ አገራቸወደ ወስደውታልና እያሠቃዩትም በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመን ታሥሮ ኖረ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ገዳሙ መለሰው።

ከመሞቱ በፊት የሚሞትበትን ጊዜ አውቆ መነኰሳቱን ሰበሰባቸውና የወንጌልን ትዕዛዝ ይጠብቁ ዘንድ በሰማያዊ መንግሥት በጎ ዕድልን ርስትንም ከእርሳቸው ጋር ይቀበሉ ዘንድ እንደ ቅዱሳን አባቶች አካሄድ እንዲጓዙ አዘዛቸው።

ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመ ነፍሱን ሊቀበሉ የቅዱሳንን አንድነት ሲመጡ አያቸውና ፈጽሞ ደስ አለው ነፍሱንም በ #እግዚአብሔር እጅ ሰጠ መነኰሳቱ ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ተሸክመው ወስደው በመዘመርና በታላቅ ምስጋና ገንዘው ቀበሩት እርሱንም ከመውደዳቸው የተነሣ ከተገነዘበት ልብስ ቆርጠው በእነርሱ ዘንድ አኖሩት ለሚታመም ሁሉ የሚፈውስ ሆነ የዚህም አባት ዕድሜ ዘጠና ዓመት ሆነ በግቢግ የሚልዋት መኖሪያው እስከ ዛሬ አለች።

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእኚህ አባት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ዮሐንስ_ብጹዕ

በዚህችም ቀን ደግሞ የተመሰገነ የአባ ዮሐንስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ይህም ተጋዳይ የምንኲስና ልብስን ከለበሰ ጀምሮ የትንቢትና በሽተኞችን የመፈወስ ሀብት ተሰጠው ዜናውም በሀገሩ ሁሉ ተሰማ።

ይህን አባ ዮሐንስን ሁል ጊዜ የሚጐበኘው አንድ መኰንን ነበረ የመኰንኑም ሚስት ወደ አባ ዮሐንስ ዘንድ እንዲወስዳት ባሏን ታምለውና ታስገደድው ነበር እርሱም የከበረ አባ ዮሐንስ ከአርባ ዓመት ጀምሮ የሴቶችን ፊት አላየም አላት። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሒዶ ሚስቱ ያለችውን ለአባ ዮሐንስ ነገረው አባ ዮሐንስም በ #እግዚአብሔር ፈቃድ የፈለገችውን እፈጽምላታለሁ አለው።

በዚያችም ሌሊት የከበረ ዮሐንስ ለዚያች ሴት በሕልም ተገልጾ እንዲህ አላት ጻድቅ ያልሆንኩ ወይም ነቢይ የኔን ፊት ታዪ ዘንድ የምትሺ አንቺ ሴት ከእኔ ምን አለሽ እኔስ ካንቺ ምን አለኝ እንግዲህስ ፊቴን ማየት አትሺ ይህንንም ብሎ በላይዋ ጸልዮ ባረካት።

በማግሥቱም የከበረ አባ ዮሐንስ በመንፈስ እንደታያት ለባሏ ነገረችው። መልኩንና አምሳያውን አመለከተችው ከዚህም በኋላ ከብዙ ሙገሳና ምስጋና ጋር ባሏን ወደ አባ ዮሐንስ ላከችው።

የከበረ ዮሐንስም ባሏን በአየው ጊዜ ፈገግ ብሎ የሚስትህ ምኞቷ የተፈጸመላት አይደለምን በዚች ዕለት በ #እግዚአብሔር ፈቃድ አግኝታኛለችና አለው መኰንኑም ሰምቶ ከትሩፋቱና ከደግነቱ የተነሣ እጅግ አደነቀ። ይህም አባ ዮሐንስ ጭንቅ በሆነ ተጋድሎ ዘጠና ዓመት ያህል ኖረ ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእኚህ አባት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_ኮርዮንና_ፊልሞና

በዚህችም ዕለት የመኰንኑ አርያኖስ የጭፍሮቹ ታላላቆች ኮርዮንና ፊልሞና ከእርሳቸውም ጋር ካሉ አርባ ወታደሮች ጋር በሰማዕትነት ሞቱ።

የሰማዕትነታቸውም ምክንያት የአክሚም ታላላቆች ከሆኑ ከሰማዕታት ዲዮስቆሮስ ከሰከላብዮስና ከብኑዲያስ የተደረገውን ተአምራት በአዩ ጊዜ የወታደርነት የማዕረግ ሽልማታቸውን ጣሉ በመኰንኑ አርያኖስም ፊት ቁመው እኛ በእውነተኛ አምላክ በ #ክርስቶስ የምናምን በግልጥ ክርስቲያን ነን ብለው ጮኹ። መኰንኑም ከእሳት ማንደጃ ውስጥ ይጥሏቸው ዘንድ አዘዘ ራሳቸውንም ሲወረወሩ ብዙዎች አዩአቸው ገድላቸውንም እንዲህ ፈጸሙ።

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ዘካርያስ_ገዳማዊ

በዚህችም ዕለት ተጋዳይ የሆነ ዘካርያስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከመመንኰሱ በፊት በጐዳና ሲጓዝ አረማውያን በርበር ተነሡበትና ያዙት ሊያርዱትም ወደዱ በ #እግዚአብሔርም ፈቃድ የገዳሙ አለቃ በዚያት ጐዳና ሲያልፍ በላያቸው ጮኸ እነርሱም ሠራዊት እንደደረሰባቸው ተጠራጠሩ ፈርተውም ሸሹ ሲሸሹም ከባሕር ገብተው ሰጠሙ።

ዘካርያስም ከመገደል በዳነ ጊዜ ይሸጥ ዘንድ ገንዘባቸውን ይዞ ወደ ከተማ ገባ የሀገሩም ገዥ ያዘው ሌባ እንደ ሆነ አስቦ ሊገለው ወደደ ግን ሥራውን በአወቀ ጊዜ ተወው።

ከዚህም በኋላ ወደ አባ ጳኩሚስ ገዳም ሒዶ የምንኲስናን ልብስ ለበሰ ሰይጣንም እስከ ቀናበት ድረስ በጾምና በጸሎት ተጠመደ ከዚህም በኋላ በአባቱ ተመስሎ በሕልም ታየውና መሞቻዬ ጊዜ ደርሷልና ትቀብረኝ ዘንድ ና አለው ቅዱሱም እውነት እንደሆነ አስቦ ወደ አባቱ ሔደ ግን በጤንነት አገኘው። የሰይጣን ተንኰልም እንደሆነ አውቆ ወደ መኖሪያው ተመለሰ ሰይጣንንም ድል እስከአደረገው ድረስ በሩን ዘግቶ እየተጋደለ ኖረ።

በሆሣዕናም ዕለት ወደ አበ ምኔቱ ሒዶ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ ፈቃድ ለመነው ፈቀደለትም በማግሥቱም ፊታቸው የሚያባራ ሦስት ሰዎች ሲጠብቁት አገኛቸውና አብሮዋቸው ሔደ።
ከዚህም በኋላ አበ ምኔቱ የአባ ዘካርያስን ቤት ሊጎበኝ ሔደ ሦስት ታላላቅ ዘንዶዎችም በምድር ላይ ሲርመሰመሱ አግኝቶ በአያቸው ጊዜ ፈራቸው እነርሱም በስሙ ጠሩት ወደነርሱም ዘወር ሲል አባት ሆይ ሲመግበን የነበረ #ጌታችን ዘካርያስ ከዚህ ወደየት ሔደ ብለው በሰው አንደበት ተናገሩት። አበ ምኔቱም ሰምቶ አደነቀ መብልንም ሰጣቸው።

አባ ዘካርያስም ወደ መኖሪያው ተመልሶ በብዙ ተጋድሎ ኖረ። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ_30)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_30_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ፊልጵስዩስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ እንግዲህ ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ፤ በአንዳች ነገርም ልዩ አሳብ ቢኖራችሁ፥ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል፤
¹⁶ ሆኖም በደረስንበት በዚያ እንመላለስ።
¹⁷ ወንድሞች ሆይ፥ እኔን የምትመስሉ ሁኑ፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ።
¹⁸ ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ።
¹⁹ መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።
²⁰ እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤
²¹ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
¹³ ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤
¹⁴ ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።
¹⁵ በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤
¹⁶ አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።
¹⁷ ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ።
¹⁸ ሎሌዎች ሆይ፥ ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ።
¹⁹ በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባዋልና።
²⁰ ኃጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።
²¹ የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ወደ ምኵራብም ገብቶ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተነጋገረና እያስረዳቸው ሦስት ወር ያህል በግልጥ ይናገር ነበር።
⁹ አንዳንዶች ግን እልከኞች ሆነው በሕዝብ ፊት መንገዱን እየሰደቡ ባላመኑ ጊዜ፥ ከእነርሱ ርቆ ደቀ መዛሙርትን ለየ፥ ጢራኖስም በሚሉት በትምህርት ቤት ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር።
¹⁰ በእስያም የኖሩት ሁሉ አይሁድም የግሪክ ሰዎችም የጌታን ቃል እስኪሰሙ ድረስ ሁለት ዓመት ያህል እንዲህ ሆነ።
¹¹ እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥
¹² ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር።
¹³ አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች፦ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ።
¹⁴ የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት።
¹⁵ ክፉው መንፈስ ግን መልሶ፦ ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው።
¹⁶ ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም።
¹⁷ ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤
¹⁸ አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር።
¹⁹ ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_30_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ ወኵሎ ዓሚረ ይድኅርዎ። (መዝ.71÷15)  ትርጉም👇
“እርሱ ይኖራል ከዓረብም ወርቅ ይሰጡታል፤ ሁልጊዜም ወደ እርሱ ይጸልያሉ፥ ዘወትርም ይባርኩታል።” (መዝ.71÷15)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_30_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
³ ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤
⁴ የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።
⁵-⁶ እነርሱም፦ አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት።
⁷ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥
⁸ ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ፦ ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው።
⁹ እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።
¹⁰ ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።
¹¹ ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
¹² ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታችን_የማርያም_ቅዳሴ_ነው። መልካም የ #ብርሃነ_ልደቱ በዓል ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
🎁🏆🚨 ገናን ምክንያት በማድረግ የ1000 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀረው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN በሉ 🏃‍♀️🏃‍♂️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/01/08 14:34:02
Back to Top
HTML Embed Code: