✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_24_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ኤፌሶን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
¹²-¹³ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።
¹⁴ እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥
¹⁵ ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤
¹⁶ ከእርሱም የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠለት በጅማት ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል።
¹⁷ እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።
¹⁴ እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።
¹⁵-¹⁶ ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።
¹⁷ ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥
¹² ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር።
¹³ አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች፦ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ።
¹⁴ የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት።
¹⁵ ክፉው መንፈስ ግን መልሶ፦ ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው።
¹⁶ ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም።
¹⁷ ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤
¹⁸ አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር።
¹⁹ ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ።
²⁰ እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_24_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ። በእንተ ጸላኢ። ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ"። መዝ. 8፥2።
“ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።” መዝ. 8፥2።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_24_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፦ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? አሉት።
² ሕፃንም ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ
³ እንዲህም አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።
⁴ እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው።
⁵ እንደዚህም ያለውን አንድ ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤
⁶ በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።
⁷ ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፥ ነገር ግን በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት።
⁸ እጅህ ወይም እግርህ ብታሰናክልህ፥ ቈርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንካሳ ወይም ጉንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።
⁹ ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል ይልቅ አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።
¹⁰ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።
¹¹ የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአልና።
¹² ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን?
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱሳን_ሐዋርያት_ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የልደት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ታኅሣሥ_25
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ሃያ አምስት በዚህች ዕለት #የአቡነ_ዮሐንስ_ከማ_ዘግብጽ፣ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ #አቡነ_ዮሐንስ_ከማ_እጨጌ፣ #አምስቱ_መቃባውያን ዕረፍታቸው ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#የአቡነ_ዮሐንስ_ከማ_ዘግብጽ
ታኅሣሥ ሃያ አምስት በዚህች ዕለት የግብጹ አቡነ ዮሐንስ ከማ ዐረፈ፡፡ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ምእመናን ከእርሱም በቀር ልጅ የላቸውም በዚህም ዓለም በሠርጉ ደስ ይላቸው ዘንድ ወደው ላሕይዋ ደም ግባቷ ያማረ ድንግል ብላቴና ያለ ፈቃዱ አጋቡት። ወደ ጫጒላ ቤትም በሌሊት ገብቶ ዘወትር እንደሚጸልይ ቆመ ወዚያች ብላቴናም ቀረብ ብሎ "ይህ ዓለም ፍላጎቱ ኃላፊ እንደ ሆነ አንቺ ታውቂያለሽ ሥጋችንን በንጽሕና ለመጠበቅ እርስ በርሳችን እንስማማ ዘንድ ትፈቅጂአለሽን?" አላት። እርሷም "ወላጆቼ አስገድደው ላንተ አጋቡኝ እንጂ ሥጋዊ ፍትወትን እንዳላሰብኳት ሕያው #እግዚአብሔር ምስክሬ ነው አሁንም እንሆ #እግዚአብሔር ልመናዬን ፈጸመልኝ" ብላ መለሰችለት።
ከዚህም በኋላ ድንግልናቸውን በንጽሕና ይጠብቁ ዘንድ ሁለቱም ተስማምተው በአንድነት በአንድ ዐልጋ ላይ እየተኙ ብዙ ዘመናት ኖሩ የ #እግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ በመውረድ ክንፎቹን አልብሷቸው ያድራል። ከጽድቃቸውም ብዛት የተነሣ ማንም ያልዘራትንና ያልተከላትን የወይን ተክልን #እግዚአብሔር በቤታቸው አበቀለ አድጋ ወጥታ ከቤታቸው ጣሪያ በላይ ተንሳፈፈች እርሷም የድንግልናቸውን መጠበቅ ታመለክታለች። ይህ ሥራ በሰው ተፈጥሮ ላይ ይከብዳልና ሁለት ወጣቶች በአንድነት የሚተኙ ከቶ የፍላጎት ሓሳብ አይነሣምን? እሳትን የሚታቀፍ ሥጋው የማይቃጠል ማን ነው? የ #እግዚአብሔር ረድኤት የምትጠብቀው ካልሆነች። ወላጆቻቸውም ብዙ ዘመን ሲኖሩ ልጅን እንዳልወለዱ ባዩ ጊዜ ጐልማሶች ስለ ሆኑ መሰላቸው።
ከዚህም በኋላ የከበረ ዮሐንስ ከማ ይህም ካም ማለት ነው እንዲህ አላት "እህቴ ሆይ እኔ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒጄ እመነኵስ ዘንድ እሻለሁ ግን ያላንቺ ፈቃድ ምንም ምን ማድረግ አይቻለኝም" እርሷም "የምትሻውን አድርግ #እግዚአብሔርም ከእኔ የተፈታሕ ያድርግህ" አለችው። ይህንንም በአለችው ጊዜ ወደ ደናግል ገዳም ወሰዳት በዚያም መንኵሳ እመምኔት ሆነች ድንቆች ተአምራቶችንም የምታደርግ ሆነች #እግዚአብሔርንም አገለገለችው።
የከበረ ዮሐንስ ከማም ወደ አስቄጥስ ገዳም ይሔድ ዘንድ በወጣ ጊዜ ፊቱ የሚያበራ ሰው ተገለጠለትና ስለ አወጣጡ ጠየቀው ዮሐንስም ከማም " #እግዚአብሔር ከፈቀደ እኔ መነኰስ መሆንን እሻለሁ" አለው። ያም ፊቱ የሚያበራ እንዲህ ብለቀ መከረው "ከአባ መቃርስ ገዳም ወደ ሚኖር ወደ ከበረ አባ ዳሩዲ በዓት ሒደህ በርሱ ዘንድ ኑር እርሱም ያመነኵስህ የምንኵስናንም ሥርዓት ያስተምርህ" ያም ፊቱ ብሩህ የሆነ ወደ አባ ዳሩዲ በዓት እስከ አደረሰው ድረስ እያጽናናው አብሮት ተጓዘ። ይህ አባ ዳሩዲም ተቀብሎ አመነኰሰው እስከ ዕረፍቱም ጊዜ የምንኵስናን ሕግና ሥርዓት አስተማረው።
ከዚህም በኋላ የ #እግዚአብሔር መልአክ ከአባ ዮሐንስ ሐጺር ገዳም በስተ ምዕራብ ሒዶ ለራሱ ከዚያ ማደሪያ ይሠራ ዘንድ አዘዘው ወደዚያም በሔደ ጊዜ ሦስት መቶ ሰዎች ወደርሱ ተሰበሰቡ የምንኵስናንም ልብስ አለበሳቸው ቤተ ክርስቲያንን ለራሳቸውም ማደሪያዎችን ሠሩ። ሥርዓትን ምስጋናን የእመቤታችንን የ #ማርያምን ውዳሴ አስተማራቸው። በአንዲትም ዕለት የእመቤታችንን የ #ማርያምን ውዳሴዋን በመንፈቀ ሌሊት ቁመው ሲጸልዩ የከበረ ሐዋርያዊ አትናቴዎስ ተገለጠለትና የረቀቁ ምሥጢሮችን ገለጠለት ከዚያችም ዕለት ወዲህ በሠለስቱ ደቂቅ ጸሎት ፍጻሜ የቅዱስ አትናቴዎስ ስም የሚጠሩ ሆኑ።
ከዚህም በኋላ በአንዲት ዕለት እመቤታችን የከበረች ድንግል #ማርያም ተገለጣለት "ይህች ቦታ ለዘላለሙ የኔ ማደሪያ ናት እኔም ካንተ ጋር እንደኖርኩ ከልጆችህ ጋር እኖራለሁ ስሜም በዚህ ገዳም ሲጠራ ይኖራል" አለችው ይህች ቤተ ክርስቲያን አምላክን በወለደች በ #እመቤታችን ስም የተመሠረተች ናትና። በላይኛውም ግብጽ ገዳማት አሉ በውስጣቸውም የሚኖሩ መነኰሳት በእርሱ ጥላ ሥር መሆን ወደው ወደርሳቸው መጥቶ የርሱን ሥርዓተ ማኅበርና ሕግ ያስተማራቸው ዘንድ እየለመኑት ወደርሱ መልክትን ላኩ እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱን ስሙ ሲኖዳ የሚባለውን ጠርቶ "እኔ እስክመለስ ለመነኰሳቱ ቁሙላቸው" አለው። እርሱም አባ ዮሐንስ ከማ ከላይኛው ግብጽ እስሚመለስ በእግሮቹ ቆመ አላንቀላፋም በምድር ላይም አልተኛም።
በተመለሰም ጊዜ ቁሞ እግሮቹም አብጠው ተልተው ከእርሳቸው ትል ሲወጣ አገኘው አባ ዮሐንስም "ልጄ ሲኖዳ ሆይ ለምን ይህን አደረግህ እኔ ቁምላቸው ብሎ ያዘዝኩህ ስለ እኔ ሁነህ እንድታስተዳድራቸው ሥራቸውን እንድትቆጣጠር እንድታዝዛቸውም ነበር" አለው። እርሱም ከእግሮቹ በታች ሰግዶ "አባቴ ሆይ ይቅር በለኝ ከበጎ ሥራ ምንም ምን አልሠራሁምና" አለው።
ከዚህም በኋላ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ድካም ተለይቶ በዘላለማዊ የተድላ ማደሪያ የሚያርፍበት ጊዜ ሲቀርብ ጥቂት ታሞ ነፍሱን በ #እግዚአብሔር እጅ በዚህች ቀን አስረከበ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ዮሐንስ_ከማ_ዘእጨጌ_ኢትዮጵያዊው
በዚህችም ዕለት ኢትዮጵያዊው አቡነ ዮሐንስ ከማ ዘእጨጌ ዐረፉ፡፡ ይኸውም ጻድቅ አባት አገራቸው ሰሜን ጎንደር ነው፡፡ በብዙዎቹ ቅዱሳን ገድል ላይ ታሪካቸው ተደጋግሞ የተጠቀሰ ሲሆን ቅዱስ ያሬድ በድርሰቱ ደጋግሞ ያመሰገናቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ከቀደምት አንጋፋ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ሲሆኑ መጽሐፍ "ኮከብ ዘገዳም" ይላቸዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ይህኛውንም አባት ግብፃዊ ናቸው ይሏቸዋል፡፡ ነገር ግን ስማቸውን ከላይ ከጠቀስናቸው ከግብፃዊው አባት ከአባ ዮሐንስ ከማ ጋር አንድ አይደሉም፡፡ ኢትዮጵያዊው አቡነ ዮሐንስ ከማ ትግራይ የሚገኘውን ቀብፅያ ገዳምን የቆረቆሩ ሲሆን ብዙ ቅዱሳን አባቶችንም በማመንኰስ የቤተ ክርስቲያን ከዋክብት የተባሉትን ቅዱሳን መነኰሳትን አፍርተዋል፡፡ በገዳማቸው ቀብፅያ የምትገኘው እጅግ አስገራሚዋና ተአምራትን የምትሠራው መቋሚያቸው ዛሬም ድረስ አለች፡፡
1250 ዓመት ያስቆጠረችውን ይህችን የጻድቁን ተአምረኛ መቋሚያ ሀገሬው በጠመንጃ ይጠብቃታል፡፡ እንደ ሰው ድምፅ የምታሰማበት ጊዜ አለ፡፡ ጻድቁ ሰሜን ጎንደር ምድረ ጸለምት ትልቅ ገዳም አላቸው። ዕረፍታቸው በዚህች ቀን ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አምስቱ_መቃብያን
ዳግመኛም በዚህች ዕለት አምስቱ መቃብያን በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ እነዚህም ቅዱሳን በሜዶናውያንና በሞዓባውያን ዘመነ መንግሥት የነበሩ ናቸው፡፡ ክፋትን የሚወዳት ስሙ ጺሩጻይዳን የሚባል አንድ ንጉሥ ነበር ከሥልጣኑም በታች የጸኑ ጭፍሮች አሉ የሚያመልካቸው ኃምሳ በወንዶች ሃያ በሴቶች አምሳል የተሠሩ ጣዖቶች አሉት በጥዋትና በማታ መሥዋዕትን ያቀርብላቸዋል ሰዎችንም እንዲሠዉ ያስገድዳቸው ነበር።
ከብንያም ወገንም የሆነ ስሙ መቃቢስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ለርሱም መልከ መካሞች የጸኑ ሦስት ልጆች አሉት ከእርሳቸውም ግሥላውን እንደ ዶሮ አንቆ የሚገድል አለ። በአንዲት ዓመታትም አንበሳ የሚገድል አለ እነርሱም ውበትንና ግርማን የተሸለሙ ናቸው ከሁሉ የሚሻል የልብ ውበትንም እነርሱ የሥጋ ሞትን ያልፈሩ #እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ናቸውና። ንጉሡም "እናንት ዓመፀኞች ለአማልክቶቼ እንዴት አትሰግዱም" አላቸው እነርሱም በአንድ ቃል "እኛ ለረከሱ አማልክቶችህ አንሰግድም እኛንም አንተንም

ለፈጠረ ሕዝቡንም በዕውነትና በቅንነት ትጠብቅ ዘንድ ላነገሠህ አንተ ቸለል ብለህ ለዘነጋኸው ለ #እግዚአብሔር እንሰግዳለን እንጂ" ብለው መለሱለት።
ከዚህም በኋላ የተራቡ አራዊትን በላያቸው እንዲሰዱ አዘዘ እነዚያም ለቅዱሳን ሰግደው ተመልሰው ከከሀድያን ሰባ አምስት ሰዎችን ገደሉአቸው። እሊህንም ቅዱሳን ወደ ወህኒ ቤት ጨመሩአቸው ሌሎች ሁለት ወንድሞቻቸውም መጥተው ከእርሱ ጋር ተቀላቀሉ። ንጉሡም አምስቱን ወንድማማቾች አይቶ እጅግ ተቆጥቶ ከሚነድ እሳት ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ ነፍሳቸውንም በእግዚአብሔር እጅ አስረከቡ።
ከዚህም በኋላ የቅዱሳኑን ሥጋ አመድ እስከሚሆን ያቃጥሉ ዘንድ ዳግመኛ አዘዘ እሳቱም ከቶ አልነካቸውም ዳግመኛም ከባዶች ደንጊያዎችን ከሥጋቸው ጋር አሥረው ከባሕር ውስጥ ያሰጥሟቸው ዘንድ አዘዘ ባሕሩም አልዋጣቸውም ለዱር አራዊትና ለሰማይ ወፎች እንዲጥሏቸው አዘዘ አዕዋፍም ክንፎቻቸውን ጋርደውላቸው ዐሥራ አራት ቀኖች ኖሩ ሥጋቸውም እንደ ፀሐይ አበራ ከዚህ በኋላ ይቀብሩአቸው ዘንድ አዘዘ።
ከዚህም በኋላ ያንን የ #እግዚአብሔርን ሕግ የዘነጋ ንጉሥ ሌሊት በዐልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ እሊህ ቅዱሳን ተቆጥተው ሰይፋቸውን መዝዘው በፊቱ ቁመው ታዩት በነቃም ጊዜ የሚበቀሉት መስሎታልና ፈርቶ ተንቀጠቀጠ። እነዚያም የከበሩ ሰማዕታት "ክፉ ነገርን ስላደረግህብን እኛስ ክፉ ነገርን አንከፍልህም በነፍስ ፍዳ የሚያመጣ #እግዚአብሔር ነውና ፍዳንስ የሚከፍልህ ፈጣሪያች #እግዚአብሔር አለ። ነገር ግን ስለዕውቀትህ ማነስና ስለ ልቡናህ ድንቁርና እኛ ደኅነኞች እንደሆን ተገልጠን ታየንህ እኛንስ የገደልከን መስሎህ ድኅነትን አዘጋጀህልን። የጣዖቶችህ ካህናትና አንተ ግን ለዘላለሙ መውጫ ወደሌለባት ወደ ገሀነም ትወርዳላችሁ" አሉት ከዚህም በኋላ ከርሱ ተሠወሩ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ_25 እና #ከገድላት_አንደበት)

#ታኅሣሥ_25_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ቲቶ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹²-¹³ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤
¹⁴ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
¹⁵ ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ዮሐንስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ።
¹³ አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጎበዞች ሆይ፥ ክፉውን አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ልጆች ሆይ፥ አብን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ።
¹⁴ አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።
¹⁵-¹⁶ ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።
¹⁷ ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።
¹⁸ ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ።
³² ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፥ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደ ሆነ ማንም አልተናገረም።
³³ ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።
³⁴ በመካከላቸው አንድ ስንኳ ችግረኛ አልነበረምና፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ የተሸጠውን ዋጋ ያመጡ ነበርና፥
³⁵ በሐዋርያትም እግር አጠገብ ያኖሩ ነበር፤ ማናቸውም እንደሚፈልግ መጠን ለእያንዳንዱ ያካፍሉት ነበር።
³⁶ ትውልዱም የቆጵሮስ ሰው የነበረ አንድ ሌዋዊ ዮሴፍ የሚሉት ነበረ፥ እርሱም በሐዋርያት በርናባስ ተባለ ትርጓሜውም የመጽናናት ልጅ ነው፤
³⁷ እርሻም ነበረውና ሽጦ ገንዘቡን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር አጠገብ አኖረው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_25_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊት ገዳም። ወከዐዉ ደሞሙ ከመ ማይ ዐውዳ ለኢየሩሳሌም። ወኀጥኡ ዘይቀብሮሙ"። መዝ 78፥2-3።
"የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥራ ለምድር አራዊት፤ ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥ የሚቀብራቸውም አጡ"። መዝ 78፥2-3።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ታኅሣሥ_25_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁶ በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፦ የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት።
³⁷ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤
³⁸ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤
³⁹ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።
⁴⁰ እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።
⁴¹ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥
⁴² ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
⁴³ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
⁴⁴ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ሠለስቱ_ምዕት_ቅዳሴ ነው። መልካም አቡነ ዮሐንስ ከማ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ #አብ _ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፳፮ (26) ቀን።
❤ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለሐዲስ_ሐዋርያ ለኢትዮጵያ ብርሃኗ ለሆኑት #ለአቡነ_ተክለሃይማኖት #በተወለዱ_በሦስት_ቀናቸው_ቅድስት_ሥላሴ ላመሰገኑበት ዓመታዊ ክብረ በዐል #እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን። በዐሉ የታላቁ ገዳም የደብረ ሊባኖስ አባቶችን ወደ ኢቲሳ ደብረ ጽላሽ ወርደው በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
#የአባታችን_የአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ልደት፦ ... ከዚህም ቀጥሎ ከዘጠኝ ወር በኋላ በታኅሣሥ በሃያ አራት ቀን ፍስሐ ጽዮን ተወለደ። በዚያችም ቀን በጸጋ ዘአብ ቤት ታላቅ ደስታ ተደረገ መካን የነበረች ሚስቱ እግዚእ ኃረያ ወንድ ልጅ ወልዳለችና። መልኩ እጅግ ድንቅ ነው እንደ ብርሌ እንደ መስታወት የሚያንጸባርቅ ነው። ቅላቱም እንደ ጽጌ ረዳ ነው ለነዳያንም ግብዣ አድርገው ዋሉ። ለአገራቸውም ሰዎች እንደየማዕርጋቸው ምሳ አደረጉላቸው።
በዓሉንም ካከበሩ በኋላ ለእግዚእ ኃረያና ለጸጋ ዘአብ #እግዚአብሔር ያደረገላቸውን በጐ ሥራውን ሁሉ እያደነቁ ወደ የቤታቸው ተመልሰው ገቡ። ይህም #እግዚአብሔር የመረጠው ልጅ በተወለደ በሦስተኛው ቀን ይህችውም የ #ጌታችን_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ የትንሣኤው ቀን በዕለተ ሰንበት ማለት ነው። ከቀኑ በሦስት ሰዓት ይህ ብላቴና እጆቹን አንሥቶ ወደ ሰማይ ተመልክቶ #እግዚአብሔርን በማመስገን እንዲህ ብሎ አሰምቶ ተናገረ "ከ #ወልድ ከ #መንፈስ_ቅዱስ ጋራ በባሕርይ በህልውና አንድ የሚሆን #አብ በአካል በስም ልዩ ነው። ከ #አብ ከ#መንፈስ_ቅዱስ ጋር በባህሪይ በሕልውና አንድ የሚሆን #ወልድ በአካል በስም ልዩ ነው። ከ #አብ ከ #ወልድ ጋር በባህርይ በሕልውና አንድ የሚሆን #መንፈስ_ቅዱስ በአካል በስም ልዩ ነው ብሎ አመሰገነ።
በሦስት ሰዓት በቅዳሴ ጊዜ #መንፈስ_ቅዱስ ወደ ወደደበት ስለሚወርድ ሕፃኑም #መንፈስ_ቅዱስ ሲወርድ አይቶ እሱ እንዳስተማረው ለፈጣሪው እየተገዛ ይህን ሦስት የምስጋና ቃል አቀረበ። እናቱም ከተመረጠ ልጇ ይህን ልዩ ምስጋና ሰምታ በልቡናዋ እያደነቀች "ልጄ ፍሥሐ ጽዮን ምን ትላለህ ይህ ቃል የአባትህ ሥራ ነው። ላንተ ግን የሚገባህ ጡት መጥባት ነውና"። ባሏ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ተመልሶ ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ ልጁ የተናገረውን ነገር ሁሉ ነገረች። ቅዱስ ጸጋ ዘአብም ነገሩን ሰምቶ አደነቀና "ልጄ #እግዚአብሔር ያሳድግህ ብዙ ዘመን ያኑርህ። በቤተ #እግዚአብሔርም እንዲህ እያልክ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለሁ" አለ።
ይህንም ብላቴና መላእክት ክንፋቸውን እየጋረዱ ዘወትር ይመግቡታል። እርሱም ክንፋቸውን ሲጋርዱት ባያቸው ጊዜ ከእነሱ ጋራ ይጫወት ነበር። ሁል ጊዜ ይስቅ ነበር እንጂ ሕፃናት እንደ ሚያለቅሱ አያለቅስም ነበር ቅኖች ሰዎች ዘወትር ደስ ይላችዋልና።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።
ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ም16።

#ታኅሣሥ_26
#ቅድስት_አንስጣስያ
አንድ አምላክ በሚሆን በ #አብ በ #ወልድ በ #መንፈስ_ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ሃያ ስድስት በዚህች ዕለት ከሮሜ አገር የከበረች ቅድስት አንስጣስያ በሰማዕትነት ዐረፈች፣ ዳግመኛ በዚህች ቀን #የቅዱስ_ አቦሊ_ጻድቅ፣ #የቅድስት_ዮልያና_ሰማዕት መታሰቢያቸው ነው።
=>እስኪ ከቅድስቷ ታሪክ በፊት ዛሬ በጥቂቱ የተባረኩ (ቡሩካት) እናቶቻችን እንዘክር:: "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል #ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ 'ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን ናትና::
+ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ #እመ_ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና።
#እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው::
1."ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው
እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከኃልዮ ንጽሕት ናት::
"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም)
2."ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: #እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና::
"ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል #ማርያም- #ማርያም
ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)
3.ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: #እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ- የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::
4.#እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት
የለችምና::
+የእመ ብርሃን ይቆየንና ደግሞ ሌሎች ቅዱሳት እናቶቻችንን እንመልከት:: እናቶቻችን ስናከብር የምንጀምረው በቅድስት
ሔዋን ነው:: ብዙ ጊዜ የእናታችን ሔዋን ጥፋቷ እንጂ በጐ ነገሯ: ደግነቷ: ንስሃዋ አይነገርላትም:: ሆኖም እናታችን
ቅድስት ሔዋን ክብር የሚገባት ሴት ናት::
#ክርስቶስ ሰው የሆነ እርሷንና ልጆቿን ለመቀደስ ነውና:: "ከመ ይስዓር መርገማ ለሔዋን ዲበ ዕፅ ተሰቅለ" እንዲል:: (ድጉዋ)
ቀጥሎ በብሉይ ኪዳን እነ ሐይከል: እድና: ሣራ: ርብቃ: አስኔት: ሲፓራ: ሐና: ቤርሳቤህን የመሰሉ እናቶቻችን በበጐው መንገድ ፈጣሪን ደስ አሰኝተዋል:: በዘመነ ሥጋዌም ቅዱሳቱ ሐና: ኤልሳቤጥ: ማርያም: ሶፍያ: ሰሎሜ: ዮሐና እና 36ቱ ቅዱሳት አንስት በጐነታቸው ያበራል::
+ከዚያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለ2,000 ዓመታት የተነሱ አእላፍ ቅዱሳት እናቶቻችንን ግን ዘርዝረን አንዘልቃቸውም:: በቅድስናቸው አራዊትን ያሰገዱ: ነገሥታትን ያንቀጠቀጡ:
አጋንንቸትን የረገጡ: በዘንዶ ላይ የተጫሙ ብዙ እናቶችን ቤተ ክርስቲያን አፍርታለች::
+ዛሬም ቢሆን በበርሃና በከተማ በጐውን ጐዳና የተከተሉ ብዙ እናቶች እንዳሉን እናውቃለን:: አንድም እናምናለን::
ግን ግን በከተሞች የምንመለከተው ሥርዓቱን የለቀቀው የበርካታ እህቶቻችን አካሔድ ለሃገርም ለቤተ ክርስቲያንም ትልቅ ስጋት
ነው:: ክብርና ነውር የማይለይበት ዘመን ይመስላል::
+ይህንን እያነበባችሁ ያላችሁ እህቶቼ! አንድ ነገር ልንገራችሁ:: በመልካቸው ብዙዎችን ያጋጩ: አጊጠው በመታየታቸው ብዙዎችን ያሰናከሉ: ለብዙ ምዕመናንም የጥፋት ምክንያት የሆኑ ብዙ ሴቶች በታሪክ ነበሩ::
+የሚያሳዝነው ግን ዛሬ ያሉት ከመሬት በታች ነው:: አፈር በልቷቸዋል:: ስም አጠራራቸውም ጠፍቷል:: በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ዛሬ በዘለዓለማዊው እሳት እየተቃጠሉ በሲኦል: በጥልቁ ውስጥ አሉ::
+እናም ወገኖቼ! ይህን አውቀን እንንቃ:: ይህ ዓለም ጠፊም: አጥፊም ነውና:: እድሜአችን ቢረዝምና ከዚህ በኋላ ለ100 ዓመታት ብንኖርም እርሱም ማለቁ አይቀርምና::
ምርጫችን ዘለዓለማዊው ሕይወት ይሁን ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን::
#ቅድስት_አንስጣስያ
የዚችም ቅድስት አባቷ ጣዖትን የሚያመልክ ነው እናቷ ግን ክርስቲያን ናት ይቺንም ቅድስት በወለደቻት ጊዜ አባቷ ሳያውቅ የክርስትና ጥምቀትን በሥውር አጠመቀቻት አውቆ ቢሆን ማጥመቅ ባልተቻላትም ነበር። ከዚህም በኋላ በበጎ አስተዳደግ አሳደገቻት በቀናች ሃይማኖት እስከ አጸናቻት ድረስ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማረቻት ጠባይዋን መለወጥ ለማንም አልተቻለውም።
አድጋም አካለ መጠን በደረሰችም ጊዜ አባቷ እንደርሱ ላለ ከሀዲ ሰው አጋባት እርሷ ግን እጅግ ጠላችው ልትገናኘውም አልፈለገችም በሴቶች ላይ በሚሆነው ግዳጅና አንዳንድ ጊዜም በደዌ የምታመካኝ ሆነች እንዲጠላትና ከእርሷ እንዲለይ ያደፈና የቆሸሸ የተጐሳቈለ ልብስ ትለብስ ነበር። ባሏም ወደ ሥራው ወጥቶ በተሰማራ ጊዜ እርሷም ስለ ቀናች ሃይማኖት የታሠሩ እስረኞችን ትጐበኝ ዘንድ ትሰማራለች ታገለግላቸውና የሚሹትን ትሰጣቸዋለች። ባሏም ይህን የምትሠራውን በአወቀ ጊዜ ወደ ውጭ እንዳትወጣ በቤት ውስጥ ዘጋባት እርሷም ከእጁ ያወጣት ዘንድ አዘውትራ በመረረ ልቅሶ ወደ #እግዚአብሔር የምትለምን ሆነች #ጌታችንም ልመናዋን ሰምቶ ያንን ሰው አጠፋው። እርሷም በሞቱ ደስ አላት ከዚህም በኋላ ለድኆችና ለምስኪኖች ስለ ቀናች ሃይማኖትም በመታመን ለታሠሩ እሥረኞች ገንዘቧን ሁሉ ሰጠች።
የሮሜ አገር ገዢም ዜናዋን በሰማ ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣት ስለ ሃይማኖቷም ጠየቃት ክርስቲያን እንደሆነች በፊቱ ታመነች ቃል ኪዳን በመግባትም ተናገራት ከበጎ ምክርዋ አውጥቶ ወደ ክህደት ሊያዘነብላት አልቻለም። በዚያንም ጊዜ በብዙ በተለያየ ሥቃይ አሠቃያት።
ከዚህም በኋላ ወደ ባሕር ያሠጥሟት ዘንድ አዘዘ ባሕሩም በሕይወቷ ተፋት ዳግመኛም በአራት ካስማ መካከል አስተኝተው ዘርግተው አሥረው ታላቅና ጽኑዕ የሆነ ግርፋትን ይገርፋዋት ዘንድ አዘዘ መኰንኑም እንዳዘዘ አደረጉባት ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰባትም። ከዚህም በኋላ ወደ አዘጋጁላት የእሳት ማንደጃ ውስጥ ይጨምርዋት ዘንድ አዘዘ በጨመርዋትም ጊዜ ነፍሷን በ #እግዚአብሔር እጅ ሰጠች በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊል ተቀበለች።
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አንስጣስያ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።
#ቅዱስ_አቦሊ_ጻድቅ
+ቅዱሱ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የ #ክርስቶስን ሕማማት ለመሳተፍ ሲተጉ ከኖሩ ጻድቃን አንዱ ነው:: መሉ ጊዜውን በበርሃ ሲያሳልፍ ብዙ ተጋድሎን ፈጽሟል:: በተለይ ሲጸልይ እግሩን ከዛፍ ላይ አስሮ: ቁልቁል ከባሕር ውስጥ ሰጥሞ ነው:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ዕረፍቱን ታስባለች::
=>አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን: ክብሩን ያድለን:: ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን::
=>ታሕሳስ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት አንስጣስያ ሰማዕት
2.ቅዱስ አቦሊ ጻድቅ
3.ቅድሰት ዮልያና ሰማዕት

=>በ 26 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
++"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን
በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ)