Telegram Web Link
ዳግመኛም ለጣዖታት መስገድን እሺ ይለው ዘንድ ቅዱስ ጢሞቴዎስን ማባበል ጀመረ እምቢ ባለውም ጊዜ የነዳጅ ድፍድፍ ሥጋውን ቀብተው ከእሳት ማንደጃ ውስጥ እንዲጨምሩት አዘዘ በጨመሩትም ጊዜ የ #እግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ከዚህ ቃጠሎ አዳነው ።

ከዚህም በኋላ ሁለተኛ ወደ ወህኒ ቤት መለሱት ተአምራትንም የሚያደርግ ሆነ በአንዲት ዕለትም በዚያ ሲጸልይ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደርሱ መጥቶ ቃል ኪዳንን ገባለት ሰላምታንም ሰጠው።

በማግሥቱም ከእሥር ቤት አውጥተው ወደ በንሑር ከተማ ወስደው ቅድስት ራሱን ቆረጡ ያን ጊዜ ንውጽውጽታ ሆነ አየርም መላእክትን ተመላች አማንያን ሰዎችም መጥተው ሥጋውን ወስደው በመልካም አገናነዝ ገንዘው ቀበሩት። የመከራውም ዘመን በአለፈ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ሠሩለት ሰኔ ሃያ ሰባት ቀንም አከበርዋት ሥጋውንም በውስጥዋ አኖሩ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_27#ከገድላት_አንደበት እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_27_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ፊልሞና 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የክርስቶስ ኢየሱስ እስር ጳውሎስ ወንድሙም ጢሞቴዎስ፥ ለተወደደውና አብሮን ለሚሠራ ለፊልሞና፥
² ለእኅታችንም ለአፍብያ፥ ከእኛም ጋር አብሮ ወታደር ለሆነ ለአርክጳ፥ በቤትህም ላለች ቤተ ክርስቲያን፤
³ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
⁴-⁵ በጌታ በኢየሱስ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ ዘንድ ስላለህ ስለ ፍቅርህና ስለ እምነትህ ሰምቼ፥ በጸሎቴ እያሳሰብሁ ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤
⁶ የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤
⁷ የቅዱሳን ልብ በአንተ ስራ ስለ ዐረፈ፥ ወንድሜ ሆይ፥ በፍቅርህ ብዙ ደስታንና መጽናናትን አግኝቼአለሁና።
⁸ ስለዚህ የሚገባውን አዝህ ዘንድ በክርስቶስ ምንም እንኳ ብዙ ድፍረት ቢኖረኝ፥
⁹ ይልቁንም እንደዚህ የሆንሁ እኔ ጳውሎስ ሽማግሌው፥ አሁንም ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ እስር የሆንሁ፥ ስለ ፍቅር እለምናለሁ።
¹⁰-¹¹ አስቀድሞ ስላልጠቀመህ፥ አሁን ግን ለእኔም ለአንተም ስለሚጠቅም በእስራቴ ስለ ወለድሁት ስለ ልጄ ስለ አናሲሞስ እለምንሃለሁ።
¹² እርሱን እልከዋለሁ፤
¹³ አንተም ልቤ እንደሚሆን ተቀበለው። እኔስ በወንጌል እስራት ስለ አንተ እንዲያገለግለኝ ለራሴ ላስቀረው እፈቅድ ነበር፥
¹⁴ ነገር ግን በጎነትህ በፈቃድህ እንጂ በግድ እንዳይሆን፥ ሳልማከርህ ምንም እንኳ ላደርግ አልወደድሁም።
¹⁵ ተቀብለህ ለዘላለም እንድትይዘው ስለዚህ ምናልባት ለጊዜው ተለይቶሃልና፤
¹⁶ ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባሪያ አይሆንም፥ ነገር ግን ለእኔ በተለየ የተወደደ ወንድም ከሆነ፥ ለአንተማ ይልቅ በስጋውም በጌታም ዘንድ ከባሪያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም።
¹⁷ እንግዲህ እንደ ባልንጀራ ብትቈጥረኝ፥ እንደ እኔ አድርገህ ተቀበለው።
¹⁸ በአንዳች ነገር የበደለህ ቢኖር ግን ወይም ብድር ያለበት እንደሆነ፥ ይህን በእኔ ላይ ቍጠር፤
¹⁹ እኔ ጳውሎስ፦ እኔ እመልሰዋለሁ ብዬ በእጄ እጽፋለሁ፤ ከዚህም በላይ ለእኔ የራስህ ደግሞ ብድር እንዳለብህ አልልህም።
²⁰ አዎን፥ ወንድሜ ሆይ፥ በጌታ እኔ እንድጠቀምብህ ይሁን፤ በክርስቶስ ልቤን አሳርፍልኝ።
²¹ ከምልህ ይልቅ አብልጠህ እንድታደርግ አውቄ እንድትታዘዝም ታምኜ እጽፍልሃለሁ።
²² ደግሞ ከዚህም ጋር የማስተናገጃ ቤት አዘጋጅልኝ፤ በጸሎታችሁ ለእናንተ እንድሰጥ ተስፋ አደርጋለሁና።
²³ በክርስቶስ ኢየሱስ ከእኔ ጋር የታሰረ ኤጳፍራ
²⁴ አብረውኝም የሚሰሩ ማርቆስና አርስጥሮኮስ ዴማስም ሉቃስም ሰላምታ ያቀርቡልሃል።
²⁵ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
¹⁰ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል።
¹¹ ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
¹² እየመከርኋችሁና የምትቆሙባት ጸጋ እውነትኛ የእግዚአብሔር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ፥ የታመነ ወንድም እንደ ሆነ በቈጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ።
¹³ ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
¹⁴ በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን። አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ በርናባስም ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ መጣ፤
²⁶ ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።
²⁷ በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤
²⁸ ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ፤ ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ።
²⁹ ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤
³⁰ እንዲህም ደግሞ አደረጉ፥ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_27_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ጸኒሐ ጸናሕክዎ ለ #እግዚአብሔር። ሰምዐኒ ወተመይጠኒ። ወስምዐኒ ቃለ ስእለትየ። መዝ.39÷1-2
“ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኸቴንም ሰማኝ።” መዝ.39÷1-2
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_27_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከዚህም በኋላ ጌታ ሌሎቹን ሰብዓ ሾመ፥ ሁለት ሁለትም አድርጎ እርሱ ሊሄድበት ወዳለው ከተማና ስፍራ ሁሉ በፊቱ ላካቸው።
² አላቸውም፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።
³ ሂዱ፤ እነሆ፥ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ።
⁴ ኮረጆም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድም ለማንም እጅ አትንሡ።
⁵ ወደምትገቡበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ፦ ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን በሉ።
⁶ በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለዚያም ይመለስላችኋል።
⁷ በዚያም ቤት ከእነርሱ ዘንድ ካለው እየበላችሁና እየጠጣችሁ ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋልና። ከቤት ወደ ቤት አትተላለፉ።
⁸ ወደምትገቡባትም ከተማ ሁሉ ቢቀበሉአችሁ፥ ያቀረቡላችሁን ብሉ፤
⁹ በእርስዋም ያሉትን ድውዮችን ፈውሱና፦ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ቀረበች በሉአቸው።
¹⁰ ነገር ግን ወደምትገቡባት ከተማ ሁሉ ባይቀበሉአችሁ፥ ወደ አደባባይዋ ወጥታችሁ፦
¹¹ ከከተማችሁ የተጣበቀብንን ትቢያ እንኳን እናራግፍላችኋለን፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ግን ወደ እናንተ እንደ ቀረበች ይህን እወቁ በሉ።
¹² እላችኋለሁ፥ በዚያን ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶም ይቀልላታል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል መልካም የጾሞ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ሰላም ለያዕቆብ ዕጉሠ መከራ በሕቁ
#እግዚአብሔር ሰማዕተ ጽድቁ። አርብዓ ወክልኤ እስከ ይከውን ኊልቁ። አባሎ በመጥባሕት አመ ሐራ ንጉሥ ሠጠቁ። መንፈቀ ሥጋሁ ጸለየ መዊቶ መንፈቁ"። ትርጉም፦ በእጅጉ (ባያሌው) መከራን የታገሠ ለ #እግዚአብሔር የእውነት ምስክሩ ለያዕቆብ ሰላምታ ይገባል፤ ቊጥሩ አርባ ኹለቱ እስኪኾን ድረስ የንጉሥ ጭፍሮች ሰውነቱን በሰይፍ በቈረጡ ጊዜ እኩሌታ አካሉ ሞቶ እኩሌታ አካሉ ጸለየ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 27።
#ለፀአተ_ነፍስከ

#መስቀል ልዩ ልዩ ልዩ አምላካዊ ተአምራትና ሕማማተ #መስቀል ከተፈጸመ በኃላ በገዛ ሥልጣንህ ለተፈጸመው ጸዓተ ነፍስህ ሰላም እላለሁ። ልዩ መዓዛ ላለው በድነ ሥጋህም ሰላም እላለሁ።

#ፈጣሪዬ_ክርስቶስ_ሆይ ዓለምን ለማዳን በተሰቀልክበት በዛ ሰዓት እነሆ #ጌታዬ_ሆይ ፀሐይ ብርሃኑን ከመስጠት ተከልክሎ ጊዜው ጨለመ ጨረቃም ደም ሆነ።

#መልክአ_መድኃኔ_አለም

#መድኃኔ_አለምን የስቅለቱን በዓል የሚያቃልልና የማያከብር ቢኖር ዕድል ፈንታው ከቀያፋና ከሐና ጋር ነው።

የሚያከብረውና መታሰቢያውን የሚያደርግ ግን #መድኃኒታችንን የተቀበሉት የዮሴፍና የኒቆዲሞስ ጓደኛቸው ይሆናል። እሱ ራሱ በኢሳይያስ አንደበት ባለፀጎች ሴቶች ተነሡ ቃሌንም ስሙኝ። የምታምኑ ወጣቶችም ነገሬን አዳምጡኝ በየዓመቱም መከራ በተቀበልኩባት ቀን መታሰቢያዬን አድርጉ ብሏልና።

ባለፀጎች ሴትች የተባሉ ሐዋርያት፣ የሚያምኑ ወጣቶች የተባሉ የጥምቀት ልጆች ናቸው። የ #መድኃኒታችን የመከራው ቀን የተባለችም ይህቺ ናት።

የመዳን ቀን ዛሬ ነው፣ የጦርነት ቀን ዛሬ ነው፣ የማሸነፍ ቀን ዛሬ ነው፣ የብረቱ በር የተሰበረው በውስጡም ያለው የተበረበረ ዛሬ ነው፣ የሞት ሥልጣን የተሻረ ሰይጣንም የታሰረ ዛሬ ነው፣ ምርኮ የተመለሰ ዛሬ ነው፣ የደዌ ቁስል የተፈወሰ ዛሬ ነው። ነብዩ ሆሴዕ እሱ ገረፈን እሱም ይፈውሰናል እሱም ያድነናል እንዳለ። በሁለት ቀን ማለትም አንዲቱ ቀን ከአዳም እስከ ሙሴ ሁለተኛይቱም ቀን ከሙሴ እስከ #መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስቅለት ያለው ነው። የዚያን ጊዜ በጨለማ ቦታ የተሰቃዩ ነቢያት ተፈወሱ። በሦስተኛው ቀን ያነሣናል የተባለውም ከ #መድኃኒታችን ስቅለት እስከ ዓለም ፍጻሜ ያለው ቀን ነው።

#ድርሳነ_መድኃኔ_አለም
#ኅዳር_28

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ሃያ ስምንት በዚህች ቀን #ቅዱስ_ሰረባሞን በሰማዕትነት ያረፈበት፣ በደብረ ቊንጽል ተጋድሏቸውን የፈጸሙ #አባ_ሊቃኖስ የተሰወሩበት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሰረባሞን

ኅዳር ሃያ ስምንት በዚህች ቀን የሀገረ ኒቅዮስ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ሰረባሞን በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም ቅዱስ በኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ለሆነ ለእስጢፋኖስ ከዘመዶቹ ውስጥ ነው። የአባቱም ስም አብርሃም ነው እርሱ የሌዊ ልጅ የዮሴፍ ልጅ ለስምዖን ወንድም ለእስጢፋኖስ እናት ወንድሟ የሆነ ነው። በተወለደም ጊዜ በአባቱ ስም ስምዖን ብለው ጠሩት አባቱም ሲሞት ክርስቲያን ይሆን ዘንድ ወደደ።

#እግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ወደ ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስ እንዲሔድ አዘዘው እንዳዘዘውም ሔደ። እርሱም የ #መድኃኒታችንን_የክርስቶስን ሰው የመሆኑን ምሥጢር ገለጠለት ግን ዘመዶቹ የሆኑ አይሁድን ስለፈራ በኢየሩሳሌም አገር የክርስትና ጥምቀትን ሊአጠምቀው አልደፈረም።

ኤጲስቆጶሱም ስለርሱ ምን እንደሚያደርግ ሲያስብ እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም ተገልጣለት ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎናስ እንዲልከው አዘዘችው።

ሰረባሞንም እየተጓዘ ሳለ እነሆ የ #እግዚአብሔር መልአክ ቀደም ብሎ በሰው አምሳል ወደ ቴዎናስ ቀርቦ ስለ ቅዱስ ሰረባሞን አስረዳው ሰረባሞንም በደረሰ ጊዜ የ #እግዚአብሔርን ሕግ አስተምሮ የከበረች የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው።

ከዚህም በኋላ ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ በሆነች በአባ ሳዊሮስ ገዳም ውስጥ መነኰሰ አባ ቴዎናስም በአረፈ ጊዜ በእርሱ ፈንታ አባ ጴጥሮስ ተሾመ። ያን ጊዜም መልክተኞችን ልኮ ይህን አባ ሰረባሞንን ወደርሱ አስመጥቶ በሊቀ ጵጵስናው ሥራ እንዲራዳው አደረገ።

ከዚህም በኋላ ኒቅዮስ ለሚባል አገር ኤጲስቆጶስነት ሾመው። ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትም በእርሱ ደስ አላቸው #እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆች ተአምራትን አደረገ በአገሩ አቅራቢያ ሰዎች የሚያመልኳቸው የጣዖታት ቤቶች ነበሩ ያጠፋቸውም ዘንድ #እግዚአብሔርን ለመነው በዚያንም ጊዜ ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻቸውና በቦታው ላይ ባሕር ሁኖ ሸፈናቸው። #እግዚአብሔርም ከሀገረ ስብከቱ ጣዖታትን ደመሰሰ ዳግመኛም #አብን #ወልድን #መንፈስ_ቅዱስን አንድ አካል የሚያደርግ የሰባልዮስን ስድብ አስወገደ።

ዲዮቅልጥያኖስም ክዶ ጣዖታትን በአመለከ ጊዜ ቅዱስ ሰረባሞን የአማልክትን አምልኮ እንደሚሽር ነገሩት እርሱም ሰምቶ ተቆጣ ወደረሱም እንዲአመጡት አዘዘ ሲወስዱትም ከንጉሥ መልክተኞች ጋር እስክንድርያ ከተማ ደረሰ ሊቀ ጳጳሳት ጴጥሮስም ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋር ብዙ ካህናት ነበሩ ሰላምታም ሰጡት ፊቱም እንደ #እግዚአብሔር መልአክ ፊት ብሩህ ሁኖ አዩት።

ወደ ንጉሡም በደረሰ ጊዜ በተለያዩ በብዙ ዓይነት ሥቃይ አሠቃየው ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ያለ ጥፋት በጤንነት አስነሣው። ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ብዙዎች አመኑ።

ሕዝቡ ሁሉ በእርሱ ምክንያት በ #ጌታችን እንዳያምኑ ንጉሡ ፈርቶ የእንዴናው ገዥ አርያኖስ ወዳለበት ወደ ላይኛው ግብጽ ሰደደው በዚያ እንዲአሠቃየውና ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጥ በዚያንም ወቅት መኰንኑ አርያኖስ የኒቅዮስ ከተማ ወደብ አቅራቢያ በመርከብ ውስጥ ነበር። መርከቢቱም ቆመች ከቦታዋም ሊአንቀሳቅሱዋት አልተቻላቸውም ቅዱስ ሰረባሞንንም አውጥተው ለሀገሩ ደቡብ ወደ ሆነ ቦታ ወስደው በዚያ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት ምእመናንም መጥተው ሥጋውን ወስደው በክብር ገነዙትና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከሥጋውም ድንቆች ተአምራት ሆኑ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ሊቃኖስ

በዚችም ቀን በኢትዮጵያ ምድር በደብረ ቊንጽል ተጋድሏቸውን የፈጸሙ አባ ሊቃኖስ ተሰወሩ።

አቡነ ሊቃኖስ ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ ናቸው አቡነ ሊቃኖስ ለየት የሚሉበት ነገር ቢኖር ዓሥሩም የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና ያበሩ ነበር፡፡ ይህንንም ገድለ አቡነ አረጋዊ "ቆመው ጸሎት በሚጸልዩበት ጊዜ ዓሥሩ የእጆቻቸው ጣቶችና ዓሥሩ የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና የሚያበሩበትና እንደመብረቅ የሚብለጨልጩበት ጊዜ አለ" በማለት ይገልጸዋል፡፡ በሥዕላቸውም ላይ ይህንኑ ለማሳየት አባቶቻችን የራሳቸውን ጥበብ ተጠቅመዋል፡፡

የአቡነ ሊቃኖስ ገዳማቸው በደብረ ቁናጽል አክሱም ከአባ ጰንጠሌዎን ገዳም አቅራቢያ ይገኛል፡፡ ጻድቁ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደረጉ ነበር፡፡ መላእክትም ዘወትር ባለመለየት ይጎበኙዋቸው ነበር፡፡ #ጌታችን_አምላካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ዘወትር እየተገለጠላቸው ይባርካቸውና ቃልኪዳን ይሰጣቸው ነበር፡፡

በጸሎታቸውም አጋንንትን አውጥተዋል፣ ድውያንን ፈውሰዋል፣ ዕውራንን አብርተዋል፣ ሙታንን አንሥተዋል፡፡ ስለዘጠኙ ቅዱሳን ሐዋርያዊ አገልግሎት ከአቡነ አረጋዊ ገድል ጋር ጥቅምት 14 በስፋት ስለተጻፈ ከዚያ ላይ ይመለከቷል፡፡

ከተስዓቱ ቅዱሳን ውስጥ አራቱ ሞትን ሳያዩ ተሰውረዋል፡፡ አቡነ አረጋዊ ጥቅምት 14 ቀን ተሰወሩ፡፡ አቡ ገሪማ ሰኔ 17 ቀን፣ አቡነ አፍጼ ግንቦት 29 ቀን፣ አቡነ ሊቃኖስ ህዳር 28 ቀን ተሰወሩ፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_28 እና #ከገድላት_አንደበት)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_28_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ገላትያ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ዘንድ ተአምራት የሚያደርግ፥ በሕግ ሥራ ነውን ወይስ ከእምነት ጋር በሆነ መስማት ነው?
⁶ እንዲሁ አብርሃም በእግዚአብሔር አመነና ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።
⁷ እንኪያስ ከእምነት የሆኑት እነዚህ የአብርሃም ልጆች እንደ ሆኑ እወቁ።
⁸ መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ።
⁹ እንደዚህ ከእምነት የሆኑት ካመነው ከአብርሃም ጋር ይባረካሉ።
¹⁰ ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና።
¹¹ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።
¹² ሕግም ከእምነት አይደለም ነገር ግን፦ የሚያደርገው ይኖርበታል ተብሎአል።
¹³ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤
¹⁴ የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ።
¹⁵ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። የሰው ስንኳ ቢሆን እርግጠኛውን ኪዳን ማንም አይንቅም ወይም አይጨምርበትም።
ወይም👇
2ኛ ቆሮ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ስለዚህ ምክንያት ምሕረት እንደ ተሰጠን መጠን ይህ አገልግሎት ስላለን አንታክትም።
² ነገር ግን የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላለስም የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናመሰግናለን።
³ ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው።
⁴ ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።
⁵ ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።
⁶ በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና።
⁷ ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ያዕቆብ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?
²² እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?
²³ መጽሐፍም፦ አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።
²⁴ ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።
²⁵ እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?
²⁶ ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ፦ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ በዚህ ስለ ምን ትደነቃላችሁ? ወይስ በገዛ ኃይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድ እንዳደረግነው ስለ ምን ትኵር ብላችሁ ታዩናላችሁ?
¹³ የአብርሃምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቈርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው።
¹⁴ እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፥
¹⁵ የሕይወትንም ራስ ገደላችሁት፤ እርሱን ግን እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው፥ ለዚህም ነገር እኛ ምስክሮች ነን።
¹⁶ በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፥ በእርሱም በኩል የሆነው እምነት በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤና ሰጠው።
¹⁷ አሁንም፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ እንደ አለቆቻችሁ ደግሞ ባለማወቅ እንዳደረጋችሁት አውቄአለሁ፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_28_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"በርህ ሠረቀ ለጻድቃን። ወለርቱዓነ ልብ ትፍሥሕት። ይትፌሥሑ ጻድቃን በእግዚአብሔር። መዝ.96÷11-12
"ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ። ጻድቃን፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ"። መዝ.96÷11-12
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_28_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማርቆስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ ከሙታንስ ሲነሡ በሰማያት እንዳሉ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፥ አይጋቡምም።
²⁶ ስለ ሙታን ግን እንዲነሡ እግዚአብሔር፦ እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቍጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን?
²⁷ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም። እንግዲህ እጅግ ትስታላችሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ሠለስቱ_ምዕት_ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና መልካም የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
#ኅዳር_29

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን #የአቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ ዘጠገሮ ልደታቸው ነው፣ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን #የቅዱሳን_ሰማዕታተ_ክርስቶስ መታሰቢያቸው ነው፣ የሰማዕታት መፈጸሚያ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ጴጥሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ የሊቀ ሐዋርያት ጴጥሮስ ደቀ መዝሙሩ #ቅዱስ_ቀሌምንጦስ_ሐዋርያ በሰማዕትነት አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ

ኅዳር ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን የአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ልደታቸው ነው።

ጻድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው፡፡ የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ህዳር 29 ተወለዱ፡፡ አባታቸው ድላሶር እናታቸው እምነ ጽዮን ይባላሉ፡፡ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል፡፡ ወላጆቻቸውም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው ሄደው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ፡፡ አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ ‹‹በምን አውቀኸኝ ነው?›› ብላ አቅፋ ሳመችውና ‹‹ከእንግዲ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ መላእክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 ትኖራለህ" ብላ ባርካው ተሰወረች፡፡

ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዩሐንስ ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ፡፡ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኃላ በደመና ተጭኖ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በድብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በጾምና በጸሎት በተጋድሎ ኖዋል፡፡ ከዚኽም በኋላ አባ ዩሐንስ ወደ ተዘጋቸላቸው ምድር በቅዱስ ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ፡፡ ይኽም ጠገሮ ያለው ገዳማቸው በሰሜን ሸዋ በመንዝና ይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር አንድ ሰዓት ከተጓዙ በኃላ ይገኛል፡፡

ሕዝቡ በተለምዶ እጨ ዮሐንስ እያለ ይጠራቸዋል እንጂ ስማቸው እጨጌ ዮሐንስ ነው፡፡ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ መስቀል ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል፡፡ በልደታቸው ቀን ኅዳር 29 ቀን መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ጸበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ጸበሉ ይወርዳል፡፡ እዛው ቆይቶ መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል፡፡ ይህ በዘመናችንም ጭምር እየታየ ያለ ታላቅ ተአምር ነው፡፡

አባታችን በታላቀ ተጋድሎ ሣሉ ሰይጣን የሀገሩን ሰዎች በጠላትነት እንዲነሡባቸው አደረገ፡፡ ሰዎቹም አባታችንን እንዴት እንደሚያጠፏቸው ይማከሩ ጀመር፡፡ ሊገድሏቸው ፈልገው ቅድስናቸው በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነውና ፈሩ፡፡ ከዚኽም በኋላ ‹‹ለምን ከመንደራችን ከወንድ ያረገዘች ሴት ፈልገን እሳቸው አስረገዟት ብለን በሐሰት እንከሳቸው?›› ብለው ተማከሩ፡፡ ብዙ ወርቅና ብርም ለአንዲት ሴት ሰጥተው በሐሰት ከእርሱ አርግዣለሁ ብላ እንድትመሰክር አደረጓት፡፡ አባታችንም በሕዝብ ፊት በሐሰት ተከሰሱ፡፡ ጻድቁም ‹‹አንቺ ሴት ከእኔ ነው ያረገሽው?›› አሏት እርሷም ‹‹አዎ ከአንተ ነው ልትክድ ነው እንዴ?›› አለቻቸው፡፡ አባታችንም በዚህ አዝነው ‹‹በአንቺና በእኔ መካከል እግዚአብሔር ይፍረድ›› ሲሉ ያች ሴት ወዲያው ለሁለት ተሰንጥቃ ሞተች፡፡ የአገሩ ሰዎችም እጅግ ፈሩ፡፡ አባታችንም ምድሪቱን እረገሟት፡፡ ‹‹የተዘራው ዘር አይብቀልብሽ፣ የተተከለው አይፅደቅ፣ ብርድና ውርጭ ይፈራረቅብሽ›› ብለው እረግመዋት በደመና ተጭነው ወደ ሰሜን ጎንደር እስቴ ጉንደ ተክለተሃማኖት ሔዱ፡፡
አቡነ ዩሐንስ በመላው ኢትዮጵያ ወንጌልን እየተዘዋወሩ ያስተማሩ ሲሆን ከቅድስናቸው የተነሣ በፀሐይ ላይ 50 ዓመት፣ በጨረቃ ላይ 50 ዓመት፣ በደመና ላይ 50 እንዲሁም ዓለምን በክንፋቸው በመዞር በደመና ላይ 50 የኖሩ ከሰው ተወልደው ከመላእክት የተደመሩ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በይፋት ጠግሮ በዓለወልድ፣ በአፋር አዘሎ፣ በመንዝ ፍርኩታ ኪዳነምሕረት፣ በደብረ ሊባኖስ፣ በጎንድ ተክለ ሃይማኖት በሌሎችም ቦታዎች በመዘዋወር በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ አባታችን ከሰማይ መስቀል የወረደላቸው ሲሆን ዛሬም በገዳማቸው የሔደ ሰው በወረደው በእጃቸው መስቀል እየተዳበሰ ቆመው በጸለዩበት ባሕር በጠበላቸው ይጠመቃል፡፡ በተጨማሪም ይይዙት በነበረውም መቋሚያቸው በመዳበር በረከትን ማግኘት ይቻላል፡፡ ቆመው ከጸለዩበት ባሕር ውስጥ ደረቅ አሸዋ ይወጣል፡፡ አባ ዩሐንስ 500 ዓመት ከኖሩ በኃላ እረፍተ ዘመናቸው ሲደርስ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከ15 ነቢያት፣ ከ12 ሐዋሪያት፣ ሄሮድስ ያስፈጃቸው ከመቶ አርባ አራት ሺ ሕፃናት፣ ከአብርሃም ከይስሐቅ፣ ከዕቆብ ጋር ሁሉንም ነገደ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ታላቅ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ "ስምህን የጠራ ገዳምህን የረገጠ፣ መባ የሰጠ፣ ቤተ ክርስትያንህን የሠራ ያሠራ የረዳ፣ ገድልህን የሰማ ያሰማ ያስተረጎመ፣ መታሰቢያን ያደረገ እስከ 10 ትውልድ እምርልሀለው፤ ንስሀ ሳይገባ አይሞትም፣ ልጅ መውለድ ባይችል እኔ ልጅ እሰጠዋለሁ፤ ገድልህን በቤትህ ያስቀመጠ እርኩስ መንፈስ፣ ክፉ አጋንንት ቸነፈር ወባ መልአከ ጽልመት አይነካውም፡፡ በገዳምህ መነኩሴ ቢቀበር በሰማይ ክንፍ አበቅልለታለሁ፤ አይሁድም አረማዊም ያላመነ ያልተጠመቀ በገዳምህ መጥቶ ቢያርፍ ይቅር እልልሃለሁ፣ እንደ መቃብሬ ጉልጎታ እንደተቀበረ አድርጌ እቆጥርልሃለሁ…" የሚል ቃል ኪዳን ከሰጣቸው በኃላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡

ቅዱስ አባታችንም በ500 ዓመታቸው ሐምሌ 29 ቀን ዐርፈው በጎንድ ተክለ ሃይማኖት ተቀብረዋል፡፡ በሰሜን ጎንደር የሚገኘውን ይህንን ገዳም ጻድቁ ራሳቸው ናቸው የመሠረቱት፡፡ ነገር ግን የገዳሙን ስያሜ በአባታቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም አድርገውታል፡፡ አቡነ ዮሐንስ ካረፉ በኋላ በእርግማናቸው መሠረት በመንዝና በይፋት ብርዱ ድርቁ ስለበዛባቸው አንድ ብቁ ባሕታዊ ከበዓታቸው ወጥተው ‹‹በሐሜታችሁ ምክንያት እጨ ዮሐንስ ስለረገማችሁ ነው የእርሱን ዐፅም ካላመጣችሁ ብርዱ ውርጩ ድርቁም አይጠፋላችሁም›› አሏቸው፡፡ ሕዝቡም አባታችን በጉንድ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከተቀበሩ ከ134 ዓመት በኃላ በቅዱሳን እየተመሩ ሄደው በሌሊት ግማሽ ዐፅማቸውን አምጥተው በሀገራቸው አምጥተው ስላስቀመጡ ብርዱና ውርጩ በመንዝ እየቀነሰላቸው መጥቷል፡፡ ዛሬም በሀገሩ ብርዱና ውርጭ ሲበዛ የጻድቁን ታቦት ሲያወጡ ውርጩ ይጠፋል፡፡ ጠገሮ በሚባለው ገዳማቸው ውስጥ የሚገኘው ጠበላቸው እጅግ አስደናቂ ነው፡፡

ዐፅማቸውን ከጉንደ ተክለሃይማኖት አምጥተው አርባ ሐራ መዳኒዓለም አጠገብ በላይ በፍሩክታ ኪዳነምሕረት መጋቢት 18 ፍልሰተ ዐፅማቸው ተከናወነ፡፡ ምድሪቷም ተባረከች፣ የዘሩትንም አበቀለች፣ ውርጩም ብርዱም ቀነሰ፣ ዝናብ አልዘንብ ሲል ወይም ሰብል የሚጨርስ አንበጣ ሲመጣ ታቦታቸው ወጥቶ ምህላ ይያዛል። ወድያውም መቅሰፍት ይርቃል፣ ዝናብም ይዘንባል፡፡ ጻድቁ ደመናን፣ ጨረቃንና ፀሐይን በእጃቸው እየያዙ ይጸልዩ ነበር፡፡ በጠገሮ፣ በአዘሎ፣ በፍርኩታና በሌሎቹም ታላላቅ ቦታቦዎች ላይ በእያንዳንዱ ገዳም
ሃምሳ ሃምሳ ዓመት በጸሎት ኖረው በአጠቃላይ በ500 ዓመታቸው ነው ያረፉት፡፡ ዐፅማቸው መንዝ ከአርባ ሐራ መድኃኔዓለም አጠገብ ፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ውስጥ ይገኛል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_ሰማዕታተ_ክርስቶስ

ኅዳር ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን በዚችም ዕለት በከሀዲው ንጉሥ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት የሞቱ የአርባ ሰባት አእላፋት መታሰቢያቸው ነው።

ቤተ ክርስቲያን ዛሬ (ኅዳር 29) የሁሉንም ሰማዕታት በዓል ታከብራለች። አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቅዱሱ ሊቅ) በመጽሐፈ ሰዓታት ሰማዕታትን:-
"መስተጋድላን ከዋክብት ብሩሃን።
ማኅትዊሃ ለቤተ ክርስቲያን።" ይላቸዋል።

በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሮም መንግስት ዓለምን የሚያስተዳድረው በሁለት ከተሞች ማለትም በራሷ በሮምና በአንጾኪያ ነበር። የወቅቱ ንጉሥ ኑማርያኖስ ሲሆን የቤተ መንግስቱ ልዑላንና የጦር አለቆች ቅዱሳኑ:- ፋሲለደስ፣ ገላውዴዎስ፣ ፊቅጦር፣ መቃርስ፣ አባዲር፣ ቴዎድሮስ (ሦስቱም)፣ አውሳብዮስ፣ ዮስጦስ፣ አቦሊ ሌሎቹም ነበሩ።

ሴቶቹ ደግሞ ቅዱሳቱ:- ማርታ፣ ሶፍያ፣ ኢራኢ፣ ታኡክልያ ሌሎቹም ነበሩ። ለእነዚህ ሁሉ የበላይ ደግሞ ቅዱስ ፋሲለደስ ነበር። ወቅቱ ከፋርስ፣ ከቁዝና ከበርበር ጦርነት የሚበዛበት ነበርና ባጋጣሚ ንጉሡ ኑማርያኖስ በሰልፍ መካከል ተመትቶ ወደቀ (ሞተ)።

የሮም መንግስትም ባዶ ሆነች። ዙፋኑን መያዝ ለቅዱስ ፋሲለደስም ሆነ ለሌሎቹ ቅዱሳን ቀላል ነበር። ግን እነሱ ዝም ብለው ጠላትን ለመዋጋት ወጡ።

በዘመኑ ደግሞ በግብጽ የፍየል እረኛ የነበረና ከልጅነቱ ሰይጣን የሚያናግረው አንድ አግሪጳዳ የሚሉት ጉልበተኛ ሰው ነበር። ንጉሡ ከወለዳቸው ልጆች ሁለቱ ሴቶች ክፉዎች ነበሩና ትንሿ አግሪጳዳን ማንም በሌለበት አንግሣ ጠበቀቻቸው። ስሙንም ዲዮቅልጢያኖስ አለችው።

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም። የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው። ትልቋ ደግሞ የትንሿን አይታ መክስምያኖስ የሚባል አውሬ አግብታ አነገሠችው። ዓለምም በእነዚህ ጨካኝ ሰዎች እጅ ወደቀች።

ሠራዊቱ ሁሉ በሚሊየን ይቆጠራሉ። የተደረገውን ሲያዩ ተበሳጩ። ይህንን የተመለከተው ቅዱሱ ፋሲለደስ ግን ልዑላኑንና አለቆችን ሰብስቦ "ይህ ዓለም ከነ ክብሩ ጠፊ ነው። ስለዚህ የተሻለውን የክርስቶስን መንግስት እንምረጥ" አላቸው። ሁሉም እንደ አንድ ልብ መካሪ ደስ ተሰኝተው ምድራዊ ክብራቸውን ሊተው ወሰኑ።

ቀጥለውም በአንድ ቤት ተሰብስበው ይጾሙ ይጸልዩ ገቡ። ወደ ውጪ የሚወጡት ለምጽዋት ብቻ ነበር። ከሃዲውም ይህንን ሲያይ የልብ ልብ ተሰማው። ከድሮ ያሰበውንና ክርስቲያኖችን የማጥፋቱን እቅድ ሊፈጽም ምክንያት አገኘ።

አባ አጋግዮስ በሚባል መነኩሴ ምክንያት "አብያተ ክርስቲያናት ይትዐጸዋ አብያተ ጣዖታት ይትረኀዋ" "ቤተ ክርስቲያኖች ይዘጉ ቤተ ጣዖቶችም ይከፈቱ" አለ። አጵሎን፣ አርዳሚስ የሚባሉ ጣዖቶችንም አቆመ።

በዚህ አዋጅ ምክንያትም የክርስቲያኖች ሰቆቃ ጀመረ። ምድር በደም ታጠበች፣ ቅዱሳኑ ቀባሪ አጡ፣ እኩሉ ተገደለ፣ እኩሉ ተቃጠለ፣ እኩሉ ታሠረ፣ እኩሉም ተሰደደ።

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተጻፈው በብራናና በብዕር አይደለም። ይልቁኑ እንደ ቀለም የሰማዕታት ደማቸው፣ እንደ ብዕር አጥንታቸው፣ ቆዳቸው እንደ ብራና ሆኖ ተጽፏል እንጂ። ሰማዕታት ለሃይማኖታቸው የከፈሉት ዋጋ እጅግ ታላቅ ነው።

ስለዚህም "ተጋዳዮች የሚያበሩ ኮከቦች፣ የቤተ ክርስቲያን ሻማዎች" ተብለው እነሱ እየቀለጡ አብርተዋል። ሰማዕትነት በብሉይ ኪዳን የጀመረና እስከ ዳግም ምጽዐተ ክርስቶስም የሚቀጥል ቢሆንም "ዘመነ ሰማዕታት" የሚባለው ከ150 እስከ 312 ዓ.ም ድረስ ያለው ዘመን ነው።

በተለይ ግን ከ270ዎቹ እስከ 312 ዓ.ም ድረስ ያሉ ዓመታት እጅግ የከፉ ነበሩና የአርባ ሰባት ሚሊየን (47,000,000) ክርስቲያኖች ደም በምድር ላይ ፈሷል። የሰማዕታት ምሥጢራቸው ቃለ ወንጌል፣ የጌታ ስብከትና ሕይወት እንጂ ሌላ አይደለም። (ማቴ.10፥16, ማር.13፥9, ሉቃ.12፣4, ዮሐ.16፥1, ሮሜ.8፥35, ራዕይ.2፥9)

የቅዱሳን ሰማዕታት መነሻቸው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ፍጻሜአቸው ደግሞ ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳሳት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ተፍጻሜተ_ሰማዕት

በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዐሥራ ሰባተኛ የሆነ የተመሰገነና የከበረ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ጴጥሮስ በሰማዕትነት አረፈ እርሱም የሰማዕታት መፈጸሚያ በመሆን ነው።

የዚህ አባት ወላጅ አባቱ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ካህናት ነው ስሙም ቴዎድሮስ ነው የእናቱም ስም ሶፍያ እነርሱም እግዚአብሔርን እጅግ የሚፈሩ ጻድቃን ናቸው ነገር ግን ልጅ አልነበራቸውም። በሐምሌ ወር በአምስት የቅዱሳን ሐዋርያት የጴጥሮስና የጳውሎስ በዓላቸው በሆነ ጊዜ ብዙ ክርስቲያኖች ያማሩ ልብሶችን ከልጆቻቸው ጋር ተሸልመው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ የዚህ ቅዱስ እናት ሶፍያ አየች። በከበረ መሠዊያውም አንጻር ቁማ ልጅን ይሰጣት ዘንድ በብዙ እንባ ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነችው።

በዚያችም ሌሊት ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ ተገለጡላትና እነሆ ክብር ይግባውና እግዚአብሔር የተባረከ ልጅን ይስጥሽ ዘንድ ልመናሽን ተቀበለ ስሙንም ጴጥሮስ በዪው አልዋት ከዚህም በኋላ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎናስ እንድትሔድና እንዲጸልይላት አዘዙዋት።

እርሷም ወደ አባ ቴዎናስ ሔዳ ጸለየላት ከዚህም በኋላ ፀንሳ ይህን ቅዱስ ወለደችው ስሙንም ጴጥሮስ ብላ ሰየመችው ዕድሜውም ሰባት ዓመት ሲሆነው ነቢይ ሳሙኤል እንደ ተሰጠ ለሊቀ ጳጳሳት ቴዎናስ ሰጠችው። ለርሱም ተወዳጅ ልጅን ሆነው አስተምሮም አናጉንስጢስነት ሾመው ከዚህም በኋላ ዲቁና ደግሞም ቅስና ሾመው በሊቀ ጵጵስናው ሥራ የቤተ ክርስቲያንም በሆኑ በብዙ መልካም ሥራዎች ሁሉ የሚረዳው ሆነ።

የሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎናስ የሚያርፍበት ጊዜ ሲደርስ በእርሱ ፈንታ አባ ጴጥሮስን ሊቀ ጵጵስና እንዲሾሙት ኤጲስ ቆጶሳቱንና ካህናቱን አዘዛቸው እርሱም በሞተ ጊዜ ይህን አባ ጴጥሮስን ሾሙት እርሱም ለአብያተ ክርስቲያን ካህናትን ሾመ።

እንዲህም ሆነ በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በአንጾኪያ ከተማ አንድ መስፍን ነበረ የሚስቱም ስም ሣራ ይባላል እርሱም ከከሀዲው ንጉሥ ጋር ተስማማ እርሷ ግን በሃይማኖቷ ጸናች በአንድነትም ሳሉ ሁለት ልጆችን ወለደች። ነገር ግን በአንጾኪያ አገር የክርስትና ጥምቀትን ልታስጠምቃቸው አልተቻላትም ስለዚህም ወደ እስክንድርያ ትሔድ ዘንድ ልጆቿን ይዛ በመርከብ ተሳፈረች።

በጉዞ ላይም ሳሉ ጽኑዕ የሆነ ማዕበል ተነሣባቸው እርሷም ልጆቿ የክርስትና ጥምቀትን ሳይጠመቁ እንዳይሞቱ ፈራች ጡቷንም በምላጭ ሠንጥቃ በደሟ ግምባራቸውን በመስቀል ምልክት ቀብታ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቀቻቸው በዚያንም ጊዜ ታላቅ ጸጥታ ሆኖ ከመሥጠም ዳኑ።

ወደ እስክንድርያ አገርም በደረሰች ጊዜ ያጠምቃቸው ዘንድ ልጆቿን ከሀገር ልጆች ጋር ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ አቀረበች ይህም አባት ያጠምቃቸው ዘንድ ወደ ልጆቿ በደረሰ ጊዜ ውኃው እንደ ሰም ሁኖ ረጋ ወደ ሌሎች ሲሔድ ግን ይፈሳል ወደዚች ሴት ልጆች ሲመለስም እንደ ሰም የረጋ ይሆናል እንዲህም ሦስት ጊዜ አደረገ አደነቀም ከእርሷም ስለሆነው ነገር ጠየቃት እርሷም የባሕር ማዕበል እንደተነሣባት ጡቷንም ሠንጥቃ በደሟ የልጆቿን ግምባራቸውን እንደቀባችና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳጠመቀቻቸው ነገረችው። ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስም
2025/01/01 02:50:27
Back to Top
HTML Embed Code: