Telegram Web Link
🌹 #የዚህ_ሳምንት_የዕለቱ_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "#ጳጳሳት_ቀሳውስት_ወዲያቆናት ሊቃነ ካህናት ሥዩማነ ቤተ ክርስቲያን እለ ሎሙ ሕግ ወሎሙ ሥርዓት #ብፁዕ_እስጢፋኖስ_ምስለ_ኵሎሙ_ቅዱሳን ለከ የዓርጉ ስብሐት #እግዚኣ_ለሰንበት አሠርጎካ ለምድር #በሥነ_ጽጌያት_ወሠራዕከ_ሰንበት_ለሰብእ_ዕረፍተ ወብውህ ለከ ትኅድግ ኃጢአተ ረቢ ንብለከ ረቢ ሊቅ ነአምን ብከ። ትርጉም፦ ሕግና ሥርዓት ያላቸው የካህናት አለቆች የቤተ ክርስቲያን ሹማምንት፣ #ዲያቆናት፣_ቀሳውስትና_ጳጳሳት_ቅዱስ_እስጢፋኖስ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ምስጋናን ያሳርጉልሃል፣ #የሰንበት_ጌታ_ምድርን_በአበቦች_ውበት አስጌጥካት፣ #ለሰው_ዕረፍትን_ሰንበትን_ሠራኽ ኃጢአትን ትተውለት ዘንድ መምህር እንልሃለን፣ ሊቅ መምህር ሆይ እናምንብሃለን። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
መስቀል ማለት ምን ማለት ነው ?
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_17_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ጢሞቴዎስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ሌትና ቀን በልመናዬ ሳላቋርጥ ስለማስብህ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹሕ ሕሊና የማመልከውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤
⁴ እንባህን እያሰብሁ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ።
⁵ በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ፤ ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፥ በአንተም ደግሞ እንዳለ ተረድቼአለሁ።
⁶ ስለዚህ ምክንያት፥ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው፥ እጆቼን በመጫኔ በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ።
⁷ እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።
⁸ እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል፤
⁹ ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥
¹⁰-¹¹ አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።
¹² ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፥ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፥ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።
¹³ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር አድርገህ፥ ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል ምሳሌ ያዝ፤
¹⁴ መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
³ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤
⁴ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።
⁵ እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵⁴ ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት።
⁵⁵ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፦
⁵⁶ እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ።
⁵⁷ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፥ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፥
⁵⁸ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ።
⁵⁹ እስጢፋኖስም፦ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።
⁶⁰ ተንበርክኮም፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ፦ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ጥቅምት_17_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇🌹

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
   "ወጽንሐሐኒ ኢትሠምር። መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር መንፈስ የዋህ። ልበ ትሑተ ወየዋሃ ኢይሜንን እግዚአብሔር"። መዝ 50፥16-17 ወይም መዝ 50፥10።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ጥቅምት_17_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ዓይኑንም አንሥቶ መባቸውን በመዝገብ የሚጥሉ ባለ ጠጎችን አየ።
² አንዲትም ድሀ መበለት ሁለት ሳንቲም በዚያ ስትጥል አየና፦
³ እውነት እላችኋለሁ፥ ይህች ድሀ መበለት ከሁሉ ይልቅ አብልጣ ጣለች፤
⁴ እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ እግዚአብሔር መዝገብ ጥለዋልና፤ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አለ።
⁵ አንዳንዶቹም ስለ መቅደስ በመልካም ድንጋይና በተሰጠው ሽልማት እንዳጌጠ ሲነጋገሩ፦ ይህማ የምታዩት ሁሉ፥
⁶ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ የማይቀርበት ዘመን ይመጣል አለ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️  🌹
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ_ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ እስጢፋስ የሢመት በዓል፣ የማኅሌተ ጽጌ አራተኛ ሳምንት (ሰንበት)ና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_18

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት አሥራ ስምንት ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ቴዎፍሎስ ያረፈበት፣ የከበረ #ቅዱስ_ሮማኖስ በሰማዕትነት ያረፈበት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቴዎፍሎስ

ጥቅምት አሥራ ስምንት በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ሦስተኛ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት ቴዎፍሎስ አረፈ። ይህም አባት ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በነገሠ በስድስተኛ ዓመት ተሾመ በወንጌላዊ ማርቆስም ወንበር ሃያ ስምንት ዓመት ኖረ።

በዘመኑ ብዙ መጻሕፍትን የተረጎመ ከእሳቸውም የወንጌላዊ ዮሐንስን ራእይና የሐዋርያ ጳውሎስን መልእክት የተረጎመ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ተነሣ ዳግመኛም ለደሴተ ቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ የሆነ ኤጲፋንዮስ ነበረ።

በዘመኑም ሰባቱ ደቂቅ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት ከአንቀላፉ በኋላ ተነሡ። ይህም አባት የሐዋርያዊ ሊቀ ጳጳሳት አባት አትናቴዎስ ደቀ መዝሙር ነው የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍትና ሥርዓቱን ሁሉ እየተማረ በእርሱ ዘንድ አደገ። ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጢሞቴዎስም በአረፈ ጊዜ ይህ አባት በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ አዋቂና አስተዋይም ስለሆነ ስለ ፍቅር ስለ ርኅራኄ ከንሰሐ በፊት ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ከመቀበል መጠበቅ ስለ ሚገባ ስለ ሙታን መነሣትና ለኃጥአን ስለ ተዘጋጀ ስለዘላለማዊ ሥቃይ ሌሎችም ጠቃሚ የሆኑ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ።

ቅዱስ ቄርሎስም ለዚህ አባት ቴዎፍሎስ የእኅቱ ልጅ ነው እርሱም በበጎ አስተዳደግ አሳደገው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት አስተማረው። ከዚያም በኋላ ወደ አባ ሰራብዮን ላከው አባ ሰራብዮንም መንፈሳዊ ተግባርን ሁሉ አስተማረው።

በአትናቴዎስም ዘመን አስቀድሞ እንዲህ ሆነ በጎ ዘመን ባገኝ ይህን ኮረብታ ባስጠረግሁት ነበር። ለከበሩ ለመጥምቁ ዮሐንስና ለነቢይ ኤልሳዕም ቤተ ክርስቲያን በሠራሁም ነበር ሲል ይህ አባት ቴዎፍሎስ አባ አትናቴዎስን ይሰማው ነበር። በሹመቱ ወራትም ይህን ነገር አስታውሶ የሚያዝንና ክብር ይግባውና ወደ #ጌታችን የሚጸልይ ሆነ።

በዚያ ወራትም ባሏ ብዙ ገንዘብ ትቶላት የሞተ አንዲት ባለጸጋ ሴት ከሮሜ አገር መጣች ሁለት ልጆቿም ከእርሷ ጋር አሉ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስንም ሲያዝን አየችውና ክቡር አባት ሆይ ምን ያሳዝንሐል አለችው። እርሱም ብዙ ወርቅ በዚህ ኮረብታ ውስጥ እያለ ድኆች ይራባሉና አላት እርሷም አንተ ስለ እኔ ጸልይ እኔም አስጠርገዋለሁ አለችው።

ይህንንም ብላ ያን ኮረብታ አስጠረገችው በውስጡም በደንጊያ ሠሌዳ እየአንዳንዱ የተከደኑ ሦስት ሣጥኖች ተገለጡ። በላያቸው ቴዳ ቴዳ ቴዳ የሚል ተጽፎባቸዋል አባ ቴዎፍሎስም በአየው ጊዜ በ #መንፈስ_ቅዱስ ምሥጢራቸውን አውቆ ቴዳ ማለት የ #ጌታ ስም ነው ይህም ለድኆች ይገባል አለ ሁለተኛውም ቴዳ የንጉሥ ቴዎዶስዮስ ነው ሦስተኛውም ቴዳ ቴዎፍሎስ ማለት ነው። የእኔ ገንዘብ ስለሆነ በዚህም አብያተ ክርስቲያናትን እሠራለሁ አለ። እሊህም ሣጥኖች በመቄዶንያዊው ፊልጶስ ልጅ በንጉሥ እስክንድር ዘመን እንደ ተቀበሩ የዘመን ቊጥር ተገኘ እርሱም ሰባት መቶ ዘመናት ነው።

ከዚህም በኋላ ያን የወርቅ ሣጥን ለንጉሥ ቴዎዶስዮስ ላከለት ስለዚያም የወርቅ መዝገብ አስረድቶ ቦታውን መጥቶ እንዲያይ አሳሰበው እርሱም በመርከብ ተጭኖ ወደ እስክንድርያ አገር መጥቶ ሁሉንም አየ የዚያንም ወርቅ እኵሌታ መለሰለት አባ ቴዎፍሎስም ብዙዎች አብያተ ክርስቲያንን ሠራ።

አስቀድሞም በቅዱሳን በመጥምቁ ዮሐንስና በነቢይ ኤልሳዕ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ሠራ ሥጋቸውንም ከእስራኤል አገር አፍልሶ አምጥቶ በውስጧ አኖረ እርሷም የታወቀች ናት ዴማስ በሚባል ቦታ ሁለተኛም በእመቤታችን በቅድስት #ድንግል_ማርያም ስም በሀገሩ ምሥራቅ በኩል ሠራ ከዚህም በኋላ በሊቀ መላእክት ሩፋኤል ስም በደሴት ውስጥ ሠራ ሌሎችንም ብዙዎች አብያተ ክርስቲያን አሳነፀ።

ንጉሡም አብያተ ክርስቲያናትን ለመሥራት ያለውን የሊቀ ጳጳሳቱን ፍቅር አይቶ በግብጽ አገር ያሉትን የጣዖታት ቤቶችን ሁሉንም ሰጠው እርሱም ተቀብሎ አፈረሳቸውና በቦታቸው አብያተ ክርስተከያናትንና የእንግዶች ቤቶችን ሠራ ሁለተኛም ምድራቸውን ሁሉ ሰጠው።

ይህም አባት ቴዎፍሎስ የክርስትና ጥምቀትን በሚያጠምቅ ጊዜ የብርሃን በትረ #መስቀል በሚጠመቁት ላይ በ #መስቀል ምልክት ሲያማትብ ያይ ነበር።

ይህ አባት ቴዎፍሎስና ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ልጆች በሆኑበት ጊዜ ሁለቱም በአንዲት ሌሊት አንዲት የሆነች ራእይን እነርሱ እንጨቶችን እንደሚለቅሙ አዩ። ከእነርሱም አንዱ ንጉሥ እንደሚሆን ሁለተኛውም ሊቀ ጳጳሳት እንደሚሆን ያቺን ራእይ ተረጎሟት እንዲሁም ሆነ።

ይህም አባት ቴዎፍሎስ ሊቀ ጵጵስና በተሾመባት በመጀመሪያዪቱ ዓመት ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ሃይማኖትን እናስተምራለን የሚሉ ሁሉ ሃይማኖታቸውን በመጽሐፍ ጽፈው ወደርሱ እንዲአቀርቡ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም አደረጉ።

ከዚህም በኋላ ንጉሡና ሊቀ ጳጳሳቱ ተነሥተው እነዚያን ጽሑፎች በመሠዊያው ላይ አድርገው ወደ #እግዚአብሔር ጸለዩ #ጌታም_ወልድ በመለኮቱ ከአብ ከ #መንፈስ_ቅዱስ ጋር ትክክል ነው ብሎ ከሚታመን በቀር ከውስጣቸው በቀናች ሃይማኖት የጸና እንደ ሌለ ገለጠላቸው። በዚያንም ጊዜ እሊህን የመና*ፍ*ቃን መጻሕፍትን እንዲአቃጥሏቸው እነዚያንም መና*ፍ*ቃን ከሚገዛው አገር እንዲአሳድዷቸው ንጉሥ አዘዘ።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም መጻሕፍትን ማንበብና መመርመር ያበዛ ነበር ስለዚህም የአውጋርዮስን መጻሕፍት አወገዘ ያወግዙ ዘንድም ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ወደዚህ አባት ወደ ቴዎፍሎስ ወደ ቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ ወደ ኤጲፋንዮስ ወደ ኤዺስቆጶሳት ሁሉ በየሀገሩ ላከ። ከዚህም በኋላ መልካም ጒዞውን በፈጸመ ጊዜ #እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#መነኰስ_ቅዱስ_ሮማኖስ

ዳግመኛም በዚህች ቀን ክርስቲያኖችን በአሳደደ በመኰንን አስቅልጵያኖስ ዘመን የከበረ መነኰስ ሮማኖስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገኖችን መኰንኑ እንዳሳደዳቸው በሰማ ጊዜ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ጋር የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰባቸው ስለ #ክርስቶስ ሃይማኖትም መክሮ አጸናቸው።

አስቅልጵያኖስም ይህን ሰምቶ እንዲአመጡት አዘዘ በፊቱም በቆመ ጊዜ አስቅልጵያኖስ በወገን የከበርክ ሮማኖስ አንተ ነህን አለው ቅዱሱም የወገን ክብር ምን ይጠቅመኛል ክብሬ ግን #ክርስቶስ ነው ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ሰምቶ እንዲሰቅሉትና ጉንጮቹን ይሰነጣጥቁ ዘንድ አዘዘ ጉንጮቹንም ሲሰነጣጥቁት ምንም አልተናገረምና መኰንኑ ትዕግሥቱን አደነቀ።

በዚያንም ጊዜ ሮማኖስ መኰንኑን እንዲህ አለው እነሆ ስንፍናህን እዘልፍ ዘንድ ፈጣሪዬ አፌን ከፈተ እውነት ነገርን ብታውቅ ለ #እግዚአብሔር እንሰግድ ዘንድ ይገባ እንደሆነ ወይም ለአማልክት እንዲነግረን ሕፃን ልጅ እንዲአመጡ እዘዝ መኰንኑም ታናሽ ሕፃንን እንዲአመጡ አዘዘ መኰንኑም ሕፃኑን ስግደት ለማን እንዲገባ ዕውነቱን ንገረን አለው። ሕፃኑም ልብ የሌለህ ደንቆሮ መኰንን በአንዲት ቃል ዓለሙን ሁሉ ለፈጠረ ለሕያው #እግዚአብሔር ስግደትና አምልኮ እንዲገባ አታውቅምን አለው።
መኰንኑም ሕፃኑን ይሰቅሉት ዘንድ አዘዘ የሕፃኑም እናት ልታየው መጣች ሕፃኑም እናቱን ተጠምቻለሁና ውኃ አጠጭኝ አላት። እናቱም ልጄ ሆይ ከዚህ ውኃ የለም ነገር ግን ወደ ሕይወት ውኃ ሒድ አለችው።

በዚያንም ጊዜ የሕፃኑን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ የቅዱስ ሮማኖስንም ምላሱን ከግንዱ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘ። ያን ጊዜ መኰንኑን ይዘልፍ ዘንድ ለአባ ሮማኖስ ረቂቅ አንደበት ተሰጠው ሲዘልፈውም መኰንኑ ሰምቶ ምላሱ እንዳልተቆረጠ ተጠራጠረ። ወታደሩንም ጠርቶ ምላሱን ያልቆረጥክ ለምንድን ነው አለው ወታደሩም የምላሱን ቁራጭ ያመጡ ዘንድ እዘዝ አለው አምጥተውለትም አይቶ መኰንኑም ወደ ወህኒ ቤት አስገብተው በዚያ አንቀው እንዲገድሉት አዘዘ። እንዲህም ምስክርነቱን ፈጽሞ የምስክርነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_18)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_18_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ቲቶ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ኤጲስ ቆጶስ፥ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ፥ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥
⁸ ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ይሁን፤
⁹ ሕይወት በሚገኝበት ትምህርት ደግሞ ሊመክር ተቃዋሚዎቹንም ሊወቅስ ይችል ዘንድ፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና።
¹⁰ የማይታዘዙና ከንቱ የሚናገሩ የሚያታልሉ ይልቁንም ከተገረዙት ወገን የሚሆኑ ብዙ ናቸውና፤
¹¹ እነዚህም ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እያስተማሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ፥ አፋቸውን መዝጋት ይገባል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶-⁷ በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።
⁸-⁹ እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።
¹⁰ ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁹-³⁰ ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
³¹ ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።
³² አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።
³³ ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤
³⁴ እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ።
³⁵ እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፦ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።
³⁶ ይህንም ብሎ ተንበርክኮ ከሁላቸው ጋር ጸለየ።
³⁷ ሁሉም እጅግ አለቀሱ፥ ጳውሎስንም አንገቱን አቅፈው ይስሙት ነበር፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ጥቅምት_18_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇🌹

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወይረውዩ እምጠለ ቤትከ። ወትሠቅዮሙ እምፈለገ ትፍሥሕትከ። እስመ እምኀቤየ ነቅዐ ሕይወት"። መዝ 35፥8-9
"ከቤትህ ጠል ይጠጣሉ፥ ከተድላም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ። የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን"። መዝ 35፥8-9
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ጥቅምት_18_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ ስለዚህ ፈሪሳውያን ሄዱና እንዴት አድርገው በነገር እንዲያጠምዱት ተማከሩ።
¹⁶ ደቀ መዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፥ እርሱም፦ መምህር ሆይ፥ እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፥ ለማንምም አታደላም፥ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤
¹⁷ እንግዲህ ምን ይመስልሃል? ንገረን ለቄሣር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? አሉት።
¹⁸ ኢየሱስም ክፋታቸውን አውቆ፦ እናንተ ግብዞች፥ ስለ ምን ትፈትኑኛላችሁ?
¹⁹ የግብሩን ብር አሳዩኝ አለ። እነርሱም ዲናር አመጡለት።
²⁰ እርሱም፦ ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት? አላቸው።
²¹ የቄሣር ነው አሉት። በዚያን ጊዜ፦ እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው።
²² ይህንም ሰምተው ተደነቁ፥ ትተውትም ሄዱ።

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 🌹
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ባስልዮስ_ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ቴዎፍሎስ እና የቅዱስ ሮማኖስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🌹የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስት ቅዱስ ቴዎፍሎስ የሃማኖትን ነገር ተናገረ፤ ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ሊቃውንት በነቂያ ጉባኤ አደረጉ ሕያው በጎ ጥበብ ኃይል አርአያ የሚሆን የሕያው ቃል አባት #እግዚአብሔር_አብ አንድ ነው ብለው አመኑ። ኤፌ.4÷5

በማያልፍ ጌትነት በማይከፈል መንግሥት ሦስቱ አንድ ናቸው ከሦስቱ ልዩ የለም ከ #ሥላሴ ፍጡር የለም፤ ከ #ሥላሴ ኑሮ ኑሮ የተገኘ የለም፤ ገዢና ተገዢ የለም፤ ቀድሞ ያልነበረ ኃላ የተገኘ የለም።

ወልድ ሳይኖር አብ ከአዝማን በዘመን ፈጽሞ አልነበረም፤ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ በዘመን አልነበረም፤ ሳይለወጡ ሳይለዋወጡ በገጽ በመልክ ፍጹማን በሚሆኑ በሦስት አካላት ጥንት ሳይኖራቸው በዘመን ሁሉ የነበሩ፤ ፍጻሜ ሳይኖራቸው የሚኖሩ ናቸው እንጂ። መዝ.90÷2፣ መዝ.93÷2፣ ሚል.3÷6

#ሃይማኖተ_አበው_ዘቅዱስ_ቴዎፍሎስ

🌹 "#ሰላም_ለቴዎፍሎስ_ቀዋሚ_ለቤተ_ክርስቲያን ዘሰመየቶ ማርያም ፈረሳዊ ዘይጸብእ በእንተ ክርስቲያን"። ትርጉም፦ ስለክርስቲያን የሚዋጋ (አርበኛ) ጋላቢ (ፈረሰኛ) ብላ ማርያም የሰየመችው #ለቤተ_ክርስቲያን_የሚከራከር_ለኾነ_ለአባ_ቴዎፍሎስ_ሰላምታ_ይገባል
#ጥቅምት_19

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት አስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ደግ ንጉሥ #ቅዱስ_ይምርሃነ_ክርስቶስስ እረፍቱ ነው፣ #ቅዱስ_በርቶሎሜዎስና_ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ፣ ስለ #ጳውሎስ_ሳምሳጢ በአንጾኪያ አገር የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ስብሰባ ተደረገ፣ የጸይለም አገር የከበረ አባት #ቅዱስ_ዮሐንስ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ይምርሃነ_ክርስቶስ

ጥቅምት አስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ደግ ንጉሥ፣ ፃድቅ ካህን፣ቤተ መቅደሱን በባህር ላይ ያነፀ መሀንዲስ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስስ እረፍቱ ነው።

ልክ እንደ አቡነ ተክለሃይማኖትና እንደነ አቡነ ዜና ማርቆስ እርሱም ሲወለድ ወደ ምሥራቅ ዞሮ አምላኩን ያመሰገነ ሲሆን ቤቱም በብርሃን ተሞልቶ ታይቶ አዋላጆቹን ሁሉ አስገርሞ ነበር፡፡ ገና በእናቱ ማህፀን ሆኖ አጎቱ ጠንጠውድም በንግሥና ላይ ሳለ "ከአንተ በኋላ የሚነግሠው ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል የወንድምህ ልጅ ነው" የሚል ንግርት ይሰማ ነበርና ‹‹ይምርሃነ ክርስቶስ›› መወለዱን ሲያውቅ ‹‹የወንድሜን ልጅ ዐየው ዘንድ አምጡልኝ›› ብሎ ላከ፡፡ ባየውም ጊዜ ደም ግባቱ እጅግ ያምር ስለነበር ‹‹ይህስ መንግሥቴን ይውረስ፣ በእውነት ልጄ ነው›› ብሎ ባረከው፡፡

ከእርሱ ጋር ስምንት ቀን ተቀምጦ በወለዳቸው ልጆቹ መካከል ሆኖ ሲጫወት በተመለከተው ጊዜ ግን በልቡ ሰይጣን አደረበትና በቅናት ሆኖ ‹‹እርሱ ነግሦ ልጆቼ ወታደሮቹ ሊሆኑ ነውን›› በማለት ይገድለው ዘንድ አሰበ፡፡ ሆኖም አማካሪዎቹ ‹‹ለጊዜው ምንም ስለማይረዳ ተወው ለወደፊቱም የንግሥና ምሥጢር እንዳያውቅ ወደ እናቱ ዘንድ መልሰውና በዚያ ከብት ሲያግድ ይደግ››ስላሉት ወደ እናቱ ላከው፡፡ እርሷ ግን በጥበብና በብልሃት አስተዋይ አድርጋ አሳደገችው። ይህንንም ሲሰማ ሊገድለው አሽከሮቹን ላከ፡፡ እናቱም የተላኩትን አሽከሮች ተቀብላ ምግብ አቅርባ አስተናገደቻቸው። ነገር ግን #እግዚአብሔር የንጉሡን ተንኮል ስለተገለጠላት ልጇን ደበቀችው፡፡ በስውርም ወስዳ ከጳጳሱ ዘንድ ዲቁና እንዲቀበል ካደረገችው በኋላ ‹‹ልጄ ሆይ! አጎትህ ሊገድልህ ይፈልግሃልና በፊቴ ከሚገድልህ ርቀህ ብትሄድ ይሻላል፣ ያዕቆብን ከኤሳው የጠበቀ አንተንም ይጠብቅህ›› ብላ ሸኘችው፡፡ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስም ወደ በጌምድር ተሰደደ፡፡ (ገድሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ በዚያም የሌዋውያን ወገን የምትሆን ቅድስት ሕዝባን አግብቶ ቅስናም ተቀብሏል ይላል።) ያም ሆነ ይህ ቅዱሱ በስደቱ ወቅት ሥጋዊውንና መንፈሳዊውን ጥበብ ተምሮ እንዳጠናቀቀና በኋላም ወንጌልን እየሰበከ፣ በተአምራቱም ሕመምተኞችን እየፈወሰ #እግዚአብሔርንም እያገለገለ እንደኖረ ታሪኩ ያወሳል፡፡

በዚህ አይነት ሁኔታ ዓመታት ሲያልፉ #እግዚአብሔር አምላክ ንጉሥ አጎቱ ጠንጠውድም መሞቱንና በዙፋኑም እርሱ እንደሚነግሥ ነገረውና በመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ወደ ሀገሩ ተመልሶ መጥቶ በላስታ ወረዳ ሳይ (ዛሬ ሸጐላ ማርያም) ከምትባል ቦታ ላይ ወንጌልን እያስተማረ፣ ድውያንን እየፈወሰ እንዲቀመጥ አደረገው፡፡ ትምህርቱንና ተአምራቱን ያዩት የአካባቢው ሰዎችም ‹‹ነፃነትና ፍቅር የሚገኝብህ የ #እግዚአብሔር ሰው ሆይ! እኛ ሰላማዊ ብርሃናዊ ብለን ስም አወጣንልህ፣ ያንተ ግን ስምህ ማን ይባላል ንገረን›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹ስሜ ይምርሃነ ክርስቶስ ነው›› አላቸው ይህኔ ሕዝቡ ሁሉ በሹክሹክታ ‹‹ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል ሲነግሥ ሃይማኖት ይቀናል፣ ፍርድ ይስተካከላል›› እያሉ አባቶቻችን ሲናገሩ ሰምተናል አሉ፡፡

ከጠንጠውድምም ሞት በኋላ ማንም እንዳልነገሠ ሲያረጋግጡ የማን ልጅ እንደሆነ እንዲነግራቸው በ #እግዚአብሔር ስም ለመኑትና የጠንጠውድም ታናሽና የዣን ስዩም ታላቅ ወንድም የሆነው የግርማ ስዩም ልጅ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ እነርሱም ‹‹የተነገረው ትንቢት ደርሷልና ሳንዘገይ እናንግሠው›› ብለው ሥርዓተ መንግሥቱን ፈጽመው በዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡

ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ በትረ መንግሥቱን ከያዘ በኋላ ሁሉም ሰው በተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ ውስጥ እንደ ወንጌሉ ቃል እንዲኖር በግዛቱ ሁሉ አወጀ፡፡ #እግዚአብሔርም የሚመሰገንበትን ቤት መሥራት አሰበና የተፈቀደለትን ቦታ እንኪያገኝ ድረስ ዛዚያ በምትባል ልዩ በሆነች ስፍራ ድንኳን ተክሎ እንደ ሙሴ አምላኩን ማገልገል ጀመረ፡፡ በዚህም ቦታ ሕዝቡን ከሰማይ በወረደለት #መስቀል እየባረከና እርሱ ለቅዳሴ በሚገባበት ጊዜ ከአምላኩ የሚሰጠውን ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ እያቆረበ ለ22 ዓመት በድንኳኗ ውስጥ ኖረ፡፡ ከነዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላም #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በክብር ተገለጠለትና እንዲህ አለው፡- ‹‹ወዳጄ ይምርሃነ ክርስቶስ ይህን ሥፍራ (ዛዚያን) ልቀቅ፣ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ቦታ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ አይወርድልህም፡፡ ወደማሳይህ ቦታ ተነሥተህ ሂድ፣ በዚያም እስከ ዕረፍትህ ቀን ድረስ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ ይወርድልሀል፡፡ ይህን ዓለም ለማሳለፍ እስከምመጣበት እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ የእኔ ጌትነት የአንተም የቅድስና ሕይወት የሚነገርበት፣ የሥጋህ የዕረፍት ቦታ የሚሆንበት፣ ለምትሠራው መቅደስ ክዳን የሚሆን ሣር የማትፈልግበት ሰፊ ዋሻ እሰጥሀለው ፣ በዚያ ቤተ መቅደሴን ሥራ፣ እኔ በምትሠራው ቤተ መቅደስ ከአንተ ጋር ለዘለዓለም ቃልኪዳኔን አቆማለሁ፡፡ በምታንጸው ቤተ መቅደስ ውስጥ ‹አቤቱ የይምርሃነ ክርስቶስ አምላክ ሆይ! ስለወዳጅህ ስለ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ብለህ ይቅር በለኝ› እያለ ‹አባታችን ሆይ!› የሚለውን ጸሎት የሚጸልይ ዕለቱን እንደተጠመቀ አደርገዋለሁ፡፡ ነገ ማለዳ ተነሥተህ ወግረ ስሂን ወደሚባለው የዕረፍትህ ቦታ ወደሚሆነው ዋሻ ሕዝብህን አስከትለህ ሂድ፤ በዚያም ቤተ መቅደሴን አንጽ›› ብሎ ቃልኪዳን ሰጠው።

ይምርሃነ ክርሰቶስም ሕዝቡን ይዞ ተነሳና አሁን ከቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሶች 42 ኪ,ሜ ርቀት ላይ ወደሚገኘውና ጥቁር አለታማ ተራራ ሥር ወዳለው የውግረ ስሂን ዋሻ አመራ። ሲደርስም ቦታው የሰዎች ይዞታ ሆኖ ስላገኘው እኔ ንጉሥ ነኝ ብሎ እነርሱን በግፍ ሳያስለቅቅ ካሳ ከፍሎ ስፍራውን ተረከባቸው። ውስጡ ግን ውሀ የቆመበት ባህርና ርኩሳት መናፍስት የሞሉት ስለነበር መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መናፍስቱን አባሮ በባሕሩ ላይ ቤተ መቅደሱን እንዴት እንደሚያንጽ ገለጠለት። እርሱም በተነገረው መሠረት ለግንባታው የሚያስፈልጉ እቃዎችን ከኢየሩሳሌም አስመጥቶ ማነጽ ጀመረ። የውሀውን ክፍል እንጨት ረብርቦ አፈር እየበተነ ደለደለው። ሰዎች በባህር ላይ መሠራቱን እንዳይጠራጠሩም አነስተኞ መስኮትነገር አበጀለት። (በዚህችም አሁን ድረስ በክንድ ርቀት ያህል ከሥር ያለው ውሀ ይነካል።) ከበላዩም ስስ ሆነው የተፈለጡ ድንጋዮችን በኖራ እያቦካ በማያያዝ በእኩል መጠን እየገነባ በመሀከላቸው እንደ መቀነት የተጠረቡ እንጨቶችን በማስገባት አሳምሮ አነፀው። ውስጡንም በሦስት ቤተ መቅደሶች ከፈለው በየመስኮትና በየበሮቹም ላይ እንደ ዐይነ እርግብ ሆነው የተፈለፈሉ ሐረጎችን አደረገበት ጣሪያውንም በሰባቱ ሰማያት ምሳሌ ምስጢር ባላቸው የተለያዩ ቅርፆች አስዋበው። ይህን አድርጎ ሥራውን ከጨረሰ በኋላም የቅዱስ ገብርኤልን የእመቤታችንንና የቅዱስ ቂርቆስን ታቦታት አስገባበት። በድጋሚም ቤተ መንግሥቱን በዛው ዋሻ ውስጥ አነጸና በአስተዳደሩ ደሀ ሳይበድል ፍርድ ሳያጓድል ሕዝቡን በክህነቱም ንፁህ ሆኖ #እግዚአብሔርን እያገለገለ ኖረ። በስተመጨረሻም ፍጥረት ሆኖ ከመሞት ሰው ሆኖ በመቃብር ከመዋል የሚቀር አይኖርምና
ንጉሣችንና አባታችን ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስም የእረፍት ዘመኑ ሲደርስ #እግዚአብሔር_አምላክ ቃል ኪዳኑን ለዘላለም እንደሚያፀናለት ነግሮት በዚህች በተባረከች #በጥቅምት_19 ቀን በክብር አሳረፈው።

መቃብሩንም አስቀድሞ እነደነገረው በዛው በተቀደሰ ዋሻ ውስጥ አደረገለት። እናም ዛሬ ድረስ ቦታው በክብር ተጠብቆ ይኖራል። ምእመናንም ቃል ኪዳኑን በማሰብ "ማረኝ ይምርሐ" እያሉ መቃብሩን ይዞራሉ። ያንን ከሰማይ የወረደለትን #መስቀልም በቤተመቅደሱ የሚያገለግሉት ካህናት አባቶች ቦታውን ለመሳለም የሚመጣውን ሕዝበ ክርስቲያን በበዓል ቀን ይባርኩበታል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባት ይምርሐነ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_በርቶሎሜዎስና_ሚስቱ

ዳግመኛም በዚህች ቀን በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ቅዱስ በርቶሎሜዎስና ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ።

እሊህ ቅዱሳንም የግብጽ ምዕራብ ከሆነ ፍዩም ከሚባል አገር ናቸው ክርስቲያኖችም እንደሆኑ በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሏቸው መኰንኑም ልኮ አስቀረባቸውና ስለ ሃይማኖት ጠየቃቸው እነርሱም ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በፊቱ ታመኑ።

መኰንኑም ጥልቅ ጒድጓድ እንዲቆፍሩላቸው በዚያም እንዲጨምሩአቸውና በሕይወታቸው እንዲደፍኑባቸው አዘዘ። መኰንኑም እንዳዘዘ አደረጉባቸው በዚህም ምስክርነታቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታቱ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#የጳውሎስ_ሳምሳጢን_ውግዘት

በዚችም ቀን ስለ ጳውሎስ ሳምሳጢ በአንጾኪያ አገር የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ስብሰባ ተደረገ። ይህ ጳውሎስም ከአንጾኪያ አገሮች በአንዲቱ አገር ኤጲስቆጶስነት በተሾመ ጊዜ ክፉ ዘርን ሰይጣን በልቡ ውስጥ ዘራበት አካላዊ ቃልን አካል እንደሌለ የ #ክርስቶስም ጥንት መገኛው ከ #ማርያም እንደሆነ እርሱም አለምን ያድንበት ዘንድ #እግዚአብሔር የፈጠረው እንደሆነ ከመለኮትም ጋር ያልተዋሐደ በላዩ ወርዶ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ አደረበት እንጂ ብሎ የሚያምን ሆነ በ #ወልድም ቢሆን በ #መንፈስ_ቅዱስም ቢሆን የሚያምን አልሆነም።

ስለዚህም ኤጲስቆጶሳት አንድነት ተሰበሰቡ የእስክንድርያ አባ ዲዮናስ የሮሜ አባ ዲዮናስዮስ እሊህ ሊቃነ ጳጳሳት ስለ እርጅናቸው ከዚያ ደርሰው ከእርሳቸው ጋር ሊሰበሰቡ አልቻሉም ነገር ግን መልእክትን ጻፉ።

የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስም እንዲህ የሚል መልእክትን ጻፈ። የ #እግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ #ክርስቶስ በመለኮቱም ከእርሱ ጋር ትክክል የሆነ እርሱም ከሦስቱ አካላት አንዱ #ወልድ ስለእኛ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል #ማርያም ያለ ዘር ስጋንና ነፍስን ነሥቶ ፍጹም ሰው የሆነ በመለኮቱ ከ #አብ#መንፈስ_ቅዱስ ጋር ትክክል ሲሆን እንደእኛ ፊጹም ሰው ሁኗል ከተዋሕዶውም በኋላ ያለ መለያየትና ያለ መቀላቀል ሁለቱ ባሕርያት አንድ ሁነዋል ከብሉይና ከሐዲስ መጻሕፍት ምስክሮችን ጠቅሶ እያስረዳ ጽፎ ይቺንም መልእክት ከሁለት ምሁራን ቀሳውስት ጋር ላካት።

በዚያንም ጊዜ አሥራ ሦስቱ ኤጲስቆጶሳትና እሊህ ሁለቱ ቀሳውስት ጉባኤ አድርገው ይህን ጳውሊ ሳምሳጢን አቅርበው የአባ ዲዮናስን መልእክት በፊቱ አነበቡ። ዳግመኛም #ክርስቶስ#እግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ የጌትነቱ ነጸብራቅ ነው የሚለውን የሐዋርያ ጳውሎስን ቃል በመጥቀስ እርሱ ከ #አብ#መንፈስ_ቅዱስ ጋር በትክክልነት እንደሚኖር አስረዱት እርሱ ግን ቃላቸውን አልተቀበለም።

ከዚህም በኋላ በእርሱ ትምህርት የሚያምኑትን ሁሉ አው*ግዘው ከምእመናን ለይተው አሳደዱት። ለምእመናንም ሥርዓትን ሠሩ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ከስሕተት ይጠብቀን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘጸይለም

በዚችም ቀን የጸይለም አገር የከበረ አባት ዮሐንስ አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ከሀገሩ ታላላቆች ወገን ናቸው የአባቱም ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሣራ ነው እነርሱም ልጆች ስለ ሌሏቸው ብዙ ዘመን ወደ #እግዚአብሔር እየለመኑ ኖሩ።

በአንዲትም ዕለት ሁለት መነኰሳት ወደ እነርሱ እንግድነት መጡ እነርሱም በክብር ተቀብለው አሳደሩአቸው። እሊህ መነኰሳትም አብርሃምን ልጅ የለህምን አሉት እርሱም እንባውን እየአፈሰሰ አባቶቼ ልጅ የለኝም አሁንማ እኔ አረጀሁ የሚስቴም የልጅነቷ ወራት አለፈ ብሎ መለሰላቸው። እሊህ መነኰሳትም ስለ እርሳቸው ጸለዩላቸው ባርከዋቸውም ጎዳናቸውን ተጓዙ።

ከጥቂትም ቀን በኋላ ቅድስትሳራ ፀነሰች ደስ የሚያሰኝም ልጅን ወለደች ስሙንም ዮሐንስ ብለው ሰየሙት በእርሱም ደስ አላቸው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት እየአስተማሩ አሳደጉት።

ዐሥራ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ መምህሩ ቤት መነኰሳት መጡ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር እንዲወስዱት ለመናቸው እነርሱም አባትህን እንፈራለንና እኛ አንወስድህም አሉት። መነኰሳቱም ወደቦታቸው እየሔዱ ሳሉ ወደ መረጠው ጎዳና ይመራው ዘንድ ዮሐንስ ተነሥቶ ወደ #እግዚአብሔር ጸለየ ከመምህሩም ቤት ወጥቶ ሊደርስባቸው ወዶ መነኰሳቱን በኋላቸው ተከተላቸው ወደ ታላቅ ወንዝም ደረሰ ብቻውንም መሻገር ፈርቶ ቆመ ከዚያም ሳለ ዓረቦች ከግመሎቻቸው ጋር መጡ ያሻገሩትም ዘንድ ለመናቸው እነርሱም ከእርሳቸው ጋር አሻገሩት አንወስድህም ወደአሉት መነኰሳት ወደ ገዳማቸው በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ደረሰ።

ከእርሳቸውም አንዱ አባ ስምዖን የሚባለው ዮሐንስን ወስዶ ደቀ መዝሙሩ አድርጎ ከሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር አኖረው።

አባ ስምዖን የሚሞትበት ጊዜ እንደቀረበ በአወቀ ጊዜ ልጆቹን ጠርቶ ከሞትኩ በኋላ በእናንተ ላይ የሚሆነውን #እግዚአብሔር ያሳየኝን እነግራችሁ ዘንድ ልጆቼ ኑ አላቸውና ከእናንተ አንዱን ጅብ ነጥቆ ይወስደዋል። ሁለተኛው ወደ ዓለም ተመልሶ ይባክናል። የሦስተኛው ግን ዜናው በዓለሙ ሁሉ ይሰማል አላቸው።

ከዚህም በኋላ አረጋዊው ስምዖን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ተመልክቶ ልጄ ሆይ በክርስቶስ ፍቅር ጽና ለብዙዎች አባት ልትሆን እርሱ መርጦሃልና አለው። አባ ስምዖንም ከአረፈ በኋላ በሦስተኛው ቀን አንዱ ረድዕ ወደ ዓለም ተመልሶ ሚስት አገባ ሁለተኛው ወዴት እንደ ደረሰ አልታወቀም። አባ ዮሐንስም ብቻውን ቀረ ፈጽሞ አዘነ በልቡ እንዲህ አለ የጓደኞቼን ወሬ እጠይቅ ዘንድ ከገዳም ወጥቼ ልውረድ ይህንንም ብሎ ከገዳሙ ወጥቶ ሲወርድ የጸይለም ጦረኞች ተቀበሉት ደም ግባታቸው ከሚአምር ከሁለት ሴቶች ጋር አሥረው ወሰዱት በጒዞም ላይ እያሉ ለእንስሶቻቸውና ለራሳቸው የሚጠጡት ውኃ አጡ። አባ ዮሐንስም ከዚህ በረሀ ውስጥ ፈጣሪዬ ውኃን ቢአወጣላችሁ ትለቁኛላችሁን አላቸው አዎን አሉት። በዚያንም ጊዜ አባ ዮሐንስ በስመ #አብ #ወወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ብሎ በምድር ላይ አማተበ ውኃም ፈልቆላቸው ጠጥተው ረኩ።
የከበረ ዮሐንስም ቃል ኪዳን እንደ ገባችሁልኝ አሰናብቱኝ አላቸው እነርሱም እንዳንተ ያለ አናገኝምና ከቶ አንለቅህም አሉት። ይህንንም ብለው ወደ አገራቸው ወደ ጸይለም አደረሱት።

በዚያንም ወራት በጸይለም አገር ታላቅ መቅሠፍት ወረደ የአበ ዮሐንስም ጌታው ከቤተሰቦቹ ሁሉና ከልጆቹ ጋር ሞተ ሚስቱም ከአንዲት ልጅዋ ጋር ብቻዋን ቀረች። የጌታውም ሚስት ቅዱስ ዮሐንስን መሠርይ እንደ ሆነ አሰበች በማደሪያውም ውስጥ እያለ ሊአቃጥሉት እሳት ለቀቁበት #እግዚአብሔርም ከእሳት ውስጥ በደኅና አወጣው የጸይለም ሰዎችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ሴቶችም ወንዶችም በ #ጌታችን አምነው በእጆቹ ተጠመቁ።

ከዚያም ተነሥቶ ወደ ሌላ አገር ሔደ። የአገር ሰዎችም ዛፎችን ሲያመልኩ አግኝቷቸው እርሱም ከክህደታቸው እንዲመለሱ አስተማራቸው ባልሰሙትም ጊዜ ምሳር ይዞ በሌሊት ወደ ዛፎቹ መካከል ገብቶ ክብር ይግባውና ወደ #እግዚአብሔር ጸለየ ምሳሩንም አንሥቶ በ #አብ#ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም እቆርጣችኋለሁ አለ። ወዲያውኑ በአንዲት ምት ዐሥር ሽህ ዛፎች ወደቁ የሀገር ሰዎችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አመኑ ሁሉም ከሴቶችና ከልጆች ጋር ተጠመቁ።

ከዚያም ዳግመኛ ወደ ሌላ አገር ሔደ ሰዎችንም እሳትን ሲያመልኩ አገኛቸው እርሱም ይህን ደንቊርናቸውን ይተዉ ዘንድ አስተማራቸው ገሠጻቸውም እነርሱም በእርሱ ላይ ተቆጥተው ከእሳት ጨመሩት። እርሱም በደኅና ወጣ ሦስት ጊዜም ጨምረውት በደኅና ወጣ ውኃቸውንም ደም አደረገባቸው የሚጠጡትም አጥተው በተጨነቁ ጊዜ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ ሁሉም አመኑ። አራት መቶ ሽህ ሰዎችም በእጁ ተጠመቁ ቤተክርስቲያንም ሠራላቸው አስተምሮም በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው ቁጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራትንም አደረገ #እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም በፍቅር አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_19)
#ጥቅምት_፲፱ (19)

እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ኤርትራ_አገር የሚገኘውን በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ እጅግ አስደናቂውን #ፃዕዳ_ዓምባ_ቅድስት_ሥላሴ_ገዳምን ለመሠረቱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል ለዕረፍታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

አቡነ ሠይፈ ሚካኤል ከአባታቸው ከዓምደ ሚካኤልና ከእናታቸው ከኅሪተ ማርያም ተወለዱ፡፡ ወላጆቻቸው #እግዚአብሔርን የሚፈሩና በጾም ጸሎት የተወሰኑ የዋኆች ስለነበሩ በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩተው አሳድገዋቸዋል፡፡ አባታቸው ቃለ #እግዚአብሔር እንዲማሩላቸው ልጃቸውን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ወስደው ለመምህር ሰጧዋቸው፡፡ መምህሩም በደስታ ተቀብለው ቅዱሳት መጻሕፍትንና ያሬዳዊ ዜማን አስተማሯቸው፡፡

ከዚህም በኋላ አቡነ ሠይፈ ሚካኤል "እኔን ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ #መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ" የሚለውን #ጌታችንን ቃል ለመፈጸም ዓለምን ከነምኞቷ ንቀው ትተው #መስቀሉን ተሸክመው #ጌታችን ተከተሉት፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ወደ ዋሻዎችና ገዳማት እየሄዱ በአድያቦ ቤተ ቂርቆስ የሚባል ገዳም ደርሰው ከአቡነ ኖላዊነኄር ግብረ ምንኵስና እየተማሩ በገዳሙ ውስጥ የነበሩ መነኰሳት እስከሚደነቁ ድረስ በጽኑ ትጋትና በብዙ ትሩፋት በተጋድሎ አገልግሎታቸውን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ከጽኑ ተጋድሏቸው የተነሣ ሰውነታቸው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፡፡ በዚህም ምክንያት አቡነ ዕንቆ ብርሃን ልብሰ ምንኵስናና አስኬማ መላእክት አለበሷቸው፡፡ እንዲህ ባለ ጽኑ ገድል በኣድያቦ ከመንፈስ አባታቸው ከአባ ዕንቆ ብርሃን ብዙ ዓመታትን ቆይተው በኋላ ወደ ዋልድባ ሄዱ፡፡ ዋልድባ ከገቡም በኋላ እዛ ከነበሩ ቅዱሳን ተባርከው ጽኑ ተጋድሏቸውን ቀጠሉ፡፡

ከዚያም በዋልድባ ቅዱሳን ፈቃድ ወደ ወገሪቆ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ሄደው አበምኔትና መምህር ሆነው አገለገሉ፡፡ አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በተሰጣቸው ጸጋ ወንጌልን እያስተማሩና ሕሙማን እየፈወሱ እስከ ጋሽ ባርካ ደብረ ሳላ የሚባል ቦታ ዞሩ፡፡ ይሄን አገልግሎታቸው ከፈጸሙ በኋላ የ #እግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል እየመራ ማረፍያ ቤታቸው ወደሆነችው ፃዕዳ እምባ ሥላሴ ገዳም በደብረ ከባቦ አደረሳቸው፡፡ በዚያም በጾምና በጸሎት ተጠምደው #እግዚአብሔርን አገለገሉ፡፡ሲጸልዩም እስከ ሰማይ ድረስ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ ይታያቸው ነበር፡፡

አባታችን በጸሎት ላይ ሳሉ አጋንንት በእባብና በንብ እየተመሰሉ ይፈታተኗቸው ነበር ነገር ግን አባታችን በጾምና በጸሎት ድል ይነሷቸው ነበር፡፡ በደብረ ከባቦ ቤተ ክርስትያን አንጸው ማኅበር አቋቁመው ለ9 ዓመት ከ6 ወር አገልግሎታቸውን እየፈጸሙና መከራ እየተቀበሉ ከቆዩ በኋላ አንድ ቀን በሰርክ ጸሎት እየጸለዩ ሳለ መልአክ መጥቶ "…ወደ ገዳሙ አስገባሃለሁና ተከተለኝ" አላቸው፡፡ እሳቸውም ከኋላው እየተከተሉ መልአኩ ወደ ዛሬይቱ ወንዶች ብቻ ወደሚገቡባት ገዳም አስገባቸው፡፡ ያቺን ለማየትም ጭምር የምታስፈራዋን መንገድ አባታችን "ጸናፌ ፅልመት"ብለው ሰየሟት፡፡ ከገቡም በኋላ በገዳሙ ውስጥ ቤተ ክርቲያን አንጸው ቤተ ማኅበር አቋቋሙ።

አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በተሰጣቸው ጸጋ ርኲሳን መናፍስትን ከሕሙማን ያወጡ ስለነበር እነዚያ አጋንንትም "እዚህ እንድትኖር አንፈቅድልህም" እያሉ በገሃድ ለሞት እስከሚደርሱ ድረስ ዐይናቸውን አፈሰሱባቸው ሆኖም ግን መልአከ #እግዚአብሔር ዳስሶ ዐይናቸውን መልሶ አበራላቸው፡፡ እንዲሁም አጋንንቶቹ በማደርያ ቤታቸው እሳት እያቀጣጠሉ በላያቸውም ትላልቅ ድንጋዮችን እየወረወሩ ከበፊቱ በእጅጉ ይፈታተኗቸው ነበር፡፡ እነዚያ የተወረወሩባቸው ድንጋዮች ግን አቡነ ሰይፈ ሚካኤል ይጸሉዩበት በነበረ ቦታ በደቡብ አቅጣጫ ተተክለው ቀርተዋል፡፡ ድንጋዮቹ እስከ አሁን ድረስ አሉ፡፡

አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በአገልግሎታቸው ለሚያምኑ እያጽናኑና እያበረቱ፣ ለማያምኑ ደግሞ አሳምነው እያጠመቁ እስከ ማዕርገ ክህነት አድርሰው ቤተ ክርስትያን ይሠሩላቸው ነበር፡፡ በስተመጨረሻ ቅዱስ አባታችን በብዙ ተጋድሎ ሐዋርያዊ ተልዕኮአቸውንና አገልግሎታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከ #እግዚአብሔር የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለው ጥቅምት 19 ቀን 1722 ዓ.ም በ96 ዓመታቸው ራሳቸው በመሠረቱም በገዳም ፃዕዳ ዓምባ ቅድስ ሥላሴ ዐርፈዋል፡፡

የአባታችን የአቡነ ሰይፈ ሚካኤልን መንገድ የተከተሉ የዚህ ገዳም መነኰሳትም በጾምና በጸሎት ተወስነው #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ "ሑሩ ወመሐሩ" (ማቴ 28፡19) ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ሐዋርያዊ ተልኮአቸውን እየፈጸሙ ብዙ አብያተ ክርስቲያናን ከከረን እስከ ኦምሓጃር ከዛ አልፎም እስከ ከሰላ ሱዳን አንጸዋል፡፡ በፃዕዳ እምባ ሥላሴ ገዳም ሐምሌ 7 ቀን የ #ሥሉስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል እና የአቡነ ሰይፈ ሚካኤል በዓለ ዕረፍታቸው ጥቅምት 19 ቀን በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በእነዚህ ክብረ በዓላት ላይ በርካታ ምእመናን ከተለያዩ ቦታዎች በመምጣት ከበረከቱ ይሳተፋሉ፡፡ ከአባታችን የአቡነ ሰይፈ ሚካኤል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።

#ጻድቁ_አቡነ_ሠይፈ_ሚካኤል_ስለመሠረቱት_ፃዕዳ_ዓምባ_ቅድስት_ሥላሴ_ገዳም

#አቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል፦ እኚህ ጻድቅ በ1669 ዓ.ም የገደሙት ይህ እጅግ ድንቅ የሆነ ገዳም ፃዕዳ ዓምባ #ቅድስት_ሥላሴ ከኤርትራ በዓንሰባ ዞን ከከረን 25 ኪ.ሜ እርቆ በደቡባዊ ምዕራብ ከባሕር ጠለል በላይ 2500 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ ወደዚህ ድንቅ ገዳም የሚያደርሰው መንገድ ዳገትና ቁልቁለት የበዛበት አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሣ ብርቱ ትዕግሥትና መንፈሳዊ ጽናት ይጠይቃል፡፡ ገዳሙ ለመድረስ ከከረን ከተማ በደቡባዊ ምዕራብ በኩል ወንዞችንና ጋራ ሸንተረሮችን ማቋረጥ ግድ ነው፡፡ ከዚያም "ድንጃ ወርቅ" በተባለ ከገዳሙ እግር ሥር በሚገኘው ረጅሞ ተራራ ከተደረሰ በኋላ ከድንጃ ወርቅ የአንድ ሰዓት ተኩል ዝግዛግ የእግር ጉዞ ያስኬዳል፡፡ ከዚያም "ማዕዶዋይ" ከተተባለው ቦታ ይደረሳል፡፡ ትርጓሜውም በርቀት የሚታይ ማለት ነው፡፡ ከማዕዶዋይ ወደ ገዳሙ ውስጥ ለመግባት ከእግር መረገጫ የማያልፍ ስፋት የሌላት በቀኝና በግራ የምታስፈራ በጭንቅ የሚሻገርዋት "ጸናፌ ጽልመት" ተብላ የምትጠራዋን አስጨናቂ ገደል ማለፍ ግድ ይላል፡፡ ይህቺን ለመሻገርም ሆነ ለማለፍ አስቸጋሪ የሆነችን መንገድ ለብዙ ጊዜ የተመላለሱባት ምእመናን ግን ከባድ እቃ በሸክም ይዘውም ቢሆን ያለ ምንም ፍርሃት ይሻገሩባታል፡፡ በጭንቅ የሚሻገርዋትን ይህችን አስጨናቂ ገደል ከታለፈ በኋላ ቀጥሎ "ደገ ሰላም" ና "መንገደ ሰማይ" የሚባል ወደ ገዳሙ የሚያስገባ ዝግዛግ መንገድ አለ፡፡

አባታችንን ወደዚህ ድንቅ ገዳም እየመራ ይዞአቸው የገባው የታዘዘ መልአክ ነው፡፡ ወደ ገዳሙ ቅጥር ውስጥ ከተገባ በኋላ ዕፁብ ድንቅ የሆኑ ልዩና መንፈሳዊ ሐሴትን የሚሞሉ በርካታ ተአምራት የተፈጸመባቸውን ነገሮችን መመልከት ይቻላል፡፡ተአምራቶቹም "ድሮ እንዲህ ነበር፣ እንደዛ ተደረገ…" ተብሎ በአፈ ታሪክ ብቻ የሚወራ ሳይሆን አሁንም ድረስ በዐይን የሚታዩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ገዳሙ አጠገብ የሚገኙት ዛፎች ብዙ ዕድሜ ከማስቆጠራቸው የተነሣ በንፋስ ኃይል ሲወድቁ ወደ ታች መውደቅ ሲገባቸው በተቃራኒው ግን ዛፎቹ የሚወድቁት ወደ ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም ገዳሙ ውስጥ በላዔ ሥጋ ሥጋን የሚበላ ንስር ሳይቀር እንኳን የሞተ እንስሳም ቢያገኝ ሥጋ የሚባል ነገር አለመብላቱ አሁንም ድረስ በዐይን
የሚታይ እውነታ ነው፡፡

እንዲሁም እዚህ ድንቅ ገዳም ውስጥ መርዛማ እባብም ነድፎ ሰው ሊገድል አይችልም፡፡ በእባቡ የተነደፈ ሰው እንኳን ቢኖር በጉንዳን የተነከሰ ያህል ይሰማዋል እንጂ ፈጽሞ አይሞትም፡፡ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ ላይ "ለሚያምኑ እነዚህ ምልክቶች ይከተሉዋቸዋል፡- በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፣ እባቡን ይይዛሉ፣ የሚገድል መርዝ ቢጠጡ እንኳን ከቶ አይጎዳቸውም" ያለው አምላካዊ ቃል እዚህ ገዳም ውስጥ ባለንበት ዘመን በግልጽ በተግባር ይታያል፡፡ ማር 16፡16-18፣ ሐዋ 28፡3-6፡፡ እንዲሁም በዚህ ገዳም ውስጥ ከነበሩ ዛፎች ውስጥ አንዱ ዳዕሮ የተባለ ትልቅ ዛፍ አለ፡፡ ከዚህ ልዩ ዛፍ ተጠምቆ የሚዘጋጀው መጠጥ ከወይን የሚጥም ኅሊናን የሚመስጥና ሕመምን የሚፈውስ ነበር፡፡ ሌላው በገዳሙ ውስጥ በዐይን ከሚታዩትና ከሚያስደንቁት ተአምራቶች ውስጥ አንዱ በክረምት ወቅት ኃይለኛ ዝናብ ሲጥል በወረደ መብረቅ ምክንያት ገዳሙ ውስጥ የሚገኘው ዐለት ተሰንጥቆ የሀገሪቱ ምስል ተስሎበት ተገኝቷል፡፡ እነዚህና ሌሎችም በርካታ ተአምራት እስከ አሁን ድረስ ጸንተው የሚገኙት የዚህ የፃዕዳ ዓምባ #ቅድስት_ሥላሴ ገዳም መሥራች በሆኑ በአቡነ ሠይፈ ሚካኤል የምሕረት ቃልኪዳን ነው፡፡
2024/12/26 06:45:55
Back to Top
HTML Embed Code: