Telegram Web Link
የሐዋርያው የቅዱስ ማቴዎስ የቀድሞው ስሙ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
18%
ስምኦን
20%
ዲዲሞስ
53%
ሌዊ
9%
ሳኦል
ከአራቱ ወንጌል መካከል ቴዎፍሎስ ለተባለ የግሪክ ባለስልጣን የተፃፈው የትኛው ወንጌል ነው?
Anonymous Quiz
14%
የማቴዎስ
48%
የሉቃስ
27%
የማርቆስ
10%
የዮሐንስ
ከሚከተሉት አንዱ በዮሐንስ ራእይ ከተገለጹት ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ አንዱ አይደልም?
Anonymous Quiz
13%
ኤፌሶን
30%
ጴርጋሞን
9%
ሎዶቅያ
49%
ሮም
†††  እንኳን ለአባ ይስሐቅ ጻድቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ ይስሐቅ ጻድቅ †††

††† ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆኑ የነበሩት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: በጊዜው ዝነኛ ከነበሩት ከታላቁ አባ ዕብሎ (ቅዱስ ዕብሎይ) ተምረዋል:: መማር ብቻ ሳይሆንም ለ25 ዓመታት ያለ መታከት በተልዕኮ አገልግለዋል::

በእነዚህ ጊዜያትም ትሕርምትን : ተጋድሎን : ትምህርተ ቅድስናንና ሌሎች አስፈላጊ መንፈሳዊ ስንቆችን ሰንቀዋል:: በመታዘዛቸው በምድር አበውን : በሰማይ እግዚአብሔርን አስደስተዋል:: በዚህም ከእግዚአብሔር ጸጋውን : ከአበው ምርቃትን አትርፈዋል::

ጊዜው ደርሶም ታላቁ ዕብሎ ሲያርፉ አባ ይስሐቅ በዓት ለይተው ደንበኛውን ተጋድሎ ጀምረዋል:: አምላካቸውን ለማስደሰትና በቅድስና ለመዝለቅም የአርምሞ ሰው ሁነዋል:: ለሚገባው ነገር ካልሆነ በቀር አያወሩም:: ምላሽም አይሰጡም:: "ለምን?" ሲባሉ
1."ለሁሉም ጊዜና ቦታ አለው::"
2."ሰው በከንቱ በማውራቱ ከጸጋ እግዚአብሔር ይርቃል" ይሉ ነበር::

አባ ይስሐቅ የክርስቶስ መድኃኒታችንን ሕማማት ለማዘከር ሁሌ ያነቡ (ያለቅሱ) ነበር:: ቅዳሴ ሲያስቀድሱ እጃቸው የሁዋሊት ታስሮ ነበር:: ቅዱሱ ሰው ለአዝማናት እንዲህ ተመላልሰው በመልካም ዕርግና ያረፉት በዚህ ቀን ነው::

††† አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው አይለየን::

††† ሚያዝያ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ይስሐቅ ገዳማዊ (የታላቁ ዕብሎይ ደቀ መዝሙር)
2.አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
6.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል

††† "የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ: የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ በእግዚአብሔር አብ ተወደው: ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ:
ምሕረትና ሰላም: ፍቅርም ይብዛላችሁ::
ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩዋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ::" †††
(ይሁዳ. 1:1)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
እንኩዋን አደረሳችሁ

"' በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ "'

+*" ሰማዕታተ ኢትዮጵያ "*+

አመ ዐሡሩ ወአሚሩ ለሚያዝያ በዛቲ ዕለት አዕረፉ ሰማዕታተ ኢትዮጵያ:: በረከቶሙ የሃሉ ምስሌነ ለዐለመ ዐለም አሜን፡፡

ከመዝ ኮነ በውስተ ሀገረ ሊብያ በዕሥራ ምዕት ወሰብዐቱ ዐመተ ምሕረት፡፡ በአሜሃ ዘመን ተንሥኡ ተንባላት እለ ስሞሙ አይሲስ በውስተ ሀገረ ኢራቅ ወሶርያ ወሊብያ ወየመን፡፡ አሐዙ ይቅትሉ ሰብአ ዘረከቡ ወፈድፋደሰ እለ ኮኑ ክርስቲያነ በእምነቶሙ፡፡

ብዙሓን ክርስቲያን ተመትሩ አርእስቲሆሙ በአይሲስ ወተወክፉ አክሊለ ስምዕ እምእላ ሀገራት፡፡ በዝ ዘመን ውእቱ ዘረከቦሙ አይሲስ ለሰብአ ኢትዮጵያ በውስተ ሀገረ ሊብያ እንዘ የሐውሩ ኀበ ሀገረ ኢጣልያ በእንተ መፍቅደ ልቦሙ፡፡ እሉ ከሀድያን ውሉደ ሰይጣን ወአራዊተ ገዳም አሐዝዎሙ ወአዘዝዎሙ ወአፍርሕዎሙ ከመ ይክሀዱ ስሞ ለኢሱስ ክርስቶስ፡፡

ወእምዝ ዘበጥዎሙ በዘዚአሁ ዝብጠታተ በእንተ ዘኮኑ ክርስቲያነ ርእዮሙ ማዕተበ ክሣዶሙ፡፡ ውእቶሙሰ አበዩ ይእዜኒ ክሂደ ሃይማኖቶሙ እመኒ አመከርዎሙ በረሐብ ወጽምዕ ወበካልኣን ኵነኔያት፡፡ ሶበ አበዩ ክሂደ ወሰድዎሙ ኀበ ምድረ በድው ኀበ አልቦ እክል ወማይ ከመ ይእመኑ እምጽንዐ ረሐብ ወጽምዕ፡፡

ወእምዝ ጠየቅዎሙ ከመ ይብትኩ ማዕተበ ክሣዶሙ ወይክሀዱ ስሞ ለእግዚአብሔር አምላኮሙ፡፡ እሉሰ ሰማዕታት ይእዜኒ አበዩ ክሂደ ስሞ ለፈጣሪሆሙ፡፡ አዲ ይቤልዎ ለአይሲስ "ኦ አይሲስ ለእመ ክህልከ ቀቲሎታ ለሥጋነ ኢትክል ቀቲሎታ ለነፍስነ፡፡ ኢንፈርሕሂ ወኢንደነግጽ እምብልሐ ሰይፍከ እስመ አቅዲሙ ነገረነ አምላክነ እንዘ ይብል ኢትፍርሕዎሙ ለእለ ይቀትሉ ሥጋክሙ ወለነፍስክሙሰ ኢይክሉ ቀቲሎታ፡፡"

አዲ ይቤለነ በውስተ ወንጌሉ ቅዱስ እስመ ኵሉ ዘከቀተለክሙ ይመስሎ ከመ ዘመሥዋዕተ ያበውእ፡፡ ይእዜኒ አንተ ላእኩ ለዲያብሎስ ፈጽም በላዕሌነ መልእክተከ ሰይጣናዌ ወአብእ መሥዋዕተከ ርኩሰ ለእምላክከ ሰይጣናዊ፡፡ ንህነኒ ናበውእ ክሣደነ ንጹሐ ለእምላክነ ዘፈጠረነ እስመ ነአምር ዘከመ ያነሥአነ በትንሣኤሁ ቅድስት አመ ዳግም ምጽአቱ፡፡

አሲስኒ አላዊ መተሮሙ አርእስቲሆሙ በሰይፍ ወኮኑ ሰማዕተ በከመ ዛቲ ዕለት፡፡ ወእምዝ ተሀውከት ኵላ ኢትዮጵያ ወኵላ ዐለም እስመ ትርእየ ትእይንተ ጥብሐቶሙ ለሰማዕታት በመስኮተ ትእይንት፡፡ ኵሎሙ ሰብአ ኢትዮጵያ አስቆቀዉ ወበከዩ ብካየ መሪረ እንዘ ይገብሩ ሰላማዌ ትእይንተ በበአዕዋዲሁ ወበበፍኖቱ፡፡

ወይብሉ በበቃሎሙ "አይሲስ አይሲስ እንተ ትቀትሎሙ ለሰማዕታት: ወታውሕዝ ደመ ንጹሓን በበፍናዊሁ ከመ ደመ አክልብት: ይደልወከ ትቁም ውስተ ዐውደ ፍትሕ ሰማያዊ፡፡"

በዝንቱ ዘመን ቈስለ ልቡ ለህዝብ በሐዘነ ሥጋ እስከነ ይብል "ፍትሐ ጽድቅ ዘዐርገት ውስተ ሰማይ ከመ ትንበር ምስለ ዘፈጠራ እግዚአብሔር እስመ ኢረከበት ውስተ ዛቲ ምድር ኀበ ትነብር ወኀበሂ ታጸልል፡፡ ናሁ ይጸርሕ ደሞሙ ለሰማዕታት ቅድመ ገጹ ለኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይረድ ፍትሐ ርትዕ ዲበ ምድር ወይሠረው አሲስ እምውስተ ገጻ ለምድር፡፡"

በረከቶሙ: ወጽንዐ ገድሎሙ ለእሉ ሰማዕታት ይሕድር ላዕሌነ ለዐለመ ዐለም አሜን፡፡

ሰላም ለክሙ በቃለ ማሕሌት ወእንዚራ፡፡
ምስለ ሰማዕታት ዘግብጽ መከራቲክሙ ዘሐብራ፡፡
ቅዱሳን ሰማዕታት ዘኦርቶዶሳዊት ሐራ፡፡
እፎ ክህልክሙ ተዐግሦ ጽኑዕ መከራ፡፡
እስከ ክሳውዲክሙ በአሲስ ተመትራ፡፡
(ኢያዕመርኩ ከመ መኑ ጸሐፎ)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ሚያዝያ ዐሥራ አንድ ቀን የከበረችና የነጻች እመሜኔት_______አረፈች።
Anonymous Quiz
17%
ቴክላ
44%
ታዖድራ
33%
እንባ መሪና
6%
አውጋንያ
ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና ወር በገባ በስንተኛው ቀን ይታሰባሉ?
Anonymous Quiz
8%
ወር በገባ በ 1
7%
ወር በገባ በ 3
71%
ወር በገባ በ 11
14%
በሁሉም➛
ቅዱስ አትናቴዎስ ከመንበረ ሢመቱ ከእስክንድርያ በአሳደዱት ጊዜ ብዙዎች ድርሳናትን እየጻፈ ለቅድስት ታዖድራ ይልክላት ነበር።
Anonymous Quiz
91%
እውነት
9%
ሐሰት
ያዕቆብ በሕልሙ ከምድር እስከ ሰማይ የተዘረጋች የወርቅ መሰላል ያየበት ቦታ____ትባላለች።
Anonymous Quiz
14%
ካራን
68%
ፍኖት ሎዛ
11%
ቤተልሄም
6%
ቤርሳቤህ
ነቀፌታዬን ከሰው መካከል አስወገደልኝ ስትል ራስዋን አምስት ወር የሰወረችው ማን ናት?
Anonymous Quiz
22%
ቅድስት ማርያም መቅደላዊት
10%
ቅድስት ማርታ
48%
ቅድስት ኤልሳቤጥ
19%
ቅድስት ሶስና
ጌታ በምኩራብ ሲያስተምር ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ ልኮኛል በማለት ያነብ የነበረው የማንን መጽሐፍ ነበር?
Anonymous Quiz
17%
የነብዩ ኤርሚያስ
66%
የነብዩ ኢሳይያስ
14%
የነብዩ ሚክያስ
3%
የነብዩ ሚልክያስ
እመሜኔት ቅድስት ታዖድራ በስንት አመቷ አረፈች?
Anonymous Quiz
29%
በ150
10%
በ200
27%
በ100
34%
በ75
Audio
"" አምላኬ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? "" (መዝ. ፳፩:፩)

"ገብር ሔር"

"በዓለ ቅዱሳን አዳም ወዳዊት"

(ሚያዝያ 6 - 2016)

🔎https://www.youtube.com/@ZikereKedusan


🔎 https://www.tg-me.com/zikirekdusn
2024/09/30 15:26:12
Back to Top
HTML Embed Code: