Telegram Web Link
#ሚያዝያ_1
አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ_ስም
ሚያዝያ አንድ በዚህች ቀን ለሙሴ ወንድሙ የሆነ #የካህኑ_አሮን የእረፍቱ መታሰቢያ ሆነ፣ የከበረ አባት #አባ_ስልዋኖስ አረፈ፣ #ጌታችን_የአባ_መቃርስ ገዳም መነኮሳትን ጸሎታቸውን ሰምቶ ከዐረቦች ወረራ
ጠበቃቸው፡፡ #ቅድስት_መጥሮንያ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው፣ #ከአበከረዙን ጋር በሰማዕትነት ያረፉት #ቅዱስ_ዮስጦስና_ሚስቱ መታሰቢያቸው
መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡

#ቅዱስ_አሮን_ካህን

ሚያዝያ አንድ በዚህች ቀን በእስክንድርያ ከተማ በሚገኝ በግብፃውያን መፅሀፍ እንደ ተፃፈ በላዕላይ ግብፅ ያለ ግብፃዊውም እንደፃፈ ለእንበረም ልጅ ለሙሴ ወንድሙ የሆነ የካህኑ አሮን የእረፍቱ መታሰቢያ ሆነ ይላሉ።

በኦሪቱ መፅሀፍ የተፃፈው ግን እስራኤል ከግብፅ ከወጡ በሁለተኛው ወር በሶስተኛው ቀን አረፈ ይላሉ። ይኸውም ግንቦት ስምንት ነበር የእስራኤል ወሮች በጨረቃ እየተቁጠሩ ዓመቱን ስለሚዞሩ በዚያች ዓመት ሚያዝያ አንድ ቀን ሆኖ ስለተገኘ።

በእኛ ዘንድ ግን የኦሪት ዘኁልቁ መፅሐፍ በአምስተኛው ወር መባቻ ስለሚል መታሰቢያውን ነሐሴ አንድ ቀን እናደርጋለን። ይህም ፃድቅ ሰው የነቢያት አለቃ ለኦሪት ሕግ መምህር ለሆነ ለሙሴ ለነቢዪት ማርያምም ወንድም ነው እነርሱም ከሌዊ ነገድ ናቸው።

እግዚአብሔርም በግልፅ ምድር ብዙ አስደናቂ ተአምራትን በእጆቹ አደረገ። እግዚአብሔርም እርሱንና ልጆቹን መርጦ ካህናቶቹ አድርጎ ከእስራኤል ልጆች ከገንዘባቸውና ከመሥዋዕታቸው ዐስራትን ሰጣቸው።

የቆሬም ልጆች በጠላትነት በተነሱበት ጊዜ እግዚአብሄር ፈርዶ አጠፋቸው ምድርንም አዘዛት አፍዋንም ከፍታዋጠቻቸው። በበጎ ተጋድሎውና የኦሪትንም ሕግ በመጠበቅ እግዚአብሔርን ከአገለገለ በኋላ ሔደ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ስልዋኖስ_ጻድቅ

በዚህች ቀን የከበረ አባት አባ ስልዋኖስ አረፈ። ይህም አባት በአስቄጥስ ገዳም ከከበረ አባ መቃርስ ዘንድ በታናሽነቱ መነኰሰ በጠባብ መንገድ ሁሉ ተጋደለ በብዙ ፆምና ፀሎተረ በመትጋት በትሕትና በፍቅር ተወስኖ ኖረ ታላቅ አባትም ሆነ። የክብር ባለቤት ጌታችንም አምላካዊ ራእይን ይገልፅለት ነበር ድንቅ የሆኑ ነገሮችንም ይነግረዋል።

ይህም እንዲህ ነው በአንዲት እለት ልቡ ተመስጦ በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ ብዙ ጊዜ ቆየ ከዚያም በኃላ ነቅቶ ራሱን ቀና አደረገ። ከእርሱ ዘንድ ያሉ ወንደረሞች መነኩሳትም በእርሱ ላይ የደረሰበትን ይነግራቸው ዘንድ ለመኑት ዝም ብሎ መሪር ልቅሶ ያለቅሳል እንጂ ሊነግራቸው አልወደደም።

ከእርሱ የሆነውን ያሰረዳቸው ዘንድ ግድ ባሉት ጊዜ እንዲህ አላቸው ተድላ ወዳለበት ገነት አውጥተውኝ በዚያ የፃድቃንን መኖሪያ አየሁ ደግሞ የስቃይ ቦታዎችንም። ሁለተኛም ብዙዎች መነኮሳትን ወደ ገሀነም ብዙዎች ምእመናን ወደ መንግስተ ሰማያት ሲወስዱአቸው አየሁ እንግዲህ እኔ ለነፍሴ የማላለቅስ ለምንድነው አላቸው።

ከዚያች ቀንም ጀምሮ በኃላ ወደዘላለም ጨለማ ሊወስዱኝ ዛሬ የዚህን የኃላፊውን ዓለም ብርሃን ማየት አልሻም እያለ ፊቱን በቆቡ ሸፍኖ የሚያለቅስ ይህም አባት በመንፈሳዊ ስራ የተጠመደ ሆነ ደቀ መዛሙርቱንም ለምግባቸው የሚሆን ስራን ከመስራት እንዳያቋርጡ ከዕለት ምግባቸው የሚተርፈውንም እንዲመፀውቱ ያዛቸዋል።

በአንዲት ቀንም አንድ ታካች የሆነ መነኮስ ወደርሱ መጣ ሽማግሌውን አባትና ደቀ መዛሙርቱን ሲሰሩ አይቶአቸው ለኃላፊ ምግብ ትሰራላችሁ ትደክማላችሁ። የዘላለም ህይወት ለሚሆን ምግብ ስሩ ድከሙ እንጂ ይህ በከበረ ወንጌል የተፃፈ አይደለምን ማርያምም የማይቀሟትን በጎ ዕድል ትምህርትን እንደመረጠች ብሎ ጠቀሰ።

ሽማግሌው አባ ስልዋኖስም እንዲህ ሲናገር በሰማው ጊዜ ደቀ መዝሙሩን እንዲህ ሲል አዘዘው። ይህን መነኩስ ከእንግዳ ማሳረፊያ ቤት አስገብተህ የሚያነበው መፅሀፍ ስጠው በሩንም በላዩ ዝጋ በእርሱ ዘንድም ለመብል የሚሆን ምንም ምን አትተው። ረድኡም ሽማግሌው መምህሩ እንዳዘዘው አደረገ።

ዘጠኝ ሰዓትም ሲሆን መነኰሳቱ ተሰበሰቡ ከሽማግሌው አባትም ጋር ፀሎት አድርገው ምግባቸውን ተመገቡ። ያን እንግዳ መነኰስ ግን አልጠሩትም እርሱም ቢጠሩኝ ብሎ ወደ ደጃፍ እየተመለከተ ይጠብቅ ነበር።

በረኃብም በተቃጠለ ጊዜ ከበአቱ ወጥቶ ወደ አባ ስልዋኖስ ሒዶ አባቴ ሆይ መነኮሳቱ ራታቸውን በሉን አለው ሽማግሌውም አዎን በሉ ብሎ መለሰለት። ሁለተኛ ደግሞ እኔ እንግዳ ስሆን ለምን አልጠራችሁኝ አለ የከበረ አባት ስልዋኖስም አንተማ ስጋዊ መብል የማትሻ መንፈሳዊ ሰው ነህ በጎ እድልን ስለመረጥክ እኛ ግን ስጋውያን ሰዎች ለስጋዊ መብል የምንሰራ የምንደክም ነን ስለዚህም ለምግባችን የሚሆነውን በእጃችን እንሰራለን ብሎ መለሰላት። ያ መነኮስም በንግግሩ እንደበደለ አወቀ። አባ ስልዋኖስንም አባቴ ሆይ እኔ በድያለሁና ይቅር በለኝ ብሎ ሰገደለት።አባ ስልዋኖስም ማርታ በመስራት እንደ ደከመች እንድከም እንስራ ከማርያም ይልቅ ማርታ የተዘጋጀች ሁናለችና ብሎ መለሰለት።

ያ ታከች የነበረ መንኰስም በዚህ አባት ትምህርት ተመክሮና ተገስፆ ሁልጊዜ የሚሰራና ከእርሱ የሚተርፈውንም ለድኆች የሚመፀውት ሆነ። ይህም አባት ስለ መንፈሳዊ ተጋድሎ ጥቅም ያላቸው ብዙ ድርሳናትንና ተግሳጳትን ደረሰ።

ዕድሜውም በመልካም ሽምግልና በተፈፀመ ጊዜ የሚያርፍባትን ሰዓት እግዚአብሔር ነግሮት በእርሱ አቅራቢያ ያሉ መነኮሳትን ጠርቶ ከእርሳቸው በረከትን ተቀበለ። በፀሎታቸውም እንዲአስቡት ለመናቸው እነርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲአስባቸው ለመኑት እርስ በርሳቸውም ተሰነባብተው በፍቅር በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_መነኮሳት

በዚችም ቀን ደግሞ በላይኛው ግብፅ ያሉ አረቦች ተሰብስበው በአስቄጥስ ያሉ አድባራትንና ገዳማትን የአባ መቃርስንም ቤተ ክርስቲያን ከበቡ በአድባራቱና በገዳማቱ ያለውንም እቃ ሁሉ ማርኩ። መነኰሳትም ተሰበሰቡ በከበሩ አባቶችም ስም ወደ እግዚአብሔር በፀሎት ማለዱ።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እነዚያን ዐረቦች አስደንግጦ አሳደዳቸው ያንጊዜም ማንም የተከተላቸው ሳይኖር ድል ሆነው ሸሹ። ከክብር ባለቤት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በቀር ማንም የተከተላቸው ሳይኖር ነው። ይቅር ብሏቸዋልና ጌታችንን አመሰገኑት፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሰማዕቷ_ቅድስት_መጥሮንያ

ቅድስት መጥሮንያ የአንዲት አይሁዳዊት ሴት
አገልጋይ ነበረች፡፡ አሠሪዋ አይሁዳዊ ሴትም
ቅድስት መጥሮንያን ክርስቲያን በመሆኗ ብቻ
ሸክም ታበዛባትና ታንገላታት ነበር፡፡
ከሃይማኖቷም አውጥታ ጌታችንን ማመንን
ልታስተዋት ብዙ ሞከረች፡፡ በአንዲት ዕለትም
አይሁዳዊቷ ይዛት ወደ ምኩባራባቸው ሄደች፡፡
ቅድስት መጥሮንያ ግን ወደ ምኩራባቸው ሳትገባ ተመልሳ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ጸሎት አደረገች፡፡

ወደ ቤታቸው ተመልሰው በገቡ ጊዜ አሠሪዋ ‹‹ወደ እኛ ምኩራብ ለምን አልገባሽም?›› ብላ ጠየቀቻች፡፡ ቅድስት መጥሮንያም "ከእናንተ ምኩራብ እግዚአብሔር ርቋልኮ፣ እንዴት ወደ እርሱ እገባለሁ! በውስጧ ልገባባት የሚገባኝ ቦታዬ ግን ክብር ይግባውና ጌታችን በከበረ ደሙ የዋጃት ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት" አለቻት፡፡ አሠሪዋ አይሁዳዊትም ከቅድስት መጥሮንያ ይህንን በሰማች ጊዜ እጅግ ተቆጥታ በኃይል ደበደበቻት፡፡ በጨለማ ቤት ውስጥ ዘጋችባትና ያለምግብና ያለመጠጥ ለ4 ቀን አሠረቻት፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ውጭ አውጥታ በጅራፍ ታላቅ ግርፋትን ገርፋ ድጋሚ በእሥር ቤት ጣለቻትና በዚያው ተንገላታ ዐረፈች፡፡ ነፍሷንም
እግዚአብሔር ተቀብሎ የሰማዕታትን አክሊል አቀዳጃት፡፡

አሠሪዋ ግን ሥጋዋን አውጥታ በመጣል በዚያም መጥሮንያ ራሷን የገደለች አስመሰለች፡፡ ቅድስት መጥሮንያ ራሷን የገደለች ስለመሰለ አይሁዳዊቷን ሴት ግን ማንም የመረመራት የለም፡፡ ነገር ግን ለተገፉ የሚፈርድ፣ለተበደሉ የሚበቀል እውነተኛ ዳኛ ልዑል እግዚአብሔር ቁጣው በዚያች አይሁዳዊ ሴት ላይወረደ፡፡ ከደርቧ ላይ ስትወርድ ድንገት ወድቃ በዚያው ከመቅጽበት ሞተች፡፡ በነፍሷም ወደ ዘላለማዊ እሳት ሄደች፡፡

ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

=>ሚያዝያ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አሮን ካህን (የሊቀ ነቢያት ሙሴ ወንድም)
2.አባ ስልዋኖስ ጻድቅ
3.ቅዱሳን መነኮሳት
4.ቅድስት መጥሮንያ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

=>+"+ ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መስዋዕትን ስለ ኃጢአት ሊያቀርብ ይገባዋል:: እንደ አሮንም በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም:: +"+ (ዕብ. 5:3)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
አባ ስልዋኖስ ደቀ መዛሙርቶቻቸውን ለምግባቸው የሚሆን ሥራን ከመሥራት እንዳያቋርጡ ከዕለት ምግባቸው የሚተርፈውን እንዲመጸውቱ አያዟቸውም ነበር።
Anonymous Quiz
50%
እውነት
50%
ሀሰት
ቅዱስ አሮንም በበጎ ተጋድሎውና የኦሪትንም ሕግ በመጠበቅ እግዚአብሔርን ካገለገለ በኋላ በየት አረፈ?
Anonymous Quiz
47%
በሖር ተራራ ላይ
27%
በሲና ተራራ ላይ
20%
በደብረ ዘይት ተራራ ላይ
5%
በደብረ ታቦር ተራራ ላይ
በውዳሴ "ማርያም" ላይ "ሳይተክሏትና ውሃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበረች። ያለ ዘር ሰው ሆኖ ያዳነን እውነተኛ አምላካችንን ክርስቶስን የወለድሽልን ሆይ አንቺ እንደርሷ ነሽ"👈የሚለው በየትኛው ክፍል ይገኛል?
Anonymous Quiz
4%
በሰኞ የሚጸለይ የውዳሴ ማርያም ክፍል
15%
በረቡዕ የሚጸለይ የውዳሴ ማርያም ክፍል
58%
በሰንበተ ክርስቲያን የሚጸለይ የውዳሴ ማርያም ክፍል
23%
በማክሰኞ የሚጸለይ የውዳሴ ማርያም ክፍል
#ሚያዝያ_2
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ_ስም
ሚያዝያ ሁለት በዚህችም ቀን የቃይናን ልጅ #የቅዱስ_መላልኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ ፊቱ እንደ ውሻ የሆነ #ቅዱስ_ክርስትፎሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ የሐሊባ ሃገር ሰው የከበረ አባት #ስምዖን ዕረፍቱ እነረደሆነ ስንክሳር በስም ይጠቅሰዋል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_መላልኤል

ሚያዝያ ሁለት በዚህችም ቀን የቃይናን ልጅ የመላልኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፡፡ መላልኤልም መቶ ስልሳ አምስት ዓመት ኖረ ያሬድንም ወለደው።

መላልኤልም ያሬድን ከወለደው በኃላ ሰባት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። የመላልኤልም መላ ዘመኑ ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ነው። ቅዱስ መላልኤልም ሚያዝያ ሁለት ቀን በእሑድ ዕለት ሞተ በማከማቻም ውስጥ ቀበሩት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ክርስቶፎሮስ (ሐዋርያና ሰማዕት)

በዚችም ቀን ፊቱ እንደ ውሻ የሆነ ቅዱስ ክርስትፎሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ ሰውን ይበሉ ከነበሩ ሰዎች ሀገር ነው በጦርነትም ማረኩት አባቱም በሐዋርያ ማትያስ እጅ ያመነ ነው። በማረኩትም ጊዜ ቋንቋቸውን አያውቅም ነበር የክብር ባለቤት ወደሆነ እግዚአብሔርም ማለደ ቋንቋቸውንም ገልጦለት እንደርሳቸው ተነሰገረ የክርስቲያን ወገኖችን የሚያሠቃዩአቸውንም ገሠጻቸው የጦር ሠራዊቱንም የሚመራ መኰንን ጽንዕ ግርፋትን ገረፈው። ቅዱስ ክርትፎሮስም መኰንኑን የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዙ ኃይሌን ባትይዘኝና ባታስታግሠኝ አንተና ሠራዊትህ ከእኔ እጅ ባልዳናችሁ ነበር አለው።

መኰንኑም ስለ ርሱ ወደ ንጉሥ ላከ ከእርሱ የሆነውንም ነገረው። ንጉሡም ወደ ርሱ እንዲያመጡት ሁለት መቶ ወታደሮችን ላከለት እርሱም ያለ መፍራት ያለ ማፈግፈግ አብሮአቸው ሔደ። በእጁ በትር ነበረች በላይዋ በጸለየ ጊዜ በቀለችና አበበች። እነዚያ ወታደሮች ተርበው የሚበሉት እንጀራ በአጡ ጊዜ ቅዱስ ክርስትፎሮስ ጸለየ በእነርሱ ዘንድ እንጀራ በዝቶ ተትረፈረፈ እጅግም አድንቀው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። አባ ጳውሎስ እጅ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቁ።

ወደ ንጉሡም ፊት በደረሱ ጊዜ ንጉስ ዳኬዎስ ሊያስፈራውና ሊሸነግለው ጀመረ ደግሞ እጅግ መልከ መልካም የሆኑ ሁለት አመንዝራ ሴቶችን ወደርሱ ሰደደ እነርሳቸው እንደሚያስቱትና በኀጢአት እንደሚጥሉት አስቧልና። እርሱ ግን ገሠጻቸው አስተማራቸውም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በደማቸው ምስክር ሁኑ። እንዲሁም እነዚያ ሁለት መቶ ወታደሮች በንጉሡ ፊት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ራሶቻቸውንም በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነትንም በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

ቅዱስ ክርስትፎሮስም ንጉሡን አንተ የሰይጣንን ሥራ የምትቀበል ማደሪያው የሆንክ ብሎ ዘለፈው ንጉሡም ተቆጥቶ በትልቅ ብረት ምጣድ ውስጥ እንዲጨምሩትና ከበታቹ እሳትን እንዲያነዱ አዘዘ። እንዲሁም አደረጉበት ነገር ግን ከጉዳት እንዳሰቡት ምንም የደረሰበት የለም። ጤነኛ ሆኖ ሰዎችን አስተማራቸው እንጂ።እጅግም አድንቀው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ቅድሱንም ከእርሷ ሊአወጡት ወደዚያች ብረት ምጣድ ቀረቡ ንጉሡም አንገቶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ የሕይወት አክሊልንም ተቀበሉ። ከዚያም በኃላ ታላቅ ደንጊያ በአንገቱ አንጠልጥለው ከጥልቅ ጉደረጓድ እንዲጨምሩት ንጉሡ አዘዘ በጨመሩትም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በጤንነት አወጣው። ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ አንገቱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ ንጉሡ አዘዘ። ቅዱሱም በእግዚአብሔር መንግስት የድል አድራጊነትን አክሊል ተቀዳጀ፡፡

ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

#ሚያዝያ_1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፣
1, ቅዱስ ክርስቶፎሮስ (ሐዋርያና ሰማዕት)
2, አባ ስምዖን ዘሃገረ ሐሊባ
3, ቅዱስ መላልኤል (የያሬድ አባት - ከአዳም ፭ኛ ትውልድ)
4, እግዚአብሔር ፀሐይን፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትን ፈጠረ

#ወርኃዊ_በዓላት
1, ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2, ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
3, ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
4, ቅዱስ አቤል ጻድቅ
5, ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
6, ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
7, አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ። ልባሞች እንደ መሆናችሁ እላለሁ፤ በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ። የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? አንድ እንጀራ ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና። 1ኛ ቆሮንቶስ 10÷14—18

ወስብሐት ለእግዚአብሔር✝️
ቅዱስ መላልኤል ያሬድ በስንት ዓመቱ ወለደው?
Anonymous Quiz
48%
በ165 ዓመቱ
16%
በ158 ዓመቱ
16%
በ166 ዓመቱ
20%
በ100 ዓመቱ
በእግዚአብሔር ኃይል ግመልን በመርፌ ቀዳዳ ያሾለከ ሐዋርያ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
16%
ሐዋርያው ማትያስ
29%
ሐዋርያው በርተለሜዎስ
42%
ሐዋርያው ታዴዎስ
13%
ሐዋርያው ፊልጶስ
Audio
"" የመጨረሻዋ ሰዓት "" (፩ዮሐ. ፪:፲፰)

"ነገረ ምጽአት"

(መጋቢት 29 - 2016)

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

🛑በቴሌግራም👉
https://www.tg-me.com/zikirekdusn
#ሚያዝያ_2_ቀን_የዕለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ማቴዎስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ ኢየሱስም ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ።
²² እነሆም፥ ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላ ጮኸች።
²³ እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት እያሉ ለመኑት።
²⁴ እርሱም መልሶ፦ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።
²⁵ እርስዋ ግን መጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ እርዳኝ እያለች ሰገደችለት።
²⁶ እርሱ ግን መልሶ፦ የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም አለ።
²⁷ እርስዋም፦ አዎን ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለች።
²⁸ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ፦ አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች።
²⁹ ኢየሱስም ከዚያ አልፎ ወደ ገሊላ ባሕር አጠገብ መጣ፥ ወደ ተራራም ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ሚያዝያ_2_ቀን #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወዓመቲከኒ ዘኢየኀልቅ። ደቂቀ አግብርቲከ ይነብርዋ። ወዘርዖሙኒ ለዓለም ይጸንዕ"። መዝ 101፥27-28። በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡት መልዕክታት  ሮሜ 11፥13-25፣ ያዕ 3፥1-13 እና የሐዋ ሥራ 14፥11-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 15፥21-29። #የሚቀደሰው_ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው።መልካም የጾም ጊዜና በዓል። በሁላችንም ይሁንልን።
2024/09/29 17:37:44
Back to Top
HTML Embed Code: