Telegram Web Link
የጸሎተ ሐሙስ ቅዳሴ የሚከናወነው በተመጠነ ድምፅ ሲኾን፣ እንደ ደወል (ቃጭል) የምንጠቀመውም ጸናጽልን ነው፡፡ ልኡካኑ የድምፅ ማጉያ ሳይጠቀሙ በለኆሣሥ (በቀስታ) ይቀድሳሉ። ለምን ምክንያቱ ምንድነው?
Anonymous Quiz
16%
ሀ, ይሁዳ በምሥጢር ጌታችንን ማስያዙን ለመጠቆም፣
4%
ለ, የዘመነ ብሉይ ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደ ነበር ለማስታወስ፣
1%
ሐ, ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ያሳየውን የተግባር ትምህርት ለማሳየት፣
33%
መ,ሁሉም
46%
ሠ, ሀ እና ለ
የምሴተ (የጸሎተ) ሐሙስ ቀን የምስጢር ቀን እየተባለ ይጠራል።
Anonymous Quiz
10%
ሐስት
90%
እውነት
ቅድስት ኢዮጰራቅስያ የስንት ዓመት ልጅ ሆና ነው ወደ ገዳም የሄደችው?
Anonymous Quiz
33%
የ 9 ዓመት
28%
የ 9 ዓመት ከ6ወር
9%
የ 8 ዓመት
29%
የ 12 ዓመት
ቅድስት ኢዮዸራቅስያ ለአንድ መኮንን ያጫት ንጉሥ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
25%
ንጉሥ አርቃዴዎስ
48%
ንጉሥ አኖሬዎስ
23%
ንጉሥ ቴዎዶስዮስ
5%
ንጉሥ ዳዊት
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የመድኃኔዓለምን የሕማሙን የሞቱን ነገር መናገር እንጀምራለን፡፡ 13ቱ ሕማማተ መስቀል እነማን ናቸው ቢሉ ተዓሥሮ ድኅሪት (የፊጥኝ መታሰር)፣ ወዲቀ ዲበ ምድር (በመሬት ላይ መውደቅ)፣ ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በአይሁድ እግር መረገጡ)፣ ተስሕቦ በማዕከለ ዓምድ (ታንቆ መጎተት)፣ ተጸፍዖ መልታሕት (ፊትን መጥፊ መመታት)፣ ተኰርዖ ርእስ (የራስ መገመስ)፣ አክሊለ ሦክ (የእሾህ አክሊል)፣ ተዐርቆተ ልብስ (ርቃን መቆም)፣ ተቀሥፎ ዘባን (ጀርባን መገረፍ)፣ ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)፣ ተቀንዎ በቅንዋት (በችንካር መቸንከር)፣ ተሰቅሎ በዕፅ (መሰቀል) እና ሰሪበ ሐሞት (ሐሞት መጠጣት) ናቸው፡፡
13ቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እነዚህ ናቸው፡፡ ምነውሳ ወሪቀ ምራቅ፣ ጽርፈተ አይሁድና ርግዘተ ገቦ ከእነዚህ ውስጥ የማይቆጠሩ? ቢሉ እነዚህ ሦስቱ ከንዑሳን የሚቆጠሩ ናቸው እንጂ ከ13ቱ ገብተው አይቆጠሩም፡፡ ስለምን አይቆጠሩም? ቢሉ ወሪቀ ምራቅ የምራቅ መተፋት ነው፡፡ አይሁድም ጌታችንን ርኩስ ምራቃቸውን ተፍተውበታል ነገር ግን ሰውን ቢተፉበት ይጸየፈዋል እንጂ ምራቅ ሕማም ሆኖ አይገድልም፡፡ ስድብም ያናድዳል ያስቆጣል እንጂ ሕማም ሆኖ አይገድልምና ጽርፈተ አይሁድ አይቆጠርም፡፡ ርግዘተ ገቦ ማለት የጌታችን ጎኑ በጦር መወጋቱ ነው፡፡ ሰውን ከሞተ በኋላ ቢወጉት ሕማሙ አይሰማውምና ርግዘተ ገቦ አይቆጠርም፡፡
13ቱን ሕማማት እንዴት ነው የተፈጸሙ ቢሉ ክፉዎች አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው የታጠቁ 300 ጭፍራዎችን አስከትለው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው ‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ ይህም ክስተት ለሦስት ጊዜ ያህል በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ ዮሐ 18፡1-14፡፡ የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡›› ዮሐ 8፡56-59፡፡ የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ በፊቱ እንዳይቆሙ አድርጎ ባጠፋቸው ነበር፡፡ ጌታችን ግን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡
ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፤ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፤ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፤ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፤ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ይህንን ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
የሕማማቱን ነገር ወደመፈጸም እንመለስ፡፡ ጌታችን 300 የታጠቀ ሠራዊት አስከትለው ሊይዙት የመጡትን አይሁድን በፊቱ ሦስት ጊዜ በጣላቸው ሰዓት በመጀመሪያው በልባቸው ጥሎ ገሃነመ እሳትን አሳይቷቸዋል፤ በሁለተኛው በጀርባቸው ጥሎ መንግሥተ ሰማያትን አሳይቷቸዋል፡፡ በሦስተኛው ደግሞ ፈረስ በቅሎዎቻቸውን ከላይ አይሁድን ከሥር አድርጎ ፊታቸውን ከኋላ ኋላቸውን ከፊት፣ ቀኛቸውን ግራ ግራቸውን ቀኝ አድርጎ በማሳየት ሁሉን ማድረግ የሚችል የባሕርይ አምላክ መሆኑን በተግባር አሳይቷቸዋል፡፡
እነርሱ ግን አንድ ጊዜ ሰይጣን በልባቸው አድሯልና ወደ ህሊናቸው መመለስ አልቻሉም፡፡ እነርሱም ‹‹እኛ ታዘን ነውና የመጣነው እባክህ ጌታ ሆይ! በፈቃድህ ተያዝልን›› ብለው ለመኑት፡፡ ሁሉ በእጁ የተያዘ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያንጊዜ ራሱን አሳለፎ ሰጣቸው፡፡
1ኛ. ተዓሥሮ ድኅሪት፡- አይሁድም ከዚህ በኋላ የጌታችንን መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የፊጥኝ ረግጠው ካሠሩት በኋላ አፍንጫውን 25 ጊዜ ቢመቱት ደሙ በመሬት ላይ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ አሥረውም ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፈ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ዮሐ 18፡12፡፡ ይህም ለአርአያ እና ለቤዛነት ነው፡፡ ቤዛነቱ አዳምንና ሔዋንን አጋንንት ገሃነመ እሳት አውርደው በእሳት ሰንሰለት የፊጥኝና የግርግሪት አሥረው ሲያሠቃዩአቸው ነበርና እነርሱንና የሰውን ልጅ በሙሉ ለማዳን ነው፡፡ አርአያነቱ በእኔ ምክንያት ያስሯችኋል ነገር ግን በፍቅሬ ታስራችሁ ኑሩ፣ መከራን ተቀበሉት እንጂ አተሰቀቁ ሲል ነው፡፡
2ኛ. ወዲቀ ዲበ ምድር፡- ክፉዎች አይሁድ ጌታችንን ካሠሩት በኋላ ከጌቴሴማኒ እስከ ሐና ቤት ድረስ 65 ጊዜ በምድር ላይ ጥለውታል፡፡ የራስ ጠጉሩንም እየያዙ እያንጠለጠሉ 25 ጊዜ እያነሡ ጥለውታል፡፡
3ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ፡- አይሁድ አሥረው እየጎተቱ ሲወስዱት የፊተኞቹ ሲስቡት የኋለኞቹ ይለቁታል ያንጊዜም በልቡ ሲወድቅ ከኋላ ያሉት ፈረሳቸውን በቅሏቸውን በላዩ ይነዱበታል፡፡ የኋለኞቹ ሲስቡት የፊተኞቹ ይለቁታል በጀርባው ይወድቃል፡፡ ቀድመውት የሄዱትም ‹‹…ወዴት ሄደ? አመለጠን?...›› እያሉ በመዘበት ተመልሰው በልቡ ላይ ይሄዱበታል፡፡ እንዲህ እያደረጉ 65 ጊዜ ከመሬት ጋር አጋጭተውታል፡፡ ሳውልም በዚያ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ነበርና ጌታችን ‹‹መመለስህ ላይቀር ለምን ትረግጠኛለህ?›› ቢለው ትንቢት ተናገረብኝ ብሎ ሳውል 440 ጊዜ አስገረፈው፡፡ ዳግመኛም በጅንፎ በትር 62 ጊዜ መቱት፤ በአለንጋ 62 ጊዜ ገረፉት፤ አፉንና አፍንጫውን ደሙ እስኪወርድ ድረስ 40 ጊዜ መቱተ፤ የእጆቹ ጣቶች እስኪደቁ ድረስ 42 ጊዜ መቱት፡፡
4ኛ. ተስሕቦ በማዕከለ ዓምድ፡- ይኽም ጉሮሮን ታንቆ እንደውሻ መጎተት ማለት ነው፡፡ ጌታችንን አይሁድ ጉሮሮውን በብረት ሰንሰለት አጥብቀው አሥረው ደም እስኪነስረው ዐይኑ ሊፈርጥ እስኪደርስ ድረስ 27 ጊዜ በጡጫ መቱት፡፡ በሁለት ታላላቅ ግንዶች መሐል አግብተው አንገቱን የታሠረበት ከግንዶቹ ጋር በማሠር የፊተኞቹ ሲስቡት የኋለኞቹ ይለቁታል በፊቱ ያለው ግንድ ልቡን ደረቱን ፊቱን ይመታዋል፤ የኋለኞቹ ሲስቡት የፊተኞቹ ይለቁታል የኋላው ግንድ ወገቡን ራሱን ይመታዋል፡፡ እንዲህ እያደረጉ 62 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡
5ኛ. ተጸፍዖ መልታሕት፡- ሊቀ ካህናቱ ሐና ወደ ቀያፋ በላከው ጊዜ ቀያፋም ‹‹‹አምላክ ነኝ ከሰማይ ወርጃለሁ› የምትል አንተ ነህን?...›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹አምላክነቴን እኔ ብቻ የምናገረው አይደለም አንተም ደግሞ ራስህ ተናገርኽ እንጂ›› አለው፡፡ ማቴ 27፡11፡፡ ቀያፋም ሎሌዎቹን ‹‹ተቀምጣችሁ አታሰድቡኝ›› ብሎ በመቆጣት ልብሱን ቀደደ፡፡ እነርሱም ይህን ጊዜ ጌታችንን ፊቱን በጥፊ መቱት፡፡ ዮሐ 18፡22፡፡ እጃቸውን ቢደክማቸው ድንጋይ ጨብጠው አጥንቱ እስኪደቅ ድረስ በድንጋይ ጥፊ 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡
6ኛ. ተኰርዖ ርእስ፡- አይሁድ ጌታችንን ‹‹ኃላፊያቱን መጻኢያቱን አውቃለሁ ትላለህ…›› እያሉ በመዘበት ፊቱን እየመቱ ራሱን እየገመሱ ‹‹የመታህ ማነው?›› ይሉት ነበር፡፡ ማቴ 26፡67፣ ሉቃ 22፡63፡፡ ዳግመኛም አክሊለ ሦኩን ለማድረግ እንዲያመቻቸው የራስ ፀጉሩን 25 ጊዜ ነጩት፡፡
7ኛ. አክሊለ ሦክ፡- እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን በልባቸው ነግሦ ክፋትን ብቻ እንዲያስቡ አድርጓቸዋልና ስቁረት ያለበት እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደ መርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው የብረት አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት አንሥተው ‹‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው ያ ሁሉ እስኪገባ ድረስ በራሱ ላይ መቱበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ ዳግመኛም እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ እንደ መርፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በዚያ በአክሊሉ 73 ስቁረት አግብተው ያ ሁሉ እስኪገባ ድረስ በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ በአንገቱ ወርዶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊሉንም እንዳሸከሙት ጲላጦስ እንዲመረምረው ከቤት ወደ አደባባይ 3 ጊዜ አመላለሱት፡፡ በ4ኛው ከአደባባይ አኑረው ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ርኩስ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ እየሰገዱ ሲነሡ በፊቱ ተፍተውበት ይነሣሉ፡፡ ጀርባውንም በዘንግ ይመቱት ነበር፡፡
8ኛ. ተዐርቆተ ልብስ፡- አይሁድ ‹‹ስቃዩን አበዛነው አሁን ደግሞ አፍሮ ደንግጦ ይሞታል›› ብለው በሰው ሁሉ መካከል ራቁቱን አቁመውታል፡፡  
9ኛ. ተቀሥፎ ዘባን፡- አይሁድ ጲላጦስን ‹‹…ኃይለኛ በደለኛ ሰው ይዘናል ጉባኤ ሥራልን›› አሉት፡፡ ጲላጦስም በጠዋት ጉባኤ ሠራላቸው፡፡ ክፉዎች አይሁድም ጌታችንን ‹‹በቃሉ ሐሰት በሰውነቱ ክፋት የለበትምና ጲላጦስ ይህን ተመራምሮ በነፃ ቢለቀውና ባይፈርድነበት ሀዘናችን ይበዛል በኋላ እንዳይቆጨን›› ብለው አስቀድመው 305 ጊዜ በሽመል ደበደቡት፡፡ በባሕርይ አምላክነቱ ቻለው እንጂ አንዱ ብቻ በገደለው ነበር፡፡
እያዳፉም ወስደው ጲላጦስ ፊት ካቆሙት በኋላ ‹‹ኃይለኛ በደለኛ ነውና ስቀለው›› አሉት፡፡ ጲላጦስም ‹‹በምን በደሉ ልስቀለው? በደሉን ንገሩኝ?›. አላቸው፡፡ አይሁድም ‹‹ሰንበትን ሻረ፣ የሰሎሞንን ቤተ መቅደስ አፈርሱት በ3ኛ ቀን እሠራዋለሁ አለ፣ ራሱን አምላክ አደረገ›› የሚሉ ሦስት ክሶችን አቀረቡ፡፡ ዮሐ 9፡16፣ 13፡29፣ 18፡30፣ ኩፋ 34፡13፣ ሉቃ 23፡1-10፣ ማር 15፡3፣ 19፡10፡፡ የአይሁድን ክፋት ማሸነፍ የማይሆንለት ሆኖ ነው እንጂ ጲላጦስ ጌታችንን ለማዳን ብዙ ለፍቶ ነበር፡፡ በሕጋቸው መሠረት የሚሰቀል አይገረፍም፣ የሚገረፍም አይሰቀልም ነበርና ጲላጦስ ‹‹ገርፋችሁ ልቀቁት›› አላቸው፡፡ አይሁድንም ዳግመኛ ‹‹ሕጋችሁ ስንት ይገረፍ ትላለች?›› ቢላቸው እነርሱም ‹‹…41 ይገረፍ ይላል ነገር ግን ለእርሱ አይበቃውም›› አሉት፡፡ ጲላጦስም ‹‹ለእርሱ ስትሉ ሕጋችሁን ትተላለፋላችሁን? በሉ እንደሕጋችሁ ብቻ ገርፋችሁ ልቀቁት፣ ከቁጥር አብልጣችሁ ብትገርፉት ግን ከደሙ ንጹሕ ነኝ›› ብሎ በፊታቸው ታጠበ፡፡ አይሁድም ‹‹ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን›› በማለት በራሳቸው ላይ ርግማን ስላወጁ ዛሬም ድረስ ወንድ ቢወልዱ ልጁ ደም ጨብጦ ይወለዳል፣ ሴት ቢወልዱ ልጅቱ ያለድንግልና ትወለዳለች፡፡
ርጉማን አይሁድ ጌታችንን ከጲላጦስ ተረክበው ከወሰዱት በኋላ አዝማሪ አስመጥተው ጌታችንን እያሰደቡት 80 ጊዜ ፂሙን ነጭተውታል፡፡ መከራውን ሲያጸኑበት አድረዋልና ደሙ እንደ ውሃ ጎርፍ ፈሷል፣ ሥጋው እየተላጠ መሬት ላይ ወድቋል፡፡ ክፉዎች አይሁድ ‹‹አሠቃቂ ግርፋትን ሲገረፍ ያየነው እንደሆነ ልባችን ሊራራ ይችላል›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሠርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነሥቶ 50 እና 60 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ሌሎቹም ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደመጀመሪያው ገራፊ ሁሉ በተራው እንደገና አንድ ብሎ ጀምሮ 50 እና 60 ይገርፈዋል፡፡ ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡ ሥጋው እየተቆረሰ ከምድር የወደቀው 76 ነው፡፡ ያበጠውና የበለዘው ግን የሚቆጠር አይደለም፡፡ ስፍር ቁጥርም የለውም፡፡

10ኛ. ፀዊረ መስቀል፡- ጌታችንን አይሁድ የዕንጨት መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጥለውታል፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ እንዲህ እያደረጉ መስቀል አሸክመው እያዳፉ ቀራንዮ አድርሰውታል፡፡
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዋት፡- ቀራንዮ ካደረሱት በኋላ አይሁድ ቁመታቸው ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸው እንደ ወስፌ እንደ መርፌ ያሉ፣ ወርዳቸው እንደሞረድ የሆኑ፣ 4 ማዕዘን የሆኑ ራሳቸው እንደ መሮ ያሉ 5 ታላላቅ ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ፡- መስቀሉን በሥሩ ተክለው ጊዜ ቀትር ሲሆን ጌታችንን ቢሰቅሉት ሥጋው በግርፋት አልቆ ነበርና የጎኑ አጥንት ተተረተረ፡፡ አይሁድም ‹‹የጎኑ አጥንት ስንት ነው? እስኪ ቁጠሩት…›› እያሉ ተዘባበቱበት፡፡ ይኽም በነቢዩ ቅዱስ ዳዊት ‹‹አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ›› (መዝ 21፡17) ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ጌታችን ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ በ7 ክንድ ከስንዝር መስቀል ላይ በጊዜ ቀትር ተሰቅሎ 7ቱን መስተፃርራን አስታረቃቸው፡፡ እነዚህም 7 መስተፃርራን እግዚአብሔርና ሰው፣ ሰውና መላእክት፣ ነፍሥና ሥጋ፣ ሰማይና ምድር፣ ሕዝብና አሕዛብ ናቸው፡፡ በቀራንዮ አደባባይ ላይ በገበያ ቀን በተሰቀለም ጊዜ አይሁድ ሲያልፉ ሲያገድሙ ‹‹…ከወንበዴዎች ጋር የተሰቀለው ያ ‹አምላክ ነኝ ከሰማይ ወርጃለሁ› ብሎ ይናገር የነበረው አይደለምን? ታዲያ ምነው ተሰቀለ!?…›› ብለው ስቀው አንገታቸውን ነቅንቀው ያልፋሉ፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹እኔም በእነርሱ ዘንድ ለነውር ሆንኩ፣ ባዩኝ ጊዜ ራሳቸውን ነቀነቁ›› ብሎ ትንቢት እንደተናገረ፡፡ መዝ 108፡25፡፡ ነገር ግን ‹‹የጌታችን ርቃን አናሳይም›› ብለው ፀሐይ ጨለመች፣ ጨረቃም ደም ሆነች፣ ከዋክብትም ረገፉ፡፡
✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ "ቅዱስ መቃርስ" ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*"+ ታላቁ ቅዱስ መቃርስ +"*+

=>ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (ቅዱስ መቃሬ) 'ጽድቅ እንደ መቃርስ' የተባለለት: የመነኮሳት ሁሉ አለቃ: ከ80 ዓመታት በላይ በበርሃ የኖረ: በግብፅ ትልቁን ገዳም (አስቄጥስን) የመሠረተ: ከ50,000 በላይ መነኮሳትን ይመራና ይመግብ የነበረ ፍፁም ጻድቅ ነው::

+በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አርዮሳውያን ደጉን ታላቅ አባት በሰንሰለት አስረው ከግብፅ ወደ እስያ በርሃ ከጉዋደኛው ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ ጋር አሰድደውታል:: በዚያ ለ2 ዓመታት ስቃይን ከተቀበሉ በሁዋላ በአረማውያን ፊት ድንቅ ተአምር አድርገው አረማውያንን ከነንጉሳቸው አጥምቀዋል::

+በተሰደዱባት ሃገርም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ስም አጠራሩ ይክበርና) እመቤታችንን: ቅዱሳን ሐዋርያትን:
አዕላፍ መላእክትን: በተለይ ደግሞ ቅዱሳኑን ዳዊትን:
ዮሐንስ መጥምቁንና ወንጌላዊውን: ማርቆስን: ዼጥሮስን:
ዻውሎስን አስከትሎ ወርዶ ተገልጦላቸዋል:: በቅዱስ
አንደበቱም የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::

+ታላቁ ቅዱስ መቃርስና ባልንጀራው መቃርዮስ ከ2
ዓመታት ስደትና መከራ በሁዋላ ስደት በወጡባት ዕለት
መልዐኩ ኪሩብ በክንፉ ተሽክሞ ወደ ግብፅ
መልሷቸዋል:: በወቅቱም ጻድቁን ለመቀበል ከ50,000
በላይ የሚሆኑ ልጆቻቸው መነኮሳት በዝማሬ ወጥተዋል::

+ስለ ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ ቅድስና ለመጻፍ መነሳት
በረከቱ ብዙ ነው:: ግን 'ዓባይን በጭልፋ' እንዲሉ አበው
ከብዛቱ የተነሳ የሚዘለቅ አይሆንም::

+ቅዱስ መቃርስ ከዘመናት በላይ በቆየበት የበርሃ
ሕይወቱ:-

1.አባ ብሶይ: አባ ባይሞይ: አባ ሳሙኤል: አባ በብኑዳን
ጨምሮ እርሱን የመሰሉ (ያከሉ) ቅዱሳንን ወልዷል::
2.ለሕይወታችን መንገድ የሚሆኑንን ብዙ ቃላትን
ተናግሯል::
3.ከገዳማት እየወጣ በብዙ ቦታዎች ቅዱስ ወንጌልን
ሰብኩዋል::
4.አጋንንትን ድል ከመንሳት አልፎ እንደ ባሪያ ገዝቷቸዋል::
5.ለዓይንና ጀሮ ድንቅ የሆኑ ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: . .
.

+በእነዚህና ሌሎች ምክንያቶችም ቤተ ክርስቲያን "ርዕሰ
መነኮሳት (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)" ስትል ትጠራዋለች::
በ97 ዓመቱ መጋቢት 27 ቀን ሲያርፍ መላእክት ብቻ
ሳይሆን አጋንንትም ስለ ድል አድራጊነቱ ዘምረውለታል::

=>ታላቁ ቅዱስ መቃርስ ካረፈ በሁዋላ ከክቡር ሥጋው
ብዙ ተአምራት ይታዩ ነበርና የሃገሩ (የሳስዊር) ሰዎች
ሊወስዱት ፈለጉ:: ሳስዊር ማለት ቅዱሱ ተወልዶ
ያደገባት: ወላጆቹ (አብርሃምና ሣራ ይባላሉ) የኖሩባት ቦታ
ናት:: የምትገኘውም ግብጽ ውስጥ ነው::

+በምድረ ግብጽ: በተለይም በገዳመ አስቄጥስ የአባ
መቃርስን ያህል ክቡርና ተወዳጅ የለምና የሃገሩ ሰዎች
የነበራቸው አማራጭ መስረቅ ነበር:: መሥረቅ ኃጢአት
ቢሆንም እነሱ ግን ስለ ፍቅር: አንድም ለበረከት (በረከትን
ሲሹ) አደረጉት::

+ወደ ሳስዊርም ወስደው: ቤተ ክርስቲያን በቅዱሱ ስም
አንጸው በክብር አኖሩት:: በዚያም ለ160 ዓመታት
ተቀመጠ:: በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን ግን ተንባላት
(እስላሞች) መጥተው ቤተ ክርስቲያኑን አጠቁ:: በዚህ
ጊዜም ሕዝቡ የጻድቁን አጽም ይዘው ሸሹ:: በሌላ ቦታም
እንደ ገና በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጸው በዚያ አኖሩት::

+በእነዚህ ሁሉ ዓመታት የመንፈሳዊ አባታቸውን ሥጋ
ያጡት የገዳመ አስቄጥስ ቅዱሳን ያዝኑ ይጸልዩ ነበርና
ልመናቸውን ፈጣሪ ሰማ:: አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት
በነበረበት ዘመን: ከገዳሙ ለሌላ ተግባር ወደ ሳስዊር
የተላኩ አበው ከታላቁ አባት ቤተ ክርስቲያን ሲደርሱ
ሰውነታቸው ታወከ::

+ይዘው ለመውሰድ ሙከራ ቢያደርጉ ሊሳካላቸው
አልቻለም:: ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ደወል
ደውሎ ሕዝቡን ሁሉ ጠርቶ ነበርና:: ሕዝቡና ሃገረ ገዢው
የሆነውን ሲሰሙ "የቅዱሱን ሥጋ ብትነኩ እንገላቹሃለን"
ብለው ሰይፍ: ዱላ: ጐመድና ጦር ይዘው መጡባቸው::

+መነኮሳቱ ግን ባዷቸውን ሊመለሱ አልፈቀዱምና ሌሊቱን
ሲያለቅሱና ሲጸልዩ አደሩ:: መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜም
ታላቁ መቃርስ በግርማ ወርዶ መኮንኑን "ለምን ወደ ልጆቼ
እንዳልሔድ ትከለክለኛለህ?" ሲል በራዕይ ተቆጣው::
በዚህ ምክንያትም መነኮሳቱ የቅዱሱን ሥጋ ተቀበሉ::

+ሕዝቡም በዝማሬና በማሕኅሌት: ከብዙ እንባ ጋር
ሸኟቸው:: ታላቁ መቃሬ ወደ ገዳሙ ሲደርስም ታላቅ ደስታ
ተደረገ:: ቅዱሳን ልጆቹ ከመንፈሳዊ አባታቸው ተባርከው
በክብር አኑረውታል::

=>አምላከ ቅዱሳን የታላቁ ቅዱስ መቃርስን ትሕትናውን:
ትእግስቱንና ቅንነቱን ያድለን:: በበረከቱም ይባርከን::

=>+"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:28-31)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
በዕለተ አርብ የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ በምድር ላይ የተፈጸሙት ታአምራት ምን ምን ናቸው?
Anonymous Quiz
4%
ሀ, መቃብራት ተከፍተዋል
2%
ለ, የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተከፍሏል
4%
ሐ, ከዋክብት እረግፈዋል(ወድቀዋል)
16%
መ, ሀ እና ለ
75%
ሠ, ሁሉም
የክብር ባለቤት የጌታችንን ጎን በጦር ወግቶ ከጎኑ በፈሰሰው ውኃና ደም ታውሮ የነበረውን አንድ አይኑ የበራለት ሰው ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
79%
ለንጊኖስ
11%
አኖሬዎስ
3%
ዮሴፍ
7%
ስምዖን
የክብር ባለቤት የጌታችንን በነጭ ልብስ በሚገንዙበት ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ከእንቅልፉ እንደነቃ ዐይኑን ገልጦ እንደ ሩቅ ብእሲ ዝም ብላችሁ አትገንዙኝ ያላቸው እነማንን ነው?
Anonymous Quiz
8%
ዮሴፍን እና ዮሐንስን
5%
ዮሐንስን እና ጵጥሮስን
79%
ዮሴፍን እና ኒቆዲሞስን
7%
ሁሉንም
የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከተናገራቸው ውስጥ የመጨረሻው ቃል ምን ነበር?
Anonymous Quiz
10%
አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ(ማቴ.27÷46)
69%
ተፈጸመ(ዮሐ.19÷30)
2%
ተጠማሁ(ዮሐ.19÷28)
18%
አባት ሆይ የሚያደርጉት አያቁምና ይቅር በላቸው(ሉቃ.23፥34)
....ከዚህ ሰው የሚወለደው አባቱን ይገድላል ይሰልባል እናቱን ይደፍራል ያገባል ጌታውን ለሞት ይሸጣል ብሎ ስለ አስቆሮቱ ይሁዳ ትንቢት የተናገረው ነብይ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
29%
ነብዩ አሞጽ
25%
ነብዩ ኤርሚያስ
13%
ነብዩ ዳንኤል
33%
ነብዩ ዕንባቆም
ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፦ አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት።
ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን፦ እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።(ዮሐ.19÷26-27) ይህ ደቀ መዝሙር ማን ይባላል!
Anonymous Quiz
33%
ሀ, ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
14%
ለ, ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
17%
ሐ, ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
3%
መ, ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ
29%
ሠ, ሀ እና ለ
4%
ረ, ሁሉም
በመነሣቱ "ክርስቶስ" የሙታን በኵር ሆነ ያለው ሐዋርያ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
24%
ሐዋርያው ጴጥሮስ
20%
ሐዋርያው ዮሐንስ
38%
ሐዋርያው ጳውሎስ
18%
ሐዋርያው ቶማስ
“ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።”👈ያለው ነብይ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
7%
ነብዩ ኤርሚያስ 7፥14
85%
ነብዩ ኢሳይያስ 7፥14
8%
ነብዩ ዳንኤል 7፥14
0%
ነብዩ አብድዩ 7፥14
መጋቢት 29 ስንክሳር ላይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ምን የምትባል ሀገር ደርሶ አስተማረ?
Anonymous Quiz
25%
እስክንድርያ
22%
አልዋሪቆን
34%
አንጾኪያ
19%
ሮም
2024/09/24 13:21:31
Back to Top
HTML Embed Code: