Telegram Web Link
https://youtu.be/nSaBYH8sh5U
‹አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ› ብሎ የመሰከረለትን ክርስቶስ ‹ሰውዬው› ብሎ ጠራው፡፡ ሊቁ ቅዱስ አምብሮስ ‹‹ስለ አምላክነቱ ‹የእግዚአብሔር ልጅ› ብሎ መስክሮለት ስለ ሰውነቱ ግን ‹ሰውዬውን አላውቀውም› ብሎ ካደ›› ሲል አብራርቶታል፡፡ በመለኮቱ አምኖ የመሰከረ ጴጥሮስ አሁን ግን ‹ሰውዬውን አላውቀውም› አለ ፤ ሆኖም ‹ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ደግሞ ከእግዚአብሔር አይደለም› (፩ዮሐ. ፬፥፫) ‹አንተ ዓለት ነህ› ተብሎ የተመሰገነው ታላቁ ዓለት በብርድ ምክንያት በአይሁድ ሎሌዎችና ገረዶች ጥያቄ ተሰነጠቀ፡፡ የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ የተሰጠው ጴጥሮስ በዚያች ምሽት ቁልፉን በእጁ ይዞ ‹በሩን› ግን አላውቀውም አለ፡፡
https://youtu.be/aIdpx29F0Lw
በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡ አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሓ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው? ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሓ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡
በድንግል ትህትና
ዝማሬ ዳዊት
#በድንግል_ትህትና

በድንግል ትህትና አለምተደነቀ /2/
እዉነተኛ መጠጥ ከሆዷ ፈለቀ /2/
ሰዉ የሚድንበት ሮማንና ገዉዝ /2/
ከሆዷ ፈለቀ እንደ ምንጭ እንደወንዝ /2/

#አዝ

ፀጋን ስላደላት የመዉለድ ስጦታ/2/
በፍቅር ሳበችው የፍጥረቱን ጌታ /2/
ሰማያዊዉ አምላክ ከእርሷ ሥጋንነሳ /2/
ፀሐይ ስለወጣ ቀረልን አበሣ /2/

#አዝ

እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር
ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ሥንከብር /2/
ታላላቅ አንስቶች እናቶች ቢባሉም /2/
አምላክን በመዉለድ እርሷን አያህሉም /2/

#አዝ

እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር
ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ሥንከብር /2/
ታላላቅ አንስቶች እናቶች ቢባሉም /2/
አምላክን በመዉለድ ድንግልን አይቀድሙም /2/

#አዝ

እግዚአብሔር ምድርን አየና በመላ /2/
ማርያምን አገኛት ከቤተ-መቅደሱ ከቤቱ ተጥላ
ከመላዕክቱ ጋር እየተጫወተች /2/
የሰማዩን መና እየተመገበች /2/

ሙሉ ዜማው በዚሁ ይወርዳል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
https://youtu.be/4okVYvgpnFo
በእርግጥም እኛ የሰው ልጆች ሁላችንም እግዚአብሔር መልኩን የሳለብን ገንዘቦቹ ነን፡፡ እንደሚታወቀው የንጉሡ የቄሣር መልኩ የታተመው በሳንቲሙ ላይና ከአብራኩ በሚከፈለው ልጁ ላይ ነው፡፡ ሆኖም ሳንቲሙ በላዩ ላይ ያለውን የንጉሥ መልክ ምንነት አያውቅም ፤ ልጁ ግን አባቱን እንደሚመስል ያውቃል፡፡ እኛም በላያችን ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን መልክ ካላወቅን ሳንቲም ብቻ ሆነን እንቀራለን፡፡ ድሪሟ እንደጠፋባት ሴት ሳንቲምም ቆሻሻ ውስጥ ገብተን ልንጠፋ እንችላለን፡፡ በላያችን ያለውን የንጉሡን መልክ ከተረዳን ግን ከሳንቲምነት ወደ ልጅነት ሕይወት ከፍ እንላለን፡፡
https://youtu.be/YqwoLdi63mI
ይህንን የመዝሙር ቻናላችንን subscribe እና share በማድረግ የምንለቃቸውን የተቀናበሩ አዳዲስ መዝሙሮች ይከታተሉ
ጲላጦስ ሆይ! ጥያቄ ጠይቆ መልሱን ሳይሰሙ መውጣት እንዴት ያለ ነገር ነው? ነጻ ላትለቅቀው ነገር ጥቂት ታግሠህ ብትሰማው ኖሮ ምን አለ? ለነገሩ ቆመህ ብትሰማው ኖሮ ‹እውነት ምንድር ነው?› ለሚለው ጥያቄህ ‹እውነትም ሕይወትም መንገድም እኔ ነኝ› ብሎ በመለሰልህ ነበር! (ዮሐ. ፲፥፮) ምስኪኑ ጲላጦስ ለእውነት ‹እውነት ምንድር ነው› ብሎ ጠየቀው፡፡ ምላሹንም ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወጣ፡፡
https://youtu.be/zGTF1BA_4ho
Channel photo updated
https://youtu.be/WObtjC8gamo
ጌታችን በሄሮድስ ፊት አለመናገሩ ብዙ ነገሮችን ያስታውሰናል፡፡ ተአምር የሚሻ ሰው ቢነግሩት መቼ ይሰማል? የምልክት ፍቅር ያለው ሰው ቃሉን የመስማት ፍላጎት የለውም፡፡ ትምህርት ቢሰጠው እንኳን ‹ቶሎ ትምህርቱ አልቆ ወደ ተአምሩ ቢሔዱ ምናለ› ብሎ ይቁነጠነጣል እንጂ የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማበት ትዕግሥት የለውም፡፡ ጌታችን ተአምሩን አይተው ብዙዎች በስሙ ሲያምኑ እንኳን ‹‹በሰው ልብ ያለውን ያውቅ ነበርና አይተማመንባቸውም ነበር›› (ዮሐ. ፪፥፳፭) ስለዚህ ለተአምር ፈላጊው ሄሮድስ በመናገር አልደከመም፡፡
https://youtu.be/POz8dNojdfE
እግዚአብሔር አምላካችን ወዶ እና ፈቅዶ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ለሆነው የነነዌ ጾም አድርሶናል፡፡ ሦስት ቀናት የሚጾመው ይህ ጾም የነነዌን ሕዝብ ከጥፋት መመለስ፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዲሁም የነቢዩ ዮናስን የዋህነት ያስረዳናል፡፡
https://youtu.be/A0ox3F9jZZk
ቤተ ክርስቲያናችን የጌታችን ግርፋት ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጊዜ እንደሆነ ስታስተምር አምስት ሺህ ነው ፣ አራት ሺህ ነው የሚሉም አሉ፡፡[83] ይህን አሰቃቂ ግርፋት በሺህ ለሚቆጠር ጊዜ መገረፉን ግን ሁሉም ሊቃውንትና የታሪክ ሰዎች ተስማምተውበታል፡፡ ጌታችን እጅግ መገረፉን የሚያሳየን መስቀሉን ባሸከሙት ጊዜ በየሥፍራው እስኪወድቅ ድረስ አቅም ማጣቱ ነው፡፡
https://youtu.be/yfgk_JNZ3Xc
የሀገሬ ሰው ከአሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም፤ አንተም አላስቀየምኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ዕርዳኝ፤ ጉልበት የሌለህ ለልጅህ ለሚስትህ ለሃይማኖትህ ስትል በሐዘን ዕርዳኝ፡፡ ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ፤ አልተውህም፡፡ ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም..ዘመቻዬ በጥቅምት ነው እና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ”  
2025/02/24 07:00:47
Back to Top
HTML Embed Code: