"የፈጸምኸውን ኃጢአት ሀብት አድርገህ አታስቀምጠው፤ ሰው ገንዘቡ ሊያደርገው የሚገባው ምርጥ ነገር ቢኖር ኃጢአቶቹን ለእግዚአብሔር በመናዘዝ ራሱን መውቀስ መቻሉ ነውና።"
#ቅዱስ_እንጦንስ
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
#ቅዱስ_እንጦንስ
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
፻፵ (140) የመጽሐፍ ቅዱስ ስሞችና ትርጉማቸው
1 ሩሐማ፦ምሕረት ማለት ነው።
2 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ነው።
3 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው።
4 ኑኃሚን፦ደስታየ ማለት ነው።
5 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
6 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል ማለት ነው።
7 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል ማለይ ነው
8 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
9 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ ማለት ነው።
10 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል ማለት ነው።
11 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል ማለት ነው።
12 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ማለት ነው
13 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
14 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው! ማለት ነው።
15 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።
16 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው።
17 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
18 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ ማለት ነው።
19 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ ማለት ነው።
20 ሣራ፦ልዕልት ማለት ነው።
21 ስምዖን፦ሰማ ማለት ነው።
22 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
23 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
24 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
25 አልዓዛር፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
26 አስቴር፦ኮከብ ማለት ነው፣
27 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ ማለት ነው።
28 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው ማለት ነው።
29 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
30 አብራም፦ታላቅ አባት ማለት ነው።
31 አብርሃም፦የብዙዎች አባት ማለት ነው
32 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው ማለት ነው።
33 አክዐብ፦የአባት ወንድም ማለት ነው።
34 ባሮክ፦ቡሩክ ማለት ነው።
35 አዳም፦መልካሙ ማለት ነው።
36 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
37 ባርቅ፦መብረቅ ማለት ነው።
38 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው ማለት ነው።
39 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል ማለት ነው።
40 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለት ነው።
41 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል ማለት ነው።
42 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት ማለት ነው።
43 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
44 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ ማለት ነው።
45 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው።
46 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት ነው።
47 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል ማለት ነው።
48 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
49 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
50 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው።
51 ኤዶም፦ቀይ ማለት ነው
52 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል ማለት
ነው።
53 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው ማለት ነው።
54 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ ማለት ነው።
55 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ ማለት ነው።
56 ሰሎሞን፦ሰላማዊ ማለት ነው።
57 ኬብሮን፦ኅብረት ማለት ነው
58 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
59 ኤደን፦ደስታ ማለት ነው።
60 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
61 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል ማለት ነው።
62 ይሳኮር፦ ዋጋዬ ማለት ነው
63 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው።
64 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው ማለት ነው።
65 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው።
66 ዮሴፍ፦ይጨምር ማለት ነው።
67 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
68 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
69 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል ማለት ነው።
70 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው ማለት ነው።
71 ምናሴ፦ማስረሻ ማለት ነው።
72 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል ማለት ነው።
73 ዲቦራ፦ንብ ማለት ነው።
74 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው።
75 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው።
76 ጽዮን፦አምባ ማለት ነው።
77 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
78 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
79 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
80 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።
81 ኄራኒ፦ሰላም እና ፍቅር ማለት ነው።
82 ሐና፦ጸጋ ወይም ስጦታ ማለት ነው።
83 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው።
84 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል ማለት ነው።
85 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ ማለት ነው።
86 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና ማለት ነው።
87 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው።
88 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ ማለት ነው።
89 እስጢፋኖስ፦አክሊል ማለት ነው።
90 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ ማለት ነው።
91 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ ማለት ነው።
92 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ ማለት ነው።
93 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል ማለት ነው።
94 ዮርዳኖስ፦ወራጅ ውሃ ማለት ነው።
95 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
96 ገነት፦የአትክልት ስፍራ ማለት ነው።
97 ሰሎሜ፦ሰላም ማለት ነው። ነው።
98 ዲና፦ፈረደ ማለት ነው።
99 ማኑሄ፦እረፍት ማለት ነው።
100 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
101 ራማ፦ከፍታ ማለት ነው።
102 ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
103 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ ማለት ነው።
104 ሕርያቆስ፦ኅሩይ ምርጥ ማለት ነው።
105 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ ማለት ነው።
106 ቶማስ፦ፀሐይ ማለት ነው።
107 ታዴዎስ፦እሸቱ ማለት ነው።(ግብራዊ ትርጓሜ)
108 ማትያስ፦ፀሐይ ወይም ምትክ ማለት ነው።
109 ቀሌምንጦስ፦ግንብ ማለት ነው።
110 አቤል፦በግ ወይም ደመና ማለት ነው።
111 ኖኅ፦ደስታ ማለት ነው።
112 ሴም፦ተሾመ ማለት ነው።
113 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም ይሳቅ ማለት ነው።
114 ሙሴ፦የውሃ ልጅ ማለት ነው
115 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ ማለት ነው።
116 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው ማለት ነው።
117 እሴይ፦ዋጋየ ማለት ነው።
118 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ ማለት ነው።
119 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ ማለት ነው፣
120 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ ማለት ነው።
121 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ ማለት ነው።
122 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው ማለት ነው፣
123 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
124 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ ማለት ነው።
125 ራኄል፦በግዕት ማለት ነው።
126 ዕዝራ፦ረዳቴ ማለት ነው።
127 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች ማለት ነው።
128 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ ማለት ነው።
129 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ ማለት ነው።
130 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ ማለት ነው።
131 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት ማለት ነው።
132 ሶምሶን፦ፀሐይ ማለት ነው።
133 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
134 ማርታ፦እመቤት ማለት ነው።
135 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር ማለት ነው።
136 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው ማለት ነው።
137 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች ማለት ነው።
138 ታዴዎስ፦ተወዳጅ ወይም ፍቁር ማለት ነው።
139 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር ማለት ነው።
140 ሄኖስ፦ሰው ማለት ነው።
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
1 ሩሐማ፦ምሕረት ማለት ነው።
2 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ነው።
3 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው።
4 ኑኃሚን፦ደስታየ ማለት ነው።
5 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
6 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል ማለት ነው።
7 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል ማለይ ነው
8 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
9 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ ማለት ነው።
10 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል ማለት ነው።
11 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል ማለት ነው።
12 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ማለት ነው
13 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
14 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው! ማለት ነው።
15 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።
16 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው።
17 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
18 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ ማለት ነው።
19 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ ማለት ነው።
20 ሣራ፦ልዕልት ማለት ነው።
21 ስምዖን፦ሰማ ማለት ነው።
22 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
23 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
24 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
25 አልዓዛር፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
26 አስቴር፦ኮከብ ማለት ነው፣
27 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ ማለት ነው።
28 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው ማለት ነው።
29 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
30 አብራም፦ታላቅ አባት ማለት ነው።
31 አብርሃም፦የብዙዎች አባት ማለት ነው
32 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው ማለት ነው።
33 አክዐብ፦የአባት ወንድም ማለት ነው።
34 ባሮክ፦ቡሩክ ማለት ነው።
35 አዳም፦መልካሙ ማለት ነው።
36 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
37 ባርቅ፦መብረቅ ማለት ነው።
38 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው ማለት ነው።
39 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል ማለት ነው።
40 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለት ነው።
41 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል ማለት ነው።
42 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት ማለት ነው።
43 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
44 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ ማለት ነው።
45 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው።
46 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት ነው።
47 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል ማለት ነው።
48 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
49 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
50 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው።
51 ኤዶም፦ቀይ ማለት ነው
52 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል ማለት
ነው።
53 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው ማለት ነው።
54 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ ማለት ነው።
55 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ ማለት ነው።
56 ሰሎሞን፦ሰላማዊ ማለት ነው።
57 ኬብሮን፦ኅብረት ማለት ነው
58 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
59 ኤደን፦ደስታ ማለት ነው።
60 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
61 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል ማለት ነው።
62 ይሳኮር፦ ዋጋዬ ማለት ነው
63 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው።
64 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው ማለት ነው።
65 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው።
66 ዮሴፍ፦ይጨምር ማለት ነው።
67 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
68 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
69 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል ማለት ነው።
70 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው ማለት ነው።
71 ምናሴ፦ማስረሻ ማለት ነው።
72 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል ማለት ነው።
73 ዲቦራ፦ንብ ማለት ነው።
74 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው።
75 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው።
76 ጽዮን፦አምባ ማለት ነው።
77 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
78 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
79 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
80 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።
81 ኄራኒ፦ሰላም እና ፍቅር ማለት ነው።
82 ሐና፦ጸጋ ወይም ስጦታ ማለት ነው።
83 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው።
84 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል ማለት ነው።
85 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ ማለት ነው።
86 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና ማለት ነው።
87 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው።
88 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ ማለት ነው።
89 እስጢፋኖስ፦አክሊል ማለት ነው።
90 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ ማለት ነው።
91 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ ማለት ነው።
92 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ ማለት ነው።
93 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል ማለት ነው።
94 ዮርዳኖስ፦ወራጅ ውሃ ማለት ነው።
95 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
96 ገነት፦የአትክልት ስፍራ ማለት ነው።
97 ሰሎሜ፦ሰላም ማለት ነው። ነው።
98 ዲና፦ፈረደ ማለት ነው።
99 ማኑሄ፦እረፍት ማለት ነው።
100 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
101 ራማ፦ከፍታ ማለት ነው።
102 ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
103 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ ማለት ነው።
104 ሕርያቆስ፦ኅሩይ ምርጥ ማለት ነው።
105 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ ማለት ነው።
106 ቶማስ፦ፀሐይ ማለት ነው።
107 ታዴዎስ፦እሸቱ ማለት ነው።(ግብራዊ ትርጓሜ)
108 ማትያስ፦ፀሐይ ወይም ምትክ ማለት ነው።
109 ቀሌምንጦስ፦ግንብ ማለት ነው።
110 አቤል፦በግ ወይም ደመና ማለት ነው።
111 ኖኅ፦ደስታ ማለት ነው።
112 ሴም፦ተሾመ ማለት ነው።
113 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም ይሳቅ ማለት ነው።
114 ሙሴ፦የውሃ ልጅ ማለት ነው
115 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ ማለት ነው።
116 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው ማለት ነው።
117 እሴይ፦ዋጋየ ማለት ነው።
118 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ ማለት ነው።
119 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ ማለት ነው፣
120 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ ማለት ነው።
121 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ ማለት ነው።
122 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው ማለት ነው፣
123 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
124 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ ማለት ነው።
125 ራኄል፦በግዕት ማለት ነው።
126 ዕዝራ፦ረዳቴ ማለት ነው።
127 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች ማለት ነው።
128 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ ማለት ነው።
129 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ ማለት ነው።
130 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ ማለት ነው።
131 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት ማለት ነው።
132 ሶምሶን፦ፀሐይ ማለት ነው።
133 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
134 ማርታ፦እመቤት ማለት ነው።
135 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር ማለት ነው።
136 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው ማለት ነው።
137 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች ማለት ነው።
138 ታዴዎስ፦ተወዳጅ ወይም ፍቁር ማለት ነው።
139 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር ማለት ነው።
140 ሄኖስ፦ሰው ማለት ነው።
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
ወርኃ ጽጌ -
(ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልላክነት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ፡፡
በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡
የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡

አንድ ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡
በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡
"ፈጣሪም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳ እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡"
© ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
***
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡
"ፈጣሪም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳ እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡"
© ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
***
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
መድኃኔዓለም
እጆቹን ለሕማም ዘረጋ። በእርሱ ያመኑ ሕሙማንን ያድን ዘንድ ታመመ።
በፈቃዱ ለሕማም ተሰጠ። ሕሙማንን ያድን ዘንድ ታመመ። የተፍገመገሙትንም ያጸናቸው ዘንድ፣ የተጣሉትን ያገኝ ዘንድ፣ የሞቱትንም ያድን ዘንድ፣ ሞትንም ይሽር ዘንድ፣ የሰይጣንንም ማሠሪያ ይቈርጥ ዘንድ።
የአባቱን ፈቃድ ይፈጽም ዘንድ፣ ሲኦልንም ይረግጥ የሕይወትንም ደጅ ይከፍት ዘንድ።
ለጻድቃን ያበራ ዘንድ፣ ሥርዓትንም ይተክል ዘንድ፣ ጨለማን ያርቅ ዘንድ፣ ሕፃናትንም ያሳድግ ዘንድ፣ ትንሣኤውንም ይገልጥ ዘንድ።
(ቅዳሴ እግዚእ)

ስለ ሌሎች መዳን ከማይጨነቅ ክርስቲያን በላይ ሰነፍ ሰው የለም፡፡ ወዳጄ “እኔ ድኻ ነኝና ይህን ማድረግ አልችልም” የምትል አትኹን፤ ባለ ኹለት ዲናሯ ሴት ትወቅስሃለችና፡፡ ዳግመኛም “ወርቅም ብርም የለኝም” ብሎ የተናገረ ጴጥሮስ ይወቅሰሃልና፡፡
"ምናምንቴ ነኝ" አትበል፤ እንዲህ ስትል ምናምንቴዎቹ ሐዋርያት እንዳይሰሙህ! "እኔ በሽተኛ ነኝ" አትበል፤ በሽተኛው ጢሞቲዎስ ይታዘብሃልና፡፡ ፈጽመህ “እኔ ሌሎች ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ማምጣት አይሆንልኝም” አትበል፡፡ በእውነት ክርስቲያን ከኾንክ ይህን ከማድረግ ይልቅ አለማድረጉ ይከብዳልና፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ እንድትኾን አድርጎ ፈጥሮሃልና ተፈጥሮህን መካድ አይቻልህም፡፡ ክርስቲያን በጨለማ ውስጥ ለሚኖሩ ወንድሞቹ ብርሃኑን ከሚከለክል ይልቅ ፀሐይ ብርሃኗን ብትከለክል ይቀላልና ስለዚህ አልጠቅምም አትበል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"ምናምንቴ ነኝ" አትበል፤ እንዲህ ስትል ምናምንቴዎቹ ሐዋርያት እንዳይሰሙህ! "እኔ በሽተኛ ነኝ" አትበል፤ በሽተኛው ጢሞቲዎስ ይታዘብሃልና፡፡ ፈጽመህ “እኔ ሌሎች ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ማምጣት አይሆንልኝም” አትበል፡፡ በእውነት ክርስቲያን ከኾንክ ይህን ከማድረግ ይልቅ አለማድረጉ ይከብዳልና፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ እንድትኾን አድርጎ ፈጥሮሃልና ተፈጥሮህን መካድ አይቻልህም፡፡ ክርስቲያን በጨለማ ውስጥ ለሚኖሩ ወንድሞቹ ብርሃኑን ከሚከለክል ይልቅ ፀሐይ ብርሃኗን ብትከለክል ይቀላልና ስለዚህ አልጠቅምም አትበል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልሆነ ነገር ደርሶብህ እንደሆነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልሆነ ነገር ወደ በጎ ነገር ይቀየራል፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@Finote_tsidk
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@Finote_tsidk
ወዳጄ ሆይ! ኃጢአተኛ ከኾንህ በደልህን ትናዘዝ ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ጻድቅም ከኾንህ ከጽድቅ (ጎዳና) እንዳትወድቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ቤተ ክርስቲያን የኃጥኡም የጻድቁም ወደብ ናትና፡፡
ኃጢአተኛ ነህን? ተስፋ አትቁረጥ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህም ንስሐ ግባ፡፡ ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” በለው፡፡
እስኪ ንገረኝ! “በድያለሁ” ብለህ ለመናዘዝ ምን ውጣ ውረድ፣ ምን ዓይነት የሕይወት መርሕ፣ ምንስ መከራ አለው? “በድያለሁ” ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው? ምናልባት (ኃጢአት ሠርተህ ሳለ) በደለኛ አይደለሁም የምትል ከኾነ ዲያብሎስም አንተን አይወቅስህም፡፡ (በድያለሁ ብለህ ንስሐ የምትገባ ከኾነ ግን) ይህን (ዲያብሎስ ሊወቅስህ እንደሚችል) አስቀድመህ አስብ፡፡ …
ስለዚህ ክብርህን እንዳይወስድብህ ለምን አትከለክለውም? ለቅጽበት ያህልስ እንኳን የማይተኛ ከሳሽ እንዳለህ ዐውቀህ ለምን በደልህን ተናዝዘሃት አታስወግዳትም?
ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” ብለህ ንገረው፡፡ እኔ ከዚህ ውጪ ከአንተ የምፈልገው ሌላ ምንም ነገር የለኝም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስም፡- “ንግር አንተ ኃጣውኢከ ቅድመ ከመ ትጽደቅ - ትከብር ዘንድ አንተ አስቀድመህ ኃጢአትህን ተናገር” ይላል (ኢሳ.43፡26)፡፡ ስለዚህ ኃጢአትህን ታስወግዳት ዘንድ ተናዘዛት፡፡
ይህን ለማድረግ ውጣ ውረድ የለውም፤ ዙሪያ ጥምጥም የቃላት ድርደራም አያሻህም፤ ገንዘብ መክፈል አያስፈልግህም፤ ወይም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉህም፡፡ አንዲት ቃል ተናገር፤ በደልህን በአንቃዕድዎ አስባት፤ “በድያለሁ” ብለህም ተናዘዛት፡፡

#የኃጥዓን_ወዳጅ
በሰው ልኬት ነውረኛ የሆንን እንደሆነ መውደዳቸው ይቀዘቅዛል ፍቅራቸው ይሸረሸራል። ለዚህ ነው ብዙዎች ልክ እስከሰራን ድረስ የሚወዱን። በምድር ያሉ እና ያለፉ ፍጥረታት ሁሉ ኃጥዓን እንደሆኑ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። ምድር ላይ በስጋ የተመላለስ ግን ኃጢያት የሌለበት አንድ አለ እርሱም እንደ እኛ ሰው የሆነ ነገር ግን እንደ እኛ ኃጥዕ ያልሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
እግዚአብሔር በባህሪው ጻዲቅ ነው። የሰው ልጆች የሆንን እኛ ደግሞ በባህሪያችን ኃጥዓን ነን። ብዞዎቻችን ጥሩ ስንሰራ እግዚአብሔር የሚወደን፤ ስራችን ደግሞ መጥፎ ሲሆን ፍቅሩ ለእኛ የሚቀዘቅዝ ይመስለናል። ነገር ግን እውነታው ይሄ አይደለም እግዚአብሔር ከእኛ በሆነ ምግባር ምክንያትነት ሳይሆን ከራሱ ባህሪ የተነሳ ይወደናል።
በእግዚአብሔር ፊት ማንም ከስራው የተነሳ ተወዳጅ ሊሆን አይችልም ለዚህ ነው እግዚአብሔር የኃጢያተኞች ወዳጅ ነው የምንለው። የእግዚአብሔር መውደዱ ልጁን በመስቀል ላይ በመስቀል ተገልጧል። የዚህ ፍቅር ማብራሪያ ከየቱም በላይ ገናና ነው እናም የማያረጅ ነው። በእግዚአብሔር ተጠላሁ ብላችሁ ይሆን?
አስተውሉ እግዚአብሔር ለአፍታ እንኳን ለእኛ ያለው ፍቅር ቀዝቅዞ አያውቅም። የሱ መውደድ የመለወጥ ስጋት የለበትም። ምናችንንም አይቶ ስላልወደደን ምናችንንም አይቶ አይጠላንም። ሰዎች ጥሩ ስንሆን ወደውን መጥፎ የሆነን ቀን ፍቅራቸው ይናዳል፣ ስንቀርባቸው ስመውን ስንርቃቸው ይነክሱናል።
እግዚአብሔር ግን ጀርባ በሰጠነው ጊዜ እንኳን ጉዳዩ ነው ብሎ ትቶን አያውቅም። ከሱ ውጪ ምንም አማራጭ እንደሌለን እርሱ ስለሚያውቅ ጀርባችንን ሰጥተነው ስንጓዝ እንኳን ከፊታችን ምንም እንቅፋት እንዳይመታን ይጠነቀቅልናል። መመለሳችንን የሚናፍቅ እውነተኛ የኃጥዓን ወዳጅ እግዚአብሔር ነው።
✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት

ተግሣፅ ዘቅዱስ ኤፍሬም
ሕይወትህን በአግባቡ መምራት ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ ትሕትናን ተለማመድ፤ ያለ ትሕትና ተገቢውን ሕይወት መምራት አይቻልም፡፡ ሥራህን ሁሉ በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጀምር፡፡ ያን ጊዜ ፍሬዎችህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይደርሳሉ።
ሰው ከትሕትና ከራቀ ከትክክለኛው መንገድ ርቋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተወ ሰውን ርኵስ መንፈስ እንደ ሳውል ያስጨንቀዋል። የጠላት ወጥመድ በማር የተቀባ ነው፡፡ በማር ጣዕም የሚማረክ ሰው ሐዘንን ሁሉ በያዘ ወጥመድ ይያዛል። ትሕትናን ውደዱ፤ ያን ጊዜ ከሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አትወድቁም፡፡ በትሕትና ክንፍ በበረራችሁ ቁጥር ሁል ጊዜ ከጠላት ወጥመድ በላይ ትሆናላችሁ።
ግልፍተኝነት እንደ በሰበሰ ረጅም ዛፍ ነው፤ ቅርጫፎቹ ሁሉ በቀላሉ የሚሰበሩ ናቸው᎓᎓ አንድ ሰው በወጣባቸው ጊዜ ከወጣበት ከፍታ ወዲያውኑ ይወድቃል፡፡ በመልካም ሐሳብ ልቡናው የበራ ሰው ግን ምስጉን ነው፤ ክብሩም ታላቅና ዘላለማዊ ነው።
እንግዲህ ራሳችንን ለመቆጣጠር እንጣር ያን ጊዜ ኃጢአታችንን እንረዳለን፡፡ ያን ጊዜም ሁል ጊዜ ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን፤ እንደ እባብ በእብሪት መወጠርን እና ራሳችንን ከፍ ከፍ ከማድረግ እንቆጠባለን፡፡ እንግዲህ ራሳችንን ዝቅ ዝቅ ማድረግን እንውደድ፤ በንጹሕ ልቡና ሆነን ምናልባት የተሰጠንን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኃጢአት ከማቆሸሽ እንታደግ ይሆናል።
መልካም ጸሎት በሳግ እና በዕንባ የታጀበ ነው፤ በተለይ ደግሞ በምሥጢር የሚፈስ ዕንባ፣ በልቡናው ከፍታ ሆኖ የሚጸልይ ጌታውን በፊቱ ያያል። እኛ የምንኖረውና የምንሔደው በእርሱ ፈቃድ ነውና። ልቡናችሁ ከጠነከረ በጌታችን ፊት አልቅሱ እርሱ የዕውቀትን ብርሃን ይገልጥላችኋል፤ ወደ እርሱ የሚወስዳችሁ አዲስ ልብንም ይሰጣችኋል።
ንስሓ የገቡና ምሕረት የለመኑ ሰዎች ዕዳቸው ተሰረዘላቸው፤ ነገር ግን ለሠራኸው በደል ምሕረት ስትለምን ወንጀልን እና በደልን፤ በወንድምህም ላይ ቂም መያዝን መተው ይገባሃል። ፍቅር ሳይኖርህ ወደ እግዚአብሔር የምታደርገው ልመና ከተዘጋው በር ውጭ ይቀራል፡፡ የጸሎትን በር የሚከፍት ፍቅር ብቻ ነው፡፡
ወንድምህን ብታስቀይም እግዚአብሐርን ታሳዝናለህ፤ ካንተ ጋር ካለው ከወንድምህ ጋር ሰላምን ከፈጠርህ ግን በሰማይ ካለው ከእግዚአብሔር ጋር ትታረቃለህ፡፡ ወንድምህን በፍቅር ብትቀበለው፣ በደሉንም ይቅር ካልከው እግዚአብሔርን ተቀበልክ፡፡
ስለዚህ በተናደዱ ሰዎች በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ፤ እንግዲህ የተበሳጩትን በማስደሰት እግዚአብሔርን አስደስተው፣ በታሰሩት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን ጎብኘው፣ በተራቡት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አብላው፤ በታረዙ ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አልብሰው፣ መንገደኛን በመቀበል እግዚአብሔርን በአልጋህ ላይ አስተኛው፤ እግሮቹንም እጠበው፣ በማዕድህም አስቀምጠው፣ እንጀራህንም ከእርሱ ጋር ተካፈል፤ ጽዋህንም ስጠው᎓᎓ እርሱ ታላቅ ፍቅሩን አሳይቶሃልና፤ እርሱ ስለ አንተ ብሎ ትበላው ዘንድ ሥጋውን ቆርሶልሃል፣ ትጠጣው ዘንድም ደሙን አፍስሷል።
(ድርሳነ ቅዱስ ኤፍሬም ገጽ 334 - 336 በዲ/ን መዝገቡ ከፍያለው የተተረጎመ)

`` ጥቂት ቃልን የሚናገር ዐዋቂ ነው ፥ መንፈሱም ቀዝቃዛ የሆነ አስተዋይ ነው። ሰነፍ ዝም ቢል ጠቢብ ሆኖ ይቈጠራል፤ ከንፈሩንም የሚቈልፍ ባለአዕምሮ ነው ይባላል። ``
―መፅሐፈ ምሳሌ ፲፯ ፡ ፳፯ ፥ ፪፰
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
―መፅሐፈ ምሳሌ ፲፯ ፡ ፳፯ ፥ ፪፰
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
ቅዱሳን ለምን መከራ ይበዛባቸዋል?
ቅዱሳን ለምን በዓይነትም በብዛትም ልዩ ልዩ መከራዎች እንደሚደርስባቸው ለእናንተ ለምወዳችሁ የምነግራችሁ በቍጥር ስምንት ምክንያቶች አሉኝ፡፡ በመኾኑም በጣም ብዙ ምክንያቶች እያሉ አንድ ምክንያትስ እንኳን እንደሌለ አድርገን ከእንግዲህ ወዲህ በሚከሰቱ ነገሮች ብንሰናከል፣ ብንጠራጠርና ብንታወክ ምንም ይቅርታ ወይም ምሕረት እንደማይደረግልን በማወቅ በታላቅ ማስተዋል ኾነው ኹላቸውም ወደ እኔ ይዙሩ፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር መከራ እንዲርስባቸው የሚፈቅድበት የመጀመሪያው ምክንያት፥ በሚያሠሩአቸው ምግባራትና በሚፈጽሙአቸው ተአምራት በቀላሉ ወደ ድፍረት እንዳይገቡ ነው፡፡
ኹለተኛ ሌሎች ሰዎች [እነዚህ ቅዱሳን] ከሰዋዊ ባሕሪያቸው በላይ ግምት እንዳይሰጡአቸውና “ሰዎች ሳይኾኑ አማልክት ናቸው” ወደሚል ድምዳሜ እንዳይደርሱ ነው፡፡
ሦስተኛ የእግዚአብሔር ኃይል ድል ሲያደርግ፣ ሲያሸንፍ እንዲገለጥና በዚህም በታመሙና በታሰሩ ሰዎች ቃሉ እንዲሰፋ ነው፡፡
አራተኛ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን የሚያገለግሉት ሹመት ሽልማትን ሽተው ሳይኾን እነዚህን የሚያህሉ መከራዎችን እንኳን ተቀብለው ለእግዚአብሔር ያላቸው ፍቅር ቅንጣትም ታህል እንዳልቀነሰ እንዲታወቅና ጽናታቸው እጅግ ደምቆ እንዲታይ ነው፡፡
አምስተኛ ልቡናዎቻችን ስለ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን እንዲያውቁ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ጻድቅና የምግባሩ ሀብት የበዛለት ሰው እልፍ ጊዜ መከራዎችን ሲቀበል ብታይ ምንም እንኳን ወደህና ፈቅደህ ባይኾንም ሊመጣ ስላለው ፍርድ - ማለትም እነዚህ ሰዎች እነዚህን የሚያህሉ መከራዎችን የሚቀበሉት ለራሳቸው ካልኾነ፣ ያለ አንዳች ደመወዝና ክብር ካልኾነ፥ እግዚአብሔርም እንዲህ የሚደክሙትን ያለ አክሊል ሽልማት ይሰድዳቸው ዘንድ እንደዚህ ያለ ነገር ይደርስባቸው ዘንድ ባልፈቀደ ነበር ብለህ - ለማሰብ ትገደዳለህ፡፡ ለዚህ ዕለት ዕለት ለኾነ ድካማቸው ዋጋቸውን የማያሳጣቸው ከኾነ ግን፥ የዚህ ዓለም ሕይወት ካለፈ በኋላ ለአሁኑ ድካማቸው ዐሥበ ፃማቸውን (የትሩፋታቸውን ዋጋ) የሚቀበሉበት የኾነ ጊዜ ሊኖር ግድ ነው፡፡
ስድስተኛ ብዙ ጸዋትወ መከራ የሚደርስባቸው ሰዎች እነዚህ ቅዱሳን ምን ምን መከራ ይደርስባቸው እንደ ነበር አስታውሰው መጽናናትን እንዲያገኙ ነው፡፡
ሰባተኛ የእነዚህን ሰዎች ምግባር ጠቅሰን ስንነግራችሁና እያንዳንዳችሁን “ጳውሎስን ምሰሉት፤ ከጴጥሮስ የሚበልጥ ሥራን ሥሩ” ብለን ስንመክራችሁ ምግባራቸውን እየተመለከታችሁ “እንደ እኛ ሰዎች አልነበሩም” ብላችሁ እነርሱን አብነት ከማድረግ እንዳትሰንፉ ነው፡፡
ስምንተኛ አንድን ሰው የተባረከ ነው ወይም በተቃራኒው ነው ብሎ ለመጥራት አስፈላጊ ኾኖ ሲገኝ ማንን ብሩክ፣ ማንን ደግሞ ኅዙን (ኀዘንተኛ) እና ርጉም አድርገን ልንቈጥር እንደሚገባ’ን እንድናውቅ ነው፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

"ኹሌም በሄድኩበት የምናገረው አንድ ነገር አለኝ"!
"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
ትዳር ፣
ምልኩስና እና
ክህነት ናቸው።
እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።
እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር፣ በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።
ምሳሌ "እንዴት?" ካልን፦
የተከበረ ትዳር የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል።
የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።
በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል።
ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ!
ተምረን ማግባትና፣ ተምረን መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?
እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ? ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ? ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ? ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?
ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ? መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ? ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?
በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ? የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ? ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?
ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ዛሬ ጥቅምት 20 የጻድቁ አባት ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው።
አባ ዮሐንስ ሐፂር ትምህርቶች፦
የጠላቱን ከተማ ለመቆጣጠር የዘመተ ንጉሥ አስቀድሞ የውኃውን መንገድ ይዘጋል፣ የእህሉንም መግቢያ ይይዛል። ያንጊዜ ጠላቶቹ ይራባሉ ይጠማሉ። በመጨረሻም እጃቸውን ይሰጣሉ። የነፍስን ፆር ለማሸነፍም በተመሳሳይ መንገድ መጠቀም ይገባል። አንድ ሰው በጾምና በረኃብ ከጸና የነፍሱ ጠላቶች ይዳከማሉ።
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
እኔ በትልቅ ዋርካ ሥር የተቀመጠንና አራዊት ሊጣሉት የመጣን ሰው እመስላለሁ። ሊቋቋማቸው እንደማይችል ከተረዳ ሸሽቶ ወደ ዛፉ በመውጣት ነፍሱን ያድናል። በእኔም የተፈጸመው ይኼው ነው። በበዓቴ ተቀምጬ ክፉ ሐሳቦች ሊቃወሙኝ ሲመጡ፣ ልቋቋማቸው እንደማልችል ባወቅኹ ጊዜ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ሸሽቼ እመሸጋለሁ። በዚያም ከጠላቶቼ ፍላፃ እድናለሁ።
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
መለወጥ የምትፈልግ ነፍስ በተመለከተ አባ ዮሐንስ እንዲህ አለ፦ በአንዲት ከተማ ውስጥ ብዙ ወዳጆች የነበሯት አንዲት አመንዝራ ሴት ነበረች። ከገዥዎቹ አንዱ ቀረባትና "መልካም ሴት ለመሆን ቃል ግቢልኝና አገባሻለሁ" አላት። እርሷም ቃል ገባችለትና ተጋቡ። ወደ ቤቱም ወሰዳት። የቀድሞ አፍቃሪዎቿ ያቺን ሴት ፈለጓት። እርስ በእርሳቸውም "ያ ልዑል ወደ ቤቱ ወስዷታል፤ ወደ ቤቱ ብንሄድ ይቀጣናል። ነገር ግን በጓሮ በኩል እንሂድ፣ ለእርሷም እናፏጭላት፥ የፉጨቱን ድምጽ ስትሰማ ከድርሱ ወርዳ ወደኛ ትመጣለች፤ በዚህም ያለ ችግር እናገኛታለን" ተባባሉ። ወደ ቤቷም ጓሮ ተጉዘው ያፏጩ ጀመር። እርሷ ግን የፉጨቱን ድምጽ ስትሰማ ጆሮዎቿን ደፈነች። ወደ ውስጣዊው እልፍኝም ገባች። በሩንም ጥርቅም አድርጋ ዘጋች። ይህች ሴት የእኛ ነፍስ ምሳሌ ናት። ወዳጆቿ የተባሉም ፈተናዎቿ ናቸው፣ ገዥ የተባለውም ክርስቶስ ነው፣ እልፍኝ የተባለውም ዘለዓለማዊው ቤት ነው። እነዚህም የሚያፏጩት ክፉዎች አጋንንት ናቸው፣ ነገር ግን ነፍስ ሁልጊዜም በክርስቶስ አምባነት ትሸሸጋለች።
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
አባ ዮሐንስ ልቡናው ከእግዚአብሔር ጋር ስለነበረ ምድራዊ ነገሮችን ይዘነጋ ነበር። አንድ ቀን አንድ ወንድም ቅርጫት ሊወስድ ወደ አባ ዮሐንስ በአት መጣ። አባ ዮሐንስም ምን ፈልጎ እንደሆነ ጠየቀው። ያም ወንድም "ቅርጫት ፈልጌ ነው" አለው። አባ ዮሐንስ ወደ በኣቱ ተመለሰና ዘንግቶት ወደ ሽመና ሥራው አመራ። ጥቂት ቆይቶ ያ ወንድም አንኳኳ አባ ዮሐንስም ወጥቶ "ምን ፈልገህ ነው?" አለው። "ቅርጫት ስጠኝ ብየህ ነበር" ሲል መለሰለት። ተመልሶ ወደ በኣቱ ሲገባ ልቡናው በሰማያዊ ነገር ስለተመሰጠ ዘንግቶት ወደ ሽመና ሥራው እንደገና ገባ። ለሦስተኛ ጊዜ ያ ወንድም ሲያንኳኳ አባ ዮሐንስ ተመልሶ መጣና "ምን ፈልገህ ነው?" አለው። "ቅርጫት ስጠኝ ብየህ ነበር" አለና መለሰለት። አባ ዮሐንስም እጁን ይዞ እየጎተተ ወደ በኣቱ አስገባውና "ቅርጫት ከፈለግህ ያዝና ሂድ፣ በእውነቱ እንዲህ ላሉት ነገሮች እኔ ጊዜ የለኝም" አለው።
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
አንድ ቀን አንድ ሰው ወደ አባ ዮሐንስ ሐጺር በኣት መጣና ሥራውን እያየ ያመሰግነው ጀመር። አባ ዮሐንስ ዝም አለውና ገመድ መሥራቱን ቀጠለ። እንግዳውም እንደገና ወሬውን ቀጠለ ፣ አባ ዮሐንስም ጸጥ አለው። ለሦስተኛ ጊዜ እንግዳው ወሬ ሲያበዛ "አንተ ወደ በኣቴ በመግባትህ እግዚአብሔር ወጥቶ ሄደ" ብሎ ተናገረው።
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
አባ ዮሐንስ እንዲህ አለ፦ "የብሕትውናን ኑሮ በከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበረ። ያ ሰው በከተማው ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውና ባለዝናም ነበር። አንድ አረጋዊ አባት ከማረፉ በፊት ያንን ሰው ሊያየው እንደሚፈለግ ለዚያ ሰው ጥሪ ደረሰው። ያም ሰው በቀን ከተጓዝኩ ሰዎች ስለሚከተሉኝ ለኔ የተለየ ክብር ይሰጡኛል ብሎ አሰበ። ስለዚህም በሌሊት ሰው ሳያየው ለመጓዝ ወሰነ። በመሸ ጊዜም አሁን ማንም አያየኝም ብሎ ተነሣና ጉዞ ጀመረ። ነገር ግን ሁለት መላእክት ታዝዘው ፣ መብራት ይዘው መንገዱን ይመሩት ነበር። ይህንን የተመለከቱ የከተማው ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ ፣ መላ ከተማው ያንን የመላእክት ብርሃን እያየ ከኃላ ተከተለው። ከክብር በሸሸ ቁጥር የበለጠ ክብርን አገኘ። በዚህም "ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል ፤ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ከፍ ይላል።" የሚለው የወንጌል ቃል ተፈጸመ (ሉቃ. ፲፬፥፲፩)።
የአበው በረከት ይደርብን

አንድ ምድራዊ ንጉሥ "ጠላቱን ያልወደደ ሰው በሞት ይቀጣል" ብሎ አዋጅ ቢያውጅ ሁሉም ሰው በአካለ ሥጋ ላለመሞት ሲል ሕጉን ለመጠበቅ የሚፋጠን አይደለምን? ወዮ! ምድራውያን ነገሥታት በሥጋዊ ሞት እንዳይቀጡን ብለን ፈርተን የሚያወጡትን ሕግ ለመፈፀም የምንፋጠን ሆነን ሳለ፥ ለነገሥታት ንጉሥ ለእግዚአብሔር ሕግ አለመታዘዛችን እንደ ምን ያለ ወቀሳ ያመጣብን ይሆን?
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"ብዙ ጊዜ ሰዎች ብልህ ነን እያሉ ይሳሳታሉ። ነገር ግን ብልህ የሚባሉት ብዙ የተማሩና ብዙ ያነበቡ ብዙ የሚናገሩ ብቻ አይደሉም። ይልቁንም ጠቢባን የሚባሉት ጥብብት መጥበቢት ብልህ ነፍስ ያላቸው፤ የእግዚአብሔርንና የሰይጣንን ለይተው ለእግዚአብሔር ሆነው የሚኖሩ ናቸው። ፍጹም ምልዓተ ኃጢአትንና ከጦር ይልቅ የሚወጉ የኃጢአት እሾሀቸውን የነቀሉ ናቸው ጠቢባን።
ጠቢባንስ እግዚአብሔርን ያለጥርጥር በሙሉ ልብ የሚያምኑት፤ አምነውም እንደ ፈቃዱ የተከተሉት፤ በክንፈ ጸጋ ተመስጠው ከልብ በሚወጣ ውዳሴ ከእርሱ ጋር ተዋሕደው የሚኖሩ ናቸው። የነፍሳቸውን ረብሕ ጥቅም አውቀው ዕለት ዕለት ያንን የሚለማመዱ በእውነት ጠቢባን እነዚህ ናቸው።"
(ቅዱስ አባ እንጦንስ)
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
ጠቢባንስ እግዚአብሔርን ያለጥርጥር በሙሉ ልብ የሚያምኑት፤ አምነውም እንደ ፈቃዱ የተከተሉት፤ በክንፈ ጸጋ ተመስጠው ከልብ በሚወጣ ውዳሴ ከእርሱ ጋር ተዋሕደው የሚኖሩ ናቸው። የነፍሳቸውን ረብሕ ጥቅም አውቀው ዕለት ዕለት ያንን የሚለማመዱ በእውነት ጠቢባን እነዚህ ናቸው።"
(ቅዱስ አባ እንጦንስ)
🇯 🇴 🇮 🇳 ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
ጀግና ከሆንክ ምን ይላል መሰላችሁ ቅዱስ ዩሃንስ አፈወርቅ "ጀግና ከሆንህ በራስህ ላይ ጦርነት አውጅበት" መቆጣት ከፈለክ መጀመርያ በራስህ ላይ ተቆጣ!። ልክስክስነትህን፣ ስግብግብነትህን፣ ክፋትህን፣ ዝርክርክነትህን፣ ዘማዊነትህን ተቆጣው!። ስንፍንሃን ተቆጣው!። በዲያብሎስ ላይ ጦርነት ክፈትበት። ከዘላለም እርስትህ ለነጠቀ፤ ከልጅነትህ ለሚያዋርድህ፤ ከፈጣሪህ ለሚያጣላህ፤ እግዚአብሔርን ያህል አባት፣ ገነትህን ያህል ቦታ፣ ልጅነትህን ያህል ተድላ ደስታ ከነጠቀህና ከክብርህ ካዋረደ በሱ ላይ መጀመርያ ተነስ!።
እውነቴን ልንገራችሁ ሰው መጀመርያ ከእራሱ እና ከዲያብሎስ ጋር ጦርነት ከገጠመ በአለም ላይ ያሉ ጦርነቶች ሁሉ ይጠፋሉ..
🗣️ 𝑨𝒃𝒃𝒂 𝑮𝒆𝒃𝒓𝒆 𝑲𝒊𝒅𝒂𝒏