Telegram Web Link
አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ቆመና "ጌታ ሆይ ተመልከት እጆቼ ንፁሃን ናቸው። ደም አላፈሰሱም የሰው ገንዘብ አልቀሙም" አለ እግዚአብሔርም መለሰለት "ልጄ ሆይ! አዎ እጆችህ ንፁሃን ናቸው ግን ባዶዎች ናቸው" አለው ይባላል።

ያልገደለ እጅ ግን ያላዳነ፣ ያልሰረቀ አጅ ግን ያልመፀወተ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ የለውም። እውነተኛው መልካምነት ክፋ አለማድረግ ብቻ ሳይሆን መልካም ማድረግም ነው። የሚጎዳንን መተው ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎች ጥቅም መድከምም ነው።

@Finote_tsidk
@Finote_tsidk
#እንደ_ኃጢአት_አዋራጅ_የለም

እንደ ኃጢአት አዋራጅ የለም፡፡ ኃጢአትን የሚያደርግ ሰው በሐፍረት ካባ ብቻ የሚከናነብ አይደለም፤ አስቀድሞ ከነበረው ማስተዋልና ማገናዘብም ይዋረዳል እንጂ፡፡ ይህንንም ለመረዳት የአዳም የቀድሞ ክብሩን ማሰብ እንቸችላለን፡፡ ዳግመኛም ኃጢአትን ከሠራ በኋላ ያገኘውን ውርደት እንመልከተው፡፡ “በሰርክ ጊዜ ጌታ በገነት ውስጥ ድምፀ ሰናኮ ብእሲ እያሰማ ወደነርሱ ሲመጣ በሰሙ ጊዜ አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር ፊት በገነት ዕንጨት መካስከል ተሰወሩ” (ዘፍ.3፥8)፡፡ በዚህስ አዳም እንደ ምን ባለ ውርደት እንደ ተያዘ ታስተውላላችሁን? ምሉእ በኩለሄ ከኾነው፣ ፍጥረታትን ካለ መኖር ወደ መኖር ካመጣው፤ የተሰወረውን ኹሉ ከሚያውቀው፤ የሰውን ልቡና የፈጠረና በኀልዮ የሠሩትን ዐውቆ ከሚፈርደው (መዝ.33፥15)፤ ልብ ያሰበውን ኩላሊት ያጤሰውን መርምሮ ከሚያውቀው (መዝ.7፥9)፤ ልቡናችን ያሰበውን ከሚያውቀው (መዝ.44፥21) ከእግዚአብሔር ሊሸሸግ መውደዱ ከማወቅ ወደ ድንቁርና ከክብር ወደ ኃሣር እንደ ኼደ ያመለክታልነ፡፡ እኛም ኃጢአት ስንሠራ እንደዚህ ነው፡፡ መሸሸግ ባንችል እንኳን መሰወርን እንሻለን፡፡ ይህን ማድረጋችንም በኃጢአታችን ምክንያት ክብራችን እንደ ምን እንዳጣን፤ ሐፍረታችንን መሸፈንም እንደ ምን እንዳቃተን ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን የሠራ ሰው እንኳንስ በረኻ በኾነች በዚህች ምድር በገነት መካከልም መደበቅ አይችልም፡፡

("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 81 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

╔═══|◉❖•❀•❖◉|═══╗
      @Finote_tsidk
╚═══|◉❖•❀•❖◉|═══╝
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡ በሌላ አገላለጽ ብነግራችኁ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ጾመ ሐዋርያት (ሰኔ ጸም) ነገ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም
(JUNE 23/2024 G.C) ይገባል፡፡

@Finote_tsidk @Finote_tsidk
✝️በዓለ ጰራቅሊጦስ✝️

ጰራቅሊጦስ የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ሲኾን፣
ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ፲፪ቱ ደቀ መዛሙርት፣ ፸፪ቱ አርድእት፣ ፭፻ው ባልንጀሮችና ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት በኢሩሳሌም ከተማ በአንድነት ኾነው ለጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ በሚያርግበት ጊዜም *እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤* /ሉቃ. ፳፬፥፵፱/ ሲል ለሐዋርያቱ በገባላቸው ቃል መሠረት ባረገ በ፲ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡
በሐዋርያት ሥራ እንደ ተጻፈው በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጣና የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም እንደ እሳት የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በኹሉም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ኹላቸውም መንፈስ ቅዱስን ከተሞሉ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ኹሉ መናገር ጀመሩ /ሐዋ.፪፥፩-፬/፡፡ ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ጰራቅሊጦስ ይባላል፡፡
ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጎልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ኾነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሰን።

♜ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♔ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♜
@Finote_tsidk @Finote_tsidk
♜ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♔ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♜
ጰራቅሊጦስ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን ነው:: በትንሣኤው ተፀንሳ እስከ ዕርገቱ ድረስ ለዐርባ ቀናት ተሥዕሎተ መልክእ (Organ formation) የተፈጸመላት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የተወለደችበት ቀን ነው:: እግዚአብሔር በባቢሎን ሜዳ የበተነውን ቋንቋ የሰበሰበበትና እንዱ የሌላውን እንዳይሰማው እንደባልቀው ያሉ ሥሉስ ቅዱስ አንዱ የሌላውን እንዲሰማ ያደረጉበት ዕለት ዛሬ ነው:: ሰው ወደ ፈጣሪ ግንብ ሰርቶ በትዕቢት ለመውጣት ሲሞክር የወረደው መቅሠፍት ዛሬ በትሕትና ፈጣሪን ሲጠባበቁ ለነበሩ ሐዋርያት ፈጣሪ ራሱ ያለ ግንብ ወርዶ ራሱን የገለጠበት ዕለት ነው::

ዛሬ እስራኤል ከግብፅ በወጡ በሃምሳኛው ቀን በሲናን ተራራ የወረደው እሳትና በጽላት ላይ የተጻፈው ሕግ የተሠጠበት ቀን ነው:: ፋሲካችን ክርስቶስ በታረደ በሃምሳኛው ቀን በሐዲስ ኪዳንዋ ደብረ ሲና በጽርሐ ጽዮን በእሳት አምሳል መንፈስ ቅዱስ ወርዶ በሐዋርያት በልባቸው ጽላት ቃሉን የጻፈበት ቀን ነው:: በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ በርግብ አምሳል በትሕትና የወረደው መንፈስ ቅዱስ ዛሬ በእሳትና በነፋስ አምሳል ወደ ሐዋርያቱ የወረደው ዛሬ ነው:: ርግብ ሆኖ የወረደው ሊመሰክርለት እንጂ ኃይል ሊሠጠው ስላልነበረ ነው:: ዛሬ ግን ለሐዋርያቱ ኃይል ሊሠጣቸው ፈልጎ በእሳትና በነፋስ ኃይሉን ገለጠ::

መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ በዚያ መገኘት ከፈለጋችሁ በቅዳሴው መካከል ተገኙ:: ካህኑን "ይህች ቀን ምን የምታስፈራ ናት? ይህች ቀን ምን የምታስጨንቅ ናት? መንፈስ ቅዱስ ከመልዕልተ ሰማያት የሚወርድባት?" ሲል ታገኙታላችሁ:: ኢሳይያስ ያየውን ራእይ ማየት ከፈለጋችሁ ወደ ቅዳሴ ገስግሱ:: ሱራፊ በጉጠት ፍሕም ይዞ ኃጢአታችሁን የሚተኩስበትን ደሙን ለመቀበል ከፈለጋችሁ ወደ ቅዳሴው ገስግሱ:: "ፈኑ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ" እያላችሁ የምታዜሙበት ዕለታዊው ጰራቅሊጦስ ቅዳሴው ላይ ተገኙ:: በአዲስ ቋንቋ ትናገራላችሁ:: የእናንተ ቋንቋ ሳይቀየር የሁሉም ቋንቋ ተናጋሪ ሰምቶ ይረዳችሁዋል::

ለሐዋርያት የተሠጠኸውን ሠጥተኸን ከሐዋርያት ያገኘኸውን ያላገኘህብን ሆይ ቅዱስ መንፈስህ ከእኛ አትውሰድብን:: የማዳንህን ደስታ ሥጠን:: በእሺታም መንፈስ ደግፈን::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 16 2016 ዓ.ም.

#share

╔═══|◉❖•❀•❖◉|═══╗
      @Finote_tsidk
╚═══|◉❖•❀•❖◉|═══╝
#ሰው_እንደ_ዘር_ነው

አባቶቻችን ሊቃውንት ሰው እንደ ዘር ነው ይላሉ። ሰው እንደ ዘር ነው ማለት ዘር ተዘርቶ የሚያድገው በሁለት መሠረታዊ ነገር ነው። በብርድ እና በጸሐይ። ዘር ዝናምና ጸሐይ ያስፈልገዋል። ዝናም ብቻ ከሆነ ሽባ ይሆናል ጸሐይ ብቻም ከሆነ ይደርቃል።

ሰውም እንደ ዝናሙ የእግዚአብሔር ቸርነት ያስፈልገዋል፤ እንደ ጸሐዩም መከራ ያስፈልገዋል። ዘር በዝናሙ እየለዘበ፣ በጸሐዩ እየበሰለ እንደሚያድገው ሁሉ ሰውም በመከራ እየጠነከረ በተስፋና በእግዚአብሔር ቸርነት እየተጽናና ያድጋል።

ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ቸርነት ብቻ ከሆነ የሚያስበው ሽባ ይሆናል። መከራ ባገኘው ጊዜ ወዲያው ተስፋ ይቆርጣል። ሃይማኖትን ሊክድ ይችላል። መከራ ብቻ ከሆነበት ደግሞ ወዲያው ደግሞ እንደዚሁ ተስፋ ቆርጦ ሊሠበር ይችላል።

ስለዚህ ዘር ዝናምና ጸሐይ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ሰውም መከራና የእግዚአብሔር ቸርነት ያስፈልገዋል።

(#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን)

@Finote_tsidk
#ዘጠኙስ_ወዴት_አሉ ?

አስር ሰዎች ከኃጢአታቸው ለመንጻት በጌታ ፊት ቀረቡ እንደመሻታቸው ሁሉም ከኃጢአታቸው ነጹ ነገር ግን መፈወሱን አውቆ እግዚአብሔር ሊያከብር የቻለው አንዱ ብቻ ነው። ጌታም ዘጠኙስ ወዴት አሉ? በማለት ተናገረ።

ይህን ጽሑፍ በማንበብ ላይ ያለህ ወንድሜ ወይም እህቴ አንተ ከዬተኛው ወገን ነህ? ምስጋናውን ከበሉ ከዘጠኙ ወይስ እግዚአብሔርን እንዳከበረው እንደ አንዱ? እግዚአብሔር በባህሪው ምስጉን ነውና የሰው ምስጋና ምንም ከፍ አያደርገውም ምንምም ደግሞ ዝቅ አያደርገውም።

ምክንያቱም እርሱ እግዚአብሔር ያለሿዋሚ የነገሰ ያለምርጫ የሚገዛ ጌታ ነውና። ነገር ግን እግዚአብሔር  ባደረገላችሁ ነገር ምን ያኽል ጊዜ አመሰገናችሁት? ምን ስጥቶኝ ላመስግነው እንዳማትሉኝ ተስፋ አለኝ።

እስኪ ትንሽ የሚመስለውን ነገር ግን ያላችሁን ነገር አስተውሉ። እና እግዚአብሔርን ለማመስገን በቂ ምክንያት የላችሁም? እግዚአብሔር ስለምፈጠሩ፣ የውስጥ እረፍት ሰጪ በመሆኑ፣ በሰላም ምሽትን የሚያነጋ በመሆኑ፣ ከዘላለም ሞት አዳኝ በመሆኑ፣ ታምኖ የሚያኖር በመሆኑ፣ አቅፎ የሚያባብል በመሆኑ፣ ከክፉ ፍላጻ የሚታደግ በመሆኑ፣ ታማኝ እረኛ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባዋል።

ሰው አጥታችሁ እግዚአብሔር ደርሶላችሁ እንደሆነ አመስግኑት፣ በችግር ውስጥ ጠርታችሁት አለው ብሎ ከሆነ አመስግኑት፣ በሀዘን ምጥ ውስጥ ሆናችሁ አይዞን ብሏችሁ እንደ ሆነ አመስግኑት፣ አይነጋልኝም ያላችሁትን መሽት አንግቶ በህይወት አቁሟችሁ እንደሆነ ክበር በሉት፣ አበቃ ብላችሁ እርሱ ግን አይ ብሎ እንደ አዲስ ነገሮችን አስተካክሎላችሁ እንደሆነ ተመስገን በሉት።

የተቆረጠ የመሰለ ተስፋችሁን ቀጥሎት እንደሆ አክብሩት፣ ተቋጨ ያላችሁትን ዘመን አድሶላችሁ እንደሆነ ከፍ በል በሉህ፣ ለቅሷችሁን በደስታ ቀይሮት እንደሆነ አመስገኑት፣ ሞታችሁን በህይወት ተክቶት እንደሆነ ተመስገን በሉት፣ እርዳኝ ብላችሁት አመት ረድቷችሁ እንደሆነ ለእርዳታው እውቅና ስጡ የምስጋናን ነዶ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ።

ምንም ያልሰጣችሁ ቢመስልም እስኪ ምን እንደ ሰጣችሁ አስተውሉ። እግዚአብሔር ምን ሰጥቶኝ ላመስግነው የሚል ሰው ሰምቼ እንደማውቅ አስታውሳለሁ። ጠላት እግዚአብሔር እንዳታመሰግኑ ሊያደርጋችሁ ሲፈልግ እግዚአብሔር በህይወታችሁ ያዳረገውን እንዳታስተውሉ ያደርጋል። ይህም አመስገኝ እንዳትሆኑ ያደርጋችኋል።

የእግዚአብሔር ስራው በህይወታችሁ ታውቆም እንደ ዘጠኙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ምስጋና መሸሸግ ደግሞ ሌላ ትልቅ ችግር ነው። ለአስተዋይ ትውልድ የምስጋናው ርዕስ እልፍ ነው። ምስጋናውን አትሸሽጉ፣ ተደርጎለት እንዳልተደረገለት፣ ተስጥቶት እንዳልተሰጠው፣ ተርፎ እንዳልተረፈ፣ እጅግ ተረድቶ ምንም እንዳልተረዳ አንሁን።

ጸሎት
እግዚአብሔር ሆይ ባደረክልን ነገር ሁሉ ምስጋናህን በልተን እና ሸሽገን እንደሆነ ምህረትህ እንለምሃለን። ያልተሸሸገ ምስጋናችን ለአንተ ይሁን ለምትረዳን ምስጋና ይድረስህ፣ አናልፈውም ያልነውን በአንተ አልፈናልና እናመሰግንሃለን እናከብርህማለን። አቤቱ አምላካችን ሆይ ምስጋና ለአንተ ይሁን። በስራህ ልክ ልናመሰግንህ ባንችልም ከምስጋናህ አንደባችን እንዳይባዝን በጸጋህ ከልለን። አሜን

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 ስኔ 20  2016 ዓ.ም ተጻፈ

@Finote_tsidk
“ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው፡፡ ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ የሚመጣውን ደስታና ሰላም አትሻ፤ ለዚህኛው ኑሮ ሙትና ለእግዚአብሔር ሕያው ሁን፤ ለእግዚአብሔር ቃል የገባኸውን አትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል፡፡ ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፤ ተጠማ፥ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔር የምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታድናት ዘንድ፡፡”

(አባ እንጦንስ)

@Finote_tsidk
"ነገር ኹሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ! !!

አንድ አንዴ በሕይወታችን ምንም የማይጠቅሙ ነገሮችን ልንመርጥ እንችላለን ።የሚያስፈልገንና የማይጠቅመን ግን መንፈስ ቅዱስ ሲመርጥልን  ነው።"

አደጋና ስጋት ፡በሽታና ስቃይ ፡እጦትና ችግር ፡ራብና ጥማት ፡ኅዘንና ትካዜ ፡የሌለው ሕይወት እጅግ ጠቃሜ እንደ ኮነ አድርገን እናስባለን ነገር ግን ይህን የሌለው ሕይወት ኹሉ ጠቃሜ ላይኾን ይችላል ።

እንደ ራሳችን ሓሳብ ሳይኾን እንደ እግዚአብሔር ሓሳብ ስንጓዝ ግን ነገር ኹሉ ለበጎ ነው ። ነገር ኹሉ ሲባልም በእኛ እይታ በጎ ነው የምንለው ብቻ አይደለም ፡ ክፉ ነው የምንለውም ጭምር እንጂ።እንደ እግዚአብሔር ሓሳብ ስሆን ማግኘትም ማጣትም ፡ጤንነትም በሽታም ለበጎ ነው።

እግዚአብሔር ለእኛ መልካም የሚያደርግልን በጎ ነው ብለን በምናስበው ነገር ብቻ አይደለም። እጅግም ክፉና አስቸጋሪ መስለው ከሚታዩን ኹኔታዎችም ለእኛ ለልጆቹ እጅግ የሚደንቅና በጎ ነገርን ማድረግ ይችልበታል።

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 

🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌
@Finote_tsidk @Finote_tsidk @Finote_tsidk
@Finote_tsidk @Finote_tsidk @Finote_tsidk
﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌
አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር። ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ። ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም። ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለህ። ይህች የንስሓ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሓም ትመራሃለች።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"ሰውን ስትረዳው ጎሳውን፣ ጾታውን፣ ሃይማኖቱን ብለህ አትርዳው ስለ ክርስቶስ ስም ብለህ እርዳው።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@Finote_tsidk
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ትዕቢት የነበረንን መልካም ምግባር ሁሉ የሚያሳምም ደግሞም የሚገድል ክፋ ደዌ ነው፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

@finote_tsidk
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ” ማቴ.10÷16

እባብ ራሱን (ጭንቅላቱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን ወይም ሰውነትህን ወይም የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን!

አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትሔድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ ይመልስልሃል፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃል፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ ኢዮብ ዕራቁቱን ኾኖ በአመድ ላይ ከሞት እልፍ ጊዜ የሚከፋ ሕይወትን እየመራ የተቀመጠ አይደለምን? ነገር ግን ሃይማኖቱን ስላልጣለ አስቀድሞ የነበረው ኹሉ እጅግ በዝቶ ተመልሶለታል፤ ጤናውና ውብ የኾነ ሰውነቱ፣ ልጆችን፣ ሀብቱን፣ ከዚህ ኹሉ የሚበልጥ ደግሞ አክሊለ ትዕግሥትን አግኝቷል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)

@finote_tsidk
@finote_tsidk
#ይቅር_በለኝ ...

የምህረት ባለቤት፣ የይቅርታ ምንጩ፣ የርህራሄ ባህሩ፣ የአዛኝነት ልኩ፣ የተቀባይነት ሚዛኑ እግዚአብሔር ሆይ ምህረትህ ጥላ ይሁነኝ። አንተን በመበደል መትጋቴን ይቅር በል። አንተን በማሳዘን መዝለቄን እኔም ጠልቼዋለሁና ምህረት አድርግልኝ።

አንተን አውቄ እንዴት እንዲህ እኖራለሁ? የአንተ ልጅ መሆኔ በግብሬ እንዲገልጥ አቅም ሁነኝ። የኔ ጌታ እኔ ምንም አቅም እንደሌለኝ ገብቶኛል አቅሜ አንተ ሁን። በራሴ ስጋ ስለለበስኩኝ ይህም ስጋ የኃጢአት ዝንባሌ በውስጡ በመኖሩ ከስጋዬ ጋር ትግል ገጥሜ አንተን እንዳላሳዝንህ ደግፈኝ። አንተን የሚያከብር የአንተ ጸጋ ይብዛልኝ።

ስጋ ለእግዚአብሔር ህግ መገዛት ተስኖታል ተብሎ በቃልህ እንደተጻፈው በስጋ ሳይሆን በመንፈስ ተገዝቼልህ ስጋዬ ደግሞ እንዲታዘዝህ እርዳኝ። ሁሌ ለነፍሴ ማድላት እንዲሆንልኝና ስጋዬን መጎሰም የምችልበት አቅም የምትሰጠኝ ጌታዬ ጸጋህን በውስጤ አፍስስልኝ።

ለቁጥር ለሚታክቱ ጊዜያት በአንተ ላይ መሸፈቴን አውቀዋለሁ፣ ብዙ ማጥፋቴን እና መበደሌን ተረድቻለሁ። ይቅር እንድትለኝ በፊትህ ቀርቢያለሁኝና የማይነጥፍ የምህረት ባለቤት እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለኝ። 

አንተን በድዬ ደስ ቢለኝ ምን ይርባኛል? አንተ በእኔ ተከፍተህ እኔ በድሎት ነኝ ብል ምንስ ይጠቅመኛል? ለአንተ ጀርባ ሰጥቼህ ፊቴ ለሌላው ቢገለጥ ትርፌ ምንድን ነው? ምን ይጠቅመኛል አንተ ካሳዘንኩኝ? ምንስ ይረበኛል ፍቃድህን አልፌ በፍቃዴ ብራመድ? ምንስ እረብ አገኛለሁ ከምትጠቅመኝ ከአንተ ሸሽቼ የስጋ መሻቴን ብከተል? ..... ምንም ምንም አልጠቀምም። ምንም ....

ልለይ እስኪ ከማይረባኝ አልሂድ በቃ ትላንት በሄድኩበት ጎዳና። በሰጠኸኝ በአዲሱ ቀን እኔም አዲስ ሆኜ መኖር እንድችል በጸጋህ ደግፈኝ። ትላንቴን ይቅር ልትል ታማኝ የሆንከው አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ በማይበጠስ የምህረት ሰንሰለት አጥረህ የምታኖረኝ አንተ ነህና ዛሬዬን በምክርህ እንድኖር ምህረትህን አብዛልኝ።

አድርጌው የማዝንበት ነገር አንተን አያከብርምና ክብርህ በሌለበት ህይወት ውስጥ እንዳልገኝ እግሮቼን እና ሃሳቤን ጠብቅ።  የማላዝንበት ነገር በማድረግ እንድኖር እና ልክ ላልሆነ ነገር ተሰልፌ ልክ እንደሆንኩኝ እንዳይሰማኝ ማስተዋልን አድለኝ።

ከላይ ስታይ መንፈሳዊ ውስጤ ሲታይ አለማዊ አልሁን፣ ሰዎች ሲያዩኝ ጥሩ ነገሬ አንተ ስታየኝ ግን መጥፎ ሆኜ አልገኝ፣ በአደባባይ መልካም በጓዳዬ መጥፎ አልሁን፣  ከጸጋህ የተነሳ አንተን በመምሰል ልምምድ ውስጥ አሳድገኝ። 

“እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤” 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥6

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም ተጻፈ

  ➟ @finote_tsidk
  ➟  @finote_tsidk
#ልንናደድ_የሚገባን_ማን_ላይ_ነው?

ብዙ ኃጢአቶችንና ወንጀሎችን የሠራ አንድ ሰው ለሠራው ኃጢአትና ወንጀል ሳይቀጣ ሲቀር አይተን ብዙዎቻችን እንበሳጫለን፡፡ ያ ሰው እንዲጠየቅና እንዲቀጣ እንፈልጋለን፡፡ ይህ ሳይኾን ከቀረ ግን ቅር እንሰኛለን፤ እንናደዳለን፡፡

እንዲህ የምንኾነው ግን የገዛ ራሳችንን ግብር ስለማንመለከት ነው፡፡ መበሳጨትና መናደድ ቅርም መሰኘት የሚገባን በገዛ ራሳችን ላይ ነውና፡፡ እያንዳንዳችን ለራሳችን እንዲህ ብለን ልንጠይቅ ይገባናል፦ "በሌሎች ሰዎች ላይ ስንት በደል ፈጸምሁ? ለዚህ በደሌስ ስንቴ ሳልቀጣ ቀረሁ?"

በራሳችን ላይ ብዙ ምሳሌዎችን እንደምናገኝ ጥርጥር የለውም፡፡ ይህን ማወቃችን ደግሞ በሌሎች ሰዎች ላይ የተቆጣነው ቁጣና የተበሳጨነው ብስጭት እንደ ጢስ ተኖ እንደ ትቢያ በንኖ እንዲጠፋ ያደርጓል፡፡ ከዚህም በላይ ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር እንድናዞር ስለ በደልነውም በደል ይቅርታንና ቸርነትን እንድንለምን ያደርገናል፡፡

እንዲያውም እኛ በበደልነው በደልና ሌሎች ሰዎች በሠሩት ኃጢአት ልዩነቱን እናስተውለው ይኾናል፡፡ ምናልባት የእኛ በደል የተሰወረና ለሌሎች ሰዎች የማይታይ ሕቡዕ ይኾናል፤ በአንጻሩ ደግሞ የሌሎች ሰዎች ኃጢአት በግልጽ የሚታይ ይኾናል፡፡

ታዲያ በዚህ ኹኔታ የእኛ በደል ንኡስ፥ የሌሎች ሰዎች ኃጢአት ግን ዐቢይ እንደ ኾነ ልናስብ ይገባናልን? በጭራሽ! ምክንያቱም በስውር የሚሠ'ራና ሌላ ሰው የማያየው በደል ብዙውን ጊዜ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ስርቆትንና ቀማኛነትን የመሳሰሉ በግልጽ የሚታዩ ኃጢአቶች ኃጢአት መኾናቸው በቀላሉ ይታወቃሉ፡፡ መታወቃቸው ብቻም ሳይኾን በቀላሉ ንስሐ ሊገባባቸውና ሊወገዱ የሚችሉ ናቸው፡፡ ውሸትን፣ ሐሜትንና በስውር ማታለልን የመሳሰሉ በስዉር የሚሠሩ በደሎች ግን በደል መኾናቸውን ለማወቅም ስለ እነዚህ ንስሐ ገብቶ ለማስወገድም እጅግ ክቡዳን ናቸው፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች ገጽ 98-99)

@finote_tsidk
2024/09/29 03:32:39
Back to Top
HTML Embed Code: