Telegram Web Link
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ፈረስ የሚጋልብ ሰው ልጓሙን በአግባቡ ካልያዘው በቀር ፈረሱም ጋላቢውም ይጎዳሉ፡፡ አንድ እባብ የነደፈው ሰው ባለመድኃኒቶችን አግኝቶ መርዙ ወደ ሰውነቱ ኹሉ እንዳይሰራጭ ካላደረገ በቀር ወደ ሞት ሊደርስ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ትንሽ ቁስል በጊዜው ጊዜ ካልታከሙት በቀር ሰፍቶና ተስፋፍቶ ትልቅ ቁስል ወደ መኾን ያድጋል፡፡

በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድም እንደዚህ ነው፡፡ የኃጢአት ቁስል የሚሰፋው ችላ ሲባል ነው፡፡ ገና ትንሽ ነው በሚባልበት ደረጃ ካላራቅነው በቀር ነገ ከነገ ወዲያ ትልቅ ቁስለ ነፍስ ይኾናል፡፡

ተመልከቱ! ዛሬ ላለመቈጣት የሚታገል ሰው ነገ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴን አይዘይድም፡፡ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴ ካልዘየደም ብዙ ባልንጀሮች ይኖሩታል፡፡ ብዙ ባልንጀሮች ካሉት የሚጠላቸውም የሚጠሉትም ሰዎች አይኖሩም፡፡ ባልንጀራ እንጂ ጠላት የሌለው ሰውም የምግባር ኹሉ ፍጻሜ የኾነውን ፍቅር ገንዘብ ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ተወዳጅ ሆይ! ወደዚህ ምግባር ታድግ ዘንድ ወደዚህ እንዳታድግ የሚያደርጉህን ጥቃቅን ኃጢአቶችን ከአንተ አርቅ፡፡ ሰፍቶ ተስፋፍቶ ነገ እንዳይቸግርህ ዛሬ በእንጭጩ እያለ ችላ አትበለው፡፡

ይሁዳ ገና የገንዘብ ፍቅር ደረጃ ላይ እያለ ራሱን ቢመረምርና ይህን ለማራቅ ቢጥር ኖሮ በኋላ ከተሰበሰበው ገንዘብ ወደ መስረቅ ባላደገ ነበር፡፡ ገና ከመጀመሪያው ደረጃ እያለ ችላ ባይል ኖሮ የኃጢአት ኹሉ ራስ የኾነው ኃጢአት ወደ መፈጸም ባልደረሰ ነበር፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደዚህ ልናደርግ እንደሚገባን ሲያስተምረን ከዝሙት ብቻ እንድርቅ ሳይኾን የእርሱ ሥር የኾነውንና አይቶ መመኘትን ችላ ልንለው እንደማይገባን ነገረን (ማቴ.5፡28)፡፡ ኃጢአት ሥር ሰዳና ሰፍታ ከመቸገራችን በፊት በችግኝ ደረጃ ላይ እያለች ነቅለን መጣል ቀላል ነውና፡፡ 

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
እሺ ብትሉ…

ልጆቼ! እስኪ ምላሴን ላሰናብትባችሁና እናንተም በትዕግሥት አድምጡኝ! የቤት ሠራተኛ አላችሁ እንበል፡፡ ይህቺ የቤት ሠራተኛችሁ የለበሰችውንና በወጥ፣ በአመድ እንዲሁም በሌላ ቆሻሻ እድፍ ያለ ልብሷን ትለብሱ ዘንድ ትፈቅዳላችሁን? በእርግጠኝነት አትፈቅዱም፡፡ ግን የብዙዎቻችን ሰውነት ከዚህ ልብስ በላይ መቆሸሽዋስ ታውቃላችሁን?

ልጆቼ! ንግግሬ በጣም እንደሚያሳምም አውቃለሁ፤ ግን ምን ላድርግ? የተስተካከለ ሕይወት ቢኖረን እንዲህ የምናገር ይመስላችኋልን? በፍጹም! አንድ የቆሰለ የሰውነት ክፍል ቢኖራችሁ ሐኪሙ ይህን ቁስላችሁ በጣቱ ሳይነካካ ማከም ይችላልን? አይችልም! እኔም እንዲህ ቁስላችሁን ካልነካካሁት በስተቀር ማከም አልችልም፡፡ ለነገሩ ሰው ሰውነትህን አትንካ ማለት ይቻላልን አይቻልም! ታድያ እኔና እንናተ እኮ አንድ አካል ነን፡፡ በክርስቶስ አንድ ኾነን የለምን? እንግዲያውስ ንግግሬን አትጥሉት፤ ክፉ ግብራችሁን እንጂ፡፡

ችግሩ ከማን ነው ከእኛው ወይስ ከቆሻሻው? አንድ ወደ ትዕይንት (ቲያትር) ቤት የሄደ ወጣት ገላዋን ገላልጣ የምትተውን ተዋናይትን አይቶ ዝሙትን መፈጸም የማያስብ ማን ነው? ደጋግሞ የዝሙት ዘፈንን የሚሰማ ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መቋቋም እችላለሁ የሚል ማን ነው? ቀኑን ሙሉ የዝሙት ጽሑፎችን ሲያነብ የሚውል ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መጠበቅ እችላለሁ የሚል ማን ነው?

ልጆቼ! ትዕይንቱን እያየነው፣ ዘፈኑን እየዘፈንነው፣ መጽሐፉንም እያነበብነው ኾኖም ግን መፍትሔ ካላገኘንበት ችግሩ እየባሰ የሚሄድ አይደለምን? እኛ ፈቃደኞች ከኾንን ግን መፍትሔው በሥጋችን ላይ ካለው ደዌ በላይ በጣም ቀላል ነው፡፡ ምክንያቱም የሥጋችን ቁስል ሐኪም፣ መድኃኒት፣ ጊዜ ያስፈልጓል፡፡ የነፍሳችንን ቁስል ግን ፈቃድ በቂ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ከእኛ በላይ በንጽሕና ሲኖሩ ሳይ በጣም አፍራለሁ፡፡ እንግዲያውስ ልጆቼ እንመለስ፡፡ ያቆሸሹንን ነገሮች እንጣላቸው፤ እንቁረጣቸው፤ እናስወግዳቸው፡፡ ሰነፎች አንሁን፡፡

ውሳኔው የእኛው ነው፡፡ መጽሐፍ ሲናገር “እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላችኋል” ይላል /ኢሳ.1፡19-20/፡፡ ስለዚህ ሁሉም ነገር በእኛ እሺታና እምቢታ የተወሰነ ነው ማለት ነው፡፡ የምንኮነነውም የምንመሰገነውም በዚሁ መሠረት ነው ማለት ነው፡፡ መድኃኒዓለም በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን ከሚላቸው ጋር በቸርነቱ ይደምረን አሜን፡፡

ምንጭ፦ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው....

ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡

"ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡

አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ ለመዳን፣ ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ  መስራቱን አቁም፡፡

#ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
"ጌታ ሆይ አንተን ምን ብሎ መጥራት እንዳለበት የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ጌታ ሆይ እናትህን ድንግል ብለን እንጥራትን? እንዲያ ብለን እንዳንጠራት የአንተ እናት መሆኑዋ ምስክር ይሆንብናል፤ ጌታ ሆይ እናት እንበላትን? እንዲህ እንዳንል ወንድ የማታውቅ ድንግል ናት፤ የእናትህ ነገር ለመረዳት የረቀቀ ከሆነ አንተን ሊረዳ የሚችል ሰው ማን ነው?"

ቅዱስ ኤፍሬም

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
የሰውን ልጅ በሩህሩህነት አሸንፈው። ቀናተኛውን በመልካምነትህ እንዲደነቅ አድርገው፤ ሁሉንም ሰው ውደድ ነገር ግን ከሁሉም ሰው ጋር ርቀትህን ጠብቀህ ኑር።

አባ እንጦንስ

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
ሆሳዕና
# የምሥጋና ንጉሥ እርሱ ማነው?

በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀትና በልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ በዓለ ሆሳዕና ነው።
ሆሳዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ሆሼዕናህÂ የሚል ሲሆን ትርጉሙም እባክህ አሁን አድንÂ ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩከ ነው፡፡Â መዝ.117፡25-26 የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያምÂ በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ በዓሉም ሆሳዕና የሚለውን ስያሜ ያገኘው በዕለቱ ከተዘመረው መዝሙር ነው፡፡

በሌላ አነጋገር ይህ ዕለት የጸበርት እሑድÂ /Palm Sunday/ ይባላል፡፡ ታሪካዊ አመጣጡ የመልካም ምኞትና የድል አድራጊነት መገለጫ ሆኖ ከደገኛው አባታችን ይስሐቅ ልደት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡ ይኸውም ሣራ የወላድነት ዕድሜዋን ጨርሳ ልማደ እንስት ከተቋረጠባት በኋላ ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ይስሐቅን በሰጣት ጊዜ ዘመዶችዋ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ የጎበኟትን አምላክ አመስግነዋል፡፡ እስራኤል ከአስከፊው የግብፃውያን አገዛዝ ተላቀው ባሕረ ኤርትራን በደረቅ ሲሻገሩ የተሰማቸውን እጥፍ ድርብ ደስታ በገለጡ ጊዜ፣ እንዲሁም ዮዲት የተባለች ንግሥተ እስራኤል ሆሎፎርኒስ የተባለ አላዊ ንጉሥን ድል ባደረገች ጊዜ ቤተ እስራኤል እንደ ሰንደቅ ዓለማ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ አደባባይ ወጥተው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

በዘመነ ሐዲስም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር ከዲያብሎስ ቁራኝነት ከሲኦል ባርነት ነጻ ለማውጣት ወደ ዙፋን መስቀሉ /ሉቃ.22፤18/ በተጓዘ ጊዜ ሕፃናት እና አእሩግ ነጻ የሚወጡበት ቀን መድረሱን እነርሱ ሳያውቁ እግዚአብሔር ባወቀ ዘንባባ በመያዝ ዘምረዋል፡፡ እስራኤል ዘንባባ በመያዝ እንዳመሰገኑት እኛም አስራኤል ዘነፍስ ዕለቱን ዘንባባ /ጸበርት/ በግንባራችን በማሰር በዓሉን በየዓመቱ እያስታወስን እናከብራለን፡፡ በዚህ ዕለት ዘንባባ እየተባረከ ለሕዝቡ ይታደላል፡፡

ሕፃናትና አእሩግ ለዳዊት ልጅ መድኃኒት መባል ይገባዋል፡፡Â እያሉ ዘምረዋል፡፡ ይህ ሁሉ በአንድ ወገን የነበረው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ሲሆን በሌላ በኩል የነበረው አቀባበል ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን ነበር፡፡ ሥርዓተ ኦሪትን፣ ትንቢተ ነቢያትን በሚገባ እንከተላለን ይሉ የነበሩ ጸሐፍት ፈሪሳውያን መምህር ሆይ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸውÂ አሉት፡፡ ጌታችንም መልሶ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉÂ ሲል መልሶላቸዋል፡፡ ቅናት አቅላቸውን ያሳታቸው ፈሪሳውያንም የዋህ የሆነው ሕዝብ ምስጋና ወደ ጥላቻ እንዲለወጥ አድርገዋል፡፡ ከሁሉ የሚያሳዝነው በዕለተ ሆሳዕና እሑድ ዘንባባ ይዘው የዘመሩለትን ጌታ ዓርብ ይሰቀል ዘንድ ይገባልÂ ብለዋል፡፡

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ በዚህም በነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ፡፡እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፣ በአህያዪቱ ግልገል በውርንጫዪቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡Â ዘካ.9፡9፤ ማቴ.21፡4፤ ማር.11፡1-10፤ሉቃ.19፡28-40፤ ዮሐ.12፤15፡፡ ጌታችን በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ የሰላም ንጉሥ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እስራኤል ዘመነ ምሕረት ሲሆንላቸው አባቶቻቸው በአህያ ጀርባ ተቀምጠው ይታዩ ነበር፡፡ ጌታም እውነተኛ የኅሊና ሰላም ይዤላችሁ መጣሁ ሲለን በአህያ ጀርባ ወደ ቤተ መቅደስ ሕይወታችን ተጉዟል፡፡

መላእክት በዕለተ ልደቱ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል በምድር ሰላም ለሰው ሁሉ ይሁንÂ /ሉቃ.2፡13/ እያሉ የዘመሩለት የሰላም ባለቤት ነው፡፡ በመዋዕለ ትምህርቱም ሰላሜን እሰጣችኋለሁÂ /ዮሐ.14፡27/ ብሎ እንዳስተማረ ያን ሰላም የሚሰጥበትን ዕለት መቅረቡን ለማመልከት ነው፡፡ በሌላ በኩልም በአህያ ጀርባ መቀመጡ ኅቡዕ ምሥጢር አለው፡፡ በአህያ ጀርባ የተቀመጠ ሰው ሌላውን አሳድዶ አይዝም፣ እርሱም ሮጦ አያመልጥም፡፡ በዚህም ጌታችን በእምነት ለሚፈልጉት የሚገኝ ቅርብ ሲሆን በእምነት ለማይፈልጉት ግን የማይገኝ መሆኑን አስተምሯል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ፀሐይ ዕድሜያችን ሳትጠልቅ በእምነት እንፈልገው፡፡ አሞጽ4፡፡ የአህያን ጀርባ ያልናቀ ጌታችን ትሑት ሰብእና እና የተሰበረ ልቡና ወዳለው ሰው ዘወትር ይጓዛል፣ የተዋረደውንና የተሰበረውን ልብ አይንቅም፡፡ ኢሳ.66፡2፤ መዝ.50፡17፡፡

ለታሰሩት መፈታትን ሊሰብክ ሰው የሆነ ጌታችን ከማሰሪያዋ በተፈታች አህያ እንደተቀመጠ ሁሉ ከኃጢአት እስራት በተፈታ ሕይወት ዛሬም ያድራል፤ የኅሊና ሰላምን ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ንስሐ ገብተን ጌታችንን ሆሳዕና በአርያም እያልን ልናመሰግነው ይገባል፡፡

ምንጭ፡ ሐመር ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ መጋቢት/ሚያዝያ 1996 ዓ.ም

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
ንጉሰ ሰላም

ጨርሰህ የምትጀምር ፣ ቃለ ሕይወትን የምትሰጥ የቃል መፍለቂያ ፣ ንጉሰ ሰላም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አመሰግንሃለሁ ። ደብረዘይትና ቤተ ፋጌ እንደሚቀራረቡ ልቤን ወደ ቃላህ አቅርብልኝ ። ከመንደር ውስጥ የምትገለገልባቸውን አህያና ውርጫይቱን እንዳገኘ የልቤን መንደር ፈትሸውና አረሙን አቃጥልልኝ። አህያና ውርጫይቱ ላይ መቀመጥህ ተአምር ነው ደንቆኛል ! እኩል የሆኑ አህዮች ላይ መቀመጥ በራሱ ከባድ ነው ፤ አንተ ግን ውርጫይቱ ላይ ተቀመጥከ ። አንዷ ትንሽ ናት  አንዷ ከፍ ያለች ናት ። አንዷ ልምጥ ነች አንዷ ደልዳላ ነች አንተ ግን በተአምራት ሁለቱም  ላይ ተቀመጥክባቸው። ምግባሬ ትንሽ ትዕቢቴ ብዙ ፣ ለትዕዛዝህ ልምጥ ለኃጢአት ብርቱ የሆንኩ ነኝ ። ሚገድብህ ድንበር የሌለ ንጉሰ ሰላም ክርስቶስ ሆይ የማልመቸውን ልጅህን ስራኝ ። በእስራኤላውያን ልማድ ሀገር ላይ ጦርነት ሲኖር ንጉሱ በፈረስ ላይ ጦር ይዞ በመንደር ውስጥ ይመላለሳል። ሀገሪቱ ሰላም ከሆነች በአህያ ላይ ተቀምጦ መንደሩን በሙሉ እንደሚመላለሳል አንተ ንጉሰ ሰላም ነህና ውርጫይቱ ላይ ተቀምጠህ ወደ ከተማው ገባህ፤ ጌታዬ ሆይ ሀገሬ ኢትዮጵያ አትገባም ወይ ? ወደ ታወከው ልቤስ አትገባም ወይ? የኔ ጌታ ቀርበህ ለከተማይቱ አዘንክ አይደል! ኢትዮጵያን ስትቀርባት ስንቴ አዝነህ ይሆን? የሰላም ንጉሷን አንተን ገፍታ መሳሪያን ስትደገፍ ለኢትዮጵያ አታዝንም ወይ ? አንተን አምላክ ብሎ ሌላ ለሚሚመኘው ልቤስ ስንቴ አዝነህ ይሆን ? ንጉሰ ሰላመቸውን ትተው የዓለማዊያንን ዕቅድ ለሚያራምዱ አገልጋዮች እንዴት አዝነህ ይሆን? ብቻ ሆሳዕና በአርያም ለአንተ ይሁን።ስባዝን በሚሰበስበኝ ፍቅርህ ፣ ስደክም በሚያበረታኝ ድምፅህ ፣ ስታሰር በሚፈታኝ ቃልህ ለዘለዓለሙ አሜን

ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ

@finote_tsidk @finote_tsidk
“ፍቅርህ ከዘባነ ኪሩብ አውርዶ በአህያ ጀርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደህ፡፡ ብዙ ዐይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሰራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደድክ፡፡ በሰማይ ሰራዊት ሠረገላ ተቀምጠህ ክብርህን ማሳየት አልወደድክም፤ በውርንጭላይቱ ላይ ተቀምጠህ ወደ ሰማይ ሰራዊት መሄድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚሆኑ ኪሩቤል ያመሰግኑሃል፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልሃል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድህን ያነጥፉልሃል፤ በምድርም ደቀ መዛሙርትህ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድህን አስተካከሉ፡፡

ወዮ! አርያማዊ ሲሆን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከመሆን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡”

#ሊቁ_ያዕቆብ_ዘሥሩግም

🇯 🇴 🇮 🇳  ♻️ 🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
ንጉሥ_በአህያ_ላይ
(ሽራፊ ሃሳብ ከሆሳዕና ምንባብ)🌿

"አህያ" ስምዋ ስድብ ከሆነ የቆየች እንስሳ ናት።  የዚህች  በዓለም ሁሉ የምትገኝ እንስሳ የሕይወት ታሪክዋ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው።  በሚበዙት ሀገራት አህያ ከባድ ሸክም ስትሸከም ትውላለች ፣  ደክሟት ለማረፍ ብትፈልግና ሸብረክ ብትል እንኳን በዱላ የሚመታት እንጂ "እስቲ አረፍ በይ" የሚላት የለም። ጀርባዋ በሸክም ብዛት የቆሰለ ፣ እግርዋ በጭነት ብዛት የተብረከረከ ፣ ዱላ ያስመረራት ፣ ዕረፍት የናፈቃት እንስሳ ናት።
ይህችን የተዋረደች እንስሳ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ አደረጋት። ዱላ በለመደችው ፣ ዕረፍት በናፈቃት በዚህች ምስኪን ላይ "ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀሊል ነው" ያለው ንጉሥ ተቀመጠባት።
🌿
ኃያላን ነገሥታት ባማረ ሠረገላ ላይ ሆነው ፣ በሠራዊት ታጅበው ፣ ነጋሪት እያስመቱ ፣ መለከት እያስነፉ ፣ ሰይፍ  በታጠቁ ጦረኞች እየተፎከረላቸው ወደሚገቡባት ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአህያ ላይ ተጭኖ ፣ በዓሣ አጥማጆች ተከብቦ ፣ በሕፃናት ዝማሬና በዘንባባ ዝንጣፊ ታጅቦ ገባ። 
🌿
ፈርተውት ሳይሆን ወደውት የሚዘምሩለት ንጉሥ ፣ ልብስ ገፍፎ የሚረግጥ ሳይሆን ልብሳቸውን አውልቀው ረግጠህ እለፍ የሚሉት ንጉሥ ፣ በቅንጦት ሠረገላ የሚሣፈር ሳይሆን "በአህያ ላይ ከተቀመጥኩ ይበቃኛል" የሚል ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።
🌿
"የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የተባለላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? "የዋህና ትሑት ንጉሥ" ያላት ሀገር ፣ ከተማይቱን  እያየ የሚያለቅስላት ንጉሥ ፣ መልካምነቱን ለመሸፈን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ እሱ አትናገሩ ቢሉ እንኳን የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው የሚመሰከሩለት ንጉሥ ያላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? የታሰሩትን አስታውሶ "ያስፈልጉኛል ፣ ፈትታችሁ አምጡልኝ" የሚል ንጉሥ የነገሠባት ፣ ዘንባባ ተይዞ ስለ ሰላም የተዘመረባት ፣ "ሰላምሽ ዛሬ ነው" የተባለላት  ያቺ ከተማ ምንኛ የታደለች ናት?

ወደ አህያይቱ ነገር እንመለስ ያቺን "ሸክም ያቆሰላትን ፣ ዕረፍት የናፈቃትን አህያ ክርስቶስ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎ ዙፋኑ አደረጋት" የሚለው ታሪክ ለአህያ ብቻ ክብር የተሠጠበት ቀን መሆኑን የሚያሳይ ከመሰለን የዋሆች ነን። አህዮች አንብበው የማይጽናኑበት ወንጌል ላይ ይህ ክስተት የተጻፈው ለእኛ እንጂ ለምንም አይደለም።

እንደ አህያ ዕቃ ባንሸከምም ፣ ጀርባችን  ባይቆስልም የልባችን ጀርባ በኃጢአት ሸክም የጎበጠ ፣ በበደል ብዛት የቆሰለብን ብዙዎች ነን። "መቼ ነው ይህንን የኃጢአት ሸክም አራግፌ ዕርፍ የምለው?" እያልን የምንሠቃይ ሞልተናል።  መድኃኔ ዓለም ያኔ የላካቸውን ካህናት ዛሬም ወደ እኛ ልኮ "ፈትታችሁ አምጡልኝ" ብሎ እኛንም ቢያስፈታን ምናለ? ለነገሩ የእኛ የኃጢአት ማሠሪያ እጅግ ትብትብ ያለ ስለሆነ ካህናቱም  "ከኃጢአት ማሠሪያ እግዚአብሔር ይፍታ" ሲሉ እንሰማቸዋለን።


🌿ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ🌿

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ንጹሕ ሆነን የረከሰ ምራቅን አለመጠየፍ እንዴት ይቻለናል? ያለ በደል የሚደረግ ውንጀላ እና ግፍንስ "በቃ" አለማለት እንዴት ይሆናልናል?

ያለ ጥፋት የሚመጣብንን ምን ያህል ጥፊዎች እንታገሳለን? ስንት ጅራፎችንስ እንቀበላለን? ስንት ውርደቶችንስ እንሸከማለን? መድኃኔዓለም ይህን ሁሉ ነገር የተቀበለው ስለ እኛ መዳን ነው።

እኔ ግን ስለ ራሴ መዳን በጀርባህ ላይ ካረፉት ጅራፎች የአንዲቱን ሰንበር ያህል እንኳን መከራ ለመቀበል ትዕግስቱ የለኝም።

"ተሰሃለኒ እግዚኦ በከመ ዕበየ ሳህልከ" - "አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ" መዝ 50፥1

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

@finote_tsidk @finote_tsidk
https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የጉልባን ታሪክ

➛ ጉልባን ከባቄላ ክክ ከሰንዴ ወይም ከተፈተገ ገብስ እና ከሌሎችም ጥራጥሬዎች ጥሬውን ወይም ከክቶ እንደ ንፍሮ ተቀቅሎ የሚዘጋጅ ምግብ ነው ። የዕለተ ሐሙስ ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመ በኋላ ምእመናን ወደ ቤታቸው ሄደው ጉልባን ሠርተው ይመገባሉ ። ለዚህም ሁለት ትውፊታዊ መሠረት እንዳሉት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያስረዳሉ እንመልከት፦ ፩ የኦሪት ምሳሌ ለመፈጸም እስራኤል ለ215 ዓመታት በግብጻውያን በባርነት ተይዘው በግፍ ተጨቁነው መኖራቸው ይታወቃል የእግዚአብሔር ፍቃድ ሁኖ እግዚአብሔር ሙሴን ፈርኦንን ህዝቤን ልቀቅ ብሎሀል ብለህ ንገረው ብሎት ነበር ። ሙሴም ፈርኦንን እግዚአብሔር ህዝቤን ልቀቅ ብሎሀል አለው ፈርኦንም እስራኤል እለቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማነው ? እግዚአብሔርን አላቅም እስራኤንም ደግሞ አለቅም በማለት አሻፈረኝ ብሎ ነበር ። እግዚአብሔርም የኃይል ስራውን በሙሴ አሳየ በመጨረሻም እምቢ ሲል እግዚአብሔር ከእንስሳትም ከሰውም ወገን በመልአክ በሞተ በኩር ግብጽ ተቀሰፈች በዚህም ፈርኦን ደንግጦ ሕዝበ እስራኤል ለመልቀቅ ተገዷል ። በዚህ ጊዜ ህዝቡ ለመውጣት ስለቸኮሉ በቤት ያለውን እህል ያልተፈጨውን ንፍሮ ቀቅለው የተፈጨውን ቂጣ ጋግረው በልተው ነው ጉዞ የጀመሩት ። እስራኤልም ከግብፅ ከወጡ በኋላም የነጻነት በዓላቸውን ሲያከብሩ ያልቦካ ኪጣ ጋግረው ንፍሮ ቀቅለው በግ አርደው ከባርነት በወጡበት ዕለት የነበረውን ሁኔታ ያስቡ ዘንድ ታዘዋል ። (ዘጸ ፲፫ ፥፩) ፋሲካ የሚለውም '' ፓሢሕ '' ከሚለው ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ማለፍ መሻገር ማለት ነው ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሴተ ሐሙስ በአልዓዛር ቤት ተገኝቶ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ይህን በዓል አክብሯል ። እኛም አሰቀድሞ በሙሴ ላይ አድሮ ሕገ ኦሪትን የሠራ ሕዝቡንም መርቶ ከነዓን ያደረሰው እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሰውን ስጋ ለብሶ ክርስቶስ ተብሎ መገለጡን በማመን ፤ ክርስቶስ ራሱ አዲሱን ሕግ ከመሥራቱ አሰቀድሞ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በዓለ ፋሲካን እንዳከበረ ሁሉ እኛም አዲስ ኪዳን ጥላ /ምሳሌ/ የሆነውን ሥርዐት እኛ ጉልባን በመመገብ ለመታሰቢያ እናደርጋለን ።
፪ የኀዘን ሳምንት መሆኑን ለማጠየቅ ፦ እንደ ሀገራችን ባሕል ንፍሮ እንባ አድርቅ ይሉታል ። ብዙ ጊዜም ለለቀስተኞች ይሠራል ። አንድም ሞት ተናግሮ አይመጣምና ሞት በድንገት ሲመጣ ለእንግዳ መሸኛ ቶሎ ሊደርስ የሚችል ምግብ ንፍሮ ስለሆነ በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች ለልቅሶ ቤት ንፍሮ የመቀቀል ልማድ አለ ።
➛ በሰሙነ ሕማማት ወቅት ምዕመናን በጌታችን መከራ ፣ ሞት እና በድንግል ማርያም ኀዘን ምክንያት ኀዘንተኞች ስለሆኑ ይህንኑ ለማመልከት ጉልባን ይመገባሉ ። የጉልባን ክርስቲያናዊ ትውፊት ይህንን ይመስላል እኛ ምዕመናን በቤተችን እንዲሰራ በመጠየቅ በመስራት ይህን ትውፊት ማስቀጠል ይኖርብናል ።

@atronosezetewahdo
@atronosezetewahdo
@atronosezetewahdo
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡

በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡  በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡

መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡

ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡

መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡

ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ  በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡ በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡

ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤  ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!

ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/28 21:44:34
Back to Top
HTML Embed Code: