Telegram Web Link
ሰላም ለትግራይ ሕዝብ ከምንጊዜውም በላይ አስፈላጊ ነው- አቶ ጌታቸው ረዳ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል በትግራይ ክልል ዓዲግራት ከተማ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከብሯል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ÷ በዓሉን ስናከብር እርስ በርስ በመተሳሰብና በአብሮነት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ዘላቂ ሰላም ለትግራይ ሕዝብ ከምንጊዜውም በላይ አስፈላጊ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በ2017 ዓ.ም የትግራይ ሕዝብን ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ አስገንዝበዋል፡፡https://www.fanabc.com/archives/263813
ም/ቤቱ ሕገ-መንግስታዊ ተልዕኮዎችን በብቃት መወጣት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕገ-መንግስታዊ ተልዕኮዎችን በብቃት መወጣት የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የም/ቤቱ 4ኛ ዓመት የምርጫ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የጽ/ቤቱ አመራሮችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ተገምግመዋል፡፡ በግምገማው ም/ቤቱ በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ በሕገ መንግስቱ የተጣሉበትን ተልዕኮዎች በብቃት መወጣት የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ…

https://www.fanabc.com/archives/263816
Live stream finished (4 hours)
ኢትዮጵያ በዘመናዊ ከተማ ግንባታና በቱሪዝም መሠረተ-ልማት ተጨባጭ ለውጦችን አሳይታለች – የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በዘመናዊ ከተማ ግንባታና በቱሪዝም መሠረተ-ልማት ተጨባጭ ለውጥ እያሳየች መሆኑን የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ተናገሩ። በ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ላይ አዲስ አበባ የተገኙ የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች÷ኢትዮጵያ አስገራሚ ባህል፣ አንድነትና ሕብረ-ብሔራዊነትያላት ሀገር አንደሆነች መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በመሠረተ-ልማት፣ በቱሪስት መዳረሻ ልማት፣ በዘመናዊ ከተማ ግንባታ፣ ለቱሪስቶች ምቹ ሁኔታዎችና…

https://www.fanabc.com/archives/263819
የሲቲው አማካይ ሮድሪጎ ሄርናንዴዝ ከውድድር ዓመቱ ተሳትፎ ውጪ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔናዊው የማንቼስተር ሲቲ አማካይ ሮድሪጎ ሄርናንዴዝ ባጋጠመው የጉልበት ጉዳት ከ2024/25 የውድድር ዓመት ተሳትፎ ውጪ መሆኑን ክለቡ አስታውቋል፡ ተጫዋቹ ጉዳቱን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ከአርሰናል ጋር ባደረገው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ነበር፡፡ የ28 ዓመቱ የዩሮ 2024 አሸናፊ ሮድሪ ማንቼስተር ሲቲ በቅርብ ዓመታት ላስመዘገበው ስኬት ቁልፉ…

https://www.fanabc.com/archives/263822
በሶማሊያ ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የሃይል ሥምሪት በጥንቃቄ መከናወን አለበት- አምበሳደር ታዬ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የሃይል ሥምሪት ጊዜ ተወስዶ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ አሳሰቡ፡፡

አምባሳደር ታዬ ከዴንማርክ አቻቸው ላርስ ሎክ ራስምሰንና ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ሼህ ሻክቡት ናህያን አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ታዬ በውይይቱ ላይ ዴንማርክ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አባል ሆና በመመረጧ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

በወቅታዊ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች እና ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ ባላት ቁርጠኝነት ዙሪያም ገለጻ አድርገዋል።

በተያያዘ አምባሳደር ታዬ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ሼህ ሻክቡት ናህያን አል ናህያን ጋር በሁለትዮሽና በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደህንነት ዙሪያ መክረዋል። https://www.fanabc.com/archives/263825
ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ1 አሸንፏል፡፡ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች ፍፁም ጥላሁንና አማኑኤል ኤርቦ አስቆጥረዋል፡፡ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ኪሩቤል ወንድሙ ከመረብ አሳርፏል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/263831
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቀን በፋና ቴሌቪዥን የተላለፈው የጥላሁን ገሠሠ ኮንሰርት ምሽት በድጋሜ ይተላለፋል፣ ይጠብቁን!
እስራኤል በሂዝቦላህ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በ79ኛው የተመድ ጉባዔ ላይ ቁጣና ዛቻ የተቀላቀለበት ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም÷ዜጎች ወደ ቀያቸው እስካልተመለሱ ድረስ እስራኤል በሂዝቦላህ ላይ የምትወስደው ሁለንተናዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ ሃማስ እጅ ከሰጠ ጦርነቱ ወዲያውኑ ያቆማል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ይሁን እንጂ እስራኤል ሂዝቦላህን በሊባኖስ የማሸነፍ ግዴታ አለባት ብለዋል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/263835
አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በካናዳ የሥራ ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በካናዳ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝታቸው ከካናዳ ምክር ቤት አፈ -ጉባዔ ጌርግ ፈርጉሰን እና ከሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያና ካናዳ የፌዴራል ሥርዓትና አሰራር ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን÷ በዚህም በሀገራቱ ምክር ቤቶች…

https://www.fanabc.com/archives/263838
Live stream finished (16 minutes)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል -ኢሬቻ
2024/09/28 06:04:09
Back to Top
HTML Embed Code: