Telegram Web Link
በቀጣዮቹ 10 ቀናት በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች የዝናቡ ስርጭት ተጠናክሮ ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣዮቹ አስር ቀናት በሁሉም የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች የዝናቡ ስርጭትተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ በቀጣዮቹ 10 ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብና በመካከለኛው የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ይበልጥ የሚጠናከሩበትና የሚስፋፉበት ጊዜ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች…

https://www.fanabc.com/archives/250544
የሚኒስትሮች ም/ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 36ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

1. በመጀመሪያ ምክር ቤቱ የተወያየው የአለም አቀፍ አቪዬሽን ኮንቬንሽንን ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የኮንቬንሽኑ መሻሻል ለሀገራችን ጥቅሞች መከበርና በዓለም አቀፍ መድረኮች የሚኖራትን የውክልናና ተሰሚነት ዕድል የሚያሰፋ እንዲሁም የሀገራችንን የሲቪል አቪዬሽን መዋቅር ዓለማቀፍ እውቅና ለማጉላት የሚረዳ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው በሦስተኛ ወገን የተሽከርካሪ አደጋ የመድን ፖሊሲ የአረቦን ተመን እና የካሳ መጠን ከፍያን ለመወሰን በወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር ለማስቻል፣ የአዋጁን ተፈፃሚነት ለማጠናከር፣ ለሦስተኛ ወገን የተሽከርካሪ አደጋ የመድን ፖሊሲ የሚከፈለውን የአረቦን ተመን እና የካሳ መጠን ለመወሰን እንዲሁም አዲስ ወደ ኢንዱስትሪው ለተቀላቀሉ በኤሌክትሪክ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ተመጣጣኝ የሶስተኛ ወገን መድህን ሽፋን አረቦን ተመን አካቶ ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡https://www.fanabc.com/archives/250550
የብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ ባንኩ በዘርፉ ከሚኖሩ ለውጦች ጋር እንዲጣጣምና የቁጥጥር አቅሙን እንዲያጎለብት ያስችለዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ ባንኩ በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ ከሚኖሩ ለውጦች ጋር እንዲጣጣም እና የቁጥጥር አቅሙን እንዲያጎለብት እንደሚያስችለው ተገለጸ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ጉባዔ÷የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ…

https://www.fanabc.com/archives/250547
በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 17 ሺህ በላይ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ምሰራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ጋር በቅንጅት ባደረገው ፍተሻ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 17 ሺህ 350 ጥይት መያዙን አስታወቀ። የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አንድ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጣሂር ሳህሊ እንዳሉት ፥ አፈወርቅ ፀጋዬ የተባለ ተጠርጣሪ መነሻውን ቆቦ ከተማ በማድረግ በሚያሽከረክረው…

https://www.fanabc.com/archives/250558
በጋምቤላ ክልል መሬት ወስደው ያላለሙ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃዳቸው ተሰረዘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በጋምቤላ ክልል በእርሻ ኢንቨስትመንት መሬት ወስደው ያላለሙ 54 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃዳቸው መሰረዙን የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ አስታወቀ፡፡ የኢንቨስትመንት ቦርዱ ሰብሳቢና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ እንዳሉት፥ በክልሉ ከ700 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች የእርሻ ኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ጠቁመዋል። የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ…

https://www.fanabc.com/archives/250562
በመዲናዋ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥብቅ የተከለከለ ነው – ቢሮው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአከራይ ተከራይ አዋጅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሕግ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥበቅ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ገለፀ። ፍትሃዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማህበረሰቡ ላይ የሚፈጥረው ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት የቤት ኪራይ ስርዓቱ በሕግ…

https://www.fanabc.com/archives/250565
ፎቶን ሞተርስ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪኖች አቅርቦት ዘርፍ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት አሳየ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ፎቶን ሞተርስ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪኖች አቅርቦት ዘርፍ ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየቱ ተገለፀ፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዳንጌ ቦሩ ከቻይናውን ፎቶን ሞተርስ ግሩፕ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡ አቶ ዳንጌ ÷ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በየዓመቱ በርካታ ችግኞችን ከማልማት ጎን ለጎን የኤሌክትሪክ መኪኖች አቅርቦት በማስፋት የአየር…

https://www.fanabc.com/archives/250568
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጋምቤላ - ምድረ ወርቅ (ዛሬ ምሽት ይጠብቁን)
አቶ አረጋ ከበደ በባሕር ዳር የልማት ሥራዎች እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው። በጉብኝቱ የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። ርዕሰ መሥተዳድሩ በጉብኝታቸው…

https://www.fanabc.com/archives/250573
የጎርጎራ ፕሮጀክት ገፅታዎች
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የፖሊስ ጀልባዎችን ለማሰራት ከኮርፖሬሽኑ ጋር ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የፖሊስ ጀልባዎችን ለማሰራት ስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡ በስምምነቱ መሰረት የሚሰሩ ጀልባዎች ዲዛይናቸው እና የጥራት ደረጃቸው ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን በጣልያንና በቻይና ሀገራት እንዲሁም በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተገመገመና አዎንታዊ ምላሽ ያገኘ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ጀልባዎቹ ሀገር በቀል በሆነው በመከላከያ…

https://www.fanabc.com/archives/250576
2024/09/28 14:18:40
Back to Top
HTML Embed Code: