Telegram Web Link
Live stream finished (1 hour)
በአውሮፓ ዋንጫ ጀርመን ሁለተኛ ድሏን አስመዘገበች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ አስተናጋጅ ጀርመን ዛሬ ባደረገችው ሁለተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሀንጋሪን 2 ለ 0 ረትታለች፡፡

ምሽት 1 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ የጀርመንን ጎሎች በ22ኛው ደቂቃ ሙሴላ እንዲሁም በ67ኛው ደቂቃ ጉንዶጋን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ጀርመን ስኮትላንድን 5 ለ 1 ማሸነፏ ይታወሳል፡፡

የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ የዛሬ መርሐ-ግብር ሲቀጥል ምሽት 4 ሠዓት ላይ ስኮትላንድ ስዊዘርላንድን ትገጥማለች፡፡

ቀን 10 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ክሮሺያ እና አልባኒያ 2 አቻ መለያየታቸው ይታወቃል፡፡
ፕሬዚዳንት ፑቲን ቬትናም ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለይፋዊ ጉብኝት ቬትናም ገብተዋል፡፡

በቬትናም በሚኖራቸው ቆይታም ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዚዳንት እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃልሲል ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ትናንት ወደ ሰሜን ኮሪያ አቅንተው ጉብኝት ማድረጋቸው እና ከሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር በሀገራዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ይታወሳል፡፡
በአውሮፓ ዋንጫ ስፔን እና ጣልያን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ሁለተኛው ዙር የምድብ ማጣሪያ መርሐ ግብር ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህ መሰረትም በምድብ ሁለት የሚገኙት ጣልያን እና ስፔን ምሽት 4 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡ በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ጣልያን አልባንያን 2 ለ 1 እንዲሁም ስፔን ክሮሺያን 3 ለ 0…

https://www.fanabc.com/archives/250503
ሁርሶ የኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ መሠረታዊ ወታደሮችን እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ የሰላም ማስከበር ማዕከል ሁርሶ የኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሠረታዊ ወታደርነት ያሰለጠናቸውን ወታደሮች እያስመረቀ ነው። ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዛሬ በመሠረታዊ ወታደርነት እያስመረቃቸው የሚገኙት ወታደሮች የ8ኛ ዙር ሰልጣኞች መሆናቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው። ተመራቂዎቹ በትምህርት ቤቱ ቆይታቸው የቀሰሙትን የንድፍና የተግባር ወታደራዊ ስልጠና በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ…

https://www.fanabc.com/archives/250507
አቶ ደስታ ሌዳሞ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የክልሉን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ለኩ ከተማ አስጀምረዋል። አቶ ደስታ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት÷ በዘንድሮው ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 2 ሺህ ቤቶችን ለማደስ እቅድ ተይዟል፡፡ ተግባሩ በአንድ ጊዜ ተሰርቶ የሚጠናቀቅ አለመሆኑን ጠቁመው÷ ለትውልድ በጎ…

https://www.fanabc.com/archives/250510
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያዊቷ መቅደስ በማርኔሊ ቤንድ በመሽከርከር ያሳየችው ትርዒት የዓለም ክብረ ወሰን በመሆን ተመዘገበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ መቅደስ ከበደ ከወገቧ ታጥፋ (ማርኔሊ ቤንድ) ተሸከርካሪ ቁስን በጥርሷ ነክሳ በመያዝ ለአንድ ደቂቃ በመሽከርከር ያሳየችው ትርዒት የዓለም ክብረ ወሰን በመሆን በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ መዝገብ ሰፈረ፡፡

ማሪኒሊ ቤንድ ጭንቅላታቸውን ከስር በማድረግና መሬት ላይ ያረፈን ተሸከርካሪ ቁስን በጥርስ ነክሶ በመያዝ ከወገብ በመታጠፍ የሚሰራ የሰርከስ ትርዒት ሲሆን፥ ይህም የሰውነታቸውን ክብደት በሙሉ ጥርስ እንዲሸከም ያደርጋል፡፡

የሰርከስ ትርዒቱ እጅግ በጣም አደገኛ እና ከባድ እንደሆነ ይገለጻል፡፡

በዚህ የሰርከስ ዓይነት ነው እንግዲህ ኢትዮጵያዊቷ መቅደስ ከበደ ለአንድ ደቂቃ በመሽከርከር ያሳየችው ትርዒት የዓለም ክብረወስን በመሆን በትናንትናው ዕለት በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ መዝገብ ላይ ስሟ የሰፈረው።

መቅደስ ከበደ ትርዒቱን ያሳየችው ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ በጣሊያን ሚላን መሆኑ ይታወቃል።
የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ከፍ ብላ እንድትታይ አድርጓል -የፕላንና ልማት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ንቅናቄ ሀገሪቱ በዓለም መድረክ ከፍ ብላ እንድትታይ ማድረጉን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ ። “በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ላይ የዩኒቨርሲቲዎች የላቀ ተሳትፎ ” በሚል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶች ፣የዘርፉ ተመራማሪዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው ።…

https://www.fanabc.com/archives/250516
የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የሚያስችል የብድር ስምምነት አዋጅ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 33ኛ መደበኛ ጉባዔ የተጀመሩ የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የሚያስችል የብድር ስምምነት አዋጅ አጽድቋል፡፡ ምክር ቤቱ በጉባዔው በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለ2ኛው የከተሞች የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት አዋጅ ነው መርምሮ ያጸደቀው፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/250519
ከ70 በላይ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች የተሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ70 በላይ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች የተሳተፉበት እና “መሬታችን ለባለሃብቶቻችን“ በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የንቅናቄ መድረኩ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተዘጋጀ ሲሆን ለሁለት ወራት የሚቆይ የንቅናቄ መድረክ መሆኑ ተገልጿል፡፡ መድረኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ…

https://www.fanabc.com/archives/250530
የ170 አምራች ኢንዱስትሪዎችን የኃይል አቅርቦት ጥያቄ መመለስ መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ባለፉት አስር ወራት የ170 አምራች ኢንዱስትሪዎችን የሃይል አቅርቦት ጥያቄ መመለስ መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴሩ የኢትዮጵያ ታምርት ፕሮጀክት ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የ2016 የአስር ወራት አፈጻጸም ገምግሟል፡፡ በዚህም በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች መሰራታቸው፣ በባለድርሻ ተቋማት ላይ የባለቤትነት ስሜትን የመፍጠር እና ንቅናቄውን ብሔራዊ አጀንዳ…

https://www.fanabc.com/archives/250533
በሕንድ በተበከለ የአልኮል መጠጥ ምክንያት ብዙዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡባዊ ሕንድ ታሚል ናዱ ግዛት የተበከለ የአልኮል መጠጥ በመጠጣታቸው ቢያንስ የ34 ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ በክስተቱ ለህልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ ከ100 የሚልቁ ሰዎችም በአጣዳፊ ተቅማጥ፣ ትውከት እና ከፍተኛ የሆድ ህመም ለሆስፒታል አልጋ መዳረጋቸውን የመንግስት ቃል አቀባይ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከ10 ያላነሱ ባለስልጣናት ከስራ መታገዳቸውም ነው…

https://www.fanabc.com/archives/250536
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ማስታወቂያ!

ጤናችን በምርታችን !


በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚብሽን ከ ሰኔ 15 - 20 /2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

በዚህ ታላቅ ኤግዚብሽን ፤-

• በሀገራችን በባህላዊ እና በዘመናዊ መድሀኒት፤
• በህክምና መገልገያ መሳሪያ
• የጤና እና የግል ንጽህና መጠበቂያ ማምረት ላይ የተሰማሩ ከአነስተኛ አስከ ከፍተኛ አምራች ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ያስተዋውቃሉ፤
• የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ውጤቶች ይቀርባሉ
• የሀገር ውስጥና አለም ዓቀፍ የንግድ ትስስሮች እና የልምድ ልውውጦች ይደረጋሉ፡፡
• ዓለም ዓቀፋዊ ተሞክሮዎችና አሰራሮችላይ ያተኮረ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ፤

እርስዎ፡- መጥው ሲጎበኙ ሀገራችን እያከናወነች ያለውን እና ወደፊት የምትደርስበትን የህክምና ግብዓት አምች ኢንደስትሪ ዘርፍ ሁለንተናዊ እድገት ይመለከታሉ፤ በርካታ ኢንቨስትመንት እድሎችም እንዳሉ ይገነዘባሉ፡፡

ይምጡ፤ ይካፈሉ፤ ይጎብኙ

ጤና ሚኒስቴር ከመድኃኒትና የህክምና መገልገያ አምራች ዘርፍ ማህበራት ጋር በመተባበር
ለበለጠ መረጃ 011 518 6262 / 952 ላይ ይደውሉ!! ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ!!
https://pharma-exhibition.moh.gov.et/
#ጤናችን በምርታች
#our health by our products
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: twitter.com/FMoHealth
YouTube: @FMoHealthEthiopia
Tiktok: @mohethiopia
Live stream finished (33 minutes)
2024/09/28 12:15:14
Back to Top
HTML Embed Code: