Telegram Web Link
17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 24 ሀገራት የሚሳተፉበት የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ላይ አስተናጋጇ ጀርመን ከስኮትላንድ በሚያደርጉት የመክፈቻ ጨዋታ ይጀመራል፡፡

ጨዋታው ሲቀጥል ነገ ቀን 10 ሠዓት ላይ ሀንጋሪ ከስዊዘርላንድ፣ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ስፔን ከክሮሽያ እንዲሁም ምሽት 4 ሠዓት ላይ ጣልያን ከአልባኒያ ይጫወታሉ፡፡

በምድብ ማጣሪያው በምድብ አንድ ጀርመን፣ ስኮትላንድ፣ ሀንጋሪ እና ስዊዘርላንድ ሲደለደሉ÷ በምድብ ሁለት ደግሞ ስፔን፣ ክሮሽያ፣ ጣልያን እና አልባኒያ ተመድበዋል፡፡

በምድብ ሦስት የተደለደሉት ደግሞ ስሎቬኒያ፣ ዴንማርክ፣ ሰርቢያ እና እንግሊዝ ሲሆኑ÷ ፖላንድ፣ ኔዘርላንድስ (ሆላንድ)፣ ኦስትሪያ እና ፈረንሳይ ደግሞ በምድብ አራት ተደልድለዋል፡፡

ቤልጂየም፣ ስሎቫኪያ፣ ሮማንያ እና ዩክሬን በምድብ አምስት እንዲሁም ቱርክ፣ ጆርጂያ፣ ፖርቹጋል እና ቼክ ሪፐብሊክ በመጨረሻው ምድብ መደልደላቸውን የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ያወጣው መርሐ-ግብር ያመላክታል፡፡

በወጣው መርሐ-ግብር መሠረትም ጨዋታው እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ ውድድሩ በ10 ከተሞች የሚካሔድ ሲሆን የመክፈቻው ጨዋታ በሙኒክ ከተማ አሊያንዝ አሬና እንዲሁም የፍፃሜው ጨዋታ በበርሊኑ ኦሎምፒክ ስታዲየም ይደረጋል፡፡

በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ከ650 ሺህ የሚበልጡ የተለያዩ ሀገራት ደጋፊዎች ወደጀርመን ያቀናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/249681
ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር ) እና ዶ/ር ደረጀ ድጉማ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር ) እና በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ የተመራ ቡድን የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል የስራ እንቅስቃሴን ጎበኘ። በጉብኝቱ በክልሉ መንግስት በጀት እየተገነባ የሚገኘውን ሪጅናል ላቦራቶሪ፣ የህሙማን ልየታና ተኝቶ ህክምና፣ የእናቶችና ህጻናት ህክምና እና…

https://www.fanabc.com/archives/249691
ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ። የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አፈፃፀም በስፋት ውይይት የተደረገበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ…

https://www.fanabc.com/archives/249695
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ እቅዱን አስተዋወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ እቅዱን ይፋ አድርጓል፡፡ የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሃይሉ እንዳሉት÷ እቅዱ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም፣ ከአውሮፓ የምርጫ ድጋፍ ማዕከልና የምርጫ ሥርዓት ዓለም አቀፍ ፋውንዴሽን በተገኘ ድጋፍ እና በባለድርሻ አካላት የጋራ ጥረት የተዘጋጀ ነው። ስትራቴጂያዊ እቅዱ ቦርዱ የምርጫ ሒደቶችን በራሱ…

https://www.fanabc.com/archives/249698
የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየተሰሩ የሚገኙ አበረታች ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ። ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት በመደገፍ ምርትና ምርታማነት እንዲጎለብት ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ለዚህም ዘር በማቅረብ፣ የውሃ ሞተርና ሸራ በነፃ…

https://www.fanabc.com/archives/249702
በጤና ዘርፍ የሚካሄዱ ምርምሮች የዘርፉን ፖሊሲ ለማጠናከር ሚናቸው የጎላ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤናው ዘርፍ እየተካሄዱ ያሉት ጥናትና ምርምሮች የዘርፉን ፖሊሲ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጤና ሚኒስቴር አስገነዘበ፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ አዘጋጅነት ሀገራዊ የጤና ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡ በሚኒስቴሩ የፖሊሲ ጥናት፣ ልማትና ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እንደገና አበበ በጉባዔው ላይ እንዳሉት÷ በጤና ዘርፍ በተመራማሪዎች እየተካሄዱ…

https://www.fanabc.com/archives/249705
በመዲናዋ የመንደር ንግድ ማህበረሰብን መቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ህግና አሰራርን የማይከተሉ የመንደር ንግዱን ማህበረሰብ መቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ። መመሪያው በከተማ አስተዳደሩ የገቢ አሰባሰብ ላይ የሚያስቸግሩ ህገወጦችን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሀላፊ አቶ ቢንያም ምክሩ ተናግረዋል። በመንደር ንግድ ቁጥጥር አሰራር ስርዓት መመሪያ ላይ ያተኮረ የውይይት…

https://www.fanabc.com/archives/249715
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ያላትን ፍላጎት ለማስፈጸም የሚያግዝ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ እቅድ ማስፈጸሚያ ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል። የባህልና ስፖርት ዘርፍ አፈጻጸምን በማስመልከት ማብራሪያ የሰጡት አቶ ቀጄላ መርዳሳ÷ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ኢትዮጵያ የአፍሪካ…

https://www.fanabc.com/archives/249718
ም/ጠ/ሚ ተመስገን የተገኙ የልማት ስኬቶችና ዕድገቶች ላይ መቆም እንደማይገባ አስገነዘቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተገኙ የልማት ስኬቶችና ዕድገቶች ላይ መቆም የለብንም ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ። የ2016 ዓ.ም የ10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዋና ዋና አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቧል። በመርሀ-ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህን…

https://www.fanabc.com/archives/249721
36 በመቶው የመድሃኒትና የህክምና ግብዓት በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ አሁን ላይ 36 በመቶውን የመድሃኒትና የህክምና ግብአት በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈን መቻሉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅዳስ ዳባ በግምገማ መድረኩ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት÷በእናቶች፣ በህፃናትና ጨቅላ ህፃናት…

https://www.fanabc.com/archives/249724
የቱሪዝም ዘርፉ ለኢኮኖሚው የሚያደርገውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ የተሰራው ሥራ ውጤት እያስመዘገበ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገሪቱን የሃብት መፍጠሪያ አማራጭ እንዲሆኑ እየተሰራ ያለው ሥራ ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ተናገሩ። የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። በመድረኩ የቱሪዝም ሚኒስትሯ÷ በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፉ ለኢኮኖሚው የሚያደርገውን አስተዋጽዖ ለማሳደግ የተሰራው…

https://www.fanabc.com/archives/249734
የወባ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም ባለድርሻዎች በትኩረት እንዲሰሩ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ ያለውን የወባ ስርጭት ለመግታት ሁሉም ባለድርሻዎች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተመላከተ። የወባ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት ያለመ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ በሚዛን አማን እየተካሄደ ነው። የሀገሪቱ አብዛኛው አካባቢ ለወባ ስርጭት አመቺ በመሆኑ 69 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ለወባ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ የጤና ሚኒስትር ዴዔታ…

https://www.fanabc.com/archives/249740
በአኝዋሃ ዞን ያለውን የተፈጥሮ ደን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚያስችል ረቂቅ ጥናት ለክልሉ ካቢኔ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በአኝዋሃ ዞን ያለውን የተፈጥሮ ደን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ባዮስፌር ሪዘርቭነት ለማስመዝገብ የሚያስችል ረቂቅ ጥናትን በተመለከተ የክልሉ ካቢኔ አባላት ተወያይተው ውሳኔ አሳልፈዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ÷ ይህንን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በዩኔስኮ በባዮስፌር ሪዘርቭነት ለማስመዝገብ ጥናት መጠናቀቁ ያስደስታል ብለዋል።…

https://www.fanabc.com/archives/249744
የሚኒስትሮች ም/ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡- 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር የ2ኛ ዙር የከተሞች የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ተጨማሪ…

https://www.fanabc.com/archives/249749
2024/11/16 09:49:55
Back to Top
HTML Embed Code: