Telegram Web Link
በተለያዩ ክልሎች ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚኒስትሪ ፈተና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ክልሎች የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ለተማሪዎች እየተሰጠ ነው፡፡

በዚህም የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚኒስትሪ ፈተና በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፣በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ በሐረሪ፣ በሶማሌ፣ በአፋርና በሌሎች ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር እየተሰጠ ነው፡፡


ተማሪዎችም በፈተና ጣቢያዎች ተገኝተው ፈተናውን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ ለሕጻናት ክትባት ተደራሽነት ፕሮጀክት 45 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለሕጻናት ክትባት ተደራሽነት ፕሮጀክት (ዜሮ ዶዝ) ዘርፈ-ብዙ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር 45 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ተደረገ፡፡ በኢትዮጵያ የሕጻናት ክትባት ተደራሽነት ፕሮጀክት (ዜሮ ዶዝ) ዘርፈ-ብዙ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ላይ ምክክር ተካሂዷል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በመድረኩ ላይ እንዳሉት÷ ፕሮግራሙ በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት በግሎባል የክትባት ኅብረት…

https://www.fanabc.com/archives/249304
የሚኒስትሮች ም/ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 በጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት የመጨረሻ የሆነው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት ግምገማ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ እንደሁልጊዜው ሁሉ የየሴክተሮችን አፈፃፀም እንገመግማለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በግምገማውም “ክፍተቶችን እናጤናለን፤ በጥንካሬዎች ላይም ለቀጣይ ሥራዎች እንነሳለን” ሲሉም አመላክተዋል፡፡
በስልጢ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ አሳኖ ቀበሌ በነነ አካባቢበደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ ዋና ሳጂን አብድረማን ረዲ ገለጹ፡፡ ትናንት ምሽቱ 3 ሰዓት ከ20 ደቂቃ አካባቢ ከወራቤ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ከቡታጅራ ወደ መናኸሪያ ከተማ ሲጓዝ ከነበረ ባለ ሦስት…

https://www.fanabc.com/archives/249323
የሲንጋፖር አየር መንገድ በበረራ ላይ ሳለ በተከሰተው መናወጥ ለተጎዱ መንገደኞች ካሳ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲንጋፖር አየር መንገድ በበረራ ላይ ሳለ ተከስቶ በነበረው የከባድ መናወጥ አደጋ ለተጎዱ መንገደኞች ከ10 ሺህ እስከ 25 ሺህ ዶላር ካሳ መስጠቱን አስታውቋል፡፡ ቦይንግ 777-300 ኢ አር የተሰኘው የሲንጋፖር አውሮፕላን 221 መንገደኞችን እና 18 የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ ከለንደን ሄትሮው ተነስቶ ሲንጋፖር ቻንጊ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ አቅዶ…

https://www.fanabc.com/archives/249291
የፌዴራል መንግሥት ግዥ እና ንብረት አሥተዳደር አዋጅ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግሥት ግዥ እና ንብረት አሥተዳደር አዋጅን አጽድቋል፡፡ አዋጅ ከዚህ በፊት በመንግሥት ግዥና ንብረት አሥተዳደር ሂደትና ትግበራ ወቅት በአፈጻጸም ሲያጋጥሙ የነበሩና ለመልካም አሥተዳደር ችግር ምክንያት የሆኑ የአሠራር ጉድለቶችን ለማረም እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ እንዲሁም ወጥ የሆነ የግዥ ማዕቀፍን ተግባራዊ…

https://www.fanabc.com/archives/249332
የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ አጸደቀ፡፡ የሕዝብ በዓላት በሥነ-ምግባር የታነጻ ሀገር ወዳድ ማሕበረሰብ ለመገንባት ብሎም ለሀገርና ሕዝብ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ሕጋዊ ዕውቅና መስጠት አስፈላጊ መሆኑ በስብሰባው ላይ ተገልጿል፡፡ በዚህም የሕዝብ በዓላት የሚከበሩት በሀገር…

https://www.fanabc.com/archives/249335
አምባሳደር ታዬ ከደቡብ አፍሪካና ቻይና ሚኒስትሮች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከደቡብ አፍሪካና ቻይና ሚኒስትሮች ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ታዬ በሩሲያ እየተካሄደ ከሚገኘው የብሪክስ ስብሰባ ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ታዬ ከቻይና አቻቸው ዋንግ ይ ጋር ባደረጉት ውይይትም ፥ በተለያዩ የትብብር መስኮች የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል ነው የተባለው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሰደር ታዬ ከደቡብ አፍሪካ የአለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ጋርም በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ... https://www.fanabc.com/archives/249340
2024/11/16 12:35:50
Back to Top
HTML Embed Code: