Telegram Web Link
እውን በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የጅምላ አፈሳ እየተፈጸመ ነውን?

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ከሰሞኑ የጅምላ አፈሳ ድርጊት እየተፈጸመ ነው የሚሉ መረጃዎች በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲሰራጩ ይስተዋላል፡፡ የጅምላ አፈሳው በተለይ በወጣቶች እና በቀን ሥራ በተሰማሩ ዜጎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን እንዲሁም ከታፈሱ በኋላ በትምህርት ቤቶችና ሌሎች ቦታዎች ውስጥ እንዲቆዩ እንደሚደረግ ይነገራል፡፡ በቀጣይም የታፈሱ ዜጎችን…

https://www.fanabc.com/archives/271044
ከጋምቤላ ክልል ከ900 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ተደረገ አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጋምቤላ ክልል በተያዘዉ በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ብቻ ከ900 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደርጓል፡፡ ክልሉ በሩብ ዓመቱ 325 ኪሎግራም ወርቅ ገቢ ለማድረግ ያቀደ ቢሆንም ከ900 ኪሎግራም በላይ ወርቅ ገቢ በማድረግ ከዕቅዱ…

https://www.fanabc.com/archives/271043
ተጠባቂው የዛሬ ምሽት የቦክስ ፍልሚያ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ58 ዓመቱ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ ጄክ ጆሴፍ ፖል ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ዛሬ ምሽት በአሜሪካ ቴክሳስ አርሊንግተን ይካሄዳል፡፡ ከዓመታት በፊት ቀጠሮ በተያዘለት ፍልሚያ የዓለም የቦክስ ባለታሪኩ ማይክ ታይሰን እና በ1997 ማይክ ታይሰን ልደቱን ካከበረለት ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ እና ዩቲዩበር ጄክ ጆሴፍ ፖል ጋር…

https://www.fanabc.com/archives/271025
በቻይና ምክትል የህዝብ ደህንነት የተመራ ልዑክ የአዲስ አበባ ፖሊስን እየጎበኘ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ምክትል የህዝብ ደህንነት ሺ ያንጁን የተመራ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ፖሊስ የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል። በጉብኝቱ በኢትዮጵያ የቻይና አምባደር ሺን ሀይን፣ የቤይጂንግ ከተማ ፖሊስ ኃላፊ ጃኦ ጃንሺን እንዲሁም የሪፐብሊኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እና የማኔጅመንት አባላቶች የሁለቱን ወንድማማች…

https://www.fanabc.com/archives/271055
አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ ነው – አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ምርታማነት ለማሳደግ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ፡፡ በድሬዳዋ ከተማ የኢንዱስትሪ ልምድ ማሰራጫ መድረክ ላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት÷ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ለተጀመረው የብልፅግና ጉዞ ወሳኝ ነው። የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ምርታማነትና ውጤታማነት ለማሳደግ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን የማስፋፋት…

https://www.fanabc.com/archives/271063
Live stream finished (36 minutes)
ፌዴራል ፖሊስና የቻይና ሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና የቻይና ሕዝብ ደኅንነት ምክትል ሚኒስትር ዢ ያንጁን በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች በቅንጅት ለመሥራት ስምምነት በደረሱባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀልን በመከላከል፣ በተፈላጊ ወንጀለኞች ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ እና ግብዓት…

https://www.fanabc.com/archives/271073
ኢትዮጵያ ሶማሊላንድ ያካሄደችውን ዴሞክራሲዊ ምርጫ አደነቀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ሶማሊላንድ ከትናንት በስቲያ ላካሄደችው ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ምርጫ ለመንግሥቷ እና ሕዝቧ ያላትን አድናቆት ገለጸች፡፡

የሶማሊላንድ የምርጫ ኮሚሽን ሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ማካሄዱን በመጥቀስ ለዚህም ያላትን አድናቆት ገልጻለች፡፡

ይህም የሶማሊላንድ መንግሥት አሥተዳደር የዳበረ መሆኑን ያሳል ነው ያለችው ኢትዮጵያ፡፡
ኢትዮጵያን ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ተመራጭ የጎብኚ መዳረሻ ለማድረግ በሚከናወነው ሥራ የቱሪስት እና የኮንፈረንስ ቪዛዎች ላይ እስከ 25 በመቶ ቅናሽ መደረጉ የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተመላከተ፡፡

የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ለማበረታታት በ2016 ዓ.ም በፀደቀው የኢሚግሬሽን ደንብ ቁጥር 550/2016 የአገልግሎት ዋጋ ተመን የዋጋ ቅናሽ መደረጉን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ማስተዋል ገዳ አስታውሰዋል፡፡

በዚህም የቱሪስት ቪዛ ከዚህ በፊት ከነበረው 25 በመቶ ቅናሽ በማድረግ ኢትዮጵያ በዓለም የቱሪዝም መዳረሻ ተመራጭ እንድትሆን እየተደረገ ባለው ጥረት የበኩሉን ሚና እያበረከተ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያን የዓለማችን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማእከል ለማድረግ የኮንፈረንስ ቪዛ ክፍያ ከዚህ በፊት ከነበረው ተመን በ23 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

https://www.fanabc.com/archives/271094
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢዝነስ ተጓዦች ዘርፍ ለ5ኛ ጊዜ ተሸለመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2024 የቢዝነስ ተጓዦች ሽልማት ውድድር ‘ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ’ በመባል ተሸለመ፡፡

ሽልማቱ በዘርፉ ለአምስተኛ ተከታታይ ዓመታት የተገኘ መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከሽልማቱ በኋለም አየር መንገዱ ደንበኞቹ ለሰጡት ድጋፍ ምሥጋና አቅርቧል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ከሆኑት ማርያም ሳሊም ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ውይይቱ ፍሬያማ እንደነበር ገልጸዋል።

ዳይሬክተሯ በከተማዋ እየተሰራ ያለውን ስራ መጎብኘታቸውን የገለፁት ከንቲባ አዳነች ከጉብኝቱ በኋላ ይበልጥ ለመደገፍ የሚያስችል ውይይት ማካሄዳቸውን ገልፀዋል፡፡

ከንቲባዋ የዓለም ባንክ በከተማ አስተዳደሩ በሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ፣ በአቅም ግንባታ፣ በተማሪዎች ምገባ፣ በትራንስፖርትና መንገድ ዘርፍ እንዲሁም በውሃና ፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የአሜሪካ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛን አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የአሜሪካ የሱዳን ልዩ መልክተኛ ቶም ፔርሎን ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱ የሱዳን ግጭት ዘላቂ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

በተመሳሳይ ከጃፓን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳድር ሺሚዙ ሺንሱኬ ጋር የተወያዩት አምባሳደር ምስጋኑ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከጃፓን መንግስት ጋር በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


https://www.fanabc.com/archives/271062
2024/11/16 11:02:46
Back to Top
HTML Embed Code: