Telegram Web Link
ኢንስቲትዩቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አቅም የተላበሱ የደህንት ካሜራዎችን ለሶማሌ ክልል አበረከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሰው ሰራሽ አስተውሎት አቅም የተላበሱ የተለያዩ የደህንት ካሜራዎችን ለሶማሌ ክልል በድጋፍ አበረከተ፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በርክክቡ ወቅት፤ ድጋፉ ኢንስቲትዩቱ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት በመንደፍ ከተሞችን ለነዋሪዎችና ለጎብኝዎች ምቹ ለማድረግ የሚሰራው ተግባር አካል መሆኑን ተናግረዋል። ካሜራዎቹ 70 ሚሊየን ብር ግምታዊ…

https://www.fanabc.com/archives/263853
የኢሬቻ በዓል እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቅቋል – አቶ ሃይሉ አዱኛ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉን አቀፍ ዝግጅት መደረጉን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡ መስከረም 25 እና 26 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከበሩትን የዘንድሮው ሆረ ፊንፊኔ እና ሆረ አርሰዴ ኢሬቻን አስመልክቶ አቶ ሃይሉ አዱኛ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች በሰጡት ማብራሪያ፥ ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ…

https://www.fanabc.com/archives/263858
እስራኤል የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ነስራላህን መግደሏን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ በሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ላይ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደች የምትገኘው እስራኤል የቡድኑን መሪ ሀሰን ነስራላህን መግደሏን አስታውቃለች። የእስራኤል መከላከያ ሃይል እንደገለጸው፤ ሀሰን ነስራላህ ቤይሩት ውስጥ በአርብ ምሽት ጥቃት ተገድለዋል። ሂዝቦላይ ጉዳዩን አስመልክቶ ያለው ነገር አለመኖሩን የገለጸው የቢቢሲ ዘገባ፤ የእስራኤል የአየር ጥቃት ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ እንደሆነ ገልጿል።…

https://www.fanabc.com/archives/263863
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ። ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ ኒውካስል ዩናይትድ የሊጉን መሪ ማንቼስተር ሲቲን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል። እንዲሁም ቀን 11 ሰዓት ላይ አርሰናል ሌስተር ሲቲን፣ ብሬንትፎርድ ዌስትሃም ዩናይትድን፣ ቼልሲ ብራይተንን፣ ኤቨርተን ክሪስታል ፓላስን እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ፉልሃምን የሚያስተናግዱባቸው ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።…

https://www.fanabc.com/archives/263867
መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ትብብር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ዓለም አቀፍ ትብብር እንደሚጠይቅ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገለጹ፡፡ ዶ/ር መቅደስ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን ላይ ለመምከር በተዘጋጀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት÷ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ…

https://www.fanabc.com/archives/263879
ድንበር ተሻጋሪ የዜጎች ፍልሰትን የተመለከተ ቀጣናዊ አውደ ጥናት በቀጣዩ ሳምንት በኢትዮጵያ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)ድንበር ተሻጋሪ የዜጎች እንቅስቃሴና ፍልሰትን የተመለከተ ቀጣናዊ አውደ ጥናት በቀጣዩ ሳምንት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) አስታወቀ። መስከረም 22 እና 23 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄደው አውደ ጥናቱ የኢጋድ አባል አገራት ድንበር ዘለል የዜጎች እንቅሰቃሴና ፍልሰት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በመለዋወጥ ቀጣናዊ ትስስር እና…

https://www.fanabc.com/archives/263882
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የለሚ ብሔራዊ የሲሚንቶ ፋብሪካን መርቀው ሥራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀን 150ሺህ ኩንታል የማምረት አቅም ያለውን የለሚ ብሔራዊ የሲሚንቶ ፋብሪካ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

ይህን ተከትሎ ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷" ይህ ሜጋ ፕሮጀክት የመንግሥታችን በፍጥነት፣ በግዝፈት እና በንፅህና የመገንባት ጽኑ አቋም ማሳያ ነው" ብለዋል።

እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን በፍጥነት እና በብቃት አጠናቅቆ ዝግጁ የማድረግ ተምሳሌት መሆኑንም ገልፀዋል።

ይህ በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ተመሳሳይ ፋብሪካዎች ተደምረው የሚያመርቱትን 50 ከመቶ የሚያመርት ፋብሪካ እውን እንዲሆን ለተሳተፉ በሙሉም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ከሁለት አመታት በኋላ ወደዚህ ስፍራ ስመለስ የአመራር መርሆዎቻችን ማሳያ በሆነው በሥራው ፍጥነት ተደንቄያለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱ በመሰል ጠንካራ ሥራ መጪው ትውልድ ድህነትን እንደማይወርስ ይልቁንም ለእድገት እና ብልጽግና ጥሩ መደላድል እንደሚጠብቀው ያሳያል ብለዋል።
https://www.fanabc.com/archives/263885
የለሚ ብሔራዊ የሲሚንቶ ፋብሪካ የምረቃ መርሃ ግብር- በምስል
2024/11/16 12:26:50
Back to Top
HTML Embed Code: