Telegram Web Link
በፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ 3 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲዬም ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት 3 ሠዓት ከ30 ላይ ሐዋሳ ከተማ ከስሁል ሽረ እንዲሁም 10 ሠዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ይጫወታሉ፡፡ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ደግሞ ባሕር ዳር ከተማ እና አዳማ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

https://www.fanabc.com/archives/263759
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት እንዲከበር ያደረጉ አካላትን አመሰገነች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓል በሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓትና ድምቀት ተከብሮ እንዲውል ላደረጉ አካላት ምሥጋና አቀረበች፡፡ ትናንት በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል ዐደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የምሥጋና መግለጫ መልዕክት አስተላልፋለች፡፡ በቀረበው መልዕክትም ሕዝበ-ክርስቲያኑ ዝናብና ቁር ሳይበግረው በጽናትና ፍጹም…

https://www.fanabc.com/archives/263767
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‹‹ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ዘጠነኛው የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮን ስያሜን ያገኘንበት ማሳያችን ነው - ከማህደራችን።
ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ከአካባቢው ነዋሪ ማህበረሰቦች ጋር አብሮ በመስራት የተፈጥሮ አካባቢን በመጠበቅ፤ በተለይም የደብረሲና ማርያም አንድነት ገዳምን በመጠበቅ ረገድ ከፍ ያለ አስተዋጻኦ ያለው ነው። በአካባቢው የሚከሰቱ ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋዎችን በተቻለ አቅም በመቅረፍ እና የገዳሙ እንቅስቃሴ በማያውክ መልኩ እንዲቀጥል የተደረገው ጥረት ከፍ ያለ ሲሆን የጎርጎራ አካባቢ ባህላዊና ታሪካዊ ፋይዳውን ጠብቆ እንዲቆይም አስችሏል።›› - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
የመስቀል በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዓሉ በተለያዩ ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ-ሥርዓቶች ነው በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው። በትናንትናው ዕለት የመስቀል ደመራ በመላ ሀገሪቱ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት መከበሩ ይታወሳል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/263771
በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል ዐደባባይ የተከናወነው የመስቀል ደመራ በዓል በምስል
የቡድን 7 አባል ሀገራት በኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡድን ሰባት አባል ሀገራት በኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡

ኢትዮጵያ በጣሊያን ሲራኩስ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድን ሰባት አባል ሀገራት የግብርና መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያን የግብርና ኢንቨስትመንት ልምድ ማካፈላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ከፍተኛ ጸጋ እንድትጠቀም የኢትዮጵያን የግብርና ፖሊሲ ከፍተኛ ዕገዛ ማድረጉን የገለጹት ሚኒስትሩ÷ ከዚህ ጋር በተያያዘም በሜካናይዝድ እርሻ እያስመዘገበች ያለውን አበረታች ውጤት አብራርተዋል፡፡

የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሂደት ኢትዮጵያ ስንዴን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ምርቶች ስኬታማ ተግባራትን እያከናወነች መሆኗን ጠቅሰው÷ ለበለጠ ውጤት በትብብር መሥራት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት የኢትዮጵያን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ-ካርታ ጨምሮ በዘርፉ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን እና እየተመዘገቡ ያሉ አበረታች ውጤቶችን በመረዳት የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በጎንደር ከተማ እየተከበረ የሚገኘው የደመራ እና የመስቀል በዓል -በምስል
2024/09/28 08:20:13
Back to Top
HTML Embed Code: