Telegram Web Link
የመስቀል ደመራ በዓል በባህርዳር ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በባሕር ዳር ከተማ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ በጸሎት ተጀምሯል፡፡

በዓሉን በጸሎት ያስጀመሩት የምዕራብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሰላማ ናቸው።

በዓሉ የአድባራትና ገዳማት አባቶችና አገልጋዮች፣ የባሕዳር ከተማ አስተዳደር የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የከተማው ሕዝበ ክርስቲያን በተገኘበት በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

በደሳለኝ ቢራራ
ምክር ቤቱ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ምክር ቤቱ ባስተላለፈው መልዕክት ÷ የመስቀል ደመራ በዓል በሕዝቡ ትልቅ ሐይማኖታዊና ሀገራዊ በዓል ሲሆን ፤ ክብረ-በዓሉ ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ብሔራዊ ቅርሶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው ብሏል፡፡

በዚህም በዓሉ ሐይማኖታዊ ትውፊቱንና ሥርዓቱን ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ለዘመናት ሲከበር ቆይቷል ሲል ገልጿል፡፡

የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ሲከበር ከሐይማኖታዊ ሥርዓተ አምልኮ ባለፈ ለዜጎች ማህበራዊ ትስስር መጠናከር፣ ለሀገራችን የቱሪስት መዳረሻ ዕድገትና ለገፅታ ግንባታ ያለው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑንም ምክር ቤቱ ጠቅሷል፡፡

የዘንድሮ የደመራ በዓልን በድምቀት በተለያዩ ሐይማኖታዊ ዝግጅቶች እየተከበረ ሲሆን ÷ በዓሉ በየአካባቢው ሐይማኖታዊ ስርዓቱንና ትውፊቱን ጠብቆ በሠላምና በአብሮነት ስሜት እንዲከበር ሁሉም በየደረጃው የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

በዓሉ ሲከበር ያጡ የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና ካለን በማካፈል በአብሮነትና በመረዳዳት ስሜት ሊሆን ይገባልም ብሏል ምክር ቤቱ፡፡
የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተከበረ ይገኛል፡፡ በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፣ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካና ሚኒስትሮች እንዲሁም የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቱሪስቶች በበዓሉ ላይ…

https://www.fanabc.com/archives/263691
ቻይና ለኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ለኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ገለጹ፡፡ የስራና ክሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ቼን ሃይ ጋር ሁለቱ ወገኖች በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መመክራቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በቻይና እድገትና ልማት ውስጥ…

https://www.fanabc.com/archives/263694
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከግሪክና ሴራሊዮን አቻዎቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ኢትዮጵያ ከግሪክ እና ሴራሊዮን ጋር ያላትን ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ከሁለቱ ሀገራት አቻዎቻቸው ጋር ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ ከግሪኩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊኦርጎስ ጀርፐትራይተስ ጋር ባደረጉት ውይይት ግሪክ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት አባል ሆና በመመረጧ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። አምባሳደር ታዬ…

https://www.fanabc.com/archives/263697
መስቀል የትዕግሥት፣ የዕርቅና የሰላም ምልክት መሆኑን ማሰብ ያስፈልጋል – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መስቀል የትዕግሥት፣ የዕርቅና የሰላም ምልክት መሆኑን ማሰብ ያስፈልጋል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ የመስቀል በዓልን አስመልክተው ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ ቅዱስ መስቀል ከኃጢአት ጥላ፣ ከጥፋት ጨለማ የወጣንበት ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት የነፍሳችን ብርሃን፣ የሕይወታችን መብራት ነው ብለዋል። ከበረቱ፣ ከታገሉ እና…

https://www.fanabc.com/archives/263701
በዓሉን ፍቅራችንና አንድነታችን በማጎልበትና በመደጋገፍ ልናከብረው ይገባል – ከንቲባ ከድር ጁሃር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓልን ስናከበር ፍቅራችንንና አንድነታችንን በማጎልበትና በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ። ከንቲባው የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ የመስቀል ደመራ በዓል በአደባባይ ከሚከበሩ ድንቅ እና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ከተቀዳጁ በዓላት መካከል አንዱ መሆኑን አንስተዋል። በዓሉን ስናከበር የእርስ…

https://www.fanabc.com/archives/263704
የመስቀል ደመራ በዓል በተለያዩ ክልሎች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል የተለያዩ ክልሎች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ በዓሉ በጋምቤላ ከተማ በርካታ ምዕምናን በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ሲሆን በአከባበር ስነ ስርዓቱ የዕምነቱ አባቶች፣ ምዕመናንና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች መታደማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያሳያል፡፡ በተመሳሳይ በዓሉ በድሬዳዋ አስተዳደር የሀይማኖት አባቶች እና በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በምድር ባቡር አደባባይ…

https://www.fanabc.com/archives/263707
መስቀሉ ባስተማረው መሰረት ችግሮችን በሰላም በእኩልነትና በፍቅር መፍታት ይገባል – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን እየተፈታተኑ ያሉ ችግሮችን መስቀሉ ባስተማረው መሰረት በሰላም በእኩልነትና በፍቅር መፍታት እንደሚገባ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ገለጹ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ኃይማኖት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በደማቅ ሥነ ሥርዓት…

https://www.fanabc.com/archives/263716
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፋና ቀለማት በዚህ ሳምንት
በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ።

በድሬዳዋ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ ያሬድ ብርሃኑ ባስቆጠራት ግብ ሲመራ ቢቆይም፤ ፋሲል ከነማ ቢኒያም ላንቃሞ ከእረፍት መልስ ባስቆጠራት ግብ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

ምሽት 1 ሰዓት ቀጥሎ በሚካሄደው የሊጉ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ይገናኛሉ።
የመስቀል ደመራ በዓል በተለያዩ ከተሞች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል በተለያዩ ከተሞች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዓሉ በጅማ ከተማ በደማቅ እየተከበረ ሲሆን የእምነቱ ተከታዮች እና በከተማዋ ከሚገኙ 17 ደብራት የተውጣጡ የተለያዩ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች እንዲሁም አባቶች በዓሉን በዝማሬና በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እያከበሩ ይገኛሉ። የመስቀል በዓል ስነ ስርዓቱን የፈለገሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ያዘጋጀ…

https://www.fanabc.com/archives/263723
2024/11/16 11:02:18
Back to Top
HTML Embed Code: