Telegram Web Link
በአንድ ቀን በደረሱ ሁለት የጀልባ አደጋዎች የ11 ስደተኞች ሕይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣልያን የባሕር ዳርቻ ትናንት በደረሱ ሁለት የጀልባ አደጋዎች ቢያንስ የ11 ስደተኞች ሕይዎት ሲያልፍ ከ60 የሚልቁት የደረሱበት አለመታወቁ ተሰምቷል፡፡ በላምፔዱሳ ደሴት አቅራቢያ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ባጋጠማት የመስጠም አደጋ የ51 ተጓዦችን ሕይወት የታደገው የጀርመኑ በጎ አድራጎት ተቋም፥ በታችኛው የመርከቧ ወለል ላይ 10 አስከሬኖች ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ እንዲሁም አንድ…

https://www.fanabc.com/archives/250214
በትግራይ ክልል 400 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ተሠራጨ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ለ2016/17 የምርት ዘመን ከሚያስፈልገው 700 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ከ400 ሺህ ኩንታል በላይ ለአርሶ አደሮች መድረሱ ተገለጸ፡፡ ቀሪው 300 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ በሚቀጥሉት 10 ቀናት ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ጊዜያዊ አሥተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ኃላፊ ኢያሱ አብረሃ (ዶ/ር) አመላክተዋል፡፡ እንዲሁም ለምርት ዘመኑ…

https://www.fanabc.com/archives/250257
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሠላም ቀጣይነት እየሠራች ነው – ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለቀጣናውና ለአፍሪካ ሠላም ቀጣይነት ባለው መልኩ ስትሠራ መቆየቷንና አሁንም ብዙ ዋጋ እየከፈለች መሆኗን የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) ገለጹ። በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ በሩሲያ ቭላዲቮስቶክ በተጀመረው የብሪክስና አጋር ሀገራት ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም ላይ…

https://www.fanabc.com/archives/250261
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ፋና80 - በዚህ ሳምንት እነማን ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋሉ? እነማንስ ይሸኛሉ?
Live stream finished (34 minutes)
ከንቲባ አዳነች ከሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ተወካዮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ከሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል። ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “የተደራጀ የሲቪል ማህበራት ተሳትፎ ለሁለንተናዊ ብልጽግና “ በሚል መሪ ቃል በከተማችን ከሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ተወካዮች ጋር ተወያይተናል” ብለዋል። የሲቪል ማኅበራት የተለያዩ የማህበረሰብ አካላትን የሚወክሉ፣ በዴሞክራሲ ማበብ፣…

https://www.fanabc.com/archives/250264
ሐሰተኛ የመረጃ ስርጭትን ለመታገል የወቅቱን የሚዲያ ባህሪ መገንዘብ እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተስፋፋ ያለውን ሐሰተኛ መረጃ በአግባቡ ለመታገል የወቅቱን የሚዲያ ባህሪ መረዳት እንደሚገባ በብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አዲሱ አረጋ ገለጹ። በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ከሰኔ 9 እስከ 12 ቀን 2016 በሚካሔደውና “ዎርልድ ማጆሪቲ ፎር መልቲፖላር ኦርደር” በሚል መሪ ሐሳብ በሩሲያ…

https://www.fanabc.com/archives/250272
የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው ጎርጎራ አሁናዊ ገጽታ በምስል
በኦዲት ግኝት መመለስ ከነበረበት ከ443 ሚሊየን ብር በላይ የተመለሰው 11 በመቶ ብቻ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 92 ተቋማት በኦዲት ግኝት መሰረት ተመላሽ እንዲያደርጉ አስተያየት ከተሰጠበት 443 ሚሊየን 23 ሺህ 846 ብር እና 23 ሺህ 55 ዶላር ውስጥ የተመለሰው 48 ሚሊየን 217 ሺህ 965 ብር ብቻ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የፌደራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ በተቋማቸው የተከናወኑ ሥራዎችን ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/250277
ቻይና ለዩክሬን ቀውስ መፍትሔ ለማምጣት እንደምትሠራ አረጋገጠች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጋር በመሆን ለዩክሬን ቀውስ መፍትሔ ለመስጠት ጥረት እንደምታደርግ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬን በፈረንጆቹ 2022 ወደ ሩሲያ ከተካተቱት ክልሎች ወታደሮቿን ካስወጣች በኋላ እና ኔቶ የመቀላቀል ዕቅዷን ከተወች ሩሲያ ተኩስ አቁማ ድርድር እንደምትጀምር መናራቸው ይታወሳል። በፕሬዚዳንቱ የተኩስ…

https://www.fanabc.com/archives/250280
አቶ ኡሞድ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ርብርብ እንዲደረግ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ርዕሰ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ጠየቁ፡፡ በክልሉ የግብርና ኢንቨስትመንት ተግዳሮቶችን እና የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በሚመለከት ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የምክክር መድረክ በጋምቤላ ከተማ ተካሂዷል። አቶ ኡሞድ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ባለሃብቶች በክልሉ ያለውን…

https://www.fanabc.com/archives/250283
ብሪክስ ለፍትሐዊ የዓለም የኢኮኖሚና ፋይናንሰ ስርዓት የሚሰራ የትብብር ማዕቀፍ ነው - አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪክስ ለዓለም ብዙሃን ማህበረሰብ ፍላጎቶች የቆመና ለፍትሐዊ የዓለም የኢኮኖሚና ፋይናንስ ስርዓት የሚሰራ የባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ የትብብር ማዕቀፍ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

በሩሲያ ቭላዲቮስቶክ እየተካሄደ ያለው የብሪክስ አባልና አጋር አገራት ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፎረም ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ የልዑካን ቡድን በፎረሙ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።


https://www.fanabc.com/archives/250291
በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ የ6ኛ ክፍል ፈተና ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነገ ጀምሮ እስከ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮው እንዳስታወቀው÷ በ183 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ86 ሺህ 222 ተማሪዎች ፈተናው ይሰጣል፡፡ በፈተና ጣቢያዎቹም ከ2 ሺህ 200 በላይ ፈታኞች፣ ከ700 በላይ ሱፐር ቫይዘሮች፣ 183 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች…

https://www.fanabc.com/archives/250296
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“አወሊያ”- የፊታችን እሁድ ጠዋት 3፡30 ይጠብቁን
የልብ ህመም በምን ምክንያት ይከሰታል?

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የልብ ህመም የልብን ስራ የሚያስተጓጉሉ የተለያዩ የልብና የደም ዝውውር ችግሮችን የሚያጠቃልልና ከባድ ከሚባሉት የህመም አይነቶች የሚመደብ ነው። የልብ የጤና ችግሮች በሁለት ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦ ከውልደት ጋር (በተፈጥሮ) የሚመጡ እና ከውልደት በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች የሚመጡ የልብ ህመም በመባል ይታወቃሉ። በተፈጥሮ የሚመጣው የልብ ህመም፡- ሕፃናት ሲወለዱ ጀምሮ አብሮ የሚመጣ…

https://www.fanabc.com/archives/250311
2024/06/18 13:32:19
Back to Top
HTML Embed Code: