Telegram Web Link
#WoldiaUniversity

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም ነባር እና አዲስ ገቢ መደበኛ የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም የሁሉም ነባር መደበኛ ተማሪዎች፣ በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችው የማለፊያ ውጤት አምጥታችሁ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ 

የመማር ማስተማር ሥራ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
#AAETQRA

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የሁለት የግል ኮሌጆች ካምፓስን የዕውቅና ፍቃድ ሰረዘ፡፡

ባለስልጣኑ ያደረገውን ድንገተኛ ኢንስፔክሽን ተከትሎ በ44 የግል ኮሌጆች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል፡፡

በዚህም ሸገር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ እና አልፋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ግሎባል ካምፓስ "ያለባቸውን ክፍተት ለማስተካከል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው" የዕውቅና ፍቃዳቸው የተሰረዘ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

ልቀት ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ "የተወሰነ ማስተካከያ ያደረገ ቢሆንም፤ ሙሉ በሙሉ ለማስተካከል በጠየቀው መሰረት የአንድ ወር ተጨማሪ ጊዜ" በባለስልጣኑ ተሰጥቶታል፡፡

የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ከነበሩ ተቋማት መካከል ስምንት ኮሌጆች ያለባቸውን ክፍተት ማስተካከላቸውን ባለስልጣኑ በምልከታ ማረጋገጡን አሳውቋል፡፡ እነዚህም፦

1. ያኔት ኮሌጅ 6 ኪሎ ካምፓስ፣
2. ዳማት ኮሌጅ ጊዮርጊስ ካምፓስ፣
3. ያኔት ኮሌጅ ሰፈረ ሰላም ካምፓስ፣
4. ኤክስፕረስ ኮሌጅ፣
5. ቅድስት ሀና ኮሌጅ፣
6. ግራንድ ማርክ ኮሌጅ፣
7. ኩዊንስ ኮሌጅ ሀና ካምፓስ እና
8. ሀራምቤ ኮሌጅ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የዕውቅና ፍቃዳቸው ታግዶ የነበሩና ያለባቸውን ክፍተት በተሰጣቸው ጊዜ ማስተካከላቸው በባለስልጣኑ በምልከታ የተረጋገጠላቸው 15 ተቋማት የዕውቅና ፍቃድ እገዳው ተነስቶላቸዋል፣ የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህም፦
1. ብራይት ኮሌጅ ልደታ ካምፓስ፣
2. ብራይት ኮሌጅ ጀሞ ካምፓስ፣
3. ልቀት ኮሌጅ 4 ኪሎ ካምፓ'ስ፣
4. ላየን ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ፣
5. ኩዊንስ ኮሌጅ መድኃኒዓለም ካምፓስ፣
6. ሳትኮም ኮሌጅ፣
7. ሀርመኒ ኮሌጅ ሀና ማርያም ካምፓስ፣
8. ኩዊንስ 5 ኪሎ ካምፓስ፣
9. ሃርመኒ ቅሊንጦ ካምፓስ፣
10. አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ፣
11. አረና ኮሌጅ፣
12. ጌጅ ኮሌጅ ሾላ ካምፓስ፣
13. ሀጌ ኮሌጅ፣
14. ኩዊንስ ኮሌጅ ዮሃንስ ካምፓስ እና
15. ኪያሜድ ኮሌጅ እንቁላል ፋብሪካ ካምፓስ እንደሆኑ ባለስልጣኑ ጠቁሟል፡፡

የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው የነበሩ 18 ተቋማት በተሰጣቸው ጊዜ ያለባቸውን ክፍተት ያስተካከሉ መሆኑን ባለስልጣኑ በምልከታ አረጋግጧል፡፡ እነዚህም፦

1. ዌልነስ ኮሎጅ፣
2. ግሬት ኮሌጅ ቡልቡላ ካምፓስ፣
3. ቢኤስቲ ኮሌጅ 18 ካምፓስ፣
4. ክቡር ኮሌጅ፣
5. ፋርማ ኮሌጅ፣
6. ቅድስት ልደታ ኮሌጅ፣
7. ኤግል ኮሌጅ፣
8. አፍሪካ ጤና ኮሌጅ፣
9. ናሽናል ኮሌጅ፣
10. ካርቫርድ ኮሌጅ፣
11. ሰቨን ስታር ኮሌጅ፣
12. ራዳ ኮሌጅ፣
13. ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ካራ አሎ ካምፓስ፣
14. ኬቢ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ፣
15. ያጨ ኮሌጅ፣
16. ኪያሜድ ኮሌጅ 22 ካምፓስ፣
17. ናይል ሳይድ ኮሌጅ እና
18. ኪያሜድ ኮሌጅ አየር ጤና ካምፓስ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለ3ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል፡፡

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 06 እና 07/2017 ዓ.ም ይከናወናል ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ "በተቋሙ ውስጥ እየተሰጡ ያሉ ስልጠናዎች ባለመጠናቀቃቸው ምክንያት" የምዝገባው ቀን ወደ መስከረም 13/2017 ዓ.ም የተቀየረ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት መስከረም 14/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
#DambiDolloUniversity

ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 22 እና 23/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም አዲስ ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችው እና በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ወደ ፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
#AksumUniversity

አክሱም ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም ከዚህ ቀደም ስትማሩበት በነበራችሁበት ግቢ በአካል በመገኘት በተጠቀሱት ቀናት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

በ2016 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁ ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም አዲስ ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ተገልጿል።

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
#RayaUniversity

ራያ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 13 እና 14/2017 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አሳውቋል።

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በራያ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች በቀጣይ ጥሪ እንደሚደረግ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
#WerabeUniversity

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለነባር የቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የ2014 እና 2016 ባች (3ኛ እና 1ኛ ዓመት) የቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። በቅጣት ለመመዝገብ መስከረም 22/2017 ዓ.ም ብቻ።

የ2013 ባች (5ኛ ዓመት) የቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 5 እና 6/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። በቅጣት ለመመዝገብ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ብቻ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የሪሚዲያል ፕሮግራም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቃቹ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
#Update

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ.ም 2ኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) እና ለድኅረ ምረቃ ትምህርት የማመልከቻ ጊዜን አራዝሟል፡፡

በዚህም የማመልከቻ ግዜው እስከ መስከረም 8/2017 ዓ.ም መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና እና የመግቢያ ፈተና ያለፉ ለትምህርት የማመልከቻ ግዜ ወደፊት እንደሚገለፅ ተቋሙ አስገንዝቧል፡፡

ለመግቢያ ፈተና ለማመልከት 👇
https://portal.aau.edu.et

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስሩ ያለው የትግርኛ ቋንቋ እና ስነ ጹሁፍ ትምህርት ክፍል እንዲዘጋ ወሰነ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ18 ዓመት በፊት የተቋቋመውን የትግርኛ ቋንቋ እና ስነ ጹሁፍ ትምህርት ክፍልን፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ሊዘጋ ነው። በፍልስፍና ትምህርት ክፍል በመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጠው ትምህርትም፤ ከዚህ ዓመት ጀምሮ እንዲቋረጥ ዩኒቨርስቲው ውሳኔ አስተላልፏል።

አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ ከእዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው፤ የትምህርት ክፍሎቹ ላለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት አዲስ ተማሪዎችን ባለመቀበላቸው ነው። የአልማዝ ኢዮቤሊዮውን ለማክበር የተቃረበው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ከሐምሌ 2015 ዓ.ም. ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ መሆኑን ተከትሎ በስሩ ያሉ የትምህርት ክፍሎችን በአዲስ መልክ በማደራጀት ላይ ይገኛል።

ከመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራስ ገዝ በመሆን የመጀመሪያው የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ የመልሶ ማደራጀት ስራውን በማከናወን ላይ ያለው የተማሪዎች የትምህርት ክፍል ምርጫዎችን መሰረት በማድረግ ነው። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው የመልሶ ማደራጀትን የሚመለከት የዩኒቨርሲቲው ሰነድ፤ “የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎባቸው የሚቀጥሉ”፣ “የሚጣመሩ”፣ “ተዋህደው አዲስ የትምህርት ክፍል የሚመሰርቱ”፣ “የሚጠናከሩ” እና “የሚቋረጡ” የትምህርት አይነቶችን ዘርዝሯል።

ዩኒቨርሲቲው እንዲቋረጡ ውሳኔ ካስተላለፈባቸው የትምህርት አይነቶች መካከል የትግርኛ ቋንቋ እና ስነ ጹሁፍ ይገኝበታል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ሲሰጥ የቆየው፤ በትግርኛ ቋንቋ፣ ስነ ጹሁፍ እና ፎክሎር ትምህርት ክፍል ስር ነበር። ሆኖም የትምህርት ክፍሉ ባለፉት ዓመታት ባጋጠመው የተማሪዎች እጥረት ምክንያት ከዘንድሮው የትምህርት ዘመን ጀምሮ እንዲዘጋ መወሰኑን የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ አቶ ሀድጉ ተካ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/14178/


ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
ጅማ ዩኒቨርስቲ የመደበኛ ነባር ቅድመ-ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ማሳሰቢያ፤

1. የአዲስ ገቢ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም አመልካቾች ምዝገባ የሚፈጸመው የNGAT ፈተና ውጤት ከተለቀቀ በኋላ በሚወጣው ማስታወቂያ መሠረት ይሆናል፡፡

2. የRemedial ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው በ2017ዓ.ም ለዩኒቨርስቲው ከሚመደቡ የፍሬሽማን ፕሮግራም ተማሪዎች ጋር ስለሆነ ይህ የምዝገባ ሰሌዳ አይመለከታቸውም።

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በዚህ ዓመት 5 ሺሕ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በዚህ ዓመት ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን አወዳድሮ 5 ሺሕ ተማሪዎች ለመቀበል ዝግጅት ላይ መሆኑን፤ የዩኒቨርሲቲው የኮምንኬሽንና ዓለማቀፋዊ ግንኙነት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳምሶን መኮነን ለ#አሐዱ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ፕሬዝዳንቱ "የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎችን እንደ ብቃታቸው በማወዳደርና በመቀበል እንዲማሩ ይደረጋል" ነዉ ያሉት።

ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፣ በመንግሥት እስኮላርሽፕ ያላቸውንና በግል ደረጃም ብቃት ያላቸውን ተማሪዎች እንደሚቀበሉም አስረድተዋል፡፡

ከፍተኛ ውጤት አምጥተዉ የሚከፍሉት ያጡ ተማሪዎችም አስፈላጊዉን መረጃ አሟልተዉ ያለ ክፍያ እንዲማሩም እንደሚደረግ አስረድተዋል።

ዩንቨርስቲዉ ሰኔ መጨረሻ 5 ሺሕ 9 መቶ 11 ተማሪዎችን ማስመረቁን ይታወሳል።

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
የ2017 የትምህርት ዘመን ትምህርት ሰኞ መስከረም 6/1/2017 ዓ.ም ይጀመራል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን ትምህርት ሰኞ መስከረም 6/1/2017 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

መልካም የትምህርት ዘመን

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለስድስት ሳምንታት ሲሰጥ የቆየውን የSTEM ስልጠና አጠናቋል።

ሰልጣኝ ተማሪዎቹ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ ትምህርቶች ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 3፣ በፓይተን ፕሮግራሚንግ፣ የህጻናት የሳይንስ ሙከራ እና ብሩህ ትውልድ ትምህርታቸውን በክረምት ወቅት ሲከታተሉ መቆየታቸው ተገልጿል።

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
#BoranaUniversity

ቦረና ዩኒቨርሲቲ ነባር የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው መስከረም 25 እና 26/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በ2016 ዓ.ም በቦረና ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ቦረና ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው መስከረም 23 እና 24/2017 ዓ.ም ሲሆን መስከረም 27/2017 ዓ.ም ትምህርት ይጀምራል ተብሏል፡፡

አዲስ የተመደባችሁ (ፍሬሽማን) ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ፡-

➧የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ስምንት (8) 3x4 ፎቶግራፍ፣
➧አንሶላ፣ ብርድልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ተጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

የBusiness እና Tap Tap 🔻  ቻናል👇
https://www.tg-me.com/+SelI4EZhRsI2NDA0
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
#ASTU & #AASTU

በ2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በቀጥታ (online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡


⚡️የምዝገባ ጊዜ፡-
ከመስከረም 06 እስከ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም

⚡️ምዝገባው የሚጠናቀቀው፡-
መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡

⚡️የምዝገባ ቦታ:
የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online https://stuoexam.astu.edu.et ०९ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡ www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et

⚡️ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡ በድህረ ገጻችን የምዝገባው ቀን ካበቃበት በኋላ እናሳውቃለን።

⚡️ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-
በምዝገባ ወቅት በመረጡት ዩኒቨርሲቲ (የፈተና ጣቢያ) በአካል በመቅረብ ይሆናል።

⚡️ማሳሰቢያ፡-
የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

⚡️በቂ አመላካቾች የሌሉባቻው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡

⚡️ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም፣

ከሚመዘገቡት አመልካቾች ውስጥ ለፈተና የሚቀርቡት ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡- www.aastu.edu.et: www.astu.edu.et እንደአመቺነቱም በe-mail የሚገለፅ ይሆናል፡፡

⚡️አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፤ ማለትም (11ኛ እና 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡

ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡

አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

⚡️የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡

በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል፡፡

⚡️በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል።

በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡

በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች መጎብኘት ይቻላል፡፡

www.aastu.edu.et ; www.astu.edu.et

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፡፡

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://www.tg-me.com/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/28 22:21:09
Back to Top
HTML Embed Code: