Telegram Web Link
#Vacancy

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ከዚህ በታች በተገለፀው የትምህርት መስክ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ በመምህርነት በቋሚ ኮንትራት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ መምህርነት
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 16
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ በህክምና የመጀመሪያ ዲግሪ
➤ የሥራ ቦታ፦ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ
➤ የመመዝገቢያ ጊዜ፦ ከሚያዝያ 8/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ብቻ
➤ የምዝገባ ቦታ፡- አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የሰው ሃብት አስተዳደር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 5

Note:

አመልካቾች ለምዝገባ ስትሔዱ የ8ኛ እና 10ኛ/12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ማስረጃ ሰርቲፊኬት እንዲሁም የሙያ ፍቃድ ምዝገባ የታደሰ ዋናውና የማይመለስ አንድ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታችሁ 3.00 እና ከዚያ በላይ ሊሆን ይገባል፡፡

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች 🔻  ቻናል👇
https://www.tg-me.com/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ተገቢው ድጋፍ ሊደረግለት እንደሚገባ ተገለጸ
***********

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ተገቢው ድጋፍ ሊደረግለት እንደሚገባ በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመላክቷል። 

ቋሚ ኮሚቴው በአካል በመገኘት የዩኒቨርሲቲውን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል፤ የዩኒቨርሲቲውን ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራንን እና ሰራተኞችም አወያይቷል።

በውይይቱ ወቅት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ችግሮቹን በትዕግስት በመቋቋም የመማር ማስተማር ስራው እንዲጀመር በማድረጉ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።

ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ መንግስት ተጨባጭ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው ያሉት ነገሪ (ዶ/ር)፤ አሁንም በዩኒቨርሲቲው እና ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በችግርነት የሚነሱ የበጀት፣ ውዝፍ የደመወዝ ክፍያዎችና ሌሎች መንግስት ደረጃ በደረጃ እየፈታቸው የሚሄዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች 🔻  ቻናል👇
https://www.tg-me.com/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝    
ለመጨረሻ ግዜ የወጣ ማስታወቂያ ‼️
#WachamoUniversity

መጋቢት 06/2016 ዓ/ም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተፈጠረው የሲስተም ችግር ምክንያት የባንኩን ገንዘብ በማጭበርበር ገንዘብ ያወጣችሁ ወይንም ያዛወራችሁ ተማሪዎች እስከ 04/08/2016 ዓ/ም እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ገንዘቡን ለባንኩ እንድትመልሱ እና የመለሳችሁበትን ማረጋገጫ /ደረሰኝ/ ከባንኩ እንድታመጡ በቀን 03/08/2016 ዓ/ም ጥብቅ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡

ስለሆነም በማስታወቂያው መሠረት ገንዘቡን የመለሳችሁ ተማሪዎችን እያመሰገንን፤ እስከ አሁን ገንዘቡን ለባንኩ ያልመለሳችሁ ከዚህ በታች ከ1 እስከ 55 ድረስ ስም ዝርዝራችሁ የተገለጠው ተማሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ እስከ 11/08/2016 ዓ/ም ድረስ እንድትመልሱ እያሳሰብን ፤ ገንዘቡን የማትመልሱ ተማሪዎች እርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑን በጥብቅ እናስታውቃለን። (ዩንቨርስቲው )

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች 🔻  ቻናል👇
https://www.tg-me.com/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎቹ የእውቅናና ማበረታቻ ፕሮግራም ሚያዚያ 10/2016 አዘጋጅቷል::

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር ዝግጅቱ ተማሪዎች በፉክክር መንፈስ እንዲሠሩና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማበረታታት እንደሆነ ገልፀዋል።

ተሸላሚ ተማሪዎች በኮሌጁ ስር ከሚገኙ 10 የትምህርት ክፍሎች ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ዓመት  ያሉና ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ውጤት ያስመዘገቡ መሆናቸው ታውቋል።

በኮሌጁ የጥራት ቁጥጥር አስተባባሪ ዶ/ር መቅደስ ማሞ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ዩኒቨርስቲው ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደመሆኑ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ተማሪዎች የበኩላቸውን አስተዋጾኦ ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ለዚህም በየመንፈቅ ዓመቱ ተመሳሳይ ኘሮግራሞችን በማዘጋጀት የማነቃቅያ ስራዎች  እንደሚካሄዱ ገልጸዋል።

በማጠቃለያም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች በልዩነት የማበረታቻ ሽልማት የተሰጠ ሲሆን የጋራ ፎቶግራፍ በመነሳት ኘሮግራሙ ተጠናቋል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች 🔻  ቻናል👇
https://www.tg-me.com/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
                
በሰኔ 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ የርቀት እና ተከታታይ መርሐግብር ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መሰረት የአገልግሎት ክፍያ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) እስከ ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም ድረስ እንዲከፍሉ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አሳስቧል።

ክፍያውን ያልፈፀመ ተማሪ የመውጫ ፈተና መውሰድ የማይችል መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች 🔻  ቻናል👇
https://www.tg-me.com/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
2024/09/28 16:21:57
Back to Top
HTML Embed Code: